uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 312
Підписники
+17324 години
+2467 днів
+1 36830 днів
Архів дописів
የጠላት ሀይል ያልጠበቀውን ኪሳራ አስተናገደ ። ለተከታታይ ቀናት ከደንበጫ ፣ ከፈረስቤት እና ከአንጀኔ በመነሳት የገሊላ ሕዝብ ለመዝረፍ እና ለማውደም የተንቀሳቀሰው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በ109ኛ ኮር እና 201ኛ  ጥምረት አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ ተመልሷል።     ከሶስት ቀን በላይ በፈጀው እልህ አስጨራሽ ውጊያ በርካታ ጠላትን መደምሰስ  ሲቻል ቀሪውን ማቁሰልተችሏል። በአውደ ውጊያውም አዋጊዎች እና የቡድን መሳሪያ ተኳሾች መደምሰሳቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ የተበሳጨው እና የአማራን ሕዝብ ማጥፋት ዓላማ ብሎ የያዘው የብልፅግና ስርዓት የነጋዴዎችን ፣የገበሬዎችን እና የገሊላ ኗሪዎችን ቤት፣ ሆቴል ፣ ሱቅ እና የሚንቀሳቀሱበትን ሞተር  አቃጥሏል፣ ዘርፏል ፣ አውድሟል። በዚህ የናደደው ማህበረሰብ  በነቂስ በመውጣት ፊለፊት ከፋኖ ጋር በመግጠም ከቀጠነው ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ተችሏል።

#ጥብቅ_የጥንቃቄ_መልዕክት❗️ #ሸር ይደረግ        ከክልል እሰከ ቀበሌ ያለዉ የብልፅግና መዋቅር በክልል እና በዞን ደረጃ ለወረዳ አመራሩ የተሰጠ ተዕልኮ 1, ሁሉም አመራር ነፃ በወጡ ቀጠናዎች በከፈተኛ ደረጃ የምርጫ ዝግጅት ማድረግ አለባቹህ። 2,ህዝብን ማወያየት እና ፋኖን ከህዝብ መነጠል 3, ፋኖን አውግዞ ማስረዳት ለህዝብ 4, በሃገር ሽማግሌዎች ፋኖዎችን ማስከዳት 5, ቀበሌዎችን ማዋቀር 6, በቀበሌ የኢህአዴግ እና የደረግ አመራሮችን መያዝ አለባቹህ 7,ወሳኝ ወሳኝ የፋኖ መረጃዎችን ማሳደድ ግራ እና ቀኝ 8,የምረጫ ታዛቢዎችን ማዘጋጀት አለባቹህ 9,ለ7ኛው ሀገራዊ ምረጫ የፀጥታ ሃይል በከፈተኛ ደረጃ  ማዋቀር 10,የፀጥታ ሀይል የስነልቦና ግንባታ መስጠት 11,ገቢ መሰብሰብ 12, በከፈተኛ ደርጃ ኬላዎችን ማጠናከር 14,በለሊት ከፋኖ ካምፕ ማጥቃት 15, ኦፒዎችን ከፋኖ ውስጥ ማዘጋጀት 16, አንዳንድ የብልፅግና አመራሮች አፋቹህ ብልፅግና ልባቹህ ግን ፋኖ የሆናችሁ መቆጠብ አለባቹህ። 17, ከፋኖዎች ውስጥ አመራር ገሎ እንዲመጣ ማዋቀረ አለባቹህ 18,የመታገያ ሚዲያዎችን ማሰደግ እና መደገፋ 19,የተቋም ንብረቶችን መለየት 20, የኮሩን አደረጃጀት በሴራ ማዳከም እና መበተን አለባቹህ 21, የአገለሉ የፋኖ ሽፋታዎችን ስቦ ማምጣት አለባቹህ።       የሚል ትዛዝ ከብልፅግናው መንደር ትዛዝ ወርዷል‼️ #ማሳሰቢያ❗️ ውድ የፋኖ አመራሮች እና አባሎች ለብልፅግና አመራር እንደ ቃሪያ ካለበለብከው አወዳደቃችን ይከፋል በኛ ስነ ልቦና እየገቡ እነሱ የአሸነፉ እንዳይመስላቹህ ባዶ ቀፎ የቀራቸው የኛ አንድነት ብቻ ነው የሚጎለን፣ አንድነቱ በፍጥነት ይቋጭና ወደ ሙሉ ማጥቃት ይሸጋገር ይህ ካልሆነ ዋጋ ያስከፍላል‼️ 10/ዐ4/2018 ዓ.ም

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለ ጦር መርሳ ግንባር ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም የማረኩት አንድ ብሬን እና 23 ክላሽ ከበርካታ ተተኳሽ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋር በምስል ማስረጃ! ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም 2ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጄ    10/04/2018 ዓ.ም በነበልባል ክፍለ ጦር የፋኖ አባላቶች ምሽግ ላይ ከበባ ለማድርግ አቅዶና አሥቦ ወደ ፋኖ ምሽግ ያቀናው ግትልትል ሰራዊት ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የፋኖ አባላት ልዩ ቦታው ሲቪለን ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ቀድመው ምሽግ በመያዝ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ላይ የመጣውን የብልፅግና ሰራዊት የመቶ አለቃ አበባው ብርጌድ አናብስቶች በደፈጣ ተኩሥ ያረገፉት ሲሆን ጠላትም ወደ ፊት መንቀሳቀስና ለማጥቃት ሲቸገር ወደኋዋላ በማፈግፈግ ሙትና ቁሥለኛውን በ3 አምቡላንሥ ሲያመላልስ ቆይቷል።  