uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 138
Підписники
+724 години
+2087 днів
+1 20130 днів
Архів дописів
‎ከስናን ወረዳ ወደ ነብር ገደል ቀበሌ የተንቀሳቀሰው ጡት ብልት #ቆ*ራ*ጩ ስርዓት አንድ ንፁሐን ሴት #ገ*ድ*ሎ ባለቤቷን #አ*ቁስ*ሎ ተመልሷል። ‎ ‎ታህሳስ 12/2018 ዓ/ም ‎ ‎ስናን ወረዳ ረ/ገበያ ከተማ የመሸገዉ #አራ*ዊት ሰራዊት ነብር ገደል ቀበሌ ላይ የስናን አባጅሜ ሻለቆችን  ሊያፍን ገብቶ ያሰበዉ ሳይካ ሲቀር፤ ‎ አቶ ግዛቸዉ ወንዴ የተባለ አርሶ አደር ቤት አስከፍቶ   የጥይት እሩምታ በመክፈት እርሱን በማቁሰል ባለቤቱን ወ/ሮ አየሁ አበባየሁን በልጆቿ ፊት በአሰቃቂ ሁኔታ #የገደ*ላት ሲሆን #አራ*ዊት ሰራዊቱ  በአናብስቶቹ ከበባ ዉስጥ ሲገባ እግር አዉጭኝ  ፈርጥጦ  ወደ  መጣበት   ተመልሷል። ‎ ‎በየአካባቢዉ የንፁሃንን ደም #ማፍ*ሰስ የለመደዉ አራዊት ሰራዊቱ ዛሬም የአማራ ሕፃናትን፣ እናቶችን፣ልጃገረዶችን፣ወጣቶችን አባወራዎችንና ቄሶችን አሰቃቂ ሁኔታ #መረ*ሸን የዘወትር ስራዉ አድርጎ ይዞታል። ‎ ‎አማራውን እንደህዝብ ይጠሉታል የምንለው  ለዚህ ነው። ‎ታህሳስ 12/2018 ዓ/ም ‎

የደቡብ ወሎ ዞን "ፓራ ኮማንዶ" በሚል ያስመረቃቸው ታጣቂዎች በወግድ የሚገኘው ካምፓቸው በፋኖ ተሰብሮ ከ34 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ፡ በርካታ ወታደራዊ ንብረትም በፋኖ ቁጥጥር
የደቡብ ወሎ ዞን "ፓራ ኮማንዶ" በሚል ያስመረቃቸው ታጣቂዎች በወግድ የሚገኘው ካምፓቸው በፋኖ ተሰብሮ ከ34 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ፡ በርካታ ወታደራዊ ንብረትም በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። ከተማረከው ንብረት መካከል ዞኑ ለታጣቂዎቹ አሰርቶት የነበረው "ፓራ ኮማንዶ" የሚል ፅሁፍ ያለበት ብዛት ያለው ቲ-ሸርት አንዱ ነው። ዞኑ ለታጣቂዎቹ አሰርቶት የነበረው ቲ-ሸርት አብዛኻኛው ደረጃውን ያልጠበቀና ሳይዙም አናሳ የሆነ ነው። ዞኑ ለእንግዲኸው ቲ-ሸርት ሲያሰራ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ቢሆን ጥሩ ነበር።

ለጀግናው የአማራ ፋኖ ሰራዊትና ለአማራ ህዝብ በሙሉ በድሮን ጥንቃቄ ዙሪያ የምፅፈው የመጨረሻውና የተጠቃለለ መረጃ ! ድሮኖች አሁን ላይ በሌሊት ጭምር ጥቃት ማድረስ በመጀመራቸው እያንዳንዱ ተዋጊ ራሱንና ጓደኛውን ለመጠበቅ እነዚህን ስልቶች በሚገባ ሊያውቃቸውና ሊተገብራቸው ይገባል። ​የድሮን ጥቃትን ለመከላከል ትልቁና ቀዳሚው ስልት ተሰባስቦ አለመታየት ነው፤ ምክንያቱም ድሮን ካላየች አትመታም። ሌላው ድሮኖች በምሽት፣ በጭጋግ ወይም በደመና ውስጥ ሆነው ሰዎችንና መኪኖችን የሚለዩት በብርሃን ሳይሆን ዕቃዎቹ በሚረጩት የሙቀት መጠን (thermal energy) መሆኑን ጠይቄ መረዳት ችያለሁ። ማንኛውም ሞቅ ያለ ነገር ማለትም የሰው አካል፣ የሞተር፣ መኪና ወይም በቅርቡ የተተኮሰ የጦር መሣሪያ ኢንፍራሬድ የተባለ ጨረር ይረጫል፤ የድሮን ካሜራ ደግሞ ይህንን ጨረር ወደ ምስል በመቀየር ኢላማውን ይለያል። ​ይህንን የሙቀት ጨረር ለመሸፈን ሙቀትን ወደ ውጭ እንዳይወጣ የሚከላከሉ ልዩ የሙቀት መከላከያ ሸራዎችን (Thermal Blankets) መጠቀም ወሳኝ ሲሆን እነዚህ ሸራዎች በሌሉበት ደግሞ ተራ ወፍራም ብርድ ልብሶችን በመጠቀም የሰውነትን ወይም የሞተርን ሙቀት ለተወሰነ ጊዜ መደበቅ ይቻላል። የተሻለው አማራጭ ደግሞ ከተፈጥሮ መከለያዎች አንዱ የሆነውን ጥቅጥቅ ያሉ ዛፎች ስር መሆን፣ ዋሻዎችን መጠቀም እና በጭጋጋማ ወይም ዝናባማ የአየር ሁኔታ መንቀሳቀስ የድሮን እይታን በእጅጉ ይጋርዳል። የዛፍ ቅጠሎች የሙቀት ጨረርን የመበተን ባህሪ ስላላቸው የድሮኑ ካሜራ ግልፅ ምስል እንዳያገኝ ያደርጉታል ይላሉ ባለሙያዎች። ​ሌላው እጅግ ወሳኝ ነጥብ ድሮኗ ቅኝት ላይ ባለችበት ጊዜ በቡድን ሆኖ ፍፁም አለመንቀሳቀስ ነው። ድሮን በአየር ላይ ባለችበት ሰዓት ፍፁም ተገትሮ መቆም ወይም መተኛት ይገባል ምክንያቱም አብዛኞቹ የድሮን ሶፍትዌሮች የሚለዩትና ትኩረት የሚያደርጉት በሚንቀሳቀስ ነገር ላይ ነው። በተጨማሪም በቡድን ተሰባስቦ ከመጓዝ ይልቅ ርቀትን ጠብቆ ተራርቆ መንቀሳቀስ የጥቃቱ ሰለባ የመሆን እድልንና የጉዳቱን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። ​ከዚህም ባለፈ ድሮኑን የማታለያ ዘዴዎችን መጠቀም ውጤታማ ነው።  ለምሳሌ ልክ እንደ እውነተኛ መኪና ወይም የሰው ስብስብ የሚመስሉ የውሸት ምስሎችን መሬት ላይ በማስቀመጥ ድሮኑ ጥይቱን በከንቱ እንዲያባክን ማድረግ ይቻላል። ድሮኑን ለማደናገር በተለያዩ ሰው በሌለባቸው ቦታዎች ትናንሽ እሳቶችን በማንደድ ወይም ሞቅ ያሉ ቁሶችን በማስቀመጥ የድሮኑ ካሜራ ትክክለኛውን የሰው ኃይል እንዳይለይ ማድረግ ይገባል። በዚህም ቦንብ አባክኖ እንዲሄድ ያደርገዋል። ​የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ የሞባይል ስልኮችንና የሬዲዮ ግንኙነቶችን መቀነስ ወይም ፍፁም ማቆም የህልውና ጉዳይ ነው።  ምክንያቱም ድሮኖች የሞባይል ሲግናልን (RF signal) ተከትለው ኢላማን በትክክል ሊመቱ ይችላሉ። ሌላው ባህላዊ ዘዴ ደግሞ ድሮን ሲመጣ የሚፈጥረውን ድምፅ በንቃት የሚከታተሉ ፋኖዎችን ወይም ቀኘዎችን በተራራ ጫፎች ላይ በመመደብና መረጃን በፍጥነት ለተዋጊው ማድረስና አስቀድሞ በመሸሸግ ከአድጋ መከላከል ይቻላል። ​ድል ለአማራ ፋኖ ! ይህ መረጃ ለሁሉም የሰራዊቱ አባላት እንዲደርስ ሼር በማድረግ የድርሻችንን እንወጣ። ©ይኸነው የሸበሉ

"..እንጦጦ ደርሰንም የሚከዳ ይኖራል" ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ አማራዬ #ወጥር #ግፋ ዝም ብለህ ድሉ ያንተ ነው!!!
"..እንጦጦ ደርሰንም የሚከዳ ይኖራል" ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ አማራዬ #ወጥር #ግፋ ዝም ብለህ ድሉ ያንተ ነው!!!

ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም #ትንቅንቁ_አሁንም_እንደቀጠለ ነው‼️ ከሰዴ ወረዳ በሌሊት በተለያዩ አቅጣጫ በመዉጣት ወደ አንድነት ማሪያም ቀበሌ ወጦ የነበረዉ የጠላት ሀይልን የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር እንዳ አውሬ አሯሩጦ በመመለስ ተሜ ወንዝ የምትባል ቦታ ላይ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ ጠላትን አንገት አስደፍቶ አሳፍሮ መልሶታል። በተደረገው ልዩ የደፈጣ ጥቃት የጠላት ሀይል የተለመደውን የሀሰት ዶክመንት ለመስራት እና የአርሶ አደሩን ንብረት ለመዝረፍ የዉሸት ፕሮበጋንዳ ለመስተላለፍ ቢሞክርም በጀግኖች ፋኖወች ጠካራ ክንድ ባደረጉት የደፈጣ ዉጊያ መመለስ ተችሏል። የፋኖ ሀይልን መቋቋም ያቃተዉ የጠላት ሀይል ተመልሶ ወደ ሰዴ ወረዳ ከተማ ጭኖ ይዞት የመጣዉን ድሽቃ ይዞ እየሮጠ ተመልሶገብቷል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

"በኦፕሬሽን ለሚ" ምክንያት የወግድ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ታፍነው ተወሰዱ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር በወግድ ግንባር ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በጠላት ኃይል ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት 12 ፓራ ኮማንዶዎች እና 2 የፓሊስ አባላት ሲደመሰሱ ከ6 በላይ የሚሆኑት ፓራ ኮማንዶዎች ቆስለው ሌሎች በሸነት ገደል መግባታቸው ይታወቃል:: ከመብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት መካከል 1ኛ (አዳነ ሀብትነው) ሻለቃ እና ከ2ተኛ (ደምሰው ጎጡ) ሻለቃ የተውጣጡ አሃዶች የጠላት ኃይልን ክፉኛ ያስደነገጠ የጦር ሜዳ ጀብዱ ስለፈፀሙ ጠላት እርስበርስ እየተወናጀለ ነው:: "ኦፕሬሽን ለሚ" የሚባለውና ወግድ ወረዳ ለሚ ቀጠና ውስጥ ካቢ ላይ የተፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት ያስከተለውን ከፍተኛ መደናገጥ ተከትሎ የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ዛሬ ማለትም ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የወግድ ወረዳ አመራሮችን በድንገት በማፈን በታህሳስ 19ኙ ጥቃት ጠርጥረናቸዋል ብለው አስረዋቸዋል:: በዚህም መሰረት የወግድ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮነን አማረ፣ የወግድ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አራጋው እና የወግድ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ እንድሪስ በ105ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ታፍነው መወሰዳቸውን የውስጥ ምንጮች አረጋግጠውልናል:: የወግድ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማናዬ ደሳለው እና የወረዳው መንግሥት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ካሳዬ ጌታቸው ለ105ኛ ክፍለ ጦር ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መሰረት የተፈፀመው አፈና ስረ- ምክንያት ታፋኞች ከፋኖ ጋር ተባብራችሁ ሰራዊታችንን አስመትታችኃል የሚል መሆኑንም ነው የደረሰን መረጃ የሚጠቁመው:: እንደሚታወቀው የአማራ ባንዳዎችን ተጠቅሞ መጣል ልምዱ የሆነው ብልጽግና ወደፊትም ታላላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱዎች በፋኖ ሲፈፀሙ ፋሽስቱ አብይ አጠገቡ ያሉትን የአማራ ባንዳዎች ተጠያቂ ማድረጉ ተገማች ነው:: የአማራ ባንዳዎች ቀን እየጨለመ ነው፤  ነገ ከነገ ወድያ በርካታ ጄኔራሎች እና ሲቪል ባለስልጣናት አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ለአብይ ወታደሮች ሽንፈት እና ሞት ተጠያቂ ናችሁ ተብለው በአደባባይ በስሙኒ ገመድ እንደሚሰቀሉ ግልጽ ነው:: ለዚህ ማሳያው በዛሬው እለት ወግድ ወረዳ ውስጥ የተፈፀመው የአፈና ድርጊት ነው ሲል የመብረቅ ክፍለ ጦር ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ጌታቸው እሸቱ መግለፁን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ሙሉጌታ ሰማኝ ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት አስታውቋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም

#የድሮን_ቅኝት‼️ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ጀምሮ ቋሪት ጣሊያ ቀጠና አካባቢው የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል ስለሆነም ጥንቃቄ ይደረግ‼️    21/ዐ4/2018 ዓ.ም

መነሻውን ከናዝሬት ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው መተሀራ ያደረገ የአገዛዙ ኃይል ወደ ሸዋ መተህብላ እየተጓዘ ባለበት በፋኖ ከባድ ጥቃት ተፈፀመበት! በፋኖ የተከፈተው ድንገተኛው ጥቃ
መነሻውን ከናዝሬት ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው መተሀራ ያደረገ የአገዛዙ ኃይል ወደ ሸዋ መተህብላ እየተጓዘ ባለበት በፋኖ ከባድ ጥቃት ተፈፀመበት! በፋኖ የተከፈተው ድንገተኛው ጥቃት ለመመከት እጅግ አስቸጋሪ ነበር የተባለ ሲሆን፡ በዚህም ለብልፅግና ቡድን የሚያገለግሉ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና የተሰማራው የጄነራል አሳምነው ፅጌ ዕዝ ሰራዊት እስከ ናዝሬት እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ድረስ በመወርወር በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀመ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል።

ቢኒያም መልካ! "206ኛ ኮር በሰጠኝ ነፃነት የጓደኛየን አቤል ሲሳይን ህይወት ታድጊያለሁ" ታህሳስ 2018/ዓ.ም ቢኒያም መልካና አቤል ሲሳይ በአረመኔው ሰራዊት ታፍሰው ድንገት ጅማ በሚገኘው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገናኙት ከአሰላና ሻሸመኔ ከተሞች ታፍሰው በጭነት መኪና ታጭቀው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ጥልመቱን እየጣሱ በሚጓዙበት ጊዜ ነበር። ከእናቶቻቸው እቅፍ ተፈልቅቀው በጨካኞች መዳፍ የወደቁት እነዚህ ብላቴናዎች በጦላይ ማሰልጠኛ ካምፕ ለ4 ወራት በሚደንቅ ፍቅር መራራውን ህይወት እየተጎነጩ ከቆዩ በኋላ ስልጠናውን ጨርሰው እንደነገሩ ተመርቀው ጎጃም ክ/ሀገር የምትገኘውን 32ኛ ክ/ጦር ሲቀላቀሉ የ17 ዓመትና የ16 ዓመት ታዳጊዎች ነበሩ። ከማሰልጠኛ ካምፕ እስከ ጎጃም ድረስ እረጅም መንገድ በሌትና በቀን ተጉዘው ደብረ ማርቆስ ሲደርሱ አዳዲስ የሰራዊት አባላት በየ ክ/ጦሩና ሻለቃዎች ሲበተኑ እነዚህ ሁለት ተዳጊዎች የ32ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንት 4ኛ ሻምበል ጋንታ 1 ላይ ሳይነጣጠሉ ተመደቡ ። ተዓምር እስከ ሚመስል ድረስ እጣፋንታቸው እስከ መጨረሻ አብሮነት የሆነላቸው ቢኒያም እና ሲሳይ በጋንታዋ ካሉ 8 ወታደሮች 5ቶች በሞት ሲለያቸው ከቀሪ አንድ ጓደኛቸው ጋር በፍርሀት ተውጠው እረጅሙ ሌሊት እስኪ ነጋ ይናፍቁ እንደነበር ከቀናት በፊት ቢኒያም መልካ 206ኛ ኮርን ከተቀላቀለ በኃላ እንዳጫወተኝ ነግሪያችሁ ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው፦ ቢኒያም መልካ ስርዓቱን በመክዳት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ በማርዘነብ ቀበሌ ከመሸገው የአረመኔው ሰራዊት 32ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንትን ለቆ በመውጣት 206ኛ ኮርን ከተቀላቀለ በኋላ ለጓደኞቹ በአደረገው ጥሪ መሰረት በሞት ጥላ ስር አብሮት የነበረውን አቤል ሲሳይን ጨምሮ ንጉሴ ቻሌ፣ ማንደፍሮ ደሴ የተባሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላትን ተቀብሎ የነፃነት አየርን እየተነፈሱ ይገኛሉ። የአረመኔው ሰራዊት ፋኖ ኩላሊት ያወጣል፣ አንገት ይቆርጣል የሚለውን ውሸት በማጋለጥ ጓደኛችን ያስተላለፈውን መልዕክት ተማምነን መጠን ያየነው አቀባበል ከጠበቅነው በላይ ሁኖብናል ያሉት የቢኒያም ጓደኞች የለበስነው ዩኒፎርም ሰልችቶናል እንደ ቢኒ ልብሳችንን ቀይሩልን እያሉ ሲጣደፉ ተመልክቻለሁ። "እዚህ ሰቀቀን የለም! እዚህ ርሀብ ጥም ፍርሀት ሰቆቃም የለም! አትፍሩ እኔም እንደናተ ተጠራጥሬ ነበር ልብሴን እንኳ የቀየሩልኝ እዚህ በመጣው በደቂቃዎች ውስጥ ነው የናፈቀኝን ነፃነት አግኝቻለሁ እናተም በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል" በማለት ለቀድሞ ጓዶቹ መልዕክት ያስተላለፈው ቢኒያም መልካ 206ኛ ኮር በሰጠው ነፃነት ከማሰልጠኛ እስከ ጋንታ ድርስ አብሮት መከራ የተቀበለውን የአቤል ሲሳይን ነፍስ መታደጉ እንዳስደሰተው ገልጿል። ቀን በቀን የአረመኔውን ሰራዊት ፍርስርስ እያደረግነው የምንገኘው እኛ! በፀና አላማ፣ በስነ ምግባር በታነፀ ሰራዊት ፣ በማይቋረጥ የህዝብ ድጋፍ ፣ በመርህና በህግ በሚመራ ትግልና መሪ ታግለን የመጨረሻውን ድል እንደምንጎናጸፍ አንጠራጠርም። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ሰራዊቱን ለማዘመን እና የሰራዊትና አዋጊውን የትግል ቁመና ለመቀየር የታለመ የኮር እና ክፍለ ጦር እስከ ሬጅመንት አወቃቀሩን ሰርቶ ጨርሷል ። በድሮው የአማራ ፋኖ በጎጃም የነበሩ 9 ክፍለ ጦሮችንና በውሳጠቸው ያሉ ብርጌዶችን በሰው ሀይል ብዛት በማሰልጠንና በማስከዳት በትጥቅ ግዥና ምርኮ ካጠነከረ በኋላ አሁን ያለውን አደረጃጀት በጣም በረቀቀና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ማደራጀት ችሏል። ከዚህ በታች የተቀመጠው አወቃቀር በቅደም ተከተል የበፊቱና የአሁኑ ተቀምጧል። እንበርታ ማሸነፋችን እውን ነው 💪 ይህ የድሮው የአማራ ፋኖ በጎጃም አወቃቀር ነው 👇 1ኛ ክፍለ ጦር ፦ ✔️ ባህርዳር ብርጌድ ✔️የጣናው መብረቅ ብርጌድ ✔️ አንሙት ያዛቸው ብርጌ ✔️ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር፦ ✔️ደጋ ዳሞት ብርጌድ ✔️መብረቁ ብርጌድ ✔️ ዮሀንስ አለማየሁ ብርጌድ ✔️መዝገበ ጮቄ ብርጌድ ✔️መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ 3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር፦ ✔️ግዮን ብርጌድ ✔️ዘንገና ብርጌድ ✔️ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ✔️ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ✔️አቤ ጉበኛ ብርጌድ ✔️ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ ✔️ቢትወደድ አያሌው መኮነን ብርጌድ 4ኛ ጃዊ ክፍለ ጦር፦ ✔️በላይ ዘለቀ ብርጌድ ✔️አንድነት ብርጌድ ✔️ገሞራው ብርጌድ ✔️አባይ መተከል ብርጌድ 5ኛ መንገሻ አቲከም ክፍለ ጦር ፦ ✔️ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ✔️ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ✔️ጓጉሳ ወንበርማ ብርጌድ ✔️ወርቅ አባይ ብርጌድ ✔️አረንዛው ዳሞት ብርጌድ 6ኛ ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር፦ ✔️ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ✔️ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ብርጌድ ✔️ቀስተ ደመና ብርጌድ ✔️ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ✔️በላይ ዘለቀ ብርጌድ ✔️ስናን አባጅሜ ብርጌድ 7ኛ ሀዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር፦ ✔️ተድላ ጓሉ ብርጌድ ✔️የቦቅላ አባይ ብርጌድ ✔️አብራጃት ብርጌድ ✔️አዋበል መብረቁ ብርጌድ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር፦ ✔️ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ✔️አባ ኮስትር ብርጌድ ✔️ደባይ ጮቄ ብርጌድ ✔️ዛንበረሀ ብርጌድ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር ፦ ✔️አባይ ሸለቆ ብርጌድ ✔️አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ ✔️ሶማ ብርጌድ እና ተጨማሪ ኮማንዶ ዩኒቲ ነበሩ ✍️ ከዚህ ቀጥሎ ደሞ አሁን በአዲስ መልክ የተደራጀው የኮር አወቃቀር ከነ አመራሮቹ ነው 👇👇 ፩/102ኛ ኮር :- 1.ሰብሳቢ ~ዘውድዓለም አዱኛ 2.ም/ሰብሳቢ ~ ምስጋነው ይታየው 3.ወታደራዊ አዛዥ .~ኮሎኔል ሸጋው ሁነኛው 3.1.ምክትል አዛዥ~፶/አ መኳንት አበጀ 3.2.ዘመቻ. ~፻/አ ይንገስ 3.3.አስተዳደር. ~፻/አ ስራው ወ/እግዚአብሔር 3.4.ስልጠና ~አብርሃም አድማስ 3.5.ሎጅስቲክስ. ~ጌታቸው አጥናፉ 3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ዘላለም ጥላሁን 4. ፖለቲካ መምሪያ ~ማንችሎት ጥላሁን 5.ፋይናንስ መምሪያ ~ኤፍሬም ሽባባው 6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ .~ ዲ/ን አብነት 7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~ ይፍረድ ወዴ 8. አደረጃጀት ~ዮሃንስ አያሌው ፪/105ኛ ኮር:- 1.ሰብሳቢ ~ ያሬድ በቀለ 2.ም/ሰብሳቢ. ~ደመላሽ አንድነው 3.ወታደራዊ አዛዥ ~፶/አ ስማቸው ቢሻው 3.1.ምክትል አዛዥ ~ ፻/አ ገረመው አጋዥ 3.2.ዘመቻ ~አንዳርጌ ቻሌ 3.3. አስተዳደር ~ማረ ቢያዝን 3.4.ስልጠና ~.ኮማንዶ ፍቅሩ ዘውዱ 3.5.ሎጅስቲክስ ~ዋ /ሳጅን ብርሃኑ ናቃቸው 3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ግዛቸው መንበር 4.ፖለቲካ መምሪያ. ~ሽገዛ ሙሉጌታ 5.ፋይናንስ መምሪያ ~.መልሰው ፍቃዱ 6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ፍሬዘር መንግስት 7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~.ዘላለም አዲስ 8. አደረጃጀት ~.አበባየሁ ባንታምላክ ፫/109ኛ ኮር:- 1.ሰብሳቢ ~ጎበዜ ጌታቸው 2.ም/ሰብሳቢ ~ክንፈመላክ ካሳ 3 ..........~ታዘበው ስየ 3.1. ምክትል አዛዥ ~፻/አ መለሰ አይናለም 3.2.ዘመቻ ~ንብረት ደሴ 3.3.አስተዳደር ~.ወርቅነህ የኔጌጥ 3.4.ስልጠና ~ደሳለኝ ዘውዱ 3.5.ሎጅስቲክስ ~ባህሩ አናጋው 3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~፻/አ ጊዮን 4.ፖለቲካ መምሪያ ~አማረ ካሴ 5.ፋይናንስ መምሪያ ~አዝመራው ቢያድግልኝ 6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~የቻለ አድማሱ 7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~.ስማቸው አባታለም 8. አደረጃጀት ~አለልኝ አያና ፬/201ኛ ኮር:- 1.ሰብሳቢ ~ ላይችሉህ ገበየሁ 2.ም/ሰብሳቢ ~ እሱባለው ባምላክ 3.ወታደራዊ አዛዥ ~ኮሎኔል አደመ ልጃለም 3.1. ምክትል አዛዥ ~፶/አ ደጉ ፈንታሁን 3.2.ዘመቻ ~ ፶/አ መኳንት ዓለም 3.3.አስተዳደር ~ ሻለቃ ዘላለም ጥላሁን 3.4.ስልጠና ~ ፲/አ ባለውጊዜ ባንተይርጋ 3.5.ሎጅስቲክስ ~.ተመስገን አድማስ 3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ ተበጀ ማተቤ 4.ፖለቲካ መምሪያ ~አረፋይኔ ተጎድ 5.ፋይናንስ መምሪያ ~ሙላቴ ዓለምነህ 6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ሃብታሙ የሱፍ 7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~አዳንከኝ እያሱ 8. አደረጃጀት ~አንለይ እንየው ፭/206ኛ ኮር :- 1.ሰብሳቢ ~ዳሞት አለኸኝ 2.ም/ሰብሳቢ ~መቻላቸውን ታፈረ 3.ወታደራዊ አዛዥ ~.፶/አ ዘላለም ደሴ 3.1. ምክትል አዛዥ ~፻/አ ደመቀ ዳምጤ 3.2.ዘመቻ ~በላይ ብዙአየሁ 3.3.አስተዳደር. ~አየነው 3.4.ስልጠና ~ሎጀስቲክ ፻/አ ክርስቲያን ደመላሽ 3.5.ሎጅስቲክስ ~፻/አ አስረስ ምህረቴ 3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ስለሽ ጌታቸው 4.ፖለቲካ መምሪያ ~ጌራወርቅ ዳኛው 5.ፋይናንስ መምሪያ ~የኔነህ ፈንታሁን 6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ባዬ ደስታ 7ጊዜያውመንግሥትመምሪያ. ~መንግሥቱ አማረ 8, አደረጃጀት ~ደረሳቸው

እጅ የሰጠ ፋኖ የለም ...! ምክንያቱም.. እጁ እሚያሰጥ እንጅ እጅ እሚሰጥ ፋኖም አማራም የለም፡፡ በታሪካችንም የለም፡፡ ሰሞኑን በቆላድባ እና በማክሰት አ-ረ-መ-ኔዉ የአብይ አገዛዝ እጅ ሰጡ እያለ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ የነበረዉም እ-ጅ-ም እ-ግ-ር የሌላቸዉ ህዝብን ሲያንገላቱ ሲያግቱ በተዘዋዋሪ አገዛዙን ሲያገለግሉ የፋኖን ስም ሲያጠለሹ የነበሩ በሆዳቸዉ የወደቁ ሆ-ድ አ-ደ-ር ሰ-ላ-ቶ-ዎ-ችን ነዉ፡፡ ምክንያቱም በፅናት እና በቁርጠኝነት የሚታገሉ ሌሎች ፅኑ ፋኖዎች እስካሉ ድረስ.. ይህ ትግል በጽናት፣ በቁርጠኝነት እና በአንድነት ፣በህብረት አረመኔው የአብይ አገዛዝ አስወግደን እንደምጥል እርግጠኛ ሁኘ እነግራችሀለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህን ትግል ላንጨረስ አልጀመርነዉም፡፡ ትግሉም ከአለት ላይ የተመሰረተ ነዉ..! አሸንፈናል፡፡ ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነዉ፡፡ © Fano Amare Achenef

ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስተዳደር በዛሬዉ እለት በደድ እየሱስ አቦ ቀብሌ ሰፊ ሕዝባዊ ዉይይቱ እንደቀጠለ ነው። @@@@@@@@@@@@@@@@ ‎ ስለሆነም ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት በሚያስተዳድራቸዉ ቀበሌዎች እየተዘዋዎረ የሕዝብ መድረኮችን በማመቻቸት ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ድርጅታዊ መዋቅሩን እያጠናከረ ሲሆን በዛሬዉ እለት ጊዚያዊ መንግስቱ የ54ኛ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊዉ እና የ201ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ በተገኙበት #በደድ እየሱስ አቦ ቀብሌ ውይይት አካሂዷል:: የህዝባዊ መድረኩም የመልካም አስተዳደር በመገምገም ህገወጥ ጮቄ ላይ የመሬት ወረራን እና አጠቃላይ የፋኖ ትግል አሁን ላይ የደረሰበትን ሁኔታ ግንዛቤ መስጠት ተችሏል ። አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም የቴወድሮሰ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት