ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 406
Підписники
+1324 години
+277 днів
+1 21530 днів
Архів дописів
ሰራተኞች 'ሲኦል' ሆነብን ያሉት የግል ድርጅት በቅጥር ግቢው ውስጥ ድብደባን ጨምሮ እየፈፀማቸው ያሉት አነጋጋሪ ድርጊቶች ተጋለጡ
አንዳንድ የመንግስትም ይሁን የግል ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው በመመቸትም ይሁን ባለመስማማት ስማቸው አልፎ አልፎ ይነሳል።
ሱፐር ደብል ቲ ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር በሸገር ከተማ፣ አለም ገና ውስጥ ካሉ የግል ድርጅቶች አንዱ ሲሆን እንደ ቀለም እና የውሀ ማጠራቀሚያ በተለምዶ ሮቶ የሚባለው ያሉ ምርቶችን ለገበያ ያቀርባል።
ድርጅቱ በሚድያዎች ላይ የገዘፈ ጥሩ ስም አለው፣ ከሰራተኞቹ ጋር እንደ የብሔር ብሔረሰብ በዓል፣ የባንዲራ ቀን ወይም ሌሎች በዓላትን ባማረ መልኩ ሲያከብር ይታያል።
"የሰራተኛውን መብትና ጥቅም የማያሰከብር ድርጅት ሁሌም ከትችት አይወጣም። ስለ ሰራተኞቹ የሚያስብና ህግ እና መመሪያ ተከትሎ የሚሰራ ደግሞ ከራሱ አልፎ ለሀገርም ምሰሶ ይሆናል" የሚለውን መልዕክት ድርጅቱ ያስተላለፈው በቅርቡ 'የሰራተኞች ቀን' ብሎ ባከበረው በዓል ላይ ነበር።
ድርጅቱ ከዚህም አልፎ በሸገር ከተማ በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን 'ዋቶ የጤና ኬላ' የዛሬ ዓመት አስመርቆ ነበር። በቅርቡ ለመቄዶንያ ገንዘብ ሲሰባሰብም ሱፐር ደብል ቲ ጀነራል ትሬዲንግ የ500,000 ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።
ታድያ ጉዳዩ፤ አቶ ፀጋዬ ደበበ የሱፐር ደብል ቲ ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ባለቤት ናቸው፣ በርካቶች ግለሰቡን የአወዛጋቢው ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር እና ዩትዩብ ቻናል መስራች በመሆናቸውም ያስታውሷቸዋል።
አቶ ፀጋዬ የድርጅታቸው ስም በሚድያ የገነነ እንዲሆን፣ ነገር ግን የስራ ቦታው 'ሲኦል' እንዲመስል እንዳደረጉ መሠረት ሚድያ ያነጋገራቸው በርካታ ሰራተኞች ይናገራሉ።
"ባለቤቱ የፈለጉትን ሰው በፀጥታ አካላት ከማስወሰድ ጀምሮ ድብደባ እንዲፈፀም ማድረግ ይችላሉ። ፖሊሶች ሲጠሩ በደቂቃ መጥተው የተባሉትን አርገው ይሄዳሉ፣ እምቢ ያለ በሚሊሻዎች ታፍሶ ለወታደርነት ወደ ካምፕ በግዴታ ሊገባ ይችላል" የሚሉት አንድ ሰራተኛ ናቸው።
ሁሉም ሰራተኞች ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል።
