uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 444
Підписники
+1624 години
+487 днів
+1 15030 днів
Архів дописів
🔥#ሰበር_ዜና‼️ በመልሶ ማጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላትን ሚካኤል ደብር ከተማ መቆጣጠር ተችሏል።      ዛሬ መስከረም 25/2018 ዓ.ም የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ከባህር ዳር ጀምሮ ሃይሉን በማሰባሰብ አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ትላንት የደረሰ ሲሆን አዲስ ዘመን ላይ ተጨማሪ ሃይልን በማከል በ2 አቅጣጫ ማለትም በደሪጣ አስታ አቅጣጫና ከአዲስ ዘመን አርኖ ጋረኖ በጅራት አቅጣጫ ሌሊቱን ሲጓዝ አድሮ በጠዋቱ ሚካኤል ደብር ሊደርስ ችሏል።   ሌላው የውጊያ ቀጠና ደግሞ ከአዘዞ ከጠዳና ከማክሰኝት ኃይሉን ለቃቅሞ ደጎማ ላይ በመድረስ መነሻውን ደጎማ በማድረግ ቀጥታ በአዲስ ዘመን ከመጣው የጠላት ኃይል ጋር በመናበብ የወገንን ኃይል መደምሰስ ነበር እቅዱ፤ ያልጠበቀው ነገር የገጠመው ጠላት በ3ቱም የውጊያ ቀጠናዎች ከፍተኛ ምትን አስተናግዷል።      ከደጎማ ወደ ሚካኤል ደብር የመጣውን የጠላት ኃይል መብረቅ ክ/ጦር በድሽቃ በታገዘ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ችለዋል።     ከአዲስ ዘመን በአስታ አቅጣጫ የመጣውን ጠላት ደግሞ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦርና  የጎ/በጋሻው ክ/ጦር አባላት በሚገባው ቋንቋ አናዘውታል።      ከአዲስ ዘመን አርኖ ጋርኖ ጅራት አቅጣጫ ፋናየ ውቤ ክ/ጦርና የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር የተወሰኑ አሃዶች በመናበብ ጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አድርሰዋል።       ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በ3ቱም የውጊያ ቀጠናዎች የተመዘገቡ ድሎች        ** 28 የጠላት ኃይል የሞተ        ** 35ቱ ደግሞ የቆሰሉ ሲሆን በአዲስ ዘመን ጤና ጣቢያና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ፣ በእንፍራዝ ጤና ጣቢያ ፣ በማክሰኝት ጤና ጣቢያና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ከመሆኑም በላይ ክፋኛ የቆሰሉት ደግሞ ወደ ጎንደር ለከፍተኛ ህክምና በሪፈር እንደተላኩ ለማወቅ ተቸሏል።    በበቀል የሰከረው ጠላት በሚካኤል ደብርና በአካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ማንገላታትን የፈፀመ ሲሆን የህዝብን ሃብትና ንብረትንም ዘርፋል።     ከዚህ በተጨማሪም ንጹሃን አርሶ አደሮችን ጠመንጃ አላችሁ አምጡ ብለው የጠየቁ ሲሆን አርሶ አደሮችም ጠመንጃ የለንም በማለታቸው ተረሽነዋል።     **  3  አርሶ አደሮች ዋሻ ማርያም ቀበሌ ላይ     **  2  ደግሞ የሚካኤል ደብር ቀበሌ ነዋሪዎች ናቸው                  የተረሸኑት ።   ** 1 ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲያገለግል የነበረው ዲያቆንን ክፋኛ በማቁሰልና   **  1 ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፈጣሪው ጋር ተገናኝቶ በጸሎት ለይ የነበረን ግለሰብም አቁስለዋል።                ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን ኃላፊ አብነት ሞላ         25/ዐ1/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ነፃ ባወጣቸው የሰሜን  ወሎ ዞን መካከል በሀብሩ ወረዳ ኸሚገኙ ከተሞች መካከል በጊራና  ከተማ  ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡ ዛሬ በዕለተ ማክሰኞ በቀን 25/01/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ ጋራና ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች 1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?   * ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ   * ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ   * የትግሉ ተግዳሮቶች    * የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ  2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ   * በወታደራዊ ቁመና   * በፖለቲካ ተቀባይነት   * የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም 3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ   * የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት   * የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት   * ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ 4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?  በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡ በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡ በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት  ፋኖ መሀመድ ሞገስ መስከረም 25/2018 ዓ.ም

የአገዛዙ የአብይ አህመድ በአማራ ላይ ያሰበውን ሲራ ሚስጥር ሲጋለጥ እናመሰግናለን አምሓራዊት ጀግና ነሽ ሽር አድርጉ በፈጣሪ ሙሉ አማራ ይስማው ይህን ሸርና ጆይን የማያደርግ አማራ ባንዳ ነው ሙስሊም ክርሰቲያን በሚኖርባት አማራ ፋኖን መውቀስ የመጨረሻው የመፍራት አላም ነው ሽር ሽር ሽር ሸር ሸር አለቀ አምሓራዊት ያአፂዎች እናመሰግናለን

ከግንባር የተላከ መረጃ ! ፈንታው ሙሀቤ እና ብርሌው ከብአዴን ጋር ድርድራቸውም ጨርሰው ሊገቡ ነው። ኮሮኔሉ የአድማ ብተና ኃላፊ ሊሆን ጨርሰዋል ከስሩ የነበሩ የተወሰኑ አመራሮችን ቦታ ተመቻችቶላቹሀ
ከግንባር የተላከ መረጃ ! ፈንታው ሙሀቤ እና ብርሌው ከብአዴን ጋር ድርድራቸውም ጨርሰው ሊገቡ ነው። ኮሮኔሉ የአድማ ብተና ኃላፊ ሊሆን ጨርሰዋል ከስሩ የነበሩ የተወሰኑ አመራሮችን ቦታ ተመቻችቶላቹሀል ብሎ ቢያወያያቸውም እኛ ለነፃነት እንጅ ለስልጣን አልወጣንም በማለት ሁሉም በሚባል ደረጃ ከእሱ በመውጣት ሌላ ቀጠና ገብተዋል። አሁን እሱ ጋር የቀሩት ከአምሳ እንደማይበልጡ እዛው ያለ ልጅ መረጃ ልኮልኛል !! በመሆኑም አንደራደርም በማለት ከእሱ የወጡትን በጠላት ለማስከበብ እንቅስቃሴውን ስለጀመረ በአካባቢው ያላችሁ የምኒልክ ዕዝ ሰራዊት ተገቢውን ከለላ በመፈፀም እንድትተባበሯቸው ስንል እናሳስባለን!🙏

"ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ጥንቃቄ" ከቡሬ ወደ አለፋ አቅጣጫ በዚህ ሰዓት የጠላት ሰራዊት በበቆሎ ውስጥ መንደር ለመንደር እና ቀጥታ አስፖልቱን ይዞ እየመጣ ይገኛል። ያው ለጥንቃቄ እና እንዳንዘናጋ ነው እንጂ ቀን አለቀን እየመጣ መረጃው ገና ከካንፕ ሲነሱ እንደሚደርሳቹ ጠፋቶን አይደለም !🙏 ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

👉 በ3 አቅጣጫ አሰፍስሶ በመጣው የጠላት ኃይል    ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ተወሰደበት ። ዛሬ መስከረም 25/2018 ዓ.ም ጠላት ከባህር ዳር ጀምሮ ያሰባሰበውን ግብስብስ ሰራዊቱን ሚካሌል ደብር ለመግባት ሙሉ አዳሩን ተገዞ በዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ላይ ውጊያ ከፍቷል። ዉጊያውን በ3 አቅጣጫ የከፈተ ሲሆን በ3ቱም አቅጣጫ ከፍተኛ ውጊያን አስተናግዷል።    ጠላት ካሰማራባቸው የውጊያ ቀጠናዎች በደጎማ አቅጣጫ ፣ ከአዲስ ዘመን  አስታና ከአዲስ ዘመን አርኖ ጋርኖ ጅራት አቅጣጫን ተከትሎ ነው የተንቀሳቀሰው።     በሁሉም የውጊያ ቀጠናዎች እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች የተካሄዱ ሲሆን በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይልም ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።            ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!             አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ                       መስከረም 25/ 2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአደረጃጀት ዜና ‼️ የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ‼️ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ ሪፎርም አድርጓል። የቢትወደ
+1
የአደረጃጀት ዜና ‼️ የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ‼️ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ ሪፎርም አድርጓል። የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድን ባለፉት ተከታታይ 6 ወራት ሲያስተዳድሩት የነበሩ አመራሮች ላይ የግማሽ አመት ተቋማዊ የስራ አፈፃፅም ከተገመገመ በኋላ የቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና የጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተሻለ ውጤት ያመጡ፣ ድርጅቱን ያሳድጉታል፤ በተሻለ ደረጃ ያስቀጥሉታል ተብሎ የታመነባቸዉን አካላት ወደ ፊት በማምጣት የአመራር ሽግሽግ ተደርጓል። እናደራጃለን፣አናሰለጥናለን፣እንመክራለን፣እናስተዳድራለን፣እናቅዳለን፣ጠላትን ድባቅ እንመታለን‼️ ፋኖነት አሸናፊነት‼️

ህዝባዊ ውይይቱ እንደቀጠለ ነው!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች የዛምበርሃ ብርጌድ አመራሮች በተገኙበት በደጀን ወረዳ  እናጅማ የዝባ ቀበሌ ህዝባዊ ዉይይት አደረጉ። በውይይቱም የተገኙት የክፍለ ጦር እና የብርጌድ አመራሮች ጦርን ከማንቃት ጎን ለጎን ዛምበረሃ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው ደጀን ወረዳ በሚገኙ ቀበሌወች ላይ በመዘዋወር የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በመፍታት፣ግዚያዊ አሰተዳደሮችን በመገምገም፣አዲስ የህዝብ አሰተዳደሮችን በማዋቀር፣ተከታታይ መድረኮችን በማዘጋጀት፣የቀበሌ የፍትህ አሰጣጥ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን የፍትህ አካላትን በየቀበሌዎች በማዋቀር የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ አሰቀምጠዎል። አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!   ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ ከአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መስከረም 25/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የወሎ ፋኖ ለሀይማኖት አጀንጃ ስለማይመች  ከጎጃም የመጡ ፋኖዎች ናቸዉ ጉዳት ያደረሱት የሚል ነገር ይዛችሁ ብቅ አላችሁ።/ቆሻሾች/ የአማራ ፋኖ ትግል እንደጀመረ  በሶስት ክላሽ ምናምን እየተባለ ከተለመጠበት ወዲህ  እንደተባለዉ ሳይሆን ቀርቶ እየጠነከረ ሲመጣ  አሁን የሚጮሁት ሰዎች  በሙስሊሙ ዘንድ ያላቸዉን ተቀባይነት ተጠቅመዉ እየተናበቡ ነገሩን ሀይማኖታዊ ቅርፅ ለማስያዝ ተንደፋደፉ። ይህንን የጀመሩት ጎንደርና ጎጃም ነበር።በወቅቱ በደንብ ያልተጠና የችኮላ ድራማ ስለነበር  እንዳይሆኑ ሆነ። የሚያሳዝነዉ በዚህ መሀል ለዚህ ስራቸዉ ሲባል ብቻ የሚከፈል ህይወት አለ። ከመንግስት በላይ እነዚህን ሰዎች የምፀየፋቸዉ የአማራ ሙስሊም ለነሱ አጀንዳ ማዳመቂያነት እንጂ  ስለሚጠፋዉ ህይወት ስለሚፈናቀለዉ ሰዉና በነሱ ምክኒያት በማሕበረሰብ መካከል ስለሚኖረዉ  ቁርሾ ቅንጣት ታህል ሀዘኔታም ሀሳብም ስለሌላቸዉ ነዉ። በአጠቃላይ የአማራ ሙስሊም  ለነኝህ ሰዎች ከአጀንዳ ማስፈፀሚያነት በየዘለለ ሚና የለዉም። ለዚህ ቆሻሻ ምግባራቸዉ ስለማይተኙ የአማራ ሙስሊም ክርስቲያንም የአማራ ፋኖ ትግል አካል ብትሆኑም ባትሆኑም  በሀይማኖት ሽፋን የሚደረግን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ መከታተል ይበጃል። የአማራ ፋኖ ትግል የህልዉና ነዉ።ይሄን ትግል  ለማደናቀፍ  የተሰማራ ቄስም ይሁን ሼኽ ወይም ሌላ የሚደርስበትን የግዱን ይቀበላል። ያለቦታችሁ ተገኝታችሁ ለሚደርስባችሁ ሀይማኖቴ አይሰራም። በቦታችሁ ተገኙ!!!  ከጀሚላ ኡመር ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አሳዛኝ ዜና!!! የአገዛዙ ሰራዊት ከጫካ ጭንብል ለባሽ ሚኒሻዎች ጋር በመሆን በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋን ፈፀመ። መስከረም 23/2018 ከጎንደር ገንዳውሀ  ብዛት ያለው የህዝብ ተሽከርካሪ በአገዛዙ ሰራዊት እየታጀበ በጉዞ ላይ እያለ ከመቃ በትንሽ ኪ.ሜ ርቀት ግራር ከምትባል ቦታ የጉዞው ታሪክ ተቀይሮ ሌላ መልክ ሊይዝ ችሏል። በማይታሰብ መልኩ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት የአማራን ህዝብ እንደ ሂሳብ ማወራረጃ ቀብድ መያዣ አድርጎ የጥፋት መንገዶችን እየፈበረከ በሰበባሰበቡ ንፁሀን የአማራውን ህዝብ ለእልቂት እየዳረገ የቆየ መሆኑ ይታዎቃል። በዚሁ ቀን የተፈፀመው ደግሞ በጣም ከባድ የጭካኔ ልክ ድራማቲክ በሆነ መልኩ እዚህ ቦታ ላይ ሲደርስ ከእጀባ የተመለሰ በመምሰል ከፊት ለፊት አካባቢው ላይ ያሰማራቸውን ጭንብል ለባሾችን በማድረግ እና ከኋላ ጨፍጫፊው የአብይ ሰራዊት በመሆን በሁሉም የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ተኩስ በመክፈት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ንፁሀንን ለእልቂትና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ዳርጓል። አካባቢው ላይ ኔት ወርክ በማጥፋት ቁስለኞችን ህክምና ለማድረስም ሆነ መረጃዎችን ለማጠናከር ተግዳሮት የሆነ ሲሆን፣ ለጊዜው ቁጥራቸው የደረሰን ሴቶችንና ህፃናትን ጨምሮ ከ18 በላይ የተሰው ሲሆኑ ከ35 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ማሳሰቢያ: በምዕራብ ጎንደር በመተማ እና አጎራባች ወረዳዎች አማራና ቅማንት ለዘመናት በአብሮነት ተከባብሮና ተጋምዶ በፍቅር የሚኖርን ማህበረሰብ፣አሁን ላይ በተለየ መልኩ የብልፅግናው አገዛዝ በመካከል ጠባጫሪ አጀንዳዎችን ፍፁም ተለዋዋጭ የሆነ ሴራ፣ በስውር ከፍተኛ በጀት በመመደብ የውስጥ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ወክሎ  እየሰራ ይገኛል። ስለሆነም የእርስ በርስ የማህበረሰብ ፍጅትን ለማስፈፀም የሚደረግን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ማህበረሰቡ ነቅቶና አውቆ አካባቢውን እንዲጠብቅና የዚሁ ተግባር አካል የሆኑትን የታጠቁም ሆነ ያልታጠቁ ቅጥረኞችን በአካባቢው ለሚገኝ የፋኖ ሰራዊት መረጃ በመስጠት እንድትተባበሩ ስንል ልባዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።        ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!       አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ  መስከረም 25/2018 ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ስዊድን🙏 All right my family

የጤና ባለሙያው ተረሸነ
+1
የጤና ባለሙያው ተረሸነ

BBC እንደዘገበው👇 ቅዳሜ ጠዋት ነበር። መስከረም 17, 2018 ዓ.ም.። በሰሜን ወሎ ዞን፣ ከወልዲያ ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳንቃ ትንሽ ከተማ በሚገኘው ጤና ጣቢያ፣ ህይወት እንደተለመደው ትቀጥል ነበር። በአንዱ ክፍል፣ ለሁለት ወራት አልጋ ይዞ የታመመ ልጁን ተስፋ ሳይቆርጥ የሚጠይቅ አባት ነበር። በሌላ ክፍል፣ የታመሙ ልጆቻቸውን ዳግም በጤና ለማየት ሌት ተቀን የሚተጉ እናትና አባት ነበሩ። በማዋለጃ ክፍል ደግሞ፣ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት አዲስ ህይወት ወደዚህች ምድር ለማምጣት ምጥ ይዟት ትታገል ነበር። የጤና ባለሙያዎችም፣ የህይወትና የሞት ሽረት በሚደረግባቸው ክፍሎች ውስጥ፣ የሰው ህይወት ለማትረፍ እዚህ እዛ ይሉ ነበር። ከቀኑ 6:00 ሰዓት ሲሆን ግን፣ ይህ ሁሉ ተስፋና ትግል በአንድ ቅጽበት ተለወጠ። ሰማዩ፣ የህይወት ብርሃንን ሳይሆን፣ ሞትን አዘነበ። ያልታወቀ ድሮን፣ በቀጥታ በታካሚዎች ተኝተው በሚታከሙበት "ክፍል 5" ላይ አረፈ። ከዚያ በኋላ የሆነውን፣ ከጥቃቱ የተረፈች አንዲት የጤና ጣቢያው ባልደረባ እንዲህ ታስታውሰዋለች፦ "ምንም ራሴን አላውቅም፤ መሬት ተሰንጥቆ የዋጠን ነው የመሰለን። ከጎኔ የነበሩት ሲወድቁ እኔን እግዚአብሔር ነው የከለለኝ።" ፍንዳታው አካባቢውን አናወጠው። የፈነዳው ጤና ጣቢያ ውስጥ ቤተሰቦቻቸው የነበሩ ሰዎች፣ ልባቸው በፍርሃት ተውጦ ወደ ስፍራው ሲሮጡ ያዩት ትዕይንት ዘግናኝ ነበር። "በደመ-ነፍስ ነበር" ይላል አንዱ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ዘጋቢ ሲናገር። "የደማውም፣ የተመታውም እየተዛዘለ ከፍርስራሹ ሲወጣ ሳይ፣ ያየሁትን ማመን አቅቶኝ ነበር።" በፍርስራሹ ውስጥ የሰው ህይወት ለማትረፍ በተደረገው ግብግብ፣ አራት "ሰላማዊ ሰዎች" ግን ሊተርፉ አልቻሉም። ዓይናቸው እያየ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ታካሚዎቻቸው ሲሞቱ የተመለከቱት የጤና ባለሙያዎች፣ የሟቾቹን ታሪክ በሀዘን ይናገራሉ። ሶስቱ፣ ልጆቻቸውን ሲያስታምሙ የነበሩ ወላጆች ነበሩ። አንደኛዋ እናት፣ ሌላኛው አባት፣ እና ለሁለት ወራት የታመመ ልጁን ሲጠይቅ የነበረው ያ ተስፈኛ አባት። የልጆቻቸውን ህይወት ለማትረፍ መጥተው፣ የራሳቸውን ህይወት አጡ። ነገር ግን ከሁሉ በላይ ልብ የሚሰብረው ታሪክ፣ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ የተፈጸመው ነው። "ማዋለጃ ክፍል ላይ የሞተች እናት አለች" ትላለች የጤና ባለሙያዋ። "አንዷ [ነፍሰ ጡር] ወልዳ ነበር፤ እሷ ግን እየወለደች እያለች ነው የሞተችው።" አዲስ ህይወት ልትሰጥ ስትታገል፣ የራሷ ህይወት ተቀጠፈ። አዋላጅ ነርሷም እጁን ክፉኛ ቆስሎ ነበር። ከሟቾቹ በተጨማሪ፣ የስድስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች ቆሰሉ። ከእነዚህም መካከል ስምንቱ፣ ህይወት ለማትረፍ ሲለፉ የነበሩ የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ነበሩ። አገልጋዮቹ፣ በገዛ ተቋማቸው ውስጥ ተጠቂ ሆኑ። በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ምክንያት መንገድ ተዘግቶ ስለነበር፣ ቁስለኞቹ ለሁለት ቀናት ያህል በስቃይ ሲያሳልፉ ቆይተው፣ ሰኞ ዕለት ወደ ወልዲያ ሆስፒታል ሊወሰዱ ችለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው በጤና ጣቢያው ውስጥ ህክምና ሲያገኙ የነበሩ የቆሰሉ የፋኖ ታጣቂዎችን ሳይሆን አይቀርም። ነገር ግን፣ ያ ዒላማ ሰባት የማይደርሱ ታጣቂዎችን ሲገድል፣ አብሮ የነፍሰ ጡር እናትን፣ የታመሙትን የሚያስታምሙ ወላጆችን እና ህይወት አድን ባለሙያዎችን ህይወት ቀማ። የጤና ጣቢያው ከ"ክፍል 5" እስከ "ክፍል 7" ድረስ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል። ፍርስራሹ፣ በውስጡ ስለነበረው ተስፋና ስለተቀጨው ህልም ምስክር ሆኖ ቆሟል። ዛሬ በሳንቃ ከተማ፣ ህዝቡ በ"ከፍተኛ ፍርሃት" ውስጥ ነው።

ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Saglan Borana, sagaltamman garba» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው። ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል። የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው። የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም። ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመት፣ መውረስና የተሰራ አገር ማፍረስ ብቻ ነው። ባጭሩ እሬቻ በኦሮሞ ብሔርተኞች የተዘረፈ እንጂ ኦሮምኛም የኦሮሞም አይደለም። እሬቻ ኦሮሞ ከባንቱ ወርሶ ኢትዮጵያን ከወረረበት የገዳ ሥርዓት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። እሬቻ የኦሮሞ በዓል/ባሕል ቢሆን ኖሮ የሚከበረው አንጋፋው ኦሮሞ በሰፈረበት በከብት አርቢው ቦረና እንጂ ከቦረና 600 ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቆ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ ገበሬዎች በሚኖሩበት ደብረ ዘይት አይደለም። እሬቻ የሚባልም የአማርኛ እንጂ የኦሮምኛ ቃል የለም። እሬቻ የሚል ስር ያለው የኦሮምኛ ቃል የለም። ባለፈው ዓመት እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን በጻፍሑት ጽሑፍ ላይ አንዱ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ባቀረበው ትችት እሬቻ አሮምኛ ነው፤ “ህርሱ” የሚል ቃል በኦሮምኛ ውስጥ አለ፤ ትርጉሙም መስጠት ማለት ነው፤ ስለዚህ እሬቻ የተወሰደው ከህርሱ ነው የሚል መልስ ቢጤ ጽፎ ነበር። ይህ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ግን የበዓሉ ትርጉም ህርሱ የሚል የኦሮምኛ ቃል ከሆነ በዓሉ ኦሮምኛ ወዳልሆነው ወደ እሬቻ ለምን እንደተቀየረ አልነገረንም። በዓሉ የኦሮሞ ከሆነ፣ ቃሉም ኦሮምኛ ከሆነ በዓሉ ህርሱ ተብሎ ለምን እንደማይከበር፤ በእርሻ የሚተዳደሩ ገበሬዎች የሚያከብሩትን ይህን በዓል ቀዳሚው ኦሮሞና ከብት አርቢው ቦረና ሳያከብረው ገርባው ብቻ ለምን እንደሚያከብረው መልስ የሰጠ ሰው እስካሁን አላየንም። በእውነቱ እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ፤ በዓሉንም ከሁሉ በፊት እሬቻን ሊያከብሩት የሚገባቸው ገርባዎች ሳይሆኑ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ቦረናዎች ነበር። ያልተበረዘው ቀዳሚው ኦሮሞ የሆነው ቦረና የማያከብረው በዓል የኦሮሞ በዓል አይደለም። ቦረና ራሱ እሬቻን የገርባ በዓል ነው የሚለው። እሬቻ የኦሮሞ ባሕል አለመሆኑን ለማወቅ ቃሉ አማርኛ እንጂ ኦሮምኛ አለመሆኑን፤ በዓሉም በእርሻ የሚተዳደሩ እንጂ የከብት አርቢዎች በዓል አለመሆኑን፤ በዓሉ ኦሮሞ የእርሻ ስራን ከመልመዱ ዘመና በፊት ዛሬ በሚከበርበት በደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ በአማሮች ሲከበር የኖረ በዓል መሆኑን፤ ገርባው እንጂ ያልተበረዘውና ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ቃሉንም ሆነ በዓሉን የማያውቀው መሆኑን፤ ይልቁንም እሬቻ ሲከበር የኖረው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ከሚኖርበት 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው። ቦረና የማያከብረውን በዓል ገርባው የኦሮሞ ነው ብሎ ማክበሩ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ገርባው ኦሮሞ አለመሆኑን ብቻ ነው። እሬቻ የኦሮሞ ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ ይሆን ነበር፤ በዓሉም በገርባው ምድር ሳይሆን ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነ ቦረና በሚኖርበት በቦረና ምድር እንጂ ቦረና ከሚኖርበት አካባቢ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ገርባ እንጂ ቦረና በማይኖርበት ምድር በሸዋ ውስጥ አይከበርም ነበር። ይኼው ነው። ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አቻምየለህ ታምሩ እሬቻ ከገዳ የወረራ ሥርዓት ጋር ምን ያገናኘዋል? እሬቻስ የማን በዓል/ባሕል ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘረጋው አረመኔያዊ የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ የኾነው ዐቢይ አሕመድ ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ እሬቻን የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል ነው ብሎናል። እሱና በስሩ የኮለኮላቸው የአፓርታይድ አገዛዙ ፊታውራሪዎች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቄሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን "ሸገርን ለማስዋብ" በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ አማሮች ናቸው] አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ያስቋረውን ሰው ሰራሽ ሐይቅ "ሆራ ፊንፊኔ" የሚል ስያሜ በማውጣት እሬቻን አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከበር አድርገዋል። ሽመለስ አብዲሳ በሸራተን አዲስ እሬቻን አስመልክቶ በኦሮሚፋ ባደረገው ዲስኩር “እሬቻ ወደ አዲስ አበባ ወደ ጥንቱ እሴት ተመልሶ እንዲከበር ውሳኔ የተላለፈው በጠቅላይ ሚኒስትራችን በዶክተር ዐቢይ አሕመድ ነው” ሲል ነግሮናል። ይህን የሽመልስ አብዲሳ ምስክርነት ይዘን የዐቢይ አሕመድን “ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት ስንመረምር በዚህ ፕሮጀክት ስም በተሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ አዲስ አበባ መሀል የተቋረውና ሆራ ፊንፊኔ ብለው የሰየሙት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለምን አላማ እንደታሰበ ግልጽ ይሆንልናል። በመሰረቱ እሬቻ የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤ ኦሮሞ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ኦሮሞ ዛሬ ኦሮምያ የሚባለውን ምድር ሳይረግጥ መስከረም በገባና መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረ የአራሾች ክብረ በዓል ነው። እሬቻ በሸዋ ውስጥ በብዛት ይከበረ የነበረው ደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ሥፍራ በነበረው ዛሬ ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ነበር። እሬቻ የኦሮሞ በዓል አለመሆኑን በተጨማሪ ለማወቅ የቃሉን ፍቺ ማየትም ይቻላል። እሬቻ የሚለው ቃል የአማርኛ ቃል እንጂ የኦሮምኛ ቃል አይደለም። እሬቻ ኦሮምኛ ነው የሚል ቢኖር የቃሉን የኦሮምኛ ግንድና ቃሉ በኦሮምኛ እንዴት አንደሚረባ ማስረዳት ይጠበቅበታል። የግዕዙ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ "ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት" በሚል ባሰናዱት መዝገበ ቃላት ውስጥ ገጽ 1153 ላይ እንደጻፉት እሬቻ ዋናው ሰብል ደርቆ ከመታጨዱና በአውድማ ተወቅቶ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ የደረሰው ተቆርጦ በበትር በመወቃት ወይም በእጅ ታሽቶ የሚቀመሰው እህል ይሉታል። ሌላው የግዕዝ ሊቅ ከሣቴ ብርሃን ተሰማም በ1951 ዓ.ም ባሳተሙት "የአማርኛ መዝገበ ቃላት" መጽሐፋቸው ገጽ 218 ላይ እረቻ ነባር የአማርኛ ቃል መሆኑን ይገልጹና ትርጉሙም መከር ከመድረሱ በፊት ቀደም ብሎ በመድረስ ለችግር ወይም ለመብል የሚውል ሰብል ይሉታል። በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው። እዚህ ላይ የቦረና ኦሮሞው ወዳጄ ጎዳና ያዕቆብ እሬቻን የኦሮሞ ባሕል ለሚያደርጉት ኦነጋውያን የሰጠውን አስተያየት መጥቀስ አስፈላጊ ነው። ጎዳና እሬቻን አብረንህ እናክብር ለሚሉት ሰዎች የሰጠው አስተያየት እንዲህ የሚል ነበር፤ "እሬቻን አብረንህ ሳናከብር ላሉኝ ወዳጆቼ ከብቶቻቸውን ለማጠጣት የእግዜር ዝናብ ከሚፈልጉ ከዘላን ማኅበረሰብ የተገኘሁት ቦረና በሚን ሁሳብ ነው ዝናብ ቆመ ብዬ ምስጋና የሚያቀርበው? በሹፌርነት ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ሰው ነዳጅ ጠፋ ብሎ ምስጋና ሲያቀርብ ሰምታችኹ ታውቃላችኹ? አርብቶ አደሩ ቦረናስ አራሽ በበሬ ሆኖ ስለ ሰብል እና አዝመራው ተጨንቆ እንኳን ዝናብ ጠፋ አሁን ሰብሌን መሰብሰብ እችላለኹ የሚለው በምን መዋቅር ነው?" ጎዳና እንዳለው ኑሮውን የከብት ጭራ እየተከተለ ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራረት ዘላን የማይመለከተውን በእርሻ የሚተዳደሩ አርሷደሮችን በዓል ያከብራል ካልተባለ በስተቀር የከብት ጭራ እየተከተለና ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራተት ዘላን ዝናብ ቆመ ብሎ ምስጋና ማቅረብ በሹፌርነት ልጆቹን የሚያስተዳድር የቤት ባለቤት ነዳጅ ጠፋ ብሎ ለፈጣሪው ምንጋና እንደማቅረብ አይነት ጤና የጎደለው ተግባር ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነገሶ ጊዳዳ፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ አቶ ይልማ ደረሳ፤ ፕሮፈሰር ተሰማ ታዓ፤ ወዘተ እንደነገሩን ደግሞ ኦሮሞ ከብት በማርባት የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የእርሻ ስራ የጀመረው ደግሞ ዛሬ በሰፈረበት አካባቢ ካገኛቸው የኢትዮጵያ ነገዶች ተምሮ መሆኑን ነግረውናል። ዘመኑም ከ17ኛውና ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው። ይህ ማለት የተሰማራበት የስራ መስክ ከብት ማርባት፤ እምነቱ ደግሞ ዋቄ ፈና ነው የተባለው ኦሮሞ የማያበቅለው እህል የሚሽትበትን ወቅት ጠብቆ ሃይማኖቱ አይደለም የተባለውን መስቀልን አሳልፎ መስቀል በሆነ በሳምንቱ እህል እንዲያበቅል፤ እሸት እንዲቀምስ ለሚያስችል ፈጣሪ ምስጋና ሊያቀርብ ይችላል ካልተባለ በስቀር ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ እሬቻን ማክበር የጀመረው ሸዋን ሲወር ያገኛቸው አራሽና እህል አብቃይ የአማራ ገበሬዎች ያመረቱት ሰብል ለፍሬ እንዲበቃና እሬቻ [እሼት] እንዲቀምሱ ላስቻላቸው ፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረውን የምስጋና ባሕል በመውረስ ነው። ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል፣ ቃሉም አማርኛ ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም። ይህ እውነት ቢሆንም ቅሉ የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ የጥንቱን በራራ ፍራሽ አድሰው እንደገና ከማቆማቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች፤ እሬቻም ከነ ቃሉ የኦሮሞ አይደለም፤ አዲስ አበባ ውስጥም ተከብሮ አያውቅም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። ኦነጋውያን እንኳን በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ቀርቶ ከቦረና ውጭ ያለው ኦሮምኛ ተናጋሪ በወራሪ አባገዳዎች መሬቱን የተቀማ፣ ማንነቱን በኃይል የቀየረና ኦሮምኛ ቋንቋ በግዳጅ እንዲናገር የተደረገ እንጂ ኦሮሞ አለመሆኑን ኦሮሞዎ ብሔርተኞቹ እነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር መሕመድ ሐሰን፣ ወዘተ እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ትክክለኛ ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ከነሱ ውጭ ያለው ነባሩ ሕዝብ ተገዶ ኦሮምኛ እንዲናገር ተደረገ እንጂ ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ አይደለም።