uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 406
Підписники
+1324 години
+277 днів
+1 21530 днів
Архів дописів
ሰበር ሰበር የድል ዜና """" የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክ/ጦር የባህርዳር ብርጌድ እና የጣናው መብረቅ ብርጌድ በጥምረት ከባህር ዳር ከተማ በቅርብ ርቀት በደህና ማርያም ቀበሌ ልዩ ስሟ ቋሪት አምባ በተባለች ጎጥ ላይ የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ኃይል ከጠዋቱ  2:30 ሰዓት የጀመረ እስከ 9:00 ሰዓት ድረስ ጠላትን እያዝረከረኩ ሲወቁት የዋሉ ሲሆን ከ50 በላይ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ውጤታማ የሆነ ስራ ተስርቷል። "" ትግል በfb ሳይሆን በተግባር ሰርተን አሳይተናል"" በዛሬው  አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች ➦ ብሬን =04 ➦ ስናይፐር=03 ➦ ክላሽ =51 """""""ምርኮኞች ዝርዝር"""" 1ኢ/ር ታደሰ ታምሩ ም/ሻለቃ መሪ 2 እያያ ድረስ የቀድሞ ልዩ ሀይል ሻለቃ መሪ 3 ለውጥነው መለሰ የሻለቃ ሎጅስቲክ 4 ብርሀን ማንደፍሮ ቲም መሪ 5እንድሪስ ይመር ቲምመሪ 6አማረ ጀንበሩ =አባል 7 ዘመነ ሙላቴ =አባል 8 ጀንበሩ ጌታነህ =አባል 9 ማንችሎት የኔው =አባል ቀሪውን የጠላት ሀይል ከባህርዳር ጭምባ በሚወስደው መስመር ፍርጠጣውን የተመለከቱ የቀጠናው ማህበረሰብ እና ሰራዊታችን "አብይ አህመድ እየገነባው ያለው ሰራዊት አሰብን ማስመለሱ ቀርቶ በማራቶን ውድድር ቢሳተፍ  ኢትዮጵያን የወርቅ ተሸላሚ ማድረግ የሚችል ነው" ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጠዋል። ይሁን እንጂ በዚህ አውደ ውጊያ የተሳተፉት የጣናው መብረቅ እና የባህርዳር ብርጌድ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ልምዳቸው እንደሆነ ድርጅታችንም ፣ ህዝባችንም ፣ ጠላትም ወዳጅም የሚያውቀው ሀቅ ሲሆን መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለው በቀጣይ ዓለምን ጉድ የሚያስብሉ አማራዊ ዘመቻዎች ማሟሟቂያ ነው ሲሉ የሁለቱ ብርጌድ ወታደራዊ አመራሮች ጠቁመዋል። በቪዲዮ ምርኮኞችን ነገ እናቀርባለን በተለያዩ ቦታወች ላይ ስለሆኑ ነው ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህ/ግንኙነት ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! ፅናት ክፍለ ጦር የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣው የሽመልስ አብደሳ ጭራቅ ሰራዊት በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ ልዩ ስሙ
+1
ሰበር ዜና! ፅናት ክፍለ ጦር የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣው የሽመልስ አብደሳ ጭራቅ ሰራዊት በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ ልዩ ስሙ ሀሙሲት በሚባል ቦታ ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል። ስልታዊ ስበት በማድረግ የጥላትን ሰራዊት ወደ ሞት ምድብ ስቦ በማስገባት  ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ተሸኝተዋል። ከ9:30 እስከ 12:30 ድረስ ጦርነቱ የዘለቀ ነበር። በዚህ ሁኔታ የጥላት ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ ሞደስ ናፈቀኝ እሮሮውን ቢያላዝንም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት ከሞደስ ናፍቆት ወደ ማይቀረው ሲዖል ተሸኝቷል። "አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት" በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተበርጭሷል። በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የሽመልስ አብደሳ ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን አስተናግዷል። አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በፓትሮል  ወደ ወገልጤና ጤና ጣቢያ እያጋዘ አምሽቷል። ድሉ እደቀጠለ ነው! ዝርዝሩን እንመለስበታለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የፅናት ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ጥቅምት 14/2081 ዓ/ም

.............የአደረጃጀት ዜና!! ............. በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የ54ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ። በዚህም አዲስ ተዋቅሮ የተጠናቀቀው 54ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት የመብረቁ ተፈራ  ብርጌድ ፣ የመዝገበ ጮቄ ብርጌድ እና መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድን ያካተተ ሆኖ ተመስርቷል ። ክፍለጦሩ በአምስት ሬጅመንቶች የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሬጅመንቶች አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በዕዙ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ማርሸት ፀሐው ደምሴ ፣ በዕዙ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ይትባረክ አንዳርጌ እና በዕዙ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን አስተባባሪነት ተጠናቋል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 14/15 የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር የማቻክሉ በላይ ዘለቀ ብርጌድ አማኑኤል ከተማ በመግባት በአንድ ባንዳ የአድማ ብተና አባል እርምጃ ወስደ
+1
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 14/15 የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር የማቻክሉ በላይ ዘለቀ ብርጌድ አማኑኤል ከተማ በመግባት በአንድ ባንዳ የአድማ ብተና አባል እርምጃ ወስደው መሳሪያውን ይዘው ወጥተዋል። ድል ለአማራ ፋኖ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! ፋናየ ውቤ ክ/ጦር የጸጥታ ስራን በመከወን ላይ እያለ ጥቃት ለመፈጸም የመጣን የጠላት ኃይል አሳፍሮ መመለሱ ተገለጸ።      ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ገደማ ከአዲስ ዘመን ተነስቶ አርኖ ጋርኖ ከተማ ላይ የፋናየ ውቤ ክ/ጦር አባላት ላይ ጥቃት ለማድረስ የህዝብ ተሽከርካሪን ተጠቅሞ የመጣን የጠላት ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት አሳፍረው ወደመጣበት እንዲመለስ አድርገዋል።       እንደደረሰም የጨበጣ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ጠላት መምጣቱን መረጃ የደረሳቸው ፋኖዎቹ በጨበጣ ውጊያውም ከ4 በላይ የጠላት አሽከሮቻቸውን እስከ ወዲያኛው እንዲወገዱ አድርገዋል።     ሰሞኑን የጠላት ኃይል ሲቪል በመልበስ የህዝብ ተሽከርካሪን በመጠቀም ከአዲስ ዘመን እስከ እንፍራዝ ማክሰኝት ድረስ እየተንቀሳቀሰ መሰንበቱ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬም ይህን ቴክኒክ ተጠቅሞ ፋኖን ለመማረክና ለመደምሰስ የነደፈው እቅድ በኪሳራ ታጅቦ ተጠናቋል ሲል የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ አብነት ሞላ ገልጿል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ  ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ከክፍለ ጦር እና ከብርጌድ አመራሮች ጋር በቀጣይ አቅጣጫ ተወያየ። አማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ  የግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ካሉት 7 ክፍለ ጦሮች እና የ 2 ብርጌድ  አመራሮች ጋር በቀጣይ አቅጣጫ ሁለት ቀን የፈጀ ጠለቅ ያለ ዉይይት አድርጓል። በዉይይቱ ላይም የሰባት ክፍለ ጦር እና የሁለት ብርጌድ ከአዛዥ እስከ  ሻለቃ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን  አመራሮቹም የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሃሳቦችን ለኮሩ ያነሱ ሲሆኑ  በተነሱት ጥያቄወች እና ሃሳቦች ላይም  የ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ  የግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ዋና አዛዥ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ፣   ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታዘበዉ ሻንበል ፣ የኮሩ ስምሪት አርበኛ አማሪዉ አያናዉ ፣ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ሙሴ ፣ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አለምነዉ መብራቱ ፣የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን  በክፍለ ጦር እና  በብርጌድ አመራሮች በየክፍል ኃላፊወች  የተነሱ ሃሳቦች እና አስተያየቶችን ተቀብለዉ ምላሽ ስጥተዉ  የቀጣይ አቅጣጫም አስቀምጠዋል። በዚህ ዉይይት ላይም ሌሎች የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዉ ለትግሉ ይበጃል ያሉትን  የየራሳቸዉን ሃሳብ እና አስተያየት አስቀምጠዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ  ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን! ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

~||| ወገልሳ! የ፩ኛ ክፍለጦር ባህርዳር ብርጌድ እና የጣናው መብረቅ ብርጌድ ባህርዳር  ኤርፖርት ወገልሳ ቀበሌ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል። ምርኮኛ እና ትጥቅ በመሰብሰብ ላይ ነው! የጣና ፎረም ተሰብሳቢ የአፍሪካ ህብረት ሠዎች ጭንቀት ስጋት ላይ ወድቀዋል።ባህርዳር  ከተማ ውስጥ  ያለው መደናገጥ ቀላል አይደለም። ዝርዝር በመዋቅር የሚቀርብ ሆኖ እስካሁን -03 ብሬን -01 ስናይፐር -01 ሻለቃ ም/መሪ 07 ምርኮኛ ተገኝቷል!

ሰበር ዜና ~~~~   ዛሬ በቀን 09/2/2018 ዓ/ም የአፍብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ 5ኛ ክ/ጦር የወርቅ አባይ ብርጌድ ቀጠና  ላይ ከፍተኛ የሆነ የብልፅግና ወራሪ ቡድን በውጊያ ሲሸነፍ በሶሪት፣ በአምበላ፣ በጎሪ ፣ በዛጋ፣ በኩራፊ ፣ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ አገውና አማራን ለማጫሪስ ከ2016 - 2017 ዓ ም ድረስ የሰራውን የፖለቲካ ሸፍጥ ቆራርጠን ጥለንዋል::       የአንድ አባት ልጆችን ለከሰረው ፖለቲካው ማካካሻ ለመስራት በማሰብ ሁለት ወንድማማቾች በጠላትነት እንዲተያዩ አድርጓቸው ቆይቷል። ይህንን ችግር ለመፍታት በነበረን የህዝብ መድረክ ላይ የአገውና አማራ እና ሙስሊምና ክርስቲያን የሚል የብልፅግና ኮተት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ገመዱን ቆርጠንዋል።   በነበረው የህዝብ መድረክ ላይ ከተሰበሰቡ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል የሃገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት አገውና አማራ የአንድ አባት ልጆች ሁነን እያለ በተሰራብን የጠላት ሴራ እርስ በርሳችን ተገዳድለናል። ወንድሙ ወንድሙን ገለይል። ይሄ ሁኔታ በመፈጠሩ ሶሪትና አምበላ ከተሞች ከከተማነት ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል ብለዋል። አሁን ችግሩን ለይተን በማወቃችን በአንድ ካልተጋመድን  ሁላችንም በተራ ይሄ ዘራፊ መንግስት እንደሚያጠፋን ተረድተናል በማለት ሃሳባቸውን ገልፀዋል።  በዚህ የውይይት መርሃ ግብር ላይ  የሚከተሉት ሃሣቦች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል። ለምሳሌ፦ 1ኛ, አገውና አማራ የሚል ትርክት ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት እንደሌላ አገው አማራ፣ አማራ አገው መሆኑን ተገልጿል :: 2ኛ, በክርስቲያኖችና ሙስሊሞች መካከል የነበረውን ልዩነት ፈተናል። 3ኛ, የአማራ ፋኖ አደረጃጀት ዓላማ ፣ ተልዕኮና ግብ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። 4ኛ, ማነኛም በአካባቢው የሚኖር አካል ፣ በባንደነትና በስርቆት የሚሰማራ ካለ እንዳሚረሸን አቅጣጫ ተሰጥቷል። 5ኛ, የፋኖ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ እና አሁን ያለበት ቁመና ሃገረ መንግስት መመሰረት የሚያስችለን ቁመና ላይ በመሆናችን ማህበረሰቡ ለፋኖ የሚያደርገውን የሎጀስቲክ ድጋፍ ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል። በዚህ መድረክ ላይ ከፍተኛ የአፍብኃ አመራሮችና የወርቅ አባይ አመራሮች ተገኝተዋል። ከተገኙት አመራሮች መካከል.. ~ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮ ዕዝ የሎጀስቲክ መምርያ ኃላፊ ፋኖ ዘመኑ ገረመው፣ ~ የአፋብ ኃ ምዕ/ አማራ ቀጠና . ቴዎድሮስ ዕዝ የፋይናንስ  መምሪያ ም ኃላፊ ዳኛው ሽባባው የአፋብ ኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የወርቅ አባይ ብርጌድ ፋኖ ሞላ አዲስ ተገኝተዋል፡፡ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አሰተሰሰብ ፣ አዲስ ተስፋ፤             ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!! @አርበኛ ዘመኑ ገረመው የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና                ቴወድሮስ ዕዝ የሎጀስቲክ መምርሪያ

