uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
2 943
Підписники
-1024 години
+77 днів
+37930 днів
Архів дописів
ጀብደኛው 34ኛ ክ/ጦር ድል ሲቀዳጅ አገዛዙ በበኩሉ በእርሻ ስራ ላይ ያለ ወጣትን ከእነ በሬዎቹ በመድፍ ገደለ! ‎ግምቦት 14/2018 ‎ ‎ለአገዛዙ የእራስ ምታት የሆነው አይበገሬውና ጀብደኛው የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በዛሬው ዕለት በአምበር ከተማ እንድሁም በሉማሜ ከተማ አቅራቢያ የአገዛዙን ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ አድርጎት ውሏል። ‎በዚህ ውጊያ ጀግንነትን ከአባታቸው ተድላ ጓሉ ሻለቃ የወረሱት የ34ኛ ክ/ጦር አካል የሆነው ተድላ ጓሉ ሻለቃ ከጥዋቱ 4:00-7:00 ሰዓት በአምበር ከተማ በመግባት በአገዛዙ ወታደሮች ላይ በወሰዱት እርምጃ ‎1 የነው የተባለ   ፖራ ኮማንዶ ‎2 ይጨክን ጫኔ   ሚኒሻ ‎3 አየለ    ሚሊሻ     እነዚህን የጠላት ሀይል ጨምሮ 12 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ 7ቱ ደግሞ ቁስለኛ መሆናቸው ተገልጿል ።በሌላ በኩል በሉማሜ ከተማ ዳርቻ ጎል ላይ ነበልባሎቹ የመብረቁ ሻለቃ አባላት ባደረጉት ዉጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል ‎ጀብደኛው 34ኛ ክ/ጦር ፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው የጨፍጫፊው አብይ አህመድ ሰራዊት በመድፍ ንፁሀንን እና እንሰሳትን ሲጨፈጭፍ የዋለ ሲሆን ህፃን  ጌትነት ንጉሴ  የተባለ የ14 ዓመት  በአነደድ ወረዳ አድስጌ ጎጥ ነዋሪ እንድሁም በጥቃቱ የቆሰለ ሲሆን  ወጣት መለሰ የኔሰው የ19 ዓመት ወጣት የጎራ ቀበሌ ዙጨ ጎጥ ነዋሪ የነበረ  በእርሻ ላይ እያለ ከነ በሬዎቹ የተገደለ ሲሆን ቀተጨማሪም 4በሬ እንድሁም 1ላም  በመድፍ ጥቃቱ ተገድለዋል። ‎ ‎አዲስ ትውልድ !አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ ‎የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

ለወረራ ወደ ሳሲት ቀጠና ያቀናው የአገዛዙ ዘራፊ ኃይል በጀግናው ሰራዊታችን ልዩ ወታደራዊ ጥበብ ተቆርጦ በሰላድንጋይ ከተማና አካባቢው ማርሽ ቀያሪ ውጊያ እስከ ምሽት ድረስ እየተደረገ መሆኑን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አስታወቀ። አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ የብልፅግናው ወራሪ ሀይል ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ፣ ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፣ ከደብ ረሲና ከተማና አጎራባች ወረዳ በርካታ ሰራዊት በማሰለፍ አለኝ የሚለውን የቡድን መሳሪያ በመጠቀም መነሸውን ከሞጃና ወደራ ወረዳ ሰላድንጋይ ከተማ በማድረግ ወደ ሳሲት ከተማና አካባቢው ለዘረፈ ቢንቀሳቀስም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ይህ ዜና እስከተቀናበረበት ምሽት 12:00 ድረስ እየተካሔደ ባለው የተቀናጀ ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃዶች የኮሩ ቃኝ፣ከንጉስ ሳህለስላሴ ክፍለጦር፣ ከራንቦ ክፍለጦር እንዲሁም ከ7ለ70 ክፍለጦር የተወጣጡ ውስን ሻለቆች በልዩ ወታደራዊ ጥበብ እጅግ አስደማሚ ድል እየተቀዳጁ ይገኛሉ። ጠላት ያሰበው ሳይሆን የፈራው ደርሶበት በጀግናው ሰራዊታችን ቆረጣ ውስጥ ገብቶ ከፍተኛ ቁጥር የለው የከገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖበት የሳሲት ከተማን ለመያዝ ባደረገው ከንቱ የቅዠት ሙከራ በጦር ጠበብቶቹ የፋኖ የቁርጥ ቀን ልጆች ውጊያው አቅጣጫውን ቀይሮ በሰላድንጋይና አካባቢው አገዛዙን ያስጨነቀ፣ ተጨማሪ ሰራዊትና የአየር ሀይል ድጋፍ ጭምር የጠየቀበት በአይነቱ ለየት ያለ ለተከታታይ ስምንት በላይ የወሰደ የቅንጅት ውጊያ እየተደረገ ሲሆን አገዛዙ በጣለው ሞርተር የአንድ አርሶ አደር መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ሲቃጠል፣ በአካባቢው ተጨማሪ የቤት እንሰሳት መገደላቸውን ኮሩ ገልጿል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ምሽት 12:00 ድረስ በጀግናው ሰራዊታችን የውጊያ የበላይነት እየተካኼደ ያለው ውጤታማ ድሎች የተመዘገቡበት የቅንጅት ውጊያ እንደቀጠለ ሲሆን ሙሉ የአውደ ውጊያ ዝርዝር መረጃዎችን ዕዙ በቀጣይ ይዞ የሚመለስ መሆኑን ከወዲሁ እየጠቆምን አሁንም ድል ለህዘብ ልጅ ለሆነው ለጀግናው ሰራዊታችን እንመኛለን። በሌላ መረጃ የጦር ወንጀለኞች ስብስብ በሆኑት በብልፅግናው አጋፋሪ የከተማዋ ከንቲባ የታጋይ ፋኖ ህፃን ልጅ መታገቱን የህፃኑ ወላጅ ቤተሰቦች ተናገሩ። በሞረት እና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ከተማ የሚገኘው የኦህዲድ ኦሮሙማ መንግስት ወንበር አስጠባቂ የአማራው የብልፅግና ቅጥረኛ በኦሮሚያ ክልል ሲፈፅም የኖረውን ግፍ እና አሰቃቂ ድርጊት ትላንት ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ላይ ህፃን ባህራን ብዙአየሁን እና እናቱን በማገት በእነዋሪ 01ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ህፃኑን እና እናቱን ለየብቻ በማሰር እያሰቃዩ ሲሆን፣ ህፃኑ በጣም ከመጮሁ የተነሳ እንጥሉ ወርዶ ለህክምና መከልከሉን የህፃኑ ቤተሰቦች ገልፀዋል። የጦር ወንጀለኛው የአገዛዙ ካድሬ ስብስቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየፈፀሙት ያለው አለም አቀፍ የጦር ወንጀል እየጨመረ ሲሆን የህፃናት ህግ እና የአለም ህፃናት መብት አስጠባቂ ተቋም ለህፃኑ በህይወት እንዲደርሱለት ስንል እናሳስባለን። አገዛዙ በታጋይ ፋኖ ኢንጂነር ብዙአየሁ ደጀኔ ላይ የፈፀመው ግፍ በዚሕ ሳያበቃ የአገዛዙ ቅጥረኞች በእንዋሪ ከተማ ከንቲባ በንዳው አቶ አጥላባቸው አጣለ ትዕዛዝ ሰጭነት ወንድሞቹን በዚህ ሰአት ለማገት በከበባ ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ የተበዳይ ቤተሰቦች በከፍተኛ ሀዘን ተናግረዋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 14/2018ዓ.ም

ሰበር ዜና ከአብይ አህመድ ካምፕ አንድ ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ ደርቦ ይዞ በመውጣት ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅሏል ። ➛ በዛሬው ዕለት በቀን 14/09/2018 ዓ.ም እያዩ ወንድሙ የተባለ
+2
ሰበር ዜና ከአብይ አህመድ ካምፕ አንድ ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ ደርቦ ይዞ በመውጣት ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅሏል ። ➛ በዛሬው ዕለት በቀን 14/09/2018 ዓ.ም እያዩ ወንድሙ የተባለ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት አባል ከ304ኛ ኮር 113ኛ ክፍለ ጦር ከ3ኛ ሬጅመንት ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጨንታ ካንፕ በመውጣት አንድ ስናይፐርና አንድ ጥቁር ክላሹን ደርቦ 22ኛ ክፍለ ጦር ባህርዳር ሻለቃን ተቀላቅሏል። ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!

የቢዛሞ ቀጠና አበጀ ጥበቡ ነበልባል ክፍለ ጦር አዲስ የቁርጥ ቀን ልጆችን በታላቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ። ​በወለጋ እና ቢዛሞ ቀጠናዎች በአማራው ማኅበረሰብ ላይ ለዘመናት ሲፈጸም የቆየውን ማንነትህን ተኮር ግፍና የህልውና ስጋት ለመቀልበስ ያለመው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የጦር ስልጠና በስኬት ተጠናቋል። የአንሻ ሰይድ እዝ አባል የሆነው አበጀ ጥበቡ ነበልባል ክፍለ ጦር፣ በስልጠናው ከፍተኛ ወታደራዊና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጅት ያደረጉ አዲስ የፋኖ አባላትን ዛሬ በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። ለረጅም ዓመታት ለስደት፣ ለግድያና ለከፋ ሰቆቃ ለተዳረገው የቢዛሞ ቀጠና አማራ ህዝብ፣ እነዚህ አዳዲስ የፋኖ አባላት የሕዝብ ጋሻ በመሆን ሕይወታቸውንና ክብራቸውን በክንዳቸው ለማስጠበቅ የተዘጋጁ መሆናቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ በስፋት ተብራርቷል። ​አዲሶቹ ምልምል አባላት በስልጠና ቆይታቸው ዘመናዊ የውጊያ ስልቶችን፣ የጦር መሳሪያ አጠቃቀምና አካላዊ ጥንካሬን ብቻ ሳይሆን፣ ጥልቅ የሆነ የዓላማ ጽናትና የሕዝብን መከራ የመታደግ መንፈሳዊ ቁመናን ታጥቀው መውጣታቸውን የክፍለ ጦሩ መረጃ ያመለክታል። "ራስን መከላከል ወንጀል ሳይሆን የህልውና ግዴታ ነው" በሚል መርህ የተመረቁት እነዚህ ወጣቶች፣ በወለጋና ቢዛሞ አካባቢ አማራ መሆን የሞትና የሰቆቃ ሰበብ የሚሆንበትን ዘመን ለማብቃት ቃል ገብተዋል። ​በምረቃው ላይ የተገኙት የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቢዛሞ ቀጠና አባላትና የአንሻ ሰይድ እዝ አዛዦች ባስተላለፉት መልዕክት፣ "አማራው ዳግም አንገቱን የሚደፋበት ዘመን አብቅቷል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። አዳዲሶቹ የፋኖ አባላትም ወገናቸውን ከጅምላ ፍጅት ለመታደግ አጥንታቸውን ለመከስከስና ደማቸውን ለማፍሰስ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርዒቶችን በማሳየት በቃለ-መሃላ ተልዕኳቸውን ተቀብለዋል። የቢዛሞ ቀጠና አንሻ ሰይድ እዝ የደህንነት ሁኔታን ከግምት በማስገባት የተመራቂዎችን ምስል ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን የገለጸ ሲሆን፣ ታሪካዊው የምረቃ ስነ-ስርዓት በታላቅ ድምቀት መጠናቀቁን ተረጋግጧል ።

የብልፅግና አገዛዝ የምርጫ ድራማ እየተራቆተ ነው፦ የአማራ ክልል ምርጫ ዕጩ የነበሩት ቄስ ንብረት አያሌው አገዛዙን በመክዳት ፋኖን ተቀላቀሉ ​የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎን በምርጫ ማጭበርሪያ ለመሸፈን የሚሞክረው የብልፅግና አገዛዝ፣ በውስጡ ባቀፋቸው ግለሰቦች ጭምር እየተዋረደ ይገኛል። በአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ስር በሚንቀሳቀሰው 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር፣ የቡግና ወረዳን በመወከል ለአገዛዙ "የጨረባ ምርጫ" የክልል ምክር ቤት ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት ቄስ ንብረት አያሌው፣ የአገዛዙን ፀረ-አማራ ገመና በማጋለጥ በይፋ ፋኖን ተቀላቅለዋል። ​ቄስ ንብረት አያሌው ፋኖን በተቀላቀሉበት ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአብይ አህመድ አስተዳደር አማራን ለማጥፋት የተማማለ ቡድን መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ የጨለማ ወቅት በምርጫ መሳተፍ ከአንድ አማራ የማይጠበቅ የታሪክ ክህደትና የደም መስዋዕትነትን መካድ መሆኑን ተናግረዋል። "በዚህ የጨረባ ምርጫ መሳተፍ ማለት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የአማራን ሕዝብ ጭፍጨፋና የታሪካዊት ኢትዮጵያን ውድቀት በይፋ መፍቀድ ነው" ሲሉ የተናገሩት የቀድሞው ዕጩ፣ አሁንም በምርጫ ሂደት ውስጥ ያሉ ሌሎች ግለሰቦች ታሪካዊ ክህደታቸውን አቁመው በአስቸኳይ ወደ ሕዝባዊ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። ​የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ የጠላቶችን ፀረ-አማራ ትርክት በማፍረስ በድል እየተጠናቀቀ መሆኑን ያስታወሱት ቄስ ንብረት፣ የብልፅግና አገዛዝ የጥፋት አዋጅ በተባበረ ክንድ እንደሚመከት ገልጸዋል። የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በበኩሉ፣ እንደ ቄስ ንብረት ያሉ ታማኝ የሕዝብ ልጆች ከምርጫ ድራማው ራሳቸውን ማግለላቸው የአገዛዙን የመጨረሻ ፍጻሜ የሚያሳይ ምልክት መሆኑን አስታውቋል። አርበኞቹ በምርጫ ስም የሚደረገውን የጥፋት ሴራ በመመከት ላይ እንደሚገኙ የገለጸው ዕዙ፣ ሌሎች አሁንም በአገዛዙ ጎን የቆሙ ወገኖች "ኑ አማራ ሁኑ" በማለት ጥሪውን አስተላልፏል።

ቄስ ንብረት አያሌው ባህሩ በቡግና ምርጫ ክልል የብልፅግና የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ ተብሎ ሲተዋወቅ የነበረ ግለሰብ ነው። በዛሬው ዕለት የብልፅግናን የምርጫ ቀልድ አላጅብም በሚል የምኒልክ ዕዝ 3
+1
ቄስ ንብረት አያሌው ባህሩ በቡግና ምርጫ ክልል የብልፅግና የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ ተብሎ ሲተዋወቅ የነበረ ግለሰብ ነው። በዛሬው ዕለት የብልፅግናን የምርጫ ቀልድ አላጅብም በሚል የምኒልክ ዕዝ 303ኛ ላስታ አሳምነው ኮርን ተቀላቅሏል።

የአገዛዙ ብልፅግና የሐሰት ምርጫን በተመለከተ ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የተሰጠ ማስጠንቀቂያ!! 64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 14/2018 ዓ.ም የአብይ አህመድ አገዛዝ የሀገራችን እድገትን የማይወዱ ወደ ሆላ ተመልሰን ስናይ የሀገራችን ጠላት የሆኑ ሀገራት አንሶላ በማንጠፍ፣ በመለመን በድህነት አራንቋ ውስጥ የሚገኘው የኢትዩጵያ ህዝብ በአስገዳጅ ሁኔታ ከፍተኛ ገንዘብ በመጣል ከሚሰበስበውን ገንዘብ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የመቶ ዓመት እቅድ እና አጀንዳ ቀርፆ በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ የተለያዩ ድሮኖችን በመግዛት እና በመለመን የአማራን ህዝብ በመድፍ፣ በታንክ፣ በከባድ መሳሪዎች እንዲሁም በሰው አልባ ድሮኖች በማዝነብ እየጨፈጨፈ የሚገኝ አርመኔዊ ስረዓት ነው። የተከበረከው የአማራ ህዝብ ሆይ የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ከምድርገፅ ለማጥፋ ከህዝባችን የሰበሰበውን ገንዘብ ለመሰረተ ልማት ስራዎች እና ለህዝባችን የሚጠቅሙ ስራዎችን ከመስራት ይልቅ የህዝባችንን በጀት ለጥፋት ተልዕኮ የሚጠቀም አምባ ገነናዊ ስረዓት ሲሆን ዛሬም ህዝባችን የመከራ ፊዳ ለማብላት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድርው ቀጠና በእነማይ እና ሸበል በረንታ ወረዳ የሐሰት #ምርጫ አካሂዳለሁ በማለት የማጭበርበሪያ ዘዴውን እየተጠቀመ መሆኑን አረጋግጠናል። የአማራ ህዝብ ከአብይ አህመድ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የአማራ ፋኖ በዚህ ሶስት ዓመት እየከፈለ ያለውን የህይወት መስዋትነት ህዝባችን የምትርዱ ቢሆንም በቢቸና እና የዕዱውሃ ከተማ የሚገኘው የብልፅግና አገዛዝ የሐሰት ምርጫ ለማካሄድ እየተወራጨፈ ቢገኝም ከታች በስም ዝረዝሩ የተመዘገባቹህ ይሁን በስም ዝርዝሩ ያልተጠቀሳቹህ ግለሰቦችን ለአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ለማስፈፀም ልትጠረነፍ እንደሆነ እና ስልጠና ልትሄዱ እንደሆነ በክ/ጦሩ የውስጥ ቀኜ መረጃ አማካኝነት በተጨባጭ አረጋግጠናል። በመሆኑም በእነማይ እና ሸበል በረንታ የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ጋር በተየያዘ አውቃቹህም ይሁን ሳታውቁ ለአገዛዙ የሐሰት ምርጫ አስፈፃሚ/ፈፃሚ በመሆን የተመዘገባቹህ እና ለምረጫ ስልጠና ለመሄድ የተዘጋጃቹህ ግለሰቦች ከእነደዚህ አይነት ድርጊት እራሳቹሁን እንድታገሉ እንጠይቃለን። የአማራ ህዝብ መገፋት፣ መበደል፣ መሳደድ እና በጅምላ መገደል ለማስቀረት በሰላማዊ ሰልፍች፣ ሰላማዊ ምርጫዎች እና በህዝባዊ አመፆች ከአንዴ ሁለቴ የተሞከሩ ቢሆንም ዛሬ ላይ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ እየደረሰበት ካለው የህልውና አዳጋ ሊድን የሚችለው የጀመርነው የትጥቅ ትግል ዳር ሲደርስ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ጀግኖች ውድ ይህወታቸውን ገብረው እዚህ ያደርሱት ትግል የሚቀልድም፣ እንቅፋት እና በአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ላይ ተሳታፊ የሚሆን የትኛውም ግለሰብ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የውስጥ መረጃዎችን በማጠንከር በአገዛዙ የሐሰት ምርጫ አስፈፃሚ/ፈፃሚ አካላት ላይ የማያዳግም የእርምት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ                     ግንቦት 14/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር

የሚሊሻ ሻንበል መሪው እና የፓራ ኮማንዶ ቲም መሪው ፋኖን ተቀላቀሉ። ========================== ...........ግንቦት14/2018 ዓ.ም በዛሬው እለት የተለያዩ አመራሮችን ወደ 20
+4
የሚሊሻ ሻንበል መሪው እና የፓራ ኮማንዶ ቲም መሪው ፋኖን ተቀላቀሉ። ========================== ...........ግንቦት14/2018 ዓ.ም በዛሬው እለት የተለያዩ አመራሮችን ወደ 201ኛ 74ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን፦ 1ኛአድባሩ ንጉስ.....የሚሊሻ ሻምበል መሪ 74ክ/ጦር የተቀላቀለ 2ኛ ዳኘ ጤናው.....ሚሊሻ 74ክ/ጦር የተቀላቀለ 3ኛ አድምጠው......ሚሊሻ 74ክ/ጦር የተቀላቀለ 4ኛ.ዘለቀ ፈቃድ ...የፓራኮማንዶ ቲም መሪ 54ክ/ጦር የተቀላቀለ 5ኛ.ዳዊት አወቀ .......ሚሊሻ 54ክጦርን የተቀላቀሉ ናቸው አሁንም ሁሉም የአማራ ልጀች እድሉን ተጠቅመው መውጣት እንዳለባቸው ሀሳባቸውን ገልፀዋል። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

There are two kinds of rulers of heights in this world. One rules the skies… the Eagle. The other rewrites history… the Hero. Both have broken away from the ordinary crowd—two sides of the very same coin. Dawit Amhara, from the village of kings!!

የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ድል ሲቀዳጅ፣የኮሩ ቃኝን ጨምሮ ከአፄ አምደ ፅዮን ኮር የተወጣጡ የክፍለጦር ሻለቆች ወደ ሳሲት ቀጠና ለዘረፋ በተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ የተቀናጀ ጥቃት እየፈፀሙ ይገኛሉ። አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ ጠላት መነሻውን ከሞጃና ወደራ ወረዳ ሰላድንጋይ ከተማ በማድረግ ወደ ሳሲትና አካባቢው ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2018ዓ.ም የተንቀሳቀሰ ሲሆን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የጀግናው አፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃዶች ከረፋዱ 2:00 ጀምሮ በከፍተኛ መናበብ እያደረጉት ባለው እየተቀናጀ ውጊያ ገና ከጅምሩ የአብልፅግናው ሰራዊት ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገደ መሆኑን የኮሩ የግንባር ዘጋቢ ገልጿል። የአገዛዙ 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦርና በርካታ የጥምር ጦር ስብስቡን አስከትሎ በሞርተርና በዙ-23 እንዲሁም በበርካታ ዶሽቃ የታጀበ ውጊያ ቢያደርግም ጀግናው ሰራዊታችን ሰፊ ቀጠናን ወስዶ አድማሱን ባሰፋው የውጊያ ቀጠና በፊላገነት፣በአባ በርሶማ፣በአይሶፌ፣በሸጋ ገበያ እና በእምቧይ ባድ ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባል ከመቸውም ጊዜ በላይ የኮሩ አሃዶችን ያቀናጀ በአገዛዙ ወራሪ ኃይል ላይ የተናበበ ውጊያ እያደረገ ይገኛሉ ሲል ኮሩ በመረጃው ገልጿል። በተመሳሳይ የግንባር መረጃ የከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰለም ሰው 3ኛ ሻለቃ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ድል ተቀዳጀ። በከሰም ንዕስ ወረዳ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ሰላም ሰው 3ኛ ሻለቃ ከአዲስ አበባ 50 ኪሎ ሜትር በቅርብ ርቀት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፍቼ ገነት ቀበሌ ድረስ ዘልቀው በመግባት የከተማ ውስጥ አፕሬሽን በማድረግ የአገዛዙን ሰራዊት ሙትና ቁሥለኛ በማድረግ የጦር መሳሪያን በምርኮ ገቢ አድርጓል። በዚህም ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:- ✅(06) የተደመሰሰ የጠላት ሀይል ✅(03) አውቶማቲክ ክላሽ ✅(02) Sks መሳሪያ ✅220 የክለላሽ ተተኳሽ በመያዝ የሰላም ሰው ሻለቃ አስደማሚ የተሳካ ኦፕሬሽን በመሥራት ግዳጁን በሚገባ ተወጥቶ መመለሱን ኮሩ አስታውቋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በባሶና ወረና ወረዳ የአርበኞች ጦር ሰራዊት በአገዛዙ አረመኔያዊ ኃይል ላይ በወሰዱት ጥቃት ድል መጎናፀፋቸውን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አስታወቀ። ​ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከደብረ ብርሃን፣ ከጎሸባዶ እና ከደነባ ከተሞች የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጥምር ጦር (መከላከያ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስና ሚሊሻ) ከደብረ ብርሃን 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አፄ ዋሻ በተባለ ቦታ በአንድ አባትና ልጅ ላይ ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም፣ በሁለቱ አባት አርበኞች (ወጣት ድጋፊ ወርቄና አቶ ወርቄ) በደረሰበት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ወደ መጣበት ተመልሷል። ​ በዚህም የአገዛዙ መከላከያ ኃይል ከደነባ ከተማ የዙ-23 ከባድ መሳሪያ በማስጠጋት በድጋሚ ከበባ ለማድረግ በሞከረበት ወቅት፣በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙት የ1ኛ እና 3ኛ ሻለቃ ተውጣጭ ቃኚዎች ፈጣን የቆረጣ ምት በመሰንዘር ​ከ 7 በላይ የጠላት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካታ ከባድ ቁስለኞችን በመያዝ የጠላት ኃይል ወደ መጣበት እንዲመለስ ተደርጓል። ​ ሆኖም የአርበኞቹን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ሰራዊት የበቀል በትሩን በንጹሃን ላይ በማሳረፍ፣ አንድ አርሶ አደር መረሸኑን፣ 5 በሬዎችን መዝረፉንና የአንድ ግለሰብ ገለባ አቃጥሎ ሄዷል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 14/2018ዓ.ም