ሱፐር ደብል ቲ ጀራል ትሬዲንግ አሁን ላይ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰራተኞች እንዳሉት የታወቀ ሲሆን በርካታ ሰራተኞች ስማቸው ሳይጠቀስ እንኳን ለሚድያ ለመናገር ሲቸገሩ ታዝበናል።
"ከስራ አንድ ደቂቃ ያረፈደ 700 ብር፣ ማስቲካ ያኘከ 1 ሺህ ብር ይቀጣል፣ ስራ መልቀቅ እፈልጋለሁ ያለ ሊደበደብ ወይ ሊታሰር ይችላል። ሁለት ቀን አንገብጋቢ ጉዳይ እንኳን ገጥሞህ ብትቀር ሙሉ በሙሉ ከስራህ ትባረራለህ" የሚሉት ሌላኛው ሰራተኛ የሚከተለውን ድብደባ እና እንግልት በመፍራት ማንም ተመልሶ መብቴ ይከበር እንደማይል ይናገራሉ።
ሰራተኛው አክለውም "መግቢያ ሰዓት ጠዋት 12:20 ሲሆን መውጫ ደግ ማታ ከ12:00 ሰዓት ነው። መቅረት፣ ማስፈቀድ የሚባል ነገር የለም" የሚሉት በርካታ የተቋሙ ሰራተኞች የድርጅቱ ባለቤት አቶ ፀጋዬ በተደጋጋሚ "እያንዳንድሽ ብሬን ቀደሽ አትጨርሺውም፣ ምንም አታመጡም፣ የፈለኩትን አደረጋለሁ" በሚለው ንግግራቸው እንደሚታወቁ ያነሳሉ።
ሚድያችን እንዳረጋገጠው በተለይ ልምድ ያላቸው ሰራተኞች ለህይወታቸው እስከሚሰጉ ድረስ ከድርጅቱ መውጣት እንደማይችሉ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ ይደርሳቸዋል።
"እወጣለሁ ያለ ልምድ ያለው ሰራተኛ ካለ ይታሰራል ወይም ይደበደባል። ሲታሰሩ ደግሞ ከአንድ ሚልዮን ብር ጀምሮ ቁጥር ይጠራና ብር ሰርቋል ወይም ሰርቃለች ይባላል። በውሸት መስክር ትባላለህ፣ 20 ሺህ ብር ይከፈልሀል፣ እምቢ ካልክ አንተም ትታሰራለህ" የሚሉት አሁን ድረስ ከፍተኛ ስጋት ላይ የሚገኙት ሰራተኞች ናቸው።
ምንጮቻችን እንደጠቆሙት በዚህ ምክንያት ስራ ለቀዉ ወደ ገጠር ከሄዱ በኋላ ከዛም ተይዘው የመጡ ይገኛሉ።
"ግለሰቡ ይኸን የሚሰራዉ ደግሞ ከፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር ነው። ደግሞ የሚገርመዉ ስንት ሰቃይ ተማሪዎች ጥሩ እየመሰላቸዉ እየገቡ ህይወታቸዉ የተበላሸ አሉ" በማለት የተናገረችው ሌላዋ ሰራተኛ ከአካል ድብደባው በላይ የአእምሮ ቁስል የሚሆን ስድብ በርካቶች ሲሰደቡ ይውላሉ በማለት ገልፃለች።
ዓለም ገና በሚገኘው ፋብሪካ ውስጥ ሰራተኞች ገብተው የሚደበዱቡበት ስፍራ እንዳለ እና ስራ ሲሰሩ ደክሟቸው ቆም ያሉ ጭምር ዱላ እንደሚከተላቸው ታውቋል፣ በዚህም ምክንያት በአንድ ቀን ውስጥ ሰው ሳይደበደብበት በማይውል ቀን እንደሌለ ሰራተኞች ጠቁመዋል።
"ምንም ሳታጠፋ ተላላኪዎች ይመደቡና አጥኑት ይባላል እያንዳንዱን ሰዉ። በወሬ ስንቱ ታሰረ፣ ስንቱ ተደበደበ! ደግሞ በጣም የሚያሳዝነዉ ዉጭ ላይ ሚዲያ ላይ እንደሱ ያለ ጥሩ ያለ አይመስልም" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰራተኞች ናቸው።
በግለሰቡ በተገነባው ሆስፒታል ውስጥ ደግሞ በእርዳታ መድሀኒት እና ዊልቼር እንደሚገባ የታወቀ ሲሆን መድሀኒቱ እና ዊልቼሩ ግን በውድ ተመልሶ ለተጠቃሚ እንደሚሸጥ ተሰምቷል።
"ማንም ሆስፒታል የሌለ መዳኒት እዚህ ሊገኝ ይችላል፣ የእርዳታዉንም በነፃ ያስገባሉ ግን በእርዳታ ስም ይቸበቸባል፣ ይህ ማለት ሀገሪቱ እየተበዘበዘች ነው" የሚሉት ደግሞ በሸገር ከተማ አስተዳደር የሚሰሩ አንድ አመራር ናቸው።
"እንደምንሰማው ብዙ ችግር በሰራተኞች ይነሳል፣ ለምሳሌ የመብት አለመከበር ጥያቄ እና የስራ ልምድ እንኳን ሲጠየቅ የመከልከል። ግለሰቡ ለብዙ ሰው የስራ እድል የከፈቱ ናቸው፣ ግን ደግሞ የደሀ ልጅ ሰቆቃ ይብቃ ማለት ይገባል" በማለት አመራሩ ተናግረዋል።
"አንዳንዴ ይኼ ነገር አገር ዉስጥ ነዉ አይደለም እንዴ? ብለህ ታስባለህ። ስራ አጥፍተህ ከሆነ ተቀጣ፣ ገንዘብ ነዉ። የሰዉ ልጅ ግን መጫወቻ ለምን ይሆናል? እስከ መቼ ስድብ፣ ዱላ፣ እስር እና ማስፈራርያ? ለምን?" በማለት አንድ ሰራተኛ ጥያቄያቸውን ሰንዝረዋል።
በሱፐር ደብል ቲ ጄነራል ትሬዲንግ በዓለም ገና ከተማ በ1999 ዓ.ም የሙከራ ምርቱን የጀመረ ድርጅት ነው።
በዚህ ዙርያ የባለቤቱን የአቶ ፀጋዬን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ሲል የዘገበዉ መሠረት ሚድያ ነው።
መረጃ!!!
በሌሊት ጠላት ወደ ደረቋ ፣ አጉትና አዲሰ አለም ለማፈን እንቅስቃሴ ስለሚያደርግ በአካባቢው የምትገኙ የወገን ሀይሎች ጥንቃቄ አድርጉ ።
ተማሪ ታምሬ አበረ በጡት ቆራጩ ሰራዊት ታግታ ተወሰደች !!
ተማሪ ታምሬ አበረ ትባላለች በምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳርምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ተወልዳ ያደገች ሲሆን የ9ኛ ክፍል ትምህርቷን ለመከታተል ወደ መርጡለ ማርያም ከተማ ትሄድና ትመዘገባለች፤ በመካከል የአረመኔው ሰራዊት አጋር የነበረው ሚሊሻ አባቷ አቶ አበረ የአገዛዙ ግፍ ሲበዛ ባለፈው ተግባሩ ተፀፅቶ ህዝቡን ከዚህ በላይ መበደል እንደሌለበት አምኖ ከባንዳነት ወጥቶ ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመልሷል። በዚህ የተበሳጨው ጡት ቆራጩ አረመኔ ሰራዊት የአቶ አበረ ልጅ ተማሪ ታምሬ አበረ ከቤቷ ዩኒፎርም ለመውሰድ ስትመጣ ጉናጉና ከተባለ ቦታ ላይ አግተው ይዘዋት ሄደዋል።
አገዛዙ ትምህርት ለማስጀመር ሞክረን ፋኖ ትምህርት ከለከለ ቢልም የፋኖ ስጋት ከነበሩት ተማሪዎችን ማገት፣ መድፈርና መግደል ውስጥ ተግባራዊ እያደረገው ነው።
ማሳሰቢያ፦ ተማሪ ታምሬ አበረን በአፋጣኝ የማይለቃት ከሆነ አባይ ሸለቆ ብርጌድ የአፀፋ እርምጃ ይወስዳል።
አማራ ያሸንፋል!!
የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ይበልጣል ጥሩነህ
የአረመኔዉ አገዛዝ ሰራዊት እየፈራሰ ይገኛል!!!
