ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 386
Підписники
+5424 години
+2347 днів
+1 43730 днів
Архів дописів
የአርበኛው ዘመነ ካሴ ወቅታዊ መልዕክት
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
ዛሬም ለዐላማው የተሶረፈ ልብ፥ ዛሬም የፀና መንፈስ፥ ዛሬም የጋለ ወኔ፥ ዛሬም የእርስበርስ መከባበርና አንድነት ያስፈልገናል።ድልና "ተአምር" የሚመነጩት እነዚህ ውብ "ተራሮች" ስር ነውና።
ተወረናል፥ የዘር ፍጅት እየተፈፀመብን ነው። ነገር ግን መንፈሳችንና ልባችን አሁንም በእጃችን ነው። መንፈሳችንና ልባችን በእጃችን እስካለ ድረስ በአብይ አረመኔ የጉብል ሰራዊት የተወረረው መሬታችንና ህዝባችን ነፃ ወጦ ህልውናው ይረጋገጣል።ይህም በመሆኑ በጦር ሜዳ፥ በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው ግንባር በየቀኑ ጠላታችንን እያሼነፍን ነው።
ልቡና መንፈሱን ራሱ ጋር አቅፎ የያዘ ህዝብ የጊዜ ጉዳይ እንጅ ድሉ ከታዛው ነው፥ የሚፈልገው ነገር ሁሉ በአጠገቡ ነው።
ከራእያችን የሚቀዳው ለሰው ልጆች ሁሉ የሚበጅ በጎው ምኞታችን በጥረታችን ይሳካል። በጎ ምኞቶች ዳር ይደርሱ ዘንድ የሚንከባከብ አንዳች አይነት የራሳቼው እግዜር አላቼው።
አለም ጠንካሮች፥ ደፋሮች፥ ፅኑዎችና ለአላማቼው የመነኑ ብቻ ዋኝተው የሚሻገሩት ውቅያኖስ ነውና በእያለንበት እንበርታ።ሁልጊዜም የሚከተሉት የአቢዮታችንና የህልውናችን አራት ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርገን እንስራ!!
1)ጉልበት-ክላሽ(የማያቋርጥ የሃይል ግንባታ፥ እስከምፃት ማንቃት ፥ማደራጄት፥ ማሰልጠንና ማስታጠቅ!)
2)እውቀት(በየደቂቃው እውቀትን መሻት፥ አዲስ ነገር ለመገንዘብ መጓጓት፥ የማያቋርጥና የማይረካ የእውቀት ረሃብ!አለምን በልኩ መረዳት!ተፈጥሮን መረዳት!
ትሁት ስልጣኔ መገንባት!በሰዎች ለሰዎች የሆነ ጨዋና ትሁት ስልጣኔ መገንባት።
ሃፍረትና ይሉኝታ የሚያውቅ ማህበረሰብ መፍጠር።ሃፍረትና ይሉኝታ የለሽ ሃገር የዞምቢ ምድር ነው የሚሆነው።ሃፍረትና ይሉኝታ የአንድ ማህበረሰብ የክብር ልብሶችና ጌጦች ናቸው።ብቻም ሳይሆን ድፍን ህዝብን ለቁሙ ከመጥፋት የሚታደጉ የአለም መድሃኒቶች ናቼው።)
3)ጠንካራ ኢኮኖሚ(ጠንካራ የኢኮኖሚ ፓወር ሳንገነባ ጠንካራ የፖለቲካ ፓወር ልንገነባ አንችልም። ገንዘባችን ስለት /ዊያፓናዝ/ ማድረግ አለብን።)
4)ፈሪሀ-እግዚአብሄር(ሞራል፣ሰው መሆን፣ሰውን ማክበር፥ ሰውን መውደድ፥ ለሰው ልጆች ሃሴት መኖር-መንፈሳዊ ልእልና)
[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም]
እስከ ምፃት አማራ!
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
በማጥራትና ማብቃት ህልውናችን እናረጋግጣለን!!
