cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ፍኖተ ቅዱሳን

Рекламні дописи
723
Підписники
Немає даних24 години
+257 днів
+8130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ደጋግማችሁ_አታልቅሱ! ሰዎች ወደ አንድ ጠቢብ ሰው እየመጡ ሁልጊዜ ስለአንድ ጉዳይ ያማርሩበታል። ይህ ጠቢብ አንድ ጊዜ ሰዎቹን አስቀምጦ አንድ ቀልድ ነገራቸው። በቀልዱ ሁሉም ሰዎች ከልባቸው በኃይል ሳቁ። ከሁለት ደቂቃ በኋላ ያንኑ ቀልድ ደግሞ ነገራቸው፤ ጥቂት ሰዎች ብቻ ፈገግ አሉ። ያንኑ ተመሳሳይ ቀልድ ለሶስተኛ ጊዜ ሲነግራቸው ግን አንድም ሰው እንኳ ሳይስቅ ቀረ። በዚህ ጊዜ ጠቢብ ሰው ፈገግ ብሎ "በተመሳሳይ ቀልድ ደጋግማችሁ ልትስቁ አትችሉም። ታዲያ በተመሳሳይ ችግር ደጋግማችሁ የምታለቅሱት ለምንድን ነው?" አላቸው! መጨነቅ ችግሮችህን አይፈታልህም፤ ጉልበትህንና ጊዜህን ያባክንብሃል እንጅ። ተንቀሳቀስ! እንደገና ጀምር!  የተሻሉ ነገሮች እየጠበቁህ ነው!
Показати все...
👍 8
ተስፋዬ አንተ ነህ የታፈነ ጩኸት ሰሚ ያጣ እሪታ በሐኪም የታገደ በያይነት ገበታ በባዕዳን ምድር የግዳጅ ዝማሬ መውጫ በሌለው ጉድጓድ የተራበ አውሬ መቋጫ የሌለው የእርስ በርስ ጦርነት ቆስቋሽ የበዛበት የማይጠፋ እሳት ጨው የሌለው ዓለም ዘይት አልባ አልጋ የሚያገሳ አንበሳ ቢከብ በዙሪያዬ ተስፋዬ አንተ ነህ አምላኬ እረኛዬ ሰው የለኝም እና ሁነኝ ከለላዬ(*2)::
Показати все...
ዝምተኛዋ ሰባኪት -  እመቤታችን ማርያም! . ስለእመቤታችን ደንግል ማርያም የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት ክፍሎችን ስንመለከት የእመቤታችን ቃላትና ንግግሮች በጣም አጭርና የተቆጠቡ መሆናቸውን እናስተውላለን፡፡ . አምላክን ያህል ልዑል እንደምትወልድ መልአክ ሲያበሥራት ከመልአኩ ጋር የነበራት ንግግር በጣም አጭርና የተቆጠበ ነበር፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የእመቤታችን ዕይታም ሆነ ንግግር በጣም በሚገርም ሁኔታ መሠረታዊ ነገሮች ላይ ብቻ የሚያተኩር ነበር፡፡ የመልአኩ ሰላምታ ረጅምና ልዩ ነበር፡- “ደስ ያለሽ፤ ጸጋንም የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች ተለይተሸ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡” ሉቃ 1፤28 . እንደዚህ ላለ ረጅምና ልዩ የመልአከ ሰላምታ የእመቤታችን መልስ እንዴት ያለ ነበር? በሚገርም ሁኔታ እንደዚህ ለረዘመው የመልአኩ ሰላምታ እመቤታችን ምንም አልመለሰችም ነበር፤ እንዲያውም “ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው” ብላ ነበር ያሰበችው፡፡ ሉቃ 1፤29 . እመቤታችን መልአክ በልዩ ሰላምታ ሰላም አለኝ ብላ ቃል እንኳን አላወጣችም! መልአክ ሰላም አለኝ ብላ አንዲት ቃል እንኳን አልተናገረችም፤ ለረጅሙ የመልአኩ ሰላምታ የእመቤታችን ምላሽ “ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው” ብሎ ማሰብ ብቻ ነበር፡፡ የዘመናችን “ባለመገለጦች” የምር መልአክ ተገልጦላቸው ቢሆንማ ምላሻቸው ምን እንደሚሆን ስናስብ በእርግጥም እመቤታችን መንፈሳዊትና የተግባር ሰባኪት መሆኗን እናስተውላለን!! . መልአኩ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣበትን ጉዳይ በረጅም ሐተታ ሲያስረዳት ቢቆይም የእኛ እመቤት ወላዲተ አምላክ ግን ሁለት ጊዜ ብቻ በአጭሩ፤ ግን ደግሞ በጣም መሠረታዊ ነገርን ተናግራለች፡፡ የመጀመሪያው “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” የሚል ሲሆን ሉቃ 1፤34፤ ሁለተኛው ደግሞ “እነሆኝ የእግዚአብሔር ባሪያው አለሁ፤ እንደቃልህ ይሁንልኝ” የሚል ነበር፡፡ ሉቃ 1፤38 እመቤታችን መንፈሳዊት ናትና እንዴት ይሆናል ሳይሆን እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነው የጠየቀችው - በአትኅቶ ርዕስ ራሷን ዝቅ አድርጋ!!! የሚሳነው የሌለ እግዚአብሔር እኔን ይመርጠኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ በሚል ትሕትና!!! ፈቃዱ ከሆነ ደግሞ “አለሁ” አለች፡፡ ትሑት ባትሆንማ ኖሮ ጥያቄዋ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል የሚል በሆነ ነበር፡፡ በእምነት ግን የበረታች ናትና መልአኩ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ባላት ጊዜ ደግሞ “እነሆኝ የእግዚአብሔር ባሪያው አለሁ፤ እንደቃልህ ይሁንልኝ” አለችው፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ለመማር የሚወድ መንፈሳዊ ሰው ካለ ከዚህ የእመቤታችን መልስ በእምነት መበርታትን፣ ራስን ለእግዚአብሔር ፈቃድ አሳልፎ መስጠትን፤ የጌታን ሐሳብ በደስታና በእሺታ መቀበልን ተምሮ ያልፋል!!! . ኤልሣቤጥን ባገኘቻትና ልክ እንደ መለአኩ በረጅም ሰላምታ ሰላም ባለቻትና ስለእርሷ ረጅም ንግግር ባደረገች ጊዜስ የእመቤታችን መልስ ምን የሚል ነበር? “ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች” በማለት በቀጥታ እግዚአብሔርን ወደ ማክበር ነበር የገባችው ሉቃ 1፤46፡፡ ስለእራሷ በተናገረች ጊዜ እንኳን ንግግሯ በቀጥታ እግዚአብሔር በእርሷ ስላደረገው ነገር ብቻ የሚያወሳ ነበር፡- “የባሪያውን ትሕትና ተመልክቷልና . . . ታላቅ ሥራን ሠርቶልኛልና” የሚል! ሉቃ 1፤48-49፡፡ . ሊማር ለወደደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ቃል የማታበዛ ዝምተኛ ሰባኪት ናት!!! አምላክን በመውለዷ የማትጓደድ፤ የክርስቶስ እናት ሆና በነፍሷ ባለፈው ሰይፍ የማትሰቀቅ፤ የአምላክ እናት ሆኜ እንዴት እሰደዳለሁ ብላ የማትኮራ፤ ግብጽ ድረስ ተንከራተትሁ ብላ የማታማርር፤ በክርስቶስ አገልግሎትና የማዳን ጉዞ ውስጥ ከፍጥረት ወገን ሁሉ የተለየ ድርሻና ሱታፌ አለኝ ብላ የማትመጻደቅ ዝምተኛ ሰባኪት ናት እመቤታችን ማርያም! ንግግሯ ቁጥብ፤ ቃላቶቿ የተመጠኑ ግን ደግሞ ነፍስን የሚያረሰርሱና በተመስጦ ሰማየ ሰማያት የሚያደረሱ ልዩ ቃላት!!! . ግንቦት አ
Показати все...
7
Repost from @NIGAT media.FW
" እመቤቴ ማርያም ሆይ ሲመሽም ሲነጋም እሰግድልሻለሁ፡፡ አስፈሪ የሆነ መለኮታዊ ግለትን [ እሳትን ] የወሰነች ማሕፀንሽንም አመሰግናለሁ፡፡ ትሁት ልቡናን ፣ የዋሕ ስብእናን ገንዘብሽ ያደረግሽ ድንግል ሆይ ስምሽን ለማመስገን ከስንፍና እንቅልፍ የነቃሁ አድርጊኝ፡፡ ለውዳሴሽም ፍጹም ትጉ አድርጊኝ ፤ የደም ግባትሽን ፀዳልም በእኔ ላይ አብሪ ፤ ከሰላምሽ አደባባይም ፍጹም የራቅሁ እንዳልሆን ለዘላለሙ አሜን፡፡" [ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ] † † † 💖 🕊 💖
Показати все...
#ሕይወት_ፉክክር_አይደለችም  አስተማሪ ታሪክ አንድ እጅግ በስጦታዎች የተሞላ ጠንካራ ገበሬ ነበር። እና አንድ ጊዜ አምላክ ለዚህ ገበሬ ተገልጦ ሶስት ምኞቶችን ሊያሳካለት እንደሚችል ነገረው። ነገር ግን አንድ መደራደሪያም አቀረበለት። ለእሱ የሰጠውን ለጎረቤቱ እጥፍ አድርጎ ለመስጠት። ገበሬው እየፈራም ቢሆን መቶ ከብቶችን እንዲሰጠው ተመኘ። ወዲያው መቶ ከብቶች አገኘ፤ ባየው ነገርም እጅግ ተደሰተ። ጎረቤቱ ሁለት መቶ እንደተሰጠው ሲያይ ግን ደስታው ሁሉ ጠፋ። ስለዚህ መቶ ካሬ መሬት እንዲሰጠው ጸለየ፤ አሁንም ጎረቤቱ የእሱ እጥፍ እንደተሰጠው እስኪያይ ድረስ ተደስቶ ነበር። ይህ ቅናት ያንገበገበው ገበሬ በተሰጠው ነገር ከመደሰትና የአምላኩን ደግነት ከማድነቅ ይልቅ በመበለጡ እጅግ ተከፋ። ብዙ ነገርም አሰበ፤ አንድ ምኞት እንደቀረው ያውቃል፤ በሚቀጥለው ምኞቱም መበለጥ አልፈለገም። የመጨረሻና ሶስተኛ ምኞቱም አንድ ዓይኔን አጥፋልኝ የሚል ሆነ። አምላክም በገበሬው ድርጊት እጅግ አዘነ። ሕይወት ፉክክር አይደለችም። የአንተ በረከት ያንተ፣ የሌላው ደግሞ የሌላው ነው። ባለህ፣ ባገኘኸውና በተሰጠህ ተደሰት፣ አመስግን እንጂ የሌሎችን እያየህ አትቅና። ቅናት እውር ያደርጋል። የራስን ጸጋ እንዳያዩ ይከለክላልና ራስህን ከአጉል ቅናት ጠብቅ።
Показати все...
👍 2
Показати все...
የስበት ሕግ ሲበረበር ክፍል 1 || the Law of Attraction || መምህር ዘበነ ለማ

