ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 678
Підписники
+2624 години
+3797 днів
+1 10930 днів
Архів дописів
የነፃነት ንስሮች የታሪክና የጽናት ምልክት የሆነው የአማራ ፋኖ
እኛ አማራዎች የታሪክ ድርሳናት በደማቅ ቀለም የከተቡን፣ የጀግንነት መዝገቦች ቀዳሚ ስማችንን የያዙ የነፃነት ልጆች ነን። በታሪክም ይሁን በአሁኑ ወቅት ባለን ማንነት፤ ለፈሪዎች ድንፋታ የማንሸበር፣ ለዛቻና ለጭቆና የማንበረከክ የጥንት አባቶቻችን ቀጥተኛ ወራሾች ነን። ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ያስከበሩት አባቶቻችን በካራማራ ጦርነት ግዳጃቸውን በድል የተወጡ።የጣሊያንን ፋሺስት ወራሪ ኃይል በክንዳቸው ገርፈው፣ አንገቱን አስደፍተው ያባረሩ። እኛም ዛሬ የቆምነው በእነዚያ ጀግኖች ክንድ ተዳብሰን፣ ወራሪን የማንፈራው የእነርሱን ደም ተክተን ነው።
ከታሪካዊው የግራኝ መሐመድ ወረራ ቀጥሎ፣ አማራን ከምድር ገፅ ለማጥፋትና ለማዳከም በብአዴን ጥላ ስር ሆኖ ከሚሰራው ከአብይ አህመድ አስተዳደር ጋር ምንም ዓይነት ዝምድናም ሆነ ትብብር የሌለን።
ይልቁንም እኛ በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የጥፋት አዋጅ ለመቀልበስ የተነሳን፣ የቁርጥ ቀን ልጆች ፋኖዎች ነን። የታላላቅ መሪዎች መንፈስና የነፃነት ዘመን የወለደን የአማራ የነፃነት ማብሰሪያ ምልክቶች ነን። በውስጣችን እንደ ዳግማዊ ምኒልክ ጥበብና አርቆ አሳቢነት፤ እንደ አሳምነው ጽጌ ቁርጠኝነትና ለአማራ ህዝብ መቆምን የተማርን፤ እንደ በላይ ዘለቀ ሽምቅ ተዋጊነትና አልበገሬነት፤ እንደ ቴዎድሮስ የአንድነትና የማንነት ፅናት የወረስን
የአባቶቻችን አጥንትና መንፈስ በውስጣችን እንደ ንስር ታድሶ፣ ለነፃነታችን ከፍ ብለን እንድንበር የአደረገን የዘመኑ ፋኖሶች ነን።
የአብይ አህመድ አየር ወለድና ኮማንዶ ኃይል ጋር ፊት ለፊት ቢጋፈጠንም፣ እኛ ግን ከዓላማችን ዝንፍ የማንል፣ ወደ ኋላ የማንመለስ "የምድር ድሮኖች" ነን። በቴክኖሎጂ ከሚመራ ድሮን ይልቅ፣ በእውነትና በማንነት የተገነባው የፋኖ ልብ ለጠላት እጅግ አስፈሪ መሆኑን በተግባር እያስመሰከርን እንገኛለን።
እኛ የአማራን ህልውና ለማስከበር የተነሳን የጥንቶቹ ጀግኖች የታሪክ አሻራዎች ነን። ለጠላት አንበረከክም፣ ለጭቆናም አንገዛም! አለቀ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
+1
ኑ የምህረት አዋጁን ተጠቀሙበት፡፡
----
የአፋብን የምህረት አዋ*ጅን ተከትሎ በቀን 6/6/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ የሚገኙ 5 የሚኒሻ አባላት እስከ ሙሉ ትጥ*ቃቸው የአፋብን ጎ/ጠ/ግዛት ዕዝ በጌምድር ክፍለጦር ጣና ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
Amare Achenef
#በቋሪት የጥፋት ኃይሉ የሞት ሽረት መጣጣር ላይ ነዉ
══════════🕊❁✿❁🕊══════════
[የካቲት 06/2018 ዓ.ም| ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት]
33ኛ ክፍለ ጦር በዐማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ በማስመዝገብ ላይ ነዉ።
"የማይበገረው ፋኖ" ክንድ ያረፈበት የብልጽግና ጦር፣ መረጋጋት አቅቶት በየጫካውና በየሸለቆው ሲባዝን ውሏል።
ከቋሪት እና ከገነት አቦ ተቀናጅቶ ለዘረፋና ለጥፋት ወደ ጣሊያ የወጣው የብርሃኑ ጁላ ጦር፣ በጀግኖቹ የፋኖ ኃይሎች በታቀደ ስትራቴጂካዊ ከበባ ውስጥ ወድቋል። በአሁኑ ሰዓት መውጫ ቀዳዳ አጥቶ በግራ መጋባት ውስጥ የሚገኘው ይህ የፀረዐማራ ጦር፣ የጀግኖቻችንን ክንድ መቋቋም አቅቶት የቁም ሲኦልን እየተጋፈጠ ይገኛል።
በቋሪት ወረዳ እያንጊያ ሽሜ ቀበሌ (በኬል) ልዩ ስፍራ፣ በነፃነት ታጋዮች በተሰነዘረ ድንገተኛና አይምሬ የድሽቃ ጥቃት አንድ ከፍተኛ የመከላከያ አመራር ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በዚሁ ስፍራ በነበረ የፊት ለፊት ውጊያ ሁለት የዐቢይ ዐማራ ሚሊሻዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ "ከሕዝቡ ትከሻ" እንዲላቀቁ ተደርገዋል።
ይህንን ድንጋጤ ለመሸፈንና ፋኖን ከጀርባ ለመምታት በብር አዳማ በኩል ወደ ጨፋቂት የተንቀሳቀሰው አረመኔው የብልጽግና ጦር፣ በ33ኛው ክፍለ ጦር የቃኝና መሐንዲስ አባላት ግንባሩን ተመትቶ በውርደት እንዲመለስ ተደርጓል።
በወረዳው ዋና ከተማ ተቆልፈው የቀሩትን የጥፋት ተላላኪዎች ለማትረፍ በብር አዳማ ሰፍሮ የነበረው ጦር ወደ ገበዘ-ማርያም ለመውረድ ቢሞክርም፣ እዚያም የፋኖ ብረት የለበሰ ክንድ ጠብቆታል።
የቋሪት ወረዳ ማህበረሰብ በልጆቹ የፋኖ ድል በመበረታታት፣ ከታጋዮቹ ጎን በመቆም የመጨረሻውን የነፃነት ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል።
የአረመኔው አገዛዝ መሠረት ተናግቷል፤ የቋሪት ምድር የጠላት መቃብር፣ የጀግኖች መፈከሪያ ሆናለች።
የአፋብን በላይ ዕዝ ፩ኛ ኮር የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የፈጸመው አኩሪ ተግባር !
የካቲት 4/2018 ዓ.ም
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ለ13 ተከታታይ ሰዓታት የዘለቀ ብርቱ ውጊያ ሲያካሂድ ቆይቶ በጀግኖች አርበኞች የሚመሩ 30 የተመረጡ የነጻነት ተፋላሚዎችን በማሰማራት በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራና ሽንፈትን ተከናንቧል ።
በአርበኛ ተመሥገን ውባንተ አባተ፣ በአርበኛ ደርሶ ይኹኔ ጥሩ ፣በአርበኛ ቻላቸው አገኝ፣ በአርበኛ ዋሴ ፣በአርበኛ ዘመነ አለሙ፣ በአርበኛ ውዱ አዲስ እና በሃምሳ አለቃ አያሌው ደራሽ የሚመራው ይሄው የልዩ ዘመቻ ቡድን፤ ከወረታ መጣ የተባለውን የፀዳሉ ደሴንና የመከላከያ ኃይል በማርበድበድ በፋኖዎች ድል አድራጊነት ተወጥቶታል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በእንቁርቁባ አቦ፣ በዓለም ሳጋ ተንሸራታች መንገድ፣ በዓለም ሳጋ መግቢያ በር (ምሳናው) እና በጣጣ አካባቢዎች ሲሆን፣ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ጠላትን በመደምሰስ የሚከተሉትን የጦር መሣሪያዎችና ምርኮኞች በቁጥጥር ስር አውሏል!
የተገኙ ምርኮዎች ዝርዝር፦
ከባድና መካከለኛ መሣሪያዎች፦
√ 01 ዲሽቃ (ሸንሸል) ከሙሉ ተተኳሹ ጋር
√03 ብሬን (ሸንሸል) ከሙሉ ተተኳሹ ጋር
√01 የ120 ኢንች የሞርታር ኦሳ (እግር)
√01 ዙ-23 (ተመትቶ ከጥቅም ውጭ የተደረገ)
ቀላል መሣሪያዎች፦
• 04 ጥቁር ጥርጥር ክላሽ
• 10 AK-47 ክላሽንኮቭ
• 01 መውዜር
የሰው ኃይልና ተሽከርካሪ፦
• 14 የመከላከያ ሠራዊት አባላት (ምር_ኮኛ)
• 06 የአድማ ብተና አባላት (ምር*ኮኛ)
• 01 ፖሊስ (ምክትል ኢንስፔክተር ተሥፋዬ አለማየሁ)
• 04 የመከላከያ ፓትሮል ተሽከርካሪዎች
ጀግኖች ማርከው ታጥቀዋል ።
+1
የአፋብን፣ ቴዲ ዕዝ፣ 201ኛ ኮር …
የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የአገዛዙ የጥፋት ምሶሶ የሆነው የብልጽግና ጥምር ጦር በከፍተኛ ፍጥነት እየፈረሰ ሲሆን፣ የአፋብንን የምህረት አዋጅ ተቀብለው ከሞጣ፣ ከቢቡኝ እና ከፈለገ ካምፕ የወጡ በርካታ የመከላከያና የሚሊሻ አመራሮች የነፃነት ታጋዩን ፋኖ ተቀላቅለዋል። ከቢቡኝ ወረዳ የሚሊሻ ቲም መሪው ይታያል እኛምአየን እንዲሁም ከመከላከያ 25ኛ ክፍለ ጦር ብርሌው ጌትነትና በዳሶ ሁሴን 54ኛ ክፍለ ጦርን ሲቀላቀሉ፣ ከፈለገ ካምፕ ደግሞ ሳይድ ዛኪርና ከድር አቡሽ 74ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
የአደረጃጀት ዜና!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ65ኛ ክ/ጦር አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የአመራር መተካካት፣ አጠቃላይ ግምገማ፣ የውህደትና የተሀድሶ ዝግጅት አድርገዋል።
በተጨማሪም በባለፈው ጠቃላይ ስብሰባ የ102ኛ ኮር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የድርጅት አመራር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ዲቢና ወርቄ ባለሸርጡ ብርጌድና የኮር መካናይዝ ከታጠቅ ክፍለጦር ጋር
በአንድ ላይ በመጣመር 65ኛ ክፍለጦር በማለት መሰየሙ ይታወቃል።
በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ65ኛ ክፍለጦር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ- ሂስ (ግምገማ) በማድረግ በቀን 5/06/2018 ዓ.ም አዳድስ የስራ ሀላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል።
1.ወታደራዊ አዛዥ.........አርበኛ አ/አለቃ ሻምበል ተሾመ
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ..አርበኛ ሞላ መንገሻ(ሞላ ጥቁር)
3.ዘመቻ መሪ ................አርበኛ ተስፋየ መርሻ
4.ም/ዘመቻ መሪ...........አርበኛ ማረጉ መልኬ
5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ መ/ር ጋሻው ደጀን
6.ወታደራዊ አሰተዳር.......አርበኛ ጀማል ሙሀመድ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ ሀብታሙ አይሎ
8.ኦርድናንስ መምሪያ...........አ/አለቃ አበበ ጌታቸው
9.ሎጂስቲክ መምሪያ...........አርበኛ ብርሀኑ ሞላ
10.ፋይናንስ መምሪያ.............አርበኛ አድኖ ቢሆነኝ
