uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 487
Підписники
-524 години
+677 днів
+84830 днів
Архів дописів
📌አሰብ ሳደርስ በቅርቡ ግብዓተ መሬትህ ይፈፀማል! “አሰብ የባህር በራችንን ወደ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመመለስ ለሚሰጠን ግዳጅ  ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል።” ይህ ከላይ ያለውን የተናገረው የኦህዴዱ የጥቅም ተጋሪ እና የአብይ አህመድ የግል ጀነራል ብርጋዴል ጀነራል ቡልቲ ታደሰ እየደሰኮረ ነው። የብልጽግና ጀነራሎች ቀፈታቸው እስከሞላላቸው ድረስ ከብልጽግና ትንንሺ አክቲቪስቶች በባሰ መልኩ በፕሮፓጋንዳ ሚዲያውን በማጨናነቅ አንደኛ ናቸው፣ የብልጽግና አገዛዝ ያለጦርነት ውሎ የማያድር በጦርነት እድሜውን ለማራዘም ከጥቅምት 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት እንመራዋለን በሚሉት ሕዝባቸው መደበኛ ጦርነት ከፍተው ዛሬም ድረስ በለብለብ ስልጠና የድሃ ልጅ እየማገዱ እነሱ ቦርጫቸውን እያሹ በድሃ ልጅ ደም መዝናናትና አሸሸ ገዳሜ ማለት የለመዱ ናቸው። ብልጽግና የወሮ በላዎች ስብስብ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ቢሆንም በጦርነት ላይ ጦርነት እየቀጠሉ የግል ጥቅማቸውን ማገበስ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው አድርገውታል። ጦርነት እንደመጀመሪያው ፕሮፓጋንዳ ቀላል አይደለም፣ ከአማራው ጋር ጦርነት ሲጀምሩ እነ ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ “አማራውን በሶስት ሳምንት ውስጥ አይደለም መሳሪያውን ቀበቶውን እናስፈተዋለን” ብለው ቢገቡም የአማራ ወጣት በቆመጥ እያንቆራጠጠ የአብይ አህመድን ሰራዊት ትጥቁን አስፈጥቶ ብሔራዊ ኃይል ሁኖ ወጥቷል፣ ከዛም አልፎ የምስራቅ አፍሪካ ሚዛን አስጠባቂ ኃይል ሁኖ ወጥቷል፣ እየወጣም ይገኛል። የድንቁርና ጌቶች የሆኑት የአብይ አህመድ የግል ጀነራሎች አሁንም አሰብ አሰብ እያሉ ነው፣ አሰብ ከመድረሳቸው በፊት ግን በቅርብ ቀን እንዴት እንደሚባረሩ ለነሱ እንቆቅልሽ ነው፣ የአማራው ኃይልም አሰባሳቢ የተቀናጀ እየሆነ እየመጣ ነው። የአማራው ኃይል አገዛዙን ለማስወገድ እየሰራ ነው። ይህም እንዲሳካ በቀጣይ ወራት •ሕዝባዊ ትጥቅ ትግል •ሕዝባዊ አመጽ •ጠንካራ ሕዝብ ግንኙነት •ዲፕሎማሲ እና •ፕሮፓጋንዳ ያቀፈና ያማከለ ትግል ማድረግ ይጠበቅበታል። ብልጽግና በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ ይፈፀማል! መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#ተወርዋሪው_አርበኛ_ድርሳን_ብርሀኔ‼️ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምስራቅ አማራ ቀጠና ፣ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ድርሳን ብርሀኔ ምስራቅና ደቡብ አማራ ቀጠና #እየተወረወረ ብ
🔥#ተወርዋሪው_አርበኛ_ድርሳን_ብርሀኔ‼️ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምስራቅ አማራ ቀጠና ፣ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ድርሳን ብርሀኔ ምስራቅና ደቡብ አማራ ቀጠና #እየተወረወረ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን በዛሬው ዕለት በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓያዕቆብ ኮር ምስረታ ላይ የበኩሉን አስተዎፆ ያደረገ ሲሆን የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል‼️ የቪዲዬ መልዕክቱን ከታች ባለው link ይመልከቱ ፣ሀሳብዎን ያስቀምጡ ፣ገፁን ይወዳጁ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/share/r/16ncTfHiXB/

አፋብኃ በከፍታ ላይ ነው! በጎንደር ሰማይ ሰር እነ ትልቁ! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እ
