ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 484
Підписники
-624 години
+457 днів
+81630 днів
Архів дописів
🔥የፋኖ መሰረታዊ መርሆ የሆነ ወደፊትም ሆኖ ሊቀጥል የሚችል ቀይ መስመር‼️
በእኔ እይታ የፋኖነት መርህ ሁለት ናቸው ።አሳምነዉነት እና ዮሐንስነት (እስከ መጨረሻው መፅናት ናቸዉ፡፡
ሁለቱ በአንዴ ከተቀናጁ የአማራ ፋኖ ለራሱ ለአማራ ሕዝብ ቀርቶ ለዓለም የሚተርፍ ሀገር በቀል
የፖለቲካና የመንግስት ተቋም ሆኖ ይቀጥላል ።
ልክ እንደ እሰራኤል ሞሳድ የአማራና የዓለም ግርማ ምልክት ሆኖ ይቀጥላል ።
አሳምነውነት ❗❗❗
.አሳምነውነት ምንድን ነዉ ?
"ጣና ዳር ለዳሩ ብዝቀዉ በአካፋ
ጉርጥ ብቻ ሆነ ዓሳ ምነው ጠፋ ?"
የሚል ግጥም በማህበራዊ ሚዲያ ሳነብ የትርጉሙን ምንነቱን ሳስብ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ሳይወለዱ ስም ወጥቶ የቆያቸዉ ገራሚ ሰው ናቸው ። በእርግጥ ሳይነገር ስም የወጣለት ለስሙም ለክበሩም ወሰን የሌለው ጌትነትና ፈጣሪነነት የባሕርይዉ ለሆነው በኋላም እኛን ለማዳን የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ ስም የወጣለት መሆኑን የጀኔራል አባት መሪጌታ በመሆናቸው ያወጡለት ይመስለኛል ።ከስሙ ወደ ፖለቲካ ፍልስፍናዉ ልሻገር ። በነገራችን ላይ በስም የሚሰየሙ ብዙ ፍልስፍናዎች አሉ ። በእኛ አገር የማውቀው አንዴ ብቻ ነው ።ይህም የአባ ገብረሃና ልጅ የሆኑት ተክሌ ገብረሃና ተክሌ አቋቋም የሚባል የቤተክርስቲያን ትምህርት አለ። አሳምነውነት በግለሰብ ስም መርሕ መሰየም አዲስ አይደለም ።በተለይም አዉሮፖዉያኑ
በደራሲ ስም ፍልስፍና መሰየም ይወዳሉ ። በሶቅራጥስ "ሶክራቲክ ክርክር "የሚባል አለ ።
አሳምነውነት ማለት የአማራ ሕልውና ትግል የሜዳ መነፅር ነው ።የአማራ ሕዝብ የሕልውና ችግር ዉስጥ ነው ከዛሬ አምስት መቶ አመት በፊት የከፋ ችግር እንዳይገጥመን እንጠንቀቅ በማለት ቀጥታ የአማራን ወጣት ፋኖ እንዲሆን ነዉ ያደረገው ።በመጨረሻም እኔም ፋኖ ነኝ በማለቱ ለሞት በቅቷል። አሳምነዉነት መስፈንጠሪያችን ነው ።
page 6
አቶ ጌትነት ይርሳው የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከ2012-2013 ዓ/ም ሲመራ እኔም ፋኖ ነኝ በማለቱ ከስልጣን ተባሮ ፋኖነት በሚስጢራዊዉ ጉባዔ የሚል መጽሐፍ ጽፏል ።
አሳምነውነት በዚህ መፅሐፍ ተገልጿል ።
አሳምነዉነት ከኢህዴን ብአዴንነት ወደ ፋኖነት የነፃነት ታጋይ መሸጋገሪያ ድልድይ ነው። ስለዚህ አሳምነዉነት የሕልውና መታገያ ፍልስፍና ነው ።ከዚህ እሳቤ ዉልፍት ያለ ታጋይና መሪ መስመሩን የሳተ የአማራን ትግል የሚያጨናግፍ ሾተላይ ስለሆነ ሌላዉ ቀርቶ ወደ ፋኖ የሚገቡት የብአዴን ሆነ የብልፅግና ወታደራዊ ና የፖለቲካ
መሪዎች የአሳምነዉነት ፍልስፍና ካልተቀበለ መቀላቀል የለባቸውም ። በዚህ ፍልስፍና መመራት የፋኖነት መንፈስ መሆኑን አዉቀዉ ይግቡ!!
በዚህ መርህ ዉስጥ የማንነት ፣የነፃነት ና የእኩልነት መርህ በዉስጡ የያዘ አጠቃላይ የአማራን የነፃነት ና የአንድነት መድበልን የያዘ ፍልስፍና ነው ።
ዮሐንስነት ❗❗❗
ዮሐንስ የጌታ ሐዋሪያ የሆነ ከክርስቶስ ትምህርት እስከ ስቅለት ድረስ የቆየ እስከመጨረሻው የፀና ነው ። የፅኑነት መገለጫ ነው ።በመጨረሻም መክሊቱ የሀዲስ ኪዳን ራዕይ ያየ በመጨረሻም ሞትን እሰካሁን ያልቀመሰ ወንጌላዊ ነው። ስለዚህ ፋኖነትም ለአማራ ሕዝብ እስከመጨረሻው የመታመን እንደ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ
የሚመጣውን አዉቆ ቀድሞ ሒሳብ ሰርቶ በመቆየት ለአማራ ሕዝብ በመታመን መፅናት ያስፈልጋል ።
ፋኖነት እነዚህን ፍልስፍናዎች በአንድነት (commulatively) የሚፈፅማቸው እንጂ በአማራጭነት (altenatively) መጠቀም አይችልም ።
ዮሐንስነት ለታመነዉ ነገር በፍቅር መዝለቅ ነው ።
የፋኖም ትግል ለአማራ ሕዝብ እስከሞት የሚታመን የመጨረሻው ፍቅር ነው። በሞት ከተገለጠ ፍቅር በላይ ሌላ ምን ፍቅር አለ?!!
ለአማራ ሕዝብ ሕይወቱን ሳይሰስት የሚሰጠውን የፋኖ እስከመጨረሻው በማፅናት ነፃነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ስለዚህ አዲስ የሚገቡ የብልፅግናና የብአዴን ሆነ ሌላ የፋኖን ትግል የሚቀላቀሉ ሰዎች አሳምነዉነትና ዮሐንስነት ማሟላት የግድ ይላቸዋል።
ሌላው ደግሞ የሚገቡት ጀኔራሎች የጥቃት ኢላማ ዉስጥ መግባት የለባቸውም ።ይህ ለብልፅግና የጮቤ መርገጫ የእናሸንፋለን የፕሮፓጋንዳ ዜና መሆን ነው ።ስለዚህ ከወያኔዎች የበለጠ የመሪ ጥበቃ ጥበብ ያስፈልጋል። ደስታውን ሀዘን እንዳናደርገዉ ከዉጊያ ቀጠና ባይርቁም የተለየ ጥበቃ ግን ያስፈልጋል ።ስለዚህ የፋኖነት መርህ
እነዚህ ሲሆኑ በእነዚህ መርህ መሰረት የአማራን ሕዝብ የሕልውና ጥያቄ ስልጣን በመያዝ ማስመለስ ነው ።
✔️ ማሳሰቢያ
በዚህ ፅሁፍ የተገለፁ ምሳሌዎች በሙሉ ሃይማኖታዊ አለመሆኑን አንባቢያን ግንዛቤ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ጽሁፉ የትግሉን አዉድ ለማስረዳት የታየበት መነፀር አገር በቀልና ሃይማታዊ ምሳሌ አለማቀፋዊ መረዳት ይፈጥራል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው ።
©ፋኖ ሰለሞን ደሴ (ፈለገ አሳምነው )
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጽ/ቤት ኃላፊ
01/13/2017 ዓ.ም
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር የተሰጠ መግለጫ‼️
ከበፍቃዱ በላይ ክ/ጦር በአንዳንድ ነገሮች አፈንገጠው ለወጡ የሰራዊት አባለት እና እንዲሁም አዲስ ወደ ትግሉ ለመግባት ፍላጎት ላለችው የአማራ ወጣቶች በሙሉ ከዛሬ ጳግሜ አንድ 01/2017 ጀምሮ እሰከ መስከረም 17/01/2018 ዓ.ም ድረስ ወደ ክፍለ ጦሩ በመምጣት እድሜው የፈቀደለት እና ሙሉ ጤነኛ የሆናችሁ ሁሉ ሴት ወንድ ሳትሉ የትግሉ ባለቤት በመሆን የተደቀንብንን የህልውና አደጋ እና የዘር ጭፍጨፋ በጋራ እንድንታደግ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን‼️
አፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር ዋና አዛዠ አርበኛ ፋኖ ውለታው አያሌው
ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ሕዝብ
ክብር እና ሞገስ ልትግሉ ሰማዕታት‼️
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የአፋብኃ አንድነት ስኬት፣ ግማሽ የአንድነት ድል ነው❗
በአፋሕድ እና በአፋብኃ መካከል የሚደረግ የአንድነት ንግግር እና ዘላቂ ስምምነት የአምሓራን የህልውና ትግል እውነተኛ እና ፅኑ የአንድነት መሰረት ያስይዛል።
አሁንም እንላለን!
ከውጭ፣ በግፊት አንድ መሆንን ከምትመርጡት መንገድ በላቀ… ከውስጥ የሚጣራውን የአንድነት ኃይል አድምጡ!!
አዲሱ አመት፣ አፋሕድ እና አፋብኃ ወደ አንድ የትግል መስመር እና ውህደት፣ አልያም ጥምረት የሚፈጥሩበት እንዲሆን የትግሉ ባለድርሻ አካላት ግፊት የምናደርግበት ይሁን!
• ጎጠኞች
• ጥቅመኞች
• ሰርጎገቦች
• እና ጥቁር የአምሓራ ጠላቶችን ቅስም ሰባሪው አንድነት ገና አልመጣም።
በተስፋ የተሞላው ነጋችን ውስጥ ግን፣ ይህ አንድነት እንዲመጣ ተስፋ እናደርጋለን!
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ለጥንቃቄ የአማራ ሚዲያዎች በሙሉ!!
ቆይ መከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ሚዲያን በታንክ እንዲመታለት ሊያዝ ነው? የቸገረ ለት …
ጳግሜ 1/2017/
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሁሉም የአማራ ህዝብ ማንነቱንና አንድነቱን ከሰርጎ ገቦች ሊጠብይ ይገባዋል ተባለ
አሁን በእውነተኛ የአማራ ልጆች ታላቅ ጥረትና ፅናት እየመጣ ያለውን አማራዊ አንድነትና የፋኖ ተቋም ዳግም ለማፍረስ የሚራሯሯጡ የውስጥ ቀበኞች እራሳቸውን ፍንትው አርገው እየገለጡ መተዋል። እነዚህ አረሞች አማራው በታሪኩ እና በእውነተኛው ጥንካሬ ልክ የምስራቅ አፍሪካ ብሎም የአለም ተፅዕኖ ፈጣሪ ሃያል እንዳይሆን ከመስራት አልፈው ለዘመናት በጉያው እንደ መዥገር ተለጥፈው የዘር እልቂት እንዲደርስበት በመረጃም በሴራም ጠላቶቹን ሲተባበሩ ኖረዋል አሁንም በዚህ ፀያፍ ምግባራቸው ቀጥለውበታል። ስለዚህ የአማራ ህዝብ ሳይከፋፈል ለህልውናው ሲባል ሰርጎገቦችን ባፋጣኝ ቆርጦ መጣል ይገባዋል። እነዚህ ፈትፋች ሰርጎ-ገብ የእናት ጡት ነካሾች አሁን አማራ አለመሆናቸውን የክፍፍል አጀንዳ እየመጡ በየማህበራዊ ገፆቻቸው እየነገሩን ይገኛሉ። እነዚህ መርዘኞች አማራነትን ለዘመናት ተጠይፈው በጎጥ በመደራጄት ጎጃሜነትን፣ጎንደሬነትን ሸዋዬነትን እና ወሎዬነትን ብቻ የሙጥኝ ያሉ በመምሰል መከፋፈል እየፈጠሩ ነው።
በመሆኑም ታጋዩ ፋኖም ሆነ ህዝቡ አንድ ሆኖ ሰርጎ ገቦችን ባለመስማት አንድነቱ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት።
ጳግሜ 1/2017/
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#ሟች ከመሞቱ በፊት‼
➾የያዝነው እውነተኛ እና ህዝባዊ ትግል ነው። በግብፅ በአረብ አገር በአውሮፓ እንዲሁም በኢትዮጵያ አማራ በመምሰል የተቀመጣችሁት የአብይ ዳቦና ፍርፋሪ ለቃቃሜ ሾተላዮች ለእናንተም ትምህርት ይሆና።
ዛሬ እስኪ ልብ የሚያሞቅ ኮሜታችሁን ልቀበል በዝግጅት ላይ ነኝ አላችሁ ወንድም እህት አማራዊያን
በዚህ ትግል እኛን የሚያዋርዱና እና ትግሉን የሚያቆሽሹ መጨረሻቸው ሞትና ውርደት ብቻ ነው።
ህዝብ ያሸንፋል።
ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#የቴሌግራም ቻናላችን ከግንባር ነች ይወዳጁት‼️
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በጎጃም ቀጠና የብልፅግና ሀይሎች እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ሰርጎ ገብ የብልፅግና ዘራፊዎችን እያፀዳ ነው።ብርጌዱ ጠላት አስርጎ ያስገባቸውን መረጃና ዘራፊዎች ረጅም ጊዜ በመውሰድ እያጣራ መያዝ ሲጀምር ሀብቴ አስፈራው የተባለ ሰርጎ ገብ የአረመኔው ስርዓት ረጅም እጅ በመሆን የፋኖን ቁመና በመሰለል እና ፋኖ እንዲጠላ በርካታ የብልፅግና ሰርጎ ገብ ሌቦችን በማደራጀትና በመምራት ከገጠር እስከ ከተማ ከፍተኛ ወንጀል በመፈጠፀም ህዝብን ሲበዘብዝ ከቆየ በኋላ በቡሬ ዳሞት ብርጌድ እና በጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ጊዮን ብርጌድ ናደው እሻለቃ ሲከበብ አጉት ከተማ ላይ መረጃ ላለመስጠት እራሱን አጥፍቷል።
ሁለቱ ግብረ አበሮቹ በቡሬ ዳሞት ብርጌድ ዘመነ ሻለቃ በቀን 28/12/2017ዓ.ም በቁጥጥ ስር የዋሉ ሲሆን ሌሎች የብልፅግና ሰርጎ ገብ ሌቦች ጀግናው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ከተማ ድረስ ሰርጎ በመግባት እንደ ሚያወጣቸው ብርጌዱ አረጋግጧል።በብልፅግናው ሰርጎ ገብ ሀብቴ አስፈራው የሚመራው ዘራፊ ቡድን ነሐሴ 21/2017ዓ.ም ቡሬ ከተማ ፈረስ ወጋ የሚባል ሰፈር በመግባት
92ሺ ብር በሀብቴ አስፈራው አጎት አካውንት የገባ
የጣት ወርቅ ቀለበት
የአንገት ብር እንጥልጥል
ከዘረፉ በኋላ እራሱን ያጠፋው የብልፅግና ዘራፊ ቡድን መሪ የተዘረፈችውን ሴት በመድፈር ወጠው ሄደዋል።በቀን 28/12/2017ዓ.ም ሲነቃበት መሳሪያ ሽጦ ለማምለጥ አጉት በሄደበት ሲከበብ እራሱን አጥፍቷል።
ይህ የአረመኔው ስርዓት አገልጋይ ሰርጎ ገብ ባንዳ መጀመሪያውኑም የብልፅግና ሚኒሻ የነበረ ሲሆን ከብልፅግና መሳሪያ ይዞ ወደፋኖ ሰርጎ የገባ ሲሆን በለቅሶ ላይ ጥር 21/5/2017ዓ.ም ሻኳ ላይ አንድ ፋኖ ተባረቀብይ በማለት የገደለ ሲሆን ታስሮ ከተፈታ በኋላ ለግዳጅ ሲላክ የራሱን እግር ተኩሶ አቁስሎ ድኗል። ግን ብርጌዱ ከሱ ጋር በግብረ አበር የሚሰሩትን ዘራፊ ቡድን አጣርቶ እስከ ሚደርስባቸው በከፍተኛ ክትትልና ትዕግሥት የቆየ ቢሆንም ካረጋገጠ በኋላ ለመያዝ ሲንቀሳቀስ በመንቃቱ እራሱን ለማፅፋት ተገዷል ሲል የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ ሁነኛው ተናግሯል።
(ጳጉሜ 01/2017ዓ.ም)
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
ፋኖ አህመድ መሐመድ (ሶሎሞን ተገኝ) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ የድሽቃ ጋንታ መሪ መልካም !
