cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የንባብ ሱሰኞች

የንባብ ሱሰኞች ጥሩና የተመረጡ መጻሕፍትን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር፥ "የንባብ ሱሰኞችን እንፈጥራለን!" በሚል መሪ ቃል ሥር የሀገራችንን የንባብ ባሕል ለማዳበር የተቋቋመ ነው። መጻሕፍትን ለመግዛትና ለማዘዝ ከፈለጉ፦ 0966-76-71-68 ላይ ይደውሉ!

Більше
Рекламні дописи
744
Підписники
Немає даних24 години
+47 днів
+2530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬም ቅናሽ አለን! የአእምሯችንን እድገት እጅግ ወሳኝ ነው። ለሰውነት እድገትና ብርታት የምንሰጠውን ትኩረት ያህልም ለአካል እድገትና ብርታት መስጠት አለብን። ንባብ ይህንን እንድናደርግ ያግዛል! የንባብ ሱሰኞችም ይኽንን ታሳቢ በማድረግ ምርጥ ምርጥ የአእምሮ ምግብ የሚሆኑ መጻሕፍትን በሃያ በመቶ ቅናሽ አቅርቦላችኋል። ከተፍ ብላችሁ ከእጃችሁ ታደርጉ ዘንድ ጋብዘናል! #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ለአንድ ቀን ባወራው (#ጥያቄ) አንዳንድ ጸሐፊያንን በጣም እንወዳቸዋለን። በመጽሐፋቸው በኩል ከልባችን ቅርብ ይሆናሉ። ለመሆኑ እርስዎ በጣም የሚወዱት እና "አንድ ቀን አግኝቼ በደንብ ባወራው/ባወራት" የሚሉት ጸሐፊ አለ ይሆን? እስቲ መልስዎን ይጻፉልን! #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መምህር መስፍን ሰለሞን በንባብ ሱሰኞች ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። መምህር መስፍን በተለይም "ሰባት ቁጥር" በተሰኘው እጅግ ተወዳጅ መጽሐፋቸው ይታወቃሉ። #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
4👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከገበያ የወጣ መጽሐፍ (#ጥያቄ) አንዳንድ መጻሕፍት "ቆይ ዛሬ"፥ "ቆይ ነገ" እያልን ለመግዛት ስንዘናጋ ከገበያ ይወጣል። 'ሳልገዛው አለቀ' ብለን የምንበሳጭበት መጽሐፍ መቼም ሁላችንም ጋር ይኖራል። ለመሆኑ እርስዎ ሳልገዛው ከገበያ ወጣ ብለው የሚበሳጩበት መጽሐፍ ምን ይሆን? እስቲ መልስዎን ይጻፉልን! #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬም እንላለን! መለወጥ የፈለገ ግለሰብ ማንበብ ግድ ይለዋል። መለወጥ የፈለገ ቤተሰብ የንባብ ባሕል ሊያዳብር ይገባዋል። መለወጥ የፈለገ ማኅበረሰብ አንባቢ ከመሆን ውጪ አማራጭ የለውም። ንባብ ዓለምን ቀይሯል፥ እየቀየረ ይገኛል፥ ለወደፊትም ይቀይራል። ራስዎትን፥ ቤተሰብዎትን፥ ማኅበረሰብዎትን እንዲሁም ብለው ዓለምን ለመቀየር የሚያስችል ብቃት ማዳበር ከፈለጉ ንባብን የየዕለት ተግባርዎ ያድርጉ! #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሁለቱ ታላላቆች ወግ! ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ድንቅ ጋዜጠኛ ነው። የኢትዮጵያን ምድር ከጫፍ ጫፍ ተመልክቷል። የማኅበረሰቡን ባሕል አብሮ በመኖር ያውቀዋል፤ የዱር አራዊቱን ጠባይ ደግሞ እንደ እጁ መዳፍ ያውቃቸዋል። ከጫካ እስከ በረሃ ድረስ! የኔታ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሊቅነት ጫፍ የደረሱ መምህር ናቸው። ቤተክርስቲያንም "መምህረ መምህራን" የሚል ማዕረግ ሰጥታቸዋለች። አራቱን ጉባዔያት ብትንትን አድርገው ያውቃሉ፤ ያስተምራሉም። የእንስሳቱን ጠባይ ከነገረ መለኮት ጋር እያገናኙ በመተንተን ደግሞ ተክነውበታል! የኔታ በጽሐ ዓለሙ እና ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የሁለት ዓለም ሰዎች ናቸው ሊባሉ ይችሉ ይሆናል። እነዚህን ሁለት ታላላቅ ሰዎች ግን ድልድይ ሆና አገናኘች - ምዕላደ ጥበብ መጽሐፍ! የንባብ ሱሰኞች ይህቺን መጽሐፍ በማከፋፈል ላይ ይገኛል። ከተፍ ብለው ከእጅዎ ያድርጉ! #የንባብ_ሱሰኞች #የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን #reading_addicts
Показати все...
👍 2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.