ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше2 955
Підписники
+424 години
+127 днів
+38830 днів
Архів дописів
ጎንደር ✊💪
ደራርቦ ማራኪው ሜጀር ጀነራል ዉባንተ አባተ 1ኛ ኮር በትናንትናው ዉጊያ የተቀረፀ ቪዲዮ✌️
የአብይን የሴራ ፖለቲካ የምናጋልጥበት ሰፊውን ስራ ይወዘን ብቅ ብለና የፊስቡክ አካውንታችን ይወዳጁን!!
https://www.facebook.com/share/1CmD4FL3eb/
#ህዝብን_የካደ_መጨረሻው_ሞት_ነው‼️
የጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝና የአብይ ወንበር ለማስጠበቀ የተሰለፈና በገዛ ሕዝብ ላይ እልቂት እየፈፅሙ መኖር አብቅቷል።
አሁንም አልረፈደም፡ ከጠላት ጎን ተሰልፋችሁ የምትገኙና ወደ አሸናፊው ለመዝለል አጥር ላይ ተንጠልጥላችሁ የተቀመጣችሁ ሰዎች ባስቸኳይ ሕይወታችሁን አትርፉ።
ሲሆን የሕልውና ትግሉን ተቀላቅላችሁ ህልውናችሁን አስከብሩ፡ ካልሆነ ግን ለልጆቻችሁና ለቤተሰባችሁ ለመኖር ከአገዛዙ በመውጣት ሕይወታችሁን አትርፉ።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ በፈፀመው ከባድ ጥቃት ከተገደሉ የመከላከያ ሻለቃ አዛዥ ጨምሮ ብዛት ያለቸዉን የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ወታደሮች መካከል የጥቂቶች ምስል ነው።
#እጅ_ስጡ_አትለቁ‼️
#ከአንገት_በላይ #ስፔሻሊስቱ ፋኖ ይችላል💪
07/ዐ9/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር
44ኛ ክፍለ ጦር ምዕራብ ጎጃም-ሰከላ- አጉት ከተማ ላይ ሻለቃ አዛዡን ጨምሮ በመደምሰስ ድል ተቀዳጄ።
ግንቦት 7/9/2018 ዓ.ም
105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ ላይ በወሰደዉ መብረቃዊ ጥቃት ብዛት ያለዉን የጠላት ሀይል ደምስሷል።
ከየቤቱ እያስወጣ የምርጫ ካርድ ውሰዱ በማለት እያስገደደ ባለበት አጭር ሰሃት 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ተወርውሮ በመድረስ የብልፅግና ስርዓት ጠባቂውን ቡድን ጉሩቦውን እያነቀ የመከላከያዉን ሻለቃ አዛዥ ጨምሮ ብዛት ያለቸዉን ዘራፊ ቡድን እስከወዲያኛዉ ማስወገድ ችሏል።
ክፍለ ጦሩ ዛሬ ሰከላ ወረዳ አጉት ላይ በፈፀመዉ ጥቃት ጠላት ሬሳውን እና ቁስለኛው ማንሳት ሳይችል በመፈርጠጥ ቤተክርስቲያን መሽጎ ቢተርፍም በደርዘን የሚቆጠር ክላሽና በሺዎቹ የሚቆጠር ተተኳሽ አስታጥቆናል።
44ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም
12 ክላሽ
1 የሻለቃ መሪዉ ሽጉጥ
2 መገናኛ
180ዐ የክላሽ ተተኳሽ
720 የብሬን ተተኳሽ ተማርኳል።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
የአፋብን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ
+7
@የ66ኛ ክ/ጦር ጥቅል ግምገማ:-
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ለ4 ተከታታይ ቀናት ጥልቅ ድርጅታዊ ግምገማ አካሄደ።
ግምገማ እና ክትትል ለአንድ ድርጅት አመራሮች እና በስሩ ላሉት አባላት ተጠያቂነትን እና ሁለንተናዊ የድርጅቱ መመሪያን ወይም
መርህን መከተል እና ማክበር ይቻል ዘንድ ተግባር እና ኃላፊነትን በመገምገም መዋቅራዊ ፍተሻ በማድረግ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ ተችሏል።
የቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና የ105ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት የክ/ጦሩን ጠንካራ ጎን በማበረታታት እና ዉስን ክፍተቶችን በማሳየት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ የክ/ጦር አመራሮች፣ የሻለቃ አመራሮች እንዲሁም የ3 ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት የሰከነ ዉይይት በማድረግ ወደ ድል ማማ ወይም ከፍታ በመዉጣት ላይ
መሆናችንን በተግባር የታየበት መድረክ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ።
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !!!
