uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
3 615
Підписники
+1324 години
+4187 днів
+1 05630 днів
Архів дописів
+4
ጨለማው የጎጃምን ተራሮች እንደ ኩታ ለብሷቸዋል። በአንድ በኩል የፕሮፓጋንዳው ማዕበል እንደ ክፉ ነፋስ ይነፍሳል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የጠመንጃው ጩኸት ያስተጋባል። ​ከሳምንት በፊት ነበር የአብይ አህመድ የቴክኖሎጂ አዳራሾች ውስጥ የሚርመሰመሱት የሳይበር ዘመቻ አድራጊዎች በቁልፍ ሰሌዳዎቻቸው አማካኝነት የአርበኛ ሀብታሙ የሱፍን ስም ለማጠልሸት መርዛቸውን መርጨት የጀመሩት። ዓላማቸው አንድ ነበር በአማራ ፋኖዎች መካከል የጥርጣሬን ዘር መዝራትና ህዝቡን ከተዋጊው መነጠል። "ሀብታሙ የለም ሀብታሙ እጁን ሰጥቷል የሚሉ ወሬዎች እንደ ሰደድ እሳት ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቀለቁት። ​ነገር ግን ሀቅና ወሬ ለየቅል ናቸው። አርበኛ ሀብታሙ ከአብይ አህመድ አገዛዝ ነፃ በወጡት ቀጠናዎች ከወሬው ማዕበል ይልቅ በተግባር ማዕበል ውስጥ እየዋኘ ይገኛል። ​ሆኖም እኛ የምንዋጋው ለወሬ ሳይሆን ለህልውና ነው" የሚለው ንግግሩ የሰሙትን ሁሉ ልብ ያሞቃል። ሆኖም ​አርበኛው ለአማራ ህዝብ፣ በውጭም በውስጥም ላላችሁ ደጋፊዎች እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፦ ​ወንድማችሁ በስራ ላይ ነው! በጠላት የሳይበር ጩኸት አትሸበሩ። እኛ እዚህ ሜዳው ላይ፣ እውነትን በደማችን እየፃፍን ነው። የነፃነት ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።Dawit Amhara ከግንባር

#የአደረጃጀት_ዜና‼️ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የ22ኛ፣ 31ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር ምስረታ ተጠናቋል። የጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አካል የሆነው የደጋው መብረቅ ኮር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አስደማሚ ተጋድሎዎችን እየፈፀመ ይገኛል። በስሩ የሚገኙትን አምስት ክፍለጦሮችን በማስተሳሰር  እረፍት አልባ አውደ ውጊያወችን በመፈፀም በጠላት ላይ በቀጠናው ፍፁም የበላይነት ወስዷል። ድርጅታችን ባወረደው መምሪያ መሰረት ኮራችንን አሁናዊ የትግላችንን አቋም በሚመጥን መልኩ የኮር አደረጃጀት ማሻሻያ አድርገናል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ለበርካታ ቀናት ውይይት ከተደረገበት በኋላ አደረጃጀቱ ተሰርቷል። ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ም/አ/ቀ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል ይጠራ የነበረው፤አሁን 106ኛ ኮር በሚል መጠሪያ ስም ተሰይሟል። እንዲሁም በደጋው መብረቅ ኮር ስር የነበሩትን ታሪካዊቷ ፅናት ክፍለጦር ፣ ጀብደኛዋ አንሻ ሰይድ ክፍለጦር፣ ምሽግ ሰባሪዋ ደጀን ክፍለጦር፣ ነበልባሏ ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለጦር፣ ተናደረፊዋ ሰንጥቅ ክፍለጦሮች እንዲሁም የወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አሃድ የነበሩትን ክፍለጠሮች ወደ ሶስት በማዋሃድ አዲሱን 106ኛ ኮርን አዋቅረናል። ስለሆነም  የሶስቱ ክፍለ ጦሮች ስያሜ፦           ✅22ኛ           ✅31ኛ እና           ✅34ኛ ክፍለጦር ተብለው ስያሜው በመስጠት የኮሩን መልሶ ማደራጀት ተግባር ተጠናቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የካቲት 26/2018 ዓ.ም

የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ በቀን 25/06/2018 ዓ.ም በጃዊ ወረዳ ቀዝቃዚት ቀበሌ ሁለት የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ንፁሃን አርሷደሮችን በድሮን ጨፍጭፏል በድሮን ጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ንፁሃን አማራዎች መካከል፦ 1. ቢተዉ ሰዉነት 2. ቄስ ሰለሞን ሞሴ 3. ልንገረዉ ታደለ 4. ዮሀንስ ለጋስ 5. ዋሴ ፍቃዱ 6. ያየህ ባዜ 7. አባ ደምሹ አጎስ 8. ንብረት ዘላለም 9. አዱኛ ተሜ 10. ገበያው መኮነን 11. ምስጋናዉ እና ተጨማሪ 4 ሰዎች በድምሩ 15 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በደረሰው አደጋ ከባድ ቁስለኛ በመሆን ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙ፦ 1. ቄስ ማስተዋል አንዷለም 2. ዮሐንስ ሙሴ 3. ጌታሁን ቸኮል 4. መልኬ ቸኮል 5. አባ ገዙ ደረበ 6. ሙሉአለም ስንሻዉ 7. አበባዉ ሽቴ 8. አበበ አንማዉ 9. ሙሉ ዉበት

በዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)‼️       ገደብየ ከተማ የነበረ ጠላት ተመታ!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው  የግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆኑት ይታየሁ እና ምስጋናው አጣኔ ብርጌድ አባላት በጥምረት የካቲት 25/2018 ዓ/ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ  በገደብየ ከተማ ዙሪያ ዳራ በተባለ ቦታ ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል ። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ ስም እየተደረገ ባለው ዘመቻ ንቁ  ተሳትፎ በማድረግ ጠላትን በመደምሰስና በመማረከ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል  ። የሁለቱ ብርጌድ ጀግኖቻችን ዛሬ በወሰዱት ኦፕሬሽን በደጎማ ከተማ ለተሰውብን አርበኛ ደመላሽ ስመኝ እና ሌሎች አርበኞች መሰዋትነት  የበቀል እርምጃ  ነው ሲሉ ጠላትን በማደን የሚታወቀው ጎንደሬ በጋሻው  ክፍለ ጦር  ሳይውል ሳያድር ደም መላሽነቱንም አረጋግጧል። በተደረገው አውደ ውጊያ በጠላት በኩል 7 የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኛን ደግሞ ወደ ዳባት ሆስፒታል አስገብቷል። በጀግኞች እጅ  በምርኮ 2 ክላሽንኮቭ መሳሪያ 400 የክላሽ ተቸኳሽ 2 ቦንብ 2 የወገብ ትጥቅ ገቢ ሁኗል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የአገዛዙን ስልጣን ለማስቀጠል እየሰሩ ያሉ ተላላኪ ባንዳዎችን አንገት እና እጅ መቁረጡን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን መሰዋት የሆኑ የጀግኖቻችን አላማ ግቡን ይመታል ።      አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!! አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ            26/ዐ6/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በአብይ አህመድ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጀ። ​​የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ 1ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ከየካቲት 24 እስከ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከደብረ ብርሃን ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች ተከታታይ ሶስት ቀናት ከአረመኔው አብይ አህመድ ኃይል ጋር ብርቱ ውጊያ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይሎች የአሳምነውን ልጆች ከበባ አድርጌ እደመስሳለሁ በሚል እቅድ ከደብረ ብርሃንና ሌሎች ከተሞች ኃይል አሰባስበው ቢመጡም በፋኖ አባላት ከፍተኛ ምት እንዲደርስባቸው ተደርጓል። ሆኖም ​ውጊያው በዋናነት በመጥቆሪያ ቀበሌ (ልዩ ስሙ 5 ቁጥር) ​በግፍት ቀበሌ ​ለሦስት ተከታታይ ቀናት በዘለቀው በዚህ አውደ ውጊያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የነጎድጎዳ ክፍለጦር አናብስቶች የአረመኔውን ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተቀዳጅተዋል። ከጠላት ኃይል የተገደሉ ጡት ቆራጩን አስከሬን በወርቀጉር ገብርኤል አካባቢ የተቀበሩ ሲሆን የቆሰሉ ደግሞ በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ። ​በተጨማሪም የአብይ አህመድ ኃይሎች የፋኖን ምት መቋቋም ሲያቅታቸው በከባድ መሣሪያ በንፁሃን መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት ሰንዝርዋል ሆኖም ግን የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ተዋጊዎች አካባቢውን መልሰው መቆጣጠር ችለዋል። ​በተያያዘ ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር በመርሐቤቴ ወረዳ አለም ከተማ ውስጥ በጠላት ኃይል ላይ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በመፈፀም ጀብድ ሰርተዋል። የናደው ክፍለ ጦር ተወርዋሪ አናብስቶች በቀን ማለትም የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1፡30 ላይ ጥቃት በመፈፀም በተለምዶ ማቁር 01 ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ውስጥ ጥበቃ (ሮንድ) ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ የብአዴን ሚሊሻዎች ላይ ​3 ሚሊሻዎች የተገደሉ ሲሆን 3 የሚሆኑት ደግሞ በጽኑ በማቁሰል ድላቸውን አጎናፅፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 26/06/2018 ዓ.ም

ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚዉል የመንገድ ስራም እየሰራ ይገኛል! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር  ከህልዉና ትግሉ ጎን ለጎን ለአካባቢዉ ማህበረሰብ  የልማት ሰራዎችን እያከነወነ የገኛል። ህዝቡም ፋኖ እየሰጠዉ ላለዉ አገልግሎትና የልማት የምንገድ ጠረጋ ጎን በጎን አብሮ እያገዘና በልማት ስራዉ እጅግ በጣም ደስተኛ ሁነዉ የበኩላቸዉን አስተዋፆ እያደረጉ ይገኛሉ። የአማራ ህዝብ መሰረተ ልማት እንዳያለማ መንገድ መብራት ዉሃ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች እንዳያገኝ ተደርጓል:: አለፍ ሲል ለአማራ ህዝብ ልማት ሰይሆን መጨፍጨፍያ ድሮን የሩሲያ ይሻላን ወይስ የቱርክ እያለ  መገደያችን እየገዛ ባለበት ወቅት በኛዉ ድርጅታች በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በልጅ እያሱ ኮር በ24ኛ ክፍለ ጦር እየተሰራልን ያለው ልማት ከልብ እናመሰግናለን ሲሉ ደስታቸዉን ገልፀዋል። እዉነትም የአማራ ህዝብ ልማት ሳይሆን ከነ ጭራሹም ከገፀ መድር ለማጥፋት የብልፅግናዉ ወንበር አስጠባቂና የስራቱ ተሳታፊ የአብይ ሎሌዎች ካድሪ አማራን ለማጥፍት ከምድር እስከ አየር ሀይል ለማጥፍት ቢያቅድም ቅዥትና ህልም ሁኖ ቀርቶበታል። ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድጎና ተመንድጎ ከህልዉናዉ ትግል ጎን በጎን ለህዝቡ መሰረተ ልማት እያለማ ይገኛል ይህ ትልቅ አቅም እንደደረሰ የሚያሳይ አንዱ የትግሉ ዉጤት ማሳያ ነዉ:: የልማት ስራዉ ቀጣይም በተሻለ ሁኔታ ታቅዶበትና  ወደ ፊትም ፋኖ በሚስተዳድራቸዉ ቀበሌና ወረዳዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 26/2018 ዓ.ም

ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚዉል የመንገድ ስራም እየሰራ ይገኛል! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ከህልዉና ትግሉ ጎን ለጎ
+2
ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚዉል የመንገድ ስራም እየሰራ ይገኛል! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር  ከህልዉና ትግሉ ጎን ለጎን ለአካባቢዉ ማህበረሰብ  የልማት ሰራዎችን እያከነወነ የገኛል። ህዝቡም ፋኖ እየሰጠዉ ላለዉ አገልግሎትና የልማት የምንገድ ጠረጋ ጎን በጎን አብሮ እያገዘና በልማት ስራዉ እጅግ በጣም ደስተኛ ሁነዉ የበኩላቸዉን አስተዋፆ እያደረጉ ይገኛሉ። የአማራ ህዝብ መሰረተ ልማት እንዳያለማ መንገድ መብራት ዉሃ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች እንዳያገኝ ተደርጓል:: አለፍ ሲል ለአማራ ህዝብ ልማት ሰይሆን መጨፍጨፍያ ድሮን የሩሲያ ይሻላን ወይስ የቱርክ እያለ  መገደያችን እየገዛ ባለበት ወቅት በኛዉ ድርጅታች በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በልጅ እያሱ ኮር በ24ኛ ክፍለ ጦር እየተሰራልን ያለው ልማት ከልብ እናመሰግናለን ሲሉ ደስታቸዉን ገልፀዋል። ©በአፋብን  ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ! የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24

የካቲት ሃያ ስድስት (26) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ (1970) ዓመተምህረት‼️ #ዝክረ_ታሪክ ከአርባ ስምንት (48) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!! ከዛሬ አርባ ስምንት (48) ዓመታት በፊት የሶማሊያ ጦር በምስራቅ በኩል ሰባት መቶ ኪሎ ሜትር በደቡብ በኩል ደግሞ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማባረር #ካራማራ_ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለበ። ቀደምት አባቶቻችን ለኛ እና ለኢትዮጵያ ነፃነት እና ክብር ሲሉ ለማመን የሚከብዱ ከባባድ ተጋድሎዎችን አድርገው ነፃ አገር ለኛ ለተተኪው ትውልዶች አውረሰውናል እኛ ተተኪ ትውልዶች ግን ያንን ታሪክ ማወቅ አልፈለግንም ይባስ ብለን በሽብር ቡድኑ የኢህዴግና የብልፅግና አገዛዝ በብሔርና በሃይማኖት ተከፍፋለን አገር ለማፍረስ እንዲሁም ሀገር ለማዳን በሚል በተለያዩ ጎራዎች ተከፍለን ታጥቀን እየሰራን ነው። የሰማዕታቱ መስዋትነት ባከነ የካራማራ ድልም የዚህ አሳፋሪ እጣ ፋንታ አንዱ አካል ሆነ፡፡ ክብር እና ሞገስ ለዚህ ድል መሰዋት ለሆኑ ጀግኖች አባቶቻችን ይሁን!! #የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️ #ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️ 26/ዐ6/2018 ዓ.ም

የአረመኔው አብይ ሰራዊት ስብጥር ከአልኮል መጠጥ በስካር ላይ ከነበሩ አምስት ወንድማማቾች ፣ ከሆቴል ዕቃ አጣቢ የነበረ ፣ የሞተር አሽከርካሪ የነበረ ከመንገድ እያፈሰ ያመጣቸው ናቸው። ፋኖ ሁሉንም ከያዙት መሳሪያና ተተኳሽ ጋር በጃዊ ኩምብር ማርኳቸዋል። እነሆ ከምርኮኞች አንደበት👇 ©ብርሃኑ ቻሌ ደመላሽ

ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ) ዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ የዓብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትን መተውታል። የደጃዝማች 4ኛ ኮር የዘራይ ክፍለ ጦር ሸጋው ብርጌድ በዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ ይ
ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)       ዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ የዓብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትን መተውታል። የደጃዝማች 4ኛ ኮር የዘራይ ክፍለ ጦር ሸጋው ብርጌድ በዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ ይካቲት 26/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ እቅድ የዓብይ አህመድ እና የብአዴን ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ወስዷል። በዚህ ግንባር የተገኘ ድል 🔸21 ጠላት ተደምስሷል። 🔸7  እጅ ሰቶ የተማረከ 🔸 16 የተማረከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የተማረከ ሲሆን በልውል ያልተቆጠረ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ተተኳሽም ተማርኳል። በቅርቡ በጀግንነት ጀብድ ፈፅመው በተሰው ህያው ጀግኖቻችን አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ) እና አርበኛ ደመላሽ ስመኝ (አዳኙ ነብር) መግነጢሳዊ መንፈስ ተጋግሎ የቀጠለው ወታደራዊ ዘመቻ ጠላትን ድል በመንሳት እየተቋጨ ይገኛል።        ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)           ተጠናክሮ ይቀጥላል!!          አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ             ህ/ግንኙነት መምሪያ

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የአማራን አርሶ አደር በረሃብና በድህነት የማንበርከክ ሴራ በወግዲ ተጠናክሮ ቀጥሏል! ​የብልፅግናው ፀረ-አማራ ቡድን የአማራን ሕዝብ ትጥቅ አስፈትቼ አምበረክካለሁ በሚል የጀመረው የሴራ ተስፋ አድማሱን አስፍቶ ወደ ዘር ማጥፋት በተጨማሪም ደግሞ ወደ ንብረት ውድመትና ዘረፋ ተሸጋግሯል። በደቡብ ወሎ ወግዲ 05 ቀበሌ (ጡንጊ) በአርሶ አደሩ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የቡድኑን ማንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ​የአቶ ጀማል አህመድ ጥሪት የሆነው ሁለት ወፍጮ ተዘርፎና ወድሟል። የሚገርመው ግፍ ግን እህሉን ከአፈርና ከአሸዋ ጋር መቀላቀላቸው ነው! ይሄ በቀጥታ "ካልራባችሁ አትገዙም" የሚል የአገዛዙ መልዕክት ነው። አንዲት ክበድ ላምና በሬ ሰርቀው መሄዳቸው ሳያንስ፣ ቤታቸውን እንዳልነበረ አድርገውታል! ​በጎረንጅ ቀጠናም ሕዝቡ ራሱን የሚከላከልበትን የግል ንብረቱን 63 መሣሪያዎች ነጥቀዋል። ይህ በግልጽ የታወጀ የዘር ማጥፋት አካል ነው። አርሶ አደሩን ሀብት አልባ በማድረግ የእለት ጉርሱን በማሳጣትና መከላከያ መሣሪያውን በመንጠቅ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ስልታዊ ጥቃት ነው። ​ይህ ግፍ በዝምታ ሊታለፍ አይገባም! ዛሬ በጀማል አህመድ ላይ የደረሰው ነገ በሁላችንም ደጅ መድረሱ አይቀርምና ሁሉም አማራ ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ይከላከል ዘንድ ዛሬም ጊዜው አልረፈደምና ከፋኖ ጋር ይሰለፍ የዘወትር መልክታችን ነው! ሚዲያዎችና ማህበራዊ አንቂዎችም የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት በተደራጀ መንገድ ህዝባችን ብሎም አለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው እያደረጋችሁ እንዳላችሁ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም የህዝባችን መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ እየሰራችሁ ካላችሁት በላቀና በተቀናጀ መንገድ እንድትሰሩ መልክታችንን እናስተላልፋለን!  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 26/2018 ዓ.ም

በአድዋ በዓል መልዕክት ምክንያት የታሰረችው ተማሪ👨‍🎓👨‍🎓 💪💪የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገዛዙን እያንቀጠቀጡት ይገኛሉ!! ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (የኦሮሚያ ምድር ዩኒቨርሲቲዎች ለአማራ ተማሪዎች መርዝ ናቸዉ'ና እያንዳንዱ ለሚፈፀመዉ ነገር ቀድመን ድምፅ እንሁን!! ​ረድኤት የ4ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ ናት ለአድዋ በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለቷ ብቻ ታስራለች። ​ ረድኤት የተባለችው ይህች ተማሪ በክፍል ተማሪዎች የጋራ መገናኛ ግሩፕ (Class Group) ላይ የአድዋን በዓል አስመልክቶ "እንኳን አደረሳችሁ" የሚል መልዕክት ስታጋራ። ከዚህ ቀደም በብሔር ምክንያት ከክፍል ተማሪዎች ጋር አለመግባባቶች እንደነበሩ የሚጠቀስ ሲሆን፣ ይህንኑ መልዕክት መነሻ በማድረግ አንዳንድ የክፍሏ ተማሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት አሳልፈው ሰጥተዋታል። ​ፖሊስ ተማሪዋን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ስልኳን በመፈተሽ፣ በውስጡ የአድዋ ጀግኖችን የሚኒሊክን እና የአማራ ፈርጦችን  ፎቶግራፎች በማግኘቱ ነገሩን ከፋኖ ጋር በማገናኘት አስሯታል። ​⚠️ ​የእስር ሁኔታ፡ በአሁኑ ሰዓት ብቻዋን ታስራ የምትገኝ ሲሆን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸሙባት መሆኑ ተሰምቷል። ​የምግብ እገዳ፡ ተማሪዎች ምግብ ሊወስዱላት ቢሞክሩም፣ የፖሊስ አባላት "ምግብ አያስፈልጋትም" በማለት ምግቡን እየመለሱ ነዉ። ነግ በእኔ ነዉ'ና መላዉ የኢትዮጵያ ተማሪ እና ማህበረሰብ መረጃዉን ሼር በማድረግ  ይተባበረን። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች።