uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
2 956
Підписники
+424 години
+147 днів
+38830 днів
Архів дописів
ከአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዓሳምነው ዕዝ የህዝብ አስተዳደር ከአርበኛ ኤፍሬም ባዬ በሰባተኛው የአብይ አህመድ የማጭበርበር ምርጫ የተሰጠ አጠር ያለች መግለጫ!!!

ከአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዓሳምነው ዕዝ የህዝብ አስተዳደር ከአርበኛ ኤፍሬም ባዬ በሰባተኛው የአብይ አህመድ የማጭበርበር ምርጫ የተሰጠ አጠር ያለች መግለጫ!!!

አገዛዙ የጨረባ ምርጫ እንዳያያደርግ በሁሉም የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሥር የሚገኙ  ፋኖዎች ተናበው በመስራታቸው ታላቅ ድል ማስመዝገብ ተችሏል። በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛታ አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር  የነበልባል ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት አባላት በምንጃር የአረርቲ ከተማን በ3 አቅጣጫ በመክበብ የአገዛዙን ሰራዊትና የብአዴን ምስለኔን ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከቦ እያስጨነቀው ይገኛል።  የነበልባል ክፍለጦር አናብስቶች ተዋጊ ፋኖዎች ሰሞኑን በምንጃር አረርቲ  ከተማ ላይ በተደጋጋሚ  በሰሩት የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽንም ሆነ በፊት ለፊት ውጊያ እረፍት የተነሳው የወረዳው ተጋላቢ ካድሬ እንደ በቀል መወጣጫ በማሰብ በአረርቲ ከተማ የሚኖሩ የፋኖ አመራር  ቤተሰብን በመሰብሰብ በግፍ እያሰረ፣ እየደበደበና እያሰቃዬ ይገኛል። በሌላው ግንባር ከሰም ኮር አክሊሉ ሀብተወልድ ክፍለጦር ከአዲስ አበባ 25 km ላይ በምትገኘው  በአሌልቱ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ኦፕሬሽን በማድረግ 6  የጠላትን ሀይል በመደምሰስ እና አካባቢውን በመቆጣጠር  በርካታ ቀበሌዎች  አርቢ ፣ኢቲሳ፣ ቀይ ገደል ፣ጎሮ፣ ጋሹ አንባ፣ የፎ እና አበቡት የተባሉ ቀበሌዎች እንዲሁም በጊንቢቹ ወረዳ ሙሉ ለሙሉ ምርጫ አለመካሄዱን አረጋግጠናል። በሌለ በኩል የአፄ አምዴ ፂዮን ኮር አካል የሆነው አፄ ዳዊት ክ/ጦር በሬማ ፣በተጎራና ድምድም ሊደረግ የታሰበውን የጨረባ ምርጫ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በአገዛዙ ሀይሎች ላይ እልህ አሰጨራሽ ግጥሚያ በማድረግ ሁሉን አቀፍ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን የታሰበው የውሸት የድራማ ምርጫ በወረዳው ሙሉ  አለመካሄዱን ኮሩ ገልጿል። በሌላ በኩል አገዛዙ የምድር ድሮኖቹን የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሰራዊትን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው በጣርማ በር ወረዳ መዘዞ ከተማ በድሮን የንፁሀንን ቤት ሲደበድብ ውሏል። በጥቃቱም አንድ አርሶ አደር የቆሰለ ቢሆንም ከቤትና ንብረት ውድመት ውጭ ንፁሀንን የመጨፍጨፍ ዕቅዱ ከሽፎበታል። በትላንትናው እለት ማለትም በቀን 23/09/2018 ዓ.ም  ማለዳ 11:00 ሰዓት ያለ የሌለ ኃይሉን ከሀገረማርያም የወረዳ መቀመጫ ከሾላ ገበያ ከተማ  አንቀሳቅሶ ጎርፎ ታዳጊ ከተማን ከፋኖ ኃይሎች ለማስለቀቅ ቢሞክርም በክንደ ብርቱዎቹ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር  ተዋጊ ፋኖዎች ብርቱ ተጋድሎ ስለገጠመው ከተማዋን መቆጣጠር አልቻለም። በዚህ የተበሳጨው ወራሪው እና አማራ ጠሉ ኃይል  ከጎርፎ ታዳጊ ከተማ በሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ወደ ከተማዋ ፍፁም ኃላፊነት ባልተሞላበት ሁኔታ ንፁሃኖች ላይ ያነጣጠረ በሚመስል መልኩ ከባባድ መሳሪያዎችን ሲወረውር የዋለ ቢሆንም የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ቃኝ ሻለቃ ፋኖዎች ተሹለክልከው እጠላት ጉያ በመግባት የጨበጣ ውጊያ ሲገትሙት ጠላት ያጠመደውን ከባድ መሳሪያ አንስቶ እራሱን ለማትረፍ እና መሳሪያውን ከምርኮ ለመታደግ ሸሽቶ ወደ መጣበት ከተማ ምሽት 1:00 ሰዓት እንዲገባ እና ተሸናፊነቱን እንዲያምን ማድረግ ተችሏል:: በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለትም በቡልጋ ክፍለጦር መተህ ብላ ከተማን የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ፋኖዎች  ሾላገበያ ከተማን በፋኖ ሰራዊት ከበባ ውሥጥ የገቡ ሲሆን ጠላት ሃገራዊ ምርጫ ብሎ ያሰበውን በፈለገው ልክ እንዳያሳካ ማድረግ ተችሏል:: በተፈጠረው የከተማ ውስጥ ተኩስ ህዝብም ቤቱን ዘግቶ  በመቀመጡ በዕለቱ ምርጫውን ሳያደርግ ቀርቷል:: በሌላ ዜና አጼ ዘርዓያዕቆብ ኮር፣ ሰባት ለሰባ ክፍለጦር እና ብሩኬ  ደምሴ ክፍለጦር በተለያየ ግንባር ጠላትን እዬቀጠቀጡት ይገኛሉ። በላይኛው አጣዬ እና በፈረዶውሀ አካባቢ የ7ለ70 ክፍለጦር የፋኖ አባላት ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምረው የአገዛዙን የጨረባ ምርጫ ሊያስመርጥ የመጣውን የጠላትን ኃይል  ገጥመው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱበት  ሲሆን በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ይምላዋ ቀበሌ ልዩስሙ ውራ በሚባል ቦታ መሀል አስፋልት ላይ አናብስቶቹ ሰባት ለሰባወች አንድ ፓትሮል ሙሉ የጠላትን ኃይል አመድ በማድረግ የጠላትን እቅደ ሙሉ ለሙሉ ማክሸፍ ችለዋል። ​በሌላ በኩል በወረኢሉ ወረዳ ኩርፊት ቀበሌ እና ማሪያም ደብረንግስት ቀበሌ ከወረኢሉ ከተማ የመጣውን ጠላት እያደቀቁት እንደሚገኙ ከግንባር የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።  በጓሳ ግንባርም ከመሀል ሜዳ የመጣውን ጠላት እዬገረፉ ወደመጣበት መልሰውታል። ​ይህ በእንዲህ እንዳለ አጼ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር በሰርዶ ቀበሌ በመግባት ሳርአምባ ቀበሌ ያለውን የአብይ ወንበር ጠባቂ ራሱን መከላከከያ ብሎ የሚጠራውን  በሜካናይዝድ በተደገፈ ውጊያ ሲያስጨንቁት ያረፈዱ ሲሆን  በፍቃዱ በላይ ክፍለጦርም በተመሳሳይ ደራ ጉንዶ መስቀል ወረዳ ቱቲ ሰኞ ገበያ አካባቢ ሊደርገው የነበረውን የብልፅግና ምርጫ ሰርገው በመግባት ብትንትኑን አውጥተውታል:: በመሀመድ ቢሆነኝ ኮር  ሥር የሚገኙት ሁሉም ክፍለጦሮች በተቆጣጠሯቸው የሽዋ ጠቅላይ ግዛት 7 ኛው አገር አቀፍ የጨረባ ምርጫ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ አገዛዙ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሤ እና የይሥሙላ ምርጫን በጣርማ በር ፣በሸዋሮቢት በመንዝ ማማ ሞላሌ ዙሪያ, በአንፆኪያ ገምዛ መኮይ ከተማ እና   በአንኮበር ወረዳ ከጠላት ጋር እየተደረገ ያለ እልህ አስጨራሽ የተኩስ ልውውጥ በተለይ በጣርማ በር ሙሉ በሙሉ የተበተነ ሢሆን በውል ያልታወቀ አመራር እንደተመታ የውስጥ አርበኞች መረጃ አድርሠውናል። በሌሎች የሸዋ አካባቢዎችም እስካሁን ውጊያዎች እደቀጠሉ ናቸው። ምንጭ፦ በአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግኑኝነት መምሪያ ዘመቻ አይሻ ሰይድ!

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የአገዛዙን የይሥሙላ ምርጫ እና የሕዝባችን የህልውና ትግል ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የጎላ ድርሻ ያለው የአማራ ህዝብ በየ ዘመናቱ የተነሱትን ውጫዊ ጠላቶች በመፋለምና ድል በማድረግ የኢትዮጵያን ብዝሃነት እንዳላስከበረና እንዳላነበረ፥ ሀገርን ከነ ልዩ ልዩ ጌጦቿ እንዳላቆመ ሁሉ የውጭ ጠላት ከውስጥ ወደረኞች ጋር በመቀናጀት በከፈቱበት የግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የስነ-ልቦና እና የአካል ጦርነት ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁ ይታወቃል። በተለይም ካላፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ይፋዊ የዘር ማጥፋት ጦርነት በአብይ አህመድና ቡድኑ ታውጆበት ጠላቱን በመመከት አስደናቂ ታሪክ በመፃፍ ላይ ነው። በመንግስትነት ስም ስልጣን የተቆናጠጠው የቀውስና የእልቂት አገዛዝ በህዝብ ድጋፍ ያገኘውን ቅቡልነት በክህደት አሽቀንጥሮ ከጣለ በኋላ በምርጫ ስም ስልጣኑን ለማራዘም ሲንደፋደፍ መቆዬቱም እንዲሁ ይታወቃል። መላው አማራና ኦሮምያ ክልሎች በጦርነት በሚታመሱበት በዚህ ወቅት፥ የትግራይን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቱን ከልክሎ ጉሮሮውን ይዞ በሚያስጨንቅበት በዚህ ወቅት ምርጫን ለማድረግ አይደለም ለማሰብ በማይቻልበት ሁኔታ የምርጫ ግርግር በመጀመር ህዝቡን እና አለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለማደናገር ሞክሯል። ይህንንም በመረዳት ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በብልፅግና የደም ድግስ ላይ የማይናወፅ አቋም ያለው መሆኑን ከማሳወቁ ባሻገር አገዛዙ ተጨማሪ የእልቂት ዘመንን የሚያዋልድበት ፖለቲካዊ ክንዉን እንዳይኖር የተደራጀ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም መላው ህዝብ በነቂስ በመውጣት ምርጫ የሚባል ነገር እንደሌለ ከምርጫ በፊት የአገዛዙ ሰራዊት በህዝብ ላይ የከፈተዉን ወረራ እና ጦርነት እንዲያቆም ጠይቋል። በርካታ ፓርቲወች፣ የፓርቲ አመራሮች፣ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ተቋማትም ተመሳሳይ አቋም ወስደዋል። በተለያዩ ቦታወች ይደረጉ የነበሩ የምርጫ አስፈፃሚወች፣ የታዛቢወች፣ የምርጫ ቦርድ ሰወች ከምርጫ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴወች እና የምርጫ ቁሳቁሶች እንቅስቃሴም መካሄድ ሳይችል ቀርቷል። ​ይህ ይሳካ ዘንድም ድርጅታችን አፋብን የአብይ አህመድ አገዛዝ ይህንን የይሥሙላ ምርጫ ለማካሄድ የፈለገው ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሳይሆን፣ በሕዝባችን ላይ ለሚፈጽመው የጅምላ ጭፍጨፋና ማፈናቀል "የመግደያ ሰርተፊኬት" ለማግኘት መሆኑን ፥ በዚህ የደም ድግስ ላይ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ ከአገዛዙ ጋር እኩል ተጠያቂ እንደሆኑና ንቅናቄያችንም አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስቀድሞ ማሳወቁ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው። ለእዚህ የንቅናቂያችን ጥሪ ከአማራ ህዝብ፣ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከፀረ-አምባገነን ኃይሎች እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያገኘነው ድጋፍ እጅግ ከፍተኛና አበረታች ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ ለትግላችን የታየው አጋርነት አገዛዙ በብቸኝነት ተገልሎ ለውድቀት መቃረቡን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው። ​ዛሬ ላይ አገዛዙ ይህንን ምርጫ ተጠቅሞ ለማግኘት ያለመውን "የመግደያ ሰርተፊኬት" እና ዓለም አቀፍ ቅቡልነት በህዝባችን እና በሰራዊታችን ብርቱ ተጋድሎ የመግደያ ሰርትፊኬቱን ቀደን የፈለገውን ፈቃድ እንዳያገኝ ማድረጋችንን በሙሉ ልብና በኩራት ለሕዝባችን እናበስራለን። የሕዝባችን ነቅቶ መጠበቅና የፋኖ ብርቱ ክንድ አገዛዙ ያቀደውን የፖለቲካ ትርፍ መና አስቀርቶታል።