በጠገዴ ወረዳ ከነ ዋዋዉ መንደር የ305ኛ ኮር የተውጣጣ ኃይል ከፍተኛ ትንቅንቅ እንዳደረገ ተዘገበ!!
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ የ305ኛ ኮር 76ኛ ክፍለ ጦር ከ1ኛ ሬጅመንት፤ ከ3ኛ ሬጅመንት እና ከ4ኛ ሬጅመንት የተዉጣጣ ሃይል በጠገዴ ወረዳ ሰጋሎ ከተማ በትናንትናው ቀን ግንቦት 06/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:00 ጀምሮ በ3 አቅጣጫ የተንቀሳቀሰዉ የብልፅግና ወራሪ ኃይል ሰጋሎ ከተማ መውጫ አጥቶ አሳሩን በልቷል።
ከሳንጃ ከተማ በመነሳት ወደ ሰጋሎ፤ ከአሸሬ ከተማ በመነሳት ወደ ሰጋሎ ከተማ እና ከቅራቅር በመነሳት ወደ ሰጋሎ ከተማ በተለያዩ አቅጣጫ እንቅስቃሴ ያደረገዉን የአብይ አህመድ ወታደር በተመረጡ ሶስት ቦታዎች ላይ በደፈጣ ተመቷል።
በወታደር ልምድ ባላቸዉ ጠበብት መሪዎች እየተመራ እስትራቴጅካል ቦታዎችን ይዞ አድፍጦ በመጠበቅ በተወሰደዉ እርምጃ በጠላት ላይ መጠነ-ሰፊ ኪሳራ ደርሷል። በአውደ-ውጊያው መጨረሻ በተሰበሰበው የወገን መረጃ መሰረት ጠላት
#ሙ*ት= 50
#ቁስለኛ = 25 በላይ ኪሳራ አስተናግዷል።
በሌላ በኩል 305ኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በስናር፣ በአዲስ-ዓለም፣ በጎደቤ፣ በአምቶከልና መሰል ቀጠናዎች ቀጠናውን በፋኖ ስም ከሚንቀሳቀሱ ዘራፊዎች የማፅዳቱ ተልዕኮ ቀጥሏል። በዚህም ከማህበረሰቡ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍና እገዛ እየተደረገላቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል።
ህልውናችንን በተባበረ ክንዳችን እናረጋግጣለን!!
ባንዴራዉ ግርማይ የ305ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም
የአማራ ልጅ ፋኖ ይለያል እኮ እኛ ከግንባር እንዲህ መረጃዎች እወነቱን ይዘን በአራቱም ማዕዘን እናደርሳችኃለን ቴሌግራም ቻናላችን ይወዳጁን
ሰበር ዜና!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦርን ለማጥቃት የመጣውን የጥላት ሀይል በመልሶ ማጥቃት ድባቅ ተመታ!
ጠላት ግንቦት 07/2018ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት በአድስ አለም በርና በስንደዶ በር የ12ኛ ክፍለጦርን ከበባ ውስጥ ለማስገባት በሁለት(2) አቅጣጫ ሙከራ ቢያደርግም ሳይሳካለት ውርደትን ተከናንቦ ተቀጥቅጦ ተመልሷል።
የቀድሞው የዞብል አምባ ክፍለጦር የሰራዊት አባላት የአሁኑ የ12ኛ ክፍለጦር ልማደኞቹ በሁሉም አቅጣጫ የመጣውን የአብይ አህመድ ቅልብተኛ ወታደር በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት መጠነ ሰፊ ኪሳራ አድርሰውበታል።
በአርበኛ ሀብተማሪያም መንበሩ የሚመራው የ12ኛ ክፍለጦር በሻለቃ በመከፋፈል በሁሉም አቅጣጫ የመጣውን የጥላት ቅጥረኛና ወራሪ ሀይል ላይ ቀድሞ ገዥ ቦታዎችን በመያዝ በሞርተርና በድሽቃ እንዲሁም በመትረየስና በስናይፐር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።
ስግብግቡ፣ በእውር ድንብር የሚመራውና ስሌት የሌለው የብልፅግና ጨፍጫፊ አገዛዝ በአቀደውና በአለመው ልክ ሳይሳካለት ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ እያንጠባጠበ ክንደ ብርቱዎቹን 12ኛ ክፍለጦር መቋቋም አቅቶት ወደ መጣበት በሽንፈት መመለስ ተችሏል።
የ102ኛ ኮር የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የ12ኛ ክፍለጦር የሰራዊት አባላት የጦር ሰፈራቸውን ሳያስደፍሩ ዛሬም እንደትናንቱ ክብራቸውን በማስጠበቅ የሀይል የበላይነት ወስደውበታል። ጥላት የ12ኛ ክፍለጦር አሀድ የሆኑት በ1ኛ ሻለቃ፣በ2ኛ ሻለቃና በ3ኛ ሻለቃ ብርቱ ምት በመፍረክረኩና አስከሬን ለማንሳት ባለመቻሉ የአየር ሀይል ቢጠቀምም ክንደ ነበልባሎችን ማቆም ተስኖት ውሏል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖን ጥቃት መቋቋም ያቃተውና ቤተ-ክርስቲያን በማውደም የሚታወቀው አገዛዝ ሆርማት ሆኖ በግምት ባስወነጨፈው መዲፍ በዋጃ ከተማ የቅርብ ርቀት በተለምዶ ዋልካ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሁለት ሲቪልና ስድስት ከብቶችን ገድሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 07/2018 ዓ.ም
የሕልውና ትግላችንን የሚፈታተኑ ድንበር ተሻጋሪ ምላሶች ሊቆረጡ ይገባል።
ግንቦት 7/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር
እያደረግነው ያለው የህልውና ትግል ድርጅት አለው። ድርጅታችንም #አፋብን ነው። የድርጅታችን 4 ግዙፍ ቅርንጫፎች (Branches) አሉት። እነሱም:-
፩) አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ
፪) አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ
፫) አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ
፬) አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ናቸው።
ከላይ የተቀመጡት ዋናዎቹ የድርጅታችን ክፍሎች መሬት ላይ እየተዊደቁ ባሉ እንቁ መሪዎች የሚመሩ ናቸው።እንደ አማራ እየተደረገ ያለው ይህ መራር የህልውና ትግል በድንበር ተሻጋሪ ረጅም ምላሶች ሊታመስና ሊበጠበጥ( disturb) በፍፁም አይገባም። ድርጅታችን በሁሉ የተካኑ(Main profesionals) የታጨቁበት ድርጅት ነው #አፋብን። በምናደርገው የትግል ጉዞ የሚፈጠሩ የውስጥ ችግሮቻችን ሰከን ብለን የመፍታት ጥበቡም አቅሙም አለን። ነገር ግን የሚገጥሙንን ጥቃቅን የውስጥ ችግሮችን ለድንበር ተሻጋሪ ረጃጅም ምላሶች አሳፈልፎ የሚሰጥ ምስጢር (Secret) አባካኝም አይጠፋም። ይህ በመኖሩ መሬት ላይ እየታገሉና የህልውና ትግሉን ከሚመሩት ጀግኖች በላይ ውስጥ አዋቂ መሳይ ድንበር ተሻጋሪ ምላሶች በየሶሻል ሚዲያው ሲውለበለቡ ይስተዋላሉ። ይህ አይነት ቅጥ ያጣ አንዱን ታጋይ ከሌላው ነጥሎ በማጀገን አንዱን በማንቋሸሽ በትግሉ መሪዎች መካከል አለመተማመንና አለመግባባት እንዲፈጠር በማድረግ የህልውና ትግሉ ወደ ድል የሚያደርገውን ጉዞ ለመግታት የሚደረግ ደጋፊ መሣይ አደገኛ እንቅስቃሴን የትግሉ መሪዎችም ታጋዩም ሁላችንም በመንቃት ድንበር ተሻጋሪ ረጅም ምላሶችን በመቁረጥ ረፉ ልንላቸው ይገባል። የምናደርገው የህልውና ትግል የውስጥም የውጭም ድጋፍ ያስፈልገዋል። የሚደረግለት ድጋፍ ግን ፍፁም ጤናማ(Good Health) የሆነ መሆን አለበት። ያ ማለት በሐሳብ፣ በጉልበትና በገንዘብ መደገፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። በአንፃሩ ግን ከፋፋይነት፣ ወሸትና አቃጣሪነት የህልውና ትግላችንን የሚረብሹና በትግሉ መሪዎችና በታጋዩ መካከል ስንጥቅን የሚፈጥሩ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ ጤናማ ያልሆኑ (Unhealthy) ድንበር ተሻጋሪ ምላሶችን መቁረጥና ረፉ ማለት መሬት ላይ ሕይወት እየተገበረበት ያለውን የህልውና ትግል የሚመሩ መሪዎች ዋናውና ቁልፍ ተግባራችን ሊሆን ይገባል። በድርጅታችን #አፋብን ውስጥ ያሉ መሪዎች አንዱና ትልቁ የኃላፊነት መለኪያቸው ምስጢር ጠባቂነት (Confidentiality) ነው። በትግሉ መሪዎች መካከል ምስጢር ጠባቂነት ካለ ድንበር ተሻጋሪ በጥባጭ ረጅም ምላስ አይኖርም። እንደ #አፋብን በአራቱም የአማራ ግዛት ያለን የድርጅቱ መሪዎች እያደረግነው ያለውን የህልውና ትግል በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ፣ የውስጥ ችግሮችን በጊዜ በመፍታትና በውስጥ መያዝ ያለባቸውን ምስጢሮችን አሳልፎ ባለመስጠት ለራስ ንስሐ መግባትና ለጣልቃ ገቦችና ለከፋፋዮች አሳልፎ ላለመስጠት መቁረብ የህልውና ትግላችን የሚፈልገው ቀዳሚው ተልኳችን መሆን አለበት። በመጨረሻም ጤናማና አስታራቂ ሐሳብ የሚናገሩ ድንበር ተሻጋሪ ምላሶችን እያበረታታን ለህልውና ትግላችን መቋጨት ይፈጠን ዘንድ ፍፁም ጤናማ የሆነ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ስንል በተሰው ሰማዕታት ጓዶቻችን ስም አደራ እንላለን!!!
ክብር ለትግላችን ሰማዕታት!!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዐዝ 206ኛ 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል
#ለአብይ_አህመድ_የተከፈለ_ውድ_ዋጋ‼️
ትናንት ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር በጎንደር ቀጠና በተለያዩ ግምባሮች የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ድባቅ የመታና ተተኳሽና መሳሪያዎችን የማረከ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አማራ ምድር በመምጣት እየወደቁ የሚቀሩ ኢትዮጵያን በቃን ለአገዛዙ ወንበር መፅናት ህይዎታችንን አንገብርም በማለት እምቢኝ ይሉ ዘንድና ከፋኖ ጋር በመቀላቀል ውድ ህይዎታቸውን ያተርፉ ዘንድና ይማሩበት ዘንድ ይህን ቪዲዮ ተለቋል‼️‼️
የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ....!
ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ ኢትዮጵያ ሰላም የላትም ስለሆነም ሁሉም ይህንን ስርዓት በጋራ ይታገል‼️
07/ዐ9/2018 ዓ.ም
ማሕደረ ማርያም የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/
✅ጉና ክፍለ ጦር፦ ስር ያሉት
👉መቅደላ አምባ ብርጌድ እና
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ ታላቅ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡
ማሕደረ ማርያም ከተማን ለመቆጣጠር በሜካናይዝድ ደረጃ በ4 አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ ተመቷል፡ በድሮን የታጀበ ጥቃት ከፍቶ ማሕደረ ማርያምን ለመያዝ ቻለ። ሠማዩ የጠራና ለድሮን ምቹ መሆኑን የተረዱ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ራሳቸውን ከድሮን ጥቃት በጠበቀ መልኩ ውሥን ሰዓታትን ጠብቀዋል።
ከጠዋቱ 5:00 ገደማ ሰማዩ በደመና ሲሸፈን የክፍለ ጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ ልዩ ግዳጅ ፈጻሚ የሆኑ ከ50+ የከተማ ዘመቻ ጠበብት ዓምሐራ ፋኖዎችን መሐል ማሕደረ ማርያም ከተማ በማሥገባት በተመረጡ ምሽጎችና በተመረጡ የመከላከያ አመራሮች ላይ ፈጣን ማጥቃት በማድረግ ውጊያውን ጀምረዋል፡፡
መሐል ከተማ ውጊያው ሲጀመር ከተማውን የከበቡት የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 2 ብርጌዶች ከውጭ ወደ ውሥጥ ማጥቃቱን አሥከተሉ። ወድያውኑም የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ የእጅ ሥራ የሆነው የጉና ክፍለ ጦር 02 ብርጌዶች፦
👉መቅደላ አምባ ብርጌድ እና
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ በጋራ
በዕብሪት ማሕደረ ማርያም ከተማ የገባውን መከላከያ ከጥቅም ውጭ አድርገውታል፡፡ አገዛዙ ድሮን ባይደርስለትም ከባድ መሳሪዎችን ቢጠቀምም ከፋኖ ሽንፈት አልዳነም፡፡
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ አብራኮች በአርበኛ ቻላቸው አገኝ፣ በአርበኛ ተመሥገን ውባንተ፣ በአርበኛ ደርሶ ይኹኔ ጥሩ እየተመሩ የአገዛኡዝን ምሽጎች አፍርሰውታል፡፡ በውግያው የአገዛዙ ከፍተኛ አመራሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ02:00 ሠዓታት እልህ አሥጨራሽ ውጊያ በኋላ ከቀኑ 07:00 ላይ የአገዛዙ ስልጣን ጠባቂ በኃይል ተምበርክኮ የማሕደረ ማርያምን ምሽግ ለቀቀ። ከማሕደረ ማርያም ተገዶ እንዲወጣ ተደረገ። ይህ ኃይል በሙሉ ተጠቅልሎ እንዲወጣ የተገደደው ወደ ግንዳ ጠመም-እሥቴ አቅጣጫ ሲሆን ከቀኑ 07:00 እሥከ ምሽት 01:30 እልህ አሥጨራሽ መደበኛ ውጊያ ተደርጓል። የአገዛዙ መከላከያ የተመካባቸው የግንዳ ጠመም ተራሮች በፋኖዎች ተደፍረዋል።
ማሕደረ ማርያም የጀመረው አውደ ውጊዬ አድማሱን አሥፍቶ ወደ ክሬቸር፣ ገንሸል፣ ናዳ፣ መተረይ፣ ዘገቦ፣ ጺዎን፣ ሹማ ባሌ፣ ፣ ረቻ ገብርኤል፣ ግንድ አጠመም መድኃኒዓለም፣ ግንዳ ጠመም ከተማ፣ ጋዤን፣ ልደታ፣ እጃግሬ፣ እማወተት ጊዎርጊሥ፣ ምሰሽ ቆይኝ ሚካኤል፣ አባ እሱባለው መገንጠያ፣ መተረይ እና ጋዠን ላይ እልህ አሥጨራሽ ውጊያዎችን አድርገው በድል ተወጥተዋል።
ዋንዛዬ እና አርብ ገበያ ከተማ ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ጀብዱ ፈጽሟል፡፡
