uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Kanalga Telegram’da o‘tish

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
2 981
Obunachilar
-224 soatlar
+507 kun
+18430 kun
Postlar arxiv
ሙሴ ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር ከእግዚአብሐር ጋር 570 ጊዜ ቃል በቃል ተነጋግሯል፡፡ 40 ቀን 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ዓሥሩን ትእዛዛት የተጻፉባቸውን ጽላት ተቀበለ፡፡ እስራኤላውያን ባዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስኪሸፍንላቸው ድረስ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚያበራበት ጊዜም ነበር፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ 120 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ እንዲያስረክበው ስላዘዘው ለኢያሱ አስረክቦታል፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ካዘጋጀ በኋላ በተራራ ውስጥ ዐረፈ፡፡ በዚያም በመልእክት እጅ በሥውር ተቀበረ፡፡ የእስራኤል ልጆችም ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሰወረ፡፡ ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጥላቸው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ይሁዳ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ገሠጸው፣ ከዚህም ሥራ ከለከለው፡፡ የእስራኤልም ልጆች ለሙሴ 40 ቀን አልቅሰውለታል፡፡ ጌታችን ስለ ሙሴ ሲናገር ከእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን ነቢይ እንደማይነሣ መስክሮለታል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! + + + የመጥምቁ ዮሐንስ አባት የበራክዩ ልጅ ካህኑ ዘካርያስ፡- የበራክዩ ልጅ ካህኑና ነቢዩ ዘካርያስ- ይህም ነቢይ ዘካርያስ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ መስከረም 8 ቀን በሰማዕትነት ያረፈ ሲሆን የመጥምቁ ዮሐንስ አባት ነው፡፡ ስለ ልጁ ዮሐንስ መወለድ ቅዱስ ገብርኤል ባበሰረው ጊዜ አምኖ ባለመቀበሉ ልጁ ዮሐንስ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ ሆኗል፡፡ ልጁ በተወለደም ጊዜ ‹‹ስሙን ዮሐንስ በሉት›› ብሎ በእጁ ሲጽፍ አንደበቱ ተከፍቶለታል፡፡ እርሱና ሚስቱ በእግዚአብሔር ሕግ ያለነቀፋ የጸኑ ደጎች እንደሆኑ ቅዱስ ወንጌል ይመሰክርላቸዋል፡፡ ‹‹በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ›› ተብሎ ነው በወንጌል ጽድቃቸው የተነገረላቸው፡፡ ሉቃ 1፡5-6፡፡ ንጉሥ ሄሮድስ ጌታችንን የሚያገኝ መስሎት 144 ሺህ ቤቴልሔም ሕፃናትን በግፍ ሲጨፈጭፍ እመቤታችን ልጇን ጌታችንን ይዛ ወደ ግብጽ ስትሰደድ ዮሐንስንም እናቱ ቅድስት አልሳቤጥ ይዛው ወደ ሲና በረሃ ገባች፡፡ ኤልሳቤጥ ከመሄዷ በፊት ግን ከባሏ ከዘካርያስ ጋር ሲሰነባበቱ የሚሆነውንም ሁሉ እርሱ ቀድሞ ያውቅ ነበርና ‹‹ሕፃኑን ልጄን ሲያጡ እኔን ይገድሉኛል፣ አንቺ ግን ወደ በረሃው ይዘሽው ሂጂና በዚያ ሸሽጊው›› ብሎ መክሯታል፡፡ ኤልሳቤጥም ከሄደች በኋላ የርጉም ሄሮድስ ጭፍሮች ዮሐንስን ባጡት ጊዜ ወደ ዘካርያስ መጥተው ‹‹ልጅህን ወዴት አድርሰኸው ነው? ወዴትስ ደበቅኸው? አሁን ከደበቅህበት አምጥተህ ፈጥነህ አስረክበን›› በማለት የፍጥኝ አስረው አሠቃዩት፡፡ ሄሮድስም ዘካርያስ ዘንድ ሄዶ ሕፃኑን ልጅ ዮሐንስን ካልሰጠው እንደሚገድለው ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም የንጉሡን ዛቻ ባለመፍራት አገልግሎቱን ቀጠለ፡፡ በመጨረሻም ንጉሡም ወታደሮቹን ልኮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል አስገደለው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የቅዱስ ዘካርያስን ሥጋውን ሰወረው፣ ደሙ ግን እንደ ድንጋይ ሆነች፡፡ ሕዝቡም እንደ ልማዳቸው ለጸሎት በመጡ ጊዜ ከካህናት አንዱ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ የረጋ የዘካርያስን ደም አገኘ፡፡ ከመሠዊያውም እንዲህ የሚል ድምፅ ተሰማ፡- ‹‹እነሆ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ተገደለ፣ የሚበቀልም እስኪመጣ ድረስ ደሙ ስትጮህ ትኖራለች›› የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ይህንንም አንዳንዶች በማሳሳት ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ስለሆነው ስለ በራክዩ ልጅ ነቢዩ ዘካርያስ የተነገረ ነው ይላሉ ግን አይደለም፡፡ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው የበራክዩ ልጅ ነቢዩ ዘካርያስ የእርጅና ዘመኑ ደርሶ ኡረት በሚባል