​ በህዝባችን ፅኑ ተጋድሎና በፋኖ ክንድ ጥንካሬ አገዛዙ የፈለገውን የፖለቲካ ቅቡልነት ሳያገኝ ቀርቶ በ ዓለም ፊት እርቃኑን አቁመነዋል፡፡ አብይ አህመድ ይህንን ምርጫ ተጠቅሞ በዓለም ፊት "ተመርጫለሁ" የሚል የሐሰት ካባ ለመልበስ የነበረው ተስፋ ከሽፏል። ይህ ድል የትግላችንን የበላይነት ያረጋገጠ ኩነት ነው። ይህ ስለመሆኑም ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በመላው ዓለም ከፍተኛ ተሰሚነት ባላቸው ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች እና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች የወጡት መግለጫዎች ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡ ​የተከናወነው "የምርጫ ቲያትር" እጅግ አስቂኝና ለወደፊቱ ትውልድ የፖለቲካ ውድቀትና የይስሙላ ምርጫ ምን እንደሚመስል ለማስተማሪያነት የሚያገለግል ተጨማሪ ክስተት ሆኖ አልፏል። ድምፅ መስጠቱም ሆነ ውጤቱ አስቀድሞ በቤተ-መንግሥት ተጠናቆ የቀረበ መሆኑን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ የአገዛዙ የገዛ ካድሬዎች እንኳ ሳይቀሩ በሚገባ እንዲረዱት ተደርጓል። ንቅናቄያችን በፈጠረው የፖለቲካ ጫና ምክንያት፣ የአገዛዙ መዋቅር ውስጥ ያሉት ግለሰቦች እንኳ በሥርዓቱ ላይ እምነት እንዲያጡና የውስጥ መከፋፈል እንዲፈጠር ሆኗል። ይህ የሚያሳየው አገዛዙ ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም እየፈረሰ መሆኑን ነው። ​ትግላችን አሁን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አምባገነኑንና ደም መጣጩን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከመንበሩ አስወግደን፣ የሕዝባችንን የህልውና ዋስትና የምናረጋግጥበት ጊዜ ቀርቧል። ስለሆነም መላው የአማራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች የጀመራችሁትን ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ፣ በአቅጣጫው የምትገኙ የፀረ-አገዛዝ ኃይሎች በጋራ እንድንቆም፣ የአገዛዙ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያላችሁ ወገኖችም ከሕዝባችሁ ጎን በመቆም የውድቀቱ ተባባሪ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በመጨረሻም ከግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ የተደረገው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ እና የጥንቃቄ መመሪያ በመጠናቀቁ ከነገ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ እንቅስቃሴወች እንዲቀጥሉ የተፈቀደ መሆኑን እናሳውቃለን። ድል ለአማራ ህዝብ! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ግንቦት 24/2018 አም አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በግሼራቤል ወረዳ ቀይ አምባ ቀበሌ የሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ከነ ሙሉ የምርጫ ቁሳቁሱ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። የምርጫ ጣቢያውን ጨምሮ አከባቢውን በቁጥጥሩ ስር ያዋለው በምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25 ክፍለጦር ከቀበሌው አመራሮችና ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል። #ዘመቻ አይሻ ሰይድ!

• የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ የምርጫ ጣቢያዎችን በመበተን የአገዛዙን እቅድ አክሽፈዉታል።። ​የጀብደኛው ምኒሊክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በሞርተር የታገዘ ጥቃት በመሰንዘር በተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ሂደት እ
+1
• የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ የምርጫ ጣቢያዎችን በመበተን የአገዛዙን እቅድ አክሽፈዉታል።።   ​የጀብደኛው ምኒሊክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በሞርተር የታገዘ ጥቃት በመሰንዘር በተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ሂደት እንዲደናቀፍ ማድረጉን አድርገዉታል። ​በዚህም በጮቢ በር፣ በስንደዶ በር እና በቆቦ ዙሪያ በሜካናይዝድ  የታገዘ ውጊያ በመክፈት የምርጫው ሂደት እንዲቋረጥ አድርገዉታል። በተጨማሪም የልዩ ዘመቻ ቃኝዎች  በሳንቃ ከተማ የሚገኘውን የምርጫ ጣቢያ ብትንትኑን በማዉጣት የዉሸት ምርጫዉን እንዳያስመርጥ አድርገዉታል ሲል የልዩ ዘመቻ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃዉን አድርሷል። ​ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!! ግንቦት 24/2018ዓ.ም

​የብልፅግናዉ አገዛዙ በራያ ቆቦ ኮባ በተባለ ስፍራ በመድፍ ጥቃት በሰላማዊ ሰዎችና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። ​በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮባ በተባለ አካባቢ አገዛዙ በሰነዘረዉ  የከባድ መሣሪያ ጥቃት በሰላማዊ ሰዎችና በቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳትና አድርሷል። ​ በአካባቢው ላይ ያነጣጠረውና በመድፍ የተደገፈው ይሄው ጥቃት የተሰነዘረው በአገዛዙ ሰራዊት ሲሆን ጥቃቱ ንጹኃን ዜጎች ባሉበት የመኖሪያ መንደርና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ቦታ ላይ በማነጣጠሩ፣ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። ከሰላማዊ ሰዎች በተጨማሪም በአካባቢው አርሶ አደሮችና እረኞች እጅ ላይ የነበሩ በርካታ የቤት እንስሳት የዚህ ጥቃት ሰለባ ሁነዋል። ​ይህ በንጹኃን ላይ የተፈጸመው የከባድ መሣሪያ ድብደባ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና መረበሽን ፈጥሯል ሲል የ101ኛ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃዉን አድርሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!! ግንቦት 24/2018ዓ.ም

ባሶሊበን ኮርክ ጊዮርጊስ 33 አድማ ብተና እና 1 ፖሊስ፤ ኮርክ ሚካኤል 6 ሚኒሻዎች በህዝብ ርብርብ በተቀበሩበት ተጋድሎ አይበገሬው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጀብድ ሰርቷል። ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በባሶሊበን ወረዳ ኮርክ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ ከአነጋጉ 11:00 ሰዓት በፈፀመው ጥቃት የአድማ ብተና 2ኛ ሬጅመንት ሙሉ ለሙሉ ስትደመሰስ 1 ብሬን 15 ክላሽ 4 አስቃጥላ የዲሽቃ ጥይት 2 መገናኛ ራዲዮ 2 የዲሽቃ አፈሙዝ 1 የብሬን አፈሙዝ 1 የዲሽቃ ሸንሸል ከነ ጥይቱ 1 ሽጉጥ ከሞት የተረፉ ሁለት የአድማ ብተና አባላት ፣ ወታደራዊ ቦርሳና ትጥቅ ተማርኳል። ዋና ሳጅን ምስጋናው ሽፈራው - ሻምበል ዘመቻ ዋና ሳጅንሞላ ምህረቱ -ም/ሻምበል አዛዥ ጨምሮ ኮርክ ጊዮርጊስ 33 አድማ ብተና እና 1 ፖሊስ፤ ኮርክ ሚካኤል 6 ሚኒሻዎች በህዝብ ርብርብ በተቀበሩበት ተጋድሎ አይበገሬው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጀብድ ሰርቷል። ቀሪ አስክሬን የአረመኔው ሰራዊት ታቅፎታል። በተመሳሳይ በደጀን ጉበያ ወንድማማቾች 34ኛ ክ/ጦር እና 64ኛ ክ/ጦር  በመቀናጀት ጠላትን መክተዋል። በአዋባል ወረዳ ከተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ጋር የተፋለመው 34ኛ ክ/ጦር በወጀል ከተማም ጥቃት ከፍቶ ውሏል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ዕለታዊ የውጊያ ውሎ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የ208ኛ ኮር ​በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው 208ኛ ኮር ከሌሎች አጋር ክፍለጦሮች ጋር በመቀናጀት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ግንባሮች ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ደማቅ ድሎችን አስመዝግቧል። በውሎውም የጠላትን የሰው ኃይልና መዋቅር ከመበተን ጀምሮ የአገዛዙን የፖለቲካ ፍላጎትና የይስሙላ ምርጫ ምኞት ሙሉ በሙሉ ያከሸፉ ስልታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ይህ የተቀናጀ ጥቃት በአካባቢው ላይ የነበረውን የጠላት የተላላኪነት ስሜት በእጅጉ ያቀጨጨ መሆኑ ታውቋል። ​የዚሁ ድል አካል በሆነውና በአፋብን ግንባር በተደረገው ውጊያ የ54ኛ ክፍለጦር ሬጅመንት 04 ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ የአገዛዙ የጭቆና መዋቅር ምሶሶ የነበረውን አመራር ደምስሷል። ቀደም ሲል የአርበኛ መሳፍንት ተስፉን ልጅ አርበኛ ገብሬ መሳፍንትን በመግደል ወደ አገዛዙ በመጠጋት በአገዛዙ የሰላም አስከባሪ መሪነትና በሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ሥልጣን ተሰጥቶት ሲያገለግል የቆየውን ግታው በጋሻው የተባለውን የአገዛዙን አመራር "ደቋ" በተባለ ልዩ ቦታ ላይ በጀግኖች ክንድ እስከወዲያኛው አለም በሸኘት ሙሉ በሙሉ እንዲደመሰስ ተደርጓል። ​በተያያዘም በዚሁ ክፍለጦር ስር የሚገኙት ሬጅመንት 01 እና ሬጅመንት 03 በበየዳ ግንባር ርን፣ በስቂያ፣ በተል፣ሰገነት እና ጠዘል በሚባሉ ቀበሌዎች ልዩ ተጋድሎዎችን በመፈጸም፣ አገዛዙ ሊያካሂደው አቅዶት የነበረውን ምርጫ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥና እንዳይካሄድ አድርገዋል። በሌላ በኩል ደግሞ  ሬጅመንት 02 በዝንጀሮ አማጋ እና አምበራ ላይ ጠላትን ፍጹም መፈናፈኛ ባጣ ሁኔታ ሲያርበደበድቡት ውለዋል። በሌላ ዜና የጭና ክፍለጦር እና የራስ ደጀን ክፍለጦር ከአምስተኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ጋር በመሆን በአምባ-ጊዮርጊስ ላይ ጠላትን አንገት አስደፍተዋል። ሁለቱ ክፍለጦሮች ከትናንት ጀምሮ ባደረጉት የጋራ ርብርብና መናበብ ከ8 በላይ ሙት እና ከ6 በላይ ቁስለኛ በጠላት ኃይል ላይ መመዝገቡ ተረጋግጧል። ​በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት በ208ኛ ኮር ከፍተኛ የአውደ ውጊያ ተጋድሎ የተደረገባቸውና የድል አሻራ ያረፈባቸው ቦታዎች ፍድቃ፣ ዛሪማ፣ አምበራ፣ ወቅን፣ ዝንጀሮ አማጋ፣ ደቋ፣ በየዳ ግንባር፣ ተከዜ አካባቢ፣ ርን፣ በተል ሰገነት፣ ጠዘል፣ በስቂያ፣ ወገራ፣ አምባጊዮርጊስ፣ ገደብጌ፣ወርቅደሞ እና ዳባት መሆናቸው ታውቋል። ይህ በየግንባሩ የተመዘገበው ስኬት የኃይላትን ቅንጅታዊ ብቃትና የሕዝባዊ ዓላማውን አሸናፊነት በተግባር ያሳየ ውሎ ሆኖ አልፏል። ድል ለአማራ ህዝብ!!! 208ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!!!

"ዘመቻ ህፃን አንሻ ሰይድ"            አራተኛ ቀን 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በተለያዩ ግንባሮች በጠላት ላይ  ታላቅ ድል ተቀዳጀ፣ የብልፅግና የጨረባ ምርጫም ተቋረጠ!      ግንቦት:- 24/ 2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በተለያዩ  የአውደ ውጊያ ግንባሮች ማለትም ግዳን ወረዳ ይባር ወይራ በር ግንባር፣ ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ዘውማሪያምና ማሪያም አምባ ግንባር እና ላስታ ወረዳ ብልባላ ዳቢያና ፀዳ ግንባር፣ መቄት ወረዳ ገረገራና ፍላቂት ግንባር በመሰለፍ ሰፍሮ የነበረውን የብልፅግና ጦር እና የብልፅግናን የጨረባ ምርጫ ለማስፈፀም ላይ ታች ሲል በነበረው የአገዛዙ ጦርና ካቢኔ ላይ እርምጃ በመውሰድ ኮሩ በተለያዩ ቦታዎች ታላቅ ድል ተጎናፅፏል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለሙሉ ቀን እስከ አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ የአገዛዙ ጦር በሜካናይዝድ የታገዘ ውጊያ ቢከፍትም ከሰቆጣ ሙጃና ብልባላ ከተማ መድፍ እያስወነጨፈ ቢውልም የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አናብስቶች በፍፁም የአባቶቹን ወኔና ጀግንነት በመላበስና የተለያዩ ምሽጎችን በመደረማመስ አልሞ ተኳሾቹ ብልፅግና አስቦት የነበረውን የውሸት ምርጫ ድግስ በተለያዩ ቦታዎች ያሰናከሉት ሲሆን በጠላትም ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግቧል። 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ከሚንቀሳቀስባቸው ወረዳዎችና የወረዳ ቀበሌዎች ብልፅግና ከ99% በላይ ምርጫ ያላስመረጠ ሲሆን በጊዜያዊነት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት ላልኪው፣ ብልባላ፣ ሙጃ፣ ወንዳች፣ ኩልመስክ፣ እንጃፋት፣ ድብኮ፣ ገረገራና ፍላቂት ከተሞች ሙሉ በሙሉ ምርጫ የተቋረጠባቸውና ያልተካሄደባቸው ከተሞች ሲሆኑ መቄት ወረዳም ሙሉ በሙሉ  ምርጫ ያልተካሄደባቸው ሲሆን የወረዳው መቀመጫ ገረገራና ፍላቂት በአካባቢው የሚገኙ ፋኖዎች ገቡተው ያቋረጡት ሲሆን እንጃፋት፣ ድብኮና ኩልመስክ ከጠላት ሙሉ በሙሉ ነፃ የወጡ ከተሞች ሲሆኑ ላልኪው፣ ሙጃና ወንዳች ከተሞችን ነፃ ለማውጣት አናብስቶቹ ለነፃነታቸው እየተዋደቁ ይገኛሉ። በዛሬው አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች:-    👉 ብሬን= 01    👉 የብሬን ተተኳሽ= 2547    👉 ጥቁር ክላሽ= 143    👉 የክላሽ ተተኳሽ= 2980    👉 የእጅ ቦምብ= 46    👉 የደረትና የወገብ ትጥቅ= 69    👉 ምርኮኛ= 20    👉 ቁስለኛ= ከ200 በላይ    👉 የተደመሰሰ:- አመራር= 2   አባል= ከ280 በላይ ሲሆን:- ብልፅግና ይዟቸው በነበሩ አንዳንድ ቀበሌዎች ላይ ህዝቡ ለምርጫ አልወጣም በማለቱ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ አድማ ብተናና አንዳንድ ሆድ አደሮችንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ሲቪል በማልበስና ሰልፍ በማሰለፍ መራጭ በማስመሰል ቪዲዮና ፎቶ ሲቀርፅ እንደዋለ ታውቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል!    መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!! ግንቦት 24/2018ዓ.ም

በዕለቱ ውጊያ የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ከዓለማየሁ ከቤ ሻለቃ ጋር በመቀናጀት ደቡብ ሜጫ መሃል ገነት (ገርጨጭ) የነበረውን የድራማ ምርጫ በቀጠናው ሙሉ በሙሉ
+3
በዕለቱ ውጊያ የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ከዓለማየሁ ከቤ ሻለቃ ጋር በመቀናጀት ደቡብ ሜጫ መሃል ገነት (ገርጨጭ) የነበረውን የድራማ ምርጫ በቀጠናው ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ የተቻለ ሲሆን በሁሉም ግንባሮች ጠላት ላይ ከፍተኛ ምት ማድረስ ተችሏል ። ደቡብ ሜጫ ወረዳ (ገርጨጭ ) የተገኙ ድሎች 🔸01ብሬን 🔸22 ክላሽ 🔸03 አይኮም መገናኛ 🔸1520 ተተኳሽ 🔸10 ምርኮኛ እና በርካታ ቁጥር ያለው ጠላት መደምሰስ ተችሏል።           ይቀጥላል...

መረጃ በጎጃም ቀጠና ! ---- በዕለቱ ውጊያ የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ከዓለማየሁ ከቤ ሻለቃ ጋር በመቀናጀት ደቡብ ሜጫ መሃል ገነት (ገርጨጭ) የነበረውን የድ
መረጃ በጎጃም ቀጠና ! ---- በዕለቱ ውጊያ የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ከዓለማየሁ ከቤ ሻለቃ ጋር በመቀናጀት ደቡብ ሜጫ መሃል ገነት (ገርጨጭ) የነበረውን የድራማ ምርጫ በቀጠናው ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ የተቻለ ሲሆን በሁሉም ግንባሮች ጠላት ላይ ከፍተኛ ምት ማድረስ ተችሏል ። ደቡብ ሜጫ ወረዳ (ገርጨጭ ) የተገኙ ድሎች 🔸01ብሬን 🔸22 ክላሽ 🔸03 አይኮም መገናኛ 🔸1520 ተተኳሽ 🔸10 ምርኮኛ እና በርካታ ቁጥር ያለው ጠላት መደምሰስ ተችሏል።           ይቀጥላል...

ዘመቻ አንሻ ሰይድ በድል ታጅቦ ወደፊት እየገሰገሰ ነዉ!! አፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው 3 ወረዳዎች የጠላት ቅስምና ሞራል ተሰብሯል። ዛሬ ቀን ማለትም 24/09/2018 ዓ.ም የኦህዴድ/ብልፅግናው ወንጀለኛ ቡድን የይስሙላ ምርጫ ህዝብን በጦር መሳሪያ እያስፈራራ  ለምርጫ ውጡ በማለት የአንባገነንነቱን ጥግ ለማሳየት ቢሞክርም የ47ኛ ክ/ጦር አናብስት እቅዱን ረብ_የለሽና ውሃን በወንፊት እንደመቅዳት ተስፋ_ቢስ አድርገውታል። የአትሮንስ_ሻለቃ፦   ከደንሳ ከተማ እስከ ጅራፍ ጎትት፣ወርቅ ማውጫ ከተማና ወዤድ ውጊያ የተደረገ ሲሆን በመሃል አማራ ሳይንት ወረዳ ሙሉ በሙሉ ምርጫ የሚሉት የወፈፌዎች ቅዤት ተግባራዊ  ሳያስደርጓቸዉ ቀርተዋል። የሁሉም ቀበሌ አባት አርበኞች በዚህ አውደ ውጊያ ግንባር ቀደም ተሰላፊና ደጀን በመሆን የወርቃማ ታሪክ ባለቤት ሆነዋል። በሌላኛዉ ግንባር ደግሞ  ታቦር_ተራራ_ሻለቃ፦ እዋ፣ከነሆር ሜዳ እስከ አጅባር ፣ መለስ ሳንቃ በር፣ ከሰኞ ሸንጎ ደፈር አስከ ሳታቦይ እና ጓሜዳ ግንባር ግብስብሱን ኃይል እየገረፉት ነው። የምርጫ አስፈፃሚው ወራሪ ኃይል በሁሉም አቅጣጫ ተበታትኗል። የጓሜዳው ጠላት እንኳን ምርጫ ሊያስመርጥ ራሱን መከላከል ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን እያንጣባጠበ ለመፈርጠጥ ተገዷል። በዚህ አውደ_ውጊያ ሆድ_አደር ከሆኑት ባንዳዎች መካከል  የፖሊስ አመራር የሆነው ዋና ሳጅን ፍሬዘር አራጌና አንዲት ስሟ ያልታወቀ አስመራጭ  ጨምሮ ሌሎችም ተቀንድሸው ደመ_ከልብ ሆነው መቅረታቸው እርግጥ ሆኗል። አሁንም በሌላኛዉ ግንባር የተሰለፈችዉ ሼህ ሁሴን ጂብሪል ሻለቃ፦ ደብረ ዘይት፣ኮሬብ፣ጎጎስ፣ ሞሰቢት እና ማሻ ከተማ ከፍተኛ ትንቅንቅ ያደረጉ ሲሆን ኮሬብ በዚህ ትንቅንቅ ላይ  5 ሚሊሻዎችን እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል። ሌሎችም ገደል የገቡና ቁስለኛ የሆኑ ሆድ አደሮች እንዳሉ ተረጋግጧል። ምርጫ የሚባል ነገርም የለም! በአጠቃለይ የ47ኛ ክ/ጦር አካላት 3ቱም ሻለቆች የዐብይ አህመድን የግል ዘበኛና ቅጥረኛ ወራሪ ኃይል ሲያቅበዘብዙት አርፍደዋል ሲል የ47ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መረጀዉን አድርሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!! ግንቦት 24/2018ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና ‼️ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 102ተኛ ኮር 11 ክ/ጦር ሜጫ እና አዴት ላይ ባደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማረከ።በአውደ ውጊያው በረከት ያሉ የመ
+2
ሰበር የድል ዜና ‼️ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 102ተኛ ኮር 11 ክ/ጦር ሜጫ እና አዴት ላይ ባደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማረከ።በአውደ ውጊያው በረከት ያሉ የመከላከያ አባላት ተማርከዋል።

ሰበር የድል ዜና ‼️ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 102ተኛ ኮር 11 ክ/ጦር ሜጫ እኔ አዴት ላይ ባደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማረከ።በአውደ ውጊያው በረከት ያሉ የመ
+2
ሰበር የድል ዜና ‼️ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 102ተኛ ኮር 11 ክ/ጦር ሜጫ እኔ አዴት ላይ ባደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማረከ።በአውደ ውጊያው በረከት ያሉ የመከላከያ አባላት ተማርከዋል።