uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

♥ፍኖት…✍🏾

♥ፍኖት…✍🏾

Відкрити в Telegram

#አጫጭር ታሪኮች #ከመፅሀፍ የወጡ ሀሳቦች #የግል ምልከታዎች #ትዕዝብቶች #እውነታዎች ያገኙበታል። ………………አሁኑኑ ይቀላቀሉ😍 😊😊😊😋 youtube ቻናላችንን subscribe ያርጉ👍 https://youtube.com/@finottube-u8w?si=a-13vZOq0UKv8BnP

Показати більше
1 011
Підписники
-224 години
-67 днів
-2430 днів
Архів дописів
“በቴሌቪዥን ከማየው በላይ በውስጤ ብዙ ጦርነት አለ። በዚህ ጦርነት ውስጥ ቁስለኛው እኔ ነኝ። የተጎዳውን የማክመው እኔ ነኝ። የሚያሳዝነው ነገር ቦንቡንም ያፈነዳውት እኔ መሆኔ ነው!”💔
@Evangadi21

ሰው መሆን ቀላል አይደለም
ሰው ለመሆን አለመሆንን ማወቅ የመጀመርያው መንገድ ነው - "ነን" ብለን ተናግረን፣ አውርተን፣ አምነን ሳንሆን ስናገኘው ደግሞ ሕማምና ቁስል ይሆንብናል - ለዛም ነው ራስን ማየት የሚያደክም ነገር ነው የምለው - ቢሆንም ሕይወት ዋጋ ያላት ከልብ ስንኖራት ነው - ያ ደግሞ የሚጀምረው ከአንዲት መነሻ ነው እሱም ትግላችሁ ከራሳችሁ ጋርና የምርም ከፈጣሪ ጋር ልባዊ ግንኙነት ሲኖራችሁ ነው። https://t.me/PsycheJourney1

ዕድል ያለው ከሰጪው ነው ለመቀበል መቅረብ አለ ስትቀርብ ደግሞ ተንኮለኛው ግዋደኛችን አለ ሰው ነን በሁለት መንገድ የምንታገል በአንድ ሞት የምንረታ አይይይ መከራችን ጣፋጭ ነው
ዕድል ያለው ከሰጪው ነው ለመቀበል መቅረብ አለ ስትቀርብ ደግሞ ተንኮለኛው ግዋደኛችን አለ ሰው ነን በሁለት መንገድ የምንታገል በአንድ ሞት የምንረታ አይይይ መከራችን ጣፋጭ ነው

ለሚጎዳህ ነገር ሁሉ አራት ነጥብ አስቀምጥ፤ ነጠላ ሰረዞች አድካሚ ናቸው። Evangadi21

🌟 የአስተሳሰብ አድማስህን ለማስፋት እና ራስህን ለመቀየር ዝግጁ ነህ? በዚህ Channel አእምሮን የሚያነቃቁ እና ህይወትን የሚቀይሩ የተለያዩ ርዕሶችን እንዳስሳለን፦ 📚 ጥልቅ የሆኑ የህይወት ጥበቦች 🧠 የሳይኮሎጂ ሚስጥሮች እና የሰው ልጅ ባህሪ ትንታኔዎች 💪 ጠንካራ ተነሳሽነትን (Motivation) የሚፈጥሩ personal develooment መንገዶች 🎓 ውጤታማ የትምህርት ስልቶች እና የማስታወስ ችሎታን ማሳደጊያ ቴክኒኮች 📖 አዳዲስ እና አስተማሪ የሆኑ የመጽሐፍ ዳሰሳዎች (book reviews) 👑 ከታላላቅ ሰዎች የህይወት ተሞክሮ የሚቀሰሙ ጠቃሚ ትምህርቶች NeuroEmpire የዕለት ተዕለት ህይወትህን፣ የአስተሳሰብ አቅምህን እና የስኬት ጉዞህን ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ምርጥ ይዘቶችን በየቀኑ ወደ አንተ ያደርሳል። 🔥 ጊዜህን ከሚያባክን የ10 ደቂቃ ጊዜያዊ መዝናኛ ይልቅ፣ ዘላቂ ለውጥ ለሚያመጣ የ10 ደቂቃ እውቀት ቅድሚያ ስጥ! 📢 አሁኑኑ NeuroEmpireን ተቀላቀል እና አእምሮህን ወደ ላቀ የዕውቀት ማማ አሸጋግር! 👉 https://t.me/neuroempire1

መከራ ፀጋው የሆነ አንዳንድ ሰው አለ። የኔ ፀጋ መከራ ነው❗️
📚ዳማ @Evangadi21

ለምስክርነት የተጠራን ሰው ዳኛው እየጠየቁት ነው፡፡ ዳኛ---------ሰውየው ሲገደል አይተሃል? መስካሪ----ሲገደል አላየሁም ሰምቻለሁ እንጂ:: ዳኛ--------በመስማት ብቻማ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? መስካሪ----ጀርባውን _ ለዳኛው በመስጠት ከት ብሎ ይስቃል:: ዳኛ--------በማን ላይ ነው እንዲህ የምትስቀው? መሰካሪ-----እንዴ መቼ ሳኩኝ? ዳኛ---------አሁን ስትስቅ ሰምቼህ የለምወይ ሲሉት:: መስካሪ----በመስማት ብቻ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል አላቸው? @Evangadi21

ገንዘብ ደስታን አይገዛም የሚል የሀይማኖት አባት እራሱ ልጁን ለደሀ አይድርም ‼️ @Evangadi21

አንተን ለምን ታሳንሰዋለህ? 😢 አንተም እኮ ፍቅር መስጠት ትችላለህ ❤️ ያንተ ፍቅር ልክ የሚታየው በሰጠኸኝ ሳይሆን እኔ በተቀበልኩህ መንገድ ነው ✨ ያንተ ትንሽ ፍቅር ለኔ ብዙ ከሆነስ ሌላ የተሻ
አንተን ለምን ታሳንሰዋለህ? 😢 አንተም እኮ ፍቅር መስጠት ትችላለህ ❤️ ያንተ ፍቅር ልክ የሚታየው በሰጠኸኝ ሳይሆን እኔ በተቀበልኩህ መንገድ ነው ✨ ያንተ ትንሽ ፍቅር ለኔ ብዙ ከሆነስ ሌላ የተሻለ አለ 🤔 ራስን ከማሳነስ መስጠት ያለብንን ብንሰጥ ሂዎት መልካም ይሆናል 🙏 @Evangadi21

ፍቅር ራስን ያስከፍላል፡፡ ፍቅር ብታገኘውም ያስከፍልሃል፣ ብታጭውም ያስከፍላል ... ከፍያው የየቅል ቢሆንም !!" @Evangadi21

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🙏✨ መልካም በዓል! 🎉 @Evangadi21
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🙏✨ መልካም በዓል! 🎉 @Evangadi21

==========...ሰላም ብትኖር እኮ...======📚 "as a human being no one can escape in the sphere of politics" ያለው ማን ነበር? ማንም ይሁን ብቻ ግን ልክ ነው ባይ ነኝ!      ሰላም ስትኖር ብቻ የሚበቅሉ፣ በረጋ አየር መሃል ብቻ የሚያብቡ ህልሞች ነበሩን።    «አገር ሰላም ብትሆን እኮ...» ብለን በቅንነትና በተስፋ የጀመርናቸው ንግግሮች፣ በየቀኑ በጉጉት የምንጥላቸው የነገ ዕቅዶች፣ በየማስታወሻ ደብተራችን ገጽ ላይ የቀረጽናቸው የወጣትነት ሕልሞች ሁሉ የበጋውን ደመና ይመስል  ተበታትነው ይተናሉ። ከየት እና እንዴትስ ይሰብሰቡ? በቃ—ሁሉም ነገር «ሰላም ብትኖር እኮ...» በሚል ምኞት ተቋጥሮ፣ ተቋጥሮ በቆመበት እንዲደርቅ ተፈረደበት።     ጊዜው ደግሞ  ይነጉዳል፤ እጭር እድሜያቺንን እያስከተሉ ዓመታት በዓመታት  ይተካካሉ ። እኛ  በተስፋ ዘብ ቆመን ጥበቃ ላይ ነበርን። «ነገ የተሻለ ይሆናል፣ አየሩ ይረጋል፣ የጨለመው ይበራል» እያልን ፀሐይ ስትጠልቅም ስትወጣም ቀና ብለን አያየን።        ነገር ግን የጥበቃችን ውጤት የሰማይ ዝናብን በበረሃ  ከመጠበቅ አለያም "ላም አለች በሳማይ..."ከሚባለው የክፍል አገር ሰው መሳለቂያ  ወሬ የተለዬ አልሆነም። ሰላም አልመጣም፤ አልፎ ተርፎም ያ ያበበውና ያሸበረቀው የወጣትነት ህልም ቀስስስ እያለ እየደበዘዘ፣ በመጨረሻም እየጨላለመ ሲመጣ ይታያል።    ከስራ ፈላጊነት ብቻ አይደለም ቢቻል ከተቀጣሪነት አጥር ባሻገር፣ የራሳችንን መንገድ ለመጥረግ የነበረን ያ ድፍረትና የወጣትነት እቅድ ሁሉ  ተበተነ። ከዕለት ተዕለት የሕይወት  ግብግብ ሰልፍ እንዲሁም ግፊት አልፈን ትልቅ ነገu ለመስራት የነበረን ምኞት፣ ከአቅም ማነስ ሳይሆን ከአካባቢው አለመረጋጋት የተነሳ ክንፉ እየታሰረ። የወጣትነት ጉልበታችንና የወደፊት ሕልማችን በጊዜ እና በሁኔታዎች ማዕበል እየተዋጠ፣ ያለ ቦታውና ያለ ጊዜው እንደ ረገፈ አበባ ለመሆን ሊበቃ ከቋፍ የደረሰ ይመስላል።     አሁን  ላይ ቆሜ ወደኋላ ስመለከት፣ ዕልፍ እቅድና ራዕይ የነበረው ወጣት በጊዜ ጥበቃና በምኞት ሰንሰለት ታስሮ ጥፍሩን በጥርሱ እየነከሰ እሚተክዝ ይመስለኛል። "ሰላም የሌለበት አገር ውስጥ ሕልምም ነጻነቱን ያጣል"እኛም የነበረን ሰፊ ህልም ሳይሆን፣ ጊዜ የሰጠንን ቁስል እያየን የምናዝን የቆመ ጊዜ ምስክሮች ሆንን።      ...በዚህ ሁሉም መሃል መሰንበት ሸጋ ነው "ስበብ ሳናበዛ ፤ሳንፈራም ሳንደፍርም"   ያልፋል በሚል ተስፋ እየተሸነጋገልን እራሳቺንን እንጠብቅ ለማለት ያክል ነው።                                              ማሙሽ ✍️                @Evangadi21

ህልም ይፀለያል እንጂ ለሰው አይነገርም !! @Evangadi21

Aster_aweke_best_music_yekosin_bahirzaf_vocal_አስቴር_አወቀ_ምርጥ_ሙ.m4a3.81 MB

ከሳህ ጠቆርክ አትበሉኝ የነገ ታሪኬን እየፃፍኩ ነው! የሁሉም ነገር ፍፃሜ ታሪክ መሆን ነው! አምሮብኝ ዘላለም ባዶ ኪስ ከምሆን ወዜ ጠፍቶ ቢያልፍልኝ ይሻለኛል! ብቻ ትንሽ ታገሱኝ❗️
ከሳህ ጠቆርክ አትበሉኝ የነገ ታሪኬን እየፃፍኩ ነው! የሁሉም ነገር ፍፃሜ ታሪክ መሆን ነው! አምሮብኝ ዘላለም ባዶ ኪስ ከምሆን ወዜ ጠፍቶ ቢያልፍልኝ ይሻለኛል! ብቻ ትንሽ ታገሱኝ❗️

“…እንደምወዳት እኮ ልነግራት ነበር። ግን ድንገት ስለምትፈልገው የወንድ አይነት ስታብራራ ሰምቼ ጉሮሮዬ ተዘጋብኝ። ፀጥ አልኩ። ውሸት ምን ያደርጋል? መስፈርቷ ውስጥ በከፊል እንኳን የለሁም። 📚ወጣ
“…እንደምወዳት እኮ ልነግራት ነበር። ግን ድንገት ስለምትፈልገው የወንድ አይነት ስታብራራ ሰምቼ ጉሮሮዬ ተዘጋብኝ። ፀጥ አልኩ። ውሸት ምን ያደርጋል? መስፈርቷ ውስጥ በከፊል እንኳን የለሁም። 📚ወጣት አበባው @Evangadi21

