cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ጥበበ ኢትዮጵያ

318ን ጥበብ ብለን፣360ን ኢትዮጵያ ብለን ቀምረን።በጥበብ ባህር እንራጫለን።

Більше
Рекламні дописи
223
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
+830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል። በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5 ✍የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል። ✍በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል። ✍በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል። ✍በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል። ✍ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል። ✍አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9 (#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
Показати все...
✍እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል። ✍በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል ። ✍ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5 ✍ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል። ✍በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል። ✍በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል። ✍በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል። ✍ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል። ✍አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9 (#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
Показати все...
👍 1
ጥበበ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ✍ስለ ቅድስት ሀገራችን መጻፍ አያሌ ዓመታትን ይወስዳል ። ምክንያቱም እንደ ህዋ የሰፋች ፣እንደ ውቅያኖስ የጠለቀች ፣ እንደ መንፈስ የረቀቀች ፣ እንደ ሌዋታን የገዘፈች ናትና። ✍ስለዚህ ቀጥታ ወደቀመረ ፊደሉ እንሄዳለን ። ✍ኢትዮጵያ ከሚለው እንደቅድሙ ግእዝ ግእዙን ስንወስድ አተየጰየ ይሆናል ።ይህንንም ስንቀምረው አ=40 ተ=10 የ=90 ጰ=400 የ=90 ስንደምረው 360 ይሰጠናል ። 360ን ለየብቻ ስንደምረው 3+6+0=9ን እናገኛለን ።9 በራስዋ በርካታ ምስጢር ያዘለች ቁጥር ናት ። ዳሩ ግን በቀመረ ፊደል ስናያት 9 ን ትሰጠናለች ። የ"በ"ን መልክዓ ፊደል ስንመለከት ደግሞ አንድም "ሰማይ ዙፋኔ ምድርም የእግሬ መረገጫ"ማለት ነው። አንደም "መጠግያ" ማለት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ማለት "ሀገረ እግዚአብሔር "የእግዚአብሔር ሀገር "ማለት ነው። ሌላው በመፅሐፍ ቅዱስ ምስጢር የሚለው ቃል 45 ግዜ ተፅፏል ይህም 4+5 = 9 ነው። ኢትዮጵያ =360=3+6+0=9 , ምስጢር 9=9 ኢትዮጵያ ለዚህ ነው ሀገራችን የምስጢር ሀገር ምትባለው ።
Показати все...
👍 3
ጥበበ ኢትዮጵያ ✍እንደሚታወቀው የቻነላችን ስም ጥበበ ኢትዮጵያ ነው።ይህ ስያሜ ምንድነው ? የሚለውን አብረን እንይ። ✍በመጀመርያ ጥበብ ስንል ከእግዚአብሔር የተቀዳ ከጠቢቡ ሰለሞን የተማርነው ራስን ገዝቶ፣ብልሃትን አንቅቶ ፣ ማስተዋልን ለብሶ መኖር ነው ማለት ነው።ይህም የነጭ አበው wisdom እንደሚሉት ማለት ነው። ✍ነገር ግን እዚህ ጋር ልንጠቀመው የፈለግነው ጥበብ የክዋኔውን ፣በተውኔት፣በዳንኪራ ፣በአጠቃላይ በስነ ፅሑፍ የሚገለጸውን አይደለም ።ይህም ምዕራብያዊያኑ Art እንደሚሉት ያለው ነው። ✍ከዚህ በመነሳት ጥበብ የሚለውን ቃል በቀመረ ፊደል ስንቀምረው 318 ይሰጠናል ። እንዴት ሆነ ቢሉ ጥበብ የሚለውን ቃል ግእዝ ግእዙን ስንወስድ ጠበበ ይሆናል ። ጠ=300 በ=9 በ=9 ይሰጠናል ። ይህንንም ስንደምረው 318 ይሆናል። ✍ 318 ሁለት አንድምታ አለው(በብሉይ እና በሀዲስ ) ✍ ከብሉይ ስንጀምር የኛው ንጉሰ ነገስት የነበረው ቀዳማዊ ምኒልክ አባቱ ጠቢቡ ሰለሞንን ጥይቆ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ከእርሱ ጋር 12,000 የሚሆኑ ሰዎች አብረውት መጥተዋል ። ከነዚህም መካከል 318ቱ የኦሪት መምህራን ነበሩ።እነዚህ መምህራን በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ሕገ ኦሪት እንዲሰርፅና ግዕዝ እንዲስፋፋ ታላቅ ሚና ተጫውቷል ። ✍ ወደ ሀዲስ ስንመለስ አርዮስ የተባለ ወልድ ፍጡር ነው በሚል የኑፋቄ ሀሳብ ራሱን ያሳወረ ሰው በተነሳ ግዜ እርሱን ለመመለስ ካልተቻለም ለማውገዝ በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት ጳጳሳት ቁጥር 318 ነበር ። ከዚህ መነሻነት የቻናላችንን ስም ጥበበ ኢትዮጵያ ብለነዋል ። በቀጣይ ኢትዮጵያን በጥቂቱ እንመለከታለን ።
Показати все...