ትምህርት ቤቶችን መንግስት በድሮን እያወደማቸው ነው። በአፋብኅ ምዕ.አ.ቀ.ቴ.ዕዝ 2ተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ያሉ የቀበሌ ትምህርት ቤቶችን መንግስት በድሮን እያወደማቸው ይገኛል። ፋኖ ለተተኪው ትውልድ በማሰብ ትምህርት ቤቶችን ለቆ ለካምፕነት የማይጠቀም ቢሆንም ምንም አይነት ፋኖ በሌለበት የሸበሌ ትምህርት ቤትን ፋኖን አገኛለሁ በሚል ቅዥት በድሮን አፈራርሶ አማራን በህይወትም በንብረትም ሊያጠፋ መምጣቱን በይፋ አረጋግጧል። መንግስት ተብዮው በአንድ በኩል ትምህርት ይጀመር እያለ ፋኖን በየወረዳወች እየጠየቀ በሌላ በኩል ደግሞ የትምህርት ተቋማትን በድሮን የማፍረሱ ድራማው ፋኖ ህፃናትን መንግስት በቀላልና በከባድ መሳሪያ ያጠፋቸዋል ብሎ የትምህርት ይከፈት አይከፈት ሀሳቡን በይደር መያዙ ትክክል መሆኑንም አረጋግጧል። በዚህ የድሮን ጥቃት  ምንም ፋኖ በአካባቢው ባይኖርም የትምህርት ቤቱን ሳር ለከብት የሚያጭዱና ጤፍ አጨዳ ለቀን ስራ የሄዱ ሶስት ንፁሀን ተሰውተዋል። ከዚህ በፊት በጎንጅ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ላይ ድሮን ተጥሎ ንፁሀን መቁሰላቸውና ላብራቶሪ ክፍሉ ሙሉ በሙሉ የህዝቡ ንብረት መውደሙ ይታወሳል።          አዲስ ትውልድ          አዲስ አስተሳሰብ          አዲስ ተስፋ የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት           ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

የአረመኔው ተላላኪ ወምበር ጠባቂዎች በመጡበት እግራቸው ፈርጥጠዋል ፦ የወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር  ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም. ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ የተፈረደበት የሥርዓቱ አገልጋዮች በሽንዲ ከተማ ታስሮ የተቀመጠው የአገዛዙ ሎሌዎች ወደ ማርቁማ ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ በክንደ ብርቱዎች የብርጌዱ አናብስቶች ከቡድን መሳሪያ እስከ ነፍስ ወከፍ መሳሪያ በታገዘ  የአጭር ሰዓት ውጊያ በማካሄድ ጠላት በመጣበት እግሩ ፈርጥጦ ወደ ሽንዲ ከተማ ገብቷል። ለጠላት የራስ ምታት ሁኖ የመጣው የወምበርማ ብርጌድ ከምሽግ ምሽግ እያስለቀቁ ሲያሯሩጡት የያዘውን ጥይት እያዝረከረከ መሄዱን የወምበርማ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ መረጃውን አድርሶናል። በሽንዲ ከተማ መሽጎ የተቀመጠ የአረመኔው #ጡት ቆራጩ ስርዓት ወምበር ጠባቂዎች በከተማዋ ተወሽቀው በፍርሃት ቆፈን ውስጥ መገኘታቸውም አክለው ገልጸዋል። 🚨 ድል ለአማራ ፋኖ❗   ፲ አ/ ኢ/ር ዘመኑ አማረ 5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ መምሪያ ሓላፊ

አሳሳቢ ጉዳይ‼️ በአማራ ክልል በሚገኝ ገጠራማ አካባቢ የተካሄደ አዲስ ጥናት፣ በአካባቢው በወጣት ሴቶችና ወንዶች ቁጥር መካከል ከፍተኛ አለመመጣጠን መኖሩንና የወሊድ መጠን ከሀገር አቀፍ አማካይ አንጻር በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ይፋ አደረገ። በብርሃን ጤና እና ስነ-ህዝብ ክትትል ሳይት የተካሄደው ጥናቱ እንዳመለከተው፣ በተለይም ከ15 እስከ 24 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለእያንዳንዱ 100 ሴቶች 167 ወንዶች እንደሚገኙ ታውቋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በአካባቢው ያለው የወሊድ መጠን (Total Fertility Rate) አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ በአማካይ 3.44 ልጆችን ብቻ እንደምትወልድ ያሳያል። ይህ አሃዝ፣ እ.ኤ.አ በ2016 ከነበረው የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ አማካይ (4.6 ልጆች) ጋር ሲነጻጸር የ25% ቅናሽ አሳይቷል። የጥናቱ አዘጋጆች እንደሚገምቱት፣ የዚህ አስገራሚ ለውጥ ዋነኛ መንስኤ ወጣት ሴቶች ለተሻለ የትምህርትና የሥራ ዕድል ፍለጋ ከገጠሩ ወደ ከተሞች በብዛት እየፈለሱ መሆናቸው ነው። ይህ ስደት በገጠሩ አካባቢ የሴቶችን ቁጥር እንዲቀንስ ሲያደርግ፣ የወሊድ መጠኑ እንዲያሽቆለቁልም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል። ጥናቱ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለውን ሰፊ ማህበራዊና ስነ-ህዝባዊ ለውጥ አመላካች መሆኑ ተገልጿል።

