cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ᴀʙʙᴀʏ ɴᴇᴡs™

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media

Більше
Ефіопія539Англійська13 615Еротика9 637
Рекламні дописи
41 718
Підписники
-9224 години
+1 0157 днів
+12 77930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ ይደን ጡዘት ቀጥሏል 🤔 ፑቲንን የዩክሬን ፕሬዘዳንት አርገውት አረፉ " ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲንን ወደዚህ ጋብዛለሁ ! " - ጆ ባይደን የNATO ፕሮግራም የሚዲያ መግለጫ ላይ ፥ የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ለንግግር ሲጋብዙ " ባይደን እንዲህ አሉ "በጣም ትጉህ የሆነው የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ፑቲን ወደ መድረክ ጋብዛለሁ" ብለው ተናገሩ በሥፍራው የነበረውን ታዳሚ አስደንግጧል። ዜሌንስኪም በጠላታቸው ፑቲን በመጠራታቸው ክው ብለው ቀርተዋል። ወዲያው ግን ጆ ባይደን ፥ " የፑቱን ነገር አሳስቢ ሆኖብን እዛ ላይ ብዙ ስለቆየሁ ነው ፤ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ " ሲሉ ስህተታቸውን አርመዋል። ዜሌንስኪ " እኔ እሻላለሁ ! (ከፑቱን ማለታቸው ነው) " ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደንም ፥ " በእርግጥም በደንብ ትሻላለህ " ሲሉ መልሰዋል። ከዚህ ቀጥሎ በነበረ አንድ መግለጫ ላይ ደግሞ የገዛ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስን " ምክትል ፕሬዝዳንት ትራምፕ " ብለው ሲጠሩ በርካቶች በድንጋጤ ተመልክተዋቸዋል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Sudan " በ2 ሳምንት ውስጥ ለቃችሁ ውጡ " - የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የውጪ ዜጎች ከዋና ከተማዋ ካርቱም እና በዙሪያ ካሉ አካባቢዎች እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ። ፖሊስ ባወጣው ማሳሰቢያ ፥ የውጪ ዜጎች ከተባሉት የሱዳን አካባቢዎች ለመውጣት የ2 ሳምንት ጊዜ ብቻ ነው የተሰጣቸው። የሱዳን በመንግሥት ወታደሮች እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገቡ በርካታ ወራት አልፈዋል። ውጊያ አሁን ድረስ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የውጪ ዜጎች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ አካባቢውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው ነው ፖሊስ ያሳሰበው። በሌላ በኩል ፥ ' በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ውስጥ የሌላ ሀገር ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አሉ ' በሚል በመገናኛ ብዙሃን መዘገቡን ተከትሎ በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመጡ የውጪ ዜጎች ላይ ጥላቻ ይስተዋላል። ከቀናት በፊት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ከ150 በላይ የውጪ ዜጎች መታሰራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። #DW #Reuters #SudanMilitary #RSF
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
" ህዝቡ በጣም ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ፣ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ነው " - ወንድማቸው የተገደለባቸው ነዋሪ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳና አካባቢው ተባብሷል በተባለ የታጣቂ ኃይሎች እገታና ግድያ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል አመልክተዋል። አቶ አወቀ ሰጠኝ የተቡ የህዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ አሽከርካሪ የሆነው ወንድማቸው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 በስራ ላይ እያለ በታጣቂዎች ጥቃት መገደሉን አመልክተዋል። በዕለቱ 18 ሰዎች አሳፍሮ ከጎንደር ተነስቶ መተማ እየተጓዘ ነበር። ' መቃ ' በተባለው ቦታ ላይ ነው ታጣቂዎች ጥይት ተኩሰው እሱን ጨምሮ 3 ሰዎች ሲገደሉ 14 ሰዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ረዳቱ ሩጦ ማምለጡን አቶ አወቀ አስረድተዋል። ሌላ ከኋላ የመጣ አንድ መኪናም ሰው ባይገደልም አስወርደው እንደሄዱ ጠቁመዋል። " ሁል ጊዜ ግድያ፣ ሁል ጊዜ እገታ፣ ሞት በቃ በጣም የሚያሳዝን ነው ፤ ገላጋይ የሌለበት ሀገር ሆነናል " ሲሉ በሀዘም ስሜት ሆነው ተናግረዋል። " ህዝቡ ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ፣ የሰው ህይወት የሚጨፈጨፍበት ሰዓትና ጊዜ ላይ ነው ያለን። ምንም የሚያድነን አላገኘንም፣ መንግስትም ሊያድነን አልቻለም " ብለዋል። መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል አስክሬን ክፍል ውስጥ ሰራተኛ የሆኑት  አቅልለው ገነቱ፥ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ተወስደው ከነበሩት መካከል እንደሆነ የተጠቆመ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ቤተሰቡ ባለመቅረቡ ቀብሩ በማዘጋጃ ቤት መፈጸሙን ተናግረዋል። አንድ ስሜ አይገለጽብኝ ያሉ የመተማ ወረዳ ነዋሪ ፥ በአካባቢው ግድያ እና እገታ ተባብሶ በመቀጠሉ ስራ ውሎ ወደ ቤት መግባት ፈታኝ እንደሆነ ገልጿል። " እገታ ብቻ መበራከቱ ሳይሆን ሰዎችም ይገደላሉ " ያለው ይኸው ነዋሪ " የታገተ ሰው ብር የጠየቃል መክፈል የማይል አይመለስም " ሲል ተናግረዋል። ከሰሞኑም ከመተማ ሆስፒታል አንድ አምፑላንስ ከነሹፌሩ መታገቱን ገልጿል። ለማስለቀቂያ 300 ሺህ መጠየቁን ተከትሎ በየመስሪያ ቤቱ እየተለመነ ነው ብሏል። እገታ በመስፋፋቱ ነዋሪው፣ ሰራተኛው መንቀሳቀስ እንደቸገረው ጠቁሟል። " በቃ ከቤት መስሪያ ቤት ከዛ ቤት እንጂ ከቤት መውጣት ከባድ ነው " ብሏል። አንድ ከጎንደር መተማ የሚሰራ ሹፌር ደግሞ ፤ " ማንኛውም ሰው ወጥቶ ለመግባት ፣ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ለመነገድም ሌላም የቀን ተቀን ስራ ለማከናወን በጣም ተቸግሯል። አስፈሪ ሁኔታ ነው ያለው። መንገዱ በጣም አስጊ ነው " ሲል ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል። #AmharaRegion #VOAAmh. #Metema
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Update (No.7) • “ እኔ 50 ሺህ፣ ጓደኛዬ 30ዐ ሺህ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃዩ ነው ” - ከእገታ የተለቀቀ ተማሪ • “ እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል ” - የታጋች ተማሪ ወንድም ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ 10 ቀናት አስቆጥረዋል። ስለታጋቾቹ ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ገንዘብ ከፍሎ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ እና የታጋች ቤተሰቦችን ስለጉዳዩ ጠይቋል። አንድ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈቀደ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ እኔ 50 ሺህ ፣ ጓደኛዬ 300 ሺ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃሉ ነው ” ብሏል። ከታጋቾች መካከል 36 የሚሆኑት ከኦሮሚያ  ሲሆኑ 28ቱ በነጻ ሲለቀቁ ሌሎች 9ኙ ግን እዛው እደታገቱ ናቸው ፤ ከአማራ እና ደቡብ የሆኑም እንዳልተለቀቁ ገልጿል። ‘ ታጋቾች ተለቀዋል፣ 7 ታጋቾች ናቸው ያልተለቀቁት ’ የሚባለው ዜና ውሸት መሆኑን ገልጾ፣ ከገርበ ጉራቻ በእግር የ1 ሰዓት የእግር መንገድ ከሚወስድ ጫካ አሁንም ከ60 በላይ ታጋቾች እንዳሉ መመልከቱን ተናግሯል። የአይን እማኙ፥ “ ያሳለፍኩትን ከባድ መከራ በቃላት አልገልጸውም ” ያለ ሲሆን ታጋቾቹ በምግብ እጦትና በብርድ እየተሰቃዩ በመሆናቸው መንግስትም እንዲደርስላቸው አሳስቧል። “ ቤተሰቦቼ ድሃ ናቸው ብዬ አልቅሼ ነው የለቀቁኝ ። ጓደኛዬ 300 ሺህ ብር ባይከፍል ግን አይለቁኝም ነበር ” ብሏል። አንድ የታጋች ወንድም በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ “ ' ልጆች ተለቀዋል ' ይባላል ፤ በርካታ ወላጆች ግን ልጆቻቸው በእገታ ላይ ናቸው። ደውለን እየጠየቅን ነው። እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል። ግን ገንዘብ የለንም !! ” ብለዋል። ሌላኛዋ የታጋች እህት በበኩሏ ፣ ታጋች እህቷ እስከ 3 ቀናት 40ዐ ሺህ ብር ላኪ እንደተባለች፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ግን ማግኘት እንዳልቻለ ገልጻላች። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚሁ ጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን፣ ሰላምና ጸጥታ ቢሮዎች ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።  በተጨማሪም፣ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ አቅርበናል። የአገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ ፥ " በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከሰጠው ወጪ የተለየ ነገር የለኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ፣ ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ በ ' ሸኔ ቡድን ታግተው ተወሰዱ ' ካላቸው 167 ታጋቾች መካከል የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ መለቀቃቸውን 7 ታጋቾች ብቻ እንደቀሩ አሳውቆ ነበር። #TikvahEthiopiaFamilyAA
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው እግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው። "ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል " ያለው ቋሚ ሲኖዶስ " በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር ፦ - መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ - ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ - ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ - ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል። በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል። በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርገውት መደበኛው ሥራቸውን በያሉበት ቦታ እየሰሩ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆነው በጾም በጸሎት እንድተጉ ጥሪ ተላልፏል። https://telegra.ph/EOTC-07-12 #ETHIOPIA #EOTC
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🔈#መልዕክት " ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦ - ሰላምን፣  - መረጋጋትን - ፍቅርን - አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #ኢትዮጵያ🙏
Показати все...