✥✥✥ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ ✥✥✥ ✥   ሰይጣን የሰውን ልብ ማወቅ አልተፈቀደለትም የሰው ነገር እንዴት ያውቃል ቢሉ በወሬ ነው። ✥    በመጽሓፍ ቅዱስም " በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? በእርሱ ያላችው ነፍሱ ናት እንጂ " በማለት ከነገረን በኋላ ለቅዱሳን ግን በተሰጣቸው ጸጋ እንኳንስ በሰው ልብ የተሰወረውን ይቅርና ሰማያዊ ምሥጢርን የማወቅ ሥልጣን እንደተሰጣቸው ይገልጻል። /፩ ቆሮ ፪፥፮ - ፲፮ / ለሰሎሞንም ከተሰጠው ጸጋ መካከል ኣንዱ የሰውን አሳብ ማወቅ ነበር /መ.ጥበብ ምዕ ፯ / ሰይጣን ግን የሰውን ልብ ማወቅ አልተሰጠውም። ✥   ስለዚህ ሰይጣን እንዳይሰማን ነገራችንን እንሰውረው ሁለት መነኮሳት ለሃምሳ ስምንት ዓመት የሥራቸውን ተቃራኒ እያወሩለት ሰይጣንን እንደቀለዱበት ተጽፎልናል፦ ሁሌ ጸሎት ምን ያደርጋል ዛሬ ተኝተን ነው የምናድረው ሲሉ ይሰማና እነዚህስ ሰነፎች ናቸው ብሎ ይተዋቸዋል እነርሱ ግን ሌሊቱን በጸሎት ሲተጉ ያነጉ ነበር። ✥    ጌታችንም በስውር መፈጸም ስለ ሚገባን ትጋት ሲያስተምረን - ስለ ምጽዋት ፦ ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ ኣትወቅ :: - ስለ ጸሎት፦ ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዝጋ። - ስለ ጾም ፦ ስትጾም እንደ ጾመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ። /ማቴ ፮ / ይለናል። ✥     አብርሃም ልጅህን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ በተባለ ጊዜ ይህንን ነገር ለሚስቱ ለሳራ ለልጁ ለይስሓቅ ሳይነግር በስውር ሊያደርገው ወደደ በዚህም የሰይጣን ፈተናው በወሬ ነውና ከቤተሰብእ እንኳን ተሠውሮ የሚሠራ የትሩፋት ሥራ እንዳለም አስረዳን። / ዘፍ ፳፪ / በጎ ሥራችን  እንዳይታወቅብን እንጂ እንዲታወቅልን አንጨነቅ።  ይቆየን ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ
Показати все...
Repost from N/a
✥✥✥ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ ✥✥✥ ✥   ሰይጣን የሰውን ልብ ማወቅ አልተፈቀደለትም የሰው ነገር እንዴት ያውቃል ቢሉ በወሬ ነው። ✥    በመጽሓፍ ቅዱስም " በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? በእርሱ ያላችው ነፍሱ ናት እንጂ " በማለት ከነገረን በኋላ ለቅዱሳን ግን በተሰጣቸው ጸጋ እንኳንስ በሰው ልብ የተሰወረውን ይቅርና ሰማያዊ ምሥጢርን የማወቅ ሥልጣን እንደተሰጣቸው ይገልጻል። /፩ ቆሮ ፪፥፮ - ፲፮ / ለሰሎሞንም ከተሰጠው ጸጋ መካከል ኣንዱ የሰውን አሳብ ማወቅ ነበር /መ.ጥበብ ምዕ ፯ / ሰይጣን ግን የሰውን ልብ ማወቅ አልተሰጠውም። ✥   ስለዚህ ሰይጣን እንዳይሰማን ነገራችንን እንሰውረው ሁለት መነኮሳት ለሃምሳ ስምንት ዓመት የሥራቸውን ተቃራኒ እያወሩለት ሰይጣንን እንደቀለዱበት ተጽፎልናል፦ ሁሌ ጸሎት ምን ያደርጋል ዛሬ ተኝተን ነው የምናድረው ሲሉ ይሰማና እነዚህስ ሰነፎች ናቸው ብሎ ይተዋቸዋል እነርሱ ግን ሌሊቱን በጸሎት ሲተጉ ያነጉ ነበር። ✥    ጌታችንም በስውር መፈጸም ስለ ሚገባን ትጋት ሲያስተምረን - ስለ ምጽዋት ፦ ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ ኣትወቅ :: - ስለ ጸሎት፦ ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዝጋ። - ስለ ጾም ፦ ስትጾም እንደ ጾመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ። /ማቴ ፮ / ይለናል። ✥     አብርሃም ልጅህን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ በተባለ ጊዜ ይህንን ነገር ለሚስቱ ለሳራ ለልጁ ለይስሓቅ ሳይነግር በስውር ሊያደርገው ወደደ በዚህም የሰይጣን ፈተናው በወሬ ነውና ከቤተሰብእ እንኳን ተሠውሮ የሚሠራ የትሩፋት ሥራ እንዳለም አስረዳን። / ዘፍ ፳፪ / በጎ ሥራችን  እንዳይታወቅብን እንጂ እንዲታወቅልን አንጨነቅ።  ይቆየን ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ
Показати все...