በድጋሚ ያለ የሌለ ኃይሉን ከኬላ ከተቋም ጥበቃ እንዲሁም የኋላ ደጄን ያለውን ጦር በማሰባሰብ   በር ተብሎ ከሚጠራው  አካባቢ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ የፋኖ አባላቶች ባደረሱበት መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ያቃተውና ከፍተኛ የሰው ኃይሉን አጥቶ በነበረበት እንዲቆምና  ሙትና ቁስለኛውን በተደጋጋሚ ሲያመላልስ እንደነበር ለማየት ችለናል። ይህንንም አሥደሳች ዜና  የሰማው ሌላኛው የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚዎች እና እራስ በሀይሉ ብርጌድ በመናበብ በተመሳሳይ ስዓት በአረርቲ  ወሌሱ ኬላ ላይ  የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚዎች የምድር ድሮኖቹ ነበሮ ሻለቃ ሲገቡ በሌላኛው  ባልጪ ኬላ ላይ እራስ በሀይሉ ብርጌድ ሸማቂ ፋኖዎች በወሰዱበት ጥቃት ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት ያጋጠመው ሰራዊት አካባቢውን በድንጋጤ ሸሽቶ ቦታውን ለቆ ሙትና ቁሥለኛውን ጥሎ ፈርጥጧል። ከዚህ በጨማሪ ባልጪ ኬላ ላይ በተደረገበት ጥቃት ከፍተኛ ጥቃትና ጉዳት ያሥተናገደው የብልፅግና ሰራዊት  አመራር ጭምር የተመታበትና የሞተበት ሰራዊት በብሥጭትና በደመ ነፍሥ በሌላ አቅጣጫ ሸንኮራ ወንዝ ላይ ቢሞክርም የፋኖን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው ወደመጣበት መመለሱን  ከሥፍራው የነበሩ እማኛኞች የነገሩን ሲሆን ይህን ተከትሎ   የብልፅግናው ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት ያሰበው ሳይሆን ባላሰበው  አቅጣጫ የውጊያ ስልቱን በመቀየር በነበልባል ክፍለ ጦር ሲቀጠቀጥ ቆይቶ በተቃራኒው ከባቢው  ሰራዊት ከበባ ውስጥ ገብቶ ከፍተኛ ኪሳራ በማስተናገድ እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል።         ድል ለአ ፋ ብ ኃ        ክብርና ሞገስ ለትግሉ        ሰማዕታት!!! ድላችን በተባበረ  ክንዳችን!!! የነበልባል ክፍለ ጦር ህ/ግንኙነት ሚዲያ ክፍል!!!

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ አቸነፍ ተሾመ የተባለ  አርሶ አደር በአገዛዙ ወታደሮች በስለት ተቆራርጦ ተገደለ! በምዕራብ አማራ ቀጠና ሰሜን ሜጫ ወረዳ አምቦመስክ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኳጃ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነዋሪ የነበረው አቶ አሸነፍ ተሾመ የተባለ ጎልማሳ አርሶ አደር ታህሳስ 03/2018 ዓ/ም ሰብል እየሰበሰበ ባለበት በአገዛዙ ወታደሮች ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው። "ወታደሮቹ መሣሪያ ደብቀሀል በሚል አርሶ አደሩ በማሳው አዝመራ እየሰበሰበ ባለበት አፍነው ወደ መኖሪያ ቤቱ ከወሰዱት በኋላ ቤቱን ፈትሸው መሣሪያ ሲያጡ፡ የአንድ መሣሪያ ዋጋ ተመን ስጠን፡ ያለበለዚያ እንገድልሀለን አሉት፡ አርሶ አደሩም መሣሪያ እንደሌለው መለሰላቸው፡ ይህን ጊዜ ሆዱላይና ደረቱን በስለት ደጋግመው ወጉት፡ ነፍሱ አልወጣ ስትላቸው ሦስት ጊዜ ደጋግመው በመተኮስ እረሽነው አ*ስ*ከ*ሬ*ኑን መንገድ ላይ ጥለውት ሄዱ" ሲሉ የአይን እማኞች ገልፀዋል። ሟች አርሶ አደር አቸነፍ ተሾመ፡ ማህበራዊ ሕይወቱ የተቃና፣ ምስጉን እና አዱኛው የሞላለት ሞዴል አርሶ አደር እንዲሁም ባለትዳር እና የስምንት ልጆች አባት እንደነበር ነው የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አርሶ አደሩ ታህሳስ 03/2018 ዓ/ም የበቆ ሰብል እየሰበሰበ ባለበት ከረፋድ 3:00 ሰዓት ገደማ በአገዛዙ ወታደሮቹ ታፍኖ መኖሪያ ቤቱ ከተፈተሸ በኋላ፡ ወታደሮቹ የጠየቁትን የአንድ መሣሪያ ተመን መክፈል ባለመቻሉ በስለትና በጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል። ወታደሮቹ አርሶ አደሩን በስለት ደጋግመው በመውጋት ነፍሱ አልወጣ ስትላቸው በድጋሚ በጥይት ተኩሰው ከገደሉት በኋላ፡ አ*ስ*ከ*ሬኑን ጎዳና ላይ አውጥተው ጥለው "በውጊያ አንድ ፋኖ ገደልን" በሚልና በኦሮመኛ ቋንቋ ጭምር እየጨፈሩ አከባቢውን ለቀው ወደ ካምፓቸው መሄዳቸውንም ተገልጿል። የብአዴን አካድሚ ሃይሎች ገበና ................................................ የአማራን ህዝብ የየተወ ማህበረሰብ በማድረግ የህዝባችንን ሁለንተናዊ መብት እና ጥቅም አሳልፎ ሲሰጥ የነበረው ሃይል ዛሬም በትግላችን ውስጥ ሰርጎ በመግባት ፈተና ሆኖብን ቆይቷል!! በተለይም አካባቢያዊነትን ለጥሬ ስልጣን ሲጠቀምበት የነበረው ቡድን ዛሬም እውነተኛ የህዝብ ልጆች የጀመርነውን ትግል ለማሳነስ እየሞከረ ይገኛል። ከብአዴን አካዳሚ የተፈለፈሉት ነውረኞች የአማራን ህዝብ ትግል ለማነወር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም!! አማራነትን አብዝተው ይፀየፉታል!! በአማራ ስም መነገድን እንጅ በአማራ ስም ዋጋ መክፈልን ይፈሩታል!! ስብዕናቸው የደላላ እና ተጠቅሞ መጣል ነው። በህዝብ ጥቅም ተደራዳሪ ነው!! ነቀርሳው ቡድን በአማራ ህዝብ ስም ይምላል፣ይገዘታል ግን ምርኮኛ ነው!! የአማራ ፓለቲካን ለስልጣን ማስጠበቂያ እንጅ ለህዝቡ መብት እና ጥቅም የሚቆጭ አይደለም!! ራስ- ጠል እና ንቅል ሲሆን ስነ ልቦናው ደግሞ ተንበርካኪ ነው። ተቸንካሪ እና ገባሪ ባህሪያቱ ደግሞ መገለጫዎቹ ናቸው!! አማራነትን ለመናኛ ፍላጎታቸው ብቻ ይጠቀሙበታል!! ብአደናዊነት በአካዳሚው የፈለፈላቸው አረሞች የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል መደበኛ ጠላት ናቸው!! ብአዴናዊ አካዳሚ የፈለፈላቸው ሃይሎች መነሻቸው ጥቅም እና መዳረሻቸው ደግሞ አማቺዝም ፓለቲካን ለልዩ ጥቅም ማስከበሪያ አድርጎ መቀጠል ነው። ከነቀርሳው ብአዴን አካዳሚ የተፈለፈለው ሃይል ማህበራዊ መሰረቱ የተዛባ፣የህዝብ ውግንና የሌለው፣ራስ ጠል እና ጥገኛ ቡድን ሲሆን በአማራ ህዝብ ጥቅም እና በስልጣን ህልውናው ላይ አይደራደርም!! የአማራን ህዝብ ጥቅም ከ50 ዓመት በላይ አሳልፎ ሲሰጥ የነበረ ቡድን ሲሆን የፓለቲካ አስተምሮው ደግሞ ወደር የለሺ ተላላኪነት ነው። ነቀርሳው ቡድን የአማራ ብሔርተኝነት የሚፈራ ስልጣኑን በአውራጃዊነት መንፈስ እና በቡድን ሲካፈል የኖረ ሲሆን በስሩ የፈጠራቸው ትላልቅ ተቋማትንና መዋቅሩን ደግሞ የህዝብ መምቻ ፣የትግል መቀልበሻ እና የህልውናው ማስቀጠያ አድርጓቸዋል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ህዝብ እና በልጆቹ ትግል የተጀመረውን አብዮት ለመቀልበስ የባንዳ ምልክት ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ  በአካዳሚያቸው ያሳደጉት ማስረሻ ሰጤ እና መስፍን ከፈለኝ /በአማራ ህዝባዊ ድርጅት /ስም ተደራድረናል ሲሉ አድስ የተሸናፊነት ትርክት ለመፍጠር ሞክረዋል!! በእርግጥ ማስረሻ ሰጤ እና ቡድን በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ምንም ተፅዕኖ የሌላቸው እንድሁም ህዝብን ለማደናገር ብቻ የሚጠቀሙበት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። ህዝብ እውነታውን ያውቃል!! የማስረሻ እና ቡድኑ ፍላጎት ተልከስካሺነት እና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ እንደሚውል ግልፅ ነው!! ስለሆነም የአድሱ ትውልድ ትግል መነሻው እና መድረሻው የሚታወቅ ዓላማው ደግሞ የአማራ ህዝብ ከገጠመው ብሔራዊ የህልውና አደጋ እንዲወጣ እንጅ በምስለ አማራዎች ፍላጎት እና ይሁንታ የጀመረነው አብዮት እንደሌለ ይታወቃል!! ትግላችን እና ዓላማው ከግለሰቦች በላይ ነው!! ህዝባችንን ለረጅም ዘመናት በስርገት ሲፈትነው የነበረው አክሺክላ እና ተላላኪ ቡድን ተሸንፏል!! በተላላኪነቱ የተሰጠውን አጀንዳም አክሺፈንበታል!! ስለዚህ የአማራ ፋኖን የህልውና ትግል ርባና ቢስ ለማድረግ ላይ ታች የምትሉ የብአዴን አካዳሚ ሃይሎች ልታርፉ እና ልታፍሩ ይገባል!! የአማራ ህዝብ እና የልጆች ትግል ያሸንፋል!! የጥገኞች፣የተላላኪዎች እና የታካኪ ሃይሎች ፍላጎት አይሳካም!! ደም የገበርንበትን ትግል ለበርባኖች አሳልፈን አንሰጥም!! ትግላችን ከሎጥ ፓለቲካ ነፃ ነው። የሰሞነኛው የእጅ ሰጡኝ ማደናገሪያ ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል የሚደረግ መፍጨርጨር ነው!! ህዝባችን እውነታውን ያውቃል!! የብልፅግና እጅ አስታጣቢዎች በየወረዳው አድስ የማጭበርበሪያ ካርድ አድርገው የያዙት የምርጫ ጉዳይም ፍሬ ቢስ ህልም መሆኑ የታወቀ ነገር ነው!! በእርግጥ ብልፅግና በህይዎት ዘመኑ ከእውነት ጋር ታርቆ አያውቅም!! በየሰፈሩ በአበል እና በኮንቴነር ወዶ የገባውን ገባሪ ቡድን በመጠቀም በፋኖ ስም ለመነገድ የተለመደ የብአዴን አካድሚዎች ፍሬ ነጭ ውሸት ነው!! ትግላችን በየቀኑ እያደገ፣እየዘመነ እና ማህበራዊ መሰረቱን እያጠናከረ እንጅ በአሉታዊ ፕሮፓጋንዳ እና በሃሰተኞች ጩኸት ቢሆን እስከ አሁንም እንጠፋ ነበር!! አሸንፍናቸው፣እንደ ዱቄት ተበትነዋል፣በየገዳሙ ናቸው ወዘተ ወዘተ የብልፅግና በሬ ወለደ ወሬ አያልቅባቸውም!! ፋኖን ማጥፋት የሚቻል ቢሆን እስከ አሁንስ ምን እያደረጉ ነበር?? ምኞት አይከለከልም!! ጥገኛው ልሂቅ የብአዴን የፋይናስ ተቋማት በሚወረውሩለት አበል ህዝቡን አብዝቶ የሚንቅ እና ምቾትን የሚወድ መሆኑ የታወቀ ነው። ነገር ግን በአማራ ስም ማልቀስ፣መነፍረቅ፣ተበደልኩ፣ ተገፋሁ እያለ ሲያላዝን ደግሞ የጉድ ነው!! በአማራ ህዝብ አንጡራ ሃብት ተምሮ  በስልጣን ስም ከአገዛዙ ወንበር ስር ሲማቅቅ የሚውለውን ራስ-ከድ ልሂቅ በታሪክ እንፋረደዋለን!! የአማራን ህዝብ ትግል በወደረኞች እና በቅጥረኛ ባንዳዎች ለመጥለፍ የሚደረገውን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት እያስተካከልነው ወደ ፊት የምንቀጥል ይሆናል!! ትግላችን ውስጥ የነበሩ ረጃጅም እጆች መነሻቸው እና መድረሻቸውም ተለይቷል!! በዘላቂነት እጃቸውን ለመቁረጥ ጠንካራ ስራዎችንም እየሰራን እንገኛለን!! መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

