cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።

Більше
Рекламні дописи
1 782
Підписники
-124 години
+197 днів
+4430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...

👍 8 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✏የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተጠናቀቀ 👉የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ስም በመግለጫው ላይ እንደገባ ተደረገ ፦ 👉የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው ዕለት በነገው ዕለት  የሚነበበውን መግለጫ የገመገመ ሲሆን 👉የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጉዳይ በመግለጫ ተካቶ እንዳይነበብ በጥቅሉ በስብከትና በመግለጫ አሰጣጥ ዙሪያ ሕጋዊ መብት ካለው አካል ውጪ መግለጫ እንዳይሰጥና በአውደ ምህረት የሚተላለፉ ስብከቶችም ቀኖና፣ዶግማ፣ሕግጋትንና መመሪዎችን በጠበቀ  መልኩ እንዲሰጡ ሲል መመሪያውን እንዲያወጣ ወስኗል። 👉የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጉዳይ ግን ለቤተክርስቲያናችን ሚዲያዎች የውሳኔው ፁሁፍ እንዲደርሳቸው በማድረግ እነርሱ በዝርዝር የብፁዕነታቸውን መልእክቶች እና  ሒደቱን በመጥቀስ ዜናና ፕሮግራም በመስራት ለሕዝብ እንዲያስተዋውቁ ውሳኔ በመስጠት መግለጫው በነገው እለት ጠዋት እንዲሰጥ በመወሰን ስብሰባውን አጠቃሏል። 👉በዚሁ አጀንዳ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ እና ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ  የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጉዳይ ከመግለጫው እንዲወጣ የማድረግ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍለዋል። 👉 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/ethiobeteseb
Показати все...
👍 23 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✏የፍርድ ቤት ውሎ 👉በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ጠዋት በዋለው ችሎት መርጌታ ብርሀኑ ተ/ያሬድን ጨምሮ በአንድ መዝገብ 20  ሰዎች የቀረቡ ሲሆን የክሰ ቻርጅ ተሰጥቷቸው ለዋስትና ብይን ከሰአት ተቀጥሯል 👉 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/ethiobeteseb
Показати все...
👍 22 2 1🙏 1
እነሆ ውይይታችን ተጀምሯል! ግቡ! አጋሩ! እናመሰግናለን!
Показати все...
👍 12
Показати все...
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እና አንድምታቸው ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እና ቀጣይ የህልውና ጉዞ አንፃር!

#መምህር_ፋንታሁን_ዋቄ #መምህር_ኃይለማርያም_ቢሻው

14👍 3
ከእውቁ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት እና ባለ ብዙ ግኝቶች ኤምሪተስ ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ጋር ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በቀጥታ ሥርጭት፤ ከደቂቃዎች በኋላ እንጀምራለን! ይህ ብርቱ ሀገራዊ የህልውና ጉዳዮች የሚነሱበት መርሐ ግብር እንዳያመጥዎ! በማጋራት እና በማስተዋወቅም እንራዳ! እናመሰግናለን!
Показати все...
👍 24
https://www.youtube.com/live/P9IMrj6y01s?si=vfnp8aufvBBBChwh የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 Youtube በዩቲዩብ 👁👁👂🏽👂🏽ይመልከቱን፣ www.youtube.com/@TunbiMedia_
Показати все...
"ለምን አማራ እና ኦርቶዶክስ?" ልዩ ቆይታ ከፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ እና መምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር! ክፍል ሁለት!

ከሳይንቲስቱ ጋር እነሆ ዛሬም! እውቅ ባለ ብዙ ግኝቶች እና የዘመናችን ስኬታማ የምርምር ሰው የሆኑት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ፣ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከቱንቢ ሚዲያ ጋር ተከታታይ ልዩ ቆይታ ያደርጋሉ! በቆይታችን ስለ ኢትዮጵያ ከፍታ፣ ወቅታዊ ችግሮች እና የመፍትሔ ትልሞች ላይ ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር ሰፊ ውይይት እና ደርጋለን። እነሆ ይህ ሁለተኛው ክፍል ነው! @Ethio_Tunbi Media

👍 15
Показати все...
አጣብቂኙ ውስጥ የገባው ሲኖዶስ! // ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?// ቆይታ ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር #ethiobeteseb

አጣብቂኙ ውስጥ የገባው ሲኖዶስ! // ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?// ቆይታ ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር #ethiobeteseb

👍 16 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✏የደረሰን  መረጃ ♦የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የዛሬ ውሎ (ግንቦት 23/ 2016 ዓ.ም ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ) ♣ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ትላንቱ ዛሬም በተለያዩ  አጀንዳዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል ፣  👉ከሲኖዶሱ ጉባዔ ውስጥ በድምፅ ተቀርፆ ስለወጣው መረጃ ማንኛውም  የሲኖዶሱ ተሰብሳቢ  ጳጳሳት ስልክ ይዘው እንዳይገቡ የጋራ  ስምምነት ላይ ቢደርሱም  ማንም ተፈትሾ እንደማይገባ ግን በዛሬው ጉባዔ ላይ የታየውን  የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል፦  👉 በዛሬ ስብሰባ ረጅም ጊዜን የወሰደው  2017 ዓ.ም በጀትን ጉዳይን  በተመለከተ ሲሆን ከብዙ አ ዉይይት በኃላ በባለሞያዎቹ ተጠንቶ የቀረበውን ጉባዔው በሰፊው ተወያይቶ  በጀቱን በማጽደቅ ውሳኔ አሳልፏል ፦ 👉ሌላው  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግብር (Tax) እንድትከፍል  ቀደም ሲል መንግስት ያዘዘውንን ትዕዛዝ አስመልክቶ ይህንን ለማስፈጸም በመንግሥት የተመለመሉ በልቶ አዳሪዎች ቢኖሩም ሲኖዶሱ ከሙዳይ ምፅዋት በተሰበሰበ ገንዘብ እንዴት ቤተክርስቲያን ግብር (Tax ) ትከፍላለች በሚል ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን ፣ ለሃይማኖት ማስፋፊያ የተሰበሰበ ገንዘብ ላይ ግብር ክፈሉ የሚለው ጫና እና ወከባ ተገቢ ባለመሆኑ ይህንን ጉዳይ መንግሥትን እንዲያናግሩ በእነ አቡነ ጎርጎርዮስ የሚመራ አምስት ልዑካንን ሲኖዶሱ ሰይሟል ፦ 👉በመጨረሻም የጳጳሳቱን የዝውውር ጥይቄ  አጀንዳ አስመልክቶ የአንዳንድ ጳጳሳት ጥያቄ ብዙዎችንም ቢያስገርም  የሀገረ ስብከት ለውጥ የሚፈልጉት ለአዲስ አበባ ለመቅረብ እና ለድሎት እና ምቾት  እንጂ  አገልግሎትን መሠረት አድርጎ እንዳልሆነ በደረሱን መረጃዎች ለማወቅ ችለናል ፦ ይኽም ቢሆን በዛሬው ስብሰባ እኬሌ ጳጳስ ወደ ዚህ ተዛወረ የሚል ውሳኔ አልተሰጠም ይሁን እንጂ የአባቶችን የዝውውር ጥያቄ አስመልክቶ የተሰየመው ኮሚቴ አጥንቶ ለነገ እንዲያቀርብ በማለት ጉባዔው  ውሳኔ አሳልፏል  👉 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/ethiobeteseb
Показати все...
👍 25