ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 606
Підписники
+6624 години
+5877 днів
+1 04130 днів
Архів дописів
አሸባሪው መንግስት የጠራው ስብሰባ በፋኖ ኃይሎች ተበተነ!
መጋቢት 08/2018 ዓ.ም
የፋሽስታዊና የጅምላ ጨፍጫፊነት ባሕርይውን ሕጋዊ እውቅና ለመስጠትና ሕጋዊ ከለላ ባለው መልኩ የጭፍጨፋ ተግባሩን አጠናክሮ ለመቀጠል የብልጽግናው አገዛዝ እያደረገ ስላለው የምርጫ ዝግጅት በትናንትናው ዕለት በጎዛምን ወረዳ ሊባኖስ ቀበሌ ላይ ወሬውን ለመንዛት የጠራውን ስብሰባ ጀግኖቹ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ የሠራዊት አባላት በትነውታል።
የአገዛዙን ቀጣይ የማደንዘዣ ሴራ የምርጫ ፕሮፓጋንዳ እየፈጸመ ላለው የአውዳሚነት ተግባር ሕጋዊ እውቅና ለመስጠት የሚያደርገውን መንደፋደፍ የተረዳው የቀበሌው ማሕበረሰብም የፋኖ ሠራዊታችን በወሰደው እርምጃ መደሰታቸውን ማወቅ ተችሏል።
የአማራ ሕዝብ የሚያዋጣውንና የሚያስፈልገውን ምርጫ ከመረጠ ቆይቷል። እርሱም አፈሙዙ ነው።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
#የድሮን_ቅኝት‼️
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና ማለትም (ደምበጫ ወረዳናና አካባቢው ፣ ማቻክል ወረዳና አካባቢው) የድሮን አሰሳ እየተደረገ ስለሆነ የወገን ኃይልና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ አይለየው‼️
08/ዐ7/2018 ዓ.ም
የዝምታው ንጉሥ
ብዕሬን ይዤ ከወረቀቱ ፊት ለፊት ስቀመጥ የዛሬዋ ንጋት እንደ ሌላው አልነበረም። እስካሁን ጽፌ አላውቅም፤ ምናልባትም ቃላትን ሰድሮ ስሜትን መግለጽ ለኔ ብርቅ ሆኖብኝ ይሆናል። ዙሪያዬን ባይ ሰው የለም። ብቻዬን ነኝ። ነገር ግን በውስጤ የሚመላለሰው ስሜትና የሚሰማኝ የህዝብ ሰቆቃ ዝም አትበል ይለኛል። ዛሬ ግን የውስጤን ልፅፍ ወሰንኩ።
በሃሳብ ሰረገላ ተጭኜ ወደ ኋላ ስመለስ፣ በአይነ ህሊናዬ አንድ ሰው ድቅን አለብኝ። የሰሞኑን የልቤን በር ያንኳኳው፣ የውስጤን ስሜት የቀሰቀሰው ያ አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ ስሙን ሳስበው የሚታየኝ የሸዋ ምድር ያ ዳገትና ቁልቁለቱ ነው። እሱ ዝምተኛ ነው። ነገር ግን የእሱ ዝምታ እንዲሁ ባዶ አይደለም። ዝምታው እንደ ወርቅ የከበረ፣ እንደ ስጦታም የታደለ ነው። ዝም ብሎ ሲያልም፣ ዝም ብሎ ሲያቅድ፣ ዝም ብሎ ሲመክት... ዝምታው ውስጥ ሺህ ቃላት አሉ።
በልብወለዱ አለም ውስጥ አርበኛ እንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ የሸዋው መብረቅ የአማራው ኩራት የነ አስራት ወልየስ አደራ በክንድህ ላይ አርፏል። ከአበቀለችው ማህፀን የወጣኸው የአንበሳ ደቦል፣ የንጉሱ ልጅ ሆይ! አንተ 'ከእኔ በፊት ህዝቤ!' ብለህ የራስህን ምቾት የናቅህ የቁርጥ ቀን ልጅ ነህ።
ወረቀቱ ላይ ጠብ የሚለው የቀለም ነጥብ የልቤን ትርታ ይወክላል። ዙሪያዬን ማንም ባይኖርም፣ እንደ ኢንጂነሩ ሁሉ እኔም በጽናት ቆሜያለሁ። ዝምታው ቢያይልም፣ የውስጥ ድምፃችን ግን እንደ ነጎድጓድ ያስገመግማል። ዛሬ ብዕሬን የጨበጥኩት ላንተ ነው፤ ለዛ ጸጥታህ፣ ለዛ ጽናትህ፣ እናም ለዛ 'ህዝቤ ይቅደም' ለሚለው የላቀ የውስጥ አስተሳሰብህ! ክብር ይገባሃል አርበኛ እንጅነር ሲያስብ ሽዋ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
ጀብድ ሰርተው ፋኖን ለተቀላቀሉ ለአድማ ብተና አባላት ሽልማት ተሠጠ‼️