በቆቦ እና ሮቢት ከተሞች ውስጥ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት ከ16 በላይ የሚሆኑት ተገደሉ! ካላኮርማ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ቃኝ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በመግባት የደፈጣ ጥቃት
በቆቦ እና ሮቢት  ከተሞች ውስጥ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት ከ16 በላይ የሚሆኑት ተገደሉ! ካላኮርማ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ቃኝ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በመግባት የደፈጣ ጥቃት ፈፅመው ድል አስመዘገቡ:: ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ቃኞች ራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ ቀን 10:00 አካባቢ በመግባት ወደ ቆቦ ከተማ መውጫ ወይለት ድልድይ ላይ ኬላ ወጥረው ከነበሩ ዙፋን ጠባቂዎች ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም እስከ አስር የሚደርሱትን ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል አስመዝግበዋል:: በተጨማሪም ራያ ቆቦ አቧሬ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ስድስት ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቶች ላይ አካባቢው ላይ የነበሩ ፋኖዎች በፈፀሙባቸው የደፈጣ ጥቃት ወደማይቀረው ተሸኝተዋል:: በዚህም በሁሉም የቤተ-አማራ አካባቢዎች የተጠናከረ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ጠላትን ረፍት የመንሳት የማዋከብና አማራጭ አጥቶ እንዲኮበልል የማድረጉ ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ      _፩ ስብሰባው በሞርተር ጥቃት ተበተነ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማ ላይ በተፈፀመው የሞርተር ድብደባ ሎሌው አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ አቋርጠው ለጥቂት በመትረፍ ወደ እንጅባራ  ፈርጥጠዋል። የብልፅግናው ሎሌ በዙፋን አስጠባቂ ሰራዊቱ ታጅቦ፤ በዙ23 እና በአረመኔ ሰራዊቱ ተከቦ፤ ቲሊሊ ከተማ ላይ ህዝባዊ የዲስኩር ስብሰባ ሊያደርግ በተቀመጠበት ጥቂት ደቂቃ ልዩነት ከወደ ፋኖ በተወሰደ የሞርተር ጥቃት አዳራሹ ላይ ሁከት በተፈጠረበት ቅፅበት በየት እንደ ወጣ ሳይታወቅ ስብሰባዉን በትኖት ፈርጦጥ እንጅባራ ከተማ እንዲገባ  ተገዷል። አረመነው ቡድን  ባለፉት ቀናት በፉነተሰላምና ቡሬ ላይ የተፋውን ቅርሻት  ዛሬም  ቲሊሊ ለመድገም ቢያስብም አይደፈሬዎቹ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች አስተንፍሰውታል። አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ በትነው ከቲሊሊ አዳራሽ በመውጣት በፓትሮል ተሳፋረው ፈጣም ወንዝ እንደተሻገሩ በተፈፀመው ተከታታይ ጥቃት አስፓልት ጫፍ በወደቀው የሞርታር ቅንቡላ ለትቂት ማምለጥ ችለዋል። በአንድ አፍ ፋኖን አጥፍተነዋል፣በትነነዋል፤ በሌላ አፍ ደግሞ በጫካ ያሉ ወንድሞቻችንን "ኑ" በሏቸው እያለ ሲያለዝን የከረመው አረጋና ተላላኪ ሎሌዎቹ፤ ያሰማሩት ጡት ቆራጭ ቡድን ጫካ ውስጥ የቀበሮ ጉድጓድ ቆፍሮ እንዳይወጣ ሁኖ ባለበት በዚህ ሰሃት 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማን ከቦ ሲያስጨንቀው፣ በሞርታር ሲደበድበው፣ ፋኖ ግዙፍ ሀይል መሆኑን ተረድቶ፤ተጨንቆ ተጠቦ በዙ_23፣በብረት ለበስ ፔምፔ ታጅቦ ለማድረግ ያሰበውን  ስብሰባ ማካሄድ ሳይችል  ለጥቂት ህይወቱን አትርፎ ፈርጥጧል። የተሰበሰበው ካድሬም ከገቡበት አዳራሽ እኔ ልውጣ እኔ፤ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሩጫ በማድረግ ወደ የመጡበት ያሰቡትን ሳያሳኩ በጭንቀት ተውጠው አምልጠዋል። የነበረውን ሁነትም በግድ በጉልበት የተሰበሰበው ህዝብ በትዝብት ሲከታተል ቆይቶ መሳቂ መሳለቂያ አድርጓቸዋል። ____፪ በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት እየፈራረሰ ነው። 1ኛ.ዳኔል ዋለ 2ኛ.ጌትነት ፀጋው 3ኛ.ስጦታው መሌ የተባሉ የአገዛዙ ሻንበል አመራሮች ሲሆኑ በሸበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ ከሚገኘው 6ኛ ዕዝ 601 ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ እሬጅመንት የአገዛዙን ሰራዊት በመክዳት ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም 1ኮርያ ክላሽ ከ150 ጥይት ከወገብ ትጥቅ ጋር ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት ተቀላቅለዋ    አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም

የጀግና መንገድ አንድ ብቻ ነው ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የጀግና መንገድ ምርጫ የማይፈለግበት አንድ ብቻ ነው። መንገዱን ግን በዓላማቸው ያልቆረቡ ከእፋቸው ያልፀዱ ፣ እንጥፍጣፊ የሞራልም፣ የህሊናም፣ የፍትሕም፣ የርትዕም ተጠየቅ ያልፈጠረባቸው ራሳቸውንም ማንነታቸውን ሃገራቸውንም ባህልና ሃይማኖታቸውን ሁሉ የረሱ  ሃጣን  ደፍረው አይሞክሩትም። ዓለምን ያልናቁትም በፍፁም አያስቡትም።  የወላዋዮችም የእግራቸው ጫፍ አይነካውም። ሳያስቡ በድንገት ዘው ብለው ከገቡበትም አንድ ጋት እርቀት ሳይጓዙበት የመንገዱ ደብዛ ይጠፋባቸዋል።  እነሱም ይጠፋሉ። የጀግኖች መንገድ ሞትን እንደ ተራ ነገር የናቁ፣ አስፈሪውን  መላዕከሞት በእጃቼው ጨብጠው አርበድብደው መዳፋቸው ላይ እንደ ጨው አሟሙተው  ጉሮሮውን ሲጥ አድርገው ገድለው አስረው፣ ገንዘው እንዳይነሳ አድርገው የረገጡ ህያው  ጀግኖች፤ በፍፁም የአርበኝነት ተጋድሎ በሚያፈሱት የደም ፍሳሽ የሚፀና ሳይኮሰኩሳቸው ስለሰነቁት ትልቅ አላማ ሲሉ እንደ ቅዱስ ጊወርጊስ መሰንጠቅን ፣ መቃጠልን፣ መቀላትን በቃ ምንም አይነት ምድራዊ ግፍና ሰቆቃን ከቁብ ሳይቆጥሩት አጥንታቸውን እንደ ዋርካ ፍልጥ ሰንጥቀው ፥ እንደ አሳ ሾህ ከስክሰው ፥ እንደ ጃርት ወስፌ መሬት ላይ ተክለው  ፥ በሰረገላ ላይ በግርማ እንደ ተሞሸረ ሙሽራ በእልፍኝ ውስጥ እንደተጋበዘ የክብር እንግዳ ትክ የሌላትን አንድያ ሕይወታቸውን ፍፁም ደስ እያላቸው በክብር ሰጠው እንደ ሰልስቱ ደቂቅ በእሳት እቶን ውስጥ በክብር አልፈው የቆረቡለትን ዓላማ ቅንጣት ሳያዛንፉ የክብር አክሊልን የሚቀዳጁበት ፣ መንታ አልባ ፣መስቀለኛም አማራጭም የሌለው ፥ እንደፈለጉ የማይንሸራሸሩበት ፣ ደስታም  መከራም እንደ ሁኔታው የሚፈራረቁበት ፥ ሽንፈት አንጎልን በመርፌ የተወጋ ያክል ጥልቅ ህመም እየተሰማህ ለድል የምትፀናበት ተሰውተህ የምታስመዘግበውን ድል እስከ መጨረሻው ድረስ አይነኬ አድርገህ ጠላቶችህ የማይደርሱበት ቦታ አርቀህ ለመስቀል የከፈልከውን ዋጋ ወደ ደስታ ቀይረህ ወደ ተሻለ  የሞራል ልዕልና የምትሸጋገርበት ከጭራ የቀጠነ ወደ ኋላ የማይመለሱበት ሽንፈትን የማያስተናግድ የድል መንገድ ነው። የጀግና መንገድ ምርጫ የሌለው በከበሩ ዋጋወች የሚገነባ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ምርጫ የሌለው አንድ ቀጭን መንገድ ብቻ ነው። ለቆረብንለት ታላቁን የአማራ ህዝብ ህልውና የማረጋገጥ አላማ ዳር ሳናደርስ ላንመለስ እጅግ ክብር እና ውድ የሆነውን የጀግኖችን ቀጭኗን መንገድ ብቻ ተከትለን ወደፊት እንራመዳለን። ድል ለታላቁ የየአማራ ህዝብ !! ድል ለጀግናው አማራ ፋኖ !! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !! ቻላቸው -የ206ኛ ኮር ምክትል ሰብሳቢ

የደጋው መብረቅ ኮር ከጋሸና ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ሃሙሲት ከተማ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገበ:: አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ በደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ሃሙሲት ከተማ በተደረገ ተጋድሎ በርካታ የጥላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል አስመዝግቧል:: ደጀን ክፍለ ጦር ታህሳስ 10/2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ላይ ከጋሸና በቅርብ ርቀት በምትገኘው ዋድላ ሀሙሲት ከተማ በተደረገው አውደ ውጊያ የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደመጣበት መልሰው ቀጠናቸውን አስከብረዋል:: በተጋድሎው 13 የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ሲደመሰሱ ቀሪዎቹ 23ቱ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ከጋሸና በሌሊቱ ተነስተው ከፋኖዎች የደፈጣ ቦታ እግር የጣላቸው የብልፅግናው አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግደው ተመልሰዋል:: ሀሙሲት ምድር ላይ ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት የዘለቀው አውደ ውጊያ ሀሙሲት ላይ የተከበቡትን የጁላ ሰራዊቶች ከከበባ ለማውጣት ከወልድያና ከአሁንተገኝ በርካታ እግረኛ ሃይል በመካናይዝድ ታጅቦ ቢመጣም ኪሳራ አስተናግዶ ወደመጣበት ተመልሷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም

🔥#ሰበር_ዜና_አረጋ_ከበደ_ለጥቂት_አመለጠ‼ በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማ ላይ በተፈፀመው የሞርተር ድብደባ ሎሌው አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ አቋርጠው ለጥቂት በመትረፍ ወደ እንጅባራ  ፈርጥጠዋል። የብልፅግናው ሎሌ በዙፋን አስጠባቂ ሰራዊቱ ታጅቦ፤ በዙ23 እና በአረመኔ ሰራዊቱ ተከቦ፤ ቲሊሊ ከተማ ላይ ህዝባዊ የዲስኩር ስብሰባ ሊያደርግ በተቀመጠበት ጥቂት ደቂቃ ልዩነት ከወደ ፋኖ በተወሰደ የሞርተር ጥቃት አዳራሹ ላይ ሁከት በተፈጠረበት ቅፅበት በየት እንደ ወጣ ሳይታወቅ ስብሰባዉን በትኖት ፈርጦጥ እንጅባራ ከተማ እንዲገባ  ተገዷል። አረመነው ቡድን ባለፉት ቀናት በፉነተሰላምና ቡሬ ላይ የተፋውን ቅርሻት ዛሬም  ቲሊሊ ለመድገም ቢያስብም አይደፈሬዎቹ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች አስተንፍሰውታል። አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ በትነው ከቲሊሊ አዳራሽ በመውጣት በፓትሮል ተሳፋረው ፈጣም ወንዝ እንደተሻገሩ በተፈፀመው ተከታታይ ጥቃት አስፓልት ጫፍ በወደቀው የሞርታር ቅንቡላ ለትቂት ማምለጥ ችለዋል። በአንድ አፍ ፋኖን አጥፍተነዋል፣በትነነዋል፤ በሌላ አፍ ደግሞ በጫካ ያሉ ወንድሞቻችንን "ኑ" በሏቸው እያለ ሲያለዝን የከረመው አረጋና ተላላኪ ሎሌዎቹ፤ ያሰማሩት ጡት ቆራጭ ቡድን ጫካ ውስጥ የቀበሮ ጉድጓድ ቆፍሮ እንዳይወጣ ሁኖ ባለበት በዚህ ሰሃት 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማን ከቦ ሲያስጨንቀው፣ በሞርታር ሲደበድበው፣ ፋኖ ግዙፍ ሀይል መሆኑን ተረድቶ፤ተጨንቆ ተጠቦ በዙ_23፣ በብረት ለበስ ፔምፔ ታጅቦ ለማድረግ ያሰበውን  ስብሰባ ማካሄድ ሳይችል ለጥቂት ህይወቱን አትርፎ ፈርጥጧል። የተሰበሰበው ካድሬም ከገቡበት አዳራሽ እኔ ልውጣ እኔ፤ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሩጫ በማድረግ ወደ የመጡበት ያሰቡትን ሳያሳኩ በጭንቀት ተውጠው አምልጠዋል። የነበረውን ሁነትም በግድ በጉልበት የተሰበሰበው ህዝብ በትዝብት ሲከታተል ቆይቶ መሳቂ መሳለቂያ አድርጓቸዋል። ዛሬ ታህሳስ 10/2018ዓ.ም እውነትም፤ ሀሞት ጀግንነትም ፣ሀይልም መሳሪያም፣ ትክክለኛ መንግስትዊ ቁመና የት ላይ እንዳለ ህዝቡ ያየበት፣ የታዘበበት ክስተት ሁኖ በድል ተመዝግቧል። አሁንም እንላለን፦#ይዘገያል_እንጅ_አህያ #የጅብ_ናት💪 ©✍️የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አለበል አወቀ 10/ዐ4/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም 2ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጄ።   በነበልባል ክፍለ ጦር የፋኖ አባላቶች ምሽግ ላይ ከበባ ለማድርግ አቅዶና አሥቦ ወደ ፋኖ ምሽግ ያቀናው ግትልትል ሰራዊት ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የፋኖ አባላት ልዩ ቦታው ሲቪለን ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ቀድመው ምሽግ በመያዝ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ላይ የመጣውን የብልፅግና ሰራዊት የመቶ አለቃ አበባው ብርጌድ አናብስቶች በደፈጣ ተኩሥ ያረገፉት ሲሆን ጠላትም ወደ ፊት መንቀሳቀስና ለማጥቃት ሲቸገር ወደኋዋላ በማፈግፈግ ሙትና ቁሥለኛውን በ3 አምቡላንሥ ሲያመላልስ ቆይቷል።  በድጋሚ ያለ የሌለ ኃይሉን ከኬላ ከተቋም ጥበቃ እንዲሁም የኋላ ደጄን ያለውን ጦር በማሰባሰብ   በር ተብሎ ከሚጠራው  አካባቢ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ የፋኖ አባላቶች ባደረሱበት መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ያቃተውና ከፍተኛ የሰው ኃይሉን አጥቶ በነበረበት እንዲቆምና  ሙትና ቁስለኛውን በተደጋጋሚ ሲያመላልስ እንደነበር ለማየት ችለናል። ይህንንም አሥደሳች ዜና  የሰማው ሌላኛው የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚዎች እና እራስ በሀይሉ ብርጌድ በመናበብ በተመሳሳይ ስዓት በአረርቲ  ወሌሱ ኬላ ላይ  የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚዎች የምድር ድሮኖቹ ነበሮ ሻለቃ ሲገቡ በሌላኛው  ባልጪ ኬላ ላይ እራስ በሀይሉ ብርጌድ ሸማቂ ፋኖዎች በወሰዱበት ጥቃት ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት ያጋጠመው ሰራዊት አካባቢውን በድንጋጤ ሸሽቶ ቦታውን ለቆ ሙትና ቁሥለኛውን ጥሎ ፈርጥጧል።    ከዚህ በጨማሪ ባልጪ ኬላ ላይ በተደረገበት ጥቃት ከፍተኛ ጥቃትና ጉዳት ያሥተናገደው የብልፅግና ሰራዊት  አመራር ጭምር የተመታበትና የሞተበት ሰራዊት በብሥጭትና በደመ ነፍሥ በሌላ አቅጣጫ ሸንኮራ ወንዝ ላይ ቢሞክርም የፋኖን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው ወደመጣበት መመለሱን  ከሥፍራው የነበሩ እማኛኞች የነገሩን ሲሆን ይህን ተከትሎ   የብልፅግናው ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት ያሰበው ሳይሆን ባላሰበው  አቅጣጫ የውጊያ ስልቱን በመቀየር በነበልባል ክፍለ ጦር ሲቀጠቀጥ ቆይቶ በተቃራኒው ከባቢው  ሰራዊት ከበባ ውስጥ ገብቶ ከፍተኛ ኪሳራ በማስተናገድ እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል።       መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ  ጌታሁን  ነው። ‎                 " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።     ‎ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም     

ከነገ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ከተማ አዲዘመን መንገድ ለመንገደኞች ክፍት ተደርጓል!!   ከማጥራትና ማብቃት ተልዕኮ ጋር በተያያዘ   የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ከታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ አዲዘመን ድረስ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ የማጥራትና ማብቃት ስራ እየተከወነ ቆይቷል። በተለያዩ ዕኩይ ፍላጎቶች በመስመሩ እየተገኙ መንገደኞችን ያንገላቱ የነበሩ ቅጥረኛ ወሮበሎች ላይ በተወሰደ ርምጃ አንፃራዊ ለውጥ የታየ ቢሆንም ቀሪ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም የሚከተሉትን ማሻሻያዎች በጊዜያዊነት አስቀምጠናል። 1ኛ .መንገዱ ከነገ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንዲሆን፣ 2ኛ.ላልተወሰነ ጊዜ በኮሩ ፈቃድ ተጥለው የነበሩ ኬላዎች እንዲነሱ፣ 3.በኮሩ የበላይ አመራር ስምሪት ከተሰጠው አካል ውጭ ማንኛውም የታጠቀ አካል በመስመሩ 5 ኪ.ሜ ርቀት እንዳይገኝ፣ ትዕዛዙን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም የታጠቀ አካል ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ፣ 4ኛ.መንገደኞች እና ማህበረሰቡ የተለመደውን ቀና ትብብር እንዲያደርግልን ሲል አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር መልዕክቱን አስተላልፏል።       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!             ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም           ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር             ጎንደር/አማራ /ኢትዮጵያ

#ጥብቅ_ማስጠንቀቂያ_ለ33ኛ #ክፍለ_ጦር_የዐፋብኀ_አባላት ═══════════❁✿❁════════════ (ታኅሣስ 10/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) አንዳንድ አባላት ከድርጅቱ አሠራር ውጪ ድርጅቱ ያስታጠቃቸውን የጦር መሣሪያ ሲሸጡ (ሲለውጡ) ይስተዋላል። ይሁን እንጂ "ለማሻሻል ነው" በሚል መልካም ድርጅታዊ እሳቤ ለጉዳዩ ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር ሳናደርግበት ቆይትናል። ነገር ግን አንዳንድ የድርጅታችን አባላት ጥቁር ክላሽንኮቭን ጨምሮ በጀግኖች መስዋዕትነት የተገኙ የጦር መሣሪያዎቻችንን ሲሸቅጡ፤ በምትኩም በጥራታቸው ዝቅ ያሉ መሣሪያዎችን ሲይዙ እና በጀግኖች ደም ሲቀልዱ እያየን ነው። ስስለሆነም ይህ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ ዕውቅና ውጪ የትኛውንም አይነት መሣሪያ መሸጥ እና ማሻሻል ፍፁም የተከለከለ መኾኑን እናሳውቃለን‼ የጊዜያዊ መንግሥታችን አባላትና መላ ደጋፊዎቻችን፦ በዚሁ አጋጣሚ መሣሪያ የሚሸጡ (የሚለውጡ) አባላትን በውስጥ መስመር በማጋለጥ ትግላችንን እንድታግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን‼ #33ኛ #ክፍለ_ጦር ▶ ጽናት እና አንድነት ለመላ ታጋዮቻችን‼ ▶ ክብር፣ ሞገስ እና ጽድቅ ለጀግኖች ሰማዕታት‼🙏🙏🙏

#በሸበል_በረንታ_ወረዳ_የሚገኘው_የአገዛዙ_አረመኔዊ_ሰራዊት_እየፈራረሰ_ነው!!💪💪💪 ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም‼️ 1ኛ.ዳኔል ዋለ 2ኛ.ጌትነት ፀጋው 3ኛ.ስጦታው መሌ የተባሉ የአገዛዙ ሻንበል አ
+4
#በሸበል_በረንታ_ወረዳ_የሚገኘው_የአገዛዙ_አረመኔዊ_ሰራዊት_እየፈራረሰ_ነው!!💪💪💪 ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም‼️ 1ኛ.ዳኔል ዋለ 2ኛ.ጌትነት ፀጋው 3ኛ.ስጦታው መሌ የተባሉ የአገዛዙ ሻንበል አመራሮች ሲሆኑ በሸበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ ከሚገኘው 6ኛ ዕዝ 601 ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ እሬጅመንት የአገዛዙን ሰራዊት በመክዳት ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም 1ኮርያ ክላሽ ከ150 ጥይት ከወገብ ትጥቅ ጋር ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!        #የቴወድርስ_ዕዝ_201ኛ_ኮር_ህዝብ_ግንኙነት          ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም

አሳዛኝ ዜና ========  ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የአዉደ ዉጊያ ሽንፈቱን መቋቋም ሲያቅተዉ ንፁሀንን ወጣቶች ላይ እንዲሁም በትምህርት ገበታ ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ ነፃ እርምጃ መዉሰዱንና የንፁሀንን አርሶ አደሮች ሀብት ንብረት ዘረፋ ፈፀመ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ ከሰም ኮር ቡልጋ ክ/ጦር የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂዎች ቀበሌዎችን ለመቆጣጠር አስበዉ ቢመጡም በክንደ ነበልባሎቹ የቡልጋ ክፍለጦር አርበኛ አብርሀም ማሞ ሻለቃ አናብስቶች የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተዉ  ወደ ገበያ እህል ጭነዉ በሚሄዱ አርሶ አደሮች በአደባባይ የዘረፋ ወንጀል እና በአካባቢዉ ወደ ገበያ ለመሄድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወጣቶች በተጨማሪ በ02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ተሬ በሚባል አካባቢ በትምህርት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች  ላይ አፈሳና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ፈፅመዋል። አማራን ካላጠፋሁ እንቅልፍ አይወስደኝም ያለዉ የብልፅግና ሴት ደፋሪ እና ጡት ቆራጭ አራዊት ሰራዊት  በቀን 8/4/2018 ቀን እሮብ እለት ከ05 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡርቃ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ከ35 ጭነት በላይ እህልና በሁለት መኪና የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ መኪና ወደ ገብያ  በመሄድ ላይ ሳሉ የሚገኙ ወጣቶችን እንዲሁም በትምህርት ገበታ ላይ በነበሩ ተማሪዎችን ከሚማሩበት ክፍል በማስወጣት እና በግዳጅ ይዞ በመሄድ ከተማዉ ዉስጥ ሲደርሱ በብልፅግና ሰራዊት ዘረፋ፤እገታ እና ድብደባዎች ተፈፅሞባቸዋል። ይህ የዘረፋ ወንጀል የተካሄደዉ ፀረ አማራ የሆነዉ የብልፅግና ሰራዊት አዛዥ ነኝ በሚለዉ ኮረኔል እና በመተህብላ 01ቀበሌ አስተዳዳሪ ነኝ በሚሉ አካላት ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጭነት እንደሆነ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ማረጋገጥ ተችሏል። በተያያዘ ይሄ ፀረ ህዝብ የሆነ ሰራዊት በ09 ቀበሌ ልዩ ስሙ ደመቆ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ለገብያ በሄዱ  አርሶ አደሮች ላይ ቤታቸዉን በመስበር የንብረት ዝርፊያ እና ዉድመት አድርሰዋል።     መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ቡልጋ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።           "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም ‎