ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 641
Підписники
+2024 години
+3787 днів
+1 08530 днів
Архів дописів
ቤተ-መንግስቱን ያስደነገጠዉ ክስተት!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ከአድስ አበባ 30 ኪ.ሜ በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ አድስ አበባ ላይ ከፍተኛ ሀይሉን እያሠባሰበ መሆኑን ተከትሎ የአገዛዙ ሀይል ለማይቀረዉ የከተማ ዉጊያ ተዘጋጅተና በሚል የመጨረሻ የሆነዉን የዉጊያ ስልት እያስተዋወቀ ይገኛል።
ከ1500 ኪ.ሜ በላይ የጀመረዉ ጦርነት ከመሸነፍና ከመደምሰስ ያላዳነዉ በመሆኑ በአድስ አበባ የከተማ ዉጊያ አደርጋለሁ በሚል ቅዠት አድስ አበቤን ለመጨፍጨፍና የመጨረሻ በትሩን በአድስ አበባ ህዝብ ላይ ለማሣረፍ እየተዘጋጀ ይገኛል።መቼም የተሰለበ ካልሆነ በስተቀር አድስ አበባ የሚኖር የመጨረሻ ዕድሉን ተጠቅሞ 15 ኪ.ሜ በመንቀሳቀስ ወንድሞቹን በአጀባ የማይቀበል ያለ አይመሥለኝም።
አፍብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና አሳምነዉ ዕዝ በበላይነት እየመሩት በመንጃር ደ/ዘይት መሥመር አየር ሀይሉን በቀላሉ መቆጣጠር የሚችል ታይቶ የማይታወቅ ሀይል የተዘጋጀ ሲሆን በሌላ በኩል በጫጫ ሸኖ ለገጣፎ የሚኒሊክን ቤተ-መንግስት በቅርብ ርቀት የሚመለከት ሌላ ሀይል በከፍተኛ ደረጃ እየተጠጋ ይገኛል።
ብልሀትና ጥበብን ከጀግንነት ጋር ከአባቶቹ የተካነዉ የጦር አዛዣችን ጀ/ተፈራ ማሞ ይህን ልዩ የሆነ ተዓምር በጥቂት ጊዚያት ሰርቶ ሊያሥደምመን የመጨረሻ ምዕራፍ ላይም ይገኛል።
ቅጥረኛና የስልጣን ዘብ የሆንከዉ መከላከያ፤አድማ ብተናና ሚሊሻ ሆይ የምህረት ጊዜዉ እያለቀ ነዉና ዕድልህን በመጠቀም ነፍስህን አትርፍ እልሀለዉ።
አማራ 4 ኪሎ ወይም ሞት!!!
+9
በ64ኛ ክፍለ ጦሩ ስር የምትገኘዋ 1ኛ ሬጅመንት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዶል።
የካቲት 13/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በሸበል በረንታ ወረዳ የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ከሬጅመንቷ አመራርና አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶል።
በውይይት መድርኩ በ64ኛ ክፍለ ጦሩ ስር የሚትገኘዋ 1ኛ ሬጅመንት ውስጣዊ ቁመናዋን በመፈተሽ፣ በመገምገም በሻለቀዋ የኦዲት ሪፖርት በማቅርብ 1ኛ ሬጅመንት የጎደሉ አመራር በማሟላት የአማራ ህዝብ ከአብይ አህመድ አርመኔዊ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ወታደሩ የፖለቲካ ግንዛቤውና አስተምዕሮው ከፍ ያለ መሆን እንዳለበት ግንዛቤ ተሰጥቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙ
የምህርት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።
የካቲት 09/2018ዓ.ም
1ኛ.መሀመድ ደምሴ
2ኛ.ቢኒያም ግዛቸው የተባሉ በእነማይ ወረዳ ጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት 6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት አባል የነበሩ ሁለት ኮሪያ ክላሽ ተተኮሽ በመያዝ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 09/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
ወርሐ የካቲት 2016ዓ.ም
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ መኮንን (ደሥታው ዘላለም መንግሥቴ)
✅በአጋጭቶ አደር ዳያሥፖራዎች የተዋከበበት
✅በፈርጣጭ ጋዜጠኞች እንዲገደል በቴሌቪዥን የታወጀበት
✅በሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዎርጊሥ የተተፋበት፣ በሀብታሙ አያሌው ተሾመ አፍራሳ በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ውባንተ አባተ ብልጽግና ነው የተባለበት፣ በጀነራል አጥናፉ የተሰደበበት፣ በደናቁርቱ ግምባር የተሰደበበት፣ በፀረ ዓምሐሮች ዓምሐራነቱን ሰጭም ነሺም የሆኑበት
✅በዓምሐራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች የተዋከበበት
✅በጋዜጠኞች፣ በሚዲያዎች፣ ከሐገር ውሥጥ እሥከ ባሕር ማዶ ባሉ አዋቂ ነን ባይ አላዋቂ ሆዳም አምሐሮች ታርጋ የተለጠፈበት
✅አካሉም ነፍሱም ማረፊያ ያጣ እንዲሆን የተደረገበት የዓምሐራ ሕዝብ ጥቁር ወር ነው።
✅አርበኛው ሐሳዊያንን በዕውነት ሰይፍ መትሮ በከፍታ፣ በንጽሕና፣ በፍጹም ዓምሐራነት እና አሥራታዊነት ለሕልውና ትግሉ እሥከ ሕይወት ሕቅታ የታመነበት እንዲሁም ታሪኩን በወርቅ የደም ቀለም የጻፈበት ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን👊
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA✊
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ቋሚ ምሥል፦ ምልዑው ዓምሐራ የነጻነት ተፋላሚ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ
''ኧረ ውብዬ አትሙትብኝ
ገና ያልጨረሥኩት ጉዳይ አለብኝ''።
+2
የምረት ጥሪውን ተቀብለው በዛሬው እለት ሁለት የብሬን ረዳት እና ሶስት የሚኒሻ አባሎች 201ኛ ኮርን 74ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
የካቲት 14/2018 ዓ.ም
1.አቡ ታገለ....ሚሊሻ ኮሪያ ክላሽ
2.ዳኘ አስሜ.....ሚሊሻ ኮሪያ ክላሽ
3.አወቀ ባንተአምላክ..ሚሊሻ
4.እያሱ አሰፋ....ከ25ክ/ጦር መከላከያ
5.ሞአስ ጋሊ....ከ25ኛክ/ጦር መከላከያ ከመርጦ ለማርያም ከተማ በመውጣት 201ኛ ኮርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ" አዲስተስፋ
አፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
+2
ከአዲስ አበባ የድንጋይ ውርወራ ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ሰማንያ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ስር የሚንቀሳቀሰው የኃይለማርያም ክፍለ ጦር አባላት፣ ልክ እንደ ንስር ከአየር ላይ ተወርውረው የጠላትን ምሽግ የመበጣጠስ ብቃታቸውን በተግባር ይታወቃሉ።
የጥይት ዝናብና የሰማይ መብረቅ በማይበግራቸው በእነዚህ ቆራጥ ተዋጊዎች ፊት፣ የአብይ አህመድ ጦርን በገባበት ገብተው የሞት ወጥመድ ውስጥ እየተገኘ ሲቀጣና የጀግንነት ጥግ ምን እንደሆነ በተጨባጭ የሚያሳዩ።
የዓድዋ ክ/ጦር መልሶ ማደራጀት (ሪፎርም) ተጠናቀቀ
🔸አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦር ለ7 ቀናት ከመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር አስተባባሪ ግብረ-ሀይል ማለትም አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ፣ አርበኛ ስጦታው ዳኛው(ባሻ)፣ አርበኛ ታደሰ ወርቁ ፣አርበኛ መቶ አለቃ ቢራራ፣ አርበኛ ኢንጅነር በየነ አለማው፣ አርበኛ ሚኒያስ አለማየሁ፤ ከኮሩ ከፍተኛ አመራር ጋር በመሆን ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ፣ የስራ ተግዳሮቶችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት ለቀጣይ ክ/ጦሯን በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ የድርጅት መርህን በተከተለ መልኩ ስራዎችን እንድትፈፅም ማድረግና ለውጤት መታተር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።
በተጨማሪ በማንኛውም አይነት የስራ ዘርፍ መርህን በተከተለ መልኩ በኃላፊነት ተግባራትን ከመከዎን ባሻገር እዝ እና ሰንሰለትን ጠብቆ መልካም የስራ ውጤቶችን እውቅና መስጠት እንደሚገባ ሁሉ መጠየቅም እንዳለ በአፅኖት ተገልጿል ተፈፃሚም ሆኗል።
በጥልቅ ግምገማ የአድዋ ክ/ጦር መልካም ስራዎችንና ተሞክሮዎችን በማድነቅ እንዲሁም እውቅና በመስጠት አድናቆትን ያገኙ ሲሆን በሁለንተናዊው የስራ ዘርፍ ተግዳሮት ሆነው የማያሰሩ እንቅፋቶችን በመለየት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ ችሎታንና አቅምን ባማከለ እና ለተሻለ ግዳጅ በሚያመች መልኩ የመሪዎች ሪፎርም ሊሰራ ችሏል።
ከዚህ በተጨማሪ የአድዋ ክ/ጦር ካሉት ብርጌዶች መካከል በሁለቱ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የብርጌድ ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።
💎የክ/ጦር ሪፎርም
1. የክ/ጦር ወታደራዊ ዋና አዛዥ...
አርበኛ.... ተመስገን ወለላው
2. ም/ወ/አዛዥ.................................
አርበኛ ...ገብረማርያም በየነ
3. የክ/ር ዘመቻ...አርበኛ ጌጤ ደሳለኝ
4. የክ/ር ም/ዘመቻ....አርበኛ ቻሌ መኩ
5. የክ/ሩ ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ...አርበኛ ገበያው አቤ
6. የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ........አርበኛ ተስፋ ጌታሁን
7.የፅ/ቤት ኃላፊ...አርበኛ ጌታቸው ማንደፍሮ
8. የህ/ግንኙነት ኃላፊ....አርበኛ ዳንኤል አቡሀይ
9.ህዝብ አስተዳደር....አርበኛ አዳም ውበት
10.አደረጃጀት.....አርበኛ ተዋቸው አንመው
11. የሰ/አስ/አስተዳደር....አርበኛ ኤፍሬም መዝገቡ
12. ሎጀስቲክ.....አርበኛ ሀብታሙ ደምለው
13.ትምህርትና ስልጠና....አርበኛ ብርሌው አበባው
14.ፋይናንስ..........አርበኛ አየሁ አለሙ
💎የብርጌድ ሪፎርም:
1ኛ...የንጋት ጮራ ብርጌድ
አርበኛ መኳንንት አንዳርጌ......ዋና ብርጌድ መሪ
አርበኛ ምረቴ አወቀ.........ምክትል ብርጌድ መሪ
አርበኛ እሸቴ ይስማው.....የብርጌድ ዘመቻ
2...የነብሮ ብርጌድ ሪፎርም
አርበኛ መኳንንት ተገኘ.....ዋና ብርጌድ መሪ
አርበኛ ፍቅሩ .. ..ምክትል ብርጌድ መሪ
አርበኛ ደሴ ባየ....የብርጌድ ዘመቻ
የተሰራውን የመሪዎች ሪፎርም ሁሉም የሰራዊት አባላት በሙሉ ድምፅ ከማፅደቃቸው በተጨማሪ ሁሉም የክ/ጦ አመራሮች በሰራዊቱ ፊት እንዲሁም የአፋብን ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ የዕዙና የኮር አመራር ባሉበት በታማኝነት፣ በፍታዊነት፣ በቅንነት፣ እዝ እና ሰንሰለትን በመጠበቅ ከትናንት ተግዳሮቶቻችን ተምረን ጠንካራ ጎኖቻችን የበለጠ አጠንክረን በተሻለ የስራ አፈፃፀም የአማራን የህልውና ትግል አሸናፊ ሆኖ የድል ችቦ ለማብራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል አማራዊ ግዴታችን እንወጣለን ሲሉ ቃል ኪዳን ገብተዋል።
