ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 721
Підписники
+4524 години
+1767 днів
+1 15530 днів
Архів дописів
ሰበር የድል ዜና!!!
ስምንተኛ ቀኑን ባስቆጠረው አውደውጊያ የአገዛዙ ጥምር ጦር አከርካሪውን ተመታ!!!
የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ቱንም ክ/ጦሮች/ ካራማራ ክ/ጦ ፣ ፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ፣ ኦሜድላ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ ፣ አድዋ ክ/ጦ ከቀጠናው አስተባባሪ ግብረሀይል ጋር በመጣመር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ ሽንፈትን ማድረስ ተችሏል።
የአገዛዙ ጥምር ጦር በሁለት አቅጣጫ ከጎንደር በሻሁራ በኩል እና በቋራ በደለጎ በኩል ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ወደ ቀጠናው ገብቶ ክፉኛ ሽንፈትን ሲያስተናግድ ሰነባብቶ በትናንትናው እለት የካቲት 02/2018 ከቀኑ 8:30_12:00 ከደለጎ ተነስቶ አባድግሱ የሰፈረውንና ከሻሁራ በኩል ተነስቶ ገንገን የሰፈረውን ዘጊ ሀይል በማዘጋጀት ከአፀደማርያምና ከጎንደር ተነስቶ ወደ ቀጠናው የገባውን የአገዛዙን ጦር ቆርጦ ከበባ ውስጥ በማስገባት፤ መውጫ መግቢያ በማሳጣት በአይበገሬዎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች እና በቀጠናው ከተመደቡ የተቋም አመራሮች ጋር የተሰራው ጀብድ ጠላትን አንገት ያስደፋና በቀጠናው ያቀደውን ተግባር መፈፀም እንዳይችል ተደርጎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙት እና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ሁሉም በየመጣበት ጨለማን ተገን አድርጎ ከቀጠናው ሊወጣ ችሏል።
በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁስ ኪሳራ ከማድረስ ባሻገር የአገዛዙ የሻለቃ ማእረግ ያለው አመራር እስከወዲያኛው ተሸኝቷል።
የሞተ ሻለቃ መሪን ጨምሮ ከ10በላይ ሲሆን
የቆሰለ ከ13 በላይ ሆኗል
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ
የካቲት 03/2018
ወለጋ‼
በዬወረዳው የታጎሩትንና አድራሻቸው የጠፉትን ሳይጨምር ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ ጃቶ እስር ቤት ያለማንም ጠያቂ እዬተሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችን ቁጥር በተጨባጭ መረጃ 5552ደርሷል።
በተያያዘ ዜና መከላከያ ለቆ የሚወጣባቸው አካባቢዎች ካድሬው ቤተሰቡን እያሸሸ ይገኛል ገዳይ ልዩ ኮማንዶ የተባለው ሀይልም በያለበት ምሽግ እዬቆፈረና በከፍተኛ ሁኔታ እዬተዘጋጀ ይገኛል አመራሮቹም ቀዬቀኑ ጮማ እዬተቆረጠላቸው ይገኛል።
አማራ ገዳዩ የአባ ገዳ ጦር ቀመከላከያ እዬታጀቡ የአማራ ቤትና ንብረትን መዝረፍና ማቃጠል ዋጋ እንደሚያስከፍል ማወቂያው ስዓት ነው።
ሰበር የድል ዜና!!!
ስምንተኛ ቀኑን ባስቆጠረው አውደውጊያ የአገዛዙ ጥምር ጦር አከርካሪውን ተመታ!!!
የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ቱንም ክ/ጦሮች/ ካራማራ ክ/ጦ ፣ ፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ፣ ኦሜድላ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ ፣ አድዋ ክፍለ ጦር ከቀጠናው አስተባባሪ ግብረሀይል ጋር በመጣመር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ
በቋራ ጥቃት ሰንዝሯል።
የአገዛዙ ጥምር ጦር በሁለት አቅጣጫ ከጎንደር በሻሁራ በኩል እና በቋራ በደለጎ በኩል ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ወደ ቀጠናው ገብቶ ክፉኛ ሽንፈትን ሲያስተናግድ ሰነባብቶ በትናንትናው እለት የካቲት 02/2018 ከቀኑ 8:30_12:00 ከደለጎ ተነስቶ አባድግሱ የሰፈረውንና ከሻሁራ በኩል ተነስቶ ገንገን የሰፈረውን ዘጊ ሀይል በማዘጋጀት ከአፀደማርያምና ከጎንደር ተነስቶ ወደ ቀጠናው የገባውን የአገዛዙን ጦር ቆርጦ ከበባ ውስጥ በማስገባት፤ መውጫ መግቢያ በማሳጣት በአይበገሬዎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች እና በቀጠናው ከተመደቡ የተቋም አመራሮች ጋር የተሰራው ጀብድ ጠላትን አንገት ያስደፋና በቀጠናው ያቀደውን ተግባር መፈፀም እንዳይችል ተደርጎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙት እና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ሁሉም በየመጣበት ጨለማን ተገን አድርጎ ከቀጠናው ሊወጣ ችሏል።
የሞተ ሻለቃ መሪን ጨምሮ ከ10በላይ ሲሆን
የቆሰለ ከ13 በላይ ሆኗል
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ
የካቲት 03/2018
በደራ ሐሙሲት እና በአምበሣሜ መካከል በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ሙሉ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ሲካሄድ አድሯል።
በዚህም በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ሦስት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ከነጫኑት ሬሽንና ወታደር መማረካቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
ትንቅንቁ ዛሬ ከንጋት ጀምሮም እንደ አዲስ ተጧጡፎ ቀጥሏል።
የውቤ ልጆች "ወደቀጠናው መግባት እንጂ መውጣት የለም" በሚል ዙሪያ ገባውን ክርችም፣ ጥርቅም አድርገው በአፈሙዝ እሳት አጥረው የጠላት ኃይልን እያበራዩት ነው።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር 1ኛ ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር የካቲት 02/06/2018 ጠላትን ሁለት ቦታላይ ቆርጦ በመያዝ ከቀኑ11:00 ሰዓት እሰከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ግብፃዊት ማሪያም ላይ እና ገነት ወንዝ ላይ በተደረገ ውጊያ ጠላት አስክሬኑን እና መኪናውን እያጠባጠበ እግሬ አውጭይ ብሎ ወደ ባህር ዳር እና ሐሙሲት ከተማ ፈርጥጣል ሐሙሲት ከተማ ላይ ያለው የጠላት ሀይል የድረሱልኝ ጥሪ ወደ ባህር ዳር ልካል ከዚሁ ጎን ለጎን ወደ ባህር ዳር አቅጣጫ ምሽግ በመቆፈር ላይ ይገኛል
የተገኘ ምርኮ
ፖሊስ =1
አድማ=2
ሚኒሻ=4
የሙት ቁጥር=7
የተገኘ ትጥቅ
ክላሽ =17
አብራረው=32
መኪና
ፖትሮል=2
አቡላንስ=1
ተተካሽ ቁጥሩ ያልታወቀ የድሽቃ እና የክላሽ በብዛት ተገኝታል
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ህ/ግ ፋኖ ፍቅሩ ባየ
+1
ለወንድሞቻችን አድማ ብተና፣ሚኒሻ፣ፖሊስ እና ሌሎችንም ጨምሮ እርስ በእርስ ማጋ*ጨት፣ማጠ*ፋፋት የጭ**ራቁ የአብይን እቅድ ከምታስ*ፈፅሙ በሰላማዊ መንገድ ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ አማራዊ ጥሪየን አስተላልፋለሁ!!
#መደማመጥ
#መናበብ
#ማስተዋል
#ማቀፍ
ጊዜ ለኩሉ!!
"ከቀረ የዘገዬ ይሻላል" !
በሁሉም ቀጠናዎች ያሉ የአማራ ባንዳዎች (አድማ ብተናና ሚሊሻ) ዘግይቶም ቢሆን የኦሮሙማ ቁማር የገባቸው ይመስላል።
ለሽምግልና 3 ቄስና ሼህ መላክ በቂ ሆኖ እያለ የገዳም መነኮሳትንና ባህታውያንን ምንም በሌሉበት አማልዱን እያሉ መሆኑ እየተሰማ ነው።
እኔ እንደምረዳው በቃ ከእናንተ የሚጠበቀው አንድም logisticsና ትጥቅ ጠላት ካምፕ ላይ እንዳይቀር አድርጋችሁ የቻላችሁትን ይዛችሁ የተረፈውን በሙሉ አቃጥላችሁ ብትወጡ አፋብን ምህረት አድርጎ የሚቀበላችሁ ይመስለኛልና ይሄን ብታደርጉ ይበጃችኋል።
እንዳለኝ መረጃ ወረታ ኮሌጅ ላይ የነበራችሁ የደቡብ ጎንደር ዞን ከ2000 በላይ ፓራ-ኮማንዶ ሰልጣኞች ግን ይዛችሁ የወጣችሁት logistics ከብዛታችሁ ጋር ሲነፃፀር አናሳ ነው፤ መስተካከል አለበት። ሆኖም ግን ጥሩ ጅምር ነው።
ከዚህ በኋላ ዲሽቃ ፣ ብሬንና ሞርተር ይዞ መውጣት እንጅ ክላሽ ከፋኖም ተርፎ በየመጋዝኑ ተከማችቶ ነው ያለው።
ስለሆነም እጅ ለመስጠት በጭራሽ አታቅማሙ ህይወታችሁን አትርፉ፤ ትናንት በጓዶቻችሁ ላይ የተወሰደው የማያዳግም እርምጃ ትምህርት ይሁናችሁ።
ድል ለአፋብን !
ውድ የፍኖተ-አማራ ሚዲያ ተከታታዮች እንዲሁም ታጋይና ደጋፊዎች በሙሉ በእያላችሁበት ሁላችሁም ሰላማችሁ ይብዛ እናልኩኝ ከግንባር ሁነን ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን ጎልጉሎ በማውጣት ግንባር ቀደም ሆናል። ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንካችን ጆይን ሸር በማድርግ ለመላው አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ ከልብ እያመሰገን ቻናላችን ይወዳጁን!! አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
♦️ የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ሃገር እመራለሁ ብሎ
በትረ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ያልፈጸመው መከራና ግፍ የለም።
ሰዎች ሃብትና ንብረት ካፈሩበት ፣ ወልደው ከኳሉበት ቀያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል ተዘርፏል አልያም ከግፍ ላይ ግፍ ተጨምሮ ወደ እስር ቤት ተወስደው ታሰረዋል።
ለዓመታት በተሰራው ስርዓት መር ግፍና መከራ የአማራ ፋኖ ትግል ተምጦ ተወለደ።
ይህ ትግል ይወለድ ዘንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በርካታ መስዋእትነትን ከፍለዋል።
ተምጦ ከተወለደም በኋላ በትግሉ ሜዳ ላይ ይህ ጽሁፍ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ክቡር የህይወት መስዋእትነት የሚከፍሉ ጀግና የአማራ ልጆች ቁጥራቸው እልፍ አእላፍ ናቸው።
