cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group https://t.me/Mezmur_Zedawit

Більше
Рекламні дописи
237
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ❤️  እንዲህ ያስተምረናል። 👉ማር ያልቀመሰውን የማርን ጣፋጭነት በቃላት መግለጽ እንደማይቻል 👉 እኛም ራሳችን ወደ ጌታ ቸርነት በኛ ቸርነት ዘልቆ መግባት ካልቻልን 👉 የእግዚአብሄርን ቸርነት በማስተማር መንገድ በግልፅ መግለጽ አይቻልም። የራሱን ልምድ. ቅዱስ ሰሎዋን ዘ አቶናዊ ❤️ ደግሞ  እንዲህ ያስተምረናል። 👉ብዙ ባለጠጎች እና ኃያላን ሰዎች ጌታን ወይም እጅግ ንፁህ እናቱን ለማየት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፣ 👉 ነገር ግን እግዚአብሔር በሀብት አይገለጥም፣ 👉ነገር ግን በትሑት ልብ... እያንዳንዱ ድሀ ሰው ትሑት መሆን እና እግዚአብሔርን ማወቅ ይችላል። 👉 እግዚአብሔርን ለማወቅ ገንዘብም ሆነ ስም አያስፈልገውም ነገር ግን ትህትና ብቻ ነው። 👉 የቱንም ያህል ብንማር እንደ ትእዛዙ እስካልኖርን ድረስ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም፤ 👉 እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በሳይንስ አያውቅም። 👉 ብዙ ፈላስፎች እና የተማሩ ሰዎች አምላክ መኖሩን ወደ ማመን መጡ, ነገር ግን እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር. 👉እግዚአብሔር እንዳለ ማመን እና እሱን ማወቅ ሌላ ነገር ነው። 👉 አንድ ሰው እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ ካወቀ፣ ነፍሱ ቀንና ሌሊት ለእግዚአብሔር ባለው ፍቅር ትቃጠላለች፣ 👉ነፍሱም ከማንኛውም ምድራዊ ነገር ጋር ልትታሰር አትችልም። ፈጣሪ እግዚአብሔር ❤️ከሁላችን ጋር ይሁን!!! https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

3
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† =>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: +በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት:: +ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች:: +ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች:: +የአምላክ እናቱ *እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: *ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: *የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: *የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: *የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: *እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች:: +ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: +አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: =>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ? 1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7) 2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1) 4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: =>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: =>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ 3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት 4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም 5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) =>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7) https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† =>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: +በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት:: +ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች:: +ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች:: +የአምላክ እናቱ *እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: *ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: *የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: *የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: *የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: *እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች:: +ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: +አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: =>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ? 1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7) 2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1) 4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: =>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: =>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ 3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት 4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም 5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) =>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
Показати все...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ግንቦት ፳፩ ደብረ ምጥማቅ ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል። በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል። ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው። ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡ ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡ ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡ በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን! 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 “ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም “ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣ መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣ ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣ ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣ ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383 https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
“እመቤታችን በሁሉም እርምጃዎቿ  የተከበረች ነበረች እጅግ ትሁት ፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲሆን እሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚሆንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ሆና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ነው፤ አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የሆኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ሆኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፡፡ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲሆኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፡፡ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትሆን ግድ የለሽነት ፈጽሞ አልነበረባትም፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው፤ ማለትም በቤት ድር የተሠሩ ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይህም በእጅጉ አብሯት የሚሄደው አለባበስና ይህ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አሁን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ በመንገዶቿ ሁሉ በመለኮታዊ ጸጋ የተመላች ነበረች፤” ሲል ስለ ድንግል ማርያም ገልጿል፡፡ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ
Показати все...
ደብረ ምጥማቅ ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰) ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰) አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ) በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መሀረባቸውን ወደ ላይ በሚወረውሩት ጊዜ እርሷ የወደደቻቸው እንደሆነ በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች፤ ሁሉም ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ እነርሱም ወደ ቤታቸውም ለመሄድ በሚፈልጉ ሰዓት ተሰናብተውና በተባርከውም ይሄዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፱) የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት መላእክትና ሊቃነ መላእክትም ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበር:: ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን  ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪) እመቤታችን ድንግል ማርያምም ጸሎታቸውን ሰምታ ያሰቡትን ትፈጽምላቸው ነበር፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ የሕዝቡን ምኞት እንደፈጸመችላቸው የእኛንም በጎ መሻት ትፈጽምልን፤ አሜን፡፡ ምንጭ:-ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +✝+ አባ ዓቢየ እግዚእ +✝+ ❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: (እንደ ወትሮው ሁሉ) ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ? ☞ መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን እገምታለሁ:: (ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!) +ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ አይጠፉባቸውም:: "ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው) +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: +ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል:: +በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: +ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: +አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ- አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: +ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: +ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: +በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል:: +ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል:: +አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: +<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: >>+ +<< ከበዙ ተአምራቱ አንዱን >>+ =>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: +ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: +ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: +ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: +"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና) ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44) + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: =>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: ❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: ❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ) 3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ) 4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ) 5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ) 6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ 4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

👍 1
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+ +በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: +ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: +ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: +በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: +ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል:: +ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: +ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: +የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል:: ❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከበረከቱም አይለየን:: =>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) 2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ 3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት 4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ 4.ቅድስት እንባ መሪና 5.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
††† እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ኤርምያስ ††† ††† ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በስድስት መቶ አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካህናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕፃንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማኅጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: (ኤር. 1:5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከሰባ ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል:: ዘመኑ ዘመነ-ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ በ722 አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው:: በኋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ በ586 ባቢሎን አወረዳቸው:: ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብጽ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት : ነቢይ : መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ : ሕዝቡን ከሰባ ዓመታት በኋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት : ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል ሰባ ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ሃምሳ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ : በመጽሐፈ ባሮክ : በገድለ ኤርምያስ : በዜና ብጹዐን : በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: ††† ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ††† ግንቦት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ (ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ ††† "ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል : ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር : ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና : በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም::" (ማቴ. ፳፫፥፴፯-፴፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/mezmur_Zedawitt
Показати все...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

👍 1👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌷እንኳን ለዳግማ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !        ✨እሑድ ሰንበት ➡️በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ➡️ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ ➡️እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ መልካም በዓል ዕለተ ሰንበት 😍
Показати все...
👍 1