በ206ኛ ኮር ቀጠና በርካታ ሰራዊት ይዞ ከቀተንቀሳቀሰው የ6ኛ ዕዝ 117ኛ ክ/ጦር የሶስተኛ ሬጅመንት ኦርዲናስ ኃላፊ ጌታአረዳ ታደለ ፣ፋይናስ ኃላፊ ቀለሙ አየለ፣ የሰው ኃይል ኃላፊው ቻላቸው ገላየ
+1
በ206ኛ ኮር ቀጠና በርካታ ሰራዊት ይዞ ከቀተንቀሳቀሰው የ6ኛ ዕዝ 117ኛ ክ/ጦር የሶስተኛ ሬጅመንት ኦርዲናስ ኃላፊ ጌታአረዳ ታደለ ፣ፋይናስ ኃላፊ ቀለሙ አየለ፣ የሰው ኃይል ኃላፊው ቻላቸው ገላየ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል። ግንቦት 14/2018 ዓ.ም ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ በድሮን ፣ በጀነራል መድፍ ፣ በዙ23 የታገዘ ውጊያ በመክፈት ጥቃት ለማድረስ የተንቀሳቀሰው 6ኛ ዕዝ፤ በጎዛምን ቀኝ አቦ፤ በስናን ደብረ ዘይት እና በደብረ ኤልያስ ማርዘነብ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ 14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ሻለቃና 24ኛ ክ/ጦር ስናን አባጅሜ ሻለቃ በመጣመር ደብረ ዘይት ላይ በመፋለም በጠላት ላይ የበላይነት በመውሰድ በርካታ ክላሽ ማርከዋል። በጎዛምን ቀኝ አቦ አካባቢ 24ኛ ክ/ጦር የቦቅላ አባይና 34ኛ ክ/ጦር በመቀናጀት ከጠላት ጋር ባደረጉት ፍልሚያ እንዲሁ ድል የተመዘገበ ሲሆን በደቂቃዎች ውስጥ ፦                1.ፍሬው ማርቆስ                2.አብርሀም ጌታቸው የሚባሉ ሁለት ዲሽቃ ተኳሾችን ጨምሮ ከ15 በላይ የሶስተኛ የሬጅመንት አባላት ብቻ በውጊያው ህይወታቸውን ማጣታቸውን 206ኛ ኮርን የተቀላቀሉ የብርሀኑ ጁላ የሰራዊት አባላት መስክረዋል። በደብረ ኤልያ ወረዳ ማርዘነብ ላይ የተጠና ጥቃት የከፈተቸው የ14ኛ ክ/ጦር ቀስተደመና ሻለቃ ሁለት መቶ አለቆችን ጨምሮ ከ50 በላይ የጠላት ኃይል በመደምሰስ 9 ክላሽ፣ 4መገናኛ ራዲዮ፣ አንድ ስታር ሽጉጥ ፣ ወታደራዊ ቦርሳ፣ የወገብ ትጥቅና ተተኳሽ መማረኩ የሚታዎስ ሲሆን 4 (አራት ንፁሐን) ንፁሐን በመድፍና በድሮን ተደብድበው ህይወታቸውን አጠዋል።         አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!       የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ይድረስ አማራ ስላልኩ ለምትሳደቡ እኔ ሌላ ብሄር አልተሳደብኩም ወደዳችሁም ጠላችሁ ዛሬም አማራ ነኝ!! ለወደደው ሚምት ላመነው የማይከዳ ምህረት የማያቅ ለሀገር ሻጭ ባንዳ ጠላቱን ሚቀጣ የምብርክክ ሚ
ይድረስ አማራ ስላልኩ ለምትሳደቡ እኔ ሌላ ብሄር አልተሳደብኩም ወደዳችሁም ጠላችሁ ዛሬም አማራ ነኝ!! ለወደደው ሚምት ላመነው የማይከዳ ምህረት የማያቅ ለሀገር ሻጭ ባንዳ ጠላቱን ሚቀጣ የምብርክክ ሚነዳ ነው እኮ ነፍጠኛ ነው እኮ አማራነት ሞልቶ የተቸረው ክፋት የሌለበት ጀግንነት እንደአባይ ሞልቶ ሚፈስበት!! በጠላቶቹ ፊት ስሙ የሚፈራ እንኳን ነፍጥ ታጥቆ በያዘው ከዘራ እንደማኛ ጤፉ ከምድር የሚዘራ ሺሁን የሚያጋድም ጀግና ነው አማራ!!! ያለውን የሚሰጥ ያለውን ማይነሳ ሰጋጅ ለአምላኩ ፈጣሪውን ማይረሳ ህይወቱን ሚሸለም ለነፍሱ የማይሳሳ ባገሩ ከመጡ ነፍጡን የሚያነሳ ክንዱ ብረት አቅላጭ ወኔው እንደአምበሳ ደረት ላይ አልሞ ቅንድብ የሚበሳ እንደበላይ ደፋር እንደቴዲ ቁጡ ወባ እንደተያዘ የሚያንቀጠቅጡ ልክእንደ አሳምነው ጀግና ነው እዳባቱ እንደአፄ ምኒልክ ልክ እንደጣይቱ ተናግሮ ሚያሳምን አንደበተ ርቱ ባርነት ሚጠላ ሟች ለነፃነቱ ለአገርና እርስቱ ነው እኮ አማራነት ጥንትም መሰረቱ!! ከእርጎ ማሩ ቅቤው ሁሉን ሳያዳላ ማኛ ጤፉን አምርቶ ፣ አላፊ አግዳሚውን አፈር ስሆን ብሎ ፈትፍቶ ሚያበላ አሁን የት ይገኛል ከነፍጠኛዎቹ ከአማራዎች ሌላ? ደግሞ ይህንን ስላልኩኝ ቅናት ይሁን ንዴት ለምትሳደቡ አድቡ አድቡ ካልሆነ ደድቡ አወ አማራ ነኝ እንጦሮንጦስ ግቡ #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር ግንቦት 13/2018 ዓ.ም ከግንባር !!!