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዘለቀ ዕዝ
የተሰጠ መግለጫ
ህልቆ መሳፍርት የሌለው የአማራ ህዝብ መከራና ስቃይ ያስቀጠለው ፋሽስታዊ የዓብይ አህመድ ቡድን በአማራ እና አማራነት ማንነት ላይ ያነጣጠረ ህልውናውን ፈፅሞ የማክሰም መዋቅር መር ሁለንተናዊ ጥቃት ለመከላከልና አደጋውን ለመቀልበስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አማራ ራሱን ለማትረፍ በነቂስ በፋኖ አደረጃጀ ተደራጅቶ ኢ ተገማች በሆነ ሁኔታ አስከፊውን አገዛዙ እያፈራረሰው ይገኛል።የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዘለቀ ዕዝ በሁሉም የሰሜን አማራ ቀጠና (ጎንደር) ዞኖች በመንቀሳቀስ አያሌ ስኬታማ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተግባራትን በመከወን ሰፊ ህዝብ እያስተዳደረና በርካታ ጠንካራ ሰራዊት እየመራም ይገኛል።ቢሆንም ትግሉን ከመታገል በላይ ትግሉን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ውስጠ አደረጃጀት የማጥራትና የማብቃት ተቋማዊ ንቅናቄ በማድረግ በአጭር ጊዜ ለ ድል የሚያበቃ የአመለካከት፣የተግባር እና የአሰራር ጥልቅ መግራት ተግባር መከወን አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል።ትግላችን በአንድ ወጥ ድርጅት እየተመራ አስከፊውን አገዛዝ በመገርሰስ ለተሟላ አማራው የተሟላ ድል እንዲጎናፀፍ የምናደርገውን በጎ ሚና ከማስቀጠል መሳለመሳ ከድህረ ዓብይ አህመድ መገርሰስ በኃላ የምትፀናውን ሀገር የሚበይንና የሚረከብ ሁለንተናዊ ዝግጅት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ብርቱ ስራዎችን በአፋጣኝ መከወን እንዳለብን እንረዳለን።
በእሳት ተፈትነው ያልተበገሩ ነባር አርበኞችና ወጣት አብዮተኛ ሙህራን መሪዎችን እንዲሁም ጀግና ሰራዊታችን ለተሻለ ድል ለአመርቂ ተቋማዊ አስተሳሰብና አሰራር ማብቃት የነገ ሳይሆን የዛሬ የግብር ግዴታችን መሆኑን የዕዙ ስራ አስፈፃሚ አመራር በመገምገም ግልፅ ስምሪት ተሰቷል።
በደም ዋጋ የጠራውን ዓላማና ግባችን ለመበረዝ ፣ለመጥለፍና ለማዳከም ከተቻለም በራሳቸው ፍላጎት ስር ለማስገበር የሚታትሩ የትግሉ ቁማርተኞችን እየመከትን መቆየታችን ታውቆና ታምኖ ያደረ ሀቅ ነው።
ላለፉት 20 ቀናት በተመረጡ ኮሮችና ክ/ጦሮች እንዲሁም ወረዳዎች የማጥራትና ማብቃት የሙከራ ስራዎቻችን ጀምረን የቆየን ቢሆንም በሁሉም ቀጠና በተሟላ ሁኔታ ንቅናቄውን ማስጀመር ታምኖበታል።
ስለሆነም ከዛሬ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ በማጥራትና በማብቃት ህልውናችን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት 45 ቀናት ውስጠ አደረጃጀታዊ ንቅናቄ በይፋ መጀመራችንን እያበሰርን በማጥራትና ማብቃት ተልዕኳችን የሚከተሉት አንኳር ተግባሮች የሚከወኑ መሆኑን በመረዳት ህዝባችንና ሰራዊታችን ያለሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርግልን ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።
፩ኛ...በተዘጋጁ ሰነዶች ስልጠና መስጠት ማለትም ህዝብ አስተዳደርን ፣ ፋይናንስ አሰባሰብና አስተዳደርን፣የሰራዊት ማደራጃ የተሻሻለ መመሪያ ፣ሀገር ዓቀፍና ዓ/ዓቀፍ የተመረጡ ጉዳዮች ዙሪያ ፣ እና ሌሎች መሰል የተሰናዱ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ ለመዋቅራችን አመራርና ዓባላት ስልጠና ይሰጣል፣
የአስተሳሰብና የተግባር እንዲሁም የአሰራር ወጥነት በማንበር ለተሻለ ግዳጅ ብቁና ንቁ ቁመና እንፈጥራለን፣
፪ኛ...በውስጥ መረጃ እና ማስረጃ ተመርኩዘን የጀመርነውን ሰርጎ ገብ ጥገኞች የማጥራትና የመግራት ተግባሮች በሁሉም ኮሮቻችን እስከ ታችኛው ሰራዊት ይፈፀማሉ።እንደ ህዝብ ህልው ሁኖ ለመትረፍ በምናደርገው መራር ትግል ተጠልለው መስዕዋትነታችን ለግል ማንኛውም ጉዳያቸው በማዋል ተመሳስለው የተሰማሩ ወንበዴዎችን ፣ ከአረመኔው ጠላት ትስስር ያላቸው የዘመናችን የዲናር ተመንዛሪዎች መርምረን እንለያለን መንጥረን እናጠራለን።
፫ኛ... ከውስጥም ሆነ ከውጭ ትግሉን ለማዳከም የተዘረጉ ኔትወርኮች ይበጣጠሳሉ።አፍራሽ ደላሎችና ቅጥረኛ ሳይበረኞች የካብ ውስጥ እባቦች የትግሉ ዕዳና ፍዳ ሁነው እንዳይቀጥሉ በጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄያችን ቅድሚያ ትኩረት ከተሰጡት ተግባሮቻችን መካከል ይጠቀሳሉ።