አገር ሞተ፡፡ ሥጋውም ያለጥፋት በዚያ ተገኝቶ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለታል፡፡ የዚህኛው የካህኑና የመጥምቁ አባት ዘካርያስ ግን ሥጋው አልተገኘም፡፡ ስለመገደሉ የደሙ ድምፅ ምስክር ሆነ እንጂ፡፡ ጌታችንም ለተረገሙ አይሁድ ስለእርሱ ሲናገር ‹‹የገደላችሁት የዘካርያስ ደም በላያችሁ ይደርሳል›› ብሏቸዋል፡፡ የዘካርያስም ደም እስከ ሰባት ዓመት ድረስ እየፈላ ደሙ ሲካሰሳቸው ከኖረ ገዥው ጥጦስ ገዳዮቹን በሰይፍ ሲገድላቸው ደሙ መፍላቱን አቁሟል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን መስከረም 8-ግብጻዊው ዕብራዊውን ሲገድለው አይቶት ለወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎ ወደ ምድያም አገር ማለትም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የካህኑን የዮቶርን ልጅ አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለዶ በኢትዮጵያ 40 ዓመት ከኖረ በኃላ የዮቶርን በጎች እየተበቀ ሳለ እግዚአብሔር በቁጥቋጦ ውስጥ በታላቅ ራእይ ተገልጦለት እስራኤልን ከግብጽ እንዲያወጣ ነግሮት ሄዶ በ10 መቅሰፍታት እስራኤላውያንን ነጻ ያወጣቸው ሊቀ ነቢያት ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡ + የመጥምቁ ዮሐንስ አባት የበራክዩ ልጅ ካህኑ ዘካርያስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ + ከሃዲው መኮንን በእጅጉ ካሠቃየው በኋላ አንገቱን በሰይፍ የሰየፈው ሰማዕቱ ቅዱስ ሉክዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡ + ሰማዕቱ ቅዱስ ዲማድዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ + ምግቡ የአጋዘን ወተት የሆነ በዕረፍቱም ጊዜ ብዙ ተአምራትን ያደረገ የከበረ ገዳማዊ ቂርቆስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ዲማድዮስ፡- ይኸውም በሃይማኖትና በምግባር ያጌጠ ስለነበር ጌታችን ተገልጦለት ሄዶ በስሙ ሰማዕት ይሆን ዘንድ አዘዘው፡፡ ከደቡባዊ ግብጽ ተነሥቶ እናት አባቱን ትቶ ወጥቶ ወደ አትሪብ በመሄድ በከሃዲው መኮንን ፊት ስለ ጌታችን መሰከረ፡፡ ከሃዲውም ገዥ ጽኑ ሥቃይ ካደረሰበት በኋላ ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ የእስክንድርያም መኮንን ሉክያኖስ በተራው አሠቃየው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ዲማድዮስ ተገልጦለት አረጋጋው፡፡ በኋላም መኮንኑ ዲማድዮስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! + + + ሊቀ ነቢያት ሙሴ፡- የፈርዖን ሴት ልጅ ‹‹ከውኃ አውጥቼዋለሁና›› ስትል ሕፃኑን ሙሴ ብላ ጠርታዋለች፡፡ ዘጸ 2፡10፡፡ እስራኤላውን በግብፅ ባርነት እየተገዙ ባለበት ወቅት ፈርዖን እስራኤላውያን ወንድ ልጅ ሲወልዱ እንዲገደል በአዋጅ አስነገረ፡፡ የሙሴም እናት ልጇ በፈርዖን ትእዛዝ መሠረት እንዳይገደልባት ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ፍራቻ ልጇን በቅርጫት አድርጋ ወንዝ ውስጥ ጣለችው፡፡ ተርሙት የምትባለው የፈርዖን ሴት ልጅ በወንዝ ገላዋን ልትታጠብ ወርዳ ሳለ በዚያ ቅርጫት አግኝታ ብትከፍተው የሚያሳሳ ውብ ልጅ አገኘት፡፡ ‹‹ይህንንስ አሳድገዋለሁ›› ብላ ወደ ቤቷ ወሰደችውና ሙሴ በንጉሡ በፈርዖን ቤት አደገ፡፡ የሙሴም እናት ተንከባካቢ ሞግዚቱ ሆና ተጥሎ የተገኘውን ልጇን እንድታሳድግ ከፈርዖን ሴት ልጅ ጋር በድብቅ ተስማምታ በንጉሡ ቤት ገባች፡፡ እናቱም ልጇን ሙሴ የፈርዖን ልጅ እንዳይባል ሃይማኖቱን፣ ማንነቱን፣ ታሪኩን፣ ባሕሉን ጠንቅቃ እያስተማረች አሳደገችው፡፡ ሙሴ 40 ዓመት በሆነው ጊዜ አንዱ ግብፃዊ ዕብራዊውን ሲገድለው አይቶት ለወገኑ ተበቅሎ ግብፃዊውን ገደለው፡፡ በማግስቱ ደግሞ ሁለት ዕብራውያን እርስ በእርሳቸው ሲጣሉ አያቸው፡፡ ሊያስታርቃቸው ፈልጎ ወደ እነርሱ ጠጋ ቢል አንደኛው ዐመፀኛ ዕብራዊ ‹‹ትናንት ግብፃዊውን እንደገደልከው ልትገድለን ትሻለህን?›› አለው፡፡ ሙሴም ‹‹በድብቅ አደረኩት ያልኩት ለካ ታውቆብኛል›› ብሎ ፈርዖንን ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሽቶ ሄደ፡፡ የምድያም አገር ካህን የሆነውን የዮቶርን (በሌላ ስሙ ራጉኤል ይባላል) ሴት ልጁን ሲፓራን አግብቶ 40 ዓመት በምድያም ተቀምጦ ሁለት ልጆችንም ወለደ፡፡ ይህችውም ምድያም የተባለች አገር ቅድስት ኢትዮጵያ ናት፡፡ የዚህም ምስክሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ዘጸ 2፡1-25፣ ኦሪት ዘኁልቅ 12፡1-12፡፡ ሕዝበ እስራኤል ከግብፅ ሳይወጡ በኋለኛውም ዘመን ጌታችን ከመወለዱም ከብዙ ዘመን በፊት በቅድስት አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ካህን እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመሰክረው ሐቅ ነው፡፡ ሙሴ በምድያም አገር ማለትም በኢትዮጵያ በዱር ሆኖ የኢትዮጵያዊውን ካሁን የዮቶርን በጎች እየጠበቀ ሳለ በቁጥቋጦ ውስጥ ታላቅ ራእይ አየ፡፡ ነበልባል ከሐመልማል ጋር ሐመልማልም ከነበልባል ጋር ተዋሕዶ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው፣ ሐመልማሉም ነበልባሉን ሳያጠፋው ተመልክቷል፡፡ ይህንንም ምሥጢር ለመረዳት ጠጋ ሲል ከቁጥቋጦው ውስጥ እግዚአብሔር ድምፅ አውጥቶ ጠራው፡፡ የቆመባት ስፍራ የተቀደሰች ስለሆነች ጫማውንም ከእግሩ እንዲያወልቅ ነገረው፡፡ ዘጸ 3፡5፣ ሐዋ 7፡30-34፡፡ ለጊዜው ሐመልማል የእስራኤል፣ ነበልባሉ ደግሞ የመከራቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐመልማሉ ነበልባሉን ያለመጥፋቱ እስራኤልም መከራውን ግብር ገብተን ቀኖና ይዘን እናርቀው ያለማለታቸው ምሳሌ ሲሆን ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥል ማየቱ የግብጽ መከራ እስራኤልን ጨርሶ ያለማጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ሙሴ ያየው የነበልባልና የሐመልማል ተዋሕዶ የመለኮትና የትስብእት ተዋሕዶ ምሳሌ ነው፡፡ ነበልባሉ ሐመልማሉን እንዳላቃጠለው ሁሉ ሐመልማሉም ነበልባሉን እንዳላጠፋው ሁሉ መለኮት ምልአቱን ስፋቱን ርቀቱን ሳይተው ሥጋም ግዙፍነቱን ሳይተው የመዋሐዳቸው አንድ አካል አንድ ባሕርይ የመሆናቸው ምሳሌ ነው፡፡ እንዲሁም ነበልባሉ የጌታችን ምሳሌ ሲሆን ሐመልማሉ ደግሞ የእመቤታችን ምሳሌ ነው፡፡ ይኸውም ነበልባሉ ሐመልማሉን እንዳላቃጠለው ሁሉ እሳተ መለኮት ጌታችንም 9 ወር ከ5 ቀን በማኅፀኗ ባደረ ጊዜ እመቤታችንን ባሕርየ መለኮቱ አላቃጠላትም፤ ሐመልማሉም ነበልባሉን እንዳላጠፋው ሁሉ ጌታችንም ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ቢሆንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠም፡፡ ይህንንም ቅዱስ ኤፍሬም በሐሙስ ምስጋናው ላይ እንዲህ ሲል ገልጾታል፡- ‹‹መለወጥ የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሐ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፣ የአብ ቃል በእርሷ ሰው ሆኗልና እሳተ መለኮቱ አላቃጠላትምና፤ ከወለደችው በኋላ ድንግልንናዋ አልተለወጠምና፤ ሰውም ቢሆን መለኮቱ አልተለወጠም በእውነት አምላክ ነውና፣ በእውነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን፡፡›› የደማስቆው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ዕፀ ጳጦስ የአምላክ እናት አምሳል ነበረች፤ ሙሴ ወደ እርሷ በተጠጋ ጊዜ እግዚአብሔር ‹አንተ የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ› አለው፡፡ እንግዲህ ሙሴ የወላዲተ አምላክን ምሳሌ ያየባት መሬት የተቀደሰች ከሆነች ምሳሌዋ ራሷ ምን ያህል የተቀደሰች ትሆን? እርሷ ቅድስት ብቻ ሳትሆን ቅድስተ ቅዱሳን ናት›› በማለት ስለ እመቤታችን አስተምሯል፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት እንዲያወጣቸው ላከው፡፡ ሙሴም ወደ ግብፅ አገር ሄዶ 10 የተለያዩ መቅሰፍቶች አመጣ፡፡ መጀመሪያ ውኃውን ወደ ደምንት ለወጠው፡፡ 10ኛው የበኩር ልጆቻቸው ሞቱ፡፡ በተአምራቱም ሕዝቡን ይዞ ከግብፅ ወጣ፡፡ የኤርትራን ባሕር በበትሩ ለሁለት ከፍሎ አሻገራቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ሕዝበ እስራኤልን በምድረ በዳ 40 ዓመት ሙሉ መና ከሰማይ እያወረደ መገባቸው፣ ከአለትም ላይ ውኃ እያፈለቀ አጠጣቸው፡፡ እራኤል ግን እጅግ ክፉዎች ነበሩና በክፋ ይነሱበት ነበር፡፡ በድንጋይ ሊወግሩት ያሉበት ጊዜም ነበር፡፡ እርሱ ግን ፍጹም በመታገስ በኃጢአታቸው እንዳይሞቱ ወደ እግዚአብሔር ይማልድላቸው ነበር፡፡

ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡በጣም ብዙ ድርሳናትን ደርሰዋል፡፡100 ዓመት በሆናቸው ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከ10 ቀን በኋላ በሞት እንደሚያርፉ ነገራቸው፡፡ ሕዝቡንም ጠርተው በሃይማኖት እንዲጸኑ ከመከሯቸውና ከተሰናበቷቸው በኋላ መስከረም 7 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ይኸውም ዕረፍታቸው የተከናወነው ኤጲፋንዮስ ባረፈ በ2ኛ ዓመቱ ዮሐንስ አፈወርቅ ባረፈ በዓመቱ ነው፡፡ጌታችን የብርሃን ሰረገላ ሰጥቷቸዋል፡፡ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣በጸሎታቸው ይማረን፡፡ + + + + + + + + + + + + + + + ሰማዕታቱ ቅድስት ራፊቃ እና አራት ልጆቿ፡- ለቅድስት ራፊቃ እና ለአራት ልጆቿ ማለትም ለአጋቶን፣ ለጴጥሮስ፣ ለዮሐንስና ለአሞን ጌታችን ለሁሉም በራእይ ተገልጦላቸው በስሙ መስክረው ሰማዕት እንሚሆኑ ነገራቸው፡፡አስቀድሞም ታላቁ አጋቶን በአገሩ ተሹሞ በሥልጣን ሆኖ ነበር። የጌታችንንም የሰማዕትነት ጥሪ ተቀብለው ከላይኛው ግብጽ ከቁስ አውራጃ ተነሥተው በከሃዲው መኮንን በዲዮናስዮስ ፊት ስለ ጌታችን አምላክነት መሰከሩ፡፡መኮንኑም ብዙ ሥቃዮችን አደረሰባቸው፡፡ጌታችንም በተአምራት ከመከራቸው ሲያድናቸው ያየ ብዙ ሰዎች ሲያምኑ መኮንኑ እጅግ ተቆጥቶ ጽኑ ሥቃይ አደረሰባቸው፡፡ማሠቃየትም በሰለቸው ጊዜ ወደ እስክንድርያው ገዥ አርማንዮስ ዘንድ ላካቸው፡፡ከሃዲው አርማንዮስም ሥጋቸውን ቆራርጦ በመንኮራኩር ውስጥ ጨመራቸው፡፡ነገር ግን ጌታችን ጤነኛ አድርጎ ፈወሳቸው፡፡ዳግመኛም ዘቅዝቀውም ሰቀሏቸው፡፡ አሁንም ጌታችን አዳናቸው፡፡በተአምራተቸውም ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡በመጨረሻም ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆርጠው ሥጋቸውን ወደ ባሕር ጣሉት፡፡ቅድስት ራፊቃና አራት ልጆቿም ሰማዕትነታቸውን በዚሁ ፈጸሙ፡፡የታዘዘ መልአክም መጥቶ ለአንዱ ባለጸጋ የቅዱሳኑን ሥጋ ያለበትን ነግሮት እንዲያወጣውና በክብር እንዲያስቀምጠው አዘዘው፡፡ባለጸጋውም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ከባሕሩ አወጥቶ የመከራ ዘመን እስኪያልፍ በክብር አኖረው፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣በጸሎታቸው ይማረን፡፡ + + + + + + + + + + + + + + + + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት እመቤታችን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክን የወለደቻት ቅድስት ሐና ልደቷ ነው፡፡ሐና ማለት ‹‹ጸጋ›› ማለት ነው፡፡አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እናት ናት፡፡እርሷም ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት፡፡የቅድስት ሐና አባት ማጣትና እናቷ ሄርሜላ ከእርሷ በተጨማሪ ሶፍያና ማርያም የሚባሉ ሌሎች ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል፡፡ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ የሆነውን ጻድቅ ኢያቄምን አግብታ ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደች፣ ድንግል ማርያምም መድኃኔዓለም ክርስቶስን ወለደች፡፡ሶፍያ ኤልሳቤጥን ወለደች፣ ኤልሳቤጥም መጥምቁ ዮሐንስን ወለደች፡፡ከሦስቱም ታናሽ የሆነችው ‹‹ማርያም›› የተባለችው የማጣትና የሄርሜላ ልጅ ደግሞ ሰሎሜን ወለደቻት፡፡ይኽችም ታላቅ እናት ቅድስት ሐና አምላክን በድንግልና ሆና በሥጋ ለወለደችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላጇ ትሆን ዘንድ የተገባት ሆናለችና ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እንረዳ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ልዩ ስጦታ የሆነች ድንግል ማርያምን እርሷ አስገኘቻት፡፡ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ አያቱ ሆናለችና ምን ያህል ክብርት እንደሆነችና እግዚአብሔር የመረጣት ንጽሕት ቅድስት እንደሆነች በዚህ ይታወቃል፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን መስከረም 7-የብርሃን እናቱ የሆነች ድንግል ወላዲተ አምላክን የወለደቻት ቅድስት ሐና ልደቷ ነው፡፡ + በ451 ዓ.ም በጉባዔ ኬልቄዶን ላይ ተገኝቶ ልዮንን የረታውና ያወገዘው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በዓለ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፡፡ + በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ በንጉሡ ልጅ ላይ ያደረውን ሰይጣን ያስወጡትና በሀገርም ላይ የመጣውን የጠላትን ጦር በመርታት ድል ያደርጉ የነበሩት አቡነ ሳዊርያኖስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ + ቅድስት ራፊቃ እና 4 ልጆቿ ቁልቁል ተሰቅለውና አንገታቸውን በመሰየፍ ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጸሙ፡፡ + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከቅዱስ ፋሲለደስ ጋር ማኅበርተኞቹ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት ሰዎችም በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ + የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የቅድስት ኤልሳቤጥም የመታሰቢያዋ በዓል ነው፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡ + + + + + + + + + + + + + + + ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፡- ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 25ኛው ነው፡፡ስለ ቀናች ሃይማኖት ታላቅ ተጋድሎን ከፈጸመ በኋላ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ መስክረም 7 ቀን ዐርፏል፡፡ንጉሡ መርቅያኖስ በጠራው ጉባዔ በጠሩት ጊዜ በቦታው ሲገኝ 636 ጉባኤተኞች ተሰብስበው ደረሰ፡፡‹‹ምን ጉድለት ተገኝቶ ነው ይህ ሁሉ የተጠራው?