uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
2 944
Підписники
-1024 години
+77 днів
+37930 днів
Архів дописів
#ሰበር_ዜና ‼️ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር  በልዩ  ተወርዋሪ ቡድን  የተሳካ  ኦፕሬሽን ፈፀመ።           ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በናደው ክፍለ ጦር አናብስቶች የከተማ ውስጥ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰራ። የአገዛዙ አገልጋይ በመሆን መንገድ በመምራት፣ መረጃ በመስጠት ፣የወገን ሀይል ላይ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ሲወጉና ሲያስወጉ በነበሩ  ሚሊሾች ላይ ትናንት ምሽት 2:00 ሰአት  በመርሓቤቴ አለም ከተማ 01 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ አጠራር ማቁር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰርቷል።   የአማራን ወጣት በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ማታ ማታ የተለመደውን የዘረፉ ግብራቸውን ለማድረስ ሮንድ እየዞሩ በነበረበት ሰአት በልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ስራ የተካኑት የናድው ክፍለ ጦር የልዩ ኦፕሬሽን ቡድኑ በከተማ ውጊያ የሚሊሻ  አባሎችን ላይመለሱ በመሸኘት ግዳጃቸውን በተሳካ ሁኔታ ተወጥተዋል። የአገዛዙ ሰራዊት በውር ድንብር አሁንም ሰላማዊ ወጣቶችን እያዋከበና ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ምንጮቻችን የገለፁልን ቢሆንም ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ከተማዋን በተኩስ ሲንጣት ማደሩን አረጋግጠናል። ጀግኖቹ ያለ ምንም ጉዳት ወደ ጦር ሰፈራቸው በመመለስ ለቀጣይ ግዳጅ ዝግታቸው እና በፀረ -አማራ ሀይል ላይ ሁሉ እርምጃቸው እንደሚቀጥል በኩራት ገልፀዋል።   በተሰራው ኦፕሬሽን የተገኜ ድል ▸  2  ሚሊሻ የተደመሰሰ ▸  1 ክላሽ እንኮቭ የተማረከ ▸ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት የቆሰሉ መኖራቸውን የክ/ጦሩ ሪፖርተር አረጋግጧል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በትላንትናው ዕለት በሸዋ ደራ ቀጠና የአርሶ አደሩን ቤትና ንብረት ያቃጠለው አንባገነን አማራ ጠሉ ብልፅግና በተመሳሳይ የጥፋት እጁ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አከለል ቀበሌ ቃቂቻ ቦካን ጫካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማኅበረሰቡ ተሳትፎ ከ1989ዓ.ም ጀምሮ  ለረጅም ዓመት ተከብሮ የነበረውን ጥቅጥቅ የደን ልማት በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ትላንት ግንቦት 11/2018ዓ.ም ከጠዋቱ  1:15 ሰዓት ላይ በእሳት መቃጠሉን ነዋሪዎች በምሬት ገልፀዋል። የእሳት ቃጠሎውን ያዩ በቀጠናው በአንድ ላይ ተዋደው ተዋልደው የሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰብ የአካባቢው ነዋሪዎች ድንገተኛ ቃጠሎ የተነሳ መስሏቸው እሳቱን ለማጥፋት በቦታው ላይ በፍጥነት የደረሱ ቢሆንም በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት  እንዳባረሯቸው እና እየተቃጠለ ያለው ጥብቅ ደንም በወረዳው አስተዳደር ይሁንታ እንደሆነና "እናንተ አያገባችሁም!" በማለት እንደተባረሩ በከፍተኛ ምሬትና በሀዘን ውስጥ ሆነው መረጃውን ለቀጠናው የኮር ዘጋቢያችን አድርሰዋል።            "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"   "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!" የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምረያ

#ሰበር_ዜና ‼️ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር  በልዩ  ተወርዋሪ ቡድን  የተሳካ  ኦፕሬሽን ፈፀመ።           ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በናደው ክፍለ ጦር አናብስቶች የከተማ ውስጥ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰራ። የአገዛዙ አገልጋይ በመሆን መንገድ በመምራት፣ መረጃ በመስጠት ፣የወገን ሀይል ላይ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ሲወጉና ሲያስወጉ በነበሩ  ሚሊሾች ላይ ትናንት ምሽት 2:00 ሰአት  በመርሓቤቴ አለም ከተማ 01 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ አጠራር ማቁር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰርቷል።   የአማራን ወጣት በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ማታ ማታ የተለመደውን የዘረፉ ግብራቸውን ለማድረስ ሮንድ እየዞሩ በነበረበት ሰአት በልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ስራ የተካኑት የናድው ክፍለ ጦር የልዩ ኦፕሬሽን ቡድኑ በከተማ ውጊያ የሚሊሻ  አባሎችን ላይመለሱ በመሸኘት ግዳጃቸውን በተሳካ ሁኔታ ተወጥተዋል። የአገዛዙ ሰራዊት በውር ድንብር አሁንም ሰላማዊ ወጣቶችን እያዋከበና ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ምንጮቻችን የገለፁልን ቢሆንም ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ከተማዋን በተኩስ ሲንጣት ማደሩን አረጋግጠናል። ጀግኖቹ ያለ ምንም ጉዳት ወደ ጦር ሰፈራቸው በመመለስ ለቀጣይ ግዳጅ ዝግታቸው እና በፀረ -አማራ ሀይል ላይ ሁሉ እርምጃቸው እንደሚቀጥል በኩራት ገልፀዋል።   በተሰራው ኦፕሬሽን የተገኜ ድል ▸  2  ሚሊሻ የተደመሰሰ ▸  1 ክላሽ እንኮቭ የተማረከ ▸ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት የቆሰሉ መኖራቸውን የክ/ጦሩ ሪፖርተር አረጋግጧል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በትላንትናው ዕለት በሸዋ ደራ ቀጠና የአርሶ አደሩን ቤትና ንብረት ያቃጠለው አንባገነን አማራ ጠሉ ብልፅግና በተመሳሳይ የጥፋት እጁ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አከለል ቀበሌ ቃቂቻ ቦካን ጫካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማኅበረሰቡ ተሳትፎ ከ1989ዓ.ም ጀምሮ  ለረጅም ዓመት ተከብሮ የነበረውን ጥቅጥቅ የደን ልማት በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ትላንት ግንቦት 11/2018ዓ.ም ከጠዋቱ  1:15 ሰዓት ላይ በእሳት መቃጠሉን ነዋሪዎች በምሬት ገልፀዋል። የእሳት ቃጠሎውን ያዩ በቀጠናው በአንድ ላይ ተዋደው ተዋልደው የሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰብ የአካባቢው ነዋሪዎች ድንገተኛ ቃጠሎ የተነሳ መስሏቸው እሳቱን ለማጥፋት በቦታው ላይ በፍጥነት የደረሱ ቢሆንም በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት  እንዳባረሯቸው እና እየተቃጠለ ያለው ጥብቅ ደንም በወረዳው አስተዳደር ይሁንታ እንደሆነና "እናንተ አያገባችሁም!" በማለት እንደተባረሩ በከፍተኛ ምሬትና በሀዘን ውስጥ ሆነው መረጃውን ለቀጠናው የኮር ዘጋቢያችን አድርሰዋል።            "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"   "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!" የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምረያ

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ መና መቀጠዋ ወረዳ የስርዓቱ አገልጋይ የነበሩ ወታደሮች ሕዝባዊ ውግንናቸውን በማሳየት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ! 1ኛ፦መታደል መላክ 2ኛ፦ ሞገስ ፀጋ
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ  መና መቀጠዋ ወረዳ የስርዓቱ አገልጋይ የነበሩ ወታደሮች ሕዝባዊ ውግንናቸውን በማሳየት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ! 1ኛ፦መታደል  መላክ 2ኛ፦ ሞገስ ፀጋው 3ኛ፦ ማሙሸ ቀኘ 4ኛ፦ ዋጋው ሞገስ የተባሉ ወታደሮች ዛሬ ግምቦት 12/2018 ዓ/ም ከኑ ሙሉ ትጥቃቸው በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር መቀላቀላቸውን አስታውቋል:: 12/09/18ዓ.ም

አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ እዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር በአደረገው ተጋድሎ ድል ተቀናጅቷል!! አረመኔው የብልፅግና ሰራዊት ከለገሂዳ ከተማ ተነስቶ ወደ ቢላላ (ክሬ ገብያ) እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሳለ ጀብደኛው ሚኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር መብረቅ ሻለቃ እና ንስር ሻለቃ ከለገሂዳ እስከ ጃማ በመዘርጋት ባደረጉት ትንቅንቅ ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል። ከግንቦት 10 _11 /2018 አ.ም በወሰደው አውደ ውጊያ በለገሂዳ የመጣውን የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ የጠላት ሀይል በመፋለም የጠላትን ትስስር የተበጣጠሰ ሲሆን በርካታ የጠላት ሀይል በመደምሰስ ከ10 በላይ የሞተ እና ከ12 በላይ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎፅፏል። የጠላት ሀይል በተደረገበት መብረቃዊ ጥቃት በመበሳጨት የፋሽስቱ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በሜካናይዝድ የታገዘ ጦርነት በመክፈት የንፁሀን አማራዉያን ቤት እና ንብረቶችን አውድሟል። በአማራ ጠሉ የአረመኔው ጥቁሩ ናዚው አብይ አህመድ ወንበር አሰጠባቂ ሰራዊት አሁንም በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ እያደረሰ ይገኛል። ቀናትን የወሠደው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ጠላትን የረፈረፉት የ105ኛ ኮር አካል የሆነው 33ኛ ክፍለ ጦር የጠላትን ሀይል የዶግ አመድ በማድረግ ድል አስመዝግቧል። መዳረሻውን ድል እና ነፃነት የሆነው የአምሃራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ33ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሠረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም

√ ትግላችን እና አማራነት ! የአማራ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ልሂቃን ሁለንተናዊ ድክመትና ውድቀት ምክንያት የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት በመገንባትና በመጠበቅ ረገድ የተጫወተው የአንጋፋነት ሚና እንደ ወንጀል ተቆጥሮበት በአገር ውስጥና በውጭ ሃይሎች መጠነ-ሰፊ ውርጅብኝ ሲወርድበትና ዋጋ ሲከፍል ቆይቷል፡፡ ሕዝባችን በቁጥሩ ቀዳሚ እንዲሁም በታሪካዊና መንፈሳዊ ዕሴቱ የሚከበር ሆኖ ሳለ፤ ማንነቱን በማይመጥን ሁኔታ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እንዲኖር የተፈረደበትና በተከታታይ መንግስታት ሲጨቆንና ግፍ ሲፈፀምበት የኖረው፣ ከዚያም አልፎ ሕልውናው አደጋ ላይ ወድቆ የሚሳደደውና የሚጨፈጨፈው ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ (ልሂቃኑ) ታሪካዊ ተልዕኳቸውን ባለመወጣታቸው ወይም በመውደቃቸው ምክንያት ነው፡፡ በአጠቃላይ፤ የአማራ ህዝብ በተከታታይ አገዛዞች (ከነገስታቱ ዘመን እስከ ዛሬ) ቁጥሩን፣ ታሪኩንና ዕሴቱን በማይመጥን ሁኔታ ሲጎሳቆልና ሲጨቆን ኖሯል፡፡ የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ለአገሪቱ ህልውና መጠበቅ የተጫወተው የአንጋፋነት ሚና እንደ ወንጀል ተቆጥሮበት በቄሳራዊያን ሃይሎች (ቅኝ ገዥዎች) ጥርስ ተነክሶበት ታሪኩ፣ ባህሉና ዕሴቱ እንዲጠለሽ፤ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እንዲጠላ አደገኛ ፀረ አማራ ትርክት ተፈጥሮ በስፋት ተሠርቶበታል፡፡ ይህ ፀረ አማራ በቅኝ ገዥዎች የተፈጠረና በሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች (በተለይም በልሂቃኑ) አእምሮ ውስጥ ሥር የሰደደ ትርክት ፍሬ አፍርቶ የአማራ ሕዝብ በሀገሩ ባይተዋር ሆኖ ያለማቋረጥ እየተፈናቀለና እየተጨፈጨፈ ይገኛል፡፡ በጥቅሉ፤ የአማራ ህዝብ ታሪኩንና ቁጥሩን በማይመጥን ሁኔታ ውስጥ የሚገኘውና ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀው በዋናነት በራሱ ልጆች ውድቀት ምክንያት መሆኑን መቀበል ይገባል፡፡ በሌላ አባባል ዋነኛው የውድቀታችን ምንጭ ውስጣዊ ነው! ይህ ሰንድ የአማራ ህዝብ በሀገር ግንባታ እና የሀገርን ህልውና በመጠበቅ ሚናው የነበረው ብርቅዬና አንፀባራቂ ታሪክ ጠፍቶ የራሱ የአማራው ህልውና አደጋ ላይ የወደቀው በውጭና በአገር ውስጥ ፀረ አማራ ኃይሎች የጥፋት ግንባር ርብርብ ቢሆንም ህዝባችን ለዚህ የበቃበት መሪ (ዋና) ምክንያት ግን የራሱ ልጆች በተለይም የልሂቃኑ ውድቀት መሆኑን በጉልህ አስምሮ የሚነሳ ሰነድ ነው፡፡ ህዝባችን ከሚገኝበት እጅግ አሳፋሪ ታሪኩንና ዕሴቱን የማይመጥን ሁኔታ ወጥቶ፣ ነፃነቱንና ህልውናውን አስከብሮ፣ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በእኩልነት፣ በፍትሕና በዲሞክራሲ መኖር እንዲችል ያጋጠመንን ውድቀትና የውድቀቱን መንስኤዎች በሚገባ ለይተን ከገባንበት አረንቋ ለመውጣት ሌት ከቀን መረባረብ ይጠበቅብናል፡፡ በአጠቃላይ፤ የትግሉ መነሻ ገፊ ምክንያት ህዝባችን የሚገኝበት ከታሪኩና ከዕሴቱ ጋር አብሮ የማይሄድ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ውርደት እንዲሁም እንደ ህዝብ የመጥፋት አደጋ ሲሆን፤ የትግሉ መዳረሻ ደግሞ የአማራን ህዝብ የህልውና ስጋት ቀልብሶ ነፃነቱን ማረጋገጥና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በእኩልነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡ ስለሆነም እንደ ታጋይ በህዝባችን ላይ የተደቀነውን አደገኛ የሕልውና አደጋ ቀልብሰን ነፃነቱን ለማረጋገጥ የትግሉን መነሻና መዳረሻ ወይም በሌላ አባባል ለምን እንደምንታገል ጠንቅቀን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ “ቃል ይገድላል፤ ቃል ያድናል” እንዲሉ ጥራት ያለው የትግል ሐሳብ (ቃል) ወሳኝ ነው፡፡ ተግባር (ትግል) ያለ ሐሳብ፣ ሐሳብም ያለ ተግባር ከንቱ ነው፡፡ ስለሆነም፤ ሐሳብና ተግባር ተመጋግበው መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ከዚህ በላይ የተገለጸውን ሐሳብ መሠረት አድርጎ ሲሆን፣ እያንዳንዱ አርበኛና የነፃነት ታጋይ (ፋኖ) ለምን እንደሚታገል ጠንቅቆ አውቆ እራሱን ለመስዋዕትነት ዝግጁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ስለ ትግሉ መነሻና መዳረሻ ለሌሎች ጓዶቹ እንዲሁም ለህዝቡ በየደረሰበት ሁሉ ማስረፅ ይጠበቅበታል፡፡ √ አማራነት ባለፉት ሠላሳና አርባ ዓመታት አማራንና አማራነትን በሚመለከት ሰፊ ክርክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ አንዳንድ ግለሰቦች (በተለይም ራሳቸው የአማራ ልሂቃን) “አማራ የሚባል ህዝብ የለም” እስከማለትና የህዝባችን ሕልውና እስከመካድ ሄደዋል፡፡ ይህም በቀጥታ ከዚህ በላይ ከተገለፀው የአማራ ልሂቃን ሁለንተናዊ ውድቀት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እነዚህ አካላት ራሳቸው አማራ ሆነው ሳለ አማራነታቸውን የሚክዱት ወይም አማራና አማራነት የሚባል ማንነት የለም እስከማለት የሄዱት አማራ የሚባለው ህዝብ በማንነቱ ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትጠፋለች ወይም ህልውናዋ አደጋ ላይ ይወድቃል ከሚል ምክንያት ነው፡- ይህን ምክንያታቸውን በአደባባይ ባይገልፁትም፡፡ ይሁን እንጂ አማራና አማራነት እነዚህ ልሂቃን የለም ስላሉት አይጠፋም፤ አለ ስላሉትም አይኖርም፡፡ የአማራ ህዝብ ለዘመናት የኖረ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ እና የሀገሪቱን ህልውናና ነፃነት በመጠበቅ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ሲጫወት የኖረ ሕዝብ ነው፡፡ የአማራ ህዝብ የተከበረ ማንነት ያለው ሕዝብ ነው፡፡ √ አማራነት አማርኛ ቋንቋን ከመናገር ወይም ቋንቋው ቋንቋዬ ነው ብሎ ከማመንና አማርኛን ከመንከባከብ ጋር ይያያዛል፡ ፡ √ አማራነት በአማራ ታሪክ፣ ዕሴት፣ ባሕል፣ ወግ ወዘተ… ከመኩራት እና ታሪኩ፣ ዕሴቱ፣ ባሕሉ፣ ወጉ ወዘተ… የእኔ ነው ብሎ ከማመን፤ እንዲሁም ታሪኩን፣ ባሕሉም፣ ዕሴቱን፣ ወጉን ወዘተ… ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ከመትጋት ጋር ይያያዛል፡፡ √ አማራነት ያለፈው ታሪኬና ሐረጌ ብቻ ሳይሆን አሁናዊና መጻኢ ዕድሌ ወይም እጣ-ፈንታዬ ከሌሎች አማሮች ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ማመን ነው ። √ ከሁሉም በላይ አማራነት “አማራ ነኝ” ብሎ ማመን ነው፡፡ √ አማራነት ከቋንቋው፣ ከታሪኩ፣ ከባሕሉና ከሥነ ልቦናው ጋር እንጂ ከደም ጥራት ወይም ከኃይማኖት ጋር የሚያያዝ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከላይ የተገለጹትንና ሌሎችን የአማራነት መለዮዎች (essentials) እስከያዘ ድረስ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶም ይሁን ሙስሊም፤ ካቶሊክም ይሁን ፕሮቴስታንት፤ ይሁዳዊም ይሁን የሌላ እምነት ተከታይ አማራ ነው፡፡ የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም። ንቃ አማራ

የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጂቷል‼️ ግንቦት 11/2018  ዓ/ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ55ኛ ክፍለ ጦርና የዳንግላ ወረዳ ጊ/መ/ አስተዳደር በጥምረት ከዳንግላ ከተማ ወጦ ወደ አባድራ ዙሪያ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ሀይል፣ ዳንግላ አባድራ ከተማ ዙሪያ አፄ ዮሀንስ ተራራ እና ቱምሀ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ጠላትን ሲረፈርፉት ውለዋል። በዚህም አውደ ውጊያ ላይ የተገኘ ድል፦ 1.14 /አስራ አራት/በላይ የተደመሠሠ 2.13/አስራ ሶስት/በላይ ከባድ ቁስለኛ 3.7 /ሰባት/በላይ ቀላል ቁስለኛ 4.1 /አንድ/ የጦር መኮነነ  አመራር 5.1/አንድ/ ስናይፐር ተኳሽ 6.7 ሰባት/ክላሽንኮፍ ምርኮ 7.1 /አንድ/አስቃጥላ የክላሽ ጥይት የተገኘ ሲሆን፣ የ55ኛ ክ/ጦር ተርቦችን መቋቋም ያቃተው የምርኮኛው ሰራዊት ከወርቅ ሚዳ ዙ_23 ይዞ ወደ ወለቴ የተጠጋ ቢሆንም በጀግኖች ምት ወደ መጣበት ወርቅ ሜዳ ከተማ  ተመልሷል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር   ህዝብ ግንኙነት

አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በአንኮበር  አፄ አምደ ፅዮን ኮር ራምቦ ክፍለጦር በሳሲት ድል ሲቀዳጁ ከሸዋሮቢት ከተማ የ103ኛ ኮማንድ ክፍለ ጦር መከላከያ ፋኖን ተቀላቅሏል። ግንቦት 11/2018 ዓ/ም በአማራ ህዝብ ላይ ዘረ ተኮር ጭፍጨፋ እያካሄደ የሚገኘው የብልፅግናውን ወጀል አራማጅ በተለመደው  ሂደት ህዝባችንን የመከራ ህይወት እዲጎነጭ መሪ መደላድል በመሆን ያላግባብ እየሞተ ያለው  ያለእዳው ገቢ መከላከያ ሰራዊት ከደብረብርሃን አራት ሃይሱዙና አራት ፓትሮል ሰራዊት በሽዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ አውራጃ አንኮበር ወረዳ ወደ ደረፎ ቀበሌ በሚጓዝበት ስአት አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ቃኘዎችና የሻለቃ 1 ፋኖዎች አይደብስ በተባለ ቦታ ላይ ደፈጣ በመጣል መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመውበታል። ከአንኮበር በሁለት መኪና አድማ ብተና ጭኖ በቁንዲ አድርጎ ወደ ደረፎ ሲቀሳቀስ የነበረው ጠላት የተመታ ሲሆን የአድማ ብተን አመራር ጭምር ወደ ሲኦል ተሸኝቷል።የብልፅግና አገልጋይ ገረዶች በአመራራቸው ሞት በአንኮበር ከተማ ከፍተኛ የጥይት ፍዳታ እያፈነዱ መሆኑን የውስጥ አርበኞቻችን መረጃ አድርሰውናል። ጠላት ከሃያ በላይ ቁስለኛውን ወደ አንኮበር የወሰደ ሲሆን ከአምስት በላይ ወደ ደብረብርሃን ሪፈር ተፅፎላቸው ሄደዋል።በአጠቃላይ በአራት አምቡላንስና አንድ ሃይሱዙ ሙትና ቁሰለኛ ሲያግዝ ያልተነሳ የጠላት አስክሬን እንዳለ ታውቋል። ወጊያው እደቀጠለ ሲሆን አጠቃላይ ዜናውን ነገ የምንመለስበት ይሆናል። ይህ በእዲህ እዳለ የአገዛዙ 104ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር መነሻውን ከሞጃና ወደራ ወረዳ ሰላድንጋይ ከተማ በማድረግ ወደ ሳሲት እና አካባቢው ለማቅናት ያደረገው ከንቱ ቅዠት በአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃዶች በሚገባ ተመቶ ተመልሷል። ኮማንዶው ጋንታ መሪ በጠዋቱ ፋኖን መቀላቀሉን ተከትሎ የተደናገጠው አገዛዙ በመንገድ መሪው ሚኒሻ አማካኝነት ወደ ጀግኖቹ መንደር ከቀኑ 6:00 ላይ ያመራ ሲሆን ልዩ ቦታው ፈላገነት በተባለ ቦታ በጀግናው ፋኖ የቅንጅት ውጊያ በሚገባ ተመክቶ ወደ መጣበት ሲመለስ በእውር ድንብር የዘፈቀደ የሞርተር ቅንቡላ ወደ ማህበረሰቡ ሲያስወነጭፍ ወሏል። የአገዛዙ ሰራዊት ከሸዋሮቢት ከተማ ከ103ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ወደ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን መቀላቀሉ   ታውቋል ይዞት የተቀላቀለው ንብረትም የሚከተለውን ይመስላል !! 👉አንድ ዘመናዊ ጥቁር ጥርጥር ክላሽንኮቭ    👉200 የክላሽ ተተኳሽ    👉አንድ የደረት ትጥቅ    👉አራት የክላሽ መጋዘን/ካዝና ይዞ በሰላም  ተቀላቅሏል። ድል ለተገፋው አማራ ህዝብ ክብር ለትግሉ ሰምአታት "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት!!

ሰላም #ፍኖተ #አማራ #ሚዲያ እንደምን አላችሁ ይህ በ 11/09/2018 ዓም በኦሮሚያ ክልል በፍቸ እና ገብረ ጉራቻ መሀከል አሊደሮ ከተማ ወጣ ብሎ የታጠቁ ወንበዴወች ተኩስ ከፍተው ጎማ መስታውት መ
ሰላም #ፍኖተ #አማራ #ሚዲያ እንደምን አላችሁ ይህ በ 11/09/2018 ዓም በኦሮሚያ ክልል በፍቸ እና ገብረ ጉራቻ መሀከል አሊደሮ ከተማ ወጣ ብሎ የታጠቁ ወንበዴወች ተኩስ ከፍተው ጎማ መስታውት መተው በማስቆም ታሳፋሪወችን አፍነው ወስደዋል የሚል መልዕክት ደርሶናል። ሌላው ተሳቢ ጎማ መስታውቱ በጥይት ተመቶ ሾፌሩ ተጎድቷል የሚል መልዕክት አለ ይህ አውቶብስ ከፊት በጥይት እንዴት እንደተመታ ይታያል ከመስትውቱ ባለፈ ዙሪያውን መመታቱን ገልፀውልናል። ወደ ህዝብ ጥይትን የሚተኩሱ በተደጋጋሚ እገታ ግድያን የሚፈፅሙ ሙሉ ተሳፋሪን አፍነው ስልክ ተደዋውለው ተደራድረው የሚኖሩ ወንበዴወችን ከመስመሩ ማፅዳት አነፍንፎ ይዞ በህግ መቅጣት ባለመቻሉ ያሻቸውን እንዲያደርጉ እድል ፈጥሯል። ይህ የመንገድ ክፍል የዘራፊ መፈንጫ መሆኑ ይታወቃል 43 ኪሎ ሜትር መንገድ መቆጣጠር አለመቻል ሾፌር ተሳፋሪ እንዲታፈን እንዲገደል እያደረገ ይገኛል መንገዱ በአገልግሎቱ እና በችግሩ ግዝፈት ልክ ጥበቃ እና ትኩረት ሊደረግለት ይገባል። ፍትህ

ዛሬ ቀን 11/09/2018አ,ም የአፋብን 206ኛ /ኮር/የ14ኛ/ክ/ጦር/የንጉሦተክላሀማኖትሻለቃ ድልተቀናጀ:- የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት መነሸውን ደ/ማርቆስ አድርጎ በሰሦስት አቅጣጫ የተግተለተለው ወደደብ
+1
ዛሬ ቀን 11/09/2018አ,ም የአፋብን 206ኛ /ኮር/የ14ኛ/ክ/ጦር/የንጉሦተክላሀማኖትሻለቃ ድልተቀናጀ:- የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት መነሸውን ደ/ማርቆስ አድርጎ በሰሦስት አቅጣጫ የተግተለተለው ወደደብርዘይት፣ወደየቦቅላ፣በየሰንበት የፋኖን ካፕ ለመያዝ ሲንቀሳቀሰ የነበርው ወራደው የብርሀኑ ጁላ ወታደር, በደብርዘይት አቅጣጫ የመጣው ሞርተር ዙ23 ጀኔራል መድፍ ቢጠቀምም :በአናብስቶቹ ክንደነበልባል የንጉሥተክላሀይማኖት ሻለቃ በከበባ እየተቀጠቀጠ ሙት፣ቁስለኛ ሆኖ ተመቶ ይገኛል:የክንደነበልባሎችን ክንድ መቆቋም ያቃተው እግሬ አውጭኝ እያለ እየፈርጠጠ ይገኛል:: አሁን ባለው ተጨባጭ መርጃ የተማርከ: -ነፍስ ወከፍክላሺለጊዜው በቁጥር የታወቀ6 -በቁጥር ያልታወቀ በርካታ የብሬን እናየክላሺ ተተኳሺ ተተኳሺተማርኳል:: -ካዘና፣የወገብትጥቅ፣መማ ርክ ተችሏል::ውጌው እንደቀጠለነው የአብይ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በአናብስቶቹ ፋኖ ተከቦ በጣርሞትእየተጨነቀ ይገኛል:: -ፋኖ አዲሱ ሙሉቀን የንጉስ ተክላሀማኖት ሻለቃ አባል የሆነው ሁለት ጥቁር ክላሺ ከጠላት በውጊያ ማርከ:: -አዲስ ትውልድ! -አዲስ አስተሳስብ!! -አዲስ ተስፋ!!! የአፋብን/206ኛ/ኮር/የ14ኛ/ክጦር/ህ/ግንኙነት

የጥንቃቄ መልዕክት ለ54 ክ/ጦር በሙሉ ‼️ በባለፈው ወር ማለትም መጋቢት 30/2018 ዓም የአብይ አህመድ ወራሪ ሰራዊትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የሰዴን ወረዳ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ይታውቃል ። እና
