ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 619
Підписники
+124 години
+3977 днів
+1 06030 днів
Архів дописів
የአድዋው ወላፈን፣ የፋኖው ድፍንፍን
ከምኒልክ አደባባይ፣ ከጣይቱ ድንኳን
ታሪክ ተረገዘ፣ የጥቁር ኩራት ቀን
አድዋ ማለት፣ የነፃነት ጮራ
ዓለም ያፈረበት፣ የጀግኖች ተራራ።
ያን ጊዜም አባቶች፣ በነጭ ጥይት መሀል
በእምነት ቆመው ነበር፣ ለሀገር መከለል
ዛሬም ያው ወኔ፣ በልጅ ደም ይፈሳል
ፋኖ ባለው ጠመንጃ፣ ታሪክ ያድሳል።
ፋኖ ማለት...
የሀገር ጠባቂ፣ የገበሬው ልጅ
ለፍትህ የቆመ፣ የጭቁን ወዳጅ
እንደ አድዋው ጀግና፣ እንደነ ተክለሃይማኖት:
ላንዲት ኢትዮጵያ፣ ለክብሯ የሚሞት።
ተራራው ምስክር፣ ሸለቆው ያውቀዋል
ፋኖ በሄደበት፣ ድል ይከተለዋል።
የአድዋው መንፈስ፣ በልቡ የነገሰ
የጠላትን ምሽግ፣ ሰብሮ ያፈረሰ።
12ቱ የዓድዋ ጦር ጄኔራሎች
"አድዋ፤ የመላው ዓለም ሕዝብ ታላቅ ድል!
የአድዋ ድል ስናከብር ቀድመው የሚመጡልን ታዋቂ የጦር መሪዎች ናቸው :: ፣ ከእነሱ ጀርባ ግን የድሉ እውነተኛ የጀርባ አጥንት የሆኑት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።
ዛሬ ደግሞ ታሪክ ብዙም የማያነሳቸውን ግን ደግሞ ያለ እነሱ ድሉ የማይታሰብ የነበሩ ጀግኖቻችንን እናስታውሳለን።
1 ኛው . የጀግኖች ኢትዮጵያውያን ሴቶች፡ ከስንቅ እስከ ዘመቻ
በጦርነቱ ወቅት "ታላቅ ገድል " የፈፀሙት ይገኙበታል ።
እነሱ ስልታዊ መሪዎች፣ የሞራል ምንጮችና ተዋጊዎችም ነበሩ።
እቴጌ ጣይቱ ብጡል፡ የጦርነቱ ስትራቴጂስትና የመቀሌውን ምሽግ የውኃ ምንጭ በማስከበብ የጠላትን አንገት ያስደፉ ታላቅ መሪ ናቸው ።
አዜብ ጋንቶ?፡ በጦርነቱ ግንባር ቀደም በመሆን ተሰልፈው ከወንዶች እኩል የጠላትን ምሽግ የሰበሩ ጀግና ናቸው ።
ልክየለሽ ባይሳ?፡ በጀግንነታቸውና በጦር ሜዳ ውሎአቸው የሚታወቁ ሌላኛው የድሉ ፈርጥ ነበሩ ።
በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶቻችን ደግሞ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ቁስለኛን በመንከባከብና በነጋሪት ድምፅ የወታደሩን ወኔ በመቀስቀስ የድሉ አዝመራ እንዲታፈስ አድርገዋል።
2ተኛ የእጅ ባለሙያዎች፡ ናቸው ። እነዚህ የጥበብ ሰዎች የድሉ መሣሪያ ቀራፂዎች በመሆን የአድዋ ጀግኖች የሚታጠቁትን መሣሪያ አበጅተው ታላቅ ገድል ፈጽመዋል።
የብረት ቀጥቃጮች፡ ጦር፣ ጎራዴና ጋሻን በመስራት ወታደሩን ያስታጠቁ ናቸው ።
የቆዳ ባለሙያዎች (ሸማኒዎችና ሰራተኞች)፦ የፈረስ እርካብ፣ ልጓም እና ለረጅም ጉዞ የሚሆኑ የቆዳ ውጤቶችን በማዘጋጀት ሰራዊቱ እንዲንቀሳቀስ ያደረጉ ናቸው ።
ባለሙያዎቹ ሌት ተቀን በመስራት የኢትዮጵያን ነፃነት ከብረትና ከቆዳ ቀጥቅጠው ሠርተዋል።
ዛሬ አድዋን ስናከብር፦
ለሴቶቻችን ጥንካሬ፣ ለባለሙያዎቻችን ጥበብና ለጀግኖቻችን ደም ክብር እንሰጣለን!
አድዋ የኢትዮጵያዊነት ማህተም ነው ፣
አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ነው።
ከደብረ ኤልያስና አከባቢው ወደ ጎፍጭማ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ብልፅግና ኃይል ላይ በተፈፀመ የቆረጣ ማጥቃት በርካታ ወታደሮች ተገደሉ!
በቀጠናው ከዚህ ቀደም ፋኖ በሚፈፅነው ጥቃት ከባድ ኪሳራ እየተከናነበ የነበረው የአገዛዙ ኃይል የሰራዊትን ደህንነት ለመገበቅ በማሰብ በከባባድ መሣሪያ ሽፋን በመስጠት እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ነው ሊመከት የማይችል ከባድ የቆረጣ ጥቃት የተከፈተበትን።
ፋኖ ወደ ጠላት ምሽግ በመግባት ከሚወስደው እርምጃ በተጨማሪ፡ ከሳንጃውግ ውጊያ ጀምሮ በጨበጫ፡ በቆረጣና በከበባ የጠላት ብልፅግና ኃይልን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ግብአተ መሬቱን መፈፀሙን አጠናክሮ ቀጥሏል።
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር የአንበሳው ጋይንት ክ/ጦር አመራሮች ከጎብጎብ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚህም በወቅታዊ የአማራ ፋኖ የትግል ጉዳይ እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን ማህበረሰቡም ትግሉን እያገዘ የቆየ መሆኑን እና በቀጣይም ከትግሉ ጎን ሆኖ የጋራ ትግል እሚያደርግባቸውን ሁለተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጭምር አሳውቋል።
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል!!!
የካቲት 22/2018 ዓ,ም
የብልፅግና ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ ዛሬም "የኢኮኖሚ ጦርነት ከፍቶ እየሰራ ይገኛል!!
የአብይ አህመድ አስተዳደር የአማራን ህዝብ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለመስበር ያለመ አዲስ የጥፋት ዘመቻ ጀምር እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ይድር ኃቅ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መመስረትን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ይሄው ስርዓት አሁን ላይ ገበሬውን ያነጣጠረ የንግድ እገዳና ማዕቀብ እያከናወነ ይገኛል።
በኦህዴድ እና በብአዴን መካከል የተመሰረተው ያልተቀደሰ ጋብቻ ዋና ግቡ የአማራን ማህበረሰብ በተለያዩ ስልቶች ማዳከም ነው። ስርዓቱ እንደ እስስት ቀለሙን እየቀያየረ፣ በአንድ በኩል የፖለቲካ ጭቆናን ሲያፋፍም፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝቡን የህልውና መሰረት የሆነውን የግብርና ምርት እያገተ ይገኛል።
በተለይም በዛሬው ዕለት ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ የሚጓጓዙ የግብርና ምርቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና እገዳ ተጥሎ ጤፍ፣ ሽንኩርት እና ሌሎች መሰረታዊ ሰብሎች።
ከአማራ ግዛት በሸኖ አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መስመሮች በመዝጋት
ይህ ወቅት የአማራ ገበሬ ምርቱን ለገበያ አቅርቦ ለቀጣዩ የምርት ዘመን የሚሆነውን የአፈር ማዳበሪያ የሚገዛበት ወሳኝ ጊዜ ቢሆንም ስርዓቱ ምርቱ ከክልል እንዳይወጣ በማድረግ ገበሬው የማዳበሪያ አቅም እንዳይኖረውና ለረሃብ እንዲጋለጥ ሆን ብሎ እየሰራ ይገኛል።
የኦሮሙማ ስርዓት እና የመጨረሻው የውድቀት በምግብ ዋስትና ላይ የተከፈተ ዘመቻ የስርዓቱን መላላጥና መውደቅ የሚያፋጥን ነው። ምርቶች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች እንዳይገቡ በማድረግ በአንድ በኩል የአማራን ገበሬ ገቢ ማሳጣት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ የሚኖረውን ህዝብ ለከፍተኛ የኑሮ ውድነትና ለረሃብ መዳረግ የስርዓቱ ስልት ሆኗል። ይህ ድርጊት የአማራን ህዝብ ወደ አላስፈላጊ ስቃይና መከራ የሚገፋ አረመኔያዊ ተግባርም ነው።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የካቲት 22/06/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ከሰም ፪ ኮር፣ ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ሪፖርተር ክፍል አርበኛ ሃቀኛው ይታፈር
ሰበር ዜና
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ሁለት ብርጌዶች ሁለት ከተሞች ላይ የነበረ ጠላትን ሲያተራምሱት አደሩ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው የግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆኑት አጥናፋ ብርጌድ በወርቅ ደሞ ከተማ ይታየው ብርጌድ ደግሞ በገደብየ ከተማ ሰፍሮ የነበረውን የአገዛዙን ቅልብ ሀይል ጥይት በማጠጣት እንደ ሰካራም ከወዲያ ወዲህ ሲያሯሩጡት አድረዋል ። የሁለቱ ብርጌድ ጀግኖች ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተሞቹ ዘልቀው በመግባት በእየ ቦታው ሲንቀሳቀስ የነበረን ጥምር ጦር ሲለቃቅሙት ያመሹ ሲሆን በርካታውን በ*ሙ* ት ሸኝተውታል ።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አንበሶች ዛሬም እንደተለመደው የብርሃኑን ጁላ ጦር ምሽቱን እንደ እሳት እራት ሲለበልቡት ሲያድሩ በአውደ ውጊያ ላይ የተገኙ ድሎች :-
🗡 15 በ*ሙ*ት የ*ተ*ደ*መ*ሰ*ሰ
🗡 12 በላይ የቆሰለ
🗡ሶስት መከላከያና አንድ አጥቦ አይለብሴ እስከ ነብሱ የተማረከ በይታየው ብርጌድ አባላት
🗡4 ክላሽ 1 አብራራው መሳሪያ ፣ 600 የክላሽ ተተኳሽ እና 5 ቦንብ ተ*ማ*ር*ኳ*ል ። በጎንደሬዎች እርምጃ የተደናገጡ የአገዛዙ ብልፅግና ካድሪዎች ፋኖዎች ባልተጠበቀ አቅጣጫ ሰብረው ሌላ ከተማ ሊቆጣጠሩ ይችላሉ በማለት በስጋት ያለ እንቅልፍ ሲያድሩ የፀጥታው መዋቅር ደግሞ ከአምባጊወርጊስ እስከ ደባርቅ ድረስ ያሌ የሌለ ሀይሉን ሰብስቦ ከተሞችን ሲጠባበቅ አድሯል ። ጀግኖቻችን ግን ስራችን በሚገባ ሰርተው ወደ መጡበት ያለ ጉዳት በሰላም ተመልሰዋል ።
አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!!
አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
የካቲት 22/2018 ዓ/ም
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃድ ዘመቻ መሪ በነበረው ሰማዕቱ አርበኛ ፍሬው አለና ስም በተሰየመው ዘመቻ ምኒልክ ዕዝ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ!
በምዕራብ ወሎ ግንባር የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ሰራዊት ድባቅ ተመታ! 2 ሞርተር 82 mm ከበርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጋር ተማርኳል:: በርካታ ጠላትም ተደምስሷል::
"በዘመቻ አርበኛ ፍሬው አለና" መቅደላ፣ ተንታ፣ አማራ ሳይንት እና ወግድ ወረዳ ውስጥ ታሪክ ተሰርቷል::
መቅደላ ወረዳ ውስጥ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ሻለቃ እና የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በቅንጅት በሰሩት ኦፕሬሽን የመቅደላ ወረዳ መቀመጫ ማሻ ከተማን ጨምሮ ሌሎች ታዳጊ ከተሞችም በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር ውለዋል::
የጠላት ሃይል የካቲት 20/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማና ተንታን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ኔትወርክ በማጥፋት የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃን ጨምሮ ወዳሉበት ቀጠና 83ኛ ክፍለ ጦርን ጨምሮ በበርካታ እግረኛ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም በሁለት ድሮን ታግዞ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ንስሮቹ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ይዞታዎቹ የነበሩትን መቅደላ ወረዳ ማሻንና አካባቢውን አስለቅቀው በመቆጣጠር ወደ ጊምባና ደሴ እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲሸሽ በማድረግና ሁለት ሞርተርን ጨምሮ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብሎም በርካታ ሰራዊት በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
በተጋድሎው የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃዋን ጨምሮ 2 ሞርተር 82mm አንድ ብሬን፣ አንድ ስናይፐር፣ ከ40 በላይ ክላሽ፣ ከ3500 በላይ የተለያየ ተተኳሽ፣ 9 የመገናኛ ባትሪ እንዲሁም 30 የጠላት ሰራዊት ማርከዋል::
ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ ወደ ተንታ ከተማ ማጥቃት በማድረግ በርካታ የጠላት ሰራዊት በመደምሰስ ተንታ ከተማን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል:: በተመሳሳይ 23ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ከሌሎች የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃዶች ጋር በመጣመር ማሻ ከተማን ተቆጣጥራለች:: ባጠቃላይ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በአምባሰል ተንታ ማሻ መቅደላና ደሴ ዙሪያ ቀጠናዎች ላይ እየተዘዋወረች ማርሽ ቀያሪ ድሎችን እያስመዘገበች ትገኛልች::
ባጠቃላይ "በዘመቻ አርበኛ ፍሬው አለና" ጠላት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን በዘመቻው የተሳተፉ ሁሉም የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ያስመዘገቡት ድል፦
2 ሞርተር
7 ብሬን
6 ስናይፐር
ከ100 በላይ ክላሽንኮቭ ከበርካታ ተተኳሽ እና ከ30 በላይ የጠላት ሰራዊት ጋር ተማርኳል::
የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሞባይል ኔትወርክ በማስጠፋት የመገናኛ አማራጭን ዘግቶ ኦፕሬሽን ለመስራት በማሰብ ዝግጅቱን አጠናቆ ካበቃ በኃላ በተወሰኑ ወረዳዎች ውስጥ እንቅስቃሴ ጀምሮ ስለነበር እንቅስቃሴውን ለመግታት ወግድ ወረዳ ውስጥ መብረቅ ክፍለ ጦር በትናንትናው እለት በአበዬ ጉርባ ቀጠና ገዛዛ አቦ አቅራቢያ ደፈጣ ጥላ በርካታ ኃይል ሙት እና ቁስለኛ ስታደርግ፣
በአማራ ሳይንት ግንባር ደግሞ የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ሻለቃ ጀብዱ ፈፅሟል:: ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ጓሜዳ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ ተካሂዷል:: ከሳይንት አጅባር ከተማ ተነስቶ ወደ ጓሜዳ ቀጠና በመግባት ከአርሶ አደሮች ግብር ለማሰባሰብ አስቦ በርካታ ኃይል ይዞ የመጣውን ጠላት ኃይል በመመከት ኦፕሬሽኑን ማበላሸት የቻለ ሲሆን ጠላት ጓሜዳን ሳይረግጥ ሲቀር በብስጭት የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ሲወረውር ውሎ የገበሬዎችን መኖሪያ ቤት እና ንብረት አቃጥሎ ወደመጣበት ፈርጥጧል::
በተለምዶ መለስሳንቃ በሩ የሚባለው ስፍራ ላይ በተደረገው ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል አባላት ስለተመቱ ቁስለኞች ሳይንት አጅባር ሆስፒታል ገብተዋል:: እዚያው አውደ ውጊያ የተደረገበት ቦታ ላይ የሞቱ እንዳሉም የካቲት 21/2018 ዓ.ም ጧት አስከሬን ሲለቅሙ ያዩዋቸው የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል::
በለጋምቦ እና ከላላ ወረዳዎች በኩል የሚንቀሳቀሰውና የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ክንፍ የሆነው ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደዉ) ክፍለ ጦር 3ኛ አህመድ አቀስታ ሻለቃ ወደ ዋርጃ ቀጠና ለመግባት በ20 መኪኖች ተጭኖ የተጓዘውን ጠላት በደፈጣ ጥቃት ዶግ አመድ በማድረግ 18 የደመሰሰ ሲሆን 23 የሚሆነው ጠላት ደግሞ ቁስለኛ ሆኖ አቀስታ የካቲት 12 ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ላይ መሆኑ ታውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃድ ዘመቻ መሪ በነበረው ሰማዕቱ አርበኛ ፍሬው አለና ስም በተሰየመው ዘመቻ የአፋብን ምኒልክ ዕዝ ታላቅ ድል ተጎናፅፏል!
በምዕራብ ወሎ ግንባር የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ሰራዊት ድባቅ ተመቷል፤ 2 ሞርተር 82 mm ከበርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጋር ተማርኳል፤ በርካታ ጠላትም ተደምስሷል::
በዚህ ዘመቻ መቅደላ፣ ተንታ፣ አማራ ሳይንት እና ወግድ ወረዳ ውስጥ ታሪክ ተሰርቷል::
መቅደላ ወረዳ ውስጥ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና የልጅ እያሱ ኮር በቅንጅት በሰሩት ኦፕሬሽን የመቅደላ ወረዳ መቀመጫ ማሻ ከተማን ጨምሮ ሌሎች ታዳጊ ከተሞችም በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር ውለዋል::
የጠላት ሃይል የካቲት 20/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማና ተንታን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ኔትወርክ በማጥፋት 83ኛ ክፍለ ጦርን ጨምሮ በበርካታ እግረኛ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም በሁለት ድሮን ታግዞ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ንስሮቹ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ይዞታዎቹ የነበሩትን መቅደላ ወረዳ ማሻንና አካባቢውን አስለቅቀው በመቆጣጠር ወደ ጊምባና ደሴ እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲሸሽ በማድረግና ሁለት ሞርተርን ጨምሮ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብሎም በርካታ ሰራዊት በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃዋም በተሳተፈችበት ውጊያ 2 ሞርተር 82mm አንድ ብሬን፣ አንድ ስናይፐር፣ ከ40 በላይ ክላሽ፣ ከ3500 በላይ የተለያየ ተተኳሽ፣ 9 የመገናኛ ባትሪ እንዲሁም 30 የጠላት ሰራዊት ማርከዋል::
ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ ወደ ተንታ ከተማ ማጥቃት በማድረግ በርካታ የጠላት ሰራዊት በመደምሰስ ተንታ ከተማን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል:: በተመሳሳይ 23ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ከሌሎች የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃዶች ጋር በመጣመር ማሻ ከተማን ተቆጣጥራለች:: ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በአምባሰል ተንታ ማሻ መቅደላና ደሴ ዙሪያ ቀጠናዎች ላይ እየተዘዋወረች ማርሽ ቀያሪ ድሎችን እያስመዘገበች ትገኛልች።
በሌሎች የደቡብ እና ምእራባዊ የወሎ ወረዳወች የምኒልክ እዝ አሃዶች ጠንካራ የማጥቃት እና የመከላከል ውጊያ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ "በዘመቻ አርበኛ ፍሬው አለና" ጠላት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን በዘመቻው የተሳተፉ ሁሉም የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ያስመዘገቡት ድል፦
👉 2 (ሁለት) ሞርተር
👉 7 (ሰባት)ብሬን
👉 6 (ስድስት) ስናይፐር
ከ100 በላይ ክላሽንኮቭ ከበርካታ ተተኳሽ እና ከ30 በላይ የጠላት ሰራዊት ጋር ተማርኳል::
ይቀጥላል...
አስረስ ማረ
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ኛ ኮር ከበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
"ክህደት ለጥቂቶች ውርደት ነው፤ ትግሉ ግን በጀግኖች መስዋዕትነትና በሕዝብ ደም የሚጸና የነፃነት ቃል-ኪዳን ነው!"
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በአማራ ተራራዎችና በየሸለቆው እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ፣ የጠላትን ምሽግ እንደ ናዳ እየናደ ባለበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፤ ጥቂት የሕዝብን አደራ የበሉ አመራሮች ለጠላት እጃቸውን በመስጠት "የውርደት ካባ" ደርበዋል። ይህንን የከሃዲዎች ድራማ ተከትሎ ክፍለ-ጦራችን በትግሉ መስመር ላይ ያሉትን እውነታዎች በማጤን የሚከተለውን ወጥ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
፩. የክብር ጥሪ፦ በተለያየ ምክኒያት እጅ በሰጡና ተልዕኮ ባነገቡ ግለሰቦች ጫና ከትግሉ ለወጡ የትግል ጓዶቻችን
በግልብ ውሳኔዎችና በአመራር ብልሹነት ምክንያት ልባችሁ አዝኖ፣ አኩርፋችሁ ከትግል ሜዳው የወጣችሁ የቁርጥ ቀን ልጆች ሆይ! ክፍለ ጦራችን በነበረው የአመራር ክፍተትና በተፈጠሩ ስህተቶች ምክንያት ትልቅ ይቅርታ ይጠይቃል። የእናንተ መራቅ ለባንዳዎችና ለጠላቶቻችን ድል ሆኖ እንዲቆጠር አንፈቅድም። ቂም በቀልን ለጠላት ትተን፣ ለሕዝባችን ህልውና ስንል ትላንት የነበረውን ቅሬታ በይቅርታ አልፈን፣ ዳግም ወደ ትግል ሜዳው እንድትመለሱና የተጀመረውን የነፃነት ጉዞ በጋራ እንድናገባድድ በሕዝብ ስም ጥሪ እናቀርባለን። የጀግና ቤቱ ትግል እንጂ ኩርፊያ አይደለምና!
፪. የተደናገጡትን መመለስና የ"እጅ መስጠት ድራማውን" ማጋለጥ
ፋኖ ሳይሆኑ "ፋኖ ነን" በማለት፣ ከአሳፋሪ ከሀዲዎች ጋር በመሆን የመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ማሟሻ በመሆን "እጅ የመስጠት ድራማ" የሰራችሁና የተደናገጣችሁ ግለሰቦች ሆይ!
ይህ የክህደት መንገድ መጨረሻው የታሪክ እርግማንና የውርደት ማቅ ነው።
በጊዜያዊ ጥቅም ተደልላችሁ ወይም በመረጃ እጥረት ተደናግራችሁ የሕዝብን ትግል ለማሳነስ የሄዳችሁበት መንገድ የትም አያደርሳችሁም።
በመሆኑም፣ የሠራችሁትን ጥፋት ተረድታችሁ፣ ከውርደት ጎዳና ወጥታችሁ ወደ ትክክለኛው የሕዝብ መስመር እንድትገቡ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርባለን።
የሕዝብ ቁጣ ሳይቀድማችሁ ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ!
፫. የባንዳዎች ክህደትና የትግሉ ጥራት
ጥቂት አመራሮች ለጠላት አጎንባሽ መሆናቸው ትግሉን አያቆመውም፤ ይልቁንም እንደ እሳት እያጠራው ይሄዳል። ጀግኖች በተራራው ላይ ነፃነትን ሲዘሩ፣ ባንዳዎች ግን በሸለቆው ውስጥ "ሆዴ አምላኬ" እያሉ ውርደትን ያመርታሉ። ክፍለ ጦራችን በባንዳዎች ክህደትና በሰርጎ-ገቦች ደባ የሚገረምበት ጊዜ የለውም። እነዚህ ግለሰቦች የሕዝብን አደራ ለጠላት "ገጸ-በረከት" አድርገው ቢያቀርቡም፣ በደራ ተራራዎች ላይ የቆመው ጽኑዓን ሰራዊታችን ግን የነፃነት አርማውን ከፍ አድርጎ ይውለበልባል። ባንዳዎች እንደ ትቢያ ይበተናሉ፤ የነፃነት ታጋዮች ግን እንደ ጽዮን ተራራ ጸንተው ይቆማሉ።
፬. የማጠቃለያ መልዕክት
ለሰራዊታችን፦ የአመራሮች መክዳት ጥንካሬያችንን ይፈትናል እንጂ ዓላማችንን አይቀይርም። ይበልጥ ተደራጅ፣ ን ተባብረው ለነፃነትህ ይቆማሉ።
ለከሃዲዎች፦ የሕዝብ ደም በከንቱ አይፈስም፤ በሥልጣንና በጥቅም የሸጣችሁት የሕዝብ አደራ ነገ መተንፈሻ ያሳጣችኋል።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
በፍቃዱ በላይ ክፍለ-ጦር
የካቲት 22/2018 ዓ/ም
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የቀስተ ደመና ሻለቃ በጠላት ላይ ጥቃትን በመፈጸም በርካታ የብልጽግና ሠራዊትን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።
የካቲት 21/2018 ዓ'ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ የሠራዊት አባላት በዛሬው ዕለት ከደብረ ኤልያስ ከተማና ከየቀጋት መገንጠያ በመነሳት ወደ አሰርማና ጎፍጭማ ቀበሌ በተንቀሳቀሰው የወራሪው የብልጽግና ሠራዊት ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸም በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ሠራዊትን ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።
አሰርማ ማርያም ላይ ታቦት ለማስከበር ሲንቀሳቀስ የነበረውን የጠላት ኃይል ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ፋኖዎች ደፈጣ በመጣል ገርፈው ሲመልሱት በተመሳሳይ ሰዓት ጎፍጭማ ከተማ ላይ በተደረገ ውጊያ በርካታ የጠላት ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
በዚህ ሰዓትም የወረዳው የብልጽግናው ሰላምና ደኅንነት ተብየው ደምሴ ከጀግኖቹ ጥይት ለትንሽ አምልጦ በባሕር ጭቃ ተነክሮ ማምለጡን ምንጮቻችን ገልጸውልናል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