የትግሉ ደጋፊ ናችሁ ብሎ አገዛዙ የፈረጃቸውን የአማራ ተወላጆች አስሯል ፤ ሃብት ንብረታቸውን አውድሟል ፣ ዘርፏል በስተመጨረሻም ቤተሰብ እንዲበተን አድርጓል።
♦️ የዚህ ግፍ ቀማሽ ከሆኑት መካከል በምስራቅ በለሳ ጓህላ ከተማ የሆቴል ፣ የመዝናኛና የአልጋ አገልግሎት ለአመታት በመስጠት በቱሪዝም መስኩ በኩል በወረዳው ከፍ ሲልም በአማራ ክልል ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያበረክት የነበረው የአርበኛ ደሞዝ ጀግናው ሃብት የሆነው ሸዋየ ሆቴል በወረዳው የብልጽግና አመራሮች ቀጥታ ትእዛዝ ተዘርፎ ፖሊስ ጣቢያ ተሰርቶበታል ፣ ወድሟል እንዲሁም በበቀል በትር እንዳልነበር ሆኗል።
♦️ መውሰድ ያልቻሉትን አውድመው ፣ ዘርፈው ከወሰዷቸው ጠቅላላ ቁሳቁሶች መካከል
1 --15 አልጋ እስከ ሙሉ ፍራሽ ፣ አንሶላና ትራስ
2 -- 2 የመብራት ጀኔሬተር
3 --124 የቢራ ካሳ እስከ ውሃው
4 --28 የለስላሳ ካሳ እስከ ውሃው
5 --65 የኘላስቲክ ወንበር
6 --26 የኘላስቲክ ጠረጴዛ
7 -- አንድ ቤት ሙሉ ሶፋ
8 ---35 ሺ ብር የፈጀ ቡፌ ወስደዋል 1ዱን ግን ሰብረውት ሂደዋል።
9 --1 የሻይ ማሽን
10 --ጠቅላላ ሙሉ የቤት እቃ
11 --65 የቤት ቆርቆሮ ነቅለው በመውሰድ ፖሊስ ጣቢያ ሰርተውበታል።
12 -- 2 ትልልቅ ሁለት ተከፋች የቤት ላሜራ በሮች
13 --50 የመስኮትና የበር ላሜራዎችን ነቅሎ በመዝረፍ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ እንዲቀመጡ ተደርገዋል።
14 -- 5 ሺ ሊትር የሚይዝ ሮቶ መውሰድ አልችል ሲሉ በጥይት በመደብደብ ከጥቅም ውጭ አድገውታል።
♦️ በጠቅላላ ዘርፈው የወሰዱትና ያወደሙት ንብረት በጥሬ ገንዘብ ሲተመን 2.5 ሚሊዮን የኢትዮጽያ ብር መሆኑን ከሆቴሉ ባለቤቶች ማረጋገጥ ችያለሁ።
በመላው አማራ በአገዛዙ የፈጸሙ ዘግናኝ ድርጊቶችን እየተከታተልን ለህዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
ጥር 02/2018 ዓ.ም
ከጥር 01/2018 እስከ ጥር 30/2018 ዓ.ም ከቡሬ፣ሽንዲ፣ፍኖተሰላም፣ደምበጫ፣አማኑኤል፣ደጋዳሞት፣እሁዲት ከመሸገው የጠላት ካምፕ በመክዳት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮርን የተቀላቀሉ ስም ዝርዝር:-
ስም የወጡበት ተቋም
1.ካሳሁ አጃናው፣ አድማ ብተና
2.ሱዲ አህመድ፣ መከላከያ
3.አመዲ ኪሮድን፣ መከላከያ
4.ድንቃየሁ ይህሳቅ፣ መከላከያ
5.ነብዩ አርባ፣ መከላከያ
6.ሙቲን ኢብራሔም፣ መከላከያ
7.ቴዲ ወርቁ፣ መከላከያ
8.ያሲን ቢልሳ፣ መከላከያ
9.አብኀዲ ሙዛንቢል፣ መከላከያ
10.ጥላሁን ፣ መከላከያ
11.ሳሙኤል አለሙ መከላከያ
12.ይናገር ጥላሁን ሚሊሻ
13.ሠማይነህ አትርሳው ሚሊሻ
14.አንሙት አዲሱ ቢተው ሚሊሻ
15. ጥላሁን አዝመራው ሚሊሻ
16. አንሙት አለበል ፖሊስ
17.ምልኬሳ ኩምሳ ሞሲሳ መከላከያ
18. መላኩ ደመላሽ መከላከያ
19.ተስፋ እንዳለው ጋሻው መከላከያ
20. ፲/አ አባደር መሀመድ መከላከያ
21.ሀብቴ ደሳለኝ ሚሊሻ
22.አያና ስዩም ሚሊሻ
23.መልኬ ልመንህ ሚሊሻ
24. ከ135 በላይ በርካታ ምልምል ሰልጣኞች
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 3/2018ዓ.ም
ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋዳሞት ወረዳ ፈረስቤት ከተማ በቀን 02/06/2018 ዓ/ም በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኮር 99 ኛ ክ/ጦር በተደረገ እጅግ ወታደራዊ ጥበብን በተሞላ አስደናቂ የከተማ ኦፕሬሽን ፈረስቤት ከተማ ላይ፤ ደጉን ጀግናውን የደጋዳሞትን ማህበረሰብ ሲያሰቃይ የነበረውን #መኳንንት የተባለ የብልጽግና ቅጥረኛ ባንዳ ፖሊስ ላይመለስ ከምደረገጽ የተወገደ ሲሆን አብሮት የነበረ ፖሊስም ከባድ ቁስለኛ በማድረግ በሞትና በህይወት መካከል ይገኛል።
👉ባንዳ ማጽዳቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 3/2018ዓ.ም
አሳዛኝ መረጃ ¡¡
ከፋኖ ጋር በቻህን ዘመቻ ወተህ ትገጥማለህ የተባለው ሜጫ ወረዳ መርዓዊ ከተማ ላይ ያለ ሚሊሻ ቆቆር (መርዝ) እየዋጠ እየሞተ ነው ።
ተው ወደኛ ኑና ጥላትን እንግጠም ተው የገዛ ህዝባችሁን አትጨፍጭፉ አልን አልሰማ ብላችሁ ከህሌናችሁ ሆዳችሁን አስቀድማችሁ ድፍን ሁለት ከርምት እና ሁለት በጋ ተኩል ከኦሮሙማ ወራሪ ቡድን ጋር አብራችሁ የገዛ ህዝባችሁ ላይ እልቆ መሳፍንት የሌለው በደል እና የዘር ማጥፋት ሥትፈጽሙ ከረማችሁ በመጨረሻው ሰአትም የፍርድ ቀን መጣባችሁ ህሌናችሁ ወቅሷችሁም ይሁን ፈርታችሁ ወይም የአማራ ህዝብ አምላክ የንጹሃን ፈርዶባችሁ እራሳችሁን ቆቆር ( መርዝ ) እየወጣችሁ እየሞታችሁ ነው ።
ዛሬ መርዓዊ ላይ 3 ሚሊሻ መርዝ ውጦ ሞቷል ።
ለኛስ ጥይት ከማባክን ዳንን ሙቱ ጥሩ ነው ።
ህሌና ያለህ ባንዳ ካለህ ግን አሁንም ቢረፍድም አልመሸም ተሎ ብለህ ከነ ትጥቅህ እንዳያስክ ወደ ፋኖ ተሸብለል እና እራስክንም ቤተሰብህንም አድን ከዛም እራስክን ከታሪካዊ ተጠያቂነት ነጻ ታወጣለህ !!
ጀሮ ያለው ይስማ !!
ድል ለጀግናው ፋኖ 💪!!
ድል ለተገፋው አማራ 💪!!
ምኒልክ ዕዝ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ሙሉ ለሙሉ ደምስሶ ያፈራረሳቸው የጠላት ክለጦሮችን ስያሜ ለራሱ መጠቀም ጀመረ!
በሰሜን ምስራቅ ዕዝ በነ ኮሎኔል አዴን ይሳቅ እና በነ ኮሎኔል ደመወዝ መንግስት ይመሩ የነበሩት 12ኛ ክ/ጦር እና 49ኛ ክ/ጦር ስያሜያቸው ለፋኖ ክፍለጦሮች የተሰጠ ሲሆን፡ በተመሣሣይ በላስታ ተራሮች ልክ እንደጨው ሟሙታ የቀረችው 65ኛ ክፍለጦር ስያሜዋን ተነጥቃለች።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ስር የቀድሞው ምስራቅ አማራ ኮር ሁለት በአዲስ እቅድ እና በአዲስ ስያሜ መምጣቱን አስታውቋል።
መጠሪያው "102ኛ ኮር" ተብሎ የተሰየመው የቀድሞው ምስራቅ አማራ ኮር ሁለት፡ በኮሩ ስር የጠላት እራስ ምታት የወገን ድል አብሳሪ ከሆኑ ክፍለጦሮች መካከል አንዷ የሆነችው ዞብል አምባ ክፍለ ጦር ስያሜዋን "12ኛ ክ/ጦር" በሚል መቀየሯን ምኒልክ ዕዝ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ገልጿል።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አካል የነበረችው 12ኛ ክፍለጦርን ሰራዊቷን ከነ መሣሪያዋ ሙሉ በሙሉ ማርኮ ያፈረሳት ምኒልክ ዕዝ፡ አሁን ደግሞ "12ኛ ክፍለጦር" የሚለው መጠሪያዋንም ወስዶባታል።
በተመሣሣይ፡ ሌላኛዋ የድል አብሳሪ የወገን ኩራት የሆነችው ካላኮርማ ክፍለ ጦር መጠሪያዋን "49ኛ ክፍለጦር" ወደሚል ቀይራለች።
49ኛ ክፍለጦር ማለት በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስር 802ኛ ኮር በኮሎኔል አዴን ይሳቅ ስትመራ የነበረችውና በያዝነው የሕልውና ትግል በራያ ተራሮች ላይ እንደጨው ሟሙታ የቀረችው ክፍለጦር ናት።
በቀድሞው ምስራቅ አማራ ኮር 2፡ ከዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ስያሜውን ወደ "102ኛ" በቀየረው በግዙፉ ኮር ስር፡ ጠላትን እግር ተወርች አስራ በአፈሙዝ አለንጋ እየገረፈች የምትገኘው ሌላኛዋ ታጠቅ ክፍለ ጦር፡ ከዲቢ እና ወርቄ ባለሸርጡ ብርጌድ እንዲሁም የኮሩ ሜካናይዝድ ቡድን ጋር አንድ ላይ በመበወዝ አንድ ግዙፍ ክፍለጦር ሆነው ስያሜያቸውን "65ኛ ክፍለጦር" በሚል መሰየማቸውን ምኒልክ ዕዝ ለመረብ ሚዲያ አስታውቋል።
65ኛ ክ/ጦር በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስር 803ኛ ኮር ስር በነሻለቃ ጫላ ስትመራ የነበረችና በ"ዘመቻ አባናደው" ሙሉ በሙሉ ተደምስሰው ከፈረሱ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ክፍለጦሮች መካከል ግንባር ቀደሟ ስትሆን፡ የክፍለጦሯን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ መሣሪያዋን ማርኮ የታጠቀው ምኒልክ ዕዝ፡ አሁን ደግሞ ስሟንም ወርሷታል።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ በተለያዩ ጊዜያቶች ባደረጋቸው አውደውጊያዎች፡ የብልፅግናው አገዛዝ "የስልጣን ማስጠበቂያየ ትልቁና ዋና ደጀን ኃይሌ" በሚል ከሚተማመንበት፡ በአቶ አሰፋ ቸኮል ከሚመራው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስር የሚገኙ በርካታ ክፍለጦሮችን ብትንትናቸውን አውጥቶ ሰራዊታቸውን በመደምሰስና በመማረክ፡ የጦር መሣሪያቸውንም ከነ ክፍለጦር ስያሜያቸው ማርኮ ወስዶባቸዋል።
ምኒልክ ዕዝ በዚህ ግስጋሴው ከቀጠለ፡ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ የሆነው አቶ አሰፋ ቸኮልን ከነ ጀሌዎቹ በአጭር ቀናት ውስጥ ማርኮ በምኒልክ ዕዝ የሰራዊት ምግብ ዝግጅት ክፍል ውስጥ የምግብ ማብሰያ እንጨት ፈላጭ ያደርገዋል በሚል ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
ጠላት እንደጉድ ረገፈ፣በርካቶች ሲማረኩ ከተሞች ነፃ ወጡ!!
