cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment▹ @Gosa_Dave1221

Більше
Рекламні дописи
536
Підписники
+224 години
+427 днів
+6430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🟢🟡🔴የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በጐሥዓ🟢🟡🔴 °༒°°༒°°༒°ክፍል ፫°༒°°༒°°༒° 📌እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ለምን ፈጠረ❓ 🔘ከዓለማት አስቀድሞ እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት /አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ ደግሞ አንድነቱን ሳይከፋፍለው/ ሲቀደስ፣ ሲሰለስ ይኖር ነበር።ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ በክብሩ በጌትነቱ ይኖር ነበረ። 📚ዮሐ፦17፥5 👈ይነበብ። 📌በዓለም ውስጥ ያሉ ፍጥረታት ስንት ናቸው❓ 🔘እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት እያንዳንዱ ቢቆጠር ፍጡር ተናግሮ ባልጨረሰው ነበር።ይህን ያህላል ተብሎም በሰዎች አዕምሮም ሊወሰን አይችልም።ነገር ግን በየወገኑ፣ በየወገኑ፤ ብዙውን አንድ፣ ብዙውን አንድ አድርገን ስንቆጥር ሃያ ሁለት ናቸው። ✍️“እስከ ሰባተኛይቱ ቀን ድረስ ሃያ ሁለት ፍጥረታትን ፈጠረ።”ይላል። 📚ኩፋሌ፦3፥9👈ይነበብ። 🔘ሊቀ ነቢያት ሙሴ የሥነ ፍጥረቱን ቁጥር የሃያ ሁለቱ አርእስተ አበው ምሳሌ አድርጎ ተናገሯል።እነዚህ አርዕስተ አበው ከአዳም ጀምሮ እስከ ያዕቆብ ድረስ ያሉ ናቸው። ✍️“ከአዳም ጀምሮ እስከ ያዕቆብ ድረስ ያሉ አበው ሃያ ሁለት ናቸው።”እንዲሁም አዳም በገነት እያለ ይጸልይባቸው የነበሩ በኋላም ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳቸው ስመ አምላክ /የአምላክ ስሞች ሃያ ሁለት ናቸው።እነዚህም፦ ✍️“አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ … ታው”ያሉት ናቸው። 📚መዝ፦118፥1👈ይነበብ። 📚ሰቆ ኤር፦ከምዕ.1-ምዕ.4 ያሉት ናቸው። 🔘ስለዚህ የሃያ ሁለቱ ፍጥረታት ቁጥር ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ክፍል ይቀጥላል...... ●በቀጣይ ክፍል የምንመለከተው፦ ✍️የሃያ ሁለቱ ሥነ ፍጥረት መገኛ❓ 🙏ወዳጆች ሆይ የክርስቶስን ምስጢር እንድናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ስለ እኔ ስለ ኃ/ሚካኤል {ጐሥዓ} ደግሞ ጸልዩ። ✍️️ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224 ❤ ✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ። 👇👇👇👇 ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 📌ምንጭ 📚መጽሐፈ ባሕረ ሐሳብ 📚ሥነ-ፍጥረት http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

🥰 1👏 1
📌መጽሐፍ ቅዱስን ተኮር ያደረገ ጅንጀና❗️🙄🙄 🔘ወዳጆቼ ግን ወዴት እየሄድን ነው? አረ ዘመን😂 እንዴዴዴዴ 📌አረ ወዳጄ ጓደኝነትም ጥግ አለው።እንዴት አትለኝም? 🔘ጓደኝነት ኬት እስኬት ነው? መነሻውና መድረሻውስ የትና የት ነው? ሆን ተብለው ከሚመሠረቱ መልካም ጓደኝነቶች ይልቅ እንዲሁ በአገጣሚ በሃሳብና በስሜት በመሳሳብ የሚፈጠሩ ጓደኝነቶች ይልቃሉ እድሜያቸውም ይረዝማል።አቅደህ የልብ ወዳጅ አታገኝም አስበህ አውጥተህ አውርደህ የኔ ከምትለው ሰው ጋር አትገናኝም።ጓደኝነት እስከ የሕይወት ምስጥረኝነት ሊዘልቅ ይችላል። 🔘ወዳጄ ግንኙነቶች የየራሳቸው ስሜትና ውስጣዊ ስህበቶች አሏቸው።ወደህ ፈቅደህ የምትቀርበው ሰው በተመሳሳይ ስሜት ሊቀርብህ ካልፈለገ ምንም አይነት ውጤታማና ዘላቂ የልብ ለልብ ወዳጅነት ልትመሰርት አትችልም። 🔘ወዳጄ ጓደኝነት መንገድ አለው።አብረህ ታጠፋለህ አብረህ ታለማለህ አብረህ ታማለህ አብረህ ታመሰግናልህ።የጥፋት አንድነትና የልማት አንድነት መገለጫቸው ጓደኝነት ብቻ ባይሆን እንኳን ከጓደኝነት ጋር የሚያገናኘው ስሜት ይኖራቸዋል። 🔘ወዳጄ የጓደኝነት ጥግ የእራሱ ምስጢር አለው የእራሱ መገለጠጫና ልኬት አለው።ደስታህን የሚያደምቅ ሃዘንህን የሚያዝን ሃሳብህን የሚቀበል ምርጫህን የሚያከብር ሁሉ ጓደኛህ ላይሆን ይችላል።ልባዊ ትስስር የሚታይና በግልፅ የሚታወቅ ተግባር ያስፈልገዋል። 🔘ወዳጄ የምታምንበት የሚያምንብህ ወዳጅ ከፈጣሪ ቢሰጥም አጠቃቀሙን ካላወቅን ግን ሊጠቅሙን ወደ ሕይወታችን የገቡ ሰዎች እንዲጎዱን እድል እንፈጥርላቸዋለን።ሊያሳድጉን የመጡትን ሰዎች ለውድቀታችን ምክንያት እናደርጋቸዋለን ሊወዱን ፍቅርን ሊያስተምሩን ሰውነትን ሊያጋቡብን የተጠጉንን ሰዎች የማይገባቸውን ስም ሰጥተን ዋጋቸውን እናሳንሳለን ከሕይወታችንም እናስወጣቸዋልን። 👉ይቀጥላል... http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

👏 1🙏 1
● 📌የባሕረ ሐሳብ ትምህርት ክፍል ፪ 👉ማታ 3:00 ሰዓት ላይ ይለቀቃል። እስከዚያው ድረስ ቻናሉን Share በማድረግ ሌሎች ይማሩ። ✍️️️ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