፬ኛ...በቅርቡ ማስረሻ ሰጤ የተባለ ከሌላ ድርጅት የተባረረ ግለሰብ ከአገዛዙ ጋር ሁኖ በበርካታ ሚዲያ ፋኖን ወክሎ ተደራድሮ የሰላም ስምምነት እንደተፈራረመ የፋኖ ሰራዊት በየ አካባቢው ትግሉን ትቶ እንዲገባ እየተሰራጨ ያለው ወሬ ድርጅታችን እና ሰራዊታችን እንዲሁም እዛችን የማይመለከት የግለሰቡና የአጭበርባሪው አረመኒያዊ አገዛዝ የመጨረሻ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ተገንዝበን ተልዕኳችን ላይ ብቻ ትኩረት እንድናደርግ መልዕክት እናስተላልፋለን።
፭ኛ...ጨፍጫፊው ስርዓት በንፁሃን ወገናችን ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ የፋኖ ዘመድ ወይም ወዳጅ አላችሁ በማለት ንፁሃን ወገናችን ያለ ጥፋት በማሰርና በማፈን እያንገላታና ሰብዓዊ መደራደሪያ እያደረገ ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል።ንብረት ማውደም፣መዝረፍ እንዲሁም ከቀዬ የማፈናቀል የሰብዓዊ ወንጀሎችን እየፈፀመ የሚገኝ መሆኑ ታውቆ የሚመለከታችሁ ሀገር በቀልም ሆነ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ማህበራት ግለሰቦችና ሚዲያዎች ጉዳዩን በአንክሮ ትከታተሉ ዘንድ እያስጨበጥን ለሚፈፀሙ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ተመጣጣኝ አፀፋዊ ርምጃ እየወሰድን እንደቆየንና አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናሳውቃለን።
ውድ ወገናችን የሰራዊታችን ዓባላትና አመራሮች እንዲሁም የትግሉ አጋሮች በሙሉ "ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄ "በሚል መሪ ቃል የጀመርነው ንቅናቄ
ከማብቃት በላይ ፤ከማታገልም በላይ፤ ከመታገልም በላይ፤ትግላችን የምንጠብቅበት የእርምት ክዋኔዎችን ገቢራዊ የምናደርግበት በመሆኑ ከወዲሁ ተረድታችሁና አስረድታችሁ ከጎናችን እንድትቆሙ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ዘመቻ ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጎንደር /አማራ/ኢትዮጵያ
የምርኮኛው አስር አለቀ ብርሃኑ ጁላ ጦር በየእለቱ እየከዳ ፤ ትጥቁን እስከ ተተኳሹ ለፋኖ ማስረከብ ላይ ይገኛል።
ስለሆነም:-
1. ያሬድ አምባዬ ከ6ኛ ኮር 32ክ/ጦር ሻለቃ 4 ሰ/ክላሽ እና
2. ሙሉ አያሌው ከ6ኛ ኮር 32 ክ/ጦር ሻለቃ 4 ታጣፊ ክላሽ ከነመሰል ጥይቶቻቸው #በመያዝ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር በላይ ዘለቀ ሻለቃን ተቀላቅለዋል።
#የእናቶችህን የእህቶቻችንን ጡት #የሚቆ*ርጥ የወንድሞቻችንን ብልት #የሚቆ*ርጥ ስርዓት የምትጠብቁ ወንድሞቻችንን በፍጥነት #መክዳት እንደሚኖርባችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፤
ኅዳር 30/ 2018 ዓ/ም
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ዘጋርድያንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስላወጡት የፋኖ ተጋድሎና በአማራ ሕዝብ ላይ ስለሚደረገው የዘር ማጥፋት ዘገባ ማብራሪያ ሰጠ።
አርበኛ አስረስ ማረ ከፍሪ ፕሬስ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ ፋኖ ትግልና ወቅታዊ አሰላለፎች እንዲሁም ስለ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባና ትኩረት ዝርዝር ነገር ተናግሯል።
አርበኛ አስረስ አፋብኃ ከተመሠረተ ጀምሮ ስላለው ትግልና የአካሄድ ክፍተቶች መስተካከልን አውስቶ ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዳገኘም ጨምሮ ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ፋኖ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ዕውቅና እያገኘ ዲፕሎማሲያዊ፣ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት አሳይቷል ነው ያለቅ አርበኛ አስረስ።
አርበኛ አስረስ ስለሰሜኑ ጦርነትና ስለፋኖ የጦርነት ተሳትፎ ተጠይቆ በሰጠው ማብራሪያ፡ ፋኖ በጦርነቱ ተሳትፏል፤ ነገር ግን ያኔ የነበረው ፋኖ ነባሩ የአማራ ሕዝብ አደራጃጀት ሲሆን ራሱን ለመከላከል ሕልውናውን ለማስጠበቅ ያደረገው እንጂ ዐቢይ አሕመድን ለመታደግ ያደረገው አይደለም ብሏል።
እንዲሁም ዘጋርድያን ጋዜጣ ፋኖ ከዐቢይ አሕመድ ጋር ተሰልፎ በትግራይ ላይ ጀኖሳይድ ፈጽሟል ብሎ የዘገበው የተሳሳተ ነው፣ አሁን ያሉት የፋኖ አመራሮችና አደረጃጀቶችን ተሳትፈዋል መባሉም ውሸት ነው ሲልም ጨምሮ ገልጿል። አሁን ያለው ፋኖ በተለየ አስተሳሰብና አደረጃጀት ለትግል የወጣ ነውም ነው ያለው።