በዘመቻ መንግስት ጥላሁን
የሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ኮር እጅግ አኩሪ ድል አስመዘገበ!!
ትናንት በ''ሥማዳ'' የጀመረው አኩሪ ድል ዛሬ በ''ዘመቻ መንግሥት ጥላኹን'' ሥም በእሥቴ መዳረሻ በአኩሪ ድል ሲደገም በጀነራል ነጋ ተገኝ መዳረሻ ደራም ላይ እየተሰለሰ ይገኛል❗
🔸የካቲት 02/2018ዓ.ም
01. እሥቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ
✅ጉና ክፍለ ጦር፦
👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ
👉አንዳ ቤት ብርጌድ
👉መቅደላ አምባ ብርጌድ
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ እና
🔸ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
በማለት ነበር። ሥማዳ ላይ በተደረገው ውጊያ ጠላቶቹን ረፍርፎ በጀግንነት የክብር መሥዋዕትነትን በተቀበለው አርበኛ ''መንግሥት ጥላኹን'' ሥም በእልህና በቁጭት ጠላትን ከሕይወት መዝገብ ሲሰርዙ ውለዋል።
ጠላት የመዋጋት ወኔ ክዶት በእሣተ ገሞራው የአማራ ፋኖ ሲምበረከክ ውሏል። በዚህ ውጊያም ብዛት ያለው ምርኮ ሲገኝ ከምርኮቹ መካከልም፦
👉05 ብሬን
👉02 ሥናይፐር
👉02 ዲሽቃ
👉አንድ ፓትሮል ሙሉ ክላሽ
👉አንድ ፓትሮል ሙሉ የክላሽና ብሬን ተተኳሽ
👉03 ሲኖ ትራክ ምርኮኛ ታጣቂ
👉ብዛት ያለው ታጣቂ የተደመሰሰ
👉87 የፖለቲካ እሥረኞች ከግዞት ነጻ የሆኑበት
👉መካነኢዬሡሥ ከተማ ከአገዛዙ ነጻ የሆነበት...
በዴንሳ ተራራ ጠላት ሲረግፍ፣ ምርኮ ሲማረክ የዋለበት ዕለት ነው።
02. ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር
በደራ ምድር ከአምበሳሜ ወደ ሐሙሲት ጓዙን ጠቅልሎ የፈረጠጠው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ''ግብጻዊት ማርያም እና ገነት ወንዝ'' ላይ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሕዋሥ የሆነችው ጣና ብርጌድ ከፊት ዘግታ ሥትመታው ከኋላ ደግሞ አፈር ውኋ ዕናት ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በብርሐን ፍጥነት ደርሰው ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እዬሰጡት ይጠኛሉ። የአቢይ አሕመድ ወምበር ጠባቂ ቡድን በዘረ ውባንተዎቹ በሁሉም የኮሩ መዳረሻ በተጠና ዕቅድ ሲገረፍ እሥከ ምሽቱ 01:00 ውጊያው የቀጠለ ሲሆን የዓምሐራ ፋኖ የበላይነቱን ወሥዷል።
የካቲት 01/2018 ዓ.ም
03. ሥማዳ/ወገዳ
በሥማዳ ወገዳ ከተማ 24:00 የፈጀ ውጊያ ቀንና ሌሊት ሲከወን የአገዛዙ ኮንክሪት ምሽጎች ተሰብረው የጠላት መቀበሪያ ሁነዋል።
✅265 ተደምስሷል
✅22 ተማርኳል።
✅ቁጥሩ ያልታወቀ በኖ የጠፋ አለ።
ከአማራ ሰማይ ስር ዘራፍ ያለው ማነው
ያ ውባንተ ከባተ ያሳምነው ልጅ ነው!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