👍 2
📌የባሕረ ሐሳብ ትምህርት የሚለቀቅበት ቀንና ሰዓት❗️ 1ኛ፦የባሕረ ሐሳብ ትምህርትዘወትር ማክሰኞ ማታ ከ3:00 ሰዓት ጀምሮዘወትር ሐሙስ ማታ ከ3:00 ሰዓት ጀምሮቻናሉን Join በማድረግ ትማሩ ዘንድ በፍቅር እንጠይቃለንhttp://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ወዳጆች ሆይ እንደምን አላችሁ? እስኪ ዛሬ እዚህ ላይ አሳብ ስጡ! ልክ ነው ወይስ አይደለም እንዲህ ማድረግ?
Показати все...
🤷‍♂ 2
📌ወዳጄ...አንተ አንድ ሌሊት መታገስ አቃተህን❓ ❖እግዚአብሔርን አምናለሁ አከብራለሁ የሚል አንድ ሰው ነበር ከዕለታት በአንደኛው ቀን አንድ እንግዳ ወደ ቤቱ ይመጣል።እሱም እንደ ክርስትናው ሥርዓት ጓዙን ተቀብሎ የሚበላውንና የሚጠጣውን የሚተኛበትንም አዘጋጅቶ ሲያብቃ እግሩን ያጥበው ጀመር።ይህ ደግ ሰው የእንግዳውን እግር እያጠበ ✍️"ዛሬ አንተን ወደ ቤቴ ያመጣልኝ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው" ይላል፤ እንግዳውም፦ ✍️"እግዚርአብሔር ማነው?" ይለዋል ዕድሜህ በጥያቄው የደነገጠው እንግዳ ተቀባይ፦ ✍️"ምን ማለትህ ነው እግዚአብሔርን አታውቀውምን?" ይለዋል፦ ✍️"ኧረ በፍጹም ስሙንም ያለዛሬ ሰምቼ አላውቅም"ይላል እንግዳው። ❖ለመሆኑ ስንት ዓመትህ ነው? ይላል የቤቱ ባለቤት፤ እንግዳውም (ስልሳ) ይላል።የቤቱ ባለቤት በጣም በመደነቅ በመናደድም ጭምር የእንግዳውን እግር ማጠብ አቋርጦ፦ ✍️"60 ዓመት እንዴት ሙሉ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሰውማ ቤቴ አያድርም" ብሎ ያባርረዋል።የቤቱ ባለቤት እኩለ ለሊት ላይ ራእይ ያያል ልዑል እግዚአብሔር ተገልጾ፦ ✍️"ዛሬ ውለህ አመሸህ?" ሲለው የቀኑን ውሎ ተናግሮ ሲያበቃ፦ ✍️"60 ዓመት ሙሉ አንተን የማያውቅ እንግዳ በቤቴ ሊያድር ሲል እኔ ያንተ ባርያ አባርርኩት" አለ። ❖እግዚአብሔርም ይህንን ስህተቱን ሊያርም ነበርና መምጣቱ ✍️"ወዳጄ ሆይ እኔ 60 ዓመት የታገስኩትን አንተ አንድ ሌሊት መታገስ አቃተህን?" .....ብሎ መክሮት ተለየው። ❖ብዙውን ጊዜ ሰው ከእግዚአብሔር ቀድሞ ፍርድ ለመስጠት ሲደክም ይታያል፤ እሱ እኛን በታገሰን ልክና መጠን ባይሆንም ምሳሌነቱን ወስደን ሰዎችን ይቅር ማለትና መታገስ አለብን። 🙏ወዳጆች ሆይ የክርስቶስን ምስጢር እንድናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ስለ እኔ ስለ ኃ/ሚካኤል {ጐሥዓ} ደግሞ ጸልዩ። ✍️️ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224 ❤ ✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ። 👇👇👇👇 ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

❖በዚችም ቀን የመብራጣንና የቀፈሐላ ኤጲስቆጶስ የንድራኦስ መታሰቢያቸው ነው።የግብጻዊው የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሴ ቤት ነው፤ ዳግመኛም ከአባ ኤሲ ጋራ በሰማዕትነት የሞቱ የአምስት ሽህ አምስት መቶና የአራት ጭፍሮች መታሰቢያ ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት❗️ 1ኛ፦አባ ኅልያን ገዳማዊ 2ኛ፦ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር) 3ኛ፦ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት 4ኛ፦ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሐ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች) 📌ሐምሌ 9 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት❗️ 1ኛ፦አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2ኛ፦አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3ኛ፦"318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4ኛ፦የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5ኛ፦አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6ኛ፦ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ✍️"ጌታ ኢየሱስም አትግደል አታመንዝር አትስረቅ በሐሰት አትመስክር አባትህንና እናትህን አክብር ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው፤ ጐበዙም ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለውጌታ ኢየሱስም ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ" አለው" 📚ማቴ፦19፥18👈ይነበብ። 🙏ወዳጆች ሆይ የክርስቶስን ምስጢር እንድናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ስለ እኔ ስለ ኃ/ሚካኤል {ጐሥዓ} ደግሞ ጸልዩ። ✍️️ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224 ❤ ✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ። 👇👇👇👇 ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

● 📌ወዳጄ እስኪ ልጠይቅህ በራስ ትተማመነለህን❗️ የቀጠለ..... 🔘ወዳጆቼ ሁሉም የሚመረጡት በናንተ ነው ለዚህ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። ከሁሉም በላይ አስከፊው የሆነው ነገር ቢኖር ስሜታዊ ሆኖ ወድያው የሚወሰን ውሳኔ ነው።ወዳጆቼ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። 🔘ወዳጆቼ ባሰባችሁት ሀሳብ ላይ መልሳችሁ ማሰብን ምረጡ።ልክ የወደቁትን ሀሳብ ስታስቡ ቆም በሉና ያሰባችሁበት ሐሳብ ላይ መልሳችሁ አስቡ።ሰውን መውቀስ ስታስቡ ቆም በሉና መልሳችሁ ባላሰባችሁት ሀሳብ ላይ አስቡ።ከሀሳብ በኋላ እደገና አስቡ። ከአላስፈላጊ ቃላት ድርጊት ትቆጠባላችሁና። 🔘ወዳጆቼ ይሄ የሕይወት የጨዋታ ሜዳ ነው።ይሄ የሕይወት የፈጣሪ አውድ ነው። ከሚፈለገው በላይ ትግል።ከሚፈለገው በታች እንቅልፍ አያስፈልግም።በመጠኑ መኖር ሕይወትን አሰልች አያደርግም። የምትታገሉት በመጠኑ መኖር ስለማትሹ ነው።የተጋነነ ነገር ትፈልጋላችሁ። ስታጡትም ባነሰ ነገር ትኖራላችሁ። ምክንያቱም ፈልጎ ያጣሰው የሚያገኘው ነገር ሁሉ ትንሽ ይሆንበታልና። 🔘ወዳጆቼ ሕይወት ንፁሕ ወረቀት ናት። ሕይወት ማንነታችሁን የምትጽፉበት ወረቀት ነው። እስካሁን በፈጠራችሁት ካልረካችሁ እራሣችሁን እየሰደባችሁ ነው።ወደ ፊትም ቢሆን ብዙ የሚያረኩ ነገሮችን መፍጠር ትገፉበታላችሁ። 🔘ወዳጆቼ የዘለዓለምን ሕይወት የዘለዓለምን ቤት ለመስራት ወይም ለመገንባት አሁን ላይ በወጣትነት እድሜያችሁ ላይ ካልጀመራችሁት በኋላ አስቸጋሪ ሊሆንባችሁ ይችላል።በኋላ የማያስቆጫችሁን ነገር በሚገባ እና በትክክል በማስተዋል ሰርታችሁ ዕለፉ። 👉ወዳጆቼ ማስተዋሉን ለሁላችንም መድኃኔዓለም ያድለን!!!!🙏 ተፈጸመ!!! 🙏ወዳጆች ሆይ የክርስቶስን ምስጢር እንድናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ስለ እኔ ስለ ኃ/ሚካኤል {ጐሥዓ} ደግሞ ጸልዩ። 🙏ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224 ❤ ✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ። 👇👇👇👇 ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

🙏 1
● 📌በአጭሩ❗️ 🔘ረመመ(አርመመ) ማለት ዝም አለ ፣ ጸጥ አለ። 🔘ነከረ ማለት ገረመ ፣ ደነቀ ፣ ዕጹብ ሆነ። 👉ከዚህ አንጻር ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ማለት ◉ምሥጢረ ሥላሴ ትደነቃለች እንጂ አትነገርም ማለት ነው። 👉ይሄም ምሥጢረ ሥላሴም ከፍጡር አእምሮ በላይ መሆኑን ለመናገር ነው። ✍️መ/ር ዲያቆን ዳዊት http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

1
🟢🟡🔴የንስሐ ሕይወት ትምህርት በጐሥዓ🟢🟡🔴 °༒°°༒°°༒°ክፍል ሦስት {፫}°༒°°༒°°༒° 📌ንስሐ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ ጸጋ ነው❗️ 🔘ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው።ለዚህ ነው ✍️"ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ (ትነፃላችሁ)፤ ከርኩሰታችሁም ሁሉ  ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ እጠራችኋለሁ።አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስኬዳችኋለሁ ፍርዴንም  ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ"በማለት የተነገረው። 📚ሕዝ፦፴፮፥፳፭-፳፯👈ይነበብ። 📌ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያቢሎስ ባርነት ነፃ መውጣት ነው❗️ 🔘እግዚአብሔር ካልፈቀደለትና ኃልሉን ካልሰጠው በቀር ተነሳሒ ልቡና ማግኘት ለሰው ልጅ በተለይ ኃጢአት ለሠለጠነበት ዲያቢሎስ ለነገሠበት ሰው ከባድ ነው።ይህንንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ✍️"እውነት እውነት እላችኋለሁ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።ባሪያው ለዘላለም በቤት አይኖርም....እንግዲህ ልጁ(ወልደ እግዚአብሔር  አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ። "በማለት ከዚህ የኃጢአት ባርነት ነፃ መውጣት የሚቻለው ከእግዚአብሔር በተሰጠችና በምትሰጥ ንስሐ መሆኑን አስተምሮናል። 📚ዮሐ፦፰÷፴፬-፴፮👈ይነበብ። 🔘በእውነት ንስሐ የገብል በፍጹም ልቡ ወስኖ ኃጢአትን የተወ ሰው በእርግጥ ከባርነት ነፃ እንደሚወጣ ✍️"እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቱ  ናችሁ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።"በማለት አረጋግጧል። 📚ዮሐ፦፰፥፴፪👈ይነበብ። 📌ንስሐ ስለእግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው❗️ 🔘ሰው በብዙ ምክንያቶች ኃጢአትን ሊተውን ይችላል። ◉ለምሳሌ ሰውን ፈርቶ፣ የሚፈልገውን ዓይነት ኃጢአት ለመሥራት አቅም ሳይኖረው ቀርቶ፣የሚፈልገውን ኃጢአት ለመፈፀም ሁኔታው ሳይመቸው ቀርቶ ወዘተ።ይህ ዓይነቱ ንስሐ ሊባል አይችልም። በመጀመሪያ ኃጢአትን ለመሥራት ማሰብን ከልቡና ፈጽሞ ማጥፋት ይገባል። 🔘የኃጢአት ፍቅር ከልቡ ሳይወጣ የኃጢአት ፍላጎት  እያለው ኃጢአትን ያልሰራ ሰው ኃጢአትን ትቷል ሊባል አይችልም።ንስሐ የሚባለው ኃጢአትን ከልቡና፣ከማሰብና ከመሥራት ፈጽሞ መከልከልና መተውን ነው። ✍️"ኃጢአትን የሚሠውር አይለማም የሚናዘዝና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።" ሲል ጠቢቡ ሰሎሞብ ተናግሯል። 📚ምሳ፦፳፰፥፲፫👈ይነበብ። ●ክፍል ይቀጥላል......በቀጣይ ክፍል ✍️እውነተኛ ንስሐ ኃጢአትን ከተው በኋላ በፍጹም መልሶ አለመስራት ነው።❗️ 🙏ወዳጆች ሆይ የክርስቶስን ምስጢር እንድናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ስለ እኔ ስለ ኃ/ሚካኤል {ጐሥዓ} ደግሞ ጸልዩ። ✍️️ጐሥዓ {ኃ/ሚካኤል} በጸሎታችሁ አስቡኝ።🙏 ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ©ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ ┈┈┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈┈ ❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇👇👇👇👇👇 💚 @Be_Gosa1224 💚 💛 @Be_Gosa1224 💛 ❤ @Be_Gosa1224 ❤ ✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ። 👇👇👇👇 ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221 ◈ ◈ @Gosa_Dave1221http://t.me/Be_Gosa1224
Показати все...
🕊🦋[ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጐሥዓ]🦋🕊

በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት። Comment ▹ @Gosa_Dave1221

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.