የጥንቃቄ መልዕክት ለ54 ክ/ጦር በሙሉ ‼️ በባለፈው ወር ማለትም መጋቢት 30/2018 ዓም የአብይ አህመድ ወራሪ ሰራዊትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የሰዴን ወረዳ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ይታውቃል ። እናም አሁንም ሰዴን መልሸ ይዤ እቀመጣለሁ የሚል ቀቢተ ቢስ ተስፈኛው የብልፅግናው ስርዓት ዝግጅት ላይ መሆኑን የአሻራ ሚዲያ ምንጮች ገልፀውልናል ። የሚገባበት አላማ 1. የፋኖ አቅም ለስለስ ያለ ከሆነ ኃይሌን አጠናክሬ እዛው እቀመጣለሁ የሚል ነው ። 2. ፋኖ ጠንከር ያለ እርምጃ የሚወስድ ከሆነና ለመቀመጥ የኃይል ሚዛኑ የሚበልጥብኝ ከሆነ እንደምንም እየተከላከልኩ የሰዴ ወረዳ የምርጫን ጣቢያ ማስፈፀምና ከምርጫ በኃላ ወደ ሞጣ መመለስ። በሚል ከየ ወረዳው ማለትም ከሞጣ፣ ጉምደወይን ፣ደብረወርቅ፣ ቢቸና እና የትኑራ ያለውን ኃይል እየቀነሰ ሰብስቦ የምርጫው ቀን እስኪያልፍ ሰዴ ወረዳን መቆጣጠር የሚል መሆኑን የውጥ አሻራ ሚዲያ ምንጮች መልፅክቱን አድርሰውናል ።     አሻራ ሚዲያ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የ22ኛ  ክፍለጦር በዋድላ እና በመቄት ወረዳዎች ታላቅ ጀብድ ተፈፅሟል! ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ዛሬ ግንቦት 11/2018ዓ.ም 12:00 ሰዓት ጀምሮ በጥላት የበላይነትን የተቆናጠጡት የቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ እና የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ትንፋሾች የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ሲረፈርፉት ውለዋል። ከቋና እስከ ቁር-አንበሳ  ጨፍጫፊው የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል። የአማራን ህዝብ ለማጥፋትና ጭፍጨፋ ለመፈፀም ተልዕኮ ተቀብሎ ወደ ክልሉ በብአዴን ዘልቆ የገባው የአገዛዙ ሰራዊት በዋድላና በመቄት ወረዳ ሜዳዎች ከ29 በላይ የተደመሰሱ ሲሆን፤ በርካታ የጥላት ሰራዊቶች ቁስለኛ ተደርገዋል። ከፋኖዎች የተሰነዘረበትን ከባድ ጥቃት መቋቋም የተሳነው የጥላት ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ ጋሸና የፈረጠጠ ሲሆን ሙትና ቁስለኞቻቸውንም በጋሸና ሆስፒታል አስገብቶ እየገነዘና እያከመ ይገኛል። በዚህ ጥቃት የተበሳጨው የጥላት ሰራዊት የሲቪሎችን አልባሳት በመግፈፍ ለቁስለኞቻቸው ቁስል ማሰሪያ ሲጠሸሙበት፤በቀሪዎች ማህበረሰቦች ላይ ድብደባ በመፈፀም  ከባድ የአካል ጉዳት ፈፅመውባቸዋል። የአማራን ህዝብ ጥላት አድርጎ የተነሳው የብልፅግና ስርዓት በዚህ አውደ ውጊያ አከርካሪው ተሰብሮ ጋሸና ከተማ ላይ የሲቃ ድምፅ እያሰማ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ106ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል፤ የ303ኛ ኮር ነጻ ባደረጋቸው ቀጠናዎች ከ4,500 በላይ ሕዝብ የተሳተፈበት ሰፊ ውይይት አካሄደ ​(ግንቦት 11/2018 ዓ.ም — አሻራ ሚዲያ) ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ነጻ ባወጣቸው ቀጠናዎች ላይ ከሕዝቡ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጥበቅ የጀመረውን ሰፊ ሕዝባዊ ውይይትና የማኅበረሰብ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በቡግና ወረዳ ቆብ ቀበሌ፣ በላስታ ወረዳ ሳርዝና ቀበሌ እንዲሁም በመቄት ወረዳ 022 (ዝቤ) እና 028 ቀበሌዎች ላይ በተከታታይ በተካሄዱት በእነዚህ መድረኮች ላይ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ዜጎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶችን ጨምሮ ከ4,500 በላይ የሚሆን እጅግ ከፍተኛ ሕዝብ በንቃት ተሳትፎባቸዋል። ​የአማራ የሕልውና ተጋድሎ ዋነኛ መሠረቱና ባለቤቱ የመጥፋት አደጋ የተደቀነበት ራሱ መላው የአማራ ሕዝብ መሆኑን የገለጹት የውይይቱ ተሳታፊዎች፣ የአፓርታይዱ የአብይ አህመድ ሥርዓት በኃይል ሊጭነው የሚሞክረውን የሐሰት የምርጫ ተውኔት ፍጹም እንደማይደግፉትና አገዛዙ ይህንን ድራማ በአስቸኳይ ሊያቆም እንደሚገባ በቁርጠኝነት አንስተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጊዜያዊው ወታደራዊ የሲቪል መዋቅር ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲያደርግ፣ እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የግድያና የደም መመላለስ (የበቀል) ድርጊቶች የሚቆሙበት ቋሚና አስተማማኝ ማኅበራዊ መፍትሔ በአማራጭነት ሊበጅለት እንደሚገባ ተወያዮቹ ገንቢ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል። ​ይህንን በስኬት የተጠናቀቀ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ በጋራና በጥምረት የመሩት በምኒልክ ዕዝ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ስር የሚገኙት 19ኛ እና 81ኛ ክፍለ ጦሮች፣ የቡግና፣ የላስታና የመቄት ወረዳዎች ጊዜያዊ ወታደራዊ ሲቪል መዋቅሮች እንዲሁም የ106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች መሆናቸው ታውቋል። ከመድረኩ መሪዎች በኩልም በውይይቱ ወቅት ለተነሱት ሕዝባዊ ጥያቄዎች ወቅቱን የጠበቀና አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፣ ይህም በሕዝቡና በፋኖ ሰራዊት መካከል ያለውን መተማመን የላቀ ደረጃ ላይ አድርሶታል። የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለአሻራ ሚዲያ በላከው መግለጫ፣ መዳረሻው ፍጹም ድልና ነጻነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ከሕዝባዊ ንቅናቄው ጋር ተናቦ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። ​አሻራ ሚዲያ - የአይበገሬዎች ልሳን!

በጭንቀት ውሰጥ ያለው ብልፅግና በዛሬው እለት ሰዴ ወረዳ እና ቢቡኝ ወረዳወችን በመድፍ በመደብደብ ንፁሀን እንስሳቶች ላይ ጉዳት አድርሷል። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ግንቦት 11/2018 ዓ.ም የተሸነፈው የአብይ አህመድ አገዛዝ የሚይዝ የሚጨብጠው ያጣው ብልፅግና በዛሬው እለተ ከጠዋቱ 2:15 ሰዓት ላይ ፀረ አማራው የብለፅግና ስርዓትከ 5ጊዜ በላይ በመድፍ ቀበሌወችን ሲደበድብ ያረፈደ ሲሆነ ቢቡኝ ወረዳ ሞልሳ ቁስቋም ቀበሌ የቄስ ንጉስ ይታየው ፈረስ ከእነ ልጇ በመድፍ የሞትበት ሲሆን በግምት 80000ሽ (ሰማኒያ ሺ ብር ) ብር የምታወጣ ሲሆን ። ...ሌላኛው የ7 ዓመት ህፃን ልጅ ካሳሁን ንጉስ የተባለ ፈረሷን ሲጠብቅ የነበረ ህፃን ተፈናጣሪ ጉዳት አድርሷል። በሌላኛው ቀጠና ደግሞ ግንቦት 06/2018 ዓ.ም በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ስርአቱ 6የባጃጅ ሾፌሮች እና ነጋዴወችን ያለምንም ምክኒያት መሀል ከተማ ጨፍጭፏቸዋል። 1.ሐብታሙ ሹምየ..ዕድሜ =27 2.አዲስ ይመን....ዕድሜ=18 3.ልደት አለማየሁ ..ባጃጅ ሹፌር 4.መኳንት ጋሻው...ባጃጅ ሹፌር 5.አምበሉ አብጤ ....ነጋዴ 6.እባቡ አስሬ መስማት የተሳነው ዕድሜ=72 7.ንጉስ ቡልጋ...ዕድሜ=17 ንፁሀንን በመግደል የአመራን ትግል ማስቆም አይቻልም። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት