uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 057
Підписники
+6824 години
+3957 днів
+1 39230 днів
Архів дописів
የኦሮሙማው ገዳ'ይ አራዊት ሰራዊት በ12 አቅጣጫ ከበባ ለማድረግ ሞክሮ አልተሳካለትም❗ [ጥር 18/2018ዓ.ም] የአገዛዙ ወምበር አሥጠባቂ ቡድን የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር እሣተ ገሞራ ዋና ሕዋሥ ''እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ'' በ12 አቅጣጫ የመጣውን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በተባበረ ዓምሐራዊ ክንድ እሥከ ምሽቱ 01:00 ሲመክቱትና ሲያርበደብዱት ውለዋል። የአገዛዙ ጨካኝ ቡድን አለኝ ያለውን የሰው ኃይልና የቡድን መሣሪያ ለመጠቀም ሞክሯል ነገር ግን አልተሳካለትም። በወታደራዊ ሳይንሥ ጥበብ ምርጥ ወታደር ምሽጉን እንደ አሥፈላጊነቱ ይቀያይራል የሚለው ሕገ ፋኖ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ኮፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር ሕዋሥያን ጥቋቁር አናብስቶቹ እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች ላይ ይሠራል። የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ጦር በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚያድርበትን መዳረሻ 360° ከብቦ ይተኛል። ደፈጣ አለው(በወታደራዊ ቋንቋ በሁሉም አቅጣጫ ሳተላይት አለው)። የሜ/ጀ ውባንተ አባተ የአብራክ ልጆች የሚያድሩበትን መዳረሻ በአንድ ሌሊት 03 ጊዜ ይቀያይራሉ። የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የውባንተ አባተ ልጆች ትናንት ያደሩብን ቦታ ከበብ ፈጽመው አድረዋል። ውባንታዊያን የምርጥ ወታደርን ሥነ ልቦና በሚገባ ታጥቀዋልና ሌሊቱን ሁሉ አካባቢያቸውን ሲያስሱ አድረዋል፤ የነበሩበትንም ምሽግ እንደ አሥፈላጊገቱ ቀያይረዋል። ኮንዶሙ የአቢይ ወታደር የውባንተ ልጆች የሌሉበትን ተራራ ከብቦ አድሯል። ዘረ ውባንተ አባተዎቹ ያዋጋኛል ያሉትን ፋኗዊ መዳኛ ምሽግ መርጠዋል። እሥቴ ዴንሳ ብርጌድንም በተመሣሣይ መልኩ በሐምሣ አለቃ አያሌው ደራሽ በኩል ቴሌን በ02 ዲሽቃ እና በብርጌዱ 02 ሻለቆች ዘግተው እንዲያድሩ ተደርጓል። የምድሪቱ ጨካኝ የኦሮሙማ ገዳ'ይ ቡድን አዳሩን ከበባ ለማድረግ የሞከረባቸው 12 ወሳኝ መዳረሻዎች፦ የአቢይ ሸዬ አራጅ ቡድን ከበባ ለመፈጸም የሞከረባቸው ቦታዎች፦ 1. ከእሥቴ በ''ልዋዬ'' ማሕደረ ማርያም ከተማ 2. ከእሥቴ በ''ምችግ'' ማሕደረ ማርያም ከተማ 3.ከእሥቴ በ''ወንድም ለየኝ'' ተራራ ማሕደረ ማርያም ከተማ 4. ከደሬ ገላውዴዎሥ በ''ዝምሐ'' ማሕደረ ማርያም ከተማ 5.ከደራ በ''ፈንድቃ'' ማሕደረ ማርያም 6.ከደብረ ታቦር በ''ወርቄ''ን ከተማ ማሕደረ ማርያም 7. ከፎገራ ወረታ በ''መነጉዘር አይደግና ግብር ጊዎርጊሥ 8.ከደብረ ታቦር ከተማ አሪንጎ በ''ኪንቲ'' 9. ከእሥቴ መካነ ኢየሱስ በ''መተሬ'' ማሕደረ ማርያም 10. ከእሥቴና ደራ በ''ጋዤን'' ማሕደረ ማርያም 11. ከፎገራ በ''ግብር'' ማሕደረ ማርያም እና 12. ከደብረ ታቦር በ''ሳጨራ'' ማሕደረ ማርያም በኩል አዳሩን ሙሉ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት 360° ከበባ ሲያደርግ አድሯል። ነገር ግን ዘረ ውባንተዎቹ ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። የቀንም የሌሊትም ደፈጣ አላቸው። ሌሊትም ማደሪያቸውን 03 ጊዜ ይቀይራሉ። የአገዛዙ ሽንት ታጣቂ ትናንት ውባንታዊያን ያደሩበትን ቀይረው አድረዋል። ጠላት ከብቦ ካደረው ጫካ ፊት ለፊት ካለ ሌላ ተራራ ምሽጋቸውን ሰርተው አድረዋል። የባዬው መልካሙ ልጆችና የኦፒ ወንዶሞች ከያዙት የቴሌ ምሽግ በጠዋቱ የውቤ አብራኮች ወዳሉበት ጎራ ሲሉ ዘረና ግብረ ውባንተዎቹ ጥበበኛዋ የእሥቴ ዴንሳ ብርጌድ አቅጣጫ መቀየር እንዳለባትና ከጠላት 300 ሜትር ርቀት ላይ እንዳሉ ይነግሯቸዋል። እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ የጠላትን ቀይ መሥመር ካለፈ በኋላ ዘረ ውባንተዎቹ አሉ የተባሉ የውጊያ ምሽጎችን ይዘዋል። ጠዋት12:30 ላይ የአገዛዙ የሽንት ጨርቅ ታጣቂ የውጊያ ፊሽካን ነፋ። ዘረ ውባንተ አባተዎቹ አሉ የተባሉ የውጊያ ቦታዎችን ከያዙ በኋላ ጠላት የፈለገውን ያክል የጥይት አይነት ናዳ ቢያዘንብ ምላሽ አልሸጠም። ነገር ግን አመች ቦታዎችን ከተቆጣጠረ ቦኋላ ከ''አምቦሹ'' ወደ ቻይና ካምፕ'' ከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ እሥከ ቡድን መሣሪያ በመጠቀም የጠላትን አንገት አሥደፍቷል። ከዚህ የውጊያ ፊሽካ በኋላ ከማሕደረ ማርያም ዙሪያ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች ፎገራን፣ፋርጣን፣ ደራንና እሥቴን አካትቶ በውጊያ እሥከ ምሽት 1:00 ሲናጡ ውለዋል። የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በ12 አቅጣጫ ከበባን ፈጽሞ አንድም የአምሐራ ፋኖን መጉዳትም ሆነ ማቁሰል አልቻለም። በተቃራኒው ለውሸት የተገረደው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በአካልም፣ በቁሥምና በሥነ ልቦና ተሰባብሮ ውሏል። ወዳጄ አምሐራው አምሐራ ነኝ ካለ የሚያቆመው ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ዕናውቃለን። ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርና የጉናዋ እሥቴ ደንሳ ብርጌድ እልልልልል ያሉዓምሐሮች ናቸውና። ዓምሐራነት በነገድ ብቻ ሳይሆን በግብርም መገለጥ አለበት❗ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑 አፋብን ሰሜን አምሐራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ መምሪያ ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ለሁሉም ይድረስ #ሼር አድርገዉ ጎበዝ ዘመነ ካሴን ለማራከስ ያልተሰራ ስራ አልነበረም። ለኔ እንኳን በግል፥ የሸዋ አማራን ይጠላል ፥ ወሎዬ ወደ ስልጣን እንዲመጣ አይፈልግም ፥ ይህንን ሲናገር ቀድተነዋል ፥ ፒሪሪም ፓራራም። አልሰማናቸውም። ዘሜን እናውቀዋለን። ጎጃሜንም ጎጃምንም እንረዳለን። አልቻሉም። አሉባልታቸው የትም አላደረሳቸውም። ተሰነካክለው ቀሩ። አሁን ደሞ የሻዕቢያ ቅጥረኛ፥ የህወሓት ተላላኪ ነው የሚል ተረት ይዘው መጥተዋል። ዘመነ ካሴ ነው እንዴ ኢሳያስን ሚሊኒየም አዳራሽ ቀለበት ያጠለቀለት። ዘመነ ነው ‘ንዴ የፕሪቶሪያ ስምምነት ብሎ ደቡብ አፍሪካ ልዑካን ቡድን የላከው። ዘመነ ነው እንዴ፥ ኢትዮጵያን ፍርስርሷን ሳናወጣት አርፈን አንቀመጥም ሲል የነበረውን ጌታቸው ረዳ አምጥቶ የሾመው። ዘመነ ነው እንዴ ስብሃት ነጋን ከስር ፈቶ በቦሌ በኩል ዴንቨር ኮሎራዶ የላከው። ዘመነ ነው እንዴ የኢትዮጵያ ሰራዊትን በተኛበት በጥይት ያስደበደበውን ጻድቃን ገብረትንሳይ ምንም ወንጀል ‘ንዳልሰራ ሰው ተቀብሎ አዲስ አበባ አጃቢ መድቦ የሚያኖረው። ዘመነ ነው እንዴ ከህውሓት ጋ’ ድርድር ይደረግ ዘንድ አባ-ገዳዎችን መቀሌ ሽምግልና የላከው። ዘመነ ነው እንዴ በሳምንት ሁለቴ አስመራ ኢሳይስ ጋ’ ሲመላለስ የነበረው። ዘመነ ነው እንዴ ለሻዕቢያ የቡና ቁርስ ፈንዲሻ እየዞረ ሲያዘግን የነበረው። ዘመነ ነው እንዴ ኢሳያስን አዲስ አበባ አምጥቶ የጦር ሚስጢር መሆን ያለበትን ኢንሳን ሳይቀር ሲያስጎበኝ የነበረው። ዘመነ ነው ወይ ?!!! ዘረኝነትን እናንተ ህገ-መንግስት ነድፋችሁ ንጡሃንን እየገደላችሁ ስታራምዱት ልክ፥ አማራ ለመብቱ፥ ለህልውናው አማራ ነኝ ሲል ወንጀል የሚሆነው በምን ቀመር ነው። ከኢሳያስ እርዳታ ስትሹ ‘ና ህውሃትን ማጥቃት ስትፈልጉ፥ ልክ ፥ ሌላው ሲያደርገው ያገር ክህደት። ማነው መስፈርቱን ያወጣው። ማንም አይሰማችሁም። Via ሄኖክ የሺጥላ

አሳዛኝ መረጃ‼️ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ እና በኢየሩሣሌ
አሳዛኝ መረጃ‼️ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ እና  በኢየሩሣሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል ።

የአሸባሪው የብልፅግና ቡድን ሰራዊትና አመራር የፋኖ ቤተሰብ በማለት የንፁሀንን ንብረት ላይ ዘረፋና ውድመት አደረሰ‼️   በቀኝአዝማች ስሜነህ ደስታ እንጅባራ ሻለቃ በሚገኘው የአከና ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዋ ወ/ሮ አበባ መኮንን የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በብልፅግናው ስርዓተ መንግስት አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ትግል ውስጥ ያለውንና ከትግል በፊት የፈታሽውን አቶ የኔው ፈጠነን ፣ ልጅሽን ፋኖ ያረጋል የኔውን እና ወንድምሽን ፋኖ መልካሙ መኮንን ን ከአማራ ህዝብ ትግል አስወጥተሽ ወደ መንግስት እንዲገቡ እስካላደረግሽ ድረስ አንቺም የፋኖ ደጋፊ ስለሆንሽ ከፍተኛ ጉዳት እናደርስብሻለን በማለት በተደጋጋሚ ሲዝቱባት የነበሩና ያሉትን ዛቻም በተግባር በመፈፀም በእርሷና በልጆቿ ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱባት ይገኛሉ። እስካሁን እርሷን ከማንገላታት በተጨማሪ የእርሷና የልጆቿ በሆኑት በሚከተሉት የንብረቶች ላይ ውድመቶች ደርሰውባታል። ህዳር 10/2017 ዓ.ም 1) 1 መኖሪያ ቤት ሶፋ ወንበርን ጨምሮ ሙሉ ንብረቱ ተዘርፏልም ወድሟልም! 2) 1 የልጄ መኖሪያ ቤት ሶፋ ወንበርን ጨምሮ ሙሉ ንብረቱ ተዘርፏልም ወድሟልም! 3) የመካከለኛ ሱቅ ሙሉ ንብረት ተዘርፏል! 4) 1 ባጃጅ ተጭኖ ተወስዷል (የልጄ ንብረት)! 5) 1 ሞተር ተጭኖ ተወስዷል (የልጄ ንብረት)! 6) 2 ካሶኒ ሙሉ የችግኝ እንጨት ተቆርጦ ተጭኖ ተወስዷል! ህዳር 08/2018 ዓ.ም በመንግስት አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተዘርፈው የተወሰዱ የቀንድ ከብቶች ብዛት 1) ድልብ በሮች = 4 2) መጫት ከብቶች = 6 3) ክበድ ከብቶች = 4 4) ድልብ ጊደር ከብቶች = 1 5) እምቦሳ ጥጆች=2 6) ጎረምሳ ጥጆች= 2 በድምሩ 19 ከብቶች ተዘርፈው ተወስደዋል። ከእነዚህ ከብቶች ውስጥ አጠቃላይ የፈረጅ ከብቶች ብዛት=14 ጥር 13/2018 ዓ.ም በመንግስት አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተዘርፈው የተወሰዱ በጎች ብዛት 1) ድልብ ሙክት በጎች= 15 (የሴት ልጄ ንብረቶች) 2) ሴት ድልብ በጎች = 5 3) ክበድ በጎች = 6 4) መጫት በጎች = 2 3) ጎረምሳ የበግ ግልገሎች= 2 በድምሩ 30 በጎች ተዘርፈው ተወስደዋል። ይህ ሁሉ በደል መድረሱን ፋኖ መልካሙ መኮንን (የተጎጅዋ ወንድም) ለክፍለ ጦሩ ህ/ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል። ይህ ስርዓት አውዳሚና የፀረ አማራዎች ስብስብ ነውና ሁሉን በሚችለው ሁሉ አስተዋፆ በማድረግና በአንድነት ታግሎ ለተጎጂዎች ፍትህን ፣ ለመላው የአማራ ህዝብና ኢትዮጵያውን ነፃነትን ማጎናፀፍ ይጠይቃል!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል! 18/ዐ5/2018 ዓ.ም

​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና የአሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና ሌሎች ከፍተኛ የ ዕዝ የኮር አመራሮች የውስጥ አንድነት ለማጠናከርና ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እየሰሩ ይገኛሉ ። ​እንደሚታወቀው አርበኛ ገዙ አካፋልኝ ላለፈው አንድ ዓመት ገደማ የራሱን ቡድን በመምራትና ትጥቅ ይዞ በመንቀሳቀስ ከአሳምነው ዕዝ ተለይቶ መቆየቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ በጋራ ለመመከት ሲባል፤ ከአናብስቶቹ የአሳምነው ልጆች በተደጋጋሚ "ወደ አማራዊ ቤታችን ተመለስ፤ የአረመኔውን የአብይ አህመድ ሰራዊት በጋራ ድባቅ እንምታ የሚል ጥሪ ሲቀርብለት ቆይቷል። ​ይህንን የአንድነት ጥሪ ውጤታማ ለማድረግ የአሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አርበኛ እኢሳያስ ደመቀ እና የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል መምሪያ ሀላፊ 100 አለቃ ተፈሪ በተገኙበት የበርሃውን ብርድና ሐሩር፣ የዳገትና ቁልቁለቱን ፈተና ሳይበግራቸው ሳይሰለቻቸው ሳይደክማቸው በታላቅ ብልሃት የውስጥ አንድነትን ለመገንባት ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። ​አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ አንድነትን በላቀ ፍጥነት ከመገንባት ባለፈ፣ በዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ስር የሚገኙ የተለያዩ የጦር ግንባሮችን በአካል እየተዘዋወሩ በመጎብኘት፣ ሰራዊቱን በፖለቲካዊ ንቃተ-ህሊና እና በአስተዳደራዊ ቁመና ወደ ተሻለ የማታገያ ደረጃ ከፍ እያደረገ ይገኛል። ​በመጨረሻም አርበኛ ገዙ አካፋልኝ የጀመረውን የተናጠል ጉዞ በመተው፣ ሙሉ ጦሩንና ትጥቁን በማስተባበር የአሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የ"ሰባት ለሰባ" ክፍለ ጦርን በይፋ ለአገዛዙ ራስ ምታት ወደሆኑት የአሳምነው ልጆች በስሩ ያሉትን የሰራዊት አባላት ለመቀላቀል ተስማምቷል። በመቀጠልም አርበኛ ገዙ አካፋልኝ እና አርበኛ ንጉስ ደርብ የአሳምነው ዕዝ በሚመድባቸው መምሪያ ላይ የድርጅቱን መርህ በጠበቀ መልኩ የሚሰጡትን ግዳጅ በብቃት እንደሚወጡ እና ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ነፃነት በጋራ ለመቆም ቃል እንገባለን በማለት ​ይህ ታሪካዊ ውህደት ለአማራ ሕዝብ የነፃነት ጉዞ መጠናከር ትልቅ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል። የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማር ታዘዘ ጥር 18/5/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ጀግኖች አላችሁ 👉አስታጥቄ በቀጣይ የሚያስታጥቀን ፀረ ድሮን እንሆ።ጠጋ ጠጋ ብለን እንቀማዋለን።
የአማራ ፋኖ ጀግኖች አላችሁ 👉አስታጥቄ በቀጣይ የሚያስታጥቀን ፀረ ድሮን እንሆ።ጠጋ ጠጋ ብለን እንቀማዋለን።

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት ጋር የሚኒሻና የመከላከያ አባላት እዬተቀላቀሉ ነው‼️ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ከአሁን በፊት ከ6
+2
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት ጋር የሚኒሻና የመከላከያ አባላት እዬተቀላቀሉ ነው‼️ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ከአሁን በፊት ከ60 በላይ የሚሊሻና የመከላከያ አባላትን ወደ ክፍለጦሩ ስቦ ያሥገባ እንደሆነ የገለፅን ሲሆን በዚህ ሁለት ቀን ብቻ (8) የሚኒሻና የመከላከያ አባለትን ስቦ አሥከድቷል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አንድነት ከተመሰረተ ማግሥት ወደ ክፍለ ጦራችን የተቀላቀሉ የሚኒሻና የመከላከያ አባላት እንዳሉት እሥከ አሁን ሥንጠብቀው የነበረው የአማራ ፋኖ አንድነት በመመሥረቱና የፋኖ አንድ ላይ መሆን የአማራን ትግል በአንድ ላይ ሆነን እንድንታገልና እንድናስመልሥ ምቹ እድል መሆኑን አውቀን  ከነ ሙሉ ትጥቃችን ተቀላቅለናል ብለዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀነውጥላል። ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ከሰም ፪ኛኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክፍለጦር ሪፖርተር ክፍል !! ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም 18/ዐ5/2018 ዓ.ም

አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ (ጆን) በ2010 ዓ/ም ከጓደኞቹ ከእነ አርበኛ ስጦታው ዳኛው (ባሻ)፣ አርበኛ እሸቴ ባየ፣ አርበኛ ኢ/ር በየነ አለማው፣ አርበኛ አስፋው ሰርፅ እና ሰለሞን አጠና፣ሻንቆ ሽባባው፣አጋየ አድማሱ፣ቻላቸው እንየው፣ርህያቆስ አበበ፣ሚናስ አለማየሁ እና ሌሎች አርበኞች ጋር በመሆን የጎንደር ከተማና የአካባቢው የፋኖን ሀይል በአራት ሻለቆችን ማለትም ጀኔራል አሳምነው ፣ ራስ አሞራው ፣ገብርየ እና ጎቤ ሻለቆች በማቋቋም የህውሃት ተላላኪ የነበረውን ታጣቂ ፅንፈኛ ክንፍ እና በከተማው ተሰክስከው የነበሩ ቅጥረኞችን ተዋግቷል አዋግቷል። የማፅዳትና የመደምሰስ ስራም ሰርተዋል። ✅ክፍል ሁለት ይቀጥላል በአርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ

መንግስት በምድርም በሰማይም ለማጥፋት ፈልጎና ሞክሮ ያልቻለው የፋኖ መሪ ማን ነው ? የትግል ጓዶቹ ምሰሶ ብለው ይጠሩታል !! ክፍል አንድ ታሪክ የአማራ ህዝብ የነፃነት መሪ የሆነው አርበኛ ከአባታቸው ከአቶ ንጉሱ ሙጨ ብሩ እና ከእናታቸው ወ/ሮ እኑየ እሸቴ ኃይሌ በቀድሞው ጠገዴ አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ዙሪያ በብቸኛዋ ኢትዮጵያዊ ጳጉሜ ወር 1978 ዓ.ም በ5ኛው ቀን ምሽት ላይ የዛሬው አርበኛ የያኔው ህፃን ዮሀንስ ተወለደ ። የልጅነት ጊዜውን እንደ ማንኛውም የአካባቢው ልጅ በእንክብካቤ ያደገ ሲሆን ቤተሰቦቹ ለተሻለ ትምህርትና ኑሮ በማሰብ ወደ ጎንደር ከተማ ስለመጡ ታዳጊው ብላቴና ዮሐንስ ንጉሱም ከቤተሰቡ ጋር ከሳንጃ ከተማ ወደ ጎንደር ከተማ መጣ ። ነገር ግን ጎንደር ከተማ ብዙም ሳይቆዩ አባቱንና እናቱን በአንድ ወቅት በሞት በማጣታቱ ከስድስት እህትና ወንድሞቹ ጋር በወላጆቻቸው ሀዘንና ናፍቆት ክፉኛ ተጎዱ። ሆኖም በሀገረ አሜሪካ ኑሮውን ያደረገው አጎታቸው እዘዘው ሙጨ እና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ድጋፍና እንክብካቤ እየተደረገላቸው አደጉ ።በተለይም እህቶቹ ሀብታም ንጉሱ እና ደስታ ንጉሱ ህፃናት ልጆችን እህትም እናትም ሁነው ተንከባክቦ የማሳደግ ኃላፊነትን በለጋ እድሜያቸው ተሸከሙ ። አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ (ጆን) እድሜው ለትምህርት ሲደርስ ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 02 ፣ ህብረት እና አንገረብ ትምህርት ቤቶች ከአንደኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የደረጃ ተሸላሚ ኮከብ ተማሪ በመሆን የተማረ ሲሆን በትምህርት ቤቶች፣ በስፖርታዊ ውድድሮች ፣በህዝባዊ በዓላት ላይ የሚደረጉ አመፆችና ህዝባዊ እንቢተኝነቶችን ታስተባብራለህ ተብሎ ለአንድ አመት ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገዷል ። አርበኛው የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት ቢያመጣም በ1997 ዓ/ም የሀገራችን ምርጫ ውጤት ምክንያት በተከሰተው ግጭትና ግርግር ከዩኒቨርስቲ ቀርቶ ወጣትነቱን በዕውቀት ለማዳበር በኢትዮጵያን ታሪክ፣ በአለም የመንግስት አስተዳደር እና በትጥቅ ትግል ዙሪያ የተፃፋ በርካታ መፃህፍትን በማንበብ ስለ መንግስት ስርዓት ለውጥና መፈንቅለ መንግስት በቂ ግንዛቤ ይዞ ጉዞውን ጀመረ ። አርበኛው ሁሉም እህት ወንድሞቹ ውጭ ሀገር ነዋሪ በመሆናቸው ከፖለቲካ እንዲርቅ እና ከሀገር እንዲወጣ ቢመክሩት እሱ ግን አያቴ ሙጨ ብሩ ለኢትዮጵያ የከፈለውን ዋጋ እኔም እደግመዋለው በማለት አያቱ ጫካ ገብቶ ከቢትወደድ አዳነ፣ ከራስ አሞራው ውብነህ እና ከብሬ ዘገየ ጋር ለሀገሩ በከፈለው ዋጋ በንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን እና የአርበኝነት ዘመን የእድሜ ልክ ጡሮታ ክፍያ መብት ሽልማት የተበረከተላቸው የሀገራችን ባለውለታ አርበኛ ነበሩ ። አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ (ጆን ) መንግስት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተሸንፎ ስልጣን ካላስረከበ አማራጩ በትጥቅ ትግል ማስወገድ በመሆኑ ለዚህ እሳቤው ያግዘው ዘንድ ሁለት አማራጮችን አሰበ አንደኛው ወደ ኤርትራ በርሃ በመሄድ ሁለተኛው ደግሞ በመንግስት ተቋማት መሰልጠን ሲሆኑ አውጥቶ አውርዶ ሁለተኛውን በመወሰን በ2001 ዓ/ም ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም በመግባት ለአንድ አመት ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ የፌደራል ፓሊስ አባል ሆነ ። አርበኛው በሙያውም በአዲስ አበባ፣ በሀረር ፣በድሬ ደዋ ተመድቦ ሀገሩንና ህዝቡን ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋሙ ተመልሶ የኮማንዶ ስልጠና ወስዶ ለአሰልጣኝነት ተመልምሎ የመከላከያ ሰራዊት አዲስ ምልምሎችንና ነባር አባላትን በገርባሳ ጅጅጋ እና ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ኮማንዶ፣ መደበኛ፣ አጫጭር ስልጠናዎችን አሰልጥኗል። እንዲሁም ከሀገር ውጭም የሶማሊያ መንግስት ወታደሮችን ውርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አሰልጥኗል ሀገራቸውን ከአልሸባብና ከዘራፊዎች እንዲጠብቁ አድርጓል ። አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ (ጆን ) ከፌደራል ፖሊስ ወደ መከላከያ ኮማንዶ በመግባት በሶማሊያ ሀገር ከአሚሶም ሰላም አስከባሪ ኃይል ውጭ ሰላም የማስከበር ተልኮ ተሰጥቶት በ2002 ዓ/ም ሀገራዊ አደራውን በሚገባ ተወጥቷል ። እንዲሁም በኢትዮጵያ ሶማሊያ በደጋ ሀቡር፣ በጎዴ፣በምስራቅ ጋሻሞ፣ በቀብሪ ደሀር፣ በቀብሪ በያ ፣አርቲቼክ፣ቦህ፣ቦህሌና ዱዱብ እና ሌሎች ቦታዎች እየተዘዋወረ አገልግሏል። ነገር ግን በሀገሪቱ ተተክሎ የነበረውን የአንድ ብሔር የበላይነትና ጠቅላይነት እንዲሁም ብቸኛ ተጠቃሚነት በመቃወሙ እና ተደጋጋሚ ለምን የሚል ጥያቄ በማንሳቱ በአንድ አሀድ ተረጋግቶ እንዳይቆይና እንዳይሰራ እንዲሁም የማዕረግ እድገትና ጥቅማጥቅም እንዳያገኝ ከልክለውታል ። አርበኛው በ2003 ዓ/ም በታችኛው ባኮል ጎልዶ ጎብ በተባለ ቦታ ከአልሻባብና ከኦብነግ ጋር በተደረገ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ ቀኝ እግሩ ላይ ቆሰለ ለህውሃት አመራሮች ሰርግና ምላሽ ሆነላቸው እንዳይታከምም ከለከሉት ። አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ (ጆን) ህክምና አለማግኘቱና በአመራሮች ጥርስ ስለተነከሰበት አሀዷን በማፍረስ ከሶማሊያ ወደ ጅቡቲ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ የገባ ቢሆንም የሚያውቃቸው አባላቱን በማግኘቱ ያስይዙኛል በማለት ወደ ባህር ዳር ከተማ በመምጣት በበጎ አድራጎት ማህበር ስም በህቡዕ ህብረተሰቡንና ወጣቱን በፖለቲካ የማነፅና ማደራጀት ስራ በመስራት አማራ በአማራነት መደራጀት አለበት በሚል ፅኑ እምነት የቤተ አማራ ህቡዕ ንቅናቄን በመቀላቀል እንቅስቃሴው አስቀጠለ። አርበኛው ባህር ዳር የሚሰራው ስራ ሲደረስበትም ወደ አ.አ በመሄድ ራሱን ሰውሮ የህቡዕ ፀረ አገዛዝ ተግባራትን ሲከውን ከቆየ በኃላ ወደ ጎንደር በመመለስ የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ግጨው ማንነት አስመላሽ ኮሚቴዎች፣ ከአካባቢው አርበኞችና ከሀገር ውጭ ከሚንቀሳቀሱ የትጥቅ ትግል አራማጆች ጋር በሰፊው በመነጋገርና በመወያየት ከእነ ጎቤ መልኬ፣ደጀኔ ማሩ ፣አታላይ ዛፌ ፣ኮሌኔር ደመቀ ዘውዱ፣ ጌታቸው አደመ ጋር በመሆን አማራነት እንደ ሸረሪት ድር እንዲተሳሰር እንደ ኑግ አንበሳ እንዲተባበር የማድረግ ስራ ሰርተዋል። በተለይም በጎንደር ከተማ ላንድማርክ ሆቴል የወልቃይት ኮሚቴ ያደረገውን የመጀመሪያ ስብሰባ ከተካፈለ ወዲያ ህዝባዊ አመፅና የትጥቅ ትግል አስፈላጊ የሆነበት ምዕራፍ መደረሱን በመተንተን ከወጣቶች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ማድረግ ተጀመረ። በ2008 ዓ/ም ጎንደር የተደረገውን ደማቅና ታይቶ የማይታወቅ ህዝባዊ ሰልፍ በመደገፍ ደማችሁ ደማቸን ፣ ህመምና ስቃያችሁ ስቃያችን፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ፣ ወልቃይት ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ ፣ ደንበራችን ተከዜ ነው የሚሉትና ሌሎች መልዕክቶች እንዲተላለፋ የተደረገበትን ንቅናቄ በመደገፍ ወደ ጎንደር ተመለሰ። በዚህ ድርጊቱም የመንግስት ደህንነቶች ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በሚል ታልጋ በ2009 ዓ/ም በጎንደር ከተማ ማራኪ ክ/ከተማ ታፍኖ በ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ2 ወራት ታሰረ።