Показати все...
የስበት ሕግ ሰይጣንን መቀበልና ሰይጣን መሆን ነው || The Law of Attraction:Exposed!!! || ክፍል 2

Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ወደ_ተሳሳተ_ምንጭ_አትሂድ በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር ገበሬ አንዲት ላም ነበረችው። ላሟን እጂግ ከመውደዱ የተነሳ አብዝቶ ይንከባከባታል። ጥሩ ሳር ባለበት ቦታ እየወሰደ ይመግባታል። በአካባቢው ወዳለ ንጹህ ምንጭ እየወሰደም ውኃ ያጠጣታል። ነገር ግን ላሟ ሁልጊዜ ትከሳለች። ከቀን ወደ ቀን የበለጠ ቀጭን ትሆናለች። ሰውዬውም እጅግ እየተገረመና ግራ እየገባው "ላሜ እንዲህ እየተንከባከብኳት ለምንድን ነው የምትከሳው?" ይል ነበር። መልሱን ለማግኘትም ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። አንድ ቀን፥ ድንገት ውኃ ጠምቶት ከምንጩ ለመጠጣት ዝቅ ሲል አንድ ነገር አስተዋለ። ውኃው ውስጥ የሆኑ አስፈሪ ነፍሳት ነበሩ። አዎ ምንጩ በአለቅት ተወሩ ነበር። ስለዚህም ላሟ በየቀኑ ከምንጩ በጠጣች ቁጥር ከውኃው ጋር አለቅቶች ወደ ሆዷ ይገቡ ነበር። ገብተውም ደሟን እየመጠጡ ያዳክሟታል። የዚህ ዘመን ሰው መንፈሳዊ ሕይወትም እንደዚህ ዓይነት ነገር ነው ያጋጠመው። ጥሙን ለማርካት ውኃ የሚጠጣው ወደ ተሳሳተ ምንጭ በመሄድ ነው። ወዳጄ  አንተም ጥምህን ለማርካት ወደ ተሳሳተ ምንጭ አትሂድ! የአቡነ ሺኖዳ ሶስት በገበያ ላይ የዋሉ ድንቅ መጽሐፍት ገዝታችሁ እንድታነቧቸው ተጋብዛችኋል
Показати все...
👍 4
"ስብከት እና አነቃቂ ንግግር ምን እና ምን ናቸው?" on YouTube https://youtu.be/hRm4bygZil0?si=G3EnvYCkAeIk8tMS
Показати все...
ስብከት እና አነቃቂ ንግግር ምን እና ምን ናቸው? | ኤማሁስ ፖድካስት Ep2

ስብከት ምንድን ነው? ልዩ ጠባዕያቱ ምን ምን ናቸው? ከአነቃቂ ንግግርስ በምን ይለያል? ይኼን እና መሰል ጥያቄዎች የተዳሰሱበት ውይይት ነው። #podcast #ስብከት #አነቃቂ ንግግር (Motivational Speech) #emmaus ~ ስለ ግብረሰዶማዊነት በኤማሁስ ፖድካስት የተደረገ ውይይት

https://youtu.be/VnqdRiVrQLM?si=RI579GymUkrWbItK

~ ስለ ኤማሁስ መንገደኞች የተደረገ ውይይት

https://youtu.be/0Ukw7Gm_Nrg?si=vPGiJ2LJ08COdYJ-

~ ግእዝ ለመማር

https://youtu.be/MnAAQa7h1bQ?si=1K-W82UDgo4FWBnh

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.