የብልጽግና መራሹ መንግስት አማራን የማጥፋት የሴራ ዘመቻ የተረዱ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየከዱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
በቀን 13/02/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴዎድሮስ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር አባይ መተከል ብርጌድን የተቀላቀሉ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ዝርዝር:-
1.ይልቃል ጓዱ= አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
2.ተመስገን ጓዱ=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
3.አገር ሰላም=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
4.አዝመራዉ ገኔ=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
5.እንደሻው አቤ=ሚሊሻ ከወርቅ ሜዳ የወጣ
6.ቢሻዉ አይኔለም= ሚሊሻ ከወርቅ ሜዳ የወጣ
7.ንጉሴ መልኩ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
8.ተሾመ ታመነ=ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
9.አከለ ሞገስ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
10.እንግዳዉ ዘሪሁን=አድማ በትን ወርቅ ሀገር ላይ የተማረከ
11.እምቢአለ አከለ=ሚሊሻ ከፓዊ መንንደር 24
12.ትርፌ ተባረክ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
13.ሙሉ ታዴ = ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
14.አስር አለቃ ትዕዛዙ= መከላከያ የ4ኛ ክ/ጦር ሰንጥቅ ልዩ ተወርዋሪ ሻለቃን የተቀላቀለ
15.አስር አለቃ ታደሰ -መከላከያ =የ4ኛ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ሰንጥቅ ሻለቃን የተቀላቀለ
16.አስር አለቃ አስማማዉእጅጉ= ከጃዊ በመዉጣት በላይ ዘለቀ ብርጌድን የተቀላቀለ
በሌላ ዜና በዛሬዉ እለት በ15/02/2018 ዓ.ም የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ ያጣዉ የአረመኔዉ የአገዛዙ መንግስት ጀኔራሎችን እና ኮለኔሎችን በመያዝ የክልል እና የዞን አመራርን ጨምሮ ከ14 በላይ ፓትሮል እና 3 ኦራል መኪና የጠላት ኃይል በመያዝ ከፓዊ ወደ ወርቅ ሜዳ ከተማ በመግባት ስብሰባ ለማካሄድ የሞከረ ቢሆንም ይህ መረጃ ቀድሞ የደረሳቸዉ የ4ኛ ክ/ጦር ነበልባሎቹ የአባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት ወደ ወርቅ ሜዳ ሰርገዉ በመግባት በአራቱም አቅጣጫ ጎሌ ካሜፕ፣ ሀይስኩል ት/ቤት ካምፕ፣ ጁኒየር ት/ቤት ካምፕ በከፈቱት መብረቃዊ ጥቃት ቦቅቧቃዉ የብልፅግና አመራር ስብሰባዉን ሳይጀምር መከረኛዉን እግረኛ ሰራዊት አጋፍጦት ፈጣሪ ሆይ አዉጣኝ በማለት ወደ መጣበት ፓዊ ከተማ ፈርጥጧል።
"አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"
ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ
ሰበር‼
ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ በትናንትናው ዕለት የአገዛዙ ጥምር ጦር ገጠራማ አማራ ወደሚኖርባቸው ቀበሌዎች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንና ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ወደ ጫንጮ ቀበሌ ፋኖ ትንኮሳ ከከፈተብን ሙሉ የደረሰ ሰብሉን ጨምሮ ቤቶችን እናቃጥላለን በሚል መፈክር ታጅቦ የገባው ሰራዊት ቤት ለቤት እዬዞሩ የአርሶ አደሩን ምጣዶች ሲሰባብሩና ሀብት ንብረቶችን ሲዘርፉ መዋላቸውን የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና በቀጣይ ይህ አይነት እጣ ፈንታ ከተደገሰላቸው ወረዳዎች መካከል ጊዳ አዬናና ሊሙ ገሊላ ወረዳዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ ወደ ዋጃ ቀበሌ ለመግባት በስሶት አቅጣጫ ሀይል መሰለፉን ከተማኝ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አማራ የሚኖርባቸው ቀበሌዎች ወደ ከተማ ወተው ወፍጮ እንዳያስፈጩና ገባያ እንዳይገባያዩ መደረጋቸውን ተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል በአሁኑ ስዓት ደግሞ እስከ ቤታቸው በመሄድ የማፈንቀልና የመጨፍጨፍ ዘመቻ መከፈቱን የዛሬው ውሎ ምስክር ነውና መላው ህዝባችን በተጠንቀቅ እንዲቆም እናሳስባለን።
ጥቅምት 15/2018ዓ.ም
+4
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት እያደራጀ ይገኛል።
በዚህም በአዲስ አደረጃጀት የ14ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት የቀሰተ ደመና ብርጌድ ፣ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ እና የንጉሰ ተክላይማኖት ብርጌድን በጋራ በአንድ ሆኖ ተመስርቷል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሬጅመንቶች የተደራጀ ሲሆን ለቀጣይ ለሚሰጣቸው ድርጅታዊ ስምሪትም ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሬጅመንት አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
ክፍለ ጦሩን መልሶ ለማደራጀት የተገኙ የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች
1 አርበኛ ምናልባት ይታየው የዲያሰፖራና ውጭ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ
2 አርበኛ ሰለሺ ከበደ የቴዎድሮሰ ዕዝ ም/አደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ
3 መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ የቴዎድሮሰ ዕዝ የሰው ሀይል ኃላፊ እና የ206 ኮር አመራሮች በተገኙበት የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
ድል ለአማራ ፋኖ!!
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
🔥በቀን 14/2018 ዓ.ም በነበረው ውጊያ የተማረኩ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም በዛሬው እለትም ተቆርጠው ቀርተው በተደረገ አሰሳ 3 የአድማ ብተና አባላት ተይዘዋል‼️
ሁሌም በተግባር መዋጋት ያልቻለው አብይ እና ሰራዊቱ ዛሬም አለኝ የሚለውን የመጨረሻ አማራጭ በደህናማርያም አካባቢ ልዩ ስሙ ሮቢት ቀበሌ መገንጠያ 5:45 ሰዓት ላይ #ድሮን የተጠቀመ ሲሆን አንድ ሲኖትራክ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ለእራሱ ሰራዊት እንኳን እንደማይሳሳ ጭካኔውን አሳይቷል።
ጥቅምት 15/2018 ዓ
©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
15/ዐ2/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና!!!
የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ አዴት ከተማ ላይ ሰርጎ በመግባት ጥ*ቃት ፈፀመ!
ጥቅምት 15,2018ዓ.ም አነጋግ 11:00 ስዓት ላይ በተለምዶ እንጨት ተራ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ጦ*ር አዛዥ በአርበኛ አቢዎት አስናቀው እቅድ ነዳፊነት አንድ ጋንታ የሰው ሃይል ይዞ በመግባት ከጠ*ላት ም*ሽግ ድረስ ተስ*ቦ በመግባት በተፈፀመው የቦንብና የጨበጣ ውጊያ ጥቃት 5 የስር*አቱ አገል*ጋይ ሚ*ሊሻ ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ እስከወዲያኛው ሲሸኙ፣
1.መዝገቡ ሁንልኝ የተባለ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ሚሊሻ ፅፈት ቤት ኃላፊ ከባ*ድ ቁ*ስለኛ በመሆን አዴት ሪፈራል ሆስፒታል ገብቷል።ከዚህም በተጨማሪ ዮኅንስ የተባለ ልዩ ኃይል ምልስ የነበረ የሚሊሻ ብሬን ተኳሽ ከባድ ቁስለኛ ሁኗል።
2. በተፈፀመው የቦ*ንብ ጥቃ*ት ሶስት ባጃጅ እና አንድ ፓትሮል ሚሊሻና መከላከያ ቁስ*ለኛ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ አዴት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፈራል ሆስፒታል ገብቷል::
➯በመጨረሻም ብርጌዱ ማስተላለፍ የሚፈልገው ጥብቅ መልዕክት:- የአገዛዙን ዙፋን ለማስጠበቅ ሲባል ንፁሃን ወገኑን እየገደለ ያለ ሚሊሻ፣አድማ ብተና፣ፓሊስ፣ካቢኔና የመከላከያ ኃይል የብል*ፅግና የወንበ*ዴ ስርአት ያበቃለ*ትና ጀን*በሩ የጠለ*ቀች መሆኑን በመረዳት ለፋኖ ተቋም በሰላም እጃቸ*ውን በመስጠት የበደ*ሉትን ህዝብ እንዲክሱና ሰላማዊ ህይዎታቸውን ከማህበረሰቡ ጋር በመቀላቀል እንዲመሩ ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል። ነገር ግን የብርጌዱን ሰላማዊ ጥሪ ወደ ጎን በማለት የአገ*ዛዙን ስር*አት ደግፎ ተል*ኮ በሚያስ*ፈፅም ማንኛውንም አካል ላይ የማያ*ዳግም እርም*ጃ የሚወ*ስድ መሆኑን ጥ*ብ*ቅ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
መውጫ:- የሚ*ከዳ ማንኛውም አካል ላይ ፋኖ እርምጃ እየወሰደ ነው። ይሰቅላችኋል፣ይቆርጣችኋል የሚል ማደናገሪያ ኃሳብ ሰራዊቱ በህዝቡ ላይ እሚፈፀመው ግ*ፍ ከንክኖት እንዳይወጣ የተጠቀሙት የማደና*ገሪያ ቃል ስለሆነ ብትመጡ በፍቅር ተቀብለን በእንክብካቤ የምንይዛችሁ መሆኑን በመረዳት ወገናችሁን ተቀላቀሉ።
የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት።
ጥቅምት 15,2018ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
የአገዛዙ ጥምር ሀይል እና አሸርጋጁ የብልፅግና አጀንዳ በቀላሉ ከማቋረጥ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ስብሰባውን መበተን ተችሏል።
በዛሬው እለት በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሽመለጋራ የዞንና የወረዳ ሆድ አደር የብልፅግና አሽከሮች ከአገዛዙ ጥምር ሀይል ጋር እንደተለመደው ስለ አማራ ሁሉን አቀፍ የጀኖሳይድ ፀያፍ ተግባራቸውን ለመፈፀምና የጥፋት አጀንዳ ይዘው ለመዶለት ስብሰባ ለማድረግ እየተዘጋጁና እየተሰባሰቡ ባለበት ስአት ነበልባሎቹ የበረሀ ፈርጦች መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት አዳነ እየተመራ እንዲሁም በአናብስቶች ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ ማስረሻ መሪነትና መረጃን ቀድሞ በማፈንፈን ሁለቱ ብርጌዶች ጠላት ባላሰበበት ሁኔታ ከቀኑ 6:00 ስዓት ወደ ቀጠናው ተስፈንጥሮ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት መፈፀም ተችሏል።ውጊያውን እስከ 9:00ስዓት በማስቀጠል በጥምር ሀይሉ ላይ ከፍተኛ ድል ማስመዝገብም ተችሏል።
በዚህ ልዩ መብረቃዊ ጥቃት ስብሰባውን ከመበተን ባሻገር የአገዛዙ ጥምር ሀይል ሙት 10፣ ቁስለኛ ከ13በላይ ሲሆን የብልፅግናው አሸርጋጅ ምስለኔዎች በየ ጓዳው ጎድጓዳው እግሬ አውጭኝ በማለት በየቤቱም ቀሚስ በመልበስ እና በመመሳሰል በየ ስርቻው በመግባት እራሳቸውን አትርፈዋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥቅምት 15/2018
+3
የጡት ቆራጩ ሰራዊት በብርሃን ፍጥነት እየፈረሰ ነዉ‼️
ከአዲስ ቅዳም ካንፕ በመዉጣት 7 የአገዛዙ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ ከድርጊታቸዉ በመጸጸት ወደ ቆንጆዎቹ ተቀላቅለዋል ቆንጆዎቹ በፍቅር ተቀብለዋቸዋል።
1, ሃብቴ አይናለም
2, ሃብታሙ አሳየ
3, ጌታቸው ቀረብህ
4, ይሁን አያና
5, ታደለ ሰውነት
6,አስማረ ለገሰ
7,ሰውነት አለማየሁ የተባሉ ሚሊሻዎች ወደ አስራ ዓለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ተቀላቅለዋል።
ይቀጥላል ገና.....
ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
ወንድሙን ሲያገኝ ደስ የማይለው ማን አለ?
አቤት ያንተስ ደሞ ከፋ! ለማንኛውም እንኳን ደስ አለህ ዝሆኔ 😂😂😂😂 እስኪ ይህችን ዝሆኔ ወርፍ አድረጓት
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ መምሪያ ከድሮን ጥቃት ራስን የመከላከል አስገዳጅ ፕሮቶኮልና ቅድመ ጥንቃቄን በተመለከተ አስቸኳይ መግለጫ ሰጠ።
የጠላት እግረኛ ሃይል ወይም ምንም ዓይነት ግዳጅ መወጣት ያልቻለዉ የዐቢይ አገዛዝ የጭካኔ በትሩን ከፍተኛ በሆነ ድሮን ጥቃት ጀምሯል፡፡ የድሮን አሰሳና ጥቃት ተጠናክሮ ከመቀጠሉ ጋር በተያያዘ በርካታ ንጹሃንና ሰራዊታችን ለኢላማ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እነዚህ ቅድመ ጥንቃቄዎች ቀድመዉ ሊወሰዱ ስለሚገባ በአስገዳጅ ሁኔታ ይተግበሩ ሲል የዕዙ ወታደራዊ መምሪያ ማሳሰቡን ብላክ ላዬን ሚዲያ ተመልክቷል።
የፋኖ ሰራዊታችን በብዛት ሆኖ ክፍት መኪኖች ላይ ማለትም እንደ ሲኖትራክ፣ ኦራል፣ አይሱዙ ወዘተ ተጭኖ መንቀሳቀስ የለበትም፡፡ አስገዳጅ በሆነ የቡድን እንቀስቃሴ ወቅት የተቆራረጠና ዝግዛግ ዓይነት ቅርፅ ያለው የጉዞ መስመር ማድረግ የድሮኑን ዒላማ ማነፍነፍና መፈለግ እንዲሁም የመመልከት አቅጣጫ ያስተዋል።
የድሮን ድምዕ ከተሰማ ወይም ምልክት ከታየ ራስን ጥላ ወዳለው በርከት ያለ ዛፍ ወይም ዋሻ መጠለል አለብን፡፡ ጥላ ከተጠለለ ካሜራው በደንብ ለመመልከትና ዒላማ ለመለየት ይቸገራል። ለመጠለል የገባንበት ዛፍ ወይም ጫካ ካለ ዉስጥ ለዉስጥ ርቀትን መጓዝ አለብን፡፡ የወገንና የተማረኩ ተሽከርካሪዎችን ቅጠል፣ ሃረግ ወይም ጨርቅ መሸፈን በቅኝት ወቅት ዒላማ እንዳይሆኑ ያደርጋል፡፡ የቤትና የመኪና የሚያንፀባርቁ መስታዉቶችን ጭቃ በመቀባት ጨረር የሚያርፍባቸውን ነገሮች ሁሉ ማደብዘዝ ይገባል ነው ያለው ዕዙ፡፡
ዕዙ በተጨማሪም ስለ ሞባይል አጠቃቀም አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን፤ ሞባይል ስልክ የሚጠቀሙ የተፈቀደላቸው የፋኖ አባላትና አመራሮች ሎኬሽን ዝግ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ የያዙት ስልክ ስማርት ከሆነ በድሮን እንቅስቃሴ ወቅት በመጀመሪያ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባትና የበረራ ምልክቱን በመጫን Airplane Mode ካደረጉ በኋላ የድሮኑ እንቅስቃሴ ዝም እስኪል ድረስ የስልኩን ባትሪን በማጥፋት፤ ስልኩ ራቅ ብሎ መቀመጥ አለበት፡፡ የትኛዉም የፋኖ አባል ስልኩ ላይ ቴሌግራምና ቴሌብር የተባሉ የመተግበሪያ አፕልኬሽኖች መኖር የለባቸዉም ብሏል፡፡
አንድ የፋኖ ሠራዊት አሃድ በትዕዛዝ ከሆነ ቦታ ሲንቀሳቀስ እስከ ሚደርስበት ቦታ ድረስ የሞባይል ስልክ ዝግ አድርጎ መንቀሳቀስ ግዴታ አለበት፡፡ በጉዞ ወቅት ለሚኖር የመረጃ ትስስር አጭር ሞገድ ራድዮኖችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የጉዞ የእንቅስቃሴና የስብሰባ ቦታ ተለዋዋጭና እጅግ ምስጢራዊ መሆን አለባቸው:: ስብሰባ ሊያደርጉበት የፈለጉት ቦታ አስቀድሞ የታወቀ ከሆነ እቅድ እንዲቀየር እናሳስባለን፡፡
የስብሰባና ሥልጠና ቦታዎችን በግልፅ ሜዳ ላይ አለማድረግ ግድ ሲሆን ከጧቱ 5:00 - 9:00 ሰዓት የጠላት ሃይል ከሳተላይት ላይ ምስል ለመዉሰድ ምቹ የሚሆንበት ጊዜ ስለሆነ የኃይል ስብስብና ክምችቶችን ሙሉ ለሙሉ በእነዚህ ሰዓት ዉስጥ አስወግዱ፡፡
የዕዙ ወታደራዊ መምሪያ አክሎም፤ ድሮን የፀሃይ ጨረር አቅጣጫ ባለበት መነፅሩ በትክክል መመልከት ስለማይችል የፋኖ ሰራዊት ቦታ ለመያዝ ሲንቀሳቀስ የፀሃይ ጨረረ መስመርን ከፊት ለፊት ማድረግ ይገባል፡፡ የቅኝት ድሮን በአካባቢው ከታየ ፈጥኖ ቦታ መቀየር፤ መሳሪያ ይዞ በቡድን አለመንቀሳቀስ፤ ቤት ዉስጥ ለምግብ ወይንም በአዳራሽ ዉስጥ ለስበሰባ አለመገኘትን በአስገዳጅ ይተግብሩ ብሏል፡፡
ብዛት ያለዉ የፋኖ ሃይል እንቅስቃሴ ማድረግ ከተፈለገ ከቀን ይልቅ በሌሊት ማንቀሳቀስ ተግባራዊ መደረግ አለበት:: በሌሊት የጉዞ ወቅትም ሆነ የካምፕ ቆይታ ጠላት የሳተላይት ምስል እንዳይወስድ የመስመር ሰልፍ ባትሪዎችን ወይንም ብዛት ያለዉ የካምፕ መብራት አለመጠቀም፡፡ የጠላት አብዛኞቹ ድሮኖች በሌሊት የማይሰሩ ሲሆን እጅግ በጣም ጥቂቶቹ በሌሊት የሚሰሩት ደግሞ የመሳሪያና ሰራዊት ክምችት አለ ተብሎ የተጨበጠ መረጃና አቅጣጫ ካገኙ ብቻ ለተጠና ኢላማ ይጠቀሙታል፡፡ በመሆኑም የወገን ሀይል በክምችት ዉስጥ ሁኖ የትኛዉም ካምፕ ዉስጥ እንዳያድር፣ ከዚህ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ሁሉም ሰራዊት በምሽግ ዉስጥ ሌሊቱንም ሆነ ቀን ራሱን በቻለ የተጠናከረ የድሮን ዋርድያ ጥበቃ እንዲያሳልፍ እናሳስባለን፡፡ ከጥንቃቄ ጉድለት የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን እንቀንስ ብሏል ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ደለለ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ም/ሰብሳቢና ጦር አዛዥ።
በዘመቻ አደም አሊ(አባናደዉ) ዘመቻ የተማረኩ የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላት በፍቃዳቸዉ ፋኖን እንደሚቀላቀሉ ተናገሩ።
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ከ መስከረም 14/2018 እስከ መስከረም 30/2018
ዓ.ም በፈጀዉ ዘመቻ አድም አሊ(አባ ናደዉ) አመርቂ ድል ማስመዝገቡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ዘመቻ ላይ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት ቡዙ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ይታወቃል።
በዚህም ዘመቻ ላይ ከ679 ምርኮኞች መካከል 100ዎቹ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሲሆኑ እነዚህ ምርኮኞችም እስካሁን በማወቅም ባለማወቅም የአማራን ህዝብ በድለናል ከአሁን ስዓት ጀምሮ ህዝባችንን በበደልነዉ ልክ ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር ተቀላቅለን እንክሰዋለን ሲሉ ተናግረዋል።
ምርኮኞቹ አክለዉም ይህ ፋሽዝም ስርዓት ምላሱ ብቻ እንደቀረ ገልፅዉ አሁንም በዚህ አገዛዝ ስር ያላቹህ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዝ ጥምር ጦር የሚላቹህ የሰራዊት አባላት እና አመራሮች አሁንም ሳይረፍድባቹህ ያላቹህበት ስርዓት አገር አፍራሽ መሆኑን አዉቃቹህ ወደ እዉነተኛ ትግል ወደሆነዉ የአማራ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዉ እኛ ተማርከን ህይወታችን ሰለተረፈ እድለኞች ነን ብለዋል።
በዚህም ለይ የ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ፅ/ቤት ኃላፊ አርበኛ ደስታዉ መለሰን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የዚሁ ዕዝ ክንፍ የሆነዉ ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዉ ምርኮኞችን በሚፈልጉት ቀጠና ባሉት ኮሮች እና ክ/ጦሮች ሂደዉ እንዲታገሉ የድልድል ስራ ሰርተዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
አፋብሃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ክፍል ኋላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን!
ጥቅምት 15 /2018 ዓ.ም