ብሔሬ ፦ አማራ ነው! ወደፊት ግን ዜግነቴ ይሆናል ነው።
ሀይማኖቴ ፦ ሙስሊም አማራ
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማራን በተመለከቱ ጉዳዬች ሀሳባችንን ስናጋራ፦
I am speaking as "an Amhara"
እንጂ
I am not speaking "for the Amhara"
ይሄንንም አስረዱን እንዳትሉ! የታች ሰፈር ሰዎች።
የማይነበብ ፊርማ አለበት!
ሙስሊም አማራዎች የአይሻ ደመላሽ የእኛም ወንድም በርታ በልልን እድሜና ጤና ይስጥህ።
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ደብረማርቆስ የቀበሌ 08 ፖሊስ ፅ/ቤት ላይ ጥቃት ተፈፀመ
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጣና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለሃይ ማኖት ብርጌድ ንሐሴ 30/2ዐ17 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሌሊት በመግባት አብማ ክ/ከተማ ቀበሌ O8 ፅ/ቤት ላይ ጥቃት ማድረስ ችሏል፡፡
በጥቃቱም የአረመኔው ሰራዊት አመራር የሚጠቀምበት የፖሊስ ጽ/ቤት እና የቀበሌ አስተዳዳሩ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ተብሏል፡፡
#ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ!
ጳጉሜ 01/2017 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+3
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ የጎጃም አገው ምድር ሶስተኛ ክ/ጦር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከክ/ጦሩ ሰባት (፯) ብርጌዶች ከተውጣጡ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱም የነበረውን አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን ለቀጣይ ስራዎችም ስምሪት በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ይህ ሁሉ ድካም ለኔ ነው የሚል የትግሉ ደጋፊ ነኝ ባይ ቡድንም ሆነ ግለሰብ፣ አክቲቪስትም ሆነ ፌስቡከር በፋኖዎች እና በአመራሮቻችን ላይ ስድብም ሆነ ዘለፋ አንፈቅድም።
ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነቆራ ፅሁፍ እየፃፉ እንዲህ በዱር በገደሉ የሚዋደቅን ፋኖ እና የፋኖ አመራሮች መዝለፍ ኢ-ሞራላዊ ወንጀል ነው።
ድል ለዐማራ ህዝብ..!
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ነሀሴ ፴ ቀን ፪ሽ፲ ፯ ዓመተምህረት።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የአንድነት ስምምነት ላይ በመድረሱ የተሰጠ የደስታ መግለጫ።
የአፋብኃ ነሀሴ ፳ ፰ ቀን ፪ሽ፲ ፯ ዓመተምህረት በጽሁፍ አንዲሁም አመራሮቹ ነሀሴ ፳ ፱ ቀን ፪ሽ፲ ፯ በድምጽ የሰጡትን የጋራ መግለጫዎች ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በታላቅ ደስታ በመቀበል ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ዝጝጁነቱን ያረጋግጣል።
በቋራ ቃል ኪዳን የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ያጋጠሙትን የውስጥ ልዩነቶች በትእግስት አና በጥበብ በመፍታት በአንድነት ለመጓዝ ስምምነት ላይ መድረሱ ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል አሸናፊነት ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በጽኑ ያምናል። አፋብኃ ዳግም አንድነታቸውን አድሰው የአማራ ህዝብን ህልውና በአሰተማማኝ እና በቀጣይነት ለማስጠበቅ የጋራ ቃልኪዳናቸውን ጽፈዋል።
በውጪ ለሚኖረው አማራ በአማራ ማህበራት ውስጥ በአባልነት በመሳተፍ፣ ማህበራቱም በአስቸኳይ ዓየንን በመቀላቀል የትግል ዋናኛ ድርሻዎች በሆኑት ፈጣን እና ቀጣይ የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የድምፅ ማሰማትና የውጭውን ማህበረሰብ እና መንግስታት ድጋፍ ለማግኘት በአፋብኃ መንፈስ እና አማራዊ ስሜት ተግተን እንድንስራ ወገናዊ ጥሪችን እያቀረብን፣ በተመሳሳይ አፋብኃን ያልተቀላቀሉ ፋኖዎችም አፋብኃን እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።
በዚህ አጋጣሚ ለቋራ ቃልኪዳን መታደስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እያቀረብን ከአፋብኃ መሪዎች በቀረበው ጥሪ መሰረት ዓየን የአማራ ተቋማትን ለማሰባሰብና ተቋማቱም ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የበኩላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ ለማስተባበር የምንችለውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን። ለአማራ ህዝባችን፣ ለፋኖ ሰራዊት፣ ለአማራ እና አጋር የህዝብ መገናኛዎች፣ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይም በውጭ ለሚኖረው አማራ በግልፅ ያቀረባችሁትን የትግል ጥሪዎች ተግባራዊነት ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በፍፀም የአማራ ብሄርተኝነት፣ በአላማና በመርህ ላይ ተመርኩዞ፣ ህብረቱን አጠናክሮ፣ አቅሙን አጎልብቶና ተግቶ እንደሚሰራ ዳግም ያረጋግጣል።
ድል ለአፋብኃ! ድል ለአማራ! ድል ለኢትዬጵያ!
ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን)
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#የብልጽግና_ሽንጉጎች_እየተራገፉ_ነው‼️
👉👉👉👉
ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ሰርጎ ገብ የብልፅግና ዘራፊዎችን ማፅዳት ጀምሯል። ባንዳ ያሰረጋቸውን መረጃና ዘራፊዎች ረጅም ጊዜ በመውሰድ እያጣራ መያዝ ሲጀምር ሀብቴ አስፈራው የተባለ ሰርጎ ገብ የአረመኔው ስርዓት ረጅም እጅ በመሆን የፋኖን ቁመና በመሰለል እና ፋኖ እንዲጠላ በርካታ የብልፅግና ሰርጎ ገብ ሌቦችን በማደራጀትና በመምራት ከገጠር እስከ ከተማ ከፍተኛ ወንጀል በመፈጠፀም ህዝብን ሲበዘብዝ ከቆየ በኋላ በቡሬ ዳሞት ብርጌድ እና በጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ጊዮን ብርጌድ ናደው እሻለቃ ሲከበብ አጉት ከተማ ላይ መረጃ ላለመስጠት እራሱን አጥፍቷል።
ሁለቱ ግብረ አበሮቹ በቡሬ ዳሞት ብርጌድ ዘመነ ሻለቃ በቀን 28/12/2017ዓ.ም በቁጥጥ ስር የዋሉ ሲሆን ሌሎች የብልፅግና ሰርጎ ገብ ሌቦች ጀግናው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ከተማ ድረስ ሰርጎ በመግባት እንደ ሚያወጣቸው ብርጌዱ አረጋግጧል።
በብልፅግናው ሰርጎ ገብ ሀብቴ አስፈራው የሚመራው ዘራፊ ቡድን ነሐሴ 21/2017ዓ.ም ቡሬ ከተማ ፈረስ ወጋ የሚባል ሰፈር በመግባት
👉92ሺ ብር በሀብቴ አስፈራው አጎት አካውንት የገባ
👉የጣት ወርቅ ቀለበት
👉የአንገት ብር እንጥልጥል
ከዘረፉ በኋላ እራሱን ያጠፋው የብልፅግና ዘራፊ ቡድን መሪ የተዘረፈችውን ሴት በመድፈር ወጠው ሄደዋል።
በቀን 28/12/2017ዓ.ም ሲነቃበት መሳሪያ ሽጦ ለማምለጥ አጉት በሄደበት ሲከበብ እራሱን አጥፍቷል።
ይህ የአረመኔው ስርዓት አገልጋይ ሰርጎ ገብ ባንዳ መጀመሪያውኑም የብልፅግና ሚኒሻ የነበረ ሲሆን ከብልፅግና መሳሪያ ይዞ ወደፋኖ ሰርጎ የገባ ሲሆን በለቅሶ ላይ ጥር 21/5/2017ዓ.ም ሻኳ ላይ አንድ ፋኖ ተባረቀብይ በማለት የገደለ ሲሆን ታስሮ ከተፈታ በኋላ ለግዳጅ ሲላክ የራሱን እግር ተኩሶ አቁስሎ ድኗል። ግን ብርጌዱ ከሱ ጋር በግብረ አበር የሚሰሩትን ዘራፊ ቡድን አጣርቶ እስከ ሚደርስባቸው በከፍተኛ ክትትልና ትዕግሥት የቆየ ቢሆንም ካረጋገጠ በኋላ ለመያዝ ሲንቀሳቀስ በመንቃቱ እራሱን ለማፅፋት ተገዷል ሲል የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ ሁነኛው ተናግሯል።
(ጳጉሜ 01/2017ዓ.ም)
© ዘመኑ አማረ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ/ኃላፊ
01/13/2017 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#ሲምፖዚየሙ_እንዳይቀሩ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ዛሬ ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።
በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል‼️
በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እንገናኝ‼️
01/13/2017 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ፋኖ በወለጋ ጽናት ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ከአርበኛ አደም ተፈራ የተሰጠ መግለጫ።
የዘመናዊ አኗኗር ዘይቤ ያስተማረው ታታሪውና ስራ ወዳዱ የአማራ ማህበረሰብ ወለጋ ምድር ላይ እንደ መጤና ወራሪ ታይቶ መንግስት መር ጭፍጨፋ ከታዎጀበትና መጨፍጨፍ፣መሳድና ንብረቱን መዘረፍ ከጀመረ ድፍን 7አመታትን አስቆጥሯል።ይህ እንዲጠፋ የተፈረደበት ማህበረሰባችን ባለፉት አመታት ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች እድል የቀናቸው በአሁኑ ስዓት አማራ ክልል የተለያዩ መጠለያ ጣብያዎች የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ እዬቀመሱ የስቃይ ኑሯቸውን እዬገፉ ሲገኙ ይችን እድል ያላገኙ ወገኖቻችን ስጋቸው የዱር አራዊት ቀለብ ሁኖ አጽማቸው በዬጫካው ወድቆ ይገኛል።
ወለጋ ምድር ላይ ከሞት የተረፍን ነገደ አማራውያን ከፈጣሪ በታች ከዝህ መንግስት መር ጭፍጨፋ ማንም ደርሶ ሊታደገን እንደማይችል ተረድተን እራሳችንን በማደራጀት መከላከል ከጀመርን አመታቶችን አስቆጥረናል።
ይሁን እንጅ እኛ ከወለጋ ምድር ከነዘር ማንዘራችን ተነቅለን አለመጥፋታችን ያንገበገባቸው ሀይሎች በዬግዜው እራሳቸው ባደራጇቸው ሀይሎች የኦሮሞ ንጹሃን ወገኖቻችንን በመጨፍጨፍ ጅራፍ እራሷን ገርፋ እራሷ ትጮሃለች እንደሚባለው ብሂል ወለጋ ምድር ሲያሻቸው የመንግስት ፋኖ ደስ ሲላቸው ጽንፈኛው ፋኖ ህዝባችን ጨፈጨፈ በሚል ህዝባችን ላይ የተቀናጀ ጭፍጨፋ ያውጁበታል።
እኛ ብሶት የወለደን የጭቁኑ የወለጋ አማራ ማህጸን ያፈራን የአማራ ፋኖ በወለጋ ህዝባችን ከሁለንተናዊ ጥፋት ለመታደግ የወጣን ከመላው ብሔር ብሔረሰብ ጋር እኩል ሁነን የመኖር መብታችን ተከብሮ እኛም የሌላውን አክብረን እንኑር እንጅ ያልነው ከማንም እንብለጥ አላልንምና መላው ኢትዮጵያውያን እንዲያውቁልን የምንፈልገው ይህ በዬግዜው ወለጋ ምድር ላይ የሚደረገውን የሁለቱንም ብሔሮች ጭፍጨፋ ገለልተኛ አካል ወደ አካባቢው በመግባት አጣርቶ እውነታውን ለህዝብ እንዲያሳውቅልን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድል የመጥፋት አደጋ ለተደቀነበት ህዝባችን‼
ጳግሜ 01/2017ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በወለጋ
ጽናት ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ
አርበኛ አደም ተፈራ
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#አማራነት ለእኛ ደስታና_ሀዘን በህይወታችን ውስጥ አይለዩንምና አባቴ በጣም የሚወደው ወንድሙ ሲሞት በጣም አዝኗል ደስም ብሎታል፦
#ያዘነው በጣም የሚወደው የቤተሰቡ ዋርካ የሆነው ወንድሙ
ሳያስበው ስለተለየው ነው።
ከቤተሰብ እህትም ሆነ ወንድም አልሞተም ነበር የመጀመሪያው ዋርካ ባልጠበቁት ቀን ሲያርፍ ያስደነግጣል!
እናም እህት ወንድሞች በጣም ይዋደዳሉ እስካሁን በልጅ ተፈትነዋል እንጂ አንድም ሰው አልጎደለም ነበር ሆኖም ሞት አይቀርምና ይሄው የመጀመሪያ ወንድሙን አጣ በዚህ እጂግ አዝኗል 😥
#ደስ_ያለው ደግሞ አሟሟቱ የጻድቅ አሟሟት ስለሆነ ነው በነገራችን ላይ በዐይኔ ያየሁትን ነው የምነግራችሁ እናም በስዓቱ ሁሉም ሰው ተደስቷል ቀንቷልም!
#እግዚአብሔር_ያሳያችሁ ማነው ትልቁን የዐቢይ ጾምን ሲጾምና ሲሰግድ እንዲሁም ሲያስቀድስ ሰንብቶ ህማማቱንም በጾም በስግደት ጨርሶ ምን ይሄ ብቻ አክፍሎ ልክ ትንሳኤ እሁድ ሆኖ እሮብ የሚምት ይህ ለእኔ ሞት አይደለም እረፍት እንጂ !እውነትም እንዲህ አይነቱ አሟሟት ያስደስታል,ያሰቀናል, ይናፍቃልም።
ነገሩ በአጭሩ ሲገለጥ እንዲህ ነበር የአባቴ ወንድም መኩሪያየ አጎቴ በጣም መንፈሳዊ ጻድቅ ሰው ከሚያሰኘው ነገር ቃለ እግዚአብሔርን፦
ወንጌል,ስንክሳር,ግድላትን, የቅዱሳንን ታሪክ በሙሉ በቃሉ ልቅም አድርጎ ይዞታል! አይይ መታደል እንዲህ አይነቱን ነገር ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም ❤❤❤
እኔ በሩቅ ሀገር ሆኜ አጎትሽኮ ቃለ እግዚአብሔር ተገልጦለት ልቅም አድርጎ ይዞታል ሲሉኝ ተደሰትኩ እናም ለመስማት ስለጓጓው እኔም ትንሽ የቅዱሳንን ታሪክ በስንክሳር ስለማነብብና ስለምሰማ ንገሩኝ ብየ ጠየኳቸው ነገሩኝ ደስ አለኝ በእንባ ጭምር ነበር የሰመዋቼው ወይ መታደል በእስተርጅና ሚስተሩን ገለጠላቸው እያልኩ በጣም ተደሰትኩ
እናም #ስንለያይ ያሉኝ ቃል አይረሳኝም ልጆቼ ተዋደዱ እኛንም እንድትቀብሩን አደራ ብለውኝ ተሰነባበትን😥---
ጸሎታቸው ምኑ ተብሎ ያልቃል ሲወጡ ሲገቡ ስሄዱና ሲተኙ ሁሉ ጸሎት ከመኩሪያዬ አንደበት አይለይም ነበር ለዚያም ነው አሟሟታቸው ያማርው! --- ብዙ ልጽፍ ነበር አንባቢ ይደክማል እረዘመ በነገራችን ላይ ስለ አባቴ ስለ ሳቅንበትና ሰለ ፎቶውም ጭምር እጽፍላችኋለሁ በተላይ በስስት ስለሚያኝ ውድ አባቴ ማወቅ ከፈለጋችሁ እጽፍላችኋለሁ የተለየ አባት ነውና ያለኝ።
ውድ አማራዊያን ቻናላችን ሁሌም መረጃ ከግንባር ሁነን የአማራን ህዝብ የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል እየሰራች ትገኛለች። እንግዲያስ እስዎ ምን ይጠብቃሉ ከታላቅ ክብር ጋር ይወዳጁን!!
ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር ያድርጉ!
👇 👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