አርበኛ አስረስ ማረ ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነት በሰጠው ምላሽ፡ አማራ ያልተሳተፈበትና ያላመነበት ስምምነት ስለነበረ አልተቀበልነውም ያለ ሲሆን፤ ያኔ አማራ ተሳታፊ ቢሆን ኖሮ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ይኖሩ ነበር ብሏል። ሆኖም ግን የፋኖ የትግል መነሻ የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው ተብሎ የሚነገረው የተሳሳተ ትርክት ነው። በእርግጥ ዐቢይ አሕመድ በአማራ ላይ ጦርነት ለመጀመር ሲፈልግ አማራን አግልሎ ያደረገው ስምምነት ነውም ነው ያለው።
አስረስ ማረ ቀጥሎም አማራ ላይ ስለተፈጸመው ዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂነት ሲያብራራ፤ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት የፈጸመ ግለሰብም ይሁን ቡድን በዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሕግ የሚጠየቅ ይሆናል። በተለይ አማራ ብዙም በማይኖርበት አካባቢ የሚፈጸሙ የዘር ማጥፋቶች ሁሉም በወንጀሉ ልክ እንደሚጠየቅ በዓለም አቀፉ ሕግ ተደንግጓል ብሏል።
የፋኖ ሠራዊት 20ሺ ብቻ ነው ብሎ ዘጋርድያን የዘገበው የተሳሳተ ነው ያለ ሲሆን፤ ዘገባው ላይ ፋኖ ብዙ ቀጠናዎችን ሸፍኗል ብሎ ተናግሮ ግን ደግሞ በቁጥር አሳንሶ ማቅረቡ የተምታታ ሪፖርት ነው ብሏል አርበኛ አስረስ።
እንዲሁም ኤርትራ ፋኖዎችን ታሰለጥናለች ተብሎ በዘጋርድያን የተዘገበው መሠረተ ቢስ ነው። የፋኖ ተጋድሎ በትልልቅ ከተሞች የተጀመረ ብዙ ዋጋ የተከፈለበት እንጂ በሥልጠና የመጣ ወይም የተለየ ቴክኒካል ድጋፍ አልተደረገለትም ነው ያለው። በተጨማሪም ፋኖ የዐፄዎችን ዘመን ሊመልስ ነው ብሎም መዘገቡ ስሕተት ሲሆን፤ የትግላችን መነሻ ባለፉት 80 ዓመታት የደረሰብንን በደል ለማስቀረትና አሐዳዊ የሚለውን ትርክት ለማስቀረት ፍትሕ ለማግኘት እንጂ ሌላ ዓለማ የለንም ነው ያለው። እንዲሁም አማራ ጨቋኝ ነው፣ የዐፄዎቹ ዘር እየተባላን የሚደርስብንን መከራ ለማስቀረትና ፍትሐዊ ሥርዓት ለመፍጠር ነው ብሏል።
በተጨማሪም የተፈጠሩ የተሳሳቱ ትርክቶች ዐፄዎቹን የሚገልጽ ሳይሆን የፈጠራ ወሬዎች ናቸው እንጂ ዐፄዎቹ በዘመናቸው የውስጥ ሰላማችንን ብቻ ሳይሆን የውጭ ወረራንም ሲከላከሉ የቆዩ ናቸው። ፋኖ የሚጋደለው ሌሎችን ለመጠቅለልና ሁሉንም ለመበየን ሳይሆን ሕልውናውን ለማስከበር ነው። ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር የጋራ ቤት ለመፍጠርም ነው ትግላችን ብሏል አርበኛው። ሌላው ዘጋርድያንም ሆነ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት የተሳሳተ ሪፖርትና ዘገባ በድጋሜ እንዳያወጡ ትልቅ ሥራ ይጠበቅብናል ብሏል።
የአማራ ትግልና ሕዝቡ እየከፈለው ያለው ዋጋ ጆሮ የተነፈገውና መሠራት ያለበት ሥራ ያልተሠራበት ነው። የአማራ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ጨምሮ እየተፈናቀለ ቤት አልባና ተሳዳጅ ሆኗል። በዚህም ዐቢይ አሕመድና ቡድኑ ብዙ ማዕቀብ ሊጣልበት የሚገባ ሰው የነበረ ነው። አሁንም መንገዶችን በመዝጋት ሕክምናና የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ፣ የደረሰን አዝመራም በማቃጠልና ሠፈርን በድሮንና በከባድ መሣሪያ በማውደም ላይ ያለው መንግሥት መር ሽብርተኝነት እንዲቆም ሁሉም አማራ ሊነሣ ይገባል ነው ያለው አርበኛ አስረስ።
አርበኛ አስረስ "ፋኖ የምሥራቅ አፍሪካ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኗል" ለሚለው ተደጋጋሚ ንግግሩ ሲያብራራም፤ ይኸን ቃል የተናገርሁት የዛሬ ዓመት ሲሆን አሁን ግን ሁሉም የሚናገረውና የተረዳው ሐሳብ ሆኗል ብሏል።
አክሎም፤ የአማራ ትግል ከጓዳ ወደ አደባባይ ወጥቷልም ሲል፤ ቀጠናውን የሚመጥን ተቋም መፍጠርና አደረጃጀት መሥራት ይጠበቃል ነው ያለው።
ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ላይ ጦርነት ይከፍታል ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄም አርበኛው ሲመልስ፤ ዐቢይ አሕመድ አሁን ዐቅም ስለሌለው ጦርነት አይከፍትም ጦሩን በትነነዋል ሲል ገልጿል። እንዲሁም ዐቢይ አሕመድ በራሱ ዐቅዶ የሚሠራው የወደብም ሆነ የቀይ ባሕር አጀንዳ የለውም እያስጮኸው ያለው የላኪዎቹን አጀንዳና ዓላማ ነው። ሆኖም አንድም ጥይት አይተኩስም ሲል ነው አርበኛ አስረስ ማረ ማብራሪያውን ያጠቃለለው።
በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም 2ኛ ኮር አመራሮችን ይፋ አደረገ
=============
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም ኮር 2ኛ ኮር ተሀድሶ በማካሄድ የኮሩ አመራሮችን ይፋ አድርጓል::
የከሰም 2ኛ ኮር ከተመሰረተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሀድሶ ያካሄደው ይህ ኮር የኮር አመራሮችን የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል ረዳት እና የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ማርከው መንግስቴ በተገኙበት ይፋ አድርጓል::
በዚሁ መሰረት የከሰም 2ኛው ኮር አመራሮች
1ኛ. አርበኛ መቶ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ ዋና መሪ
2ኛ .አርበኛ ደጉ ተሥፋዬ ድርጂት ጉዳዮች ኃላፊ
3ኛ. አርበኛ እንዳልካቸው ግርማ የአሥተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ
4ኛ.አርበኛ ሃምሳ አለቃ ጎሽመው ኃይሌ ወታደራዊ አዛዥ
5ኛ.አርበኛ እሸቱ ተ/ሚካኤል ም/አዛዥ ለኦፖሬሽናል።
6ኛ. አርበኛ ገረመው ታደሰ ም/አዛዥ ለአሥተዳደር
7ኛ.አርበኛ ፍቃደ ወርቁ ም/አዛዥ ለሎጀሥቲክ
8ኛ.አርበኛ ወርቁ ደርቤ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
9ኛ . አርበኛ ምክሩ ብዙነህ የፋይናንሥ ኃላፊ
10.አርበኛ አሥር አለቃ ሙልጌታ ፍቅሬ ዘመቻ መምሪያ
11ኛ.አርበኛ ወርቁ ሽመልሥ ምክትል ዘመቻ መምሪያ
12ኛ.አርበኛ ይታገሥ ጌታሁን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
13ኛ.ትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ----------
14ኛ. አርበኛ ሳሙኤል ፀጋዬ አደረጃጄት ዘርፍ ኃላፊ
15ኛ.አርበኛ ኃይሌ መሥፍን ኦዲት እና ቁጥጥር ኃላፊ
16ኛ.አርበኛ ይታገሥ ተሾመ ህግ ክፍል
17ኛ.አርበኛ ኮማንደር ነጋሽ አሠፋ ህግ ክፍል
18ኛ.አርበኛ ብርሃነ ቀፀላ ህግ ክፍል ኃላፊ
19ኛ.አርበኛ ሃምሳ አለቃ ሰለሞን አድነው ሥልጠናና ክህሎት ኃላፊ
20ኛ. አርበኛ እንግዳ በላይነህ ሃብት አሰባሳቢ ኃላፊ
21ኛ.አርበኛ አሸናፊ ብርሃኑ ፐረሶኔል
22ኛ አርበኛ ደመቀ ሥለሺ የኮር ፀኃፊ
23ኛ.አርበኛ ዘላለም ወርቅነህ ኦርዲናንሥ
24ኛ አርበኛ ክትነህ ሽፈራ ኦዲትና ቁጥጥር
25ኛ .አርበኛ አባይ ተሾመ ግዥ ክፍል
26ኛ.መረጃና ደህንነት ---------------
27ኛ አርበኛተፈሪ ሀይሉ የህዝብ ደህንነትና ፀጥታ ኃላፊ
28ኛ.አርበኛ አይናለም ዘረጋው ሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ
29ኛ.አርበኛ ተመሥገን ባረጋ ህክምና ክፍል
30ኛ.አርበኛ አለማዬሁ ጌታነህ ኦዲትና ቁጥጥር
31ኛ.አርበኛ የሺጌታ ተገኝ ም/ ፋይናንሥ ኃላፊ
32ኛ. አርበኛ ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ም/ሥለጠናና ክህሎት
33ኛ.አርበኛ ጋዜጠኛ አበባዬሁ ሰይፊ ሪፖርተር
34ኛ .አርበኛ ሰለሞን ገብሩ ባዶ አምሥት መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።
እነዚህ አመራሮች የተሰጣቸውን ሀላፊነት ተቀብለው ወደ ስራ የገቡ መሆናቸውንም የአማራ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና 2ኛ ከሰም ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሶናል::
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
#የደጅ_አዝማች_በላይ_ዘለቀ_እና_የሽፈራው_ገርባው_ልጆች_ከአገዛዙ_አረመኔዊ_ሰራዊት_ጋር_ሲፋለሙ_ውለዋል።
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ፣ 5ኛ ሬጅመንት እና የክፍለ ጦሩ ቃኝና መሀንዲስ በሸበል በርንታ የዕዱኃ ከተማ ት/ቤት፣ ገዳያሱ ቀበሌ እና እነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ከባድ ውጊያ ሲያካሂዱ ውለዋል።
201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ በየዕዱኃ ዙሪያ ገዳያሱ ቀበሌ የአገዛዙ ሰራዊትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርግ በቢቸና ከተማ የሚገኘውን የአረመኔው ሰራዊት ስቦ በማውጣት እስከ ጮለሚት ማርያም አፋፍ እና ወይናም ድርስ ከባድ ተገሃድሎ በማድርግ የጠላትን ሀይል ቅስሙን ሰብሯል።
በሁለቱም ቀጠና በተደረገው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ ክንዳቸው እንደ እሳት የሚፋጀው የ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላት በአገዛዙ አርመኔ ሰራዊት አባላት ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል። በሸበል በርንታ የዕዱኃ ከተማ ት/ቤት፣ ገዳያሱ ቀበሌ እና ቢቸና ከተማ አካባቢ በተደረገው ውጊያ:-
➣ 9 የአገዛዙ አባላት ሲደመሰሱ
➣ከ8 በላይ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል
➣አገዛዙ ይጠቀምበት የነበረው አንድ ተሽከርካሪ ከአገዛዙ የሰው ሀይል ጋር ከቢቸና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው #የቀጋን ሰፈር ከጥቅም ውጭ ተደርጓል።
➣በየዕዱኃ ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ ኃይል በተሰጠው ስምሪት አማካኝነት በሀሳብና በተሰጣቸው ግዳጅ ስምምነት ማጣታቸውንና መግባባት ባለመቻላቸው ምክንያት በስሜት መንፈስ ሲተራመሱ 1 የአገዛዙ የጠላት ኃይል በእራሱ ጥይት መቁሰሉን እና ከጎኑ ያለውን 1 ጓዱንም አብሮ ቁስለኛ ማድረጉን አረጋግጠናል። የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በአንሸንፕ ቀበሌ:-
➣ወ/ሮ ይርገድ አባተ
➣አርሶ አደር አቶ ውበቱ ሀብታሙ በአሰቃቂ ሁኔታ በአገዛዙ ተገድለዋል።
➣ህፃን ማርየ አባት የገዛዙ አረሜኔዊ ሰራዊት ከባድ ቁስለኛ አድርጓታል። በፋኖ በትር ክፍኛ የተመተው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በአርሶ አደሮች ቤት ውስጥ እየገባ በግድግዳ ላይ የተሰቀሉ የወገብ ዝናሮች እና የአርሶ አደሩ 5 አካባቢ መሳሪያ
1.አቶ አሸናፊ አባተ ቴሌ ጠባቂ
2.አርሶ አደር ወዳጄ በለጠ
3.አርሶ አደር ከፋለ ወዳጄ
4.አርሶ አደር አስከጃይ መለሰ
5.ቄስ ይበልጣል አስናቀ የተባሉ አርሶ አደሮችን ከቤታቸው አስገድዶ የዕዱኃ ከተማ በመውሰድ ፋኖን ማሪኪያለሁ ለማለት የውሸት ፕሮፖጋንዳ እየሰራ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ
+6
ከውጊያው ጎን ለጎን የህዝብ መድርኮች እና ማህበረሰቡን የማደራጃት እና መልሶ መገንባት ስራ እየተሰራ ይገኛል
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
በቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 74ኛ እንዲሁም 54ኛ ክፍለጦር በሸበል በረንታ በጎንቻ ሲሶ እነብሴ እና ቢቡኝ ወረዳ የማህበረሰብ እና የሲቪል ሰርቫንቱን የወረዳው ጊ/መንግስት አመራሮች ውይይት አካሂደዋል።
በውይይት መድረኩ :-
➣የቀበሌ ሊቀመንበር
➣የቀበሌ ፀሀፊ
➣የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ
➣የቀበሌ ገቢና ሀብት አሰባሰብ
➣የቀበሌ ፀጥታና ምክትል
➣የቀበሌ የወጣት ጉዳይ
➣የቀበሌ የጎጥ ሽማግሌ
➣የቀበሌ የሀገር ሽማግሌ በቀበሌ (
➣ህዝብ ያመነባቸው አስታራቂ የሀገር ሽማግሌዎች ተዋቅረዋል።
የህዝባዊ ውይይት መድርኩን የ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች በቅርብ ቀን ድርጅቱ ያወረደውን አደረጃጀት በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት በማድርግ ማብራሪያ ሰተዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
አፋብሐ ቢዛሞ ዕዝ ብረሃኑ ምስጋናው መብረቁ ክፍለ ጦር እና ይበልጣል መኮነን አድስ አለም ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን ኪረሙ ወረዳን ተቆጣጥረዋል
ዝርዝሩን በረፋዱ የዜና ሰከታችን ይጠብቁን
ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክ/ጦር
ገ/መሥቀል ብርጌድ
ጣይቱ ሻለቃ
ገና መጫወቻ ከተማ 02 ቦታዎች ላይ በወሰደው የታቀደ የደፈጣ ጥቃት ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት።
+2
ብራቮ አፋሮች
የብልፅግና ግፍ የሰለቸዉ የአፋር ወጣት ጥራኝ ጫካዉ ብሎ ተደራጅቷል
የአማራ ፋኖ አብይ ላይ ካኮረፈ የትኛዉም ሀይል ጋር በጥምረት የአገዛዙን ቀ*ብር ማፋጠን አለበት
ከ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የተሰጠ የማስጠንቀቂያ መልዕክት!