11.የህዝብ ግንኙነት.............አርበኛ ይርጋ ተበጀ
12ስልጠና መምሪያ.........አርበኛ አ/አለቃ ሰማነ ተመቸ
13.የህግ መምሪያ.............አርበኛ አማከለ በሪሁን
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
በደብረ ታቦር ከተማ የፋኖን ሰይፍ የቀመሱ የአድማ ብተናና ሕዝባዊ ፖሊሥ መሪ የዓቢይ ዙፋን ጠባቂ ተላላኪዎች❗
ትክክለኛ ቁጥራዊ የታጣቂ ምርኮ፣ ድምሰሳና ቁሳዊ ምርኮዎችን በውጊያው ተሳታፊ ከሆኑ 02ቱም ዕዞች ለማሰባሰብ እየጣርን ነው❗
ቋሚ ምሥሎች የተወሰዱት ከሆድ ዘመዶቻቸው ቲክ ቶክ ተጠቃሚዎች የተወሰደ ነው❗
N.B
✅ሥማዳ ወገዳ ከተማ ላይ ብቻ 275 ሚሊሻ እንደተደመሰሰ፣ በመቶ የሚቆጠር ምርኮኛ እንዳለ የ05 ቀናት ግብር ምሥክር ነው።
✅ከእሥቴ የወጣው አድማ ብተናና ሚሊሻ 30+ ተሽከርካሪውን ከነሙሉ ቁስ፣ ተተኳሽና ከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ እሥከ 02 ዲሽቃ መማረኩ፣ አድማና ሚሊሻው መማረኩ የ 04 ቀናት ትውሥታ መሆኑን ልብጰይሏል።
✅ደራ ሐሙሲት ላይ 02 ዲሽቃ፣ 01 ኦባማ ሙሉ የክላሽና ዲሽቃ ተተኳሽ መማረኩ፣ 01 ኦባማ ሙሉ መሣሪያ መማረኩ የ 02 ቀናት ትናንታዊ ግብር ነው።
✅ከወጂ እሥከ አለም ሳጋ ድረሥ በነበልባሉ ፎገራ ክ/ጦር 02 ብርጌዶች(ክርሥትያን ታደለ ብርጌድና ቴዎድሮሥ ብርጌድ) የተማረኩ 03 የመከላከያ ፓትሮሎች ምሥክር ናቸው።
✅ደብረ ታቦር ከተማን ለማውደም አገዛዙ የተጠቀመውን የዓየር ጥቃት ዓለም የተመለከተው ነው። የደብረ ታቦሩን ዝርዝር ኩነታት ለማቅረብ መረጃዎችን እያሰባሰብን ነው።
#የአደረጃጀት_ዜና‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክ/ጦር አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርገዋል።
በተጨማሪም በባለፈው በነበረው አጠቃላይ የ102ኛ ኮር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የድርጅት አመራር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ዞብል አምባ ክፍለጦር ይባል የነበረውን ስያሜ 12ኛ ክፍለጦር በማለት እንዲጠራ የተወሰነ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ- ሂስ(ግምገማ) በማድረግ በቀን 5/06/2018 ዓ.ም አዳድስ የስራ ሀላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል።
1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ሀብተማሪያም መንበሩ
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ........አርበኛ ነጋ ከበደ
3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ ጌታሁን ደመቀ
4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ አማረ ሞገስ
5.የፖለቲካ መምሪያ.......አርበኛ መ/ር በላይ አረፍ
6.ወታደራዊ አሰተዳር.........አርበኛ ሞላ ዝናቤ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ አሸናፊ በላይ
8.ኦርድናንስ መምሪያ...........አርበኛ ሻምበል ሞላ
9.ም/ኦርድናንስ.................አርበኛ አድሱ ሞላ
