cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Orthodox new mezemure

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን የህይወት ቃል ጌታ እግዚአብሔር በገለጠልን ፀጋ መጠን የምንካፈልበት ሲሆን! " ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤"ቲቶ 2÷11 ስለዚህ ፀጋ ያየነውን የዳሰስነውን በስልጣን ቃል ለትውልድ ሁሉ በእምነት እናውጃለን!! ቤተሰባችን ስለሆናችሁ በክርስቶስ ፍቅር እንወዳችኃለን!!

Більше
Рекламні дописи
207
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

_አዲስ_ዝማሬ_ተናገር_አለኝ_Tenager_Alegn_ዘማሪ_ዲያቆን_አቤል_መክብብ_Offic_tRYLzgENjK0.m4a1.49 MB
_አዲስ_ዝማሬ_ዮሐንስ_ፍቁረ_እግዚእ_ዘማሪ_ዲያቆን_አቤል_መክብብ_mahtot_oxg1Ltt03j0_599.m4a1.25 MB
የተሻለ_ነገር_ዘማሪት_መስከረም_ወልዴ_New_Ortodox_mezemur_3UbYfFjRU_Q_139.m4a2.26 MB
_አዲስ_ዝማሬ_በቅዱስ_አጠራርህ_ዘማሪ_ዲያቆን_ዘለዓለም_ታከለ_ዘጎላ_New_Mezmur_B_qRX7Tnl7rrs.mp37.60 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
_አዲስ_ዝማሬ_ማርያም_ዘማሪ_ዲያቆን_ዘለዓለም_ታከለ_ዘጎላ_New_Mezmur_Maryam_hVLx8FBYWEE.m4a1.74 MB
ORTHODOX_TEWAHIDO_MEZMUR_ትዝ_አለኝ_በላዔ_ሰብ_ygrTowQy5X0_140.m4a5.20 MB
_ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_ታደሰ_አሳዳጊዬ_New_Orthodox_Mezmur_Asadagiye_P4nVRiL1TQU.m4a3.01 MB
👍 2
Показати все...
TikTok · አንድ ቀለም ከዲ/ን ዶ/ር ጋር

12.3K likes, 178 comments. “#ከሡከሡ #ከሡ_ከሡ#ጋር #አብይፆም🙏 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ሀገሬኢትዮጵያ🇪🇹💚💛❤️ #ቃለህይወት_ያሰማልን #foryoupage #fyp #foryou #habeshatiktok #ተዋህዶ #ኦርቶዶክስ ”

👍 2
እንዲህ ጹሙ በፆም ውስጥና ከፆም ውስጥ ያለውን ምሥጢር ለመለየት በፆም ውስጥ ከፆም መጠቀም ያስፈልጋል ። ክርስቲያን በንግግሩና በሕይወት አካሄድ መስመሩ እግዚአብሔርን ያከብራል ። ግን ደግሞ ክርስቲያን በአንድ ነገር አምላኩን ለማክበር ይቸገራል ፦ በሀሳቡ ። ሀሳብ እግር ካገኘ የትግበራ ቁልፍ ነው ። ብዙ ኃጢአቶች ምንጫቸው ሀሳብ መሆኑ ግልጽ ነው ። በትምህርት ክፍለ ጊዜ ሀሳብ በጽሑፍ ይታሰራል ። በክርስትናው ሕይወት ደግሞ ሀሳብ በፆምና በጸሎት ይታሰራል ። ጸሎት ስለችግር ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ናፍቆንም ሲሆን እርካታ አለው ። ፆምም ከምግብ አድማ ይልቅ የመንፈስ ሲሆን በረከት አለው ። ፆም የክርስቲያኖች ዕድል ነው ። ዕድልነቱ ደግሞ የተመረጠ መሆኑን ይሰብካል ። ፆም ክርስቶስን የምንመስልበትም አንዱ መንገድ በመሆኑ ክቡር ነው ። ፆም ክርስቶስ ቀጥሎም ክቡራን አባቶች ያለፉበት በመሆኑ የክርስትናው ቁልፍ ነው ። ፆም የዓመትበአል ናፍቆት ሳይሆን የመንፍስ ናፍቆት ነው ። ብዙዎች በፆም  ውስጥ  ከፆሞ አይጠቀሙም ። ፆም የታሪክ ዝክር የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ ። ፆም ግን በትውልድ መካከል ክርስቲያን በእምነት ታሪክን ለትውልድ እንዲያስቀምጥ ያደርጋል ። ጌታችን አርባ ቀንና አርባ ሌሊት የጦመው ለምንም ዝክር አይደለም ። በጦም ግን የመንፈስ ቅዱስ አብሮነት ፣ የሕይወት ምሪት ፣ የክርስትናው ካርታ ፣ የፀጋ ሞተር  ከጸባዖት ይፈስሳልና ለክርስቲያን የዓመትና የወራት ትውስታው እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አስርግጦ ይናገራል ። ክርስቲያኖች አንድ ነገር እናስተውል የምንይዘውና የምንፈታው ፆም የለም ። ወደ ዓለም ከመኮብለል የሚይዘን ፣ ከዲያብሎስ ሽንገላ የሚፈታን ፆም ግን አለ ። ፆም ይዣለሁ አይባልም ነውር ነው ። የምንፆም ከሆነ ፆሙ እንደያዘን ሕይወታችን ፣ ውሎችን ፣ ንግግራችን ይመሰክራል ። ፆምን ፈታው አይባልም ነውር ነው ። የመንፆም ከሆነ ከዲያብሎስ እስራት የተፍታው ሕይወታችን በራሱ ምሥክር ነውና መናጋርም አያስፈልግም ። አዎ የምይዘውም የምንፈታውም ፆም የለም ። አዎ ፆም የምግብ አድማ አይደለምና  ክብር ይግባውና ጌታችን ጦምን በጦመበት ገዳመ ቆርንጦስ ውስጥ ከመግበታቱ ቀፊት የበላው ስጋ ሲወጣም የበላው ሥጋ የለም ። ፆም ለእግዚአብሔር እሺ ማለትነውና ለሰይጣን እንቢታን ይፈልጋል ። ክርስቲያኖች በፆም ጊዜ ሥጋና ገንቢ ምግቦችን የማንበላበት ዋና ምክንያት የሥጋ ሀሳብና ስሜትን ለሞቆጣጠር ቢሆንም ፤ በዛው ልክ ለሰይጣን እንቢ ማለትም ፍቱን መድኀኒት ነው ። ሰይጣንን እንቢ ሳይሉ ሥጋ አለመብላት ምስኪንነት ነው ። ትክክለኛው ፆም እግዚአብሔር እሺ በሚል ልብ በፊቱ መንበርከክ ነው ። ሰይጣን ፆምን ሊያስፈታ ሥጋ አያበላንም ። አዳምን ላስታውሳችሁ ። አዳም እፀ በለስን የበላው በመንፋሱ ሳይሆን በእጁና በአፉ ነው ። በፆም ሰዓት ሥጋ ነክ ነገር ብንቀምስ መንፈሳችን ሳይሆን በአእምሮአችን ትዕዛዝ በእጅና በአፋችን ነው የምቀምሰው ። ይህ የሥጋ ፆም ነው ። ብዙ ክርስቲያኖች የፆም አቅማቸው የሥጋው ስርዓት ላይ ነው ። ይህ ግን የፆም አንዱ ክፍል ይሁን እንጂ የፆም ሙሉ አካል ነው ማለት አይቻልም ።  የብዙ ክርስቲያኖች ፆም ቢሆን በሚጠቅም ባይሆን በማይጎዳ ስርዓት ላይ እየተራመደ ነው ። በፆም ውስጥ ሥጋ ስለበላን የሚጎዳ ሰው የለም ። ሥጋ ስላልበላን ግን የፆምን ጉልበት ማግኘት ይቻላል ። ቢሆንም አይጎዳም ባይሆንም አይጎዳም ። እንግዲህ ፆም ክቡር ነውና አጀንዳ ያስፈልገዋል ። ፆም ግብ አለውና ትጋት ያስፈልገዋል ። ፆም የምሪት ስንቅ ነውና የቃሉ መግቦት ያሻዋል ። ፆም በእግር ኅሊና ሰማይ መድረስ ነውና ጽሞና ያስፈልገዋል ። ፆም ከራስ መዳን ነውና አርምሞ ያሻዋል ። ፆም የንስሐ በር ነውና ቅዱስ ቁርባን ያስፈልገዋል ። ፆም መንፈሳዊ ደጅን ለሕይወት መክፈት ነውና ንጹህ ልብ ያሻል ። መንፍስ ሲፆም ፆም ፆም ይሆናል ። በሥጋ ዓይንና ስርዓት ብቻ የሚፆም ፆም ስራ ሆኖ ያደክማል ። በመንፈስ የሚፆም ፆም ግን ናፍቆት ሆኖ ያረካናል ። የመንፈስ ፆም ምንድነው ? የሕይወት መጽሐፍ እንዲህ ይላል ፦ ''ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። " /ማቴ 6:14/። የመንፈስ ፆም ከሆኑቱ አንዱ ይቅርታ ነው ። ይቅርታ የቂም ማረከሻ መድፍ ነው ። ይቅርታ ባለበት ስፍር ቂም ይንቀጠቀጣል ። ይቅርታ የዘመናት ትኩስ ዜና ነው ። ክርስቶስ ዛሬም ፍቅሩ የማይለመድ ትኩስ ዜና የሚሆንብን ይቅርታ ሕይወቱ ስለሆነ ነው ። ይልቅስ  ፆም አንዱ መሥፈርቱ ንስሐ ነውና ይቅር ባይነትን በፆም ውስጥ እንደ መሥፈርት ማካተት ያስፈልጋል ። ይቅር ብትሉ አለ ጌታችን ። በሉና መባለን ፈልጉ እንደማለት ነው ። ለመሆን መሆንን መኖር ያስፈልጋልና ። የሰዎችን በደል አንድ ብለን ከቆጠርን ያልቃል ። ኃጢአታችንን ግን አንድ ብለን ለመቁጠር ስንነሳ አለማለቁ ተደቅኖብን ዝም እንላለን ። አዎ ጌታችን በጢቂቱ ታምነሃልና በትልቁ እሾምሃለሁ /ማቴ25:21/  ያለውን በዚህ ስፍራ ማስታወስ ያስፈልጋል ። ትንሹን ይቅር ብላችሁ ትልቁን ተቀበሉ  ማለቱ ነው ። የእግዚአብሔር ይቅርታ ትልቅ ነው ። እግእግዚአብሔር ትልቅ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በቂ ስለሆነም እረፍት ነው ። ጌታ ይቅርታው ልክ የሌለው ከምሕረቱ የሚበልጥ ትልቅ ኃጢአት ስለሌም ጭምር ነው ። ከትልቁ እግዚአብሔር የነሰነስ ትንንሽ ይቅርታ የለም ። ለትልቁ ኃጢአታችን ታላቁ ምሕረቱ አለ ። ያለ ይቅርታ መፆም ልክ እንደ አርቴፊሻል አበባ ነው ። ወይ አይለመልም ። ወይ ይደርቅ ። ወይ መዓዛ የለው ። ወይ ማደግ አይታይበት ። ወይ መትረፍ አይታይበት ። ልክ እንዲሁ ደግሞ በይቅርታ ልብ መፆም የሕይወት ልምላሜ በእግዚአብሔር ቃል ማግኘት ነው ። የልብ ስፋት በመንፈስ ቅዱስ አቅም መሞላት ነው። ለወድም መቆረስ የተሰጠን በመስጠት ማረፍ ነው ። ፆም የንስሐ በረከት ነውና  ንስሐ የይቅርታ መቃተት ነው ። ለዚህ መቃተት ደግሞ የሌሎች ነፍስ ታስራ ከሆነ መልስ አይገኝለትም ። ቃሉን ማስተዋል ያስፈልጋል ።  ''ብትሉ" ነው የሚለው ። ሲሉ መባለን መጠበቅ ጥሩ ነው ። መግቢያን ማሳመር ነውና ። ሰድበው የተደባደቡ አሉ ይቅር ብለው ደግሞ የሚተቃቀፉ አሉ ። ይቅርታ የጥሩ መግቢያ ብቻ ሳይሆን ጥሩ መግባብያ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም ። ጌታችን በሉና መባልን ጠብቁ አለ ። እንግዲህ የሰዎችን ነፍስ አስራችሁ ዛሬ በፆሙ ነጭ የለበሳችሁ አስተውሉ ። በሉና መባልን ፈልጉ ። በሉና የመባልን በረከት ተቀበሉ ። አዎ ይቅርታ ስትሉ ይቅር መባልን ትታቀፋላችሁ ። ይቅርታ የፆም መሥፈርት በመሆኑ እንዲህ ጹሙ ፦ በይቅርታ ። እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው ። ይቅር ባይ ሰውም ይወድዳል ። እግዚአብሔር መሐሪ ነው ለምሕረት ልቡን የሚከፈተውን ይወድዳል ። እግዚአብሔር እንደ ልቤ እንዲለን ይቅርታ አንዱ መንገድ መሆኑን መዘንጋት ጥሩ አይደለም ። እግዚአብሔር የዘመኑን ምሥጢር እንዲገልጥልን ጸሎት ፤ እግዚአብሔር ከዘመኑ ክፋትና ነውር እንዲያስመልጠን ፆም አትራፊ መሆኑን መረዳት ይገባል ። በመንፈስ ፆም እግዚአብሔር ይባርካችሁ !! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.