64ኛ ክፍለ ጦር ላይ የነበሩ ችግሮቻችን ቤታችን ዘግተን በመወያየት ፈተናል። የጠላት ራስ ምታት የበላይ ትንፋሽ ወደፊት ፤ አንድ ማንኪያ ቅንነት ካለ እናሸንፋለን ዛሬም የሆነው ይኸው ነው‼️ ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ በመካከላችን ንፋስ አይገባም:: መሪያችን አረበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለው ቤታችን ዘግተን ችግራችን ፈተናል ::ጠላት በእንድነቱ ምስረታ ጭንቀት ውስጥ የገባ ሲሆን:- የቴወድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና የኮር አመራሮች የ64ኛ ክፍለጦር አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ጥያቄዎች የነበራቸው በክፍለ ጦሩ ውስጥ የነበሩ አባላት 3ቀን የፈጀ ጥልቅ ግምገማ ና ውይይት  በማካሄድ የውስጥ ችግሮች በመለየት መፍትሔ እና  ቀጣይ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ ተችሏል።  እንዲሁም ውይይትና ግምገማውን መሰረት ያደረገ  አዲስ የስራ ስምሪት በመስጠት ተጠናቋል።  በተግባር በዉጊያ የተሸነፈው  የአብይ ቡድን  በሚዲያ ለመከፋፈል ያለ እረፍት 24ሰዓት ቢሰራም እኛ ግን ቤታችን ዘግተን በመምከር ችግራችን በመፍታታት በአንድነት የወጣንለትን ዓላማ በማሰብ ጦራችን በመሰብሰብ የጠላት ቅስም መስበር ችለናል። ከዚህ በሗላ መሪዎቻችን እና ድርጅታችን የሰጠነን ተልእኮ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ( ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም )       ጥር 18/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ይህ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ X ገፅ ነው። https://www.facebook.com/share/17sksxUJKG/

ድርድርን እንደ ተስቦ ***** የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ የሚታገለው ለስር -ነቀል ለውጥ እንጅ በዘር ማጥፋት ወንጀል ለፍርድ ከሚቀረብው የብልፅግና ስርዓት ጋር ለመደራደር አይደለም!! የአማራ ህዝብ የገጠመውን ብሔራዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በምናደርገው ትግል ውስጥ የድርድር ነገር አይታሰብም!! ድርድር የምናደርገው ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋር ብቻ ነው። ከዘር አጥፊ ስርዓት ጋር ለድርድር መቅረብ ሺንፈት፣ራስ ወዳድነት፣ገባሪነት እና ስቀቀናምነት ነው። ባንዳነትን እና ገባሪነትን የሚፀየፈው የአማራ ህዝብ ትግል በድል የሚጠናቀቅ እንጅ" ድርድር" በሚባል ወረርሺኝ የሚቀለበስ ትግል አልጀመርንም!! አፋብን ለስርዓት ለውጥ የሚታገል የአማራ ህዝብ ድርጅት ነው። ነገር ግን አፋብንን እንደ አብን እና እንደ መአህድ ከፅንሱ ለማፍረስ መሞከር በፍፁም አይታሰብም!! የአማራን ህዝብ ትግል እየሻሻጡ አረበኝነት ስላቅ ነው። #አርበኝነት በተግባር ታግሎ በማሸነፍ የህዝባችን የቀደሙ ጥያቄዎች በክብር መመለስ እንጅ በስናዳሪነት እና በተደራዳሪነት መንፈስ ለአማራ ህዝብ እየታገልኩኝ ነው ማለት ቀልድ ነው። ስለዚህ የአማራ ፋኖ ትግል እስከ ቀራንዮ ድረስ መሆኑ የተረጋገጠ ነው። መንገድ ላይ በቁስ፣በስልጣን እና በአሻጥር መንገዳገድ በጠላትነት ያስፈርጃል!! ግልፅ ጠላትነት መሆኑም ሊታወቅ ይገባል!! አፋብን ደም የተገበረበት ድርጅት እንጅ ሱፍ እና ከረባት ለባሾች የመሰረቱት ፓርቲ አይደለም!! ደም የገበርንበትን እና አጥንት የከሰከስንበትን ድርጅት በአመራር ስም ለማሻሻጥ ደለላ ሆኖ ለመቅረብም መንገድ ማመቻቼት በፍፁም ወንጀል ነው። ትግላችን ፀረ-ህዝብ የሆነውን የብልፅግናን ስርዓት በመንቀል በምትኩ አድስ ስርዓት መትከል ነው። ከዚህ ውጭ በአማራ ህዝብ እና በልጆቹ ትግል ስም የተጀመረውን አብዮት አሳልፎ ለመስጠት የሚንገዳገድ ቡድን ካለ በፍፁም ተቀባይነት የለውም። ርባና ቢስ ሃሳብም ነው!! በዓለም ላይ በፈፅሞ ዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የነበሩ ስርዓቶች ሁሉ ለህግ እና ለፍትህ ቀርበዋል። በአማራ ህዝብ ላይ ፈፅሞ ዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ስርዓትም ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ እንታገላለን!! የአማራ ህዝብ ትግል በድርድር የሚመለስ ጥያቄ የለውም!! ስለዚህ ደም የተገበረበትን ትግል ልክ እንደ 1983 እና 2010 ትግሉን ለጥገናዊ ለውጥ ማመቻቼት መሞከር የጥቁር ክህደት ጅማሮ ነው። በዓለማችን ታሪክ የህልውና ትግል ከገጠማቸው አይሁዶች፣ሩዋንዳውያን መማር የሚቻለው ነገር ቢኖር ትግላቸውን በአሸናፊነት አጠናቀው ዘር አጥፊዎችን ለፍርድ ማቅረባቸውን ታሪክ ይናገራል። ስለዚህ በድርድር ስም ትግሉን ለመጥለፍ አደናጋሪ ሃሳብ እና ህዝብን ባልተገባ መንገድ ለማሳሳት መሞከር በፍፁም ነውረኝነት ነው። የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል በተወሰኑ ቡድኖች ሃላፊነት ብቻ የሚዘወር አይደለም!! የትግላችን ዕጣ ፋንታ ጫካ ያለው ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነ ሁሉ ሃላፊነት አለበት!! ሁኔታው "ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ" ሆነ እንጅ አፋብን በአሁኑ ስዓት ስለ አጠቃላይ የትግሉ ሁኔታ እና ቀሪ ስራዎች ስለማስተካከል ትኩረት ሰጥቶ መስራትን እንጅ ድርድርን አስመልክቶ በሚዲያ ቀርቦ አስተያየት መስጠት ጊዜው አይደለም!! አፋብን እንደ ድርጅት ሰራዊት ማዋሃድ፣ጠንካራ ድፕሎማሲ መስራት፣ጠንካራ ዘመቻዎችን ማቀድ፣ስትራቴጅካዊ ስራዎችን ማሰብ፣የፓለቲካ ፕሮግራም እና ማንፌስቶ ማዘጋጀት እንድሁም ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዓላማዎችን በመለየት ድርጅቱ እግር እንድትክል ማድረግ እንጅ የድርድር አጀንዳን በዓለም አቀፍ ማዲያ ቀርቦ ማስተጋባቱ አንድምታው ድርጅታዊ ጥርጣሬን መፍጠር ነው። ይሄ ዓይነት ልምምድ ከመርህ አንፃር ተቀባይነት የለውም። የብዙሃኑን ፍላጎትን ጭምር ያላከበረ ነው። ስለሆነም በድርጅታችን ውስጥ በህዝብ ግንኙነትም መምሪያውም ይሁን በድርጅቱ ዋና ዋና አመራሮች የሚተላለፉ ቃለ ምልልሶች በድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ ተግባር እና ሃላፊነታቸው ብቻ ስለሚፈቅድላቸው ድርጅታዊ ጥሰት መፈፀም ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ትግል አይሸጥም ፤አይለወጥም!! ትግላችን የአሸናፊነት ትርክትን በማንበር ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በመሆን አድስ ስርዓት የመትከል እንጅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፈፀመ ስርዓት ጋር በሚደረግ ድርድር የሚመለስ የህዝብ ጥያቄ የለንም!! ሰራዊት እና ህዝባችንም የድርድር ወረርሺኝን በሚያስተላልፉ አካላት ላይ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል። በአማራ ህዝብ ትግል እና በህዝባችን ጥያቄዎች ላይ ተላልፈው የተገኙትን ሁሉ ልክ እንደ ብልፅግናው ስርዓት በይፋ የምንታገላቸው ይሆናል። በአበው ብሂል "ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት" እንደሚባለው ሆኖ እውነትን፣ሃቅን፣ፍትህን እና የወጣንበትን የትግል ዓላማ በመጠምዘዝ ትግላችን ከሃዲዱ እንዲወጣ አድስ ትርክት ለማንበር መሞከር ታሪካዊ ጠላትነት መሆኑንም ለማስገንዘብ እንወዳለን!! ክቡር ለተሰውት ድል ለአማራ ህዝብ