ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 534
Підписники
+24824 години
+5847 днів
+97230 днів
Архів дописів
♦️አርበኛ ልብአርግ ሙላትን አሳዶ ለመያዝና ለመደምሰስ በሁለት አቅጣጫ የመጣው ጠላት እርምጃ ተወሰደበት።
ዛሬ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ሰብሳቢ ልብ አርግ ሙላትንና የተወሰኑ አመራሮችን እንዲሁም የድል በር ብርጌድ አባላትን ለመደምሰስ ከማክሰኝትና ከደጎማ ንቅናቄ ያደረገው የብልጽግና ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጎ ተመልሷል።
በድንዛዝ ከፍተኛ ቦታዎች ያልጠበቀው ጥቃት የገጠመው ጠላት እግሩ ወዳመራው ከፈመርጠጡም በላይ ይዞት የሄደው ሰራዊቱ በየ አቅጣጫው መበተኑም ታውቋል።
♦️ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ትግል ውስጥ በመታገል ላይ በሚገኙ የፋኖ ቤተሰቦች ላይ ብልጽግና የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ታውቋል።
የድል በር ብርጌድ አዛዥ ሙሌ ወርቁ ወንድም ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።
የለምባ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ባየ ቀናው እስከ ህፃን ልጁ በብልጽግና አረመኔ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነዋል።
በአማራ የህልውና ትግል ውስጥ በመሳተፍና በመታገል ላይ የሚገኙ አማራዊያንና ቤተሰቦቻቸው ላይ በሁሉም የአማራ አካባቢዎችና በመላው ኢትዮጵያ የበቀል በትር በተደጋጋሚ መፈጸሙን በተለያዩ የዜና እወጃችን መዘገባችን ይታወሳል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አብነት ሞላ
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
@Baye Desta Per
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በአንድ ኦባማ የጭነት ተሽከርካሪ የነበሩ 23 የአድማ ብተና አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል።
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
=======================================
አነፍናፊ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በጎዛምን ወረዳ ቸርተከል ንዑስ ከተማ ወረራ ፈፅሞ በተመለሰ የጠላት ኃይል ላይ በደብረ ማርቆስ ከተማ ንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ጤና ጣቢያ አካባቢ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በአንድ ኦባማ ተሽከርካሪ ላይ የተጫኑ አየድማ ብተና አባላት ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል።
ታልጋ ቁጥር 22472 ኮድ (3) ባለቤትነቷ የግል የሆነችውን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ኦባማ በማስገደድ ከቸርተከል ወደ ደብረማርቆስ ከተማ እየገቡ ባለበት በንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ቀበሌ ጤና ጣቢያው አካባቢ ሲደርሱ በ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደረሰባቸው የቦምብ ጥቃት ሀለት ጋንታ መሪዎችን ጨምሮ 23 አድማ ብተና አባላት መሞታቸው ተውቋል።
የጠላትን መውጫ መግቢያ በቦምብ አጥረው እያጋዩት የሚገኙት የ206ኛ ኮር አዳኞች በተከታታይ በፈፁሙት የተሳካ ኦፕሬሽን ጠላት የሚመካባቸውን ካድሪዎችና ወታደራዊ አመራሮች እያስወገዱ ሲሆን በተሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ የብልጽግና ነዶዎች በቦምብ ተቃጥለዋል።
የጠላትን ካድሪ ባናጠለ መልኩ ከመደምሰስ ባለፈ በአይነቱ ለየት ያለ ጥቃት መክፈት የሚያስችል አቅም መገንባቱን እንዲሁ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በአራት አቅጣጫ የመጣው የብልፅግና ጦር በክንደ ነበልባሎቹ ክፉኛ ተመታ!
መጋቢት:-22/2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ክንፍ የሆነውን ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በአሁኑ 30ኛ ክፍለ ጦርን አፍናለሁ ብሎ በአራት አቅጣጫ የመጣውን የብልፅግና ጦር በመጣበት አራት አቅጣጫ በክንደ ነበልባሎቹ ተገርፎ ተመልሷል።
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ላስታ ወረዳ መነሻውን ከብልባላ ከተማ ወደ ይምርሐ አቅጣጫ ያደረገው የደቡብ ዕዝ 204ኛ ኮር 38ኛ ክፍለ ጦር የጁላ ሰራዊት በጠረዛ ወርቅ አምባ ግንባር፣ ዳቢያ ግንባር፣ አራትያ ተራራ ግንባር እና ገርባጤ ግንባር በአራት መጋቢት 20/2018 ዓ/ም ጧት 2:00 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በፈጀ አውደ ውጊያ የጠላት ኃይል ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዷል።
በዚህ አውደ ውጊያ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ መከላከያ በጥቁር አማራ ሚሊሻዎች እየተመራ አሳዶ ለመያዝ፣ ከበባ ለማድረግና ቀጠናውን ለማስለቀቅ ብሎ አስቦ ቢመጣም ፋኖዎቹ ጠላትን ስቦ በማስገባት 16ቱን በመደምሰስና 22ቱን በማቁሰል ጠላት ወደነበረበት ቀበሮ ጉድጓድ ምሽጉ ብልባላ ተራሮች አፍሮ እንዲመለስ ተደርጓል።
በተያያዘ መረጃ ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር የአሁኑ 19ኛ ክፍለ ጦር አይና ከተማ ላይ በአይና ገብርኤል አቅጣጫ በመግባት መጋቢት 21/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 እስከ ሌሊት 6:00 ሰዓት የተሳካ የከተማ ኦፕሬሽን በመስራት 12 በመደምሰስና 15ቱን በማቁሰል 10 ጥቁር ክላሽ በመማረክ የጠላትን ኃይል አዛብተው ወጥተዋል።
በሌላ አቅጣጫ ከአይና ከተማ ወደ ቋሮ ጠላት በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ፋኖዎቹ ሶፋ ገብርኤል ከሚባል ቦታ ቆረጣ በመግባት ጠላትን ሲያርበደብዱት ውለው 24 የጠላት እስከሬን እና 18 ቁስለኛውን ታቅፎ ወደ መጣበት እንዲመለስ አድርገውታል።
እንዲሁም የአገዛዙ ብልፅግና የውስጥ ተላላኪ ባንዳዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ዋሉ!
የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር በአሁኑ 14ኛ ክፍለ ጦርን አሳድዳለሁ ብሎ የመጣውን የብልፅግና ጦር በመመከትና በማጥቃት በአፀፋዊ ምላሽ ለብልፅግና ያደሩ ተላላኪ ባንዳዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።
መነሻውን ከአስከተማ በጨረቃ በር ጥቅር ግምባር፣ ከላልኪው በጭፍሮ ወይሎ ግምባርና ኩራዝባይ ግምባር ወደ ዘውማርያም የተጓዘውን የጠላት ኃይል መጋቢት 21/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመመከትና በማጥቃት በጠላት ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ጠላትን ወደ መጣበት ሲመልሱት ላልኪው ከተማ ላይ በቆረጣ በመግባት የአገዛዙ ተላላኪ ብልፅግና ባንዳዎችን ስቦ በማስወጣት ፋኖዎቹ የተሳካ ኦፕሬሽን ሰርተዋል።
በአውደ ውጊያው ከተቀዳጁት ድል ጎን ለጎን በተደረገው ውጤታማ ኦፕሬሽን የ2018 ዓመተ ምህረትን የብልፅግና የጨረባ ምርጫን ለማስፈፀም ደፋ ቀና የሚሉ እንዲሁም የውስጥ ተላላኪ ስድስት ጥቁር አማራ ባንዳዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ከእንደዚህ አይነት የተላላኪነትና የባንዳነት ተግባር እንዲቆጠብ ሲሉ የክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች አሳስበዋል።
በመጨረሻም ሦስቱ ክፍለ ጦሮች 14ኛ ክፍለ ጦር፣19ኛ ክፍለ ጦርና 30ኛ ክፍለ ጦር ያደረጉት የተሳካ ኦፕሬሽንና መናበብ የጠላትን የኃይል አሰላለፍ ያዛባና የወገን ግዳጅ የመፈፀም አቅም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የታየበት ሲሆን ጀግኖች አሁንም ለአማራ ህዝብ ህልውና ሲሉ በወሎ ተራሮች ስር እየተዋደቁ መሆኑና አሁንም ትግላችን እስከሚጠራ አንዳንድ የብልፅግና እንክርዳዶች ስለሚኖሩ እንክርዳዱ ከስንዴው እስከሚለይ እና በግለሰቦች የተንጠለጠለ የአማራ ትግል ባለመኖሩ ትግላችን እስከምፅአት ነው ሲሉ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ምክትል ሰብሳቢ አርበኛ ፋኖ ታዘበው ሻምበል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።
ድላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት:-22/2018 ዓ/ም
⚠️ እስከመቼ በዚህ መንገድ እንጓዛለን?
የትግሉ ጥረትና መስዋዕትነት በፕሮፖጋንዳ ሽንፈት እንዳይቀለበስ የሚከተሉት ነጥቦች በአስቸኳይ ማረም ይገባል::
* ከመክዳት በፊት መከላከል፦ አባላት ለጠላት እጅ ከመስጠታቸው በፊት የውስጥ ችግሮችን በውይይት መፍታትና ክትትል ማድረግ ሲገባ ፤ ካመለጡ በኋላ ስም ማጥፋት ትርጉም የለውም፤ የክህደት መንገዱን ቀድሞ መዝጋት ብልህነት ነው።
* የመረጃ ደህንነት፦ ከዳተኞች ይዘውት የሚሄዱት መረጃ በትግሉ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። አመራሩ መረጃን የመከፋፈልና (Compartmentalization) የመጠበቅ ስራ ላይ ሊጠነክር ይገባል።
* ተጠያቂነት፦ ወንጀል የሰሩ አባላት አምልጠው ለጠላት ፕሮፖጋንዳ ግብዓት ከመሆናቸው በፊት በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ነገም ወንጀል ሰርቶ ብልፅግናን እንደማምለጫ ሊቆጥር የተዘጋጀ እልፍ ፋኖ ይኖራል::
* የውስጥ ሰላም፦ ፋኖ የጠላትን ሰራዊት አስከድቶ ወደ ራሱ ማምጣት ሲገባው፣ የራሱ አባላት ወደ ጠላት እንዲሄዱ ምክንያት መሆን የለበትም። በደረጃው ያሉ ቅሬታዎችና ልዩነቶች በንግግር መፍታት ነገ ሃገረ መንግሥት እገነባለሁ ለሚል ኃይል ልምምድም እንዲሁንም ለሚጠብቀው ህዝብም ማሳያ ይሆነዋልና።
እናም እስከመቼ ስም በማጥፋት እንቀጥላለን:: ትግሉ ከስሜትና ከጅምላ ፍረጃ ወጥቶ በስልትና በስነ-ልቦና የበላይነት ሊመራ ይገባል!!
ድል ለአማራ ህዝብ!
የስልጠና ማስታወቂያ ቀን:22/7/18-01/8/18 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የዳ/ቴድሮስ 5ኛ ኮር አካል የሆነው #መብረቅ ክፍለ-ጦር በተለያዩ ተቋማት የነበሩ ምልስ ወታደሮችን የታሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ መደበኛ ሰራዊቱ መቀላቀል ይፈልጋል
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ የምዝገባ ቀን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ባሉ የምዝገባ ቀናት ተገኝታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።
1 የተሟለ ተክለሰውነት ያለው ያላት ተንቀሳቅሶ መስራት የሚችል
2 እድሜ ከመሰረታዊ ወታደር እስከ መስመራዊ መኮንን ከ40 አመት በታች የሆነ/ች
3 ከሻለቃ በላይ ማረግ ያለው ያላት እድሜ ከ50-60
4 ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ/ች
5 በተቋም መመሪያና ደንብ ተገዥ የሆነ/ች
6ህዝብን ለማገልገልና ለመታገል ዝግጁ የሆነ/ች
7 የስርዓቱን ጨቋኝነት የተረዳ/ች
8 በማህበረሰቡ ዘንድ የተመሰገነ/ች
9 በምንም አይነት ወንጀል ውስጥ ያልተሳተፈ/ች
የአማራ ህዝብ የህሉና ተጋድሎ በአንድ ተቋም በአንድ መሪ እየተመራ በድል ጎዳና ላይ በሚገኝበትና የአሸባሪው ብልፅግና ስርዓት በመውደቅ አፋፍ ላይ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የትግሉ አካል በመሆን የታሪኩ ባለቤት እንሁን !
#ህሉናችን በተባበረ ክንዳችን 💪
#ድል ለተገፋው ህዝባችን 💪
#ክብር ምስጋና ለትግሉ ሰማዕታት 🙏
በድል ግስጋሴ ወደፊት እየተራመደ ያለው 106ኛ ኮር በዳውንት ወረዳ ታላቅ ድል ተቀዳጀ::
አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ በ106ኛ ኮር ቃኝ እና የ31ኛ ክፍለ ጦር ሻለቃዎች መጋቢት 22/2018 ዓ/ም በዳውንት ወረዳ የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲደረግ፤አንድ መኪና ተመቶ ተገልብጧል!! የኮሩ ቃኝና የ31ኛ ክፍለ ጦር የተለያዩ ሻለቃዎች በጥምረት የጥላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲደረግ በርካቶች ከመከላከያ ጥርናፌ እየወጡ ይገኛሉ!!
በ02 ቀበሌ የጎራዳ፣ጡቂያ (02) ቀበሌ እና የቅጠል(011) ቀበሌ የፋሽስቱ ሰራዊት ከ17 በላይ ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ፤በ011 (የቅጠል) ቀበሌ መከላከያን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ባስ ላይ ታርጌት ተደርጎ ተመቶ መኪናው የተገለበጠ ሲሆን በውል ቁጥሩ ያልታወቀ የጥላት ሰራዊት ጉዳት ማድረስ ሲቻል በሌሎች የጥላት ሰራዊት ላይ ደግሞ ከኋላ ኪሳቸው የፋኖ ቀለሀ ተችሯቸዋል።
ጣረሞቱን እያሳለፈ ያለው የስርዓቱ ተከፋይ ሰራዊት በፋኖዎች አፈሙዝ መውጫ መግቢያ በሩ ተዘግቶበት በየቀኑ በፍርሀት ጎዳና ሲሸረደድ ተራ በተራ እየተቀነደሸ በመገኘቱ የተነሳ፤በዚህ ውጊያ ከሰባት በላይ የመከላከያ ሰራዊት ፈርሰዋል። ለአብይ ስርዓት አንዋጋም እያሉ ወደ ፋኖ ጎዳና የሚጎርፉት ቁጥራቸው ከቀን ቀን እየጨመረ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ መምሪያ ሀላፊ!
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
➡️አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በርካታ የጠላትን ሀይል ደመሰሰ!!
____1ኛ
በትናንትናው ዕለት በቀን 21/07/2018 ጠላት ከፈረስ ቤት ከተማ መነሻውን በማድረግ ወደ ዳማ ማርቆስ እንቅስቃሴ ቢያደርግም እሳት በሚተፉት ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የሻለቃ -2 አባላት ከጥዋቱ 1:00 ጀምሮ በሦስት ቦታወች ላይ ማለትም ሁላሳይ ፤አገሜ ዮሐንስ እና ቴሌው አፋፍ ወጊያ የተጀመረ ሲሆን እስከ ምሽቱ 1 ስዓት የቆየ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ነበር በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት ከነፍስ ወከፍ እስከ ዙ-23 የተጠቀመ ቢሆንም ከሞት እና ምርኮ ማዳን አልቻለም በዚህ አውደ ውጊያ ሁለት የጠላት ኃይል በክንደ ነበልባሎቹ የተማረከ ሲሆን በርካታ የጠላት ኃይል ሙት እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሻለቃ -5 ዝቋላ በተባለ ቦታ ውጊያ የተከፈተ ሲሆን በዚህ አውደ ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል ሙት እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል ።
በትናንትናው ውሎ በ99ኛ ክ/ጦር የተማረከ
1ኛ ሁለት የጠላት አባላት
2ኛ 6 ክላሽንኮቭ
3ኛ በርካታ የክላሽ ተተኳሽ እና የብሬን ተተኳሽ መማረክ ተችሏል።
__2ኛ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ወራሪ ሃይል ላይ በትናትናው ዕለት መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ባደረገው ከባድ ትንቅንቅ ብዛት ያለው የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተቻለ፡፡
ጠላት መነሻውን ከዝንድብ በማድረግ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የ77ተኛ ክፍለጦር አናብስቶች ሻለቃ 2 እና ቃኝና መሀንዲስ በጂጋና በማክሰኚን ከተማ መካከል ልዩ ቦታዋ ሳቅ በሳቅ በተባለች ቦታ ላይ የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት በአንድነት ባደረጉት ተጋድሎ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደመጣበት አሯሩጠዉ መልሰውታል፡፡
የጠላትን እንቅስቃሴ ቀድመው የተረዱት ነበልባሎች 2ኛ ሻለቃና ቃኝና መሀንዲስ ገዢ ቦታ በመያዝ በፈፀሙት ጥቃት ሙትና ቁስለኛው ያደረገ ሲሆን ከየጎሬው ሲለቃቅም ያደረው የአገዛዙ ሰራዊት ከ15 በላይ ሙት እና በርካታ ቁስለኛ በሲኖ ተሽከርካሪ በመጫን ወደ መጣበት ተመልሷል፡፡
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 22/07/2018 ዓ.ም
በአፋብን ምኒሊክ ዕዝ እና በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የጥምረት ውጊያ በበትላንትናው ዕለት በጀግናው ሰራዊታችን የተማረኩ የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ምርኮኞች
መገርሳ ቢሄድ ደመቀ ቢካዳ፦
ማስረሻ ቢከዳ፥ፍቅሩ ወዶ ቢገባ፦
ፈንታሁን እጁን ቢሰጥ፥እያሱ ቢኮበልል፦
አብይ አህመድን ከመውደቅ የአማራን ህዝብ ነፃ ከመውጣት ፋኖን ከአሸናፊነት አይከለክለውም።
ባንዳዎች ትላንትም ገብተዋል።ዛሬም እየገቡ ነው።ነገም ይቀጥላሉ።
እንኳን መስዋእትነት ባለበት የትጥቅ ትግል ሰላማዊ ትግል ውስጥም ህዝባቸውን በምስር ወጥ የሸጡ እንደ በለጠ ሞላ እና ጋሻው መርሻ አይነት ፍጡራንን አይተናል።
የአማራን ህዝብ ከአሸናፊነት የሚያግደው ምንም የለም!!!
በአማራነቱ በግፍ እስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ንጋቱ በምርመራ ወቅት ከተፈፀመበት ድብደባ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሕመም ላይ ነው።
በደሴ ከተማ ተወልዶ ያደገው ስንታየሁ ንጋቱ ገብረየስ ባለ ትዳር እና የልጆች አባት ነው።
ጠቅላላ መካኒክና ማሽኖችን መጠገን እና በብየዳ ስራ ተሰማርቶ ራሱንና ቤተሰቦቹን እያስተዳደረ ባለበት ነው በዘረኝነት ልክፍት ያደገው ፀረ አማራው አቢይ አህመድ በሚመራው በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ አማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ለግፍ እስር የተዳረገው ብሎም በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፍትህ ለመሰቃየት የበቃው።
በተጻፈውም ባልተጻፈውም ሕጉ አማራነትን እንደ ወንጀል በመቁጠር በተለይም ከ2015 ጀምሮ በሰፊው የአማራ ሕዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከፍቶ በምድርና በአየር ኃይሉ የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል በአረመኔነት እየፈፀመ ያለው አገዛዝ በፌደራል ማ/ቤቶች እንኳ በሕግ ስም ቢያንስ ከ300 በላይ አማራዎችን ያለፍትህ አግቶ ይገኛል።
ይህ በምርጫ ስም እያጭበረበረና ኮሮጆ እየገለበጠ ዘረኛ የሆነ የአንባገነን አገዛዙን ለማስቀጠል እየተንፈራገጠ የሚገኘው የአቢይ አህመድ የእኩይ ፣ የእብሪትና የድንቁርና ደመ ነፍሳዊ ስርዓት በማንነታቸው የተነሳ ፣ አትግደሉን ፣ አታፈናቅሉን ፣ እንደ ዜጋ እንታይ ፣ እኛም ሀገር እና መንግስት ይኑረን ማለታቸው እንደ ወንጀል እየቆጠረ በርካታ የአማራ ልጆችን ጾታ እና እድሜ ሳይለይ ያለ ፍትህ አግቷቸው ይገኛል ።
ከሞት ከተረፉት ነጻነትና ፍትህ ፈላጊ አማራዎች መካከል አንዱ የሆነው ስንታየሁ ንጋቱ ትናንትን በረሱ ፣ ነገ ሌላ ቀን መሆኑን በማያስተውሱ በአገዛዙ እኩይ የዘኝነትና የመጠፋፋት አላማ አስፈጻሚዎች ብዙ ፈተና አሳልፏል።
በምርመራ ስም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ሜክሲኮ) በጨለማ ክፍል ፣ በአዋሽ አርባ እና በሰመራ ተወስደውና ሲቪሎች ሕጉ በማይፈቅደው በወታደራዊ ካንብ ጭምር መንግስታዊ እገታ ተፈፅሞባቸው አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ረገጣ ከተፈፀመባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መካከል አንደኛው ገፈታ ቀማሽ ፣ ተጠቃሽ ነው።
በከፍተኛ ሕመም ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ንጋቱ በሜክሲኮ በፀረ አማራው ኮማንደር አዱኛ ረጋሳ ቢሮ ክፉኛ ተገርፏል ፤ ብዙ ግፍ ተፈጽሞበታል።
በእነ ስንታየሁና በማይተዋወቁ አባሪዎቹ ላይ "የከሸፈው ሴራ" በሚል የተለመደ እና እጅ እጅ የሚል እርካሽ ፕሮፖጋንዳ የሰራ መሆኑ አይዘነጋም።
ከደረሰበት ድብደባ ጋር በተያያዘ የቀኝ ኩላሊቱ ፌል አድርጓል ፤ የዘር ፍሬው ላይ ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።
አሁን ላይ በቂሊንጦ ፣ በቃሊቲ ፣ በአባ ሳሙኤል ፣ በዝዋይ እና በሌሎች ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ አማራዎች እጣፈንታ እንደሆነው በቤተሰቦቹ ላይ ማስፈራሪያ ፣ ማዋከብ እና ዛቻ ተፈጽሟል ፤ እንዲበተኑም ተደርጓል።
"የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኃላፊዎች ፍርድ ቤቱ በነፃ ቢለቅህ እኛ መንግስት ስለሆንን አፍነን ወስደን እንገልሃለን" ብለው ዝተውበታል።
ማህተቡን በመቁረጥም "አይደለም ይህችን ያረጀች ሐይማኖት ነውና ገና ሁላችሁንም እናጠፋችሃለን" በማለት እንዳስፈራሩትና የነውረኝነትና የጥላቻ ጥግ እንዳሳዩት ለማወቅ ተችሏል።
ስንታየሁ ንጋቱ አሁንም ካለበት የጤንነት ከባድ ችግር አንጻር በቂ እና የተሻለ የሚባል ሕክምና እያገኘ እንዳልሆነ ይናገራል ፤ መፍትሄ በሌለው በተንዛዛ ቀጠሮ ተማሯል።
በግፈኞች የደረሰበትን ጉዳት ተከትሎ ገና ለገና በማስረጃነት እንዳይያዝባቸውና ለምን መረጃ ሰጣችሁ በሚል እንዳይባረሩ የሚሰጉ የሕክምና አካላትም በቂ መረጃ አይሰጡትም።
ስንታየሁን ጨምሮ አያሌ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ እና በሕመም ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ ችግር እየተጠበሱ ያሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ብሎም የተበተኑ ቤተሰቦቻቸው የወገንን ሁሉንአቀፍ ድጋፍ በእጅጉ ይሻሉ።
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ከዘመንና ከትውልድ ጋር የተጣሉ ሆድ አምላኩ ፣ ጨካኝና ዘረኛ ግፍ ፈጻሚዎች ከሞራል ፣ ከሕግ እና ከታሪክ ተወቃሽነትና ተጠያቂነት መቼም አያመልጡ!
ይህ ሞትን ንቆ ለነጻነትና ክብሩ ፣ ለፍትህና ለእኩልነት እንዲሁም ለአብሮነት እየተዋደቀ ያለ ፣ እየተነሳ ያለ ትውልድ ይፋረዳቸዋል ፤ በስራቸው ልክ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል ~ አንጠራጠርም ፤ እየሰጣቸውም ነው!
(አውሎግሶን አንድነት ፣ መጋቢት 21/2018)
+1
የብልፅግና ሰላም አስከባሪ አባል ሁለት መሳሪያ ይዞ 102ኛ ኮርን ተቀላቅሏል ።
መጋቢት 18/2018ዓ.ም
የአብይ አህመድ ሰራዊት ከራሱ ከብልፅግናው ስርዓት ላይ ጀብድ እየፈፀመ አፋብንን እየተቀላቀ ይገኛሉ ። በዛሬው ዕለትም በቀን 22/07/2018ዓ.ም ከመራዊ እና ገርጨጭ ከመሸገው ሀይል ወጥተው 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል ። በስርአቱ ሰላም አስከባሪ ተብሎ የሚጠራው ሀይል አባል የሆ ነው ውዴ ጊዜ የተባለ ከመራዊ እና የ79ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት አባል የሆነው አሳዬ አፋኘ የተባለ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት አባል ከገርጨጭ የወጡ ሲሆን ውዱ ጊዜ ሁሉት መሳሪያ ይዞ 11ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል ።
የጎቤ ክፋለ ጦር ሬጅመንት 3 ጃንሱማ በተሰኘ ልዩ ቦታ በጠላት ላይ በወሰደዉ ማጥቃት የ53ኛ ክፍለ ጦር አሃድ የሆነዉን ጠላት ሙትና ቁስለኛ አደረገ።
ከ18 በላይ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነበትን የዛሬ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ውጊያ ያደረገችው ጎቤ ክ/ጦር ሬጅመንት 3 ብርቱ ተጋድሎ በማድረግ ላይ መሆኗ ሲታወቅ ተቅበዝባዡ አልጌ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ከበላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ና ኮር ጋር እያደረገ ያለው ውጊያ ከሶስት ቀናት በላይ አስቆጥሯል።
ህልውናችን በአርበኝነታችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በእነማይ እና ሸበል በረንታ ድል ተቀዳጄ።
64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
በሳምንት ውስጥ ሶስት ተከታታይ ውጊያወችን ያደረገው፤ ሶስት የጠላት ደፈጣወችን ተሻግሮ 200 ኪሎ ሜትር የተጓዘው በጀግኖች ደም የተገነባው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዛሬም ተዓምር መስራቱን ቀጥሏል።
ከሶስት ቀናት በፊት በሸበል በረንታ የወረደውን የአምባ ገነኑ አብይ አህመድ አገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊትን እስከ ብቸና ያሯሯጠው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በጎጃም ግዙፉ ክፍለ ጦር ነው።
በቁጥር በረካታ ሰራዊት እና የቡድን መሳሪያዎች ያሉት በሰለጠነ ወታደራዊ ኃይል የገነበው የበላይ ትንፋሾች የሚመሩት ግዙፍ ክፍለ ጦር በወገኖቹ ታማቹ አርበኛ ጥላሁን አበጄን መጋቢት 21/2018 ዓ.ም በቁጥቋጥ ቀበሌ ከከበባ በማውጣት ተዓምር ሰርቷል።
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም አርበኛ ጥላሁን አበጀ ከጥቂት አጃቢወቹ ጋር ብቻ በወይንየ እና አካባቢው ቀበሌ ቁጥቋት ጎጥ ባለበት ቦታ በጠላት ከበባ ውስጥ መግባቱ የተነገራቸው የክፍለ ጦሩ ጥበበኛ መሪወች በሰጡት ስምሪት የአይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሰራዊት በእነማይ ሰቀላ ገብሬል እና በሸበል በረንታ ወይንየ፣ ቁጥቋጥ፣ እነቡክሪት ጎጥ፣ ወርጎ እና አካባቢው ቀበሌ የጡጭ ጎጥ፣ የዕዱውኃ ኪዳነ ምህርት የጠላት ምሽግ ላይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ከባድ ውጊያ አድርገዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ አረመ*ኔዊ ሰራዊ ከፍተኛ ኪሳር የገጠመው ሲሆን በውጌው የተገኙ ድሎች:-
🕳 ከ40 በላይ የአገዛዙ አስከሬን ከሰቀላ ቀበሌ በሁለት አይሱዙ ጭኖ ወደ ብቸና ከተማ የገባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በድብቅ በጨለማ ወደ ሚቀብርበት ቦታ ለማጓጓዝ በዝግጅት ላይ ይገኛል። በሁለቱም ቀጠና በተደረገው ውጊያ ከ60 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ተደምስሰዋል።
🕳በተደረገው አውደ ውጊያ ቁጥሩን ለጊዜው ማወቅ ያልቻልነው ነገ ይፋ የምናደረገው የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ ብተና ፣ሚሊሻ አባላት ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጦል።
የአማራን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት አጀንዳ ቀረፆ እየሰራ የሚገኘው አገዛዝ በአይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ከባድ ብትር የገጠመው ዛሬም በእነማይ ማህበረ ብርሃን ቀበሌ መድፍ በመጥመድ የተኮሳቸው የመድፍ ሀሩሩ በንፁሃን ህዝባችን ላይ ጉዳት አድርሷል።
ክፍለ ጦሩ በአደረገው አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎችን ተጨማሪ የውጊያ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናልደ
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሕዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
የአፋብን ሁለቱ ዕዞች ምኒልክ ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሰራዊት በመደምሰስና በመማረክ እንዲሁም የነፍስ ወከፍ መሳርያ እና ተተኳሽ በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት በነበረው ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ የተደረገ እንዲሁም የተማረከ ሲሆን በምኒልክ ዕዝ በኩል 104ኛ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ከ106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለ ጦር እና 105ኛ ኮር አሃዶችም የተሳተፉ ሲሆን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት የመሃመድ ቢሆነኝ ኮር እና አፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃድ አባላቶች በጥምረት በመዋጋት ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
በዚህ ታላቅ ድል በተመዘገበበት ተጋድሎ 15 የጠላት ሰራዊት የተማረከ ሲሆን 25 ክላሽ፣ ከ1200 በላይ የድሽቃ ተተኳሽ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የብሬን እና የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም ወታደራዊ ቁሳቁስ ከጠላት ተማርኳል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