እንደሚታወቀው ጸረ አማራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥፋት አውጆ ወደ ተግባር በመግባት አያሌ አማራውያንን በእግረኛና በአየር ኃይል መጨፍጨፍ፣ማፈናቀልና ሀብት ንብረታቸውን ማወደምና መዝረፍ ከጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ለዚህ እኩይ ተግባር ማስፈጸሚያም በብድርና በልመና ከውጭ ሀገራት ከሚቀበለው ጥሬ ገንዘብና የጦር መሳሪያ በተጨማሪ በሀገር የሚገኙ የመሰረተ ልማትና የተቋማትን ካፒታል ወደ ራሱ ካዝና በመገልበጥ ተቋማቱ እንዲራቆቱ በማድረግ ምንም አይነት ተግባራዊ አገልግሎት እንዳይኖራቸው ከማድረጉም በላይ ገንዘቡን የአምሐራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ለሚውሉ መሳሪያዎች መግዣና ለጥፋት ሠራዊቱ ደሞዝ እያዋለ ይገኛል።
ከሰሞኑሞ ይህ ሥርዓት የጤና መድኅንና የትምሕርት አገልግሎት ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ክፍያ እንዲሰበሰብና እንዲጀመር መምሪያ መስጠቱ ይታወቃል።
በመሆኑም የ14ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች በሚከተሉት ምክንያቶች እነዚህን ተግባራት ማከናወን አይቻልም።
1. ትምሕርት ማስጀመርን በተመለከተ፦
ድርጅታችን አፋብኃ በጉዳዩ ላዩ አስቀድሞ አውጥቶት ከነበረው መግለጫ በተለየ መልኩ ትምሕርት እንዲጀመር የሚፈቅድ መምሪያ እስካላወረደ ድረስ ምንም አይነት የትምሕርት እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም።
2. የጤና መድኅን ክፍያን በተመለከተ፦
ከላይ እንደተጠቀሰው አገዛዙ ከዘርፉ የሚሰበሰውን ገንዘብ ለታለመለት ተግባር የማያውለው ከመሆኑም በላይ ገቢውን ለሕዝባችን መጨፍጨፊያ መስሪያ ግዥና ለሚሊሻ፣ ለአድማ ብተናና ለፖሊስ ደሞዝ ክፍያ የሚያውለው በመሆኑ ማሕበረሰባችን በከንቱ መበዝበዝ ስለሌለበት የጤና መድኅን ክፍያ መክፈልም ሆነ ማስከፈል አይቻልም።
ይህን መምሪያ ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ለሚወሰድበት እርምጃ ኃላፊነቱን ራሱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ድል ለአማራ ፋኖ!
14ኛ ክፍለ ጦር
#አንቀጠቀጥነው_አደል😂😂
እንድ ትንኝ በዝናብ ሰዓት በዝሆን ጀሮ በመግባት ትጠለላለች እናም ያ የተጠለለችበት ዝሆን ጉዞ ላይ ነበረና ድልድይ ሲሻገር ድልድዩ ንቅናቄ መፍጠሩን የተመለከተችዋ #ትንኝ ። አንቀጠቀጥነው_አደል ብላ ለራሷ ድርሻ (ክሬዲት) ለመስጠት ሞከረች ይባላል😂
ይህንን ታሪካ ያመጣነው ልክ እንደ ትንኟ እድል ቀንቷቸው ሰርገው በመግባት ትግላችንን የጊዜ ማሳለፊያ ፣ የሀብት ማካበቻ ወዘተ አድርገው የቆዩ ጥቁር አማራዎች ለትግሉ #ቁልፍ_ሰው እድርገው ያለ እነሱ ትግሉ የማይራመድ ይመስላቸዋል፣ ግን ራሳቸውን ያዋርዳሉ እንጂ የኛን ድል ማስቆም አይችሉም! ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ከመጀመሪያውም ፈተናዎቻችን ነበሩ!!
ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለም ፣ ማንም መጣም ሆነ ሄደ ድል ከማድረግ የሚያስቆመን ምድራዊ ኃይል የለም!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘረያቆብ ኮር አናብስቶች በከፊል!
29/ዐ3/2018 ዓ.ም
"አርበኛ እና ባንዳ"
"አርበኛ ማለት ጀግና ቆራጥ ልበ ሙሉ፣ እደሻማ እየቀለጠ እንደ ጨረቃ እና ፀሀይ ብርሀን የሚሰጥ ነው።"
"ባንዳ ማለት እንደ አሀያ፣ ፈረስ እና አሳማ በልቶ የማይጠግብ እብርት የለሽ መስክ እሚያጠፋ (ትውልድ እሚያጠፋ) እኔ እና ለእኔ ብቻ የሚል በሆዱ የሚገዛ ሀገር እና ትውልድ የሚሸጥ አሽከር ማለት ሲሆን እሱም ሆነ የሱ ትውልድ ነቀርሳ ነው።"
ነቀርሳን ቆርጠን ካልጣልነው፣ ይስፋፋል ያጠፋል። የአሁኑ የአማራ ትግል ለየት የሚያደርገው አርበኛችንን እንደ አይን ብሌናችን ጠብቀን የምናነግስ ሲሆን ባንዳን እንደነቀርሳ ቆርጠን በመጣል "በቀይ እና በጥቁር መዝገብ" መዝግበን የምንይዝበት ጌዜ ነው።
የአማራ ህዝብ ፈጣሪውን የሚፈራ እና ሰው እሚያከብር ግብረ ገብ ህዝብ ነው። ይሁን እንጂ በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ በሚኖረው የአማራ ህዝብ ላይ በየግዜው መልኩን እና ስሙን እየቀየረ ስልታዊ እና ግልፅ በሆነ መንገድ በህይወት እና በአካል እንዲሁም በቁስ ውድመት ሲካሄድበት የነበረ እና እየተካሄደ ያለበት ህዝብ ነው ።በአማራ ህዝብ ላይ በጅምላ እና በተናጠል፣ ጊዜ ወይም ቦታ ሳይመርጥ፣ በመኖሪያ ቤት፣በስራ ቦታ፣በጉዞ ላይ፣ በእስር ቤት (ማረሚያ ቤት ህጋዊ መንገድ ስለሆነ እስር ቤት ይባልልኝ) የሰውን ልጅ የሚያክል ፍጡር እድሜ፣ጾታን እና ሀይማኖትን ሳይለይ ቤታቸው ውስጥ ስለተቃጠሉት፣በመኪና ተጎትተው ግፍ ስለተፈፀመባቸው፣ሆዳቸው ተቀዶ ሽል ስለወጣው እናቶች፣አንገታቸው እና ጡታቸው ስለተቆረጠው ወንድም እና እህቶች፣ በግፍ ስለተገደሉት የሀይማኖት አባቶች፣ መነኩሳት እና ሽወች ፣ ስለወደመው የሀይማኖት ተቋም እና ገዳማት የሚደረገው የህልውና ትግል ነው።
ስለሆነም አማራን ከምድረ ገፅ እዳይጠፋ ቀድመው በነቁ እና ባነቁን የዘመናችን አርበኞች አማካኝነት እሚካሄደው የህልውና ትግል ሁሉም አማራ እና ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ እሚደግፈው ትግል ነው።
የማፍያ ቡድኖች የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈፀም እና እብርት የለሽ ሆዳቸውን ለመሙላት የአማራን የህልውና ትግል እና ለውጥ ፈላጊ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ መደራደሪያ ተጠቅመውበታል።በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዋች በመሽሎክሎክ ድርጅት ሲመሰርቱ እና ሲያፈርሱ የነበሩ ግለሰብ እና ቡድኖች እውነተኛ ፋኖ ሲሰባሰብ እና ሲመክር ተልኮአቸው እዳልተሳካ በመረዳት የነበራቸውን የውስጥ ማንነት በግልፅ እና በገሀድ አሳይተውናል።
ፋኖ ፀሀይ እና ብርድ፣ዱር እና ገደል ፣እርሀብ እና ጥም ተቋቁሟ ለእኔ እና ለአንተ ወይም ለአንቺ ህልውና የሚታገል እና የሚያታግል፣ የማረከውን የጥላት ሀይል ተከባክቦ አብልቶ አጠጥቶ ወታደራዊ ስራዕትን በጠበቀ መልኩ ለቀይ መስቀል የሚያስረክብ፣ በተቆጣጠረው አካባቢ ባንክ እና ፍይናንስን ጠብቆ የሚይዝ የህዝብ ዘብ አደራ ጠባቂ ቅድመ-መንግስት ነው።
ይሁን እንጂ አንድ አንድ ባንዳዋች አንዴ ፋኖ ፣ አንዴ ብልፅግና በመዝለል ፋኖ ውስጥ ሆነው እብርት የለሽ ሆዳቸው መሙላት እደማይቻል የተረዱ ድፍን ቅል ጭንቅላት ያላቸው የፋኖን (የአማራን ህዝብ) ስም ተገቢ ባልሆነ እና በማይገልፀው መልኩ ስም ሲያጠፉ ሰምተናል።
ስለሆነም እነዚህን መሰል ነቀርሳ ባንዳዎች ጀሮ ሊሰጣቸው አይገባም።
+2
በመጨረሻም እጅ ሰተው ተማርከዋል!!
የወረዳው 10 ሚሊሻዎች ተማረኩ...
የአፋብኀ በላይ ዕዝ ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር
ሰሜን ብርቅዬ ክ/ጦር ራስ ገብሬ ብርጌድ በሰሜን ቀጠና በዋግ ዝቋላ ወረዳ ጀብድ ፈፀመች ።
ብርጌዷ በተጠና ኦፕሬሽን ህዳር 28/2018 ዓም የሎሌውና ባንዳው ብአዴን የጀርባ አጥንት የሆኑትን ቅጥረኛ ሚሊሻዎችን በጥይት ቆልታ ማርካለች።
የቀበሌ ሊቀመንበር
የፀጥታ አስተዳደር
የብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ
የወጣቶች ጉዳይን ጨምሮ 10 ምልሻዎች እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከናቸዋል።
እነዚህ ቅጥረኞች በህዝባችንና በትግላችን ላይ አያሌ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩና በተኩስ ልውውጥ ዕድለኛ ሁነው እጃቸውን ወደ ሰማይ ቀስረው የማረክናቸው ናቸው።በርካቶች በፈቃዳቸው ፈርሰው እየተቀላቀሉ ሲሆን ቀሪው ፈቃደኛ ያልሆነው ላይመለስ እየተሸኘ ይገኛል።
በላጎ ተወርዋሪ ልዩ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በላጎ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ሞቴ ከተማ ላይ ምሽግ ሰርቶ ሊቀመጥ የነበረው አድማ ብተናና ሚኒሻ ምሽጉን ሰርቶ አንድም ቀን ሳይውልና ሳያድር የበላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ በዛሬው እለት ማለትም ህዳር 29/2018 ዓ.ም ምሽጉ ድረስ ዘልቆ በመሄድ መብረቃዊ የሆነ ጥቃት አድርሶ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ቀሪው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ደሴ ከተማ ፍርጥጦ ገብቷል::
በዚክም የተገኙ መሳሪያወች ክላሽኮፍና ተተዃሽም የተገኘ ሲሆን በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበትና የደነገጠ ሲሆን የበላጎ ሻለቃ ተወርዎሪ አናብስቶቹ በሰሩት መብረቃዊ ጥቃት በድል የታጀበውና ድላቸውን እያጣጣሙ ውሏቸውን ሞቴ ከተማ ላይ አድርገዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