›› ሲላቸው ‹‹በንጉሡ ትእዛዝ ተጠርተን ነው›› አሉት፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ‹‹ይህ ጉባኤ ስለ ጌታችን ክብር ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጨ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ነገር ግን የጉኤው መሰብሰብ በንጉሡ ትእዛዝ ከሆነ ንጉሡ እንዳሻው ይምራው›› አላቸው፡፡ከዚህም በኋላ የክርስቶስን ባሕርይ ለሁለት የሚከፍለው የክህደትን ቃል በውስጡ የያዘውን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ ቀደደው፡፡ለጉባኤውም ርትእት የሆነች ሃይማኖትን ገለጸ፡፡የተዋሕዶንም ምሥጢር በነፍስና በሥጋ እንዲሁም በእሳትና ብረት እየመሰለ አስዳ፡፡ጌታችን ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት ተጠርቶ ሄደ፣ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን አደረገው›› እያለም በብዙ ምሳሌዎች ሲያስረዳቸው ከጉባኤው ሊከራከረው የደፈረ ማንም አልነበረው፡፡ነገር ግን ክፉዎች ጉባኤውን በከሃዲው በልዮን ምክር ወዳዘጋጀው ንጉሡ መርቅያንና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክያል መልዕክት ልከው ከዲዮስቆሮስ በቀር እነርሱ ያዘዙትን ሃይማኖትንና ትእዛዝ የሚቃወም እንደሌለ በመናገር ነገር ሠሩበት፡፡ነገር ግን በጉባኤው ውስጥ ንስጥሮስን ያወገዙ አባቶችም ነበሩበት፡፡ንጉሡም ቅዱስ ዲዮስቆሮስን አስጠርቶት ከሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እስከ ማታ ድረስ ሲከራከሩ ዋሉ፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስ እንዳልተመለሰላቸው ባዩ ጊዜ ንግሥቲቷና ንጉሡ በእርሱ ተቆጥተው ክፉኛ አስደበደቡት፡፡ጽሕሙን ነጭተው ጥርሱንም አስወለቁት፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም የተነጨ ጽሕሙንና የወለቀ ጥርሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ በመላክ ‹‹እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው›› አላቸው፡፡ለጉበኤው የተሰበሰቡ ኤጲስ ቆጶሳትም በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን ዐይተው ፈሩና ከከሃዲው ንጉሥ መርቅያኖስ ጋር ተስማሙ፡፡ክብር ይግባውና ‹‹ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት አሉት›› ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስም እነርሱ የጻፉለትን መዝገብ እንዲልኩለት ሲጠይቃቸው ላኩለት እርሱም ጽፎ የሚፈርምበት መስሎአቸው ነበርና፡፡እርሱ ግን አባቶቻችን ሐዋርያት ካስተማሯት ከቀናች ሃይማኖት በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና የ318 ኤጲስ ቆጶሳት አባቶቻችን ከሠሯት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ፡፡መና*ፍቁ ንጉሥም ይህን ጊዜ እጅግ ተናዶ ጋግራ ወደምትባል ደሴት እንዲያግዙት አዘዘ፡፡የሀገረ ቃው ኤጲስ ቆጶስ አባ መቃርስ አብሮት ተሰደደ፡፡ሌሎቹ ግን ሸሹ። ከዚህም በኋላ እነዚያ የካዱ 636 ኤጲስ ቆጶሳት ተቀምጠው በኬልቄዶን ለራሳቸው መመሪያ የሚሆናቸውን ሥርዓት ሠሩ፡፡በጋግራ ደሴት ያለው ኤጲስ ቆጶስም ከንጉሡ ጋር የተባበረ ነበርና አቡነ ዲዮስቆሮስ ላይ ብዙ መከራ አደረሰበት፡፡የደሴቱ ሰዎች ግን በቅዱስ ዲዮስቆሮስ እጅ የሚፈጸሙ ተአምራትን እያዩ እጅግ ያከብሩት ነበር፡፡ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን ወደ እስክንድርያ ሄዶ ሰማዕት እንደሚሆን ትንቢት ነገረውና ከነጋዴዎች ጋር ላከው፡፡እንደተናገረውም አባ መቃርስ በእስክንደርያ ሰማዕት ሆኖ ዐረፈ፡፡አቡነ ዲዮስቆሮስ ግን በዚያቹ በጋግራ ደሴት ሰማዕትነቱን ፈጽሞ በክብር ዐርፏል፡፡ምእመናንም ሥጋውን በዚያው አኖሩት፡፡የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ + + + + + + + + + + + + + + + አቡነ ሳዊርያኖስ፡- የግሪክ አቴናን ፍልስፍናና ጥበብ ጠንቅቀው የተማሩ ናቸው፡፡ምግባር ሃይማኖታቸው የሰመረ፣ ትሩፋት ተጋድሏቸው የቀና ነው፡፡ብሉይን ከሐዲስም አጠናቀው ተምረዋል፡፡ወላጆቻቸው ያወረሷቸውን እጅግ የተትረፈረፈ ንብረት ሸጠውና ለጦም አዳሪዎች መጽውተው ለድኆች ማደሪያና ለእንግዶች ማሪፊያ ቤት ሠርተው ነዳያንን ይንከባከቡ ጀመር፡፡ይህንንም የጽድቅ ሥራቸውን የሮሜው ጻድቁ ንጉሥ አኖሬዎስ ሲሰማ እጅግ ደስ ተደስቶ አስመጥቶ ከእርሱ ጋር በቤተ መንግሥቱ አማካሪና አባቱ አድርጎ አኖራቸው፡፡ከንጉሡም ጋር አብረው ሁልጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በሙሉ ለጸሎት ቆመው ያድራሉ፡ጻድቁ የገብላው አገር ንጉሥ ሴት ልጁን ሰይጣን ይዟት ሳለ ደብዳቤ በመጻፍ ልከው በልጅቷ ላይ ያደረውን ሰይጣን በደብዳቤአቸው ብቻ አስወጥተውታል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ በሀገር ላይ የመጣ የጠላትንም ጦር እያሸበሩ ድል ያደርጉ ነበር፡፡ይኸውም የቍስጥንጥንያው ንጉሥ አርቃዴዎስና አኖርዮስ በገብላ አገር ኤጲስቆጶስነት ከሾሟቸው በኋላ የፋርስ ሰዎች እነዚህን ደጋግ ነገሥታት ሊወጓቸው ሽተው በኃይል በመጡባቸው ጊዜ ወደ አባ ሳዊርያኖስ መልአክትን ላኩ፡፡አባታችንም ለቅዱሳን ነገሥታቱ ‹‹እኛ የክርስቶስ ከሆንን መንግሥታችንም የክርስቶስ ነው፣ እንዲህም ከሆነ የጦር መሣርያ የጦር ሠራዊትም አንሻም…››ብለው ደብዳቤ ጽፈው እንደላኩ ነገሥታቱ ያለ ምንም ጦርነት የፋርስን ሀገር ሰዎች አሸንፈው ወደ ሀገራቸው መልሰዋቸዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ በገብላ አገር ኤጲስቆጶስነት ከተሾሙ በኋላ የሙሴን ሕግ በማወቁ የሚመካ አንድ ስሙ ስቅጣር የሚባል አይሁዳዊ ወደ እርሳቸው መጥቶ ተከራከራቸው፡፡የጻድቁንም ቃላቸውን ሊሰማቸው አልቻለም ነበር፡፡በዚህም ጊዜ ጌታችን ለአቡነ ሳዊርያኖስ ተለጠላቸውና ‹‹እኔ ካከበርኳቸው ወገኖች ይሆናል›› በማለት እንደሚያምን ነገራቸው፡፡ያም አይሁዳዊ ወደቤቱ በገባ ጊዜ ወገኖቹ አይሁድ ሲኦል ውስጥ ሆነው ሲሠቃዩ በራእይ ተመለከተ፡፡‹‹ከሃዲዎች ዘመዶችህን እነሆ እይ›› የሚል ድምንም ሰማ፡፡በማግሥቱም ይህ አይሁዳዊ ወደ አቡነ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእግራቸው ሥር ወድቆ እንዲያስተምሩትና የክርስቶስ ወገን እንዲያደርጉት ለመናቸው፡፡እርሳቸውም አስተምረው ከሀገሩ ሰዎች ጋር አንድ ላይ አጠመቋቸው፡፡የቀሩት ብዙ አይሁድም በጌታችን አምነው ተጠመቁ፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ሥራየኛ ጠንቋዮችን ሁሉ እያሳመኑ አስተምረው አስጠምቀዋቸዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ስለ ዮሐንስ አፈወርቅ ስደትና እንግልት ያለችበት ድረስ ሄደው ንግሥት አውዶክስያን ቢመክሯትና ቢገሥጹዋትም በክፋቷ ጸንታ አልሰማቸው ብትል ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄደዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ተአምራታቸው

💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0

🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ መስከረም ፮ (6) ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ" ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" አባ ሳሙኤል ዘዋሊ "*+ =>ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን:: +በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ ቦታ አላቸው:: በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል : ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል:: +እነዚህም:- 1.ሳሙኤል ዘዋልድባ 2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ 3.ሳሙኤል ዘቆየጻ 4.ሳሙኤል ዘግሺ 5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና 6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው:: +በተመሳሳይም በግብጽ የደብረ ቀልሞኑን ኮከብ ጨምሮ (መልአኩን ቀውስጦስን ከጌታ ያማለዱት) ብዙ ሳሙኤሎች ተነስተዋል:: የድሮ እናቶቻችን በእውነት ስም መሰየሙን ይችሉበታል:: "ሳሙኤል" ማለት "ሰምዓኒ እግዚአብሔር ስዕለትየ - እግዚአብሔር ልመናየን ሰማኝ" ማለት ነውና:: +ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን (በ1295) በምድረ አክሱም ነው:: ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ:: +የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ጻድቁ ገና በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠጥተዋል:: ለዚህም ይመስላል ገና ሕጻን ሳሉ ምናኔን የተመኙት:: +ከልጅነታቸው ጀምረው ወላጆቻቸውን ያገለገሉት ሳሙኤል ትምሕርታቸውን ሲፈጽሙ የተጉዋዙት ወደ ደብረ በንኮል ነበር:: በጊዜውም የጻድቁ ወላጆች ዐርፈው እንደ ነበር ይነገራል:: ደብረ በንኮል ማለት የታላቁ ኮከብና አበ መነኮሳት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነው:: +መድኃኒነ እግዚእ ለሃገር ብርሃን የሆኑ ቅዱሳንን ያፈሩ ዘንድ ሲተጉ እግዚአብሔር 7ቱን ከዋክብት ሰጣቸው:: ክእነዚህ መካከልም ቀዳሚው አቡነ ሳሙኤል ናቸው:: ቀሪዎቹ ደግሞ እነ አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ : ሳሙኤል ዘጣሬጣ : ሳሙኤል ዘቆየጻና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን የመሰሉ ናቸው:: +አቡነ ሳሙኤል ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ሆነው በደብረ በንኮል ተጋድሎን አሐዱ አሉ:: እንጨት ይሰብራሉ:: ውሃ ይቀዳሉ:: እህል ይፈጫሉ:: በፍጹም ልባቸውም ይታዘዛሉ:: ጐን ለጐን ደግሞ ከቅዱሱ አበ ምኔት መድኃኒነ እግዚእ ጽንዓትን : ትሕትናን : ትሕርምትን ይማሩ : ሥርዓተ ገዳምንም ያጠኑ ነበር:: +ከአገልግሎታቸው ማማር የተነሳ ሁሉን ደስ ማሰኘት ቻሉ:: በዚህ ጊዜም ጻድቁ አበ ምኔት አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊንና 6ቱን አበው ጠርተው ለምንኩስና አቀረቧቸው:: "ይገባቹሃል!" ሲሉም ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና አሸጋገሯቸው:: +በዚያች ቀን 7ቱ ሲመነኩሱ ከሰማይ ብርሃን ወርዶ በመታየቱ ቅዱሳኑ "ከዋክብት ብሩሃን" ተባሉ:: ለተወሰነ ጊዜም በዚያው በገዳሙ አገለገሉ:: የአቡነ ሳሙኤል ዘመዶች ግን እየመጡ ጻድቁን ስላስቸገሩ 7ቱም ቅዱሳን ተመካክረው : ከአባታቸው መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው ከደብረ በንኮል ወጡ:: +ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራቸው ሲሔዱ 3ቱ (ማለትም ሳሙኤል ዘዋሊ : ያሳይ ዘመንዳባና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ) ወደ ጣና ሔዱ:: በዚያም ለጥቂት ጊዜ አብረው ከቆዩ በሁዋላ ለአገልግሎት ተለያዩ:: አቡነ ያሳይ "መንዳባን" : አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ "ጉጉቤን" ይዘው እዛው ጣና አካባቢ ሲቀሩ አባ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሔዱ:: +ዋልድባ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በጌታ ፈቃድ የተመሠረተ ሲሆን 860ው መሥራች ቅዱሳን በመሠወራቸው እንደ ጠፍ ይቆጠር ነበርና አቡነ ሳሙኤል እንደ ገና አቀኑት:: +ጻድቁ በዋልድባ የመጨረሻውን ትሕርምት ከመያዛቸው በፊት በጊዜው ከፍተኛ የሆነ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል:: ቀጥለውም ኑሯቸውን ከግሩማን አራዊት ጋር አድርገዋል:: በስዕለ አድኅኖው እንደምናየው ለዘመናት በአንበሳ ጀርባ ላይ ተጭነዋል:: +ጧት ማታም ብዙ ግሩማን አራዊትን እያስከተሉ ለአገልግሎት ደክመዋል:: ጻድቁ ከትሕርምት ብዛት እህል ትተው የሻገተ ጐመንና መልኩን የለወጠ ውሃን ለቁመተ ሥጋ ይጠቀሙ ነበር:: +አንድ ቀንም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሳቸው መጥቶ ባረካቸው:: አካላቸውንም በቅዱስ ምራቁ አትቦ ቀባቸው:: በዚህ ጊዜም ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተመሉ:: የክርስቶስን ሕማማት እያሰቡም እልፍ ጊዜ ይሰግዱ: ጀርባቸውን ይገርፉም ነበር:: +እግራቸውን በሰንሰለት አሥረው ይጋደሉም ነበር:: በዚህ ግብራቸው አጋንንትን አሳፍረው: ፈጣሪያቸውን ደስ አሰኙ:: ከቆይታ በሁዋላም ዋልድባ በመነኮሳት ተሞላ:: ደቀ መዛሙርት በዙ:: ቀዳሚው ግን አባ ዘሩፋኤል ጻድቅ ነው:: +አቡነ ሳሙኤል ከድንግል እመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር ነበራቸው:: ዘወትር ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በተመስጦ ያደርሱላት: ፈጽመውም ያመሰግኗት ነበር:: ይህንን ሲያደርጉ ከመሬት ክንድ ከፍ ብለው ይንሳፈፉ ነበር:: +ተከታዮቻቸው ሲርባቸውም ውሃውን በቅዳሴ ማርያም ነጭ ሕብስት ያደርጉት ነበር:: "ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ:: ረሰዮ ሕብስተ ሳሙኤል ጽጌ ሃይማኖት ዘሐቅለ ዋሊ:: ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ:: ስረዪ ኃጢአትየ ወዕጸብየ አቅልሊ:: እስመ ኩሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ::" እንዳለ ሊቁ:: (ማኅሌተ ጽጌ) +እመ ብርሃንም ስለ ፍቅር ነጭ እንቁ ሰጠቻቸው:: ሰማያዊ ሕብስትን መገበቻቸው:: ንጹሕ ዕጣንንም አበረከተችላቸው:: ለ12 ዓመታትም ከሰማይ ካህናት ጋር አጠኑ:: ድንግል ማርያም "እንዳንተ ውዳሴየንና ቅዳሴየን በፍቅር የሚደግምልኝን አማልደዋለሁ" ስትላቸው:- +ጌታ ደግሞ ገዳማቸውን ዋልድባን ቀድሷታል:: ቀድሞም በስደቱ ባርኩዋት ነበር:: የጻድቁ ዜና ፈጽሞ ብዙ ነውና ለዛሬ በዚህ ይብቃን:: የዋልድባው ኮከብ አቡነ ሳሙኤል ያረፉት ታሕሳስ 12 ቀን በ1395 ሲሆን ዕድሜአቸውም 100 ዓመት ነበር:: =>ጻድቁ ዛሬ በዓለ ፍልሠታቸው ሲሆን : ይህ የተደረገውም ከደብር ዓባይ ወደ ዋልድባ ነበር:: << ለጻድቁ ክብር ይገባል !! >> =>አምላከ ሳሙኤል በምልጃቸው ሃገራችን ከጦርነት: ሕዝቦቿን ከስደት ይሰውርልን:: ሞልቶ ከተረፈ በረከታቸውም አይንሳን:: =>+"+ የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ:: +"+ (ሮሜ. 12:14-16) 《ወስብሐት ለእግዚአብሔር》

✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ ✝✝✝ ✝ መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +" ቅድስት ሐጊያ ሶፍያ "+ ✝ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት:: +በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች:: +በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ: እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔ ዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት:: +ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች:: +የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው:: +ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር:: +ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ:: +የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል:: ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው: የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር:: +በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው:: +" ቅዱስ ማማስ ሰማዕት "+ ✝የሰማዕቱ ወላጆች ቴዎዶስዮስና ታውፍና ሲባሉ ማማስ የሚለው የስሙ ትርጉም 'ዕጉዋለ ማውታ - እናት አባቱ የሞቱበት' ማለት ነው:: ለምን እንደዚህ ተባለ ቢሉ:- በዘመነ ሰማዕታት ስደት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይዘውት ተሰደው ነበር:: ማምለጥ ባይችሉ ይዘው አሠሯቸው:: +በእሥር ቤትም ከስቃዩ ብዛት 2ቱም ልጃቸውን ማማስን እንዳቀፉት ሕይወታቸው አለፈች:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተች አንዲት ሴትም ራርታ እነርሱን አስቀብራ: እርሱን አሳድጋዋለች:: ስሙንም 'ማማስ' ብላዋለች:: +ቅዱሱ ባደገ ጊዜ የወላጆቹን ጐዳና በመከተሉ ተይዞ ለፍርድ ቀረበ:: ክርስቶስን አልክድም በማለቱም ብዙ ስቃይን አሳልፎ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱስ ማማስ ከዐበይት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በአንበሳ ጀርባ ላይም ይቀመጥ ነበር:: +" አቡነ አሮን መንክራዊ "+ ✝ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ:: በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ:: +አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ:: የአቡነ አሮን ወላጆች ገብረ መስቀልና ዓመተ ማርያም የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ነበሩ:: ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል:: +ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኳን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል:: +ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ወሎ መቄት ውስጥ በሚገኘው ገዳማቸው ዐርፈው ተቀብረዋል:: ገዳሙ እስካሁን ያለ ሲሆን ድንቅ ጥበበ እግዚአብሔር የሚታይበት ነው:: ጣራው ክፍት ሲሆን ዝናብ አያስገባም:: +" አፄ ልብነ ድንግል "+ ✝እኒህ ንጉሥ ኢትዮዽያን ለዓመታት (ከ1500 እስከ 1532 ዓ/ም) ቢያስተዳድሩም 15ቱ ዓመት ያለቀው በስደት ነው:: ከደጋጉ አፄ ናዖድና ንግሥት ወለተ ማርያም ተወልደው: በሥርዓቱ አድገው ቢነግሡም: በክፉ መካሪዎች ጠንቅዋይ ወደ ቤታቸው ገብቶ ሃገሪቱን ለመከራ ዳርጉዋታል:: +ዛሬም ድረስ ጠባሳው ያለቀቀው የግራኝ ወረራ ለ15 ዓመታት ሃገሪቱን ያለ ካህንና ቤተ ክርስቲያን አስቀርቷት ነበር:: ብዙ ክርስቲያኖችም ሰልመው ቀርተዋል:: አፄ ልብነ ድንግል ግን ደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ገብተው ንስሃ ጀመሩ: አለቀሱ: ተማለሉ:: +እመቤታችን ተገልጣም "ይቅርታን በነፍስህ እንጂ በሥጋህ አታገኝም" አለቻቸው:: እርሳቸውም ሱባኤውን ቀጥለው: 'ስብሐተ ፍቁርን': 'መልክአ ኤዶምን' የመሰሉ መጻሕፍትን ደርሰው በዚህች ቀን በ ዓ/ም ዐርፈዋል:: እኛ ክርስቲያኖችም እናከብራቸዋለን:: +የቅዱሳኑ አምላክ የወዳጆቹን ፈተና አስቦ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቡንም ከስደት ይሰውርልን:: ከበረከታቸውም አይለየን:: +መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 2.ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ 3.ቅዱስ ማማስ ሰማዕት 4.ቅዱሳን ቴዎዶስዮስና ታውፍና 5.አቡነ አሮን መንክራዊ 6.አፄ ልብነ ድንግል =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ 6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) ++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5) ‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››