uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Kanalga Telegram’da o‘tish

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
194
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-730 kun
Postlar arxiv
አመስግኑ እንጂ?!! •ስንቶች ያላገኙትን ረመዷንን አግኝታችሁ •የፈለጋችሁትን እየተመገባችሁ •ያሻችሁን እየጠጣችሁ •ነብዩ እንኳን ያላገኙትን ኑሮ እየኖራችሁ እንዴት አሏህን አታመሰግኑም?

ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ‏مَن قام رمضان إيمانًا واحتِسابًا، غُفِرَ له ما تَقدَّم مِن ذَنْبِه "ረመዷንን አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ከወንጀሉ ያለፈው ምህረት ይደረግለታል።" [ቡኻሪይ፡ 37] [ሙስሊም፡ 759] . * የቆመ ማለት፦ የሌሊት ሶላት፣ ተራዊሕ፣ ተሀጁድ የሚሰግድ ማለት ነው። * አምኖ ማለት፦ ወደ አላህ መቃረቢያ እና የነብዩ ﷺ ሱና እንደሆነ አምኖ፤ እንዲሁም ለይዩልኝ ሳይሆን በኢኽላስ የፈፀመ ከሆነ ማለት ነው። * አስቦ ማለት:- በተግባሩ ከአላህ አጅሩን አስቦ ማለት ነው። = IbnuMunewor

ሀሰነል በስሪ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላሉ፦ "ኢስቲግፋር በቤታችሁ ውስጥ፣ በቀጠሮዋችሁ ቦታ፣ በመንገዳችሁ፣ በሱቃችሁ ፣ ስትቀማመጡ የትም ቦታ ሆናችሁ አብዙ ምክንያቱም የአላህ ምህረት መቼ እንደሚወርድ አታውቁም" [ التوبة لابن أبي الدنيا 151 ]

ዓሚር ኢብኑ ዐብዱ ቀይስ ረዲየላሁ ዐንሁ ማለዳ ሲሆን እንዲህ ይሉ ነበር፦ "ጌታዬ ሆይ ሰዎች በሙሉ ለተለያየ ጉዳያቸው ተበታትነዋል።የኔ ጉዳይ ደግሞ ወንጀሌን እንድትምርልኝ ነው ፍላጎቴ።" {አዙሕድ ሊኢብኑ አቢ ዓሲም(225)}

ሰራተኛን በየትኛውም መልኩ አትበድሉ። በምግብ አትቅጡ። አትምቱ። ልጆቻችሁ ሰራተኛ ላይ አይቅበጡ። በነሱ ላይ ከአላህ ጋር የሚያጣላችሁን ክፉ ቃል አትናገሩ። ራሳችሁ ላይ ቢሆን በማትፈልጉት መልኩ እንቅልፍና ረፍት አትንሱ። ከአቅም በላይ የሆነ ስራ አትስጡ። ሐቃቸውን ሳትሸራርፉ ስጡ። ሶላት እንዲሰግዱ እዘዙ። የነሱ ሐቅ በናንተ ላይ ከሚኖር፣ የናንተ ሐቅ ቢቀር ይሻላል። ደካማ ላይ ጉልበተኛ አትሁኑ። ከውጭም ይሁን ከውስጥ ልክስክስ ወንዶች ወይም ጎረምሳ ልጆች ከነሱ ጋር እንዳይባልጉ ጥንቃቄ አድርጉ። ሰበብ አድርሱ። በባህሪም ይሁን ሃላፊነትን በመወጣት በኩል ሁኔታቸው የማይጥም ከሆነ በነሱ ሰበብ ወንጀል ላይ ከመውደቅ በሰላም መሸኘት ይሻላል። = IbnuMunewor

