cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሚኒሊክ TV

He is still our hero!

Більше
Рекламні дописи
1 290
Підписники
+324 години
+307 днів
+12730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 1
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 3
ይኸውም፦ 1) ሀምሌ 10/2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ አውቶብስ ተራ እና በመርካቶ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ስለምን ለአማራ ተፈናቃዮች ድምጽ ሆንክ በሚል ታስሯል። 2) ጳጉሜ 3/2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ እና በአባ ሳሙኤል ታስሯል። 3) መጋቢት 28/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) ታስሯል። