uk
Feedback
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች 💡

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች 💡

Відкрити в Telegram

😊 እንኳን 😊 ወደ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ ... 🎙️ ይሄ ቻናል ያላወቃቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ ፣ በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት... . . . @FACT433 @FACTS_433ET | 2018 ዓ.ም 🇪🇹🇪🇷

Показати більше
2 610
Підписники
+224 години
+17 днів
-1330 день
Архів дописів
በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ለጉብኝት ወደ Belgium ሄዶ እዚያ ባደረገው ስብሰባ ከተጋበዙት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ሃሳብ ለመስጠት ተነሳች፡፡ ወጣቷ፦ “የርስዎ መንግሥት በጣም አስጠሊታ ነው።
በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ለጉብኝት ወደ Belgium ሄዶ እዚያ ባደረገው ስብሰባ ከተጋበዙት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ሃሳብ ለመስጠት ተነሳች፡፡ ወጣቷ፦ “የርስዎ መንግሥት በጣም አስጠሊታ ነው። ስርዓታችሁ አስጠሊታ፣ አካሄዳችሁ አስጠሊታ፣ ባለስልጣኖቻችሁ አስጠሊታ፣ ሁለመናችሁ አስጠሊታ ነው”። መለስ_ዜናዊ፦ “ጥሩ ነው:። አስጠሊታ ልንሆን እንችላለን። አሁን እዚህ የመጣነው ግን ለቁንጅና ውድድር አይደለም” @FACT_433 💡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሴቶች ዝምተኛ ወንድ ይወዳሉ ዝምተኛ ወንድ" ለሴቶች ማራኪ የሚሆንባቸው ምክንያቶች አሉ! ​1. የምስጢራዊነት ኃይል፦ ዝምተኛ ወንድ እንደ ተቆለፈ መጽሐፍ ነው። ሴቶች ደግሞ ተፈ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሴቶች ዝምተኛ ወንድ ይወዳሉ ዝምተኛ ወንድ" ለሴቶች ማራኪ የሚሆንባቸው ምክንያቶች አሉ! ​1. የምስጢራዊነት ኃይል፦ ዝምተኛ ወንድ እንደ ተቆለፈ መጽሐፍ ነው። ሴቶች ደግሞ ተፈጥሯዊ የሆነ የማወቅ ጉጉት ስላላቸው፣ "ምን እያሰበ ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በራሱ ትልቅ መስብዕና ይፈጥራል። ሁሉንም ነገር ዘክዝኮ የሚያወራ ወንድ በፍጥነት ሊሰለች ይችላል፤ ዝምተኛው ግን ሁልጊዜ አዲስ ነገር ፍለጋ ውስጥ ያቆያቸዋል። ​2. እንደ መልካም አድማጭ መታየቱ፦ ብዙ ሴቶች ስሜታቸውንና ሃሳባቸውን የሚረዳቸው አድማጭ ይወዳሉ። ዝምተኛ ወንድ ደግሞ ወሬ ስለማያቋርጥና በጥንቃቄ ስለሚያደምጥ፣ "በጣም ይረዳል" የሚል ግምት ይሰጠዋል። (ምንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ ዝምታው በሃሳብ ሌላ ዓለም ውስጥ ሆኖ ቢሆንም! 😅) ​3. የመረጋጋትና የጥንካሬ ምልክት፦ በማህበራዊ ስነ-ልቦና፣ ብዙ የማይለፈልፍ ወንድ እንደ በሳልና በራሱ እንደሚተማመን (Confident) ይቆጠራል። "ብዙ የሚናገር ብዙ ይሳሳታል፣ ዝም የሚል ግን ያውቃል" የሚል የተለመደ ግንዛቤ ስላለ፣ ዝምታው እንደ ጥንካሬ ይወሰድለታል። ​4. "Bad Boy" ቫይብ (Vibe)፦ ብዙውን ጊዜ በፊልሞች ላይ የምናያቸው ጀግኖች ዝምተኞች፣ ቁጥቦችና በድርጊት የሚያምኑ ናቸው። ይህ ምስል በብዙዎች አእምሮ ውስጥ "ዝምተኛ ወንድ ጠንካራ ነው" የሚል አመለካከት እንዲሰርጽ አድርጓል። @FACT_433 💡

ንጉሡ የአሰብ ወደብን ሰረተዉ አስረክበውን ነበር 😊 @FACT_433 💡
ንጉሡ የአሰብ ወደብን ሰረተዉ አስረክበውን ነበር 😊 @FACT_433 💡

የህንድ ሴቶች 11% የሚሆነውን የአለም ወርቅ ይይዛሉ - ከአሜሪካ ፣ አይኤምኤፍ ፣ ስዊዘርላንድ እና ጀርመን ጥምር ክምችት የበለጠ ነው። @FACT_433 💡
የህንድ ሴቶች 11% የሚሆነውን የአለም ወርቅ ይይዛሉ - ከአሜሪካ ፣ አይኤምኤፍ ፣ ስዊዘርላንድ እና ጀርመን ጥምር ክምችት የበለጠ ነው። @FACT_433 💡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆች አቴንስ፣ ግሪክ 1957/1958 ዓ.ም @FACT_433 💡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆች አቴንስ፣ ግሪክ 1957/1958 ዓ.ም @FACT_433 💡

ስፓርታከስ (Spartacus) በጥንታዊ ሮም ታሪክ ውስጥ እጅግ ዝነኛ የሆነውና የባሪያዎችን አመጽ የመራ ታዋቂ ግላዲያተር ነው። የእሱ ታሪክ ከጭቆና ወደ ነፃነት የሚደረግ ትግል ተምሳሌት ተደርጎ ይወ
+3
ስፓርታከስ (Spartacus) በጥንታዊ ሮም ታሪክ ውስጥ እጅግ ዝነኛ የሆነውና የባሪያዎችን አመጽ የመራ ታዋቂ ግላዲያተር ነው። የእሱ ታሪክ ከጭቆና ወደ ነፃነት የሚደረግ ትግል ተምሳሌት ተደርጎ ይወሰዳል። ​ ✅ ስፓርታከስ በትውልዱ ትሬሺያን (Thracian) — የአሁኗ ቡልጋሪያ አካባቢ ሰው ነው። መጀመሪያ ላይ በሮማውያን ሰራዊት ውስጥ ወታደር የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ግን አምልጦ በማመጹ ተይዞ በባርነት ተሸጠ። አካላዊ ጥንካሬ ስለነበረው ካፑዋ (Capua) በተባለች ከተማ በሚገኝ የግላዲያተሮች ማሰልጠኛ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ። ✅ ​በ73 ዓክልበ. ስፓርታከስና ሌሎች 70 የሚሆኑ ግላዲያተሮች የወጥ ቤት ቢላዎችንና መሣሪያዎችን በመያዝ ከማሰልጠኛ ቤቱ አመልጡ። ይህ ቀላል ሽሽት ወደ ትልቅ ጦርነት ተቀየረ፦ 🚛​የባሪያዎች ጦር፦ ስፓርታከስ በመንገዱ የሚያገኛቸውን ባሪያዎች ሁሉ ነፃ እያወጣ ጦሩን አጠናከረ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው ከ120,000 በላይ የሚሆን ተዋጊዎችን ማሰባሰብ ቻለ። ✅​የሮምን ሰራዊት ማሸነፍ፦ የሮም መንግሥት መጀመሪያ ላይ እንደ ቀላል ሽፍታ ቢያየውም፣ ስፓርታከስ ግን የሮምን ታዋቂ ጄነራሎችና ሰራዊት በተደጋጋሚ በማሸነፍ መላው ሮምን በድንጋጤ አንቀጥቅጦ ነበር። @FACT_433 💡

ግላዲያተሮች ከአራዊት ጋር የሚጋጠሙበትም ትርኢት ነበር። ይህ ዓይነቱ ውጊያ ቬናቲዮ (Venatio) ተብሎ ይጠራል። ​ስለ አንበሳና ሰው ግጥሚያ ጥቂት አስገራሚ ​1. ቤስቲያሪ (Bestiarii) -
ግላዲያተሮች ከአራዊት ጋር የሚጋጠሙበትም ትርኢት ነበር። ይህ ዓይነቱ ውጊያ ቬናቲዮ (Venatio) ተብሎ ይጠራል። ​ስለ አንበሳና ሰው ግጥሚያ ጥቂት አስገራሚ ​1. ቤስቲያሪ (Bestiarii) - የአራዊት ተዋጊዎች ​ከአራዊት ጋር እንዲዋጉ የሚደረጉ ሰዎች "ቤስቲያሪ" ይባላሉ። እነዚህ ሰዎች እንደ መደበኛ ግላዲያተሮች ክብር አይሰጣቸውም ነበር። ብዙ ጊዜ በሞት የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ወይም እስረኞች ምንም ዓይነት መከላከያ ሳይሰጣቸው ከአንበሳ ጋር እንዲጋጠሙ ይደረግ ነበር (ይህም "Damnatio ad Bestias" ወይም ለአራዊት መሰጠት ይባላል)። ✅​ሮማውያን ለዚህ ትርኢት ሲሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አንበሶችን፣ ነብሮችንና ዝሆኖችን ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ ያስመጡ ነበር። አንበሶቹ ግልፍተኞች እንዲሆኑና በሰው ላይ እንዲዘሉ ለማድረግ ለቀናት በጨለማ ክፍል ውስጥ ተርበው እንዲቆዩ ይደረጋል። ✅​አንበሶቹ ወደ ሜዳው የሚገቡት በበሩ በኩል ብቻ አልነበረም። በኮሎሲየም ወለል ስር 28 የሚሆኑ በእጅ የሚሳቡ መሳቢያዎች (Lifts) ነበሩ። አንበሶቹ በድንገት ከመሬት ስር ብቅ እያሉ ተዋጊውን እንዲያስደነግጡት ይደረጋል፣ ይህም ለተመልካቹ ትልቅ ትርኢት ነበር @FACT_433 💡

<የሰው ልጅ ሕያው ምሳሌ> ይህ ፎቶ የተነሳው በቱርክ ፎቶግራፍ አንሺ ነው። የፎቶው መልእክት ይች ትንሽ ልጅ በአንድ የቱርክ መንደር የምትኖር ፍየል ጠባቂ(እረኛ) ናት  ታዲይ ይች
<የሰው ልጅ ሕያው ምሳሌ> ይህ ፎቶ የተነሳው በቱርክ ፎቶግራፍ አንሺ ነው። የፎቶው መልእክት ይች ትንሽ ልጅ በአንድ የቱርክ መንደር የምትኖር ፍየል ጠባቂ(እረኛ) ናት  ታዲይ ይች ልጅ ከምትጠብቃቸው ፍየሎች መሀል ድንገት አንዷ ፍየል ትወልዳለች የወለደችውን ፍየል ከምትጠብቅበት ቦታ ወደ ቤቷ ለመውሰድ ትፈልጋለች ይሁንና መንገዱ በረዶ ስለነበር የወለደችው እናትና ልጇ በቅዝቃዜው ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ ብላ በማሰቧ የፍየሏንና የሕፃኑን ሕይወት ለመታደግ  እናቲቱን ፍየል እሷ  በትከሻዋ ተሸክማ አዲስ የተወለደውን ግልገል ደግሞ ውሻዋን አሸክማ ወደቤታቸው ለመጓዝ ቀዝቃዛውን ተራራ እየወጡ የሚያሳይ ፎቶ ነው። እናም ይህ ይህ ፎቶ የሰው ልጅ ሕያው የመልካምነት ምሳሌ ነው ተብሎለታል እኛ ሰው በየ መንገዱ ክረምት ከበጋ ያውም ያለ በቂ ልብስ  ውሎ ሲያድር ይበርደው አይመስለንም እሷ ግን ፍየሏ ስለወለደች ብቻ እናቲቱም የወለደችውም ልጅ  ሊቀዘቅዛቸው ይችላል በዚህም የተነሳ ጉዳት ላይ ሊወድቁ  ይችላሉ ብላ በማሰብ  በልጅነት አቅሟ አዝላ ያውም በበረዶ የተሞላውን ተራራ ከቅዝቃዜ ጋር እየታገለች ተጉዛለች።  ልዩነታችን ሰው መሆናችን ላይ ነው ሰው ስትሆን እንኩዋንን ለሰው ልጅ ለእንሰሳትም ታዝናለህ እውነትም የሰው ልጅ የመልካምነት ህያው ምሳሌ !!! @FACT_433 💡

ከፍጥረት ሁሉ አደገኛው ፍጥረት ማን ይመስላቸዋል ሴት ልጅ ናት ወገኔ ሴትን ልጅ በጣም ተጠንቀቅ አለም በሴት ጠፍታ በሴት ብትድንም እናትም እህቶቻችን ሴቶች ቢሆንም ተፈጥሯቸው ግን እጅግ አደገኛና ሀ
ከፍጥረት ሁሉ አደገኛው ፍጥረት ማን ይመስላቸዋል ሴት ልጅ ናት ወገኔ ሴትን ልጅ በጣም ተጠንቀቅ አለም በሴት ጠፍታ በሴት ብትድንም እናትም እህቶቻችን ሴቶች ቢሆንም ተፈጥሯቸው ግን እጅግ አደገኛና ሀያል እንደሆኑ የታሪክ መዛግብትም ይነግሩናል። የስነ-ልቦና አባት ተብሎ የሚታወቀው Sigmund Frued ለ36 ዓመት ስለሴት አጥንቶ በመጨረሻም አንድ ነገር ተናገረ "የሴትን ልጅ ትክክለኛ ስሜት ማወቅ አይቻልም 99 chamber አላቸው አለን ታላቁን በአለቅኔ ፑሽኪንን ለዚህ እንደ ምሳሌ ያነሳል ፑሽኪንን ለሚስቱ ሲል ከፈረንሳይ ልዑል ጋር ገጥሞ በመጨረሻም በልኡል ሰይፍ ከተቀላ በኋላ የፑሽኪን ሚስት በፍቅር አይን ልኡሉን አግባታዋለች። ሲግመንድ እንደሚለው የሴትን ስሜት መረዳት አትችልም 100 ወዳጆች ቢኖሩዋት ለመቶውም ተመሳሳይ የፍቅር ስሜትና ፍላጎት ማሳየት ትችላለች። ለየትኛው ጥሩ የፍቅር ስሜት እንዳላት ከእራሷ ውጪ ማንም በትክክል አያውቅም! የግብፆን ንግስት ኪሊዮፓትራን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል እሷ ላይ ብዙ ባታሊዮን ጦር ያዘመተውን ጄነራል አንድም ጦር ሳታዘምት ብቻዋን ሴትነቷ በሰጣት ተፈጥሮ እንዴት እንደምትመልሳቸው መዛግብትን ማገላበጥ በቂ ነው! የሴትን ተፈጥሮ የተረዳው የእስራኤሉ ሞሳድ እንኳን አብዛኛውን የስለላ ተቋም ምልምሎች ሴቶች ናቸው። የእኛም ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ለስለላ ተግባር እንደ ታንጉት የአሉትን ሴቶችን ይጠቀሙ ነበር። @FACT_433 💡

በ 1962አ.ም። አንድ የብሪታንያ ጋዜጣ አዘጋጅ Brendon Grimshaw የተባለ ሰው... ሰዎች በቡና ጠረጴዛ ላይ ብቻ የሚነጋገሩትን ሕልም መሳይ ወሬ እሱ ህይወቱ ላይ በእውነት አደረገው። ስራው
1962አ.ም። አንድ የብሪታንያ ጋዜጣ አዘጋጅ Brendon Grimshaw የተባለ ሰው... ሰዎች በቡና ጠረጴዛ ላይ ብቻ የሚነጋገሩትን ሕልም መሳይ ወሬ እሱ ህይወቱ ላይ በእውነት አደረገው። ስራውን ተወ። የከተማ ምቾትን ተወ። የተረጋጋ ደመወዝን ተወ። እና በ8,000 ፓውንድ ብቻ በሲሼልስ ያለችውን ትንሽ የተተወች ማንም የማያያትን Moyenne የምትባል ደሴትን ገዛ። ሰዎች “ገነት ገዛ” ብለው አስቡ። ነገር ግን ያገኘው ገነት አልነበረም —አስፈሪ ፀጥታን ነበር። ደረቅ መሬት። የተበተነ ቁጥቋጦ። ውሃ የሌለው አካባቢ። የሕይወት ምልክት የሌለው ቦታ። ግን እሱ ያየው አስፈሪነቱን አልነበረም — እድል ነበር የተመለከተው። ለ40 ዓመታት ባልተቋረጠ ጥረት.... በገዛ እጁ ከ16,000 በላይ ዛፎች ተከለ። 3 ኪ.ሎ ሜትር የእግር መንገድአስፋልት አነጠፈ በኮሪደሮቹ ላይ በድንጋይ ተቀረፁ ውብ ስዕሎችን ሳለ ። ከ100 በላይ ጥንታዊና ታሪክ ያላቸውን ግዙፍ ኤሊዎችን አመጣ። ቀስ በቀስ… ወፎች መጡ። እፅዋት በቀሉ። ደሴቲቱ ከሞተች መሬት ወደ ሕያው ሥነ-ምህዳር ተለወጠች። አንድ ሰው ብቻ ምድረ በዳን ገነት አደረገ። ከዛ........... የደሴቲቱ ውበት ወሬ ሆነ። አንድ የሳውዲ ልዑል 50 ሚሊዮን ዶላር አቀረበ። Brendon Grimshaw ፈገግ ብሎ። “እምቢ” አለ። ቀናት አልፈው ወሬው ተመለሰ። “100 ሚሊዮን አድርጌ እሰጥሃለሁ… ሽጥ!” በዓለም የብዙ ሰዎች ሕይወት የሚቀይር ገንዘብ። እሱ ግን አንድ ቃል ብቻ አለ፦ በድጋሚ “እምቢ።” አልሸጥም ብሎ ተናገረ መጨረሻ ላይ.. “200 ሚሊዮን ዶላር ወሬ ሳታበዛ ሽጥ!” ተባለ። 200 ሚሊዮን! ሰዎች ይህን ቁጥር ለመጠራት እንኳ ይንቀጠቀጣሉ። እሱ ግን ምንም ሳይመስለው በኩራት “አሻፈረኝ አልሸጥም ብሎ መለሰ። ይህ ቦታ የሚሊየነሮች የግል መጫወቻ አይሆንም። ለሁሉም ሰው የተከፈተ ብሔራዊ ፓርክ ይሆናል።” አለ 2009 ላይ ሕልሙ እውን ሆነ። Moyenne ደሴት ብሔራዊ ፓርክ ሆነች። እሱ..በ2012 ሲሞት ባንክ ሂሳቡ ውስጥ ትልቅ አልነበረም። ግን የማይሸጥ ነገር ለህዝብ ትቶ ሞተ፦ ተፈጥሮ። ሕይወት። ክብር። ሰዎች ገንዘብ ይተዋሉ። እሱ ግን ዘላለማዊ ርስት ተወ። ብዙዎች በ Brendon Grimshaw ውሳኔ ተደነቁ ግማሾቹ የትክክለኛ ሰው መሆን ውሳኔ ብለው ክብር ሲሰጡት ሌሎቹ ግን ለቤተሰቦቹ እና ለልጆቹ ያላሰበ ዝናን ፈልጎ የልጆቹ ህይወት ሜዳ ላይ ትቶ የሄደ እንዳይለወጡ ማነቆ የሆነ ራስ ወዳድ አባት ብለው ዘለፋት.... እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ? 8ሺህ ፖውንድ የገዛችሁትን ደሴት 200ሚሊየን ዶላር ሽጣችሁ ለልጆቻችሁ ሀብት ንብረት ታወርሳላችሁ ወይስ ለሰፊው ማህበረሰብ በማሰብ ለህዝብ አውርሳችሁ ትሞታላችሁ?🙄 እኔ ከልጆቼ ማህበረሰብ ይበልጥብኛል ያለኝን ነገር ለማህበረሰቡ ለህዝብ አውርሼ እሞታለሁ እናንተስ?😂😂😂😂😂

ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ቁስ ፡ ተሰርቶ ሰላሳና አርባ አመታት ፡ ምናልባትም ከዛም በላይ የሚቀመጥ በመሆኑ አንዳንድ እቃዎቹ ከወርቅ መሰራት አለባቸው ፡ የወርቅ ሽቦ ፡ ከንፁህ ወርቅ የተሰሩ አንዳ
ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ቁስ ፡ ተሰርቶ ሰላሳና አርባ አመታት ፡ ምናልባትም ከዛም በላይ የሚቀመጥ በመሆኑ አንዳንድ እቃዎቹ ከወርቅ መሰራት አለባቸው ፡ የወርቅ ሽቦ ፡ ከንፁህ ወርቅ የተሰሩ አንዳንድ እቃዎች ። ትናንሽ የወርቅ ብሎንም ሊሆን ይችላል ። ..... ሌላው እዚህ ውስጥ የብርና የመዳብ ማእድናትም አሉ ። እንዲሁም ከፍተኛ ሙቀት ያለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ እቃዎች የሚሰሩት ከፕላቲኒየም ነው ። እንደዛ ካልሆነ ሊቀልጡ ይችላሉ ። .... ዋና የሚባለው ክፍል ደግሞ የሚሰራው ፡ ክብደቱ ከአልሙኒየም በሚቀል እና ከብረት ብዙ እጅ በሚጠነክር ቤሪየም ከሚባል ውድ የብረት አይነት ነው ። ...... ከነዚህ ሁሉ ማእድናት የተሰራው ይህ የሰአት ሞተር የሚመስል እቃ ፡ ሌላ ሳይሆን ፡ እያንዳንዱ ሚሳይል ውስጥ የሚገኝ ፡ የሚሳይል ማሰቢያ አእምሮ ወይም በሚሳይል ውስጥ የሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ ክፍል ነው ። .... የዚህ እቃ አሰራር እንደየ ሚሳይሉ አይነትና ፡ ወቅታዊነት እንዲሁም እንደ ሰሪው ሀገር ቢለያይም ፡ ከሆነ ቦታ የተተኮሰ ሚሳይል ፡ ከተላከበት ቦታ ርቀት አንጻር ቦታውን ሳይረሳ ፡ አቅጣጫውን ሳይስት ፡ ብዙ ሺህ ኪሎሜትሮችን አቋርጦ እየሄደ ኢላማውን የሚመታው በነዚህና ፡ መሰል ኮምፒውተሮች እያሰበ ነው ። ዋሲሁን ተስፋዬ @FACT_433 💡

✅ቀኑን ሙሉ ከቤት ጠፍቶ ሲጫወት ነው የዋለው ፡ እና ልክ እንደሁሌው ዛሬም እናቱ ልጄ ጠፋ ብላ በፍለጋ ሰፈሩን ስታካልል እንደቆየችና. .. ቤት ሲገባ . .. " ጎረምሳው. .መጣህ ? " ተብሎ ምን
ቀኑን ሙሉ ከቤት ጠፍቶ ሲጫወት ነው የዋለው ፡ እና  ልክ እንደሁሌው ዛሬም እናቱ ልጄ ጠፋ ብላ በፍለጋ ሰፈሩን ስታካልል  እንደቆየችና. .. ቤት ሲገባ . .. " ጎረምሳው. .መጣህ ? "  ተብሎ ምን እንደሚጠብቀው ከልምድ  ያውቃል ። 😔✅ዛሬ ግን ከሚጠብቀው ዱላ ለማምለጥ ፡ ለማገዶ እንዲሆን ይቺን  ጭራሮ ለቃቅሞ  እየሄደ ነው እንግዲህ  ❤️ @FACT_433 💡

#አለቃገብረሃና በአንድ ወቅት አለቃ ገብርሀና ተራራ ላይ ተሸምጦ በዜማ እያንጎራጎረ ባለበት ሰሀት ከሩቅ አንድ ገበሬ አህያውን መሸከም እስኪያቅታት አሸክሞ በያዘው ጎረብ እየገረፋት ይመለከታል።ይሄኔ
#አለቃገብረሃና በአንድ ወቅት አለቃ ገብርሀና ተራራ ላይ ተሸምጦ በዜማ እያንጎራጎረ ባለበት ሰሀት ከሩቅ አንድ ገበሬ አህያውን መሸከም እስኪያቅታት አሸክሞ በያዘው ጎረብ እየገረፋት ይመለከታል።ይሄኔ አለቃ ገብርሀና ይበሳጫል (እየሱስ በአህያ ተሰቅሎ ስለተጓዘ ለአህያ ትልቅ ክብር አለው) እናም ወደ ገበሬው ተጠግቶ"ለምን ትገርፈዋለህ"ይለዋል ገበሬውም"ቤቴ እሩቅ ነው።ይህ አህያም አልንቀሳቀስ አለ ታድያ ምን ላርግ ልግረፈው እንጂ"ይለዋል አለቃም ካሰበ ቡሀላ"ለመሆኑ እንዲህ የከበደው ምን ብታሸክመው ነው" ገበሬውም"ሚጥሚጣ ነው ሚጥሚጣ" አለቃ ወየም ሳቅ አለና"እህ ዝም ብለህ አደል የምትዋቃው በል ከተሸከመችው ሚጥሚጣ ዛቅ አርግና ቂጧን ቀባት ይለዋል"ገበሬውም ዛቅ አርጎ ይቀባታል።ይሄኔ አህያዋ ጥላው ተፈተለከች ገበሬው ሊደርስባት ቢል አቅቶት ቀረ ይሄኔ ወደ አለቃ ገብርሀና ይመለስና"በምን ልድረስባት ጥላኝ ተፈተለከች"ይለዋል አለቃ ሆየም"እህ በሱ ሚጥሚጣ እጅህ ቂጥህን ነካ አርገው"ይለዋል።ገበሬውም ሱሬውን አውልቆ ቅብት አረገው ይሄኔ እንደጉድ ተፈትልኮ አህያዋን ቀድሟት ቤቱ ገባ😁 ምንጭ :- የሳተርን❤️ @FACT_433 💡

Charli chapli በህይወት እንደነበረ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ 4ቱ ......... 1) "ወደምድር እየተመለከትክ ቀስተደመናን መመልከት አትችልም፤ምን ችግሮችና ፈተና ቢበዛብ አንገትህን ቀና
Charli chapli በህይወት እንደነበረ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ 4ቱ .........
1) "ወደምድር እየተመለከትክ ቀስተደመናን መመልከት አትችልም፤ምን ችግሮችና ፈተና ቢበዛብ አንገትህን ቀና አድርገህ ጥሩውን ነገር ለመመልከት ሞክር" 2) " ያለፈገግታ ያሳለፍከው ቀን የባከነ ቀን ነው፤ሁሌም ፈገግ በል " 3) " ዝናባማ ቀናቶች ይመቹኛል፤ ማንም ማልቀሴን አያስተውልም " 4) " የኔ የልብ ጓደኛ መስታወቴ ነው፤እኔ እያለቀስኩ እሱ በጭራሽ አይስቅም " የቱ ተመቻቹ ? 1) 👏      2) 👌     3) 💔    4) ❤️ @FACT_433 💡

የሰው ልጅ ሲሞት በሰውነቱ ውስጥ ዋና ዋና ባዮሎጂካዊ እና ኬሚካዊ ለውጦች በቅደም ተከተል ይከናወናሉ፦ ​ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች (The Stop) ​ልብ መምታቱን ሲያቆም፣ የደም ዝውውር ወዲያውኑ ይ
የሰው ልጅ ሲሞት በሰውነቱ ውስጥ ዋና ዋና ባዮሎጂካዊ እና ኬሚካዊ ለውጦች በቅደም ተከተል ይከናወናሉ፦ ​ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች (The Stop) ​ልብ መምታቱን ሲያቆም፣ የደም ዝውውር ወዲያውኑ ይገታል፡- ​ኦክስጅን ማጣት፦ ሴሎች ኦክስጅን ማግኘት ያቆማሉ። በዚህም ምክንያት ኃይል (ATP) ማምረት አይችሉም። ​የአንጎል መሞት፦ የአንጎል ሴሎች ከ3 እስከ 5 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ኦክስጅን ካላገኙ መሞት ይጀምራሉ። ​የሙቀት መቀነስ (Algor Mortis)፦ የሰውነት ሙቀት በየሰዓቱ በግምት በ0.8°C መጠን እየቀነሰ በመሄድ ከአካባቢው አየር ሙቀት ጋር ይተካከላል። መገርጣት (Pallor Mortis)፦ ደም መዘዋወር ስለሚያቆም በ15 ደቂቃ ውስጥ ቆዳ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ ይይዛል። ​ደም መርጋት፦ ደም በመሬት ስበት ምክንያት ወደ ታችኛው የሰውነት ክፍል ይወርዳል። ይህም በቆዳ ላይ ወይንጠጅ ቀለም እንዲታይ ያደርጋል። ​መገተር ከ2 እስከ 6 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የሰውነት ጡንቻዎች ይገተራሉ። ይህ የሚሆነው ጡንቻን የሚያላሉ ኬሚካሎች ስለሚጠፉ ነው። @FACT_433 💡

​አንድ አስከሬን ሳይቀበር ሜዳ ላይ ቢቀመጥ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ነፍሳትና ባክቴሪያዎች ይወርሩታል። በአፈር ውስጥ ከተቀበረ ግን እንደ አፈሩ ዓይነት፣ እንደ እርጥበቱና እንደ ሙ
አንድ አስከሬን ሳይቀበር ሜዳ ላይ ቢቀመጥ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ነፍሳትና ባክቴሪያዎች ይወርሩታል። በአፈር ውስጥ ከተቀበረ ግን እንደ አፈሩ ዓይነት፣ እንደ እርጥበቱና እንደ ሙቀቱ መጠን አጽም (አጥንት) ለመሆን ከጥቂት ወራት እስከ ዓመታት ሊፈጅበት ይችላል። አስከሬን አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛ ድምፅ (እንደ ማቃሰት ወይም መጮህ) ሊያወጣ ይችላል። ይህ ግን ነፍስ ስላለች ሳይሆን፣ በሰውነት ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች ጋዝ ስለሚያመርቱና ያ ጋዝ በጉሮሮ ወይም በሳንባ በኩል ወጥቶ የድምፅ አውታሮችን ስለሚያርገበግባቸው የሚፈጠር ክስተት ነው @FACT_433 💡

​ድመቶች በጣም ጠባብ በሆኑ ቀዳዳዎች ውስጥ አልፈው መሄድ ይችላሉ። ይህ ሊሆን የቻለው አከርካሪ አጥንታቸው እጅግ ተለዋዋጭ (Flexible) ስለሆነና የትከሻ አጥንታቸው (Clavicle) ከሌሎች አጥ
+1
​ድመቶች በጣም ጠባብ በሆኑ ቀዳዳዎች ውስጥ አልፈው መሄድ ይችላሉ። ይህ ሊሆን የቻለው አከርካሪ አጥንታቸው እጅግ ተለዋዋጭ (Flexible) ስለሆነና የትከሻ አጥንታቸው (Clavicle) ከሌሎች አጥንቶች ጋር በጡንቻ እንጂ በአጥንት ባለመያያዙ ነው። ይህም ሰውነታቸውን እንደፈለጉ እንዲያጠፉ ይረዳቸዋል። ​ ✅የመስማትና የማሽተት ብቃትመስማት፦ ድመቶች ከሰው ልጅም ሆነ ከውሻ የተሻለ የመስማት ችሎታ አላቸው። በተለይ አይጦችና ሌሎች ትናንሽ እንስሳት የሚያወጡትን በጣም ቀጭን ድምፅ (Ultrasonic sounds) መለየት ይችላሉ። ​ጆሮ፦ የድመት ጆሮ ወደ 180 ዲግሪ ሊዞር የሚችል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ 32 የተለያዩ ጡንቻዎችን ይጠቀማሉ። ​ ✅"ሚያው" (Meow) የሚለው ድምፅ ​የሚገርመው ነገር፣ አዋቂ ድመቶች እርስ በእርሳቸው ለመግባባት "ሚያው" አይሉም። ይህንን ድምፅ የሚያወጡት ከሰው ልጆች ጋር ለመግባባት ብቻ ነው። እርስ በእርሳቸው ለመግባባት ግን የሰውነት እንቅስቃሴን፣ ሽታንና ሌሎች ትናንሽ ድምፆችን ይጠቀማሉ። ​ ✅አይናቸውና ጨለማ ​ድመቶች በጭለማ ውስጥ ለማየት ከሰው ልጅ በ 6 እጥፍ ያነሰ ብርሃን ብቻ ይበቃቸዋል። በአይናቸው ውስጥ ያለው Tapetum Lucidum የተባለ ክፍል ብርሃንን አንፀባርቆ እንዲመለስ ስለሚያደርግ፣ በሌሊት አይናቸው ሲበራ ይታያል። @FACT_433 💡

የነብር ቆዳ ላይ ያሉት ነጠብጣቦች "ሮዜትስ" (Rosettes) ይባላሉ። እነዚህ ምልክቶች በቁጥቋጦዎችና በዛፍ ጥላዎች ውስጥ ሳይታዩ ለመደበቅ (ለመሸሸግ) ይረዱታል። ይህም አደኑን ሳያስተውል እስከ
የነብር ቆዳ ላይ ያሉት ነጠብጣቦች "ሮዜትስ" (Rosettes) ይባላሉ። እነዚህ ምልክቶች በቁጥቋጦዎችና በዛፍ ጥላዎች ውስጥ ሳይታዩ ለመደበቅ (ለመሸሸግ) ይረዱታል። ይህም አደኑን ሳያስተውል እስከ ሦስት ሜትር ድረስ ተቀርቦ እንዲያጠቃ ያስችለዋል። @FACT_433 💡

✅የአዞ እንባ" የሚለው አባባል የመጣው አዞዎች ሲመገቡ አይናቸው እንባ ስለሚያወጣ ነው። ይህ ግን ከሀዘን የመጣ ሳይሆን፣ ምግብ በሚውጡበት ጊዜ አየር በሳይነስ ቀዳዳዎቻቸው ውስጥ ስለሚያልፍና የእንባ
የአዞ እንባ" የሚለው አባባል የመጣው አዞዎች ሲመገቡ አይናቸው እንባ ስለሚያወጣ ነው። ይህ ግን ከሀዘን የመጣ ሳይሆን፣ ምግብ በሚውጡበት ጊዜ አየር በሳይነስ ቀዳዳዎቻቸው ውስጥ ስለሚያልፍና የእንባ እጢዎቻቸውን ስለሚጫነው የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ሂደት ነው @FACT_433 💡

✅​ሰሜን ኮሪያ የውጭ ማዳበሪያ መግዛት ስለማትችል፣ መንግስት እያንዳንዱ ዜጋ የተወሰነ መጠን ያለው "የሰው ሰገራ" ለግብርና ስራ እንዲያበረክት ያስገድዳል። ይህንን ኮታ ለመሙላት ሰዎች ሰገራ እስከ
✅​ሰሜን ኮሪያ የውጭ ማዳበሪያ መግዛት ስለማትችል፣ መንግስት እያንዳንዱ ዜጋ የተወሰነ መጠን ያለው "የሰው ሰገራ" ለግብርና ስራ እንዲያበረክት ያስገድዳል። ይህንን ኮታ ለመሙላት ሰዎች ሰገራ እስከ መሻሻጥ እና እስከ መስረቅ የሚደርሱበት ጊዜ አለ ይባላል። ✅የ"ቅጣት" ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ​በሰሜን ኮሪያ የሚሸጡ ሬዲዮዎች እና ቴሌቪዥኖች የሚመረቱት በመንግስት ጣቢያዎች ላይ ብቻ "Lock" ተደርገው ነው። የውጭ ሀገር ፕሮግራም እንዳያሳዩ ተደርገው ነው የሚሰሩት። አንድ ሰው በድብቅ የውጭ ጣቢያዎችን ለማዳመጥ ሬዲዮውን ቢከፍትና ፖሊስ ቢይዘው ከባድ እስራት ይጠብቀዋል። ✅የአሁኑ መሪ አባት ኪም ጆንግ ኢል ፊልም በጣም ይወዱ ነበር። የሰሜን ኮሪያ ፊልሞች ስላልጣሟቸው፣ አንድ የታወቀ የደቡብ ኮሪያ ፊልም ዳይሬክተር እና ባለቤቱን (ተዋናይት) በድብቅ አፍነው ወደ ሰሜን ኮሪያ አስመጡ። ለስምንት ዓመታት እዚያው አስረው የፈለጉትን አይነት ፊልም እንዲሰሩላቸው አድርገዋል። በኋላ ላይ ነው ዳይሬክተሩ አምልጦ ወደ ኦስትሪያ የገባው። @FACT_433 💡