ግዙፉ ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦርን ''ዋንዛዬ'' ከተማ ላይ ለማፈን በ 4 አቅጣጫ ማለትም፦በሰገጅ ማሪያም፣ በሐሙሲት፣ በበክስ እና በአምበሳሜ በኩል የመጣው የአገዛዙ ኃይል ተመቷል፡፡ 'ሰገጅ ማርያም'' እና ዋንዛዬ ከተማው ላይ ለማፈን ሞክሮ በጣና ገላውዴዎሥ ፋኖዎች ጥቃቱ ተመክቷል፡፡ እንደ ንስር ታዳሾቹ ጣና ገላውዴዎሦች በአገዛዙ ላይ የሥነልቦና የበላይነትን፣ የአካልና የቁሥ ኪሳራ አድርሷል፡፡
ከበባውን ሰብረው የወጡ ብርጌዶች መካከልም ''አፈር ውኋ ዕናት ብርጌድ'' ፋኖዎች የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆኑት መቅደላ አምባ ብርጌድ እና ገብረ መሥቀል ብርጌድ ማሕደረ ማርያም ከተማ ላይ ውጊያ መሆናቸውን እንደተረዱ በብርሐን ፍጥነት ከዋንዛዬ አርብ ገበያ ከተማ በመድረሥ አርብ ገበያ ከተማ የከተመውን የብርሐኑ ጁላ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ አድርገውታል።
አውደ ውግያው ቀጥሎ ከግንዳ ጠመም እሥከ ልጫ
የጉና ክፍለ ጦር ቃኝና መሐንዲሥ እና የክፍለ ጦሩ ሥራ አሥፈጻሚ፦
✅ በአርበኛ አዛዥ ደሳለኝ እና
✅በአርበኛ ወንዱ አንተ አሰፋ እየተመሩ ጀብዱ ፈጽመዋል፡፡
ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 2 ብርጌዶች ጋር በጥምረት ከማሕደረ ማርያም ተመትቶ ወደ ግንዳጠመም የሸሸው ኃይል ከግንዳ ጠመም እሥከ ልጫ እንዳይንቀሳቀስ አድርገው በከበባ እንዲመታ አድርገዋል። ግንዳጠመም ላይ ልክ እንደ ማሕደረ ማርያም የጨበጣ አውደ ውጊያ ተካሂዷል። የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትም ይህ ቦታ መካነ መቃብሩ እንደሆነ በተደጋጋሚ አይቶ ወጥቷል፡፡
ገላውዴዎሥ ከተማ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲሥ
የ1ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲሥ ሰራዊት በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ዋና ኃላፊ አርበኛ ''ቢራራ ደምሴ መንግሥቴ'' እየተመራ ከአምበሳሜ የመጣው ዙ-23 እና መሰል ሜካናይዝድ መሣሪያዎች ከባድ አውደ ውጊያ ወደሚደረግበት ግንዳጠመም እንዳይደርሥ ለማድረግ ገላውዴዎሥ ቴሌ ላይ ዌጊያው ተጀምሯል። ውጊያውም አድማሱን አሥፍቶ ሙሉ ገላውዴዎሥ ከተማ፣ ውባንተ ተራራ፣ ሞሻ፣ ጉማራ፣ ልጫ እና በሌሎች ቦታዎች ተደርጓል። በዚህ ውጊያ የጠላት ኃይል ለሆድ ዘመዱ እንዳይደርሥ ተደርጓል። በጠላት ላይም ቁሳዊና አካላዊ ኪሳራዎች ደርሰዋል።
05. እሥቴ(መካነ ኢየሱስ)
✅ጉና ክፍለ ጦር
👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ሥሪቶቹ አናብሥት እሥቴ ዴንሳዎች ወንድሞቻቸው ከባድ ትንቅንቅ ላይ መሆናቸውን ሲረዱ ረዢም ርቀት ተጉዘው የእሥቴ መናገሻ ወደሆነችው መካነ ኢዬሡሥ ከተማ በመግባት የአቢይ አሕመድን ጥምር ኃይል ከደንጎልት ጀምረው ሙሉ መካነ ኢየሱስ ከተማን ተቆጣጥረው አምሽተዋል። ውጊያ ያደረጉትም በቀበሌ 03፣ 02፣01 እና ሙሉ የመካነ ኢየሱስ ከተማ ነው። በጠላት ላይ የሥነ ልቦና የበላይነትንና የአካል ጉዳትን አድርሰዋል። ዘገባውን የአፋብን ሰሜን ዓምሐራ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅ ዓለው ፀጋ አለባቸው አጠናቅሮታል፡፡
የዜጎቹን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ እሱ ቀጥታ በመጨፍጨፍና ለጥቃት በማመቻቸት የተጠመደም የብልፅግና አገዛዝ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ላይ በተፈፀመ ጥቃት የ30 ዜጎች ሕይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆኗል ተባለ!
የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ባለበት አካባቢ የክልሉ ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ በለበሱ ታጣቂዎች የተፈፀመው ይሄው አሰቃቂ ጭፍጨፋ፡ የሥርዓቱን መላሸቅና ከጥፋት ኃይሎች ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት ይፋ ያደረገ ነው ተብሏል።
ግንቦት 04/2018 ዓ/ም እለተ ማክሰኞ ጠዋት በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ የታቀደና አሰቃቂ ጥቃት ተፈፅሟል።
ጥቃቱ የተፈፀመው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ባለበት አካባቢ መሆኑን የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል።
ዜጎች በካምፕ አቅራቢያ ታግተው ሲታረዱና ሲዘረፉ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ዝምታን መምረጡ የስርዓቱን ተባባሪነት የሚያሳይ ነው።
ጭፍጨፋውን የፈፀሙት ታጣቂዎች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል የሚለብሰውን ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱና እንደ ብሬንና ስናይፐር ያሉ የቡድን መሣሪያዎችን የታጠቁ መሆናቸው ታውቋል።
ይህም ጥቃቱ በአገዛዙ መዋቅር ውስጥ ባሉ ኃይሎች የተቀነባበረ ስለመሆኑ ያረጋግጣል።
ታጣቂዎቹ አውቶብሶቹን አስቁመው ተሳፋሪዎችን ወደ ጫካ ካስገቡ በኋላ ንብረታቸውን ዘርፈው በመሬት ላይ በማንበርከክ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽነዋቸዋል።
በዚህም ምክንያት ቢያንስ 30 ሰዎች ወዲያውኑ የተገደሉ ሲሆን ሌሎች ከ50 በላይ ተጓዦች ደግሞ ለከባድ ቁስል ተዳርገዋል።
በቆሰሉ ወገኖች ላይ የደረሰው ግፍ ሳይበቃ፡ መንገዶች በመዘጋታቸው ምክንያት ተጎጂዎችን ወደ ሆስፒታሎች ወስዶ ለማከም ባለመቻሉ በአንድ አነስተኛ ጤና ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ተጎጂዎች መካከል የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ በመተከል የደረሰው ጭፍጨፋ የብልፅግና አገዛዝ ስርዓት ዜጎችን ከመጠበቅ ይልቅ ለጥፋት ኃይሎች ማመቻቸቱንና ንፁኋንን ለሞት አሳልፎ መስጠቱን የቀጠለበት አሳፋሪ ክስተት ነው።
+1
የ፩ኛ ኮርን ቀጣና በአራት አቅጣጫ የወረረው ጠላት ሲቀጠቀጥ ውሏል። ሶስት ድሮኖችን በአንድ ጊዜ አየር ላይ በማሰለፍ በብዙ አጣጫ የተንቀሳቀሰው ጠላት በደራ- ዋንዛዬ፣ አርበያ ገበያ፣ ጉራምባ፣ ፋርጣ- ማህደረ ማርያም፣ እስቴ- መካነ እየሱስ ከባድ ምት አርፎበታል። መካነ እየሱስ ከተማ በአሁኑ ሰዓት በሰራዊታችን እጅ ይገኛል።
በዕለቱ ውጊያ አንድ ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ስናይፐር፣ ክላሽ እና በርካታ ተተኳሽ ተማርኳል።
ይቀጥላል...
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ በምዕራብ ወሎ ግንባር በዘረ-ፈጁ እና ጨፍጫፊው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ድልን ተቀዳጀ!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለጦር አትሮንስ ሻለቃ ከአማራ ሳይንት(አጅባር) ከተማና ከመሃል ሳይንት(ደንሳ) ከተማ ከወርቅ ማውጫ እስከ መሃል ሳይንት ትምህርት ቤት የጠላት ጥምር ጦርን ማለትም መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ ብተና፣ ሚኒሻ እና የፓሊስ ሀይሎች ላይ በእነ አልሞ አይስቴ የቀኝአዝማች ይታገሱ አራጋው ልጆች ለወሬ ነጋሪት ሳይተርፍ ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል።
የአትሮንስ ሻለቃ አናብስቶች የጠላትን እንቅስቃሴ ቀድመው በማንበብና የጠራ መረጃ በመስራት ለማጥቃት የመጣውን ወኔውንም ጥበቡንም የተነጠቀውን የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ደፈጣ ውስጥ በማስገባት አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። በዚህ አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች ሰብዓዊ ጉዳት፦
✅ የተደመሰሰ 45 የጥምር ጦር አባላት
✅ 38 ቁስለኛ
ከጠላት የተገኘ (የተማረከ) መሳሪያ፦
✅ ክላሽንኮቭ =9
✅አብራራው=3
✅ ፋል=1
✅የብሬን ተተኳሽ=1700
✅የክላሽ ተተኳሽ=812
✅ቦንብ=18
✅የወገብ ትጥቅ=18
ከዚህ በተጨማሪም ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጠላት ሲጠቀምበት የነበረ ሶስት(3) መኪኖች ከጥቅም ውጭ ማድረግ ተችሏል ሲል የክፍለጦሯ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኋላፊ አርበኛ እዮብ አሸናፊ አስታውቋል።
©አፋብን ወሎ- ቤተአማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረ የብልፅግና ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 30ኛ ክፍለ ጦር ቃኝዎች ባደረጉት የደፈጣ ጥቃት ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረውን የብልፅግና ሰራዊት ሰኞ ገበያ ከምትባል ቦታ ደፈጣ በመጣል ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲያስተናግድ ተደርጓል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ግንቦት 06/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ ጧቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን ሁለት መድፍ፣ አምስት ኦራል፣ ሁለት ሲኖትራክ፣ ስድስት አይሱዙ፣ ሶስት ፓትሮል ከነሙሉ ቁሳቁሱ ግራና ቀኝ አጅቦ ለማሳለፍ በተንቀሳቀሰበት ጊዜ ፋኖዎቹ ገዥ ቦታና ደፈጣ በመያዝ የጠላትን ኃይል ሲያራግፉት አርፍደዋል።
በተደረገው የደፈጣ ጥቃት ኦፕሬሽን 16 የተደመሰሰና 11 የቆሰለ ሲሆን በደረሰበት መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት የተደናገጠው የብልፅግና አገዛዝ ጦር ዙ-23 መሳሪያን በመጠቀም በዘፈቀደ በመተኮስ የሁለት(2) አርሶ አደሮችን ቤትና ንብረት ማቃጠሉ ታውቋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 06/2018 ዓ/ም