በመጨረሻም የዕዝ ግብረሀይሉና የኮሩ አመራር የአድዋን ክ/ጦር አመራሮች በጋራ በመሆን ድርጅታዊ መርህንና አሰራርን ተከትሎ መስራት፣ በየዘርፉ በተጠያቂነትና በኃላፊነት ስራዎችን መከወን፣ በግምገማ ተግዳሮቶችን መለየትና አቅጣጫ ማስቀመጥ፣ የተሻለ የስራ አፈፃፀምን ማስቀጠልና ለታሪክ መሰነድ እንደሚገባ በጋራ መክረዋል።
ተስተውለው የነበሩ እክሎች መደገም የሌለባቸው መሆኑን በማፅናት በቀጣይ የበለጠ ስኬታማ ስራ ለመስራት በአዲስ አቅም ለመስራት ቃል በመግባት የክ/ጦሩ መልሶ ማደራጀት (Reform) በስኬት ተጠናቋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
ይካቲት 14/2018 ዓ.ም
ከአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የቀረበ ጥሪ!!
እንደሚታወቀው አረመኔው አብይ አህመድ እና የስርዓቱ ቀንበር ተሸካሚ ብአዴን አማራን ከምድር ገፅ ለማጥፋት ሌት ከቀን እየሰሩት እንደሆነ መላው የአለማችን ህዝብ የሚያውቀው የምድር ሐቅ ነው። በመሆኑም ይህን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመጣል ሰራዊታችን እና የጦር መሳሪያዎችን እያዘመንን ወደፊት በብርሃን ፍጥነት እየገሰገስን እንገኛለን።
ድርጅታችን አፋብን የምህረት አዋጅ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል። ሆኖም ጥሪ ተደርጎላችሁ ለመውጣት በዝግጅት ላይ ያላችሁ የመከላከያ አባል፥የአድማ መከላከል፥ የሚኒሻ እና በማነኛውም በፖለቲካ እንደ እየ መክሌታችሁ በብልፅግናው ስርዓት ውስጥ የምትገኙ እንዲሁም ከመከላከያ ተመላሽ፣ ከአድማ መከላከል ተመላሽ፣ ከህዝብ ፖሊስ ተመላሽ፣ ከሚሊሻ ተመላሽ የሆናችሁ እና ከዚህ በፊት በፋኖ አደረጃጀት ቆይታችሁ አሁን በተለያዩ ጉዳዮች ከትግሉ ርቃችሁ የቆያችሁ፤ በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ ከየካቲት 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር በሚገኝባቸው ቀጠናዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
1.ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/የሆነች
2.የአማራ ተወላጅ የሆነ/የሆነች እና በብሔርተኝነት ትግሉ ሙሉ በሙሉ ያመነ/ያመነች
3.ማንኛውንም ሃይማኖት ማክበር የሚችል/የምትችል
4.ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆነ/የሆነች
5.ስለተወለደበት አካባቢ ሙሉ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
6.ምንም አይነት ሱስ የሌለበት/ባት
7.ከአካል ጉዳት ነፃ የሆነ/የሆነች
8.ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ/የሆነች
9.ማንበብና መፃፍ የሚችል/የምትችል
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር
የካቲት 14/2018 ዓ.ም
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በእናርጅ እናውጋ ወረዳ መጠያ ቀጠና ከሚገኘው ማህበረሰብ ጋር የድርጁቱ የኮሩ እና የክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።
➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧
የካቲት 14/2018ዓ.ም
በውይይቱም፦
1.የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ትግል መነሻ ምክንያቶች
2.ለአማራ ፋኖ ትግል ማድረግ ስላለባቸዉ ሁለተናዊ ድጋፍ።
3.ህዝቡ ተደራጅቶ ራሱን ከወራሪ ስርዓት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት
4.ስለ ፋኖ የትግል አቋምና አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ከህዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና በቂ ምላሽ በአመራሮች ተሰጥቷል። በውይይቱም ሙስሊም እና ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች እና አማኞች የወንድማማችነት እና የቤተሰባዊነት ፍቅር በማሳየት እና በንቃት ተሳትፈዋል ።
ተሰብሳቢወች በመጠያ ከተማ የአብይ አህመድን ስርዓት የሚነቅፍ የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄድ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ" አዲስ ተስፋ
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ያ የበሻሻው ጨቅላ፣ ትላንት ፊቱ ላይ የተስፋ መቁረጥ ጥላ አጥልቶ ታየ። የሥልጣን መንበሩ እንደ ሸክላ ሲሰነጠቅ የታየው ይመስል፣ በሰራዊት ታጥሮ ወደ ወለጋ አቀና። በዚያም የፍርሃትና የክፋት መርዝ የታጨቀበትን ንግግር ለሕዝቡ አፈሰሰ። "አማራና ትግሬ ተባብረው መንበራችሁን ሊቀሙባችሁ ነው፤ ተነሱ፣ መክቱ!" እያለ የገዛ ወገኑን በጥርጣሬ ሰይፍ ሊያስታጥቅ ሞከረ። ትላንት በወለጋ የፈሰሰውን ደም ከትግራዩ እልቂት ጋር እያነጻጸረ፣ "እኛ የፈጀነው ይበልጣል" ብሎ ሲፎክር አንደበቱ አልተሳሰረም ነበር። የሰው ልጅ ትውስታ አጭር ይመስለዋል፤ ነገር ግን ያ የፈሰሰው ደም ገና አልደረቀም።
የኦሮሞ ሕዝብ ግን ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል። እነዚህ ኃይሎች የሚመጡት ለሕዝቡ ሳይሆን፣ ለዚያ ለበሻሻው ልዑልና ለኦህዴድ ወንበር እንደሆነ ሊገነዘብ ይገባል። "የሰራኸውን በደል ዋጋህን ክፈል" ሊለው እንጂ፣ ሕዝቡን ሊወጋ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ደግሞ በምቾት ዓለም ውስጥ ሆነው "መሪ ነን" የሚሉ ድሬዎችና የሜንጫ አቀንቃኞች፣ ይህንን እውነት በድፍረት መናገር ካልቻሉ የታሪክ ተጠያቂዎች ይሆናሉ። አብይ አህመድ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ፣ ከጀርባው የአማራን መሬት የማጥፋትና የመቆራረስ ተንኮል አዝሎ እንደሆነ ትላንት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ላይ የተፈጸመው ሴራ ህያው ምስክር ነው።
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ፍኖተ አማራ ለየት የሚያደርገው የአማራ ፋኖ የታጋዮች ሚዲያ መሆኑ ነው እሱም መሬት ላይ ተራራና ገደሉን ብርዱንና ፀሐይኑ አብረን ተቋቁመን መስራታችን ነው ለዚህም ጠላቶቻችን አጀንዳ ይዘው እየመጡ ነው እኛም አለን ብለናል ከዛሬ ቀን ጀምሮ እንወያያለን እንሰለጥናል ሚዲያችን አብረን እናሳድጋለን ከአማራ የቁርጥ ቀን ልጆቹ ጋር አብረን ተራራና ብርዱን ወጠን ወርደን አውደ ውጊያዎች አብርን እየሰራን እንገኛለን ይወዳጁን!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