አፋብኃ በከፍታ ላይ ነው! በጎንደር ሰማይ ሰር እነ ትልቁ! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ የጦር ጠበብቱ ድርሳን ብርሀኔ ሸዋ ተገኝቷል። ቀጣይ ደግሞ አርበኛ ዝናቡንና አርበኛ ሳሙኤል ባለድልን ክተት አውጀው ጦራቸውን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ የጦር ጠበብቱ ድርሳን ብርሀኔ ሸዋ ተገኝቷል። ቀጣይ ደግሞ አርበኛ ዝናቡንና አርበኛ ሳሙኤል ባለድልን ክተት አውጀው ጦራቸውን ይዘው ሸዋ ይገባሉ ብለን እንጠብቃለን። ታዲያ ከዚህ በላይ ጥምረት አለ ? አፋብኃ አታጋይ ድርጅቴ ወደፊት ብቻ💪 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ጋሸዋ! ዛሬያችንን ለ1:00 ደቂቃ በአካል ተገኝተህ ብታይልን የነፍሳችን ሀሴት አሁን ካለበት በመቶ እጥፍ ከፍ ይል ነበር። ኮ/ል ደራሲ እና አርበኛ አሰግድ ነበርን በልባችን ውስጥ የትግላችን ዕርዕዮ
ጋሸዋ! ዛሬያችንን ለ1:00 ደቂቃ  በአካል ተገኝተህ ብታይልን የነፍሳችን ሀሴት አሁን ካለበት በመቶ እጥፍ ከፍ ይል ነበር።   ኮ/ል ደራሲ እና አርበኛ አሰግድ ነበርን በልባችን ውስጥ የትግላችን ዕርዕዮት ሆነህ ለዘላለም  ትቀጥላለህ! አርበኛ አብደላ እንድሪስ ! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "የፖለቲካ መኮንኖችን" በድምቀት አስመረቀ:: ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "ፀሃፌ
+1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "የፖለቲካ መኮንኖችን" በድምቀት አስመረቀ:: ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ የፖለቲካ መኮንን ማሰለጠኛ ማዕከል" የሚል ፕሮጀክት በማቋቋም የመጀመሪያ ዙር የፖለቲካ መኮንኖችን ለበርካታ ቀናት ሲያሰለጥን ቆይቶ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል። የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የፖለቲካ ዘርፍ ሥር የተቋቋመው የፖለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል በኢትዮጵያ የፖለቲካና የድፕሎማት ታሪክ ደማቅ አሻራ ባለቤት በሆነው ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ስም በመታሰቢያነት ተሰይሟል። ከሁሉም ኮሮች የተመለመሉ ሰልጣኝ የፖለቲካ መኮንኖች በርካታ ዉጣዉረዶችን አልፈው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለምረቃ በመብቃታቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የተላለፈ ሲሆን የመኮንን ተመራቂዎቹ በሰለጠኑት መሰረት በአማራ ብሔርተኝነት መስመር ትግሉን በትጋትና በንቃት ለማገልገል፣ ድርጅታችን አፋብኃን ለመጠበቅ፣ ፖለቲካዊ ሥራዎችን ለመስራት ቃል ገብተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#አስጨናቂው_ጦር_ከ4ኪሎ_በቅርብ_እርቀት💪 አስደማሚው የአፋብኃ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር አንድ ምስረታ።‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኮር ምስረታ አካሄደ ‎================ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አምስት ክ/ጦሮችን ወደ አንድ በማሰባሰብ ግዙፉን የፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር አንድ መስርቷል:: ‎ ‎ይህንን ኮር አፄይኩኖ አምላክ፥ ሰባት ለሰባ፥ ነጎድጓድ፥ ናደው እና በፍቃዱ በላይ ክ/ጦሮች በአንድ ላይ ሁነው ነው የመሰረቱት :: ‎ ‎ይህ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ምስረታ ሥነ ስርዓት የአሳምነው እዝ አመራሮች፥ የየክ/ጦር መሪዎች፥ የፋኖ አባላት፥ አባት አርበኞች፥ የሀይማኖት አባቶች፥ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኤፍራታና ግድም ወረዳ በደራሲና አርበኛ አሰገድ መኮነን መቀመጫ ማጀቴ ተካሄዷል:: ‎ ‎በዚህ የኮር ምስረታ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አፄ ይኩኖ አምላክ፥ ሰባት ለሰባ ፥ነጎድጓድ ፥ ናደው እና በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር የፋኖ አባላት በወታደራዊ ሰልፍ ተመው በመምጣት ተሳታፊ ሁነዋል:: ‎ ‎የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ምስረታ ፕሮግራም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል እና ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና መሪ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እስካሁን የገጠሙንን በርካታ ተግዳሮቶች በፋኖ አርበኞቻችን እና በማህበረሰባችን ጥንካሬ ተወጥተን የጋራ መሰባሰቢያ ቤታችንን ከሸንኮራ እስከ ቋራ ተጉዘን ገንብተን በመጣን ማግስት ታላቁን የፄ ዘርያይቆብ ኮር መመስረት መቻላችን ጥንካሬያችን የታየበት በመሆኑ ሁላችንም ደስ ሊለን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል:: ‎ ‎በኮር ምስረታው የተገኙት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል እና የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ፊት አውራሪ ድርሳን ብረሀኔ ከአሳምነው ዕዝ ጋር በጋራ በመስራት የጥላትን ቅስም የምንሰብርበት ወቅት ሩቅ አይደለም ብለዋል:: ‎ ‎ይህንን የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ምስረታ በተመለከተ የስም ስያሜ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ በኩል ማብራሪያ ተሰጥቶ የዕዙ የድርጅት ጉዳዮች  የቀጣይ እቅድ የሚያመላክቱ መልእክቶች ተላልፈዋል:: ‎ ‎በዚህ የኮር ምስረታ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ ዋና አዛዥ ፊት አውራሪ ባዩ አለባቸው የፋኖ ኃይል ሊከተላቸው የሚገቡ የቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችና ወታደራዊ መመሪያ ምን መምሰል እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል:: ‎ ‎የኮር ምስረታ ፕሮግራሙም በተለያዩ መጣጥፎች፥ ግጥሞች፥ ሽለላና ቀረርቶ በድምቀት ከተካሄደ በኋላ  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል እንዲመሰረት ከሸንኮራ እስከ ቋራ ተራራ ሸንተረሩ ቁርና ብርዱ እንዲሁም የጠላት ሀይል ሳይበግራቸው አንድ የአማራ ቤት ሰርተው ለተመለሱት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የቃል ኪዳን ምልክት የሆነችውን የአባቶቻችን የቃል ኪዳን አርማ የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማ በማበርከት ለቀጣይ መሪነት ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል:: ‎ ‎በመጨረሻም የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ም/ል መሪ በአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የአፄ ዘርአያዕቆብ ኮር አንድ መሪ ሁነው የተመደቡ የፋኖ አመራሮች ቃለመሀላ እንዲፈጽሙ ተደርጎ የተመደቡ አመራሮች የአማራ ህዝብ የጣለባቸውን አደራ በብቃት እንዲወጡ ጭምር መልእክት በማስተላለፍ እና ከብልጽግና ጋር ወግነው ለሚሰሩ አመራሮች፥ የአድማ ብተና ፥የሚኒሻ ፥ እና የመከላከያ አባላት የፋኖን ትግል እንዲደግፉ ጥሪ በማስተላለፍ ፕሮግራሙ ተጠናቋል:: ‎የኮሩን አመራሮች ዝርዝዝ ሙሉ መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።             "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ©አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል        ጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም ‎ ጠፋ የተባለው 4ኪሎ አቅራቢያ የሚገኘው የሸዋ ፋኖ በኮር ተከስቷል‼️ 03/13/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥በአዲሱ ዓመት አማራነትን ፀረ-አማራነት ከማይደርስበት ሰገነት እናስቀምጠዋለን‼️ ምላጭ የመዋጥ ያክል ከብዶ የነበረው አማራዊ አንድነት በአንድ ማንኪያ ቅንነት ጥሩ የአዲስ አመት ዋዜማ ላይ እንድንገኝ አድርጎናል ። ይሔ አማራዊ አንድነት በፍጥነት እየተጎዘ በሚሄድበት ወቅት ከሚፈለገው ቦታ ለመድረስ በአንድነት ጉዞ ውስጥ የሚገኙ መንገደኞች የኋላ እና የፊት መስታውት በመመልከት ፣ አቅጣጫ በመጠቆም ፣ መስታውት በመወልወል ወይም ፀሎት በማድረግ ማገዝ አማራዊ ግዴታው ነው ። ነገር ግን የባሱን መሪ ፣ ፍሬን እና ነዳጅ መቆጣጠሪያውን  ለሹፌሩ መተው ደግሞ ጉዞውን ሙሉ ጤነኛ እንዲሆን ያደርጋዋል ። በዚህ ጉዞ ላይ ለተሳፋሪዎችም ሆነ ለሹፌሩ ሳይናገር ለመውረድ የሚሞክር ካለ ግን ፈጣሪ ፣ ህዝብ ፣ጊዜ እና ታሪክ የትውልዱ መሣቂያ እና መሣለቂያ ያደርጉታል ። የአማራነት ሰይፍም ይበላዋል ። የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ባለቤቶች አማራነትን በብዙ ሰው ሰራሽ እና ስርዓት መር ችግሮች ከቀበሩበት የብረት በርሚል ውስጥ  አዲሱ ትውልድ ከቀበሩበት አውጥቶ ለዓለም ህዝብ እያሣየው ይገኛል ። ከዚህ ስንደርስ ግን እልፍ አይተኬ የጀግኖች ህይወትን ገብረንበት፣ እልፎች አካለ ጎደሎ ሁነውበት፣ እልፎች ወሕኒ ቤት ታጉረውበት፣ እልፎች ሀብት ንብረታቸውን አጠው በስደት አገር ሰሪ አገር አልባ ሁነውበታል  ። በነዚህ አስቸጋሪ የአማራው ዓመታቶች ፈጣሪ ፣ ታሪክ ፣ ጊዜ እና ህዝብ  በደንብ እየታዘቡን ወየም እየመዘኑን ይገኛሉ ። ከአራቱ ሚዛኖች በአንዱ ተመዝኖ የወደቀ ሰው ደግሞ በፍፁም ዋጋ የማያወጣበት ወድቆ የማይነሳበት ደረጃ ላይ ይደርሳል ። ምንም አይነት ሰዋዊ ልዩነቶች ቢኖሩብንም እንኳን እንደ ህዝብ ላለመጥፋት ቤት ንብረታችን ጥለን የወጣን የአማራ ልጆች አንድ ለመሆን የሚያስቸግረን ጉዳይ ይኖራል ተብሎ አይገመትም  ። ወቅቱ ምንም በዓይንህ ማየት ማትፈልገው ሰው እንኳን ቢሆን ለህዝባችን አንድነት ሲባል ቀድመህ ይቅርታ ጠይቀህ ወደ ስራ ምትገባበት ጊዜ ነው ። በነፃ ለነፃነት የሚታገል ታጋይ እና አታጋይ ትልቁ ደሞዙ ' ነፃነት ' ነው ። ነፃነት ደግሞ በነፃ አይገኝም ። ነፃነት ጨርሶ የሚያጠፋ ወይም የሚያም 'ዱላ' አለው ። ዱላው የወንድም ከሆነ ደግሞ ቢያምም ያድናል ።  አማራነት ወደ ባለቤቱ የአማራ ህዝብ እንዲመለስ ደግሞ አዲሱ ትውልድ አንድ አማራ እና አንድ የጥይት ፍሬ እስክትቀረው ድረስ ታግሎ ያስከብረዋል ። አማራነትን ፀረ አማራነት ከማይደርስበት ሰገነት ከፍ አድርጎ ያስቀምጠዋል  ። አማራነትን ባለቤቱ ብቻ ሊያውቀው በሚችለው መፍቻ ተቆልፎ ይቀመጣል ። ምክንያቱም አማራነት የባለቤቱ ውድ ንብረት ስለሆነ እና በአደራ ለሌሎች የማይሰጥ ማንነት ስለሆነ ። ፈጣሪ ሁሌም ጥሩ ዘመኖችን ሲሰጠን ቆይቷል ። እነዚያን ዘመናቶች ጥሩ ወይም መጥፎ ምናደርጋቸው እኛው የእርሱ ፍጥረቶች ነን ። አሁን ግን ፈጣሪ ጥሩ ዘመን ብቻ አይደለም የሠጠን ጥሩ መሪ እና መልካም አጋጣሚዎችን ፈጥሮልናል ። የተሠጡንን መልካም አጋጣሚዎች  ለአማራው እና ለፍትሕ ወዳድ ሀገሬው የሚበጅ አድርጎ መጠቀም ወይም መስራት ደግሞ የዚህ ትውልድ ለነገ የማይባል አሁናዊ ስራው ተደርጎ መታወጅ አለበት ። ይሔን ጊዜ እና መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ሳንጠቀም ከቀረነ እና እንደ ህዝብ ካልጠፋነ ሌላ 500 ዓመት ከመከራ እና ጭቆና ጋር ለመጠበቅ እንገደዳለን ።  እኛ ደግሞ ይህ እንዲሆን የማንፈልግ ትውልዶች ነን ። በጳጉሜ ውሐ መንፃት ለሠውነታችን እና ለልብሶቻችን ብቻ ሳይሆን ለአስተሳሰባችንም ስለሚጠቅም በደንብ እንጠቀምበት ።   ' እጅ ከለቀቀ ብልሐት አለቀ ' የሚለው  የሕፃናት የብይ ጨዋታ ህግ ለአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ አሰላለፍም ይሰራል ። እጃችን  ላይ ያለውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ በማስተዋል መጠቀም ለነገ ቤታችን ማማር ትልቅ ጉልበት ስለሚኖረው ለመጠቀም ግዴለሽ መሆን አያስፈልግም ።                     ሰገነቱ ላይ እንገናኝ !                  መልካም ዓዲስ ዓመት ! አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ! ©አርበኛ ግሩም ምሳሌ የቴዎድርስ ዕዝ ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ 03/13/2017 ዓ.ም

🔥#የፋኖ_ሰራዊት_አስመርቀናል‼️ አፋብኃ ራስ አሞራው ፫ኛ ኮር ደጃዝማች አያሌው ብሩ ክ/ጦር ብቁ ስልጠና የወሰዱ የሰራዊት ዓባላትን አስመርቋል። መመልመል፣መቀስቀስ፣ማደራጀት፣ማሰልጠን፣ማስተዳደር ተ
+6
🔥#የፋኖ_ሰራዊት_አስመርቀናል‼️ አፋብኃ ራስ አሞራው ፫ኛ ኮር ደጃዝማች አያሌው ብሩ ክ/ጦር ብቁ ስልጠና የወሰዱ የሰራዊት ዓባላትን አስመርቋል። መመልመል፣መቀስቀስ፣ማደራጀት፣ማሰልጠን፣ማስተዳደር ተግባራት አጠናከክረን እየቀጠልን ነው። © አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ              ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

የአማራ ጠላቶች :- 1/ ስልጣኔያችንን አውድመውብናል ፤ 2/ ዕድገታችንን አቋርጠውብናል ፤ 3/ ርስታችንን ነጥቀውናል ፤ 4/ከብሔራዊ ጥቅም እና ብሔራዊ ተሳትፎ ገፍተውናል ፤ 5/ ተሳዳጅ እና ተፈናቃይ አድርገውናል ፤ 6/ እውቀታችንን ፣ ጥበባችንን ፣ ባህላችንን ፣ ሐብታችንን ፣ ፍልስፍናችንን አስጥለውናል ፤ 7/ ሁለንተናዊ ተስፋ ቢስ አድርገውናል ፤ የዚህ ዘመን የእኛ ትውልድ :- 1/ ታሪካዊ ውድመቱን በውል ተገንዝቧል ፤ 2/ የጠላቶቹን አሰላለፍ ፣ አቅም ፣ ፍላጎት እና ያስከተሉበትን ሁለንተናዊ ጥፋት ተረድቷል ፤ 3/ ያመለጡት ዕድሎችን በደንብ ታዝቧል ፤ 4/ ዛሬ ላይ መገኘት ባለበት ቦታ ፣ ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ፤ 5/ መሬት ላይ ላለው ነባራዊ ችግር አስቻይ የመፍትሔ እርምጃ እየወሰደ ነው ፤ 6/ ድርጅታዊ ትግል ጀምሯል ፤ 7/ አዳጊ አመራርነት ፈጥሯል ፤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) !! 1/ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 2/ ደቡብ አማራ ቀጠና ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ዕዝ 3/ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 4/ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አሁን ላይ ያሉ ፀጋዎች :- 1/ አንገብጋቢ የትግል ምክንያት ፤ 2/ ሰፊ መልከኣ ምድር ፤ 3/ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ፤ 4/ ያልተነካ እና ያልተለካ ዕምቅ የተፈጥሮ ሐብት ፤ 5/ ለመታገል የተዘጋጀ ማህበረሰብ ፤ 6/ ደካማ ጠላት ፤ የፋኖ የጨዋነት መለኪያዎች :- 1/ ከፍተኛ ሰብዓዊ ትኩረት ማድረጉ ፤ 2/ የመሰረተ ልማት ጥበቃ ማድረጉ ፤ 3/ ህገ ወጥነትን ማስወገዱ ፤ 4/ ስኬታማ እና ውጤታማ ጊዜያዊ አስተዳደር መዘርጋቱ ፤ የቀጣይ የአማራ ትግል አቅጣጫዎች :- 1/ ጠንካራ የትርክት ግንባታ ፤ 2/ አመራርነት ፈጠራ እና ዕድገት ፤ 3/ የህዝብ ቅስቀሳ እና ሐብት ማሰባሰብ ፤ 4/ የፖለቲካ ሪዮት ዓለም ማስረጽ ፤ 5/ አቃፊነት እና ተባባሪነት ፤ 6/ የአብዮታዊ ብሔርተኝነት ፖለቲካዊ ዕድገት ፤ የትግሉ የግንባታ መስኮች :- 1/ የሐይል ግንባታ ፤ 2/ የፖለቲካ ግንባታ ፤ 3/ የትርክት ግንባታ ፤ 4/ የዲፕሎማሲ ግንባታ ፤ 5/ የመሳሪያ ግንባታ ፤ 6/ የምጣኔ ሐብት ግንባታ ፤ የአማራ ትግል አሸናፊነት የኢትዮጵያውያን የሰላም አሸናፊነት ምሳሌ ፣ የምስራቅ አፍራካ የሰላም አርዓያ ፣ ለአፍሪካ የሰላም እና አንድነት ሞዴል ፣ ለአለም ሰላም ባለ ጉልህ ድርሻ ያለው ነው ። አማራ በቅርቡ ወደ ትናንት የስልጣኔ ከፍታው ይመለሳል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !! ©ፋኖ ማርሸት ፀሐይ ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አገዛዙ የሞባይል ካርድ የሸለማቸው የቋሪት አጥቦ አይለብሴ ሚሊሾች ናቸው😂😂 አይ አለመማር ጉዳቱ አይ በሆድ ማሰብ ክፋቱ ! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እ
አገዛዙ የሞባይል ካርድ የሸለማቸው የቋሪት አጥቦ አይለብሴ ሚሊሾች ናቸው😂😂 አይ አለመማር ጉዳቱ አይ በሆድ ማሰብ ክፋቱ ! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ሀብቴ ወልዴ!! #የእናታለም ጎንደር የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ! 🔥 💪 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ሀብቴ ወልዴ!! #የእናታለም ጎንደር የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ! 🔥 💪 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሰበር ዜና የልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች በጋራ በከፈቱት ጠንካራ ውጊያ የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ውጫሌ ከተማን ተቆጣጥረው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ዛሬ ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር ስር ያሉ ክፍለ ጦሮች የደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በቀጠለው ተጋድሎ እስከ መሀል ከተማ በመግባት የየጁ ክፍለ ጦር ራስ አሊ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ እና ራምቦ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በተናበበ ፍፁም በተቀናጀ መልኩ የተሳካ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት ውለዋል ። እስካሁን ከ10 በላይ ፖሊስ እና ሚሊሻ ሲገደል በቁጥር ያልተረጋገጠ የወራሪው መንግስት ወታደር ሚሊሻ አድማ ብተና አና ፖሊስ ቁስለኛ ሆኗል:: በተጨማሪም ሶስት የሚሊሻ አባላት ምርኮኛ በማድረግ ውጊያው እንደ ተፋፋመ ቀጥሏል:: በዚህ ውጊያ የልጅ እያሱ ኮር የበቀል በትሩን አጠናክሮ በመቀጠል ውጫሌ ከተማ ያለውን የብልፅግና ግብስብሰ የፀጥታ ኀይል እና ካድሬ እያጠራ ይገኛል፡፡ የአብይ ሠራዊት ከወልድያ እና ከደሴ ሁለት ዙ23 እና አንድ መድፍ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ ኪ.ሜ ርቀት ቆሞ ከመተኮስ በዘለለ ምንም ፋይዳ ያለው ተግባር ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡ በተጨማሪም በተደረገው ከፍተኛ የከበባ ውጊያ አንድ ከፍተኛ (ኮሎኔል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) የመከላከያ አመራርም ጭምር ተገድሏል። ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ጮቤ የሚያስረግጥ ድል እየጠበቅን ከበባውን አጠናክረን ይዘናል፡፡ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራው ኩራት #ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የሳቱ ጉማጅ ✅ ያ የባህርዳር ስታዲየም በስሙ የደመቀበት ✅ሺወች በፎቶው ሹራብ ያስሩለት ✅ሚሊዮኖች ከእርሱ ጎን ነን ብለው በፎቶው ባነር አስርተው ሰልፍ የወጡለት ✅ብዙዎች በምስሉ ስአት እና ጌጣጌጥ ያስሩለት ✅መላው አማራ ድምፁን ሲስማ በወኔ የሚሽበርለት ✅ከማንም የገዘፈ የሞራል ልዕልና ያለው ✅ዕንቁ አርበኛ ✅ዕንቁ ታጋይ ✅ዕንቁ የህዝብ ልጅ በስሜን ኢትዮጵያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ፣በምዕራብ ኢትዮጵያ ፣በመካከለኛው ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሉት ነገደ አማሮች በተስፋ የሚጠብቁት ልዩ የዘመኑ ክስተት የትውልዱ አብሪ ኮኮባችን ዘሜችን መከታ ጋሻችን የነፃነት ድልድያችን ከኔ እድሜ ቀንሶ ላንተ ይስጥልኝ የስማዩ ጌታ አንተ ላይ የሚስነዘሩ ላንተ የማይገቡ ነገሮችን በሙሉ አላህ ለኔ ያድርግልኝ ላንተ የሚገቡና አንተን የሜስደስቱ መልካም ነገሮች በሙሉ የምታምነው አምላክ እግዚአብሔር ወዳንተ ያቅርብልህ በሄድክበት ሁሉ ደስታንና ድልን ያጎናፅፍህ ሽርኛን ምቀኛን ሴርኛን በስው ተመስለው ከሚቀርቡ ተኩላዎች አላህ ይጠብቅህ ክንዳለሜ በርግጥም አንተን የሚያውቁና ስላንተ ዱአና ፀሎት ሲያደርጉ የሚውሉ ሚሊዮን እናቶች አሉህ የነሱም ድምፅ ነው ዛሬን እድትኖራት ያደርገህ ከአምላክ በታች ወደፌትም የጀመርከው ትግል ከጫፍ ደርሶ አላማህ ፍላጎትህ ተሳክቶ ያዘነው ህዝብህ ተደስቶ ፣የተራበው ጠግቦ ፣ያጣው አግኝቶ ፣ያመመው ተፈውሶ ህዝቡ በደስታ ፍንድቅ ፏ ፈሺ ብሎ ዋጋ ለከፈልክልን በሙሉ ውለታህን ከፍለን ባንጨርስ እንኳን የሚገባህን ክብርና ምስጋና እደምናቀርብልህ አልጠራጠርም ይሄ ደግሞ የምንግዜም ምኞትና ህልሜ ነው ደግሞም ይሳካል ኢንሻ አላህ!! በበኩሌ የአማራን ትንሳኤ ያየሁ ቀን ደከመኝና ስለቸኝ ሳልል ማይክራፎኔን ይዥ እየዞርኩ ለከፈልክልን መስዋዕት በሙሉ ስላንተ ስለጀግንነትህ ፣ ስለ ጥንካሬህ ፣ ስለ ትዕግስትህ ፣ ስለ የትግል ቆራጥነትህ ፣ አስተዋይነትህ፣ስለ ትህትናህ ፣ ትንሺ ትልቅ ሳትል ስው አክባሪነትህ፣ ወዳድነትህ፣ሁሉንም እደራስህ የምታይበትን ንፁህ ልብህ ፣ ተስፋ ስጭነትህ፣ እና ለህዝብህ ያለህን አመለካከትና፣የመሪነት ብቃትህን ድምፄን ጎላ በማድርግ ህዝብ አይደለም አበደች እንደ ብለው ቀርፀው አለም አቀፍ ማህበርስብ ስለ አንተ እዳይልኝና እድስማልኝ የምንግዜም ምኞቴ ነው ይሄንን የማደርገው ስለምወድህ ብቻ አይደለም ስለሚገባህም ጭምር ነው ወላሂ ላንተ የማይገባህ ነገር ምን ሊኖር ይችላል??በምድር ላይ አሉ የተባሉ ውብ እና ውድ እና መልካም ነገሮች በሙሉ ይገቡሀል!! #በርግጥ አንተን የሚጠሉ አሉ ነገር ግን አስርግጨ የምናገርው ነገር ቢኖር ጥላቻ ሳይሆን ምቀኝነት & የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው ፀር አማራ፣ፀር ስላም እንዲሁም የብልፅግና ካልሲ አጣቢወች አሽርጋጆች & አጎብዳጆች በተጨማሪም ለህዝባቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ከርሳሞች ብቻ ናቸው። ዳግማዊ በላይ ዘለቀ ብየሃለሁና በርታልኝማ አለቃ❤️🤗 አድስ ትውልድ አድስ ተስፋ አድስ አስተሳስብ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ ድል ለአማራ ብሔራዊ ኃይል አፋብኃ🦾🦾 ድል ለመላው የአማራ ህዝብ💚💛❤️ አይስማም እናሽንፋለን🔥🔥 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