መጋቢት 08/2018 ዓ/ም
መጋቢት 01/2018 ዓ/ም የአገዛዙ 4/አራት የአድማ ብተና አባላት አዲስ ቅዳም ከመሸገው የጠላት ካፕ በመውጣት 105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለ ጦርን ሲቀላቀሉ 12 /አስራ ሁለት/ መሳሪያዎችንና 12 ትጥቆችን አስከነ ሙሉ ተተኳሻቸው ይዘው የፋኖ አባላትን መቀላቀላቸው ይታወሳል።
1ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል
2ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል
3ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል
4ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል በጋራ በመሆን፣ በሰሩት ጀብዱ ከአፋብን ሊቀ መንበር ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የአርበኝነት የምስክር ወረቀትን ጨምሮ የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱን በውክልና ያበረከቱት የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ አመራር፣የ44ኛ ክ/ጦር አመራርና የ55ኛ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ተካሄዷል።
በሽልማቱ ላይ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ፻ አለቃ ማርቆስ አሞኘ ከጠላት ጎን ወግናችሁ የአማራን ህዝብ የምትወጉ የአማራ ተወላጆች እንደወንድሞቻችሁ በየትኛውም አጋጣሚና ስዓት ብትመጡ ቤታችን ክፍት ነው።ከዚህ ውጭ ግን ምህረትና ርህራሄ እንደሌለን እንድታውቁት እንፈልጋለን ብለዋል።
ሌላኛው በሽልማቱ ወቅት መልክት ያስተላለፉት ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ44ኛ ክ/ጦር የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ በላይ አሠፋ የሠራችሁት ጀብድ ለሌሎች ሆዳም አማራዎች ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ፣ሌሎች በተሳሳተ መንገድ ሄደው ወገናቸውን የሚጨፈጭፉ አማራዎች ከናንተ ብዙ መማር አለባቸው ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃለማርያም ማሞ ክፍለጦር የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ!
መጋቢት 7 2018 ዓ/ም
የአማራን ህዝብ ትጥቁንም ቀበቶውንም አስፈትቼ እቀልድበታለሁ በሚል ንቀት ጦርነት የከፈተብን ጠላታችን ዛሬ ደሞ ምርጫ ምረጡ እያለን ነው። እኛ ጦርነት የታወጀብን አማሮች የእልውና ትግል ላይ ነን! ይህ ዛሬ ምርጫ እያለ የሚቀልድ እና በአማራ ህዝብ ላይ የእልውና አደጋ የሆነን ኃይል ፆታ ሳይለይ ሴቱንም ወንዱንም ጨፍጭፏል እድሜ ሳይመርጥ ህፃናትንም አዛውንቶችንም ረሽኗል የትምህርት ደረጃ የስራ ሁኔታ ሳይመርጥ አማራን አሳዷል ገድሏል ሌላው ቀርቶ የኃይማኖት አባቶችን ቀሳውስት ዲያቆናትን በግፍ ረሽኗል።
ይህ የአማራ ህዝብ ጠላት በህዝባችን ላይ ያልፈፀመው ምንም አይነት ምድራዊ ግፍ የለም። እንግዲህ ይህ የአማራ ህዝብ ጠላት ዛሬ ምርጫ ምረጡኝ እያለን ነው። እኛ መልሳችን ልንጥልህ እየታገልንህ ነው የሚል ነው። እያሸነፍነውም ነው። በዚህ ምርጫ በሚል ስላቅ ምክንያት ስንት ወንድሞቻችንን የሰዋንበትን ትግላችን ላይ እንቅፋት የሚሆን ሁሉ ጠላት ነው!! በሰማዕታት ደም አንቀልድም!!
እየተሸነፈ ያለ የህዝብ ጠላት ኃይል ምርጫ የሚሉት ቀልድ አይሉት ቁምነገር ጀምሯል። ምረጠኝ የሚለውም እየገደለው እና እያሳደደው ያለውን የአማረን ህዝብ ነው እየገደለን መልሶ ምረጡኝ ማለት ግዳያውን እና ጭፍጨፋውን እንድቀጥል ፍቀዱልኝ ማለት ነው።
የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በሚቆጣጠራቸው እና በሚያስተዳድራቸው ከዚህ በታች በስም በተዘረዘሩ የከሰም ሀገረማርያም ወረዳ ቀበሌዎች እና ከተሞች ውስጥ ምንም አይነት የምርጫ እንቅስቃሴ እንደማይደረግ ምርጫም እንደማይካሄድ እናሳስባለን።
፩) ሾላ 01ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ
፪) ቱለፋ ንዑስ ወረዳ ቡልጋ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
፫) ንፋስ አባ ቀበሌ
፬) ሰኮሩ ቀበሌ
፭) ጉርፎ ቀበሌ
፮) አክርሚት ቀበሌ
፯) ስቻት ቀበሌ
፰) ይርማታገር ቀበሌ
፱) ውሃ ሜዳ ቀበሌ
፲) ዛላ ዘባባ/መስኖ/ቀበሌ
፲፩) ቅዱስጌ ቀበሌ
፲፪)/የወላት ቀበሌ
፲፫)ኮረማሽ ንዑስ ቀበሌ
፲፬) የነቾህ ቀበሌ
፲፭) ሀገረማሪያም አቦ ቀበሌ
፲፮) አባ ቡኖ ቀበሌ
፲፯) የለጥ ቀበሌ
፲፰) ሰበሌጥ ቀበሌ
፲፱) ሶስት አባ ቀበሌ
፳) ሸረር ቀበሌ
፳፩) የናጉር ቀበሌ
፳፪) እንኮይ ቀበሌ
፳፫) ንብጌ ቀበሌ
፳፬) ደብረ ፅጌ
ይህ ማሳሰቢያ ተቃዋሚ ድርጅቶንም የሚመለከት ሲሆን ከላይ በስም በተዘረዘሩት አካባቢዎች ላይ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳም ሆነ ምርጫ አይደረግም ስለሆነም:-
፩ኛ) የአማራ ህዝብ ጠላት ከሆነው "ብልፅግና" ከሚባል ፀረ አማራ ድርጅትጋ በመሰለፍ በወረዳው የምርጫ ቅስቀሳ የምታደርጉ የጠላት ተወካዮች በመሆናችሁ የማያዳግም እርምጃ እንዳምንወስድ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እናተው ራሳችሁን ከጠላትጋ የተጠጋችሁ እንደምትሆኑ እናሳውቃለን።
፪ኛ) "ተቃዋሚ ድርጅት" በዚህ ወቅት የአማራ ህዝብ ለምርጫ ፖለቲካ ዝግጁ አይደለም ህዝባችን የተከፈተበትን ጦርነት እየመከተ እና ጠላትን ልክ እያገባ ባለበት በዚህ ከባድ ወቅት በምርጫ ሰበብ ፈተና ባትሆኑብን መልካም ነው። ሆኖም ግን በማን አለብኝነት ወይም በግዴለሽነት ተወካዮቻችሁን ልካችሁ የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎችን ካደረጋችሁ ተወካዮቻችሁን በቁጥጥር ስር አውለን በእስር እንደምናቆይ ንብረትም እንደምወርስ እያሳወቅን በዚህም ሂደት ለምናወጣው ወጪ በተወካዮቻችሁ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት በሙሉ ተጠያቂዎች እንደምትሆኑ እናሳስባለን።
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማር ታዘዘ የፊስቡክ አካውንት ፒጁ ሪስክ ስላለው ከታች በአለው ሊንክ እየገባችሁ free meta በሉለት https://www.facebook.com/profile.php?id=61581657125998
የፋኖ አመራርና ሰራዊት ያለበትን ቀጠና አጠቃለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው የጁላ ሰራዊት ሁለት ዲሽቃ ተኳሾቹን አስደምስሶ አንድ ብሬን አስማርኮ ተመለሰ!
መጋቢት:-07/2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር አመራርና ሰራዊት ያለበትን ቀጠና አጠቃለሁ በማለት የተንቀሳቀሰው ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ዕዝ የብልፅግና ሰራዊት በዋግ፣ ላስታ፣ መቄትና ቡግና በሰፊው የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ተመቶ ተመልሷል።
መጋቢት 05/2018 ዓ/ም መነሻውን ከላሊበላ በሹምሽሃ በሦስት አቅጣጫ ማለትም በእርፋ፣ በጉልበት ተራራ እና በሙጫ በረት ያደረገው የጠላት ኃይል 19ኛ ክፍለጦርን አጠቃለሁ በሚል በሌሊት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው የተቀጠቀጠ ሲሆን 10 ሲደመሰስበት ከ17 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስ ይዞ ተመልሷል።
በዚህ አውደ ውጊያም ላስታ ወረዳ ገለሶት ቀበሌ ከመንገድ ዳር ቤቱ የሆነው አባት አርበኛ መልካሙ አበራ ጠላት ተሰልፎ ወደ ወገን ቀጠና እየመጣ መሆኑን ሲረዳ ከጣት ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ የወረረው ደሙ እንደ እቶን እሳት የተንቀለቀለው የአባቶቹ ልጅ አርበኛው መሳሪያውንና ትጥቁን አሟልቶ ብቻውን ቀድሞ ደፈጣና ምሽግ በመያዝ የገጠማቸው ሲሆን ስድስቱን እንደደመሰሰ ተኳሹ እንዳለቀበት እና ጠላት እንደደረሰበት ሲያውቅ አንዲት ፍሬ ጥይት ስትቀረው ለራሱ በመጠቀም ታላቅ ገድል፣ ለትውልድ የሚተላለፍ አኩሪ ታሪክ ሰርቶ ተሰውቷል።
መጋቢት 06/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ጠላት በሦስት አቅጣጫ ማለትም በድሐና አምደወርቅ ወደ ቆብ፣ ከአይና ቡግና በብርኮ ወደ ቆብ እንዲሁም በዶሮላባ ጎንደር በር ቅዱስ ሀርቬይ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ብርኮ ላይ በተደረገው ውጊያ 19ኛ ክፍለ ጦር በአምስት ቦታዎች ማለትም በምሳናው በር፣ በጭቃው፣ በቴሌው፣ በውርምሽና ብርኳኳ ላይ ማጥቃት የተደረገ ሲሆን ብርኮ እና ብርኳኳ ላይ ሁለት ድሽቃ ተኳሾችን ጨምሮ 27 የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 14 ጥቁር ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቁ ተማርኳል።
በሌላ መረጃ 19ኛ ክፍለ ጦር አባት አርበኞች በድሐና አምደወርቅ የመጣውን የጠላት ኃይል ሲያርበደብዱት የዋሉ ሲሆን አንድ ብሬን፣ ስምንት ጥቁር ክላሽ ሲማርኩ ስምንት የጠላት ኃይልን ደምስሰዋል።
በመጨረሻም የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ደቡብ ዕዝ 204ኛ ኮር 38ኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት አስር አለቃ ዮሐንስ ወንድሙና ም/አስር አለቃ ሙሐመድ ሰይድ ሁለት ጥቁር ክላሽ፣ስድስት ካዝና፣ ሁለት የደረት ትጥቅ፣ 420 የክላሽ ተተኳሽ፣ ስድስት የዕጅ ቦምብ በመያዝ 30ኛ ክፍለ ጦርን መጋቢት 07/2018 ዓ/ም ተቀላቅለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ መምህር ቢሆነኝ
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 7/2018 ዓ.ም
ጠላት ያሰለጠነው ፓራ ኮማንዶ ጦር አየተናደ የምረት አዋጅን በመጠቀም ዛሬም ፋኖን በመቀላቀል ላይ ናቸዉ ‼️⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰
........መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
እነ አረጋ ከበደ ለ45 ቀን አሰልጥነው አማራን ለማስጨፍጨፍ ተማምነው ያስቀመጡት ሚሊሻ ስብስብ ፓራኮማንዶ የተባለው ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም ነው እና ሃይል እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ በተለያየ መንገድ እየተገለፀ ሲሆን ዛሬም፦
1.እርጥባን የኔነህ....1 ኮርያ ክላሽ ከግንደወይን ከተማ
2.እንዳለው ጥላሁን.. 1 ኮርያ ክላሽ ከግንደወይን
3.ስላባት አዝመራው... 1 ኮርያ ክላሽ በመያዝ ከደ/ወርቅ የፓራኮማንዶ አባላት በመውጣት 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
"አኩሪ ታሪካችን በክንዳችን ይፃፋል!"
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
♦️የአፋብን በላይ እዝ ፋኖዎች በጓህላ ከፍተኛ ቦታዎች የጠላትን ኃይል በጥይት አረር ሲቆሉት መዋላቸው ተገለጸ።
ዛሬ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም አፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮርና ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አንድ ብርጌድ በጥምረት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በ4 የአውደ ውጊያ ግንባሮች ስቦ በማስገባት ቴክኒክ ዘው ብሎ የገባውን የጠላት ኃይል የጥይት ዶፍ ሲያወርዱበት ውለዋል ።
ጓህላ ከተማን ወዲያውኑ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን ሞርተር የተባለውን የቡድን መሳሪያ በሰፊው መጠቀምም ተችሏል።
የሞርተር ድምጽን ሲሰማ የሚርበተበተው ጠላት ከተማውን ለቆ ከከተማዋ በስተ ምእራብ አቅጣጫ ከሚገኘው መሽጉ ፈርጥጦ ሊገባ ችሏል።
ከጠላት ምሽግ ድረስ ዘልቆ በመግባት በቦምብና ጨበጣ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አድርገዋል።
ከጓህላ በስተ ደቡብ አቅጣጫ ጨውጫዊት ከሚባለው ከፍተኛ ቦታ ላይ የመሸገው ጠላት በፋኖ ድሽቃ ከፍተኛ ምትን ያስተናገደ ሲሆን ለሰዋዊና ፖለቲካዊ ኪሳራም ተዳርጓል።
በዚህም ሰበብ ከመሸገበት ቦታ ተወስኖ ብቻ እንዲቀመጥ ተደርጓል።
♦️በጠለቀ የጀግንነት ወኔ እየፎከረና እየሸለለ የገባው የወገን ኃይል የስነ ልቦና የበላይነት ከመጎናጸፋም በላይ የጠላትን ኃይል የማከናወን አቅም እንዲሟሽሽ ማድረግም ተችሏል።
➛ በዛሬው አውደ ውጊያከተገኙ ድሎች
✔️11 እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።
✔️ 06 ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል። ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2 ቀናት በፊት ማለትም በቀን 05/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አህዶች ወርሃላ ዙሪያ ፣ ማዛርብ ፣ስሁር ፣ አላንጌ እና ፈንጣን ጨምሮ ከብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል ጋር ውጊያ የተካሄደ ሲሆን በውጊያውም 06 ጠላት ኃይል ክፉኛ ቁስለኛ መሆኑ ታውቋል።
ብልጽግና የመጭውን ስርዓታዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ በፋኖ ፈርጣማ ክንድ የለቀቃቸውን ከተሞች መልሶ ለመያዝ በሰማይና በምድር የታገዘ ውጊያዎችን እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ የካቲት 07/2018 ዓ.ም
#ሰበር_ዜና‼️
በሬማ ከተማ ዙሪያ የሚኖሩ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ መጠን የተጣለበት የገንዘብ ተመን ካላዋጣችሁ በሚል በኃይል በመደብደብ ላይ በነበሩ የብልፅግናው ሰላም አስከባሪ ወንበዴዎች ላይ ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን አስታወቀ❗️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
መጋቢት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የአገዛዙን ዕድሜ በማራዘም፣ በህዝባችን ላይ ተጨማሪ የመከራና የጭቆና ዓመታትና የባርነት ዘመንን ለመጫን፣ በአገዛዙ ወታደሮች በየቀኑ እየተጨፈጨፈ ያለውን የአማራን ህዝብ በጉልበት በማስገደድና በኃል ድብደባ በፈፀሙ የዘመናችን ጥቁር ጣልያኖች ላይ ሰራዊታችን ያለምንም ርህራሔ ለአገዛዙ ዕድሜ ማራዘሚያ የሚሆን የገንዘብ መዋጮ በሚጠይቁ ካድሬዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ ከድርጅቱ በወረደለት ትዕዛዝ መሰረት በሬማ ከተማ የሚገኙ የአገዛዙ ሎሌ ወንበር አስጠባቂዎች ላይ የመጀመሪያውን ቅጣት በጀግኖቹ የአስማረ ዳኜ ልጆች መወሰዱን ኮሩ አስታወቀ።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ የሚዳና ሬማ ወረዳ በሬማ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ላይ በከተማው ዙሪያ ያሉ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ያለ ፈቃዳቸው በኃይል ለብልፅግና ፓርቲ መዋጮ እንዲከፍሉ በ30 የሚሊሻ አባላት ከየቤታቸው ተደብድበው በአስገዳጅነት የተፈፀመውን ኢ-ዲሞክራሲ በሆነ መንገድ በወንጀል ስራ ላይ በነበሩ የወረዳው ሰላም አስከባሪዎች ላይ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የአፄ ዳዊት ክፍለጦር በጀግናው አስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ መብረቃዊ ርምጃ መውሰዱን ኮሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል።
መረጃው እንደደረሳቸው በቦታው ላይ ተወርውረው የተገኙት የክፍለጦሩ አስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ ቃኝዎች በወሰዱት ድንገተኛ ጥቃት በሬማ ከተማ ዙሪያ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ያለ ፈቃዳቸው ለአገዛዙ ዕድሜ ማራዘሚያ የተጣለባቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ኃይልን በመጠቀም በድብደባ ላይ በነበሩ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ሲወስዱ ቀሪዎቹ እግሬ አውጭኝ ብለው በመፈርጠጥ ነብሳቸውን ያተረፉ ሲሆን ከባድ ጉዳት ያስተናገዱትን የሚሊሻ አባላት ወደ አለም ከተማ እናት ሆስፒታል በሪፈር መላካቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ሀኪም አበበ አላዩ ገልጿል።
አርበኛው በመልዕክቱ እንደገለፀው የአስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ በወሰዱት መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ የሰላም አስከባሪ አባል በሆነው አቶ ሽትዬ አባቡን ጨምሬ በሌሎች ለጊዜው ስማቸው ባልታወቀ አባላቱ ላይ ርምጃ በመውሰድ ለወንጀል መስሪያ ሲጠቀሙበት የነበረውን ሁለት ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ መማረካቸውን ያስታወቀ ሲሆን አሁንም ከጠላት ጋር በመሰለፍ ህዝባችንን ለተጨማሪ ጥቃት አሳልፎ የሚሰጥን ማንኛውንም አካል የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂዎች ላይ ሰራዊታችን የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አሳስቧል።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
አንድነታችን አሸናፊነታችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 07 /2018 ዓ.ም
ጄኔራል ተፈራ ማሞ - የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ለኮማንዶ ተመራቂዎች ያስተላለፉት መልዕክት!
አፋብን💪
የክህደት ድግስና የማይበገረው የአማራ ህዝብ የአድማስ ጋሻ
በቤተ-መንግሥቱ ጨለማ ኮሪደሮች ውስጥ የክፋት አዝመራቸውን ለመሰብሰብ የሚጣደፉ አፈ-ቀላጤዎች ተሰብስበዋል። እነ ቂስ ሞገስ ዳንኤል ክስርት የቃላት መርዛቸውን እንደ ማር እያጣፈጡ፣ የአማራን ሕዝብ ታሪክ ከመጽሐፈ-ሕይወት ለመደምሰስ ይዶልታሉ። እነዚህ የአገዛዙ ዳይፐሮች የጌታቸውን የጥፋት ጉዞ በውሸት ሽቶ ለመቀባት ቢሞክሩም የሴራቸው ጠረን ግን ከአድማስ ባሻገር ይከረፋል።
ቢሳካላችሁማ የአማራን ዘር ከምድር ገጽ አጥፍታችሁ በታሪክ መቃብር ላይ የክህደት ድንኳን ትተክሉ ነበር። ነገር ግን ይህ ሁሉ የፕሮፓጋንዳ ጩኸትና የመንገድ ላይ ስልት ከውድቀታችሁ በፊት የምታሰሙት የባዶነት ድምፅ መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ግን በአድማስ ማዶ አንድ ታላቅ ኃይል እንደ ንጋት ኮከብ በርቶ ይታያል።
የአማራ ዲያስፖራው ለወገኑ የማይናወጥ ደጀን ለአብይ አህመድና ለተከታዮቹ ደግሞ እንደ አረም ማጥፊያ መድኃኒት ሆኖ ብቅ ብሏል። ጠላቶቻቸው በድንጋጤ የሚመለከቱት ይህ ኃይል፣ የጥፋት መርዛቸውን የሚያክሽፍ እውነተኛ ጋሻ ነው።
አሁን ሰዓቱ የንግግር ሳይሆን የሥራ ነው፤ የጩኸት ሳይሆን የጥበብ ነው። በውጭ የሚኖረው ወገን ነገሮችን በብስለት የሚመዝንበት፣ ሥራዎችን በብልጠትና በስትራቴጂ የሚመራበት የመጨረሻው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ታሪክ ይመሰክራል የጥላቻው ማዕበል በአለት ላይ ተጋጭቶ ይፈራርሳል፣ የሕዝቡ ጽናት ግን እንደ ዐባይ እየገሰገሰ ይቀጥላል። Dawit Amhara ከግንባር