10. ጤና መምሪያ.............አርበኛ ወርቁ ተበጀ
11.ስልጠና መምሪያ..........አርበኛ አለሙ መልኩ
12.ሎጂስቲክ መምሪያ........አርበኛ ኑርየ ይማም
13.ም/ሎጂስቲክ........አርበኛ አማረ ይርዳው
14.ፋይናንስ ሀላፊ....አርበኛ ሙሉጌታ ዘውዱ
15.የህዝብ ግንኙነት...........አርበኛ ዳዊት ጌትነት
16.ሀብት አፈላላጊ..............አርበኛ ነጋ ፈንታው
17.የህግ መምሪያ..............አርበኛ አበበ በላይ
18.ሴቶች ጉዳይ..................አርበኚት ቤቲ ተሾመ
19.የክ/ጦር ዳኛ................አርበኚት አበባ ሲሳይ
20.ንብረት ክፍል.........አርበኛ ጥላሁን አየነ (አባ ጫንቃ)
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
06/ዐ6/2018 ዓ.ም
ተጠናክሮ በቀጠለው አውደ ውጊያ ዋግሹም ብርጌድ ታላቅ ድል አስመዘገበ!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነው ዋግሹም ብርጌድ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ድሃና ወረዳ አርቢት ከተማ ላይ በመግባት የአገዛዙን ሚሊሻ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል።
የዋግሹም ብርጌድ ቃኝዎች የካቲት 06/2018 ዓ/ም አመሻሽ ላይ አርቢት ከተማ ላይ በመግባት ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን አንድ ጓድ ሚሊሻ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ አምስት ክላሽንኮፍ፣ 340 የክላሽ ተተኳሽ በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል።
በተያያዘ መረጃ አንድ ሚሊሻ ሁለት ክላሽና 250 የክላሽ ተተኳሽ ሙሉ የወገብ ትጥቁን በመያዝ ዋግሹም ብርጌድን ተቀላቅሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የብርጌዱ ቃል አቀባይ አርበኛ ፋኖ ጥጋቡ መረጃውን አድርሷል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 07/2018 ዓ.ም
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና ወግነው ህዝባቸው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ነባራዊ ሁኔታውን በመረዳት በውጊያና በፈቃዳቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ ቀጥለዋል!
በዚህም ዘጠኝ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የሚሊሻ አባላቶቹ መካነ ሰላም ዙሪያ በነበረ አውደ ውጊያ በቀላል መስዋዕትነት እጃቸውን ለክፍለ ጦሩ በመስጠት ህይወታቸውንም ማትረፍ ችለዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት መቋቋም አቅቶት ከመቶ በላይ ንፁሃኖችን መጨፍጨፉ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በዚሁ በወግዲ ወረዳ ዙሪያ በዘሞድ ከተማ ከ150 ኩንታል በላይ የማህበረሰቡን እህል ዘርፎ በመውሰድ ፀረ-ህዝብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
ስቦ የማስከዳት ዜና....!