"በሽምቅ እና መደበኛ ውጊያ ጥበብ አንታማም፤ ይህን ጥበብ የከተማ ውጊያ ላይም እንደግመዋለን" (ኮሎኔል ፋኖ ሞገስ ዘገዬ ከጳጉሜው የቃሊሙ ጀብዱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የተናገረው) ኮሎኔል ብላችሁ አትጥሩኝ "ፋኖ ሞገስ" ነው ስሜ ብሎ በቁጣ ተናግሮ ያውቃል። ኮሎኔል ሲሉት አይወድም። ሌሎች አቶ ሆነው ሳሉ ጄኔራልነት ያምራቸዋል፤ እሱ ግን ኮሎኔል ሆኖ ሳለ በወል ስም ፋኖ ብላችሁ ጥሩኝ አለ። ይህ ሰው ንፁህ እና ጀግና ነው። ምንም አይነት ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎት የለውም። የእሱ ፍላጎት ህዝብ ተኮር ነው። የአማራ ህዝብን ማዳን እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ መታደግ ይሻል። ሁሌም ይህን ዘረኛ ስርዓት ብሎ ነው ንግግር የሚጀምረው። ዘረኝነትን አጥብቆ ይጠላል። ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ልዩ ፍቅር አለው። እነሱ ቢበደሉ የእነሱ ፋኖ ይሆናል። እሱ እንዲህ ነው። ፍትሀዊ ነፍስያ ናት ያለችው። የተናገረው ነገር ንግግር ብቻ ሆኖ አይቀርም ይልቁንስ በተግባር ነው የሚታየው። ይህ ጀግና እጅጉን ታማኝ እና ሀቀኛ እንዲሁም ገራገር እና ደፋር ወታደር መሆኑን አብረውት የሰሩ እና የኖሩ ሁሉ ይመሰክራሉ። ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ ከምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት ጋር በነበረው ቆይታ ኮሎኔሉ ስለ ከተማ ውጊያ ተናግሮ ነበር። በሳምንቱ ቃሊም ከተማ ውስጥ የምኒልክ ዕዝ ሰራዊት ገብቶ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀመ። በዚያኑ ሰሞን ዋርካው ምሬ ወዳጆ "በቅርቡ ተአምር እንሰራለን" የሚል ፉከራ መሳይ ንግግር አድርጎ ነበር። አርበኛ አበበ ፈንታው ደግሞ "ትግሉ ህዝባዊ ነው" ብሏል። ህዝብ የፋኖን የማድረግ አቅም ገምግሞ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አርበኛው መስክሮ ህዝባዊ መሰረት አለን ሲል አርበኛ ሔኖክ አዲሴ በበኩሉ "እናሸንፋለን" የሚል ምኞት መሳይ ንግግር ማድረጉን ልብ ይሏል። እነዚህ ንግግሮች እንግዲህ በወርሀ ነሀሴ መጨረሻው ሳምንት ላይ በተለያዩ መድረኮች የተደረጉ ናቸው። የአመራሮች ንግግር በተግባር የተተረጎመበት የጳጉሜው ድል አስደማሚ ነበር። በወቅቱ ማለትም አምና ልክ በዛሬው እለት በወሎ ቤተ አምሓራ ሰማይ ስር በሰሜኑ ክፍል ከወልዲያ እና ሳንቃ መሀል ተራራማይቱ ቃሊም ከተማ ውስጥ እነ ሞት አይፈሬ በጨለማ ዳብሰው ደመኛቸው የሆነውን የ48ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንት ሰራዊት በየማሽላው ውስጥ እየተከተሉ ሲለቅሙት አድረዋል። ቃሊም ከተማ ዙሪያዋን እንደተከከበበች ያወቀው ጠላት በከባድ መሳሪያ እገዛ ሊመክት ቢሞክርም ላታመልጭኝ አታሯሩጭኝ አይነት ነገር ገጥሞት የጨለማ ጥይት ሲሳይ ሆነ። ስትራቴጅክ የጦር ሰፈር ተብሎ የሚጠራውና ወያኔ ደርግ ጋር ሁለት ወር የተዋጋችበት በላጎ ተራራ አቅራቢያ የምትገኘውን ቃሊም ከተማን ለማትረፍ ከደጋ በላጎ ስትንቀዥቀዥ የመጣችው 48ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንት ሰራዊት ሰምጥ ትግባ ስርጥ ሳይታወቅ በአንድ ሰአት ልዩነት ብቻ ለቁጥር አዳጋች አባል እጅ ወደ ላይ ብሎ በሰልፍ ገቢ ሆኗል። እጅ አብሰጥም ያሉት በርካቶች ባሉበት ጭቃ ሆነዋል። የቆሰሉም አሉ። እስከ ሌሊቱ 9 ሰአት በዘለቀው የቃሊሙ ጦርነት 2 ሞርተር፣ 1 ዲሽቃ፣ በርከት ያሉ ብሬኖች እና ስናይፕሮች፣ ብዛት ያለው ክላሽ እና በሳጥን ሙሉ ሙሉ ተተኳሽ ለምኒልክ ዕዝ ገቢ ሆኗል:: ካምፕ ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ነገር ሁሉ የያኔው የአማራ ፋኖ በወሎ (የዛሬው ምኒልክ ዕዝ) ፋኖዎች ቆጥረው ጭነዋል። 48ኛ ክፍለ ጦር መስከረም 2015 ዓ/ም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በበላጎ ግንባር የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትን ስላስበላች በጥቁር ደም ስትፈለግ የነበረች ክፍለ ጦር ናት። የምስራቅ አማራ ፋኖ በመጨረሻው ዙር ወያኔ ጋር እንዳይዋጋ አድርገው ራያን ለትግሬ ሊሰጡ አስበው እነ ግርማ የሺጥላ በወልዲያው ውይይት ላይ ውሳኔ አሳልፈው ፋኖ በላጎ ተራራን ይልቀቅ ሲሉ ዋርካው ምሬ "አንለቅም" በማለቱ ይቺ ክፍለ ጦር እና በጄኔራል ሞሲሳ የሚመራው 105ኛ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት በስተምዕራብ እና በጀርባ በኩል ሆነው አዋክበው በሴራ 31 ፋኖዎችን የሞሲሳ ኃይል ገድሏል። ክፍለ ጦሯ ወዲያው ከበላጎ ተነስታ አላውሀን ተሻግራ ስትጓዝ ሞሲሳም በልዩ ዘመቻ ሰራዊቱ እነ ሲላምላክ ደጉን እና ሌሎች በወቅቱ የአሳምነው ብርጌድ ጓድ የነበሩትን ጀግኖች ሲበላ ወያኔ የቀንየለይ ብላ ከተፍ አለች። ጀግናው ሰማዕት ሲላምላክ ደጉ በወቅቱ የአሳምነው ብርጌድ አስተዳደር እንደነበር ልብ ይሏል። በወንድሞቹ አምና ደሙ በደንብ ተመለሰለት። የአምናውን ውጊያ ንድፍ እነ ኮሎኔል ሞገስ ሰርተውት በዝነኛው አርበኛ በለጠ ሸጋው አዋጊነት ለማመን የሚከብድ ድል ነው የተመዘገበበት:: ይህ ጀግና ባለበት ግንባር ሁሌም ድል አለ። ማርሽ ቀያሪው ይሉታል ጓዶቹ። ቃሊም ከተማ ውስጥ አምና በጳጉሜ በሌሊት የተሰራው ጥንቅቅ ያለ ስራ የዋርካው ልጆች ስትራቴጅክ የጦር ሰፈር የተቆጣጠሩበት ድንቅ ተጋድሎ ነው። በላጎ ተራራ ማለት ወደ ሮቢት እና ጎብዬ እንድሁም ሳንቃ ከተሞች የሚያልፍን የጠላት ኃይል መቆጣጠሪያ ሲቱዌሽን ሩም ማለት ነው:: ከወልዲያ ወደ ባህርዳር የሚጓዘውን መንገድ ድልብ ላይ ለመቁረጥ የሚያስችል የጥቁር አስፋልት መቀስ የሆነ ተራራ መሆኑንም ልብ ይሏል። በላጎ ተራራ በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር መግባቱ ወልዲያ ላይ ያለውን ጠላት ጭምር እረፍት ለመንሳት ያስችላል ተብሎ ስለሚታመን ነው ኦፕሬሽኑ የተሰራው። በኦፕሬሽኑ ሞርተር ተማርኳል፤ ሞርተር ደግሞ 16 ኪ/ሜ ድረስ ይመታል። የጠላት ክምችት ያለበትን ካምፕ እና ተግተልትሎ በኦራል የሚጓዝን ጠላት ድባቅ ለመምታት ሞርተር ተመራጭ ነው። የሞርተር ቅንቡላ የመታው ጠላት ሰውነቱ ተቦጫጭቆ ነው እንደ ቅጠል የሚረግፈው። በቃሊሙ ውጊያ የወንድሞቻቸውን ጀርባ ለጠበቁት መንገድ ቆራጭ የወገን ኃይል አባላትም አክብሮት መስጠት እና አብሮ ማስታወስ ተገቢ ነው። በተለይ የሰማዕቱ ጀግና (ሻለቃ ደምስ ይመር) ልጆች ወልዲያ ውስጥ ካሉ ካምፓች ጠላት እንዳይወጣ መንገድ ዘግተው ሲታኮሱ ነበር። ወደ ቃሊም አናስገባም ብለው የብረት አጥር ሆነው አድረዋል። የያኔው ልጅ እያሱ ክፍለ ጦር (የዛሬው ኮር) ኃይልም ሌላ ቦታ መንገድ ዘግቶ እንደነበር ሰምቻለሁ። የኮሎኔል ፈንታው አንጃ የሆነው ፅናት ክፍለ ጦር ጓዶችም ተመሳሳይ የወንድምነት እና ፋኖነት ስራ ሰርተዋል። መንገድ መዝጋት ደጀንነት ነው። ከተፋላሚው ወገን ያላነሰ አበርክቶ ነው። የጠላት ኃይል እብዳይጨመር ማድረግ የወገንን ሰራዊት ማትረፍ እና ጠላትን ነጥሎ ኃይሉን አሳስቶ ማስመታት ነው። የጨለማ ጥይት ሳይፈሩ በሞት ሸለቆ ውስጥ ተረማምደው አኩሪ ገድል ለፈጸሙ ወንድሞቻችን ያለኝን አክብሮት ዛሬም ለመግለጽ እወዳለሁ። የሀውጃኖ እውነተኛ ወንድሞች፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ የመንፈስ ልጆች እና የጄኔራል አሳምነው ጽጌ አምሳያ ወንድሞቻችን ሆይ በእናንተ ስራ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጅጉን እንደሚኮራ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ። የቀራችሁ ነገር ቢኖር ድሉን መደጋገም ነው። 48ተኛን በመታችሁበት አግባብ ሌሎችንም ማቅመስ ከእናንተ ይጠበቃል። ሰሜን ምስራቅ ዕዝ፣ ደቡብ ዕዝ፣ 6ተኛ ዕዝ እንዲሁም የአየር ወለድ እና ኮማንዶ ዕዝ ወሎ ቤተ አምሓራ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል። የእነዚህ 4 እዞች ኃይል ለምኒልክ ዕዝ ነው የተመደበው። ምኒልክ ዕዝ 4 ዕዞችን እንደ ዘንዶ ውጦ ልናየው እንሻለን። ድል ለወንድሞቻችን። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️