በደብረማርቆስ  ከተማ ውስጥ የአድማ ብተና አዛዡን  ኢላማ ያደረገ  ጥቃት ሲፈፀም ፖዊ ፖሊስ ጣቢያው ላይም ጥቃት ተፈፅሟል። በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረ ማርቆስ ወንቃ አካባቢ በሁለት ፖትሮል ላይ ሆነው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም የአድማ ብተና  አዛዥ ኢንስፔክተር እንዳለው አላምርን  ጨምሮ በርካታ ፖሊሶችን ማቁሰልና መደምሰስ ተችሏል። ሁለቱን ፖትሮሎችም  በተካሄደው ማጥቃት ከጥቅም ውጪ ማድረግ ተችሏል። እኒህ ፖሊሶች ማታ ማታ  ጨለማን ተገን አድርገው የደብረማርቆስ እና አካባቢውን ማህበረሰብ ስልክና ገንዘብ የሚዘርፉ፣ የሚደበደቡና የሕዝብን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ  እና ሆዳቸው በሕዝብ ገንዘብ የሞሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለናል። በትናንትናው ዕለት  ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር አባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት መተከል አዉራጃ ወደ ፓዊ ከተማ ሰርገዉ በመግባት በጠላት ላይ ኪሳራ አድርሰዋል። ተወርዋሪ ኮከቦቹ ፓዊ ከተማ በመግባት ፖሊስ ጣቢያው ላይ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት በርካታ የአብይ ተላላኪ ፖሊሶችን መግደል እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። በተመሳሳይ በትናንተናው ዕለት  አስር ዓለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ችጓሊ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ችጓሊ ከተማ የሚገኘዉን የአረመኔዉን ጡት ቆራጭ ካንፕ ሙሉ በሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር  የጠላትን ሎጅስቲክ ሙሉ በሙሉ መማረክ የተቻለ ሲሆን ቀንደኛ የስርዓቱ የጭን ገረድ ባንዳ በቁጥጥር ስር ዉሏል።ብዛት ያለዉ  አድማ ብተና እና ሚሊሻ መደምሰስና ማቁሰል ተችሏል። ፎቶ  :- ኢንስፔክተር እንዳለው አላምር የ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ አድማ መከላከል አዛዥ  ቆስሎ ደብርማርቆስ ሆስፒታል የሚገኝ።

ሰበር ቲሊሊ ‼️ 💪💪💪 ደም መላሹ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ‼️ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦ ጥምር ጦር  ታላቅ ጀብድ ፈፅሟል ። ጀብደኛዉ ክ/ጦር አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ፣አድማ ብተና፣ጡት ቆራጩን የአረመኔዉ አገዛዝ እንደ ጉድ ተወቅቷል። አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማ ላይ ድል ተቀዳጅቷል አንጋፋው ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ሰሃት ቲሊሊ ከተማን በመቆጣጠር ጡት ቆራጭ የሆነዉን ወንበዴ ቡድን አሳር ቁም ስቅሉን ሲያሳዩት አርፍደዋል። የአገዉ ምድር ድሮኖች፦ #ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ #ግዮን ብርጌድ #ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ እንጅባራ ብርጌድ #ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ #አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድና                               #ቡያ ሻለቃ በተሳተፉበት ዉጊያ የጠላትን ሀይል ብትንትኑን በማዉጣት ከፍተኛ ሰብአዊ ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል። የክ/ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ደሞዝ ግርማ (ዴቭ) በመራዉ አዉደ ዉጊያ  ጠላት በከፍተኛ ደረጃ ተቀጥቅጧል። በመሸጉበት