በመደራጀት ላይ ያለው ራስ አንቺም ክፍለ ጦር ከዘመቻ አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ከተገኘው ድል ተጨማሪ የጠላት ሃይልን ኮብልለው ወደ ህዝብ ልጅ ለሆነው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን)አራት የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻዎች እጃቸውን ሰተዋል።
ራስ አንችም ክፍለ ጦር ጀግንነት ብቻ ሳይሆን የምርኮ አያያዝ ሰብአዊነትና ሩህሩህነት መለያ ባህሪያቸው መሆኑን በምትቀሳቀስበት ቀጠና ሁሉ ያለው ማሕበረሰብ ምስክርነቱን ይሰጣል።
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 06 /2018 ዓ.ም
የጨፍጫፊው ሥርዓት ምስለኔ የሆነውና በ"ቀንድ አውጣ" የሚመራው የሞጣ ቡድን፤ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋና በጎጃም አመራሮች ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ ገጥሞታል። የገምጋሚዎቹ ሃሳብ እንደሚያመለክተው፣ የሞጣው ቡድን አባላት ልበ-ከንቱና አርቆ ማሰብ የማይችሉ ጥቃቅን ሰዎች ናቸው።
አብይ አህመድ ከቱርክ፣ ከአረብ ኤምሬትስና ከሩሲያ ድሮኖችን በመግዛትና ከሕዝብ ገንዘብ በመሰብሰብ የገዛ ወገኑን እየጨፈጨፈ፣ የአማራን እናት ማቅ እያለበሰ ይገኛል። የሞጣው ቡድን የአማራን ሕዝብ በድሮንና በጥይት ከማስጨፍጨፉ ባለፈ፣ ከክልል እስከ ዞን ያሉ አመራሮቹ ከድሃው ጉሮሮና ከዓለም አቀፍ እርዳታ ሳይቀር እየነጠቁ ለግል ጥቅማቸው አውሉታል።
ይህ ቡድን "ፋኖን በትነነዋል፤ አማራ ክልልን ለምጥን እንገዛዋለን" እያለ ለሥርዓቱ ያለውን ታማኝነት ለመግለጽ ቢሞክርም፣ ሌብነቱ ግን ጣሪያ ነክቷል። በአሁኑ ወቅት በአክቲቪስቶችና በተለያዩ አካላት ፊት ለፊት የሚጋፈጠው ይኸው ቡድን፣ ለሥርዓቱ አገልጋይ ሆኖ መዝረክረኩን ቀጥሏል። ቢሆንም ግን ፋኖ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወሎና በጎጃም በቅርቡ በወሰደው እርምጃ የሚሊሻውንና የአድማ ብተናውን ኃይል ግብዓተ መሬት ፈጽሟል።
ጨፍጫፊው ሥርዓት ከውጭ ባስገባቸው ድሮኖች 19 ጊዜ ቦምብ በመጣል፣ እንደ አጣዬና ሻሸመኔ ሁሉ የደብረ ታቦርን መሥሪያ ቤቶች ወደ አመድነት ቀይሯቸዋል። ይህ አልበቃ ብሎት፣ ቀደም ሲል "አሩሲን አማራ ፋኖ አቃጠለው" እንዳለው ሁሉ፣ ዛሬም በከፈታቸው የሐሰት (Fake) አካውንቶችና በአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን በኩል "ደብረ ታቦርን ፋኖ አቃጠለ" የሚል የሐሰት ወሬ እየነዛ ይገኛል።
ፋኖ የሚታገለው ለአማራ ሕዝብ ህልውና ሲሆን፣ "ቀንድ አውጣ" ግን የሚታገለው ለአብይ ጨፍጫፊ ሥርዓት መሆኑን ሕዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝቡ የአብይ ሥርዓት እንደማይበጀው ተረድቶ፣ ፋኖ የትጥቅ ትግል ሳይጀምር በፊት በአደባባይ ሥርዓቱን ተፍቶታል። ዛሬ ለፋኖ ቀለብ፣ ትጥቅና መጠለያ የሆነው ራሱ የአማራ ሕዝብ ነው።
"ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል" እንደሚባለው፣ ደብረ ታቦርን በድሮን አጋይተው ፋኖ አቃጠለ የሚል የ"በሬ ወለደ" ወሬ በሶሻል ሚዲያ ቢለቁም ሰሚ የላቸውም። የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግራይ፣ የጋምቤላ፣ የአፋር፣ የሶማሌና የቤንሻንጉል ሕዝቦችን ደም ለስምንት ዓመታት ሲያፈስ የቆየውንና የምስራቅ አፍሪካ ስጋት የሆነውን ይህን ሥርዓት ለመገርሰስ፣ የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ተጀምሯል።
ሕዝቤ ሆይ! "እምቢ" በል! የሞጣው ቡድንም ከጨፍጫፊው ጋር አብሮ ከመቀበር ይልቅ፣ ሕዝብህን በአረብ ኤምሬትስ ድሮን ከሚያስጨፈጭፈው የአብይ ሥርዓት ተለይተህ ለሕዝብህ ወግን። አብይ ዝላይ የሚያበዛ ግን እንደ ቁንጫ በቀላሉ የሚጠፋ ነው።