ዕረፍቷ ለማርያም ✍ጥር ሀያ አንድ ቀን መርገም የሌለባት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታርፋለች።ሐዋርያት እርሷን ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ በሚጓዙበት ግዜ አይሁዶች ያይዋቸውና "እነዚህ ልጇ ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን የነበሩ አይደሉምን ? አሁን ደግሞ እሷ ዐረገች ተነሳች እያሉ እንዳይበጠብጡ ኑ ሥጋዋን እናቃጥል "ብለው ተመካከሩ ። በጊዜው አርበኛ ነኝ ይል የነበረው ታውፋንያም የእመቤታችንን ክብርት ሥጋ ይገለብጥ ዘንድ በሞከረ ግዜ ቅዱስ ገብርኤል እጁን ቆረጠው ።ከዚያም ጌታችን እና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ የእናቱን ሥጋ ወደ ገነት ወስዶ በዕፀ ሕይወት ስር አስቀመጠው ። ወደቀደመ ሥልጣኔያችን እንመለስ!!! ያጋሩ ለመቀጠል 👇👇👇 @dagidan77721 @dagidan77721 @dagidan77721
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✞ እመቤታችን ✞ እመቤታችን በቀኝ ቆማለች የብርሐን ልብሷን ተጎናጽፋለች ሠዓሊተ ምሕረት መዝገበ ጸሎት አቁራሪተ መዓት የጌታዬ እናት/2/ እመቤታችን *** የብርሐን ልብስሽን እመቤታችን *** ነይ ተጎናጽፈሽ እመቤታችን *** ሠዓታቱን ሥናደርስ እመቤታችን *** ንዒ ሥንልሽ እመቤታችን *** በሠጠሽ ቃል ኪዳን እመቤታችን *** እንድታስምሪን እመቤታችን *** እንለምንሻለን እመቤታችን *** ከእግርሽ ሥር ወድቀን        /አዝ = = = = = እመቤታችን *** ከኪሩቤል ድንግል እመቤታችን *** አንቺ ትበልጫለሽ እመቤታችን *** ከሦስቱ አካል አንዱን እመቤታችን *** ወልድን ሥለ ወለድሽ እመቤታችን *** ስለእዚህ ድንግል ሆይ እመቤታችን *** እንወድሻለን እመቤታችን *** ዘወትር ጠዋት ማታ እመቤታችን *** እንማልዳለን        /አዝ = = = = = እመቤታችን *** ለሥም አጠራሩ እመቤታችን *** ክብር ይግባውና እመቤታችን *** እናት እንድትሆኚኝ እመቤታችን *** ሸልሞኛልና እመቤታችን *** ሥምሽን ሥጠራ እመቤታችን *** ሠዎች ያዝኑልኛል እመቤታችን *** ሞገሴ ነሽና እመቤታችን *** ይድረስሽ ምሥጋና        /አዝ = = = = = እመቤታችን *** ድንቅ ድንቅ ነገር እመቤታችን *** ነብያት ተናገሩ እመቤታችን *** ሐገረ እግዚአብሔር እመቤታችን *** ድንግል ናት እያሉ እመቤታችን *** ሁለተኛው አዳም እመቤታችን *** ከአንቺ ተወለደ እመቤታችን *** የተዘጋው ደጃፍ እመቤታችን *** በአንቺ ተከፈተ #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።    ╔​✞══●◉❖◉●══✞╗       ✞✞ ✞✞ ✞✞ ✞✞ ✞✞   ❖ @mezmuredawit ❖   ❖ @mezmuredawit ❖   ❖ @mezmuredawit ❖      ✞✞ ✞✞ ✞✞ ✞✞ ✞✞   ╚✞══●◉❖◉●══​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Показати все...
◦•●◉_እመቤታችን_◉●•◦_2023_10_30_07_40_50_121.mp32.70 MB
👍 1
✞ ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞ ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪) የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪) ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪) ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪) ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪) እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)          /አዝ = = = = = ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪) በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪) ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪) /አዝ = = = = = ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪) እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪) ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪) እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪) 👉ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።    ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗        ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞    ❖ @mezmuredawit  ❖    ❖ @mezmuredawit  ❖    ❖ @mezmuredawit  ❖         ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞   ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Показати все...
convert_1598074239287.mp32.10 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.