አስቸኳይ መረጃ ‼️ የጠላት ሀይል እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ላይ በለሊት ከበባ ለመፈፀም እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ የተረጋገጠ መረጃ ደርሶናል ። ጠላት በጥናፋ መውጫ ዛንጨፈና ፣ በምክሬ ደንጎልትና በዘንጃ
አስቸኳይ መረጃ ‼️ የጠላት ሀይል እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ላይ በለሊት ከበባ ለመፈፀም እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ የተረጋገጠ መረጃ ደርሶናል ። ጠላት በጥናፋ መውጫ ዛንጨፈና ፣ በምክሬ ደንጎልትና በዘንጃ በኩል ብዛት ያለው ሀይል እያንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ስማዳ ወረዳ ጠርንፎ በዝግጅት እንዳለ ለማወቅ ተችሏል ። በተደጋጋሚ እንደገለፅነው ከምርጫ በፊት ጠላት ያለ የሌለ ሀይሉን በመጠቀም ምርጫ በሰላም አካሂዳለሁ የሚል እቅድ እንደያዘ ስንገልጽ ቆይተናል ። ጀነራል ውባንተ (1ኛ) ኮርና ጀነራል ከፊያው (206ኛ) ኮር የተቀናጀ ጥምረት በማድረግ የጠላት እቅድ እንድታከሽፋ እናሳስባለን ። በተለይ ጉና ክፍለጦር ፣ ውባንተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ፣ ሀይሌ ዘ ውባን ክፍለጦርና አንበሳው ጋይንት ክፍለጦር በአንድነት በመቆም የጠላትን እቅድ ማክሸፍ አለባችሁ ። Gashaw Gizat Yared Gedefaw Guna Temesgen Wubanite Yekoye Abeje Mola Demewez Gidaf

አንድ ወር😡 የደፈጣው ንጉስ ብላቴናው አርበኛ አንደበት ክንዳለም በ13/08/2018 ሳሊ ላይ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ለአማራ ህዝብ ክብር ሲል በክብር ወደቀ!!
+2
አንድ ወር😡 የደፈጣው ንጉስ ብላቴናው አርበኛ አንደበት ክንዳለም በ13/08/2018 ሳሊ ላይ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ለአማራ ህዝብ ክብር ሲል በክብር ወደቀ!!

እውነት ይደበቃል እጂ አይጠፋም !!! አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ አጣዬ ላይ ከሸኔ ጋር ሲፋለም ቆይቶ ይሄ መግስት የብልፅግና ስርአት በነፍጥ ካልሆነ በሰላም ፖለቲካ ለውጥ አይመጣም ብሎ ከአጣዬ ከተማ ለቆ
+2
እውነት ይደበቃል እጂ አይጠፋም !!! አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ አጣዬ ላይ ከሸኔ ጋር ሲፋለም ቆይቶ ይሄ መግስት የብልፅግና ስርአት በነፍጥ ካልሆነ በሰላም ፖለቲካ ለውጥ አይመጣም ብሎ ከአጣዬ ከተማ ለቆ ለመጀመሪያ ጊዜ በግል ንብረቱ የጦር መሳሪያ ገዝቶ ጫካ በመግባት ከአጣዬ ቅርብ እርቀት ላይ መሀል ወዝ ቀበሌ አይገብር በምትባል ስፍራ የመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸው ፋኖዎች በ2014 ዓ .ም ይህ ሰው የመጀመሪው የሽዋ ፋኖ ብሎ የመሰረተ ሲሆን ዛሬ ላይ ህልሙ ለተሳካለት ጀግና ክብር ይገበዋል። ኢሳያስ ደመቀ መልኩ የበሰለ ቲማቲም የሚመስል እንኳን ለተወለደው ለብአድ አይን የሚያሳሳ ሲሆን በተለያየ ጊዜ መበለጥን የማይወዱ የግዴ ልጆች ለመጣል ቢታገሉትም በፈጣሪ እና በክንዱ ዛሬ ላይ ደርሷል ። ያልገባቸው በ24 :00 አራት ኬሎ ያለውን ቤተ መግስት እንረከባለን ሲል ብልፅግና ሰላሳ ሁለት ጥርስ ስለነበረው በወቅቱ ይሳለቁ ነበር የዚህ ጀግና ሀሳብ አብይ አህመድን እና የሱ ጀነራሎች ደግጠው የአባታችን ቤተ መግስት እያሉ ያራግቧታል ጋዲሎ ሜዳ ላይ ሲናገራት ፊሽከውን ነፍተን ሲል ሰዎች ተደሰቱ እደነዚህ ያለ ጀግኖችን ማበረታታት ያስፈልጋል ። ብርሀኑ ጁላ ስድ አደግ እንኳን እዲህ አይልም የአባታችን ቤተ መግስት ያለው ከአርበኘው ድምፅ ከሰመው የተወሰደች የድንጋጤ ሀሳብ ነው ። የአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የመጀመሪያ ዙር ፍኖ ተመራቂዎች !!! አርበኛ ኤፍሬም ባዬ እንደ ከተበው ፁሑፍን