ታዕዚያ እያሉ 3ቀን ስራ ፈትቶ መቀመጥ ለታዕዚያ እያሉ  ቀናቶች መለየት መሰረት የለዉም ታዕዚያ  እያሉ   እርድ እያረዱ የመጣዉን ሁሉ ማብላት ለሟቹ አይጠቅመዉም ለሟቹ የሚጠቅመዉ ዉሀ ለሚስኪኖች ገዝቶ መሶደቅ ቁርዓን በሟቹ ስም ነይቶ መስጅድ ማስቀመጥ በማቹ ስም ነይቶ ቢዕር(ጉርጓድ ወሀ ማስቆፈር በማቹ ስም ነይቶ መስጅድ የሚሰራ ከሆነ በቻሉት መጠን  መነየት ለሟቹ የሚጠቅመዉ ዱዓ ማድረግ አሏህ እንድምረዉ  ዱዓ ማድረግ አሏህ እንድያዝንለት ዱዓ ማድረግ እንጅ ቀን እየለዩ ታዕዚያ እያሉ 3ቀን ስራ ፈትቶ መቀመጥ እርድ እያረዱ የመጣዉን ሁሉ ማብላት ከሞተ 7ቱ  40ዉ  አመታቱ  ፍየል በግ   ማረድ ጫት ማቅረብ ያሲን በጀመዓ መቅራት ይሄ ሁሉ መሰረት የለዉም ወላጆቻችንም ዘመድ ቤተሰብ ሲሞት ብር ላኩ ለሶደቃ ሲሏቹህ አስተምሮቸዉ ንገሯቸዉ

ጣፋጭ የቁርኣን ቲላዋ ለእነዚያ ለአመኑትም የፈርኦንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ፡፡ የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን (ምሳሌ አደረገ)፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ (ሱረቱል ተህሪም)

በሶላት ላይ እጅ የሚነሳባቸው ቦታዎች:– ① የመክፈቻ ተክቢራ ጊዜ (ተክቢረተል ኢሕራም)፣ ② ወደ ሩኩዕ ሲወረድ፣ ③ ከሩኩዕ መልስ እና ④ ከመጀመሪያው ተሸሁ፞ድ (አተ፞ሒያ፞ቱ) ሲነሱ። IbnuMunewor

በዚያ ከእሱ ውጭ ምንም አይነት እውነተኛ አምላክ በሌለው ጌታ ይሁንብኝ በዚች ምድር ላይ ለረጅም ዘመናት መታሰር ያለበት አካል ቢኖር ምላስ ነው። ዐብደላህ ቢን መስዑድ

ነብዩ صلى الله عليه وسلم "ሰዎችን በገንዘባችሁ አታዳርሷቸውም።ነገር ግን ፈታ ባለ ፊት እና በመልካም ስነምግባር ሁሉንም ማዳረስ ትችላላችሁ"ብለዋል። ሀዲሱን በዛር የዘገቡት ሲሆን ኢብኑ ሀጀር ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ሀዲስ ነው ብለውታል። ዐብደላህ ቢን ሙባረክ رحمه الله መልካም ስነምግባር ምን ምን ጉዳዮችን እንደሚያካትት ሲጠየቁ "ፊትን ፈታ ማድረግ፣ መልካምን መለገስ እና መጥፎን መገደብ"መሆኑን ጠቅሷል።

ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ አብዛሀኞቹ አካላቸው በሚያገኘው ስንቅ በሚበላውና በሚለብሰው ነገር ላይ ነው አላህን የሚያመሰግኑት። ከተራው ሰው ወጣ ያሉ ሰዎች ግን ሩሓቸው በሚያገኘው ስንቅ በተዉሒድ እና በኢማን ላይ ነው አላህን የሚያመሰግኑት። (መዳሪጁ ሳሊኪን)

በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ~ ① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣ ③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣ ④ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⑥ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⑦ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣ ⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ) ⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ (11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ (12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣ (13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ (14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ (15) ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣ (16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ (17) በዒሻእ ሶላት ላይ እየተዘናጉ አሳልፎ ዘግይቶ መግባት፣ (18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ (19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣ (20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣ (21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣ (22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) (23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ (24) አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ (25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ (26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ ©: ኢብኑ ሙነወር

+6
ما_تيسر_من_سورة_مريم_٢_عبدالرحمن_مسعد.mp31.23 MB

+9
ما_تيسر_من_سورة_الرعد_٣_عبدالرحمن_مسعد.mp38.80 KB

+9
ايات الحج ١ - عبدالرحمن مسعد.mp34.12 MB