ጅቦቹን ከመክሰሰህ በፊት የአህያ አመልህን ቶሎ ተው❗️
@Evangadi21

ዶስቶየቭስኪ Note from Underground መፅሀፉ ላይእንዲህ ይላል... "እምላለው በጣም ንቁ እና ራስን በጣም የሚያውቅ ሰው መሆን በሽታ ነው፡፡'' ዶስቶየቭስኪ ሰው ራሱን፣ ድርጊቱን፣ ስሜቱን እና ሌሎች ሰዎች ስለእሱ የሚያስቡትን እጅግ ዐብዝቶ ሲመረምር ጤናውንም ሰላሙንም ያጣል ይላል። ሁሉንም ነገር መጠየቅ ስትጀምር፦ "ለምን እንዲህ አደረጉ?'' “ሰዎች ስለእኔ ምን ያስባሉ?'' "የተናገርኩት ትክክል ነበር?" "ብወድቅስ?" “ይህ ድርጊቴ ስለእኔ ምን ይናገራል?" ከዚያ ማሰብ ከመረዳት ወደ እስር ቤት ይቀየራል። በጣም የሚያሳዝነው ነገር፣ ህይወትህን በጥልቅ ተረድተህ፤ ግን በሰላም መኖር አለመቻልህ ነው፡፡ ሌላ ሰው ስህተት ይሠራል፣ ይቀጥላል። ነገር ግን ከመጠን በላይ የሚያስብ ሰው አንድን ስህተት ለሰዓታት ይመረምራል፤ ምክንያቱን ይፈልጋል፣ ራሱን ይወቅሳል፣ ሌሎች ምን እንደሚያስቡ ይገምታል.... ''እውቀት ነፃነት ሊሰጥህ ይችላል፤ ነገር ግን ከመጠን በላይራስን መመርመር ከሆነ፣ ያው እውቀት እስር ቤትህ ሊሆን ይችላል።" የUnderground Man አሳዛኝነት ይህ ነው፦ አእምሮው በጣም ይሰራል፣ ግን ሕይወቱ ካለበት አይንቀሳቀስም፡፡ © tiktok @Evangadi21

እየተዋደድን ነበር "እየተዋደድን ነበር፣ ግን አብረን ለመሆን አልቻልንም፡፡ ፍቅራችን እውነት ነበር፣ እጣ ፈንታችን ግን አልተስማማም፡፡ አብረን ያለምናቸው ህልሞች በመንገድ ላይ ቀሩ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንጓዝ የነበረው ጉዞም ሳይጀምር ተቋረጠ። አብረን ያለምናቸው ቀናቶች ሁሉ ሕልም ሆነው ቀሩ፤ እኔ ግን አሁንም በእነዚያ ሕልሞች ውስጥ ተቀርቅሬ እኖራለሁ። ከሰው መለየት ያማል፣ ነገር ግን ከምትወደው ሰው ተለይተህ እሱን መርሳት አለመቻል የበለጠ ያማል።ዛሬ ከልቤ ውስጥ ብትኖሪም፣ ከሕይወቴ ግን ርቀሻል። ስምሽን ሳስብ ፈገግ እላለሁ፣ በተመሳሳይ ጊዜም ልቤ ይጎዳል። ምክንያቱም የምወድሽን አንቺን ማጣቴ ሳይሆን፣ አብሬሽ ልኖር ያልቻልኩትን ሕይወት ማጣቴን ሳስበው ያመኛል። ✍🏾ያልታወቀ ሰው @Evangadi21

እኔ እና ልቤ ግን ታዝበነዋል !! ስላመንኩት፥ ለሰጠኝ ፍቅር ዋጋ ስለሰጠሁ፥ እየተመቸኝ አልችልም ስለማልል፥ ስለሚወዱኝና ደጅ ስለሚጠኑ ወንዶች እያወራሁ ስለማልመጻደቅበት ...እኔን ማግኘት መጓጓት ቀነሰ ጥፋቱ ላይ ስለማላተኩር፤ ቅሬታዬን ስለማላሳየው፣ በልቤ ከሌሎች ጋ ስለማላወዳድረው የማይገባኝ መሰለው! ቅር ይለዋል ብዬ የማስበውን ስለማላደርግ፥ ቅድሚያ ስለምሰጠው፥ ስለምወደው ዋጋዬ አልገባውም። እየተወኝ ሁኔታው ሁሉ ውለታ እንደዋለ ነው፡፡
እየበደለ ውለታ ዋልኩ እንደሚል ሰው ክፉ የለም❗
ክፉ አለመሆኔን እንዴት እንዳለማወቅ መቁጠር ተቻለው?! ረስቶት ነው !? እንዴት አድርጎ ቀልቤን ለመግዛት እንደደከመ ፥ እንዴት አድርጎ ደጅ ጠንቶ እንደቀረበኝ፥ እንዴት አንቆለጳጵሶ እጁ እንዳስገባኝ...ሲያገኘኝ እና ሳገኘው የነበረውን ሁኔታውን ሁሉ ረስቶታል! ሰነፍ እንዲህ ነው....በእጁ የያዘው ውድ አይመስለውም !! ሰነፍ እንዲ ነው..... የሚደረግለት ካልተነገረው አይገባውም !! ሰነፍ እንዲ ነው ..... ሲቆጠርበት አያይም !! ሰነፍ አንዲ ነው .......የሚፈልገውን ሲይዘው ያንስበታል !! ሰነፍ እንዲ ነው .....መከተል እንጂ ማስከተል አይችልበትም !! ሰነፍ እንዲ ነው .....ደስታው ያለው ሽምያ ውስጥ ነው !! እኔ እና ልቤ ግን ታዝበነዋል !! @Evangadi21