uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Kanalga Telegram’da o‘tish

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
2 981
Obunachilar
-224 soatlar
+507 kun
+18430 kun
Postlar arxiv
✝ጾመ ጽጌን ለምትጾሙ ታላላቆቼ : እህቶቼና ወንድሞቼ . . . ❀እንኩዋን አደረሳችሁ! ❀በውስጥ መስመር ጥቂቶቻችሁ ጾሙ መቼ እንደሚገባ ጠይቃችሁኛል። #ጾመ_ጽጌ ሁሌም ቢሆን የሚገባው መስከረም 26 ነውና ሊቀየር አይችልም። ❀ስለዚህ ከነገ (መስከረም 26) ጀምሮ ጾመ ጽጌ ትገባለች። ❀ላደለው፥ አቅሙም ላለው ይህንን ጾም መጾም ታላቅ ክብርና ፍቅር ነው። ❀የማንጾምም ብንሆን በሚቀጥሉት 40 ቀናት ተድላ ደስታ ባናበዛ ጥሩ ነው። ❀ጊዜው የፈጣሪ ስደትና የድንግልም መከራዋ የሚታሰብበት ነውና ማዘን ይገባል። ❀ነገር ግን በእነዚህ 40 ቀናት ሠርግን ጨምሮ ተድላ ሥጋን አብዝቶ መከወን ከአሳዳጁ ሔሮድስ ጋር መወገን ነውና እናስብበት። ❀በተለይ ሠርግ ማድረጉ ይከብዳል። ❀ግን ጾሙ የፈቃድ ነውና የሚጾመው በትህትናና በፍቅር ሊያደርገው ይገባል። ❀አድሏችሁ የምትጾሙ ወገኖቼም በጸሎታችሁ አስቡን❀ ☞ሁላችንንም በድንግል ፍቅር ከልሎ ለዚሁ ማዕረግ ያብቃን:: አሜን:: (ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ)

"ነፍሳችሁን ተመልከቱ ሰውነታችሁንም ንፁህ አድርጉ የባልጀራችሁንም በደል አታስቡ ማንም ከወንድሙ ጋር በቁጣ እንዳይኖር አስተውሉ።እግዚአብሔር ያያል ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ።ወደ ሕይወት መድኃኒት እንቅረብ ጸጋ ኾኖ የተሰጠነንም ሥጋውንና ደሙን እንቀበል።"    ቅዳሴ እግዚእ

††† እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ስንዱ #እመቤት #ቤተ_ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት #መጸው (ጽጌ): #ሐጋይ (በጋ): #ጸደይ (በልግ) ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል:: #ዘመነ_መጸው / #ወርኀ_ጽጌ/ #ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም:- 1.የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ:- *የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን:: *የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን:: *የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን:: *ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን:: *ዘመኑ የበረከት ነው:: 2.በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት (የደስታ ወቅት) ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው:: ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው:: በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል:: "ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም: አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም: አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም: ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::" ††† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን #ወርኀ_ትፍስሕት ያድርግልን:: ††† ቅዱስ ዮናስ ነቢይ ††† ††† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ #ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: (1ነገ. 17:17) እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች:: ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ:: "ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ (ገራገር) የለምና እንቢ አለ (ሰምቶ ዝም አለ):: #እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ #ተርሴስ ኮበለለ:: ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው:: ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ #ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: (ማቴ. 12:39) ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት (እጣ ወድቆበታልና) "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው:: እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው:: ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ #ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል:: የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው:: ††† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: ††† መስከረም 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ጸአተ ክረምት (የክረምት መውጫ) 2.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ 3.ቅዱስ እንጦንዮስ 4.ቅድስት በርባራ 5.ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ 6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት 2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት 4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ 5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) 6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ 7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ ††† "ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::" ††† (ማቴ. 12:39) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ መስከረም ፳፫ (23) ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን #ጻድቃን_ወሰማዕት #አውናብዮስና_እንድርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ #ቅዱሳን_አበው_አውናብዮስ_ወእንድርያስ +"+ =>4ኛው መቶ ክ/ዘ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዘመነ ከዋክብት ይባላል:: ምናልባትም በዓለም ላይ ላለፌት 1,500 ዓመታት ያንን ዘመን መልሶ ማየት አልተቻለም:: *ያ ዘመን ብዙ #ሰማዕታት ነበሩበት:: *ያ ዘመን ብዙ #ሊቃውንት ነበሩበት:: *ያ ዘመን ብዙ #ጻድቃን ነበሩበት:: *ያ ዘመን ብዙ #ደናግል ነበሩበት:: *ያ ዘመን ብዙ #መነኮሳት ነበሩበት:: *ያ ዘመን ብዙ #ባህታውያን (ግኁሳን) ነበሩበት:: +ዘመኑ #ዘመነ_ብርሃን ነው:: እልፍ አእላፍ ቅዱሳን በዚህ ዘመን አብርተዋልና:: ጠላት ሰይጣንን ከቦታው አሳድደው አስጨንቀውታል:: በዚህ ዘመነ ብርሃን ከወደ ምሥራቅ ካበሩ ከዋክብት መካከል ደግሞ በዚህ ዕለት አባቶቻችን ቅዱሳን አውናብዮስና እንድርያስን እናዘክራለን:: +ቅዱሳኑ ባለ ብዙ ሃብት ነበሩ:: ከሰማዕታት: ከጻድቃን: ከደናግል: ከሊቃውንቱም አሉበት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ¤በተጠቀሰው ዘመን በቅዱስ #ጊዮርጊስ ሃገር በልዳ ከከበሩ ወገኖች ተወልደዋል:: +የቅዱሳኑ ወላጆች ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ባለ ሥልጣኖችና ሃብታሞች ነበር:: ልጆቻቸውን (አውናብዮስንና እንድርያስን) ሥጋዊውንም: መንፈሳዊውንም ትምሕርት አስተምረዋቸዋል:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ወላጆቻቸው የዚህን ዓለም ነገር ሲያስቡላቸው: እነሱ ግን የተሻለውን እድል ያስቡ ነበር:: +ዘወትር ገድላተ ቅዱሳንን ያነቡ: ዜና አበውን ይሰሙ ነበርና ይመንኑ ዘንድ ልቡናቸው አወካቸው:: በአንዲት ሌሊት ግን በመንፈስ ቅዱስ አጋዘዥነት ወስነው: ከሃገራቸው #ልዳ ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ:: +ክብር ለቅዱሳኑ #አባ_ሮማኖስና #አባ_በርሶማ ይሁንና በወቅቱ በሶርያ ምድር ገዳማዊ ሕይወት ተስፋፍቶ: ብዙ አድባራት በበርሃ ውስጥ ነበሩ:: 2ቱ ቅዱሳንም በአንዱ ገዳም ውስጥ ገብተው አገለገሉ:: +ተጋድሏቸውን እያበረቱ እስከ ምንኩስና ደረጃም ደረሱ:: ተጋድሏቸው በጾም: በጸሎትና በትእግስት ብቻ አይደለም:: በትሕትና በፍቅር በደግነትና በመታዘዝም ጭምር ነበር እንጂ:: +የምንኩስናና የገዳማዊ ሕይወት ጠላት 'ፍቅረ ዓለምና ፍትወት እንስሳዊት' ናቸው:: አንድ ሰው ከዚህ ዓለም ቁሳቁስ ሳይርቅ መናኝ መሆን አይችልም:: ቅዱሳኑ ግን በመንኖ ጥሪት ይህችን ዓለም ከነኮተቷ ናቁዋት: አቃለሏት:: +የሥጋ ፈቃዳቸውን ያጠፉ ዘንድ ሰውነታቸውን በጾምና በጸሎት: ዕረፍትም በማሳጣት ቀጧት:: #እግዚአብሔር ደግሞ ስለዚህ ፈንታ ጸጋውን አበዛላቸው:: ቅዱሳኑ በሶርያ ገዳማት ለዘመናት ከተጋደሉ በሁዋላ ወደ ግብጽ ለመውረድ ወሰኑ:: ምክንያታቸው ደግሞ:- 1ኛ.ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ 2ኛ.ከቅዱሳን አበው ለመባረክ እና 3ኛ.ለተሻለ ተጋድሎ ለመብቃት ነበር:: እየጸለዩ እያመሰገኑም ግብጽ: ቀጥሎም ገዳመ አስቄጥስ ደረሱ:: +ታላቁ #ርዕሰ_መነኮሳት_አባ_መቃርስን ፊት ለፊት ቢያገኙት ደስ አላቸው:: ሐሴትንም አደረጉ:: እግዚአብሕርን በማደሪያዎቹ ማግኘት ይቻላልና:: የታላቁ ቅዱስ ደቀ መዝሙር ሆነው: በድንግልና ተጠብቀው: በተጋድሎ በርትተው በቦታው ለ3 ዓመታት ቆዩ:: +እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ፈልጐአቸው ነበርና በዚያ ሰሞን በከተማ የነበሩ ሊቃውንት ወደ ገዳም መጡ:: ገዳማውያንንም ዻዻስ ስላረፈብን "የምንሾመው መልካም እረኛን ስጡን" አሏቸው:: +ገዳማውያኑ ሱባኤ ገብተው ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ አውናብዮስን መረጠ:: አበውም ቅዱሱን ዽዽስና ሲሾሙት ወንድሙን እንድርያስን ረዳት አደረጉት:: 2ቱ ቅዱሳን ከበርሃ ወደ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ ተጋድሏቸውን ለማበርታት ወሰኑ:: +ምክንያቱም ለአንድ ገዳማዊ ከተማ ውስጥ ከመኖር በላይ ፈተና የለምና:: ቅዱሳኑ ቀን ቀን ድውያንን ሲጠይቁ: ሙታንን ሲቀብሩ: ሕዝቡን ሲያስተምሩ: ሥጋውን ደሙን ሲያቀብሉ ውለው ሌሊት ይጋደላሉ:: +ለፈቃደ ሥጋቸው ሳያደሉ እንዲህ ባለ ቅድስና ኖረው ደግሞ ሌላ ፈተና መጣ:: የከተማው ሃገረ ገዢ አረማዊ በመሆኑ "ለጣዖት ስገዱ: ክርስቶስን ካዱ" ይል ጀመር:: ቅዱሳኑ ሕዝቡን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ሊያስተምሩ ወደዋልና መኮንኑን "ተው! ተሳስተሃል" አሉት:: +በዚህ ምክንያትም ብዙ ስቃይ ገጠማቸው:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት ሰማዕት ሆነዋል:: ጌታም ስለ ድንግልናዊ ሕይወታቸው: ስለ ወንጌል አገልግሎታቸውና ስለ ሰማዕትነታቸው 3 አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል:: =>አምላከ አበው ቸርነቱን ይላክልን:: የቅዱሳኑን በረከትም ያሳድርብን:: =>መስከረም 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ጻድቃን አውናብዮስ ወእንድርያስ (ሰማዕታት) 2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ መንክራዊ 3.ቅድስት ቴክላ ድንግል 4.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት 2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት 3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) 4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ 5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ 6.አባ ሳሙኤል 7.አባ ስምዖን 8.አባ ገብርኤል =>+"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ #ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ #ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: +"+ (1ዼጥ.3:13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ግሼን ደብረ ከርቤ ††† ††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::" ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል:: በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ:: የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል:: አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል:: ††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል:: በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል:: በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው:: ††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ † ††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው:: የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ:: ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ:: እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት:: ††† ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና ††† ††† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ:: በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ:: በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው:: አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ:: ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ:: ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ:: አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል:: ††† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን:: ††† መስከረም 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ 2.ብዙኃን ማርያም 3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት 4.ቅዱስ ቆዽርያኖስ ሰማዕት 5.ቅድስት ዮስቴና ድንግል 6.ቅዱስ ጢባርዮስ ሐዋርያ

💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0

🌼መስከረም 20 ✝ቅድስት ቴዎብስታ ✝በወጣትነቷ በትዳር  ልጅ ወልዳ ባሏ ከሞተባት በኃላ እግዚአብሔርን ለማገልገል በምናኔ ለመኖር ቆርጣ የተወሰነ ጊዜ በቤቷ በጸሎት ተወስና።የኒቂዎስ ሊቀ ጳጳስ ወደኾነው አባ መቃርስ  ከሚባል  ዘንድ ኼዳ እንዲያመነኩሳት ጠየቀችው። እሱም ወጣትነቷን አይቶ የኔ ልጅ የምናኔ ሕይወት ይከብድሻል ዓመት ራስሽን ፈትኝና አመነኩስሻለኹ ቃሌነው ብሎ ሥርዓት ሰርቶላት ወደ ቤቷ ተመለሰች። ✝ ለአንድ ዓመት ልጇ ቂጣ በቀዳዳ እያቀበላት ጽኑ ተጋድሎን ተጋደለች ልጇ ፲፪ዓመቱ ነበረ። ✝ ቀጠሮ በሰጣት በዓመቱ አባ መቃርስ ተኝቶ እንደ ራዕይ ያለ ያያል ቅድስት ቴዎብስታ መጥታ አባቴ ምነው ሳታመነኩሰኝ ረሳኸኝ ወደ እግዚአብሔር ልኼድነኝ አለችው እርሱም ልጄ ሳላመነኩስሽማ አትኼጅም ብሎ የምንኩስና ሥርዓት አደረሰላት የምንኩስና ልብስ አልብሷት ቀጥሎ ቆብ ሊያለብሳት ሲል ቆብ የለም የተዘጋጀ  የራሱን ቆብ አውልቆ አለበሳት ለፍጹማን የሚሰጠውን አሰኬማም አለበሳት እርሷም ይኼን ስላደረክልኝና ደስ ስላሰኘኸኝ ይኽን መስቀል እንካ ብላ የብር መስቀል ሰጠቻቸው። ✝አባ መቃርስ ሲነሳ ከራሱ ላይ ቆቡ የለም በእጁ ላይ መስቀሉን አገኘው ተነስቶ ከደቀመዝሙሩ ጋር ወደ ቤቷ ቢኼድ አርፋ አገኛት። ✝ልጇ ሲያለቅስ ምን ኾነኽ ነው ልጄ ሲሉት እናቴ ጠርታኝ ጳጳሱ ይመጣል: የሚሉኽን ኹሉ ስማቸው ከዚኽ በኋላ የእሳቸው አደራነኽ አለችኝ አላቸው። በሯን ቢያንኳኩ የሚከፍት የለም ከፍተው ሲገቡ በመስቀል አማትባ አርፋ አገኟት። ሲመለከቱ ያመነኩሱበት ቆባቸው ቀሚሱ በራሷ ላይ አገኙት ተደፍተው ምርር ብለው አለቀሱ እግዚአብሔር ፍላጎቷን ፈጽሞላታልና። እርሳቸው በረከትሽ አመለጠኝ ብለው አለቀሱ። እርሷን በክብር በዝማሬ ሊቀብሯት ሲኼዱ አንድ ድውይ ዝማሬውን ሰምቶ ምንድነው ብሎ ሲጠይቅ ከክርስቲያኖች ወገን ቅድስት ቴዎብስታ አርፋ ሊቀብሯት እየወሰዷት ነው ሲሉት "ቴዎብስታ ሆይ ባዳንሽኝስ በፈጣሪሽ ባመንኩ ብሎ ሳይጨርስ እጁ ተዘርግቶ ድኖለታል በዚኽም ምክንያት እሱም ሁሉም ቤተሰቡ በክርስቶስ አምነዋል። ✝ጸጋ በረከቷ ይደርብን። በአላማ ያጽናን።አሜን። ✝ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን እንዲኽ ብሎ አመስግኗታል። "በጽድቅ ስራ ለዳነችና ለአምላክ ቀናኢ ለኾነች የተመረጠች ሴት ቅድስት ቴዎብስታ ሰላምታ ይገባል":: ተአምኆ ቅዱሳን የቅዳሜ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት  ✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/