cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

መንፈሳዊ ግጥም

Рекламні дописи
314
Підписники
+324 години
+367 днів
+4130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

++ ኪነጥበብ - እንካ ሰላምትያ! (ድንቅ መንፈሳዊ እንካ ሰላምትያ) (1): እንካ ሰላምታ? (2): በምንትያ (1): በመሰንቆ (2): ምን አለ በመሰንቆ? (1): ለሰው ይበጀዋል መኖር በቤቱ ፈጣሪውን አውቆ። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ? (1): በደውል (2): ምን አለ በደውል? (1): መሆን ያስፈልጋል የዋህ እንደ ርግብ ብልህ እንደ እባብ። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በከበሮ (2): ምን አለ በከበሮ? (1): ዘመንም ህይወትም አብሮ ይቀየራል ከአምና ዘንድሮ። ፣ (1): እንኪ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በጽላት (2): ምን አለ በጽላት? (1): ለተዋህዶ እናት ለቅድስቷ ቤት ጠበቃ ሁንላት። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በሰረገላ (2): ምን አለ በሰረገላ? (1): ፊተኞች ስንባል እንዳንሆን ኋለኛ መትጋት ያስፈልጋል ከእንግዲህ በኃላ። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በጧፍ (2): ምን አለ በጧፍ? (1): አይዞህ በርታ ተነስ አምላክ ይመራሃል የህይወትህን ሰልፍ። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በጉልላት (2): ምን አለ በጉልላት? (1): የቅዱሳን ፀሎት ምልጃ በረከት ትልቅ ዋጋ አላት። ፣ (1): እንካ ሰላምትያ (2): በምንትያ (1): በሻማ (2): ምን አለ በሻማ? (1): ምልጃ በረከቷ ሁሌም አይለየን የሰማእቷ አርሴማ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። @kinexebebe
Показати все...
👍 2
Показати все...
TikTok · ORTHODOX POEM

Check out ORTHODOX POEM’s video.

1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ለልቤ ጥያቄ ዉስጤን ላስጨነቀዉ ይዘገያል እንጂ እግዚአብሔር መልስ አለዉ🙏❤🙏❤🙏❤
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
❤❤❤እንኳን ደስ አላቹ ቤተሰብ🙏🙏🙏 በ 5 ቀን ዉስጥ 300 ቤተሰብ ማፍራት ችለናል በእናንቴ እርዳታ አሁንም ሁላቹም Share እያደረጋቹ ጉዞ ወደ 1K ግሩፑን ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇👇👇 ግጥም ካላቹ መላክ ይቻላል 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Diriba12
Показати все...
👉ስማኝ ልጄ!!! ❇️ ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!! ❇️ ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!! ❇️ ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!! ❇️ አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!! ❇️ ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!! ❇️ ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!! ❇️ ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!! ❇️ ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!! ❇️ ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!! ❇️  ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሳትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!! ❇️ ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!! ❇️ እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!! ❇️ አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!! ❇️  ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!! ❇️ ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!! ❇️ አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!
Показати все...
👍 2
በዚህ ግሩፕ መንፈሳዊ ገጥም ብቻ ስለምናቀርብ Join በማረግ ይከታተሉን🙏🙏🙏
Показати все...
👍 1
#ስንቶቻቹ ናችሁ የሐዋርያትን ፆም እየፆማቹ ያላቹ?     አይ የኔ ነገር!!! ================== እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ ስዋሽ ስቀጥፍ ህግን ስተላለፍ ስሰድብ ሳደማ የሰው ስጋ ሳማ ባይኔ ሳመነዝር የሰው ሰው ሳማትር ገላዬን ሳራቁት አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት ስረሳ ስቃይህን መስቀል ህማምህን ያን ሁሉ ግርፋት ነብሴ ሳያስጨንቃት አይ እኔ በሀሰት ስመሰክር በሀጢያት ስዳክር ለማይሞላ ኑሮ ሳልሻል ዘንድሮ ፆሙ ተጋመሰ ጊዜው ተጋመሰ ጌታ ሆይ አቤቱ አስበኝ ለንሰሀ አብቃኝ እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው "ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" የንሰሀ ህይወት ይስጠን! _______
Показати все...
👍 4
#ሳልፆም_ሊፈሰክ_ነው። @Mgetem     አይ የኔ ነገር!!! ================== እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ ስዋሽ ስቀጥፍ ህግን ስተላለፍ ስሰድብ ሳደማ የሰው ስጋ ሳማ ባይኔ ሳመነዝር የሰው ሰው ሳማትር ገላዬን ሳራቁት አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት ስረሳ ስቃይህን መስቀል ህማምህን ያን ሁሉ ግርፋት ነብሴ ሳያስጨንቃት አይ እኔ በሀሰት ስመሰክር በሀጢያት ስዳክር ለማይሞላ ኑሮ ሳልሻል ዘንድሮ ፆሙ ተጋመሰ ጊዜው ተጋመሰ ጌታ ሆይ አቤቱ አስበኝ ለንሰሀ አብቃኝ እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው "ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" የንሰሀ ህይወት ይስጠን! _______ @Mgetem @Mgetem_bot @Mgetem_group
Показати все...
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 .የመጨረሻ ዙር ግጥም ውድድር ተማፀኚ ከስሁታን መዳፎች ላይ የምትለምኝ የፅድቅ መባ ለአንዲት ቀን ሳት'ቀኝ መስከረምሽ ስንቴ ጠባ ዝንብ አረፈ ከአደይሽ እሸት ወይንሽ እረገፈ የከፋ ቀን ተደረበ መስከረምሽ እያለፈ በትርሽን ወደሽ ሰጥተሽ ሙሴሽ ቢሆን ራስ ገፊ ህዝብሽ እንደሁ ደርሶ ተጓዥ እንዴት ይሆን የምታልፊ የንግስናው ዘመን አፄ ፈርዖንሽ በትር ይዟል ባህር ሰንጥቅ ያልሽው ሙሴ ሀጥያት አንቆት ይሄው ፈዟል የዮቶር ቤት ቤተ ሳባ የኩሽ ምድር ጥቁር መሬት ከንቦችሽ ከናፍር ላይ መፍሰስ ይዟል ይሄው እሬት አንች ጦቢያ ሀዘን ውጦሽ ሳቅሽ ሞቷል እጅሽ ታጥፏል መሰል ዛሬ አንጀትሽም ማረን ትቷል አትታክች ለተማፅኖ አበፅዒ መዳፍሽን መሀረነ በይ ዘወትር አታስነፊ ከንፈርሽን ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን) ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t.me/zemaritnsae 🏆🏆🏆🏆🏆 ግጥም ለመላክ . 👇👇👇 . @Tins7
Показати все...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 .የመጨረሻ ዙር ግጥም ውድድር ተማፀኚ ከስሁታን መዳፎች ላይ የምትለምኝ የፅድቅ መባ ለአንዲት ቀን ሳት'ቀኝ መስከረምሽ ስንቴ ጠባ ዝንብ አረፈ ከአደይሽ እሸት ወይንሽ  እረገፈ የከፋ ቀን ተደረበ መስከረምሽ እያለፈ በትርሽን ወደሽ ሰጥተሽ ሙሴሽ ቢሆን ራስ ገፊ ህዝብሽ እንደሁ ደርሶ ተጓዥ እንዴት ይሆን የምታልፊ የንግስናው ዘመን አፄ ፈርዖንሽ በትር ይዟል ባህር ሰንጥቅ ያልሽው ሙሴ ሀጥያት አንቆት ይሄው ፈዟል የዮቶር ቤት ቤተ ሳባ የኩሽ ምድር ጥቁር መሬት ከንቦችሽ ከናፍር ላይ መፍሰስ ይዟል ይሄው እሬት አንች ጦቢያ ሀዘን ውጦሽ ሳቅሽ ሞቷል እጅሽ ታጥፏል መሰል ዛሬ አንጀትሽም ማረን ትቷል አትታክች ለተማፅኖ አበፅዒ መዳፍሽን መሀረነ በይ ዘወትር አታስነፊ ከንፈርሽን ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን) ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t 🏆🏆🏆🏆🏆 እንዲ ለቀቅላችሁ የምትፈልጉ ግጥም ለመላክ . 👇👇👇 . @Diriba12
Показати все...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.