ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 632
Підписники
+124 години
+3977 днів
+1 06030 днів
Архів дописів
+1
ሞተ አሉት እንጅ ጀግናኮ አይሞትም
የአማራይቱ ልጅ እጁን አይሰጥም!!
💪💪💪
አርበኛ ማንዴላ የወንዶቹ ወንድ
አንዳንተ ጀግና ሽህ ይወለድ።
መሀል ላይገብቶ በለው እያለ
ያን ባንዳ ሁላ ሲያምሰው ዋለ።
መሄዱን ይሂድ ጀግና ስስት ነው
እሱን ሚተካ አምሳያው ማነው።
ይህንም ስላልኩ ሙቷል አትበሉ
የጀግና ዘሩ ብዙ ነው በሉ።
ሞተ አሉት እንጂ ጀግናኮ አይሞትም
የአማራይቱ ልጅ እጁን አይሰጥም!!
ክብር ለጀግና ሰማዕታት ጓዶቻችን ይሁን!!🙏🙏🙏
እዚህ ሰፈር እየወጡ በቲክታክ እና facebook ላይ እየወጡ ታጋይ ታጋይ ስለተጫወቱ እና በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ስም ስለማሉ ብቻ ታጋይ ይመስሉን የነበሩ ግን መሬት ላይ አንድም ጠብ እሚል ስራ ሰርተው እማያቁ አደናጋሪወች ለጠላት እጅ ሰተዋል።
እንደነዚህ አይነት ሌባ እና አደናጋሪ የፋኖ አባላትን መቆጣጠር እሚቻለው ጠንካራ ወታደራዊ መዋቅር በመስራት ጠንካራ መጠይቅ ያለው ተቋም ሲመሰረት ነው። ይሄንን ለማድረግ ድርጅታችን አደረጃጀቶችን ለማዘመን ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ጠናካራ እዝ እና ሰንሰለት ያለው ሰራዊት ለምገንባት ቀን ከሌት እየተጋ ባለበት ሰአት ላይ ቅርብ ወራጆች ወርደዋል። መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እንጦጦ ስንደርስም ሚከዳ ይኖራል ብሎ የለ?
አበጀ በለው ገርዬ
በቅንነት፣በታማኝነት እና በፅናት አለን በቦታችን‼️
በዚህ ትግል ውስጥ ቅርብ ወራጆችን እያስተዋልን ነው።ቅርብ ወራጅ ድሮም ነበር ፣አሁንም አለ ፣ወደ ፊትም ይኖራል ።
"እንጦጦ ስንደርስም የሚከዳ አለ !" አይደል ያለው አብዮታዊው መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ....
ሽኮኮዎች ለምን ቅርብ ይወርዳሉ?
ምን አይነት ሰዎች ናቸው ቅርብ እየወረዱ የሚገኙት?
ለሚሉት ቁልፍ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ የቅርብ ወራጆች ጠባይ መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፦
1ኛ.ትግሉ የወራት ብቻ እድሜ ያለው የመሰላቸው ግለሰቦች፦አብዮታዊ ትግሉ በአጭር ተቋጭቶ እነሱም የድሉ ተካፋይ ለመሆን በስሜት የተቀላቀሉ ፤ትግል መውጣት መውረድ፣መራብ መጠማት ፣ስሜትን ከፋና ዝቅ የሚያደርግ ተቀያያሪ እንቅስቃሴና ተግባር የሚታይበት በአጠቃላይ የከበረ መሰዕዋትነት የሚከፈልበት መራር መሆኑን በደንብ ያልተገነዘቡ ግለሰቦች ቅርብ ወራጆች ሆነው ይገኛሉ።
2ኛ.አብዮታዊ ትግሉ ነፃ ያወጣቸው ታጋዮች፣መሪዎች፦የአማራው አብዮታዊ ትግል ነፃ ያወጣቸው ታጋዮች እንዲሁም መሪ የሆኑ ግለሰቦች መኖራቸው እሙን ነው ።እነዚህ ግለሰቦች ከቤታቸው ቁጭ ባሉበት ትውልዱ ነፃ አውጥቷቸው የትግሉ አካልና የትግሉ መሪ ያደረጋቸው አሉ።አብዛኞቹ የህልውና ትግሉን በደንብ ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ታላቅ ሃላፊነት በቆራጥነትና በፅናት እየተወጡ የሚገኙ ሲሆን ጥቂቶች ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ ያገኙትን እድል ለአልተገባ ድብቅ አላማና ፍላጎት ሲያውሉ ይገኛሉ።ይህ ከህልውና ትግሉ በተቃራኒ የሚያስሄድ ሴራና ተንኮል ሲነቃባቸው በአጋጣሚ ያገኙትን "የታጋይነት ፥የመሪነት ካባ" ለጠላት መደራደሪያነት እንዲሁም እጅ መነሻነት በመጠቀም ወደ ጠላት ካምፕ ሲገቡ ይታያል።
3ኛ.ታዋቂነት፣ዝና እና አድናቆት በመሻት ብቻ የተቀላቀሉ ግለሰቦች፦በዚህ ውሰጥ የሚገኙ ግለሰቦች በትግሉ ውሰጥ ካደረጉት በላይ እንዲመሰገኑ፣አንዲታወቁ ይፈልጋሉ።ከልክ ያለፈ ክብርና አድናቆት ይሻሉ።የሚፈልጉትን ክብር፣አድናቆት እና ዝና ያጡ የመሰላቸው ወቅት ከትግሉ ገለል ይላል።ለጠላት ርካሽ ፓለቲካ መጠቀሚያ ይሆናሉ።
4ኛ.ትግሉን ለግል ጥቅም ለማዋል የሚፈልጉ ግለሰቦች፦የተሰጣቸውን ታላቅ የህዝብ አደራ ለራስ ጥቅም፣የገንዘብ ማካባቻ እና መዘነጫ ማዋል።ለህዝብ እታገላለሁ እያሉ ህዝብን መዝረፍ፣ማገት እና የራስን ጥቅም ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ።ይህንን አጉል ተግባራቸውን በመረጃ ፣ በማስረጃ በግምገማ ሲገኙ እና ተጠየቅ ሲመጣ ያለምንም ርህራሄ ጥቅማቸው በመነካቱ እየከዱ ወደ ጠላት ካምፕ ይገባል።
.............
መታወቅ ያለበት፦ይህ ትግል የአማራ ህዝብ ፥ የህዝባችን ትግል ነው ።አብዮታዊ ትግሉ ሃዲዱን ጠብቆ ከድል ማማ ላይ እንዲደርስ በንስር አይን የሚከታተል፣በቆቅ ንቃት የሚጠብቅ እዩኝ እዩኝ የማይል፣ራሱን ለትግሉ አሳልፎ የሰጠ ንቁ እና ብቁ ያደፈጠ በርካታ ትውልድ አለ።ሚዲያ ካገነነው፣ ከሚታየው እና ከሚታወቀው ቅርብ ወራጅ ከሆኑ የዘመን ሽኮኮዎች በላይ እልፍ ብርቱ ታጋይና መሪዎች አሉ።
እንፅና!
የፀና ትውልድ የድሉን ዋንጫ በድል አደባባይ ከፍ ያደርጋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
Hailemichael Bayeh
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ከየካቲት 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ጥብቅ የክልከላ /ማስጠንቀቂያ/ መልዕክት:-
====================
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ከአሁን በፊት በፋይዳ/ዲጅታል/ መታወቂያ ጋር በተያያዘ የክልከላ አዋጅ ማውጣቱ ይታወቃል፤
እንደሚታወቀው አምባ ገነኑ አብይ አህመድ መሩ የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ህዝብና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ብርቱ ተጋድሎ ከመቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ እየተንፈራገጠ እንደሆነ ይታወቃል።
አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ #ኢትዮጵያ:-ዜጎች በሰላም ወጥተው የማይገቡባት፣ በስደትና በርሀብ የሚሰቃዩባት፣ የጦርነት አውድማ ሀገር ሆና ሳለ አገዛዙ ስልጠኑን ለማስጠበቅ #ከአረብ ኤምሬት በሚገዛ የድሮን እና መሰል መሳሪያዎች ፣ ከሀገር ውስጥ ትርምስ አልፎ ከጎረቤት ሀገር ጋር እንደ ተናካሽ ውሻ የጦርነት ጉሰማ የእጎሰመ ኢትዮጵያ በሳለፈቻቸው ዘመናት ሁሉ አይታው በማታውቅ መልኩ ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ማድረጉ አለም ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው።
አገዛዙ ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሀይማኖት ጦርነት እና የብሔር ጦርነት እንዲነሳ ዜጎች አንድም ቀን ቢሆን የሰላም አየር አንዳይተነፍሱና በሰላም ወጥተው በሰላም እንዳይገቡ የማይቆፍረው ጉድጓድ፤ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በቁም ቅዠት ላይ የሚገኘው አረመኔው የብልጽግና አገዛዝ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ባላገናዘበ መልኩ ፋይዳ/ዲጅታል መታወቂያ ያልያዘ ማንኛውም ግለሰብ የግብርና ግብዓት፣የባንክ፣የመብራት፣የጤና፣ የወሳኝ ኩነት፣ ወዘተ ምንም አይነት አገልግሎት ማግኘት የማይችል መሆኑን አሳውቋል።
ፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ ያወጣው የዲጅታል(ፋይዳ) መታወቂያ አጠቃቀም አዋጅ/መመሪያ የሚያስከትላቸው ማህበረ-ሰብአዊና ሀገራዊ ጉዳቶች፡-
1ኛ. ዜጎች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን የሚገድብ ነወ።
2ኛ. ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው ከፍተኛ ለሆነ ጥቃት ስለሚያጋልጥ እና አገዛዙ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ብቃትና ቁመና ላይ ስለማይገኝ።
3ኛ. የኢኮኖሚው አጠቃላይ እንቅስቃሴው በአንባገነን ስርዓት በወደቀበት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የሀገሪቱን ፋይናንስ በገዥው መደብ በሞኖፖሊ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዕድል ስለሚፈጥር።
4ኛ.ዲጅታል/ፋይዳ/ መታወቂያው የህልውና ተጋድሎ እያደረገ ያለውን የአማራን ህዝብ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ታልሞ የተዘጋጀ ስለሆነ።
5ኛ. ኢኮኖሚያዊ ስጋት ፦ መታወቂያው ከባንክ፣ ከንግድ ፈቃድ እና ከንብረት ዝውውር ጋር በማገናኘት፤ አገዛዙ የባለሀብቱን እና የዜጎችን ነጻ የገንዘብ ዝውውር በመገደብ የማይፈልጋቸውን ባለሀብቶች በቀላሉ በማንነታቸው በመለዬት የገቢ ምንጫቸውን ለመዝጋት አመች ስለሆነ ። "ያልታዘዘ አይሸጥም፣ አይገዛም" የሚል ኢኮኖሚያዊ ባርነት መፍጠር መቻሉ።
6ኛ. ማኅበራዊ ስጋት፡- ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ ከማኅበራዊ አገልግሎት (ትምህርት፣ ጤና፣ ጋብቻ፣እድር፣ወሳኝ ኩነት፣ወዘተ) ጥቃት የሚያደርስ መሆኑ
7ኛ. በአገዛዙ ታፍነው በግዴታ ወደ መከላከያ ተቋም ገብተው በመክዳት ላይ ያሉ የመከላከያ አባላትን ወደ ቤተሰቦቻቸው በሚንቀሳቀሱበት ሰአት በቀላሉ መንገድ ላይ መለዬት የሚያስችል መሆኑና ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ።
የዲጅታል/ፋይዳ/ መታወቂያ ከላይ የዘረዘርናቸውን እና መሰል እጅግ ከፍተኛ ችግሮችን በማህረሰባችን ላይ እንደሚያስከትል የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ጠንቅቆ ይረዳል።
ስለሆነም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የሚከተሉትን ክልከላዎችን አስቀምጧል፦
1ኛ. ለማንኛውም ግለሰብ የተላለፈ መመሪያ
======================
1. ማንኛውም ግለሰብ ይህንን መታወቂያ እንዳይመዘገብ እና እንዳያወጣ ኮሩ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።
2. ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች በመምጣት ፈጣንና ግልጽ በሆነ መልኩ የራሱን የመታወቂያና የአስተዳደር ሥርዓት አገልግሎት ማግኘት የሚችል መሆኑን ያሳውቃል።
3ኛ. ማንኛውም ግለሰብ የዲጅታል/ፋይዳ/ መታወቂያ ይዞ ኬላ ላይ ማለፍ፣በማንኛው ከተሞችም ሆነ ቀጠናዎች መንቀሳቀስ ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ኮሩ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።
2ኛ.ለሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት
===============
1ኛ. ለባንክ ተቋማት፦ ማንኛውም የባንክ ተቋማት የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጡን ከአሁን በፊት እንደ ነበረው በቀበሌ መታወቂያ እንዲያደርግና የፋይዳ መታወቂያ ያልያዘ አገልግሎት ማግኘት የማይችል መሆኑን የጣለውን እገዳ በአስቸኳይ እንዲያነሳ።
2ኛ. ለመብራት፣ቴሌ እና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ለማንኛውንም ግለሰብ በቀበሌ መታወቂያ አገልግሎት እንዲሰጡ።
3ኛ.የዲጅታል/ፋይዳ/ መታወቂያ ህትመት ለሚሰሩ ተቋማት
==============
የዲጅታል/ፋይዳ/ መታወቂያ ህትመት የሚሰሩ ማንኛውም ተቋም/ድርጅት/ በአስቸኳይ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በጥብቅ ያስጠነቅቃል።
⛔️ማሳሰቢያ፦
=======
1ኛ. ኮሩ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች ከላይ የተዘረዘሩ ክልከላዎችን የተላለፈ ግለሰብም ሆነ ተቋም (ድርጅት) የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ከባድ የሆነ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ያስጠነቅቃል።
2ኛ. ይህ መምሪያ በኮሩ ስር በሚገኙ በሁሉም ክ/ጦሮቻችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
አዲስ ትዉልድ ፤ አዲስ አስተሳሰብ ፤ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ባንዳ የሚሊሻ አባላትን ማፅዳቱን እንደቀጠለ መሆኑ ተገለፀ ።
የካቲት 17/06/2018 ዓ.ም አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በራስ በኃይሉ ሻለቃ (፫ኛ) አራት የሚሊሻ አባላት (የአማራ ባንዳዎች) ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ ።
ነበልባል ክፍለ ጦር በራስ በኃይሉ ሻለቃ (፫ኛ) ፋኖዎች በባንዳ ሚሊሻ አባላት ላይ የተደረገ የቦንብ ጥቃት በማድረስ 1 ሚሊሻ እስከወዲያኛው የተሸኘ ሲሆን፤ 3 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ፤ በአሁን ሰዓት በህክምና ላይ እንደሚገኙ የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ።
ይህ ጥቃት የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ላይ በአረርቲ ከተማ ሸዋገነት አካባቢ ጌቶቻቸውን ለመጠበቅ ወደ ጥበቃ ኬላ በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት አሳረኛው ፋኖ በእጅ ቦንብ በመወርወር፤ እንኳን ጌቶቻቸውን እራሳቸውን መጠበቅ የማይችሉ ለሆዳቸው ሲሉ የሚሞቱ ሆድ-አደሮች ፥ የሰፈር አውደልዳዮች መሆናቸውን የራስ በኃይሉ ሻለቃ ሸማቂ አንድ የፋኖ አባል ይናገራል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በዚህ ጥቃት የተደናገጡት የሚሊሻ አባላቶች በአካባቢ ያገኙትን ተላላፊ መንገደኛ ንፁሃን ዜጎችን ሲያሰቃዩና ሲደበድቡ እንደነበር ሁኔታውን የታዘበና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ ነግረውናል፤ ሲል ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን መረጃውን አድርሶናል ።
© አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
ትልቁ ብሔራዊ ጥቅም ህዝብን ከአምባገነን ቀንበር ነጻ ማውጣት ነው።
ብሔራዊ ጥቅም።(National Interest) የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ በአምባገነን አገዛዞች ዘንድ እንደ ጭንብል የሚያገለግል፣ የተቃዋሚ ነን ባዮች ደግሞ የራሳቸውን ፍርሃት ወይም ጥቅመኝነት የሚሸፍኑበት የፖለቲካ ቁማር ሆኗል።
በአንድ ሀገር ውስጥ "ብሔራዊ ጥቅም" የሚባለው ነገር ትርጉም የሚኖረው "ብሔር" (ህዝቡ) ሲኖር ብቻ ነው። ህዝቡ በገዛ ሀገሩ በድሮን በሚጨፈጨፍበት፣ በሰላም ወጥቶ የመግባት መብቱ የተነጠቀበት እና በረሃብና በእስራት በሚማቅቅበት ሁኔታ ስለ "ብሔራዊ ጥቅም" መስበክ የለየለት ፌዝ ነው።
ብሔራዊ ጥቅም ማለት የአንድን ሀገር ህዝብ ደህንነት፣ የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የባህል ማንነት እና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ማለት ነው። ከየትኛውም ጉዳይ በፊት የህዝብ ደህንነት ቀዳሚ ነው። የዜጎች ህይወት የማይጠበቅባት ሀገር፣ ጥቅሟ ተጠበቀ ሊባል አይችልም። የንጹሃን ደም እየፈሰሰ ስለ ወደብ ወይም ስለ ዲፕሎማሲያዊ ድል ማውራት "ሬሳን በወርቅ እንደማልበስ" ይቆጠራል። ሉዓላዊነት ማለት መሬቱ ብቻ ሳይሆን በላዩ ላይ የሚኖረው ህዝብ በነጻነት የመወሰን ስልጣኑ ነው። አምባገነን አገዛዝ ህዝቡን ሲያፍን፣ እሱ ራሱ የሀገር ሉዓላዊነት ትልቁ ጠላት ነው።
የአገዛዙና የአድርባይ ተቃዋሚዎች "ብሔራዊ ጥቅም" እንደ ማታለያ ስልት ሲጠቀሙበት እያየን ነው። አምባገነን አገዛዞች ስልጣናቸው ሲወዘወዝ እና ህዝባዊ ትግልና አመጽ ሲበረታባቸው፣ ትኩረት ለማስቀየር "ሀገር እየፈረሰች ነው" ወይም "ብሔራዊ ጥቅማችን ተደፈረ" የሚሉ የውሸት ነጋሪቶችን ይጎስማሉ።
አምባገነን አገዛዞች፤ የውጭ ጠላት በመፍጠር የውስጥ ጭቆናውን ለመሸፈን የውጭ ጠላት እንዳለ በማስመሰል ህዝቡን "ከጎኔ ቁም" ይላሉ። የሚገርመው ግን፣ እነዚህ አገዛዞች ለስልጣናቸው ሲሉ የሀገሪቱን ድንበር፣ ለም መሬት እና ስትራቴጂካዊ ሀብቶች ለባዕዳን አሳልፈው ሲሰጡ አይሳቀቁም።
የአድርባይ "ተቃዋሚ" ተብየዎችና የ"ብሔራዊ ጥቅም" ሙዚቃን ስናዳምጠው እና ጭንብላቸው ሲገፈፍ ይህን ይመስላል። ሕዝባዊውን የፋኖን ትግል ለማራከስ "በብሔራዊ ጥቅም አንደራደርም" የሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በትክክለኛው ትርጉሙ ተቃዋሚ ሳይሆኑ የአገዛዙ ተቀጥላዎች (Puppets) ናቸው። የእነዚህ አሻንጉሊቶች ፕሮፖጋንዳ በፖለቲካ መንጸር ሲታይ፦
አንደኛ፤ ድርጊቱ የለየለት የሞራል ውድቀት ነው። ዜጎች በድሮን ሲጨፈጨፉ ዝም ብለው፣ አገዛዙ በዲፕሎማሲያዊ መድረክ ሲወጠር "ሀገራዊ ጥቅም" ብለው መጮኻቸው ለህዝብ ደህንነት ደንታ እንደሌላቸው የሚያሳያ አሳፋሪ ነገር ነው።
ሁለተኛ፤ የስልጣን ፍርፋሪ ፍለጋ የሚደረግ መኩነስነስ ነው። እነዚህ ፓርቲዎች ከአገዛዙ ጋር በስምምነት ለመኖር እና ጥቂት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ሲሉ ህዝባዊ ትግሉን እንደ ስጋት ያዩታል። ለዚኽም የአምባገነኑ አገዛዝ የዘወትር ጥሩምባ ነፊ ይሆናሉ።
ሦስተኛ፤ ሕዝብን የካዳ ተላላኪነት ነው። አገዛዙ የሚነፋውን የፕሮፓጋንዳ ዋሽንት ተቀብለው በማስተጋባት፣ የህዝቡን የትግል ወኔ ለመስበር እና ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዳያገኝ እንቅፋት ለመሆን እየሰሩ ነው፤ ትንሽ ጊዜ ከመግዛት ያለፈ ሌላ ረብ ባይኖረውም ቅሉ፤ ትክክለኛ የሕዝብ ወኪል ነኝ የሚል ተቃዋሚ እሳቤ ግን እንዲህ የሚል ነው "ህዝብ የሌላት ሀገር፣ ዜጋ የማይከበርባት ምድር ምንም አይነት ብሔራዊ ጥቅም ሊኖራት አይችልም። ትልቁ ብሔራዊ ጥቅም ህዝብን ከአምባገነን ቀንበር ነጻ ማውጣት ነው!"...
አርበኛ Estibel Alemu Zerihun
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የገጠር ታዳጊ ከተሞችና መንደሮችን ኢላማ ያደረገ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ንፁሃኖች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ቀጥሏል!
በዚህም የካቲት 16/2018 ዓ.ም ወደ መቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ተደጋጋሚ ሞርተር በማስወንጨፍ አንድ አርሶ አደር ሲገደል አንድ አርሶ አደር ከባድ ቁስለኛ አድርጓል:: ቤት ንብረትም አውድሟል በተጨማሪም ሁለት የቀንድ ከብቶችን ገድሏል::
ባለፈው ጊዜ ጥር 23/2018 ዓ.ም በመቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጠመሬ በተባለ ቦታ ላይ የሞርተር የዙ23 ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም የዘጠኝ አባውራ ቤቶችን ከነ ሙሉ ንብረታቸው አውድሟል::
ይህ ወንጀል እንድፈፀም ያደረገው በጊዜው ግንባሩን ሲመራ የነበረው ኮሎኔል ቤቶቹ እንድወድም ትዕዛዝ መስጠቱን በጊዜው የኮለኔሉ አጃቢ የነበረው እና አሁን አንድ ማካሮፍ ሽጉጥ እና አንድ ጥርጥር መሳሪያ ይዞ የከዳውና ልጅ እያሱ ኮርን የተቀላቀለው አጃቢው ምስክርነት ሰጥቷል::
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጥር 23 ካቃጠላቸው ዘጠኝ ቤቶች በተጨማሪ የካቲት 16/2018 ዓ.ም አንድ ቤት በማቃጠል ቁጥሩን ወደ አስር ከፍ አድርጎታል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
የንጋት ብርሃን አናብስቶች፡ የዓሳምነው ዕዝ ጀግኖች
የታሪክ ማህደር በደምና በእንባ ሊከተብ፣ የአንድ ትውልድ ህልውናም በጨለማ ጥላ ሊዋጥ በካፊያ ላይ በነበረበት ያን ክፉ ቀን፤ ሞት በአማራ ምድር ላይ ክንፉን ዘርግቶ ነበር። የአብይ አህመድ ስርዓት አስጠባቂዎች የጥፋት አዋጅ አውጀው፣ የአማራን ዘር ከምድር ገፅ ለማጥፋት ቆርጠው ተነሱ። ነገር ግን፣ የታሪክ አምላክ ሌላ እቅድ ነበረው።
በአራቱ ማዕዘናት የሚገኙ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ እንደ መብረቅ ብልጭታ በብርሃን ፍጥነት ተነሱ። አንዱ ሌላውን ጎጃምን ጎንደርን ወሎን ጠራ፤ የሸዋ ተራሮች በጀግኖች ድምፅ አስተጋቡ። መጀመሪያ ላይ በእጃቸው የነበረችው አንዲት "እግር" ክላሽንኮቭ ብቻ ነበረች። ጠላት በንቀት ቢያያቸውም፣ በልባቸው ውስጥ የነበረው የነፃነት እሳት ግን ከማንኛውም ዘመናዊ መሣሪያ በላይ የሚፋጅ ነበር።
ከአንድ እግር ክላሽ ወደ መካናይዝድ ጀግንነት ማለት ካለህ ላይ ሰርቀህ ሳይሆን፣ ካለው ላይ ነጥቀህ ታሪክ መስራት ነው" እንዲሉ፤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጀግኖች ጠላትን እያሸበሩ መሣሪያውን መማረክ ጀመሩ። ትናንት በእግሩ ይጓዝ የነበረው ሰራዊት፣ ዛሬ በመካናይዝድ ኃይል ተደራጀ። በተለይም በደቡብ አማራ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው የዐሳምነው ዕዝ፣ የኮርና የዕዝ አመራሮች በታላቅ ብልሃትና ወታደራዊ ጥበብ ሰራዊቱን መርተው ወደር የለሽ ድልን ተቀዳጁ።
ዛሬ ታሪክ ተቀይሯል። የኦሮሞ ጽንፈኛ ኃይሎችን ወረራ በጽናት ተቋቁመው፣ ከበባውን ሰብረው የወጡት እነዚህ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ አሁን የሚገኙት በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት በቅርብ ርቀት ላይ ነው።
የዳግማዊ ምኒልክ ልጆች ዳግም ለኢትዮጵያ አንድነትና ለአማራ ህልውና ዘብ ቆመዋል። ለአዲስ ትውልድ የነፃነት ፋና ሆኗል። የሸዋ ምድር ዛሬም የጀግኖች አውድማ መሆኗን ለዓለም አሳወቀች። የጥፋት ኃይሎች ሲንቀጠቀጡ፣ የነፃነት አርበኞች ግን በድል አድራጊነት ወደ ፊት እየገሰገሱ ነው።
የአቢይ አሕመድ አገዛዝ ከኤርትራ ጋር ለማደርገው ጦርነት የዓማራ ክልል በሎጀስቲክ ከጎኑ እንዲሰለፍ ያወጣው ዕቅድ ከዓምሐራ ፋኖ እጅ ገብቷል።
የአቢይ አሕመድ አገዛዝ በነአረጋ ከበደ(ቀንድ አውጣ) በኩል ከአምሐራ ሕዝብ ጥሬ ገንዘብ እና የእህል ዓይነቶች ተሰብስበው ወደ ኦሕዴድ ብልጽግና ገቢ ይደረግልኝ ሲል ጠይቋል❗
የዓምሐራን ሕዝብ ከመጋቢት 24/2010ዓ.ም ጀምሮ የጥፋት አዋጅ አውጆ በጅምላ እየገደለህ፣ በጅምላ እያፈናቀለህ፣ በጅምላ እየዘረፈህ ከተሞችህን ፣ በጅምላ እያወደመ፣ የአሣምነው ፅጌ ተቋም የሆነው ዓምሐራ ልዩ ኃይልን በብጣሽ ወረቀት አፍርሶብህ፣ ትናንት በጁንታው ጦርነት በሽህ የሚቆጠሩ ልጆችህን ካሥጨረሰ በኋላ መጠቀሚያ አድርጎ ጥሎህ፣ የአምሐራ ሕዝብ የትግል ጽንሥ የሆኑ የአምሐራ ርሥቶችን እንደ ድሬዳዋና አዲሥ አበባ ቀምቶህ፣ ቤተ ዕምነቶችህን አውድሞብህ፣ መዋቅራዊ ጥቃት እየፈጸመብህ፣ በዓለም ሕዝብ የተጠላህ እንድትሆን እየሰራብህ፣ አለ የተባለውን የአየር ጥቃት በንጹሐን ነዋሪዎች ላይ የድሮን ቦምብ እንደዝናብ እያወረደብህ፣ አርሶ አደርህ ማዳበሪያ ተከልክሎ እንዲደኸይ እየተሰራብህ እና በጥቅሉ ጅምላ ዘር ማጥፋት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ የሚገኘው አውሬው የኦሕዴድ ብልጽግና ዛሬም ዓይናችኹን ጨፍኑና ላሞኛችኹ ሢል በአማራ ብልጽግና በአረጋ ከበደ በኩል ተከሥቷል።
ትንንት ነገደልኳችኹ ሥላልበቃኝና ከኤርትራ ጋር ለማደርገው ጦርነት ገንዘብም እሕል በዓይነትም አውጡልኝ ብሏል በአማራ ብልጽግና በኩል። መሞቻችሁን ተተኳሽም ሆነ ሎጀሥቲክ የምታቀርቡት እናንተ ናችኹ ሲል የከተማና የገጠር ነዋሪዎች የተጠየቁትን እንዲያወጡ አዝዟል።
አውሬው የኦሕዴድ አገዛዝ የአማራ ክልልን ህዝብ የሚያደቅቅበት አዲስ ዕቅድ ተፈጻሚነቱ በአማራ ብልጽግና እንደሆነ አዝዟል። ይኸም ከኤርትራ ጋር ጦርነት ልገጥም ስለሆን ለጦርነቱ ተተኳሽ መግዥያ የሚሆን እና ለወታደሩ ቀለብ መሰብሰብ ያለበት ከህዝቡ ነው በማለት በብርና በአይነት አቅዶ አውርዷል። እነ አረጋ ከበደ ዕቅዱ በዝቷል የሚል ጥያቄ አቅርበው የነበር ቢሆንም ሰሚ ባያገኙም በቀምጫያቸው አቢይ ሸኔ በቀጥታ ወደስራ እንዲገቡ ብቻ ነው የታዘዙት።
ኦሕዴድ ብልጽግና ከዓማራ ክልል በነአረጋ ከበደ በኩል እንዲሰበሰብ ያዘዘው፦
✅ በብር ቢያንስ ሶስት ቢሌን ስምንት መቶ ሀያ አምስት ሚሌን(3,825,000,000) ብር እንዲሰበስቡ ይህን ብር ለመሙላት፦
👉ከሁሉም መንግስት ሰራተኛ=2000ብር
👉ከከተማ ኗሪ ከእያንዳንዱ=400ብር
👉ከአርሶ አደር ከእያንዳንዱ=300ብር
👉ከዝቅተኛ ነጋዴ=1000ብር
👉ከተሻለ ነጋዴ ዝቅተኛ=10000ብር
እንዲሰበሰብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
✅በዓይነት ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት ሽ ሶስት መቶ ሀያ (296,320)ኩንታል በዝርዝር ተቀምጧል።
ቦለቄ፣ሩዝ፣በቆሎ፣ገብስ፣ስንዴ፣ሽንብራ፣ባቄላ፣አተር፣ምስር፣በሶ፣የደረቀ እንጀራ፣ቆሎ፣ዳቦ ቆሎ፣መኮረኒ እና ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶች የኤርትራ ጦርነት ተጀመረም አልተጀመረም ሰብስቦ ያስረክባል።የአማራ ክልል አመራር የቀጣይ ስራው የድሀ ቤት እየቆፈቆፈ ብር አምጡ፣ ዱቄት አምጡ ምስርም ይቻላል እያለ የኔ ቢጣ ሁኖ የመሪነት ክብር እንዳይኖረው ያደርገዋል።
ለመላው የዓምሐራ ሕዝብና ለአቢይ ሸኔ አማሮች የሚተላለፍ መልዕክት፦
ለአምሐራ ሕዝብ ገዳይ አገዛዝ ተላላኪ የሆንክ የሥርዓቱ አገልጋይ በየትኛውም መንገድ ተባባሪና አሥፈጻሚ ሆነህ ብትገኝ ለሚደርሥብህ ጉዳት ዓምሐራ ፋኖ ኃላፊነት አይወሥድም። በምድር ላይ እንዳትኖር የተፈረደብህ የዓምሐራ ሕዝብ ደግሞ አገዛዙ የሚላችሁን ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን ዕውነታ ተረድታችሁ፣ በቅርቡ ዋጋ የከፈላችኹበትን የወልቃይትና የራያ ርሥትህን እንዴት ኦሕዴድ ብልጽግና እንደቀማችኹ ተረድታችኹ፣ አሁናዊ የዓምሐራ ሕዝብን የባርነት ሕይወት ተመልክታችኹ አገዛዙ ለሚያቀርብላችኹ ተጠየቅ ምላሻችኹ ሕዝባዊ አቢዮት እንደሆነ ማሣየት አለባችሁ። ዓምሐራው ባርነትን በቃኝ ሲል ትግሉን ሕዝባዊ በማድረግና በአንድ ዓምሐራነት በመቆም ፋሽሥቱን የኦሕዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከነግሳንግሱ ወደ ኤርታ-ኣሌ እሣተ ገሞራ መወርወር አለበት።
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔐✊👊
፩.ዓምሐራ🔐
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ደሳለኝ አጃቢ ኮማንዶ ታዘብ ስጦታው በድምሩ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ 2 የጦር መሳሪያ በመያዝ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ሻለቃን ከተቀላቀለ በኋላ በየወረዳዎች እየተንቀሳቀሰ ህዝብን እያስተማረ ነው:: መከላከያ ሰራዊት ተብዬው የፋሽስቱ አብይ አህመድ መጠቀሚያ ኃይል የአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ ኮማንዶ ታዘብ በዝርዝር ለህዝብ አስረድቷል::
የፋሽስቱ አብይ መንግስት በሀይማኖት ሰበብ አማራን ለመከፋፈል የተጓዘበትንም እርቀት ኮማንዶ ታዘብ አብራርቷል::
ይህ ወንድማችን ከጠላት ከድቶ ወደ ወገን ሲመጣ ኮሎኔል ደሳለኝ በድንጋጤ የተነሳ ታሞ እንደነበረ ሰምተናል:: ከህመሙ ሲያገግም ከእንግዲህ አጃቢ አልፈልግም፤ እናንተ ናችሁ ወይ እኔን ጠብቃችሁ የምታድኑኝ በማለት ሰራዊቱ እና ቀሪ አጃቢዎቹ ላይ እንደ ቁራ ጩሆባቸዋል የሚል መረጃ ደርሶናል::
ክብር እንደ ኮማንዶ ታዘብ ላሉ ቆራጭ የአማራ ልጆች!!
206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 5:30 በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 11 አድማ ብተናዎች ሲገደሉ 8 የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
የካቲት17/2018 ዓ.ም
=============================
በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 5:30 ከመስጊድ አካባቢ ወደ ሀዲስ አለማየሁ አደባባይ ሰራዊት ጭኖ ሲሔድ በነበረ አንድ ፓትሮል ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት 5 (አምስት) አድማ ብተና ሲገደሉ 6 አድማ ብተናዎች ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
በተመሳሳይ ስዓት እንዲሁ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በስላሴ ካምፕ በመሸጉ አድማ ብተናዎች ላይ በፈፀመው ጥቃት 6 የሚሆኑት በቦምብ ጋይተው ሲሞቱ 3ቱ (ሶስት) ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
ተከታታይነት ባለው የአዳኙ ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል እየተደመሰሰ ሲሆን በደብረ ማርቆስ ከተማ፣ በወጀልና ሉማሜ ከተሞች እንዲሁ ከባድ ጥቃት በጠላት ላይ ማሳረፍ ተችሏል። የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 5:30 በሁለት ቦታ የቦምብ ጥቃት የፈፀመው የ206ኛ ኮር አነፍናፊ አዳኝ ቡድን በድምሩ 11 (አስራ አንድ) አድማ ብተና መግደል 8 (ስምንት) የሚደርሱትን ከባድ ቁስለኛ ማድረግ መቻሉን ቡድኑ አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
[ የካቲት 17/2018ዓ.ም]
የአቢይ አሕመድ ጥምር አራዊት ሰራዊትን ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት ከፀጉር ኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮካ፣ ከቆለይ እሥከ ዓለም ሳጋ፣ ከእንቁርቁባ እሥከ ተንሸራታች ድረሥ በደምብ ገርፈውታል።
ውጊያው ከመጀመሩ ጠላት የዓምሐራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተሥኖት አድማ ብተናዎች ተደምሥሠዋል፣ ተማርከዋል፣ ትራፊክ ፖሊሥ እሥከ ወድያኛው ተሸኝቷል፣ ሚሊሺያ ተሸኝቷል፣ የአቢይ መከላከያ ተማርኳል ተደምስሷል።
ጠላት የመዋጋት ሞራሉ ደቅቆ እየተንጠባጠበ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል። ብርቱ ምት ከዓምሐራ ፋኖ የገጠመው አራዊት ሰራዊትም በበቀልና በአጥፊነት ግብሩ 03 ንጹሐን የከተማው ነዋሪዎችን በጭካኔ በጥይት መትቷቸዋል። የተመቱት ንጹሐን 02ቱ ሴቶች ሲሆኑ 01ዱ ደግሞ ወንድ ነው።
ተሥፋ የቆረጠ አገዛዝ ከዚህ የበለጠ ጭካኔውን በንጹሐን ላይ እንደሚያሳርፍ ሕዝቡ አውቆ አውሬውን አገዛዝ ወግድ ማለት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔑✊
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
፩ ዓምሐራ🔑
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው
ቋሚ ምሥል፦ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በከፊል