የቲሊሊ 1ኛ ደረጃ ህብረት የትምህርት ቤት ካምፕ ላይ በሞርተር ሲደበደብ ካምፑን ለቀዉ በመሮጥ እንደ ቀበሮ በማሱት ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረዋል፤ ከመሃል ከተማ እስከ ጅባይታ በተዘረጋው የእጅ በእጅ ውጊያ ጠላት ላይ ከፍተኛ ምት በማሳረፍ ቅስሙን መስበር ተችሏል። ይህንንም ተከትሎ ከእንጅባራ እየተግተለተለ የመጣው ሀይል ሽፋን ሆኖ ሊያተርፍ ቢሞክርም ቺማ ስላሴ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ሲገረፍ አርፍዷል። ለሶስት ሰሃታት በዘለቀው አውደ ውጊያ                                   ከ20 በላይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ወደ ላይኛዉ ሲላክ                           ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ፣አድማ ብተና፣ጡት ቆራጩ የአረመኔ አገዛዝ ሰራዊት ቁስለኛ ሁኗል። ፋኖነት አሸናፊነት‼️ ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ  (እሳቱ)

ሰበር ዜና ከበረኸት ወረዳ መተህ ብላ ከተማ ደብረብርሃን ሄዳ ሽልማት መቀበል ላልቻለችው  ቀፀላ ተገኑ የተላከ የሽልማት ቁሳቁስ በፋኖ የመረጃና ደህንነት ሰዎች ቁጥጥር ስር ዋለ። በወ/ሮ ሰዓዳ ኢብራሒም (ጀማነሽ) የሰ/ሸዋ ዞን ብልግና ፖርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና በወ/ሮ  የሮምነሽ ጋሻውጠና የሰ/ሸዋ ዞን የሴ/ህ/ጉ መምሪያ ኃላፊ ተፈርሞ የወጣ የምስክር ወረቀትና ጋቢ መነሻዉን ከደብረ ብርንን መድረሻውን በረኸት  ወረኸት ወረዳ መተህ ብላ ከተማ ባደረገ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መኪና  ተጭኖ  በንቀሳቀስ ላይ እያለ አክርሚት በተባለ ቦታ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክ/ጦር ተስፋ ብርጌድ የመረጃና ደህንነት ሰዎችና የብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች  ቁጥጥር ስር ዉሏል። እንደ አይጥ ከጎሬያቸዉ መዉጣት ያልቻሉት እና ደብረ ብርሃን ሄደዉ ስብሰባም ሆነ ሌሎች ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ያልቻሉት የወረዳዉ ካድሬዎች ወደ ወረዳዉ በቀላሉ መግባትም ሆነ መዉጣት እንደማይቻል የተረዱት መካሻ አለማየሁ፣ሰአዳ ኢብራሂም እና መሰሎቻቸዉ የሰ/ሸዋ  ዞን አመራሮች ምንም አይነት ስራ ባልሰሩበት በሀሰት ሪፖርት እራሳቸዉን እያረኩ በርቀት መመሰጋገኑን ቀጥለውበታል። በወቅቱ እቃዉ ከቦታዉ ሲንቀሳቀስ ቀድሞ መረጃ የነበራቸዉ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ብርጌድ የመረጃና ደህንነት ባለሙያዎችና  አመራሮች  ጥብቅ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዉ ያለምንም በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።         መረጃዎን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም  ሪፖር ነው።        " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ‎       ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

#የድሮን_ቅኝት_መረጃ‼️ 👉ዛሬ ደብረ ማርቆስ ዙሪያ ለሊቱን ከ10 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት ድረስ የድሮን አሰሳ ተደርጓል ለወገን ይዳረስ‼️ 👉እንዲሁም ጅጋና አካባቢው ፣ሆዳንሽ አካባቢው ፣ማ
#የድሮን_ቅኝት_መረጃ‼️ 👉ዛሬ ደብረ ማርቆስ ዙሪያ ለሊቱን ከ10 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት ድረስ የድሮን አሰሳ ተደርጓል ለወገን ይዳረስ‼️ 👉እንዲሁም ጅጋና አካባቢው ፣ሆዳንሽ አካባቢው ፣ማክሰኝንና አካባቢው ፣ መንዝና አካባቢ እንዲሁም ፍኖተሰላም ዙርያ መንዝ ጭፋሪት አካባቢ በዛሬው ዕለት የድሮን ቅኝት ተደርጓል ጥንቃቄ ይደረግ 14/ዐ2/2018 ዓ.ም