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ " እኛ በሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን። ይኸው ሱዳን ውስጥ ስቃያችንን እያየን ነው። በተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን ተሰብስበው እንዲታሰሩ እና ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ሆኗል። ለአመታት በኖርንበት ሀገር ምንም በማናውቅበት ሁኔታ ሰብሰው አስረውናል። 30 እና 40 ዓመት በላይ የኖሩ ጭምር ታስረዋል። ምክንያት ስንጠይቅ ' ከላይ ነው ትዕዛዙ ' ይሉናል። ሰዎቹ የሌ/ጄነራል አልቡርሃን ናቸው። ጭራሽ ' ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF ለሚባለው) መረጃ  ትሰጣላችሁ ' የሚል ነገር ያወራሉ የጄነራሉ ሰዎች። እስካሁን ያለው የታሳሪ ብዛት ከ600 በላይ ይሆናል።  ህጻናት እና ሴቶች በብዛት አሉ ፣ ነፍሰጡሮች ፣ አዛውንቶች፣ ህመም ያለባቸው ሰዎችም አሉ። ምቹ ባልሆነ ስፍራ ፣ በየሜዳው ነው ያለነው ፤ ከሙቀቱ ተደምሮ እጅግ ስቃያችንን እያየን ነው።  ራሳቸውን ስተው የነበሩ ሴቶችም አሉ። ወደ ህክምና ተብሎ ከተወሰዱ በኃሏ የት እንደደረሱ አይታወቅም። ' እዚህ መኖር አትችሉም ' ከተባልን የለፋንበትን ንብረት ይዘን ወደ ሀገራችን እንዲመልሱን ይደረግ። የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጩኸታችንን ይስማንና ካለንበት ስቃይ ያሶጣን። " - በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን #TikvahEthiopiaSUDAN
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 1.17 ትሪሊዮን መሻገሩን አስታወቀ መንግስታዊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ 135.4 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን በመግለፅ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ  ከ ብር 1.17 ትሪሊዮን መሻገሩን አስታዉቋል። ባንኩ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ትርፍ ማስመዝገቡን እና ይህም በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መቀመጡን ገልጿል። በበጀት ዓመቱ 218 ቢሊዮን ብር  በላይ የብድር አገልግሎት ማቅረብን፤ 91% ወይም ብር 198 ቢሊዮን የሚበልጠው ለግሉ ሴክተር የተለቀቀ ብድር  መሆኑን በማሳወቅ የብድሮች ክምችት በዓመቱ ማጠቃለያ 2.6% ደርሷል ብሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2023/24 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ባቀረበው ሪፖርት በበጀት ዓመቱ በቁጥር ከ1.56 ቢሊዮን የሚበልጥ ግብይት፤ ወይም በገንዘብ ከብር 31.6 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውር መፈፀሙን በመግለፅ ከ1.19 ቢሊዮን ወይም 72% የሚሆነው ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተከናወነ ነዉ ማለቱ ካፒታል ከተቋሙ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል ።
Показати все...
#National_Exam ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የፈተናው መጠናቀቅን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።
Показати все...
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ከሚገኙ ተፈታኞች መካከል ጎልማሳ የኃይማኖት አባቶች እና የኃይማኖት መምህራን ይገኙበታል፡፡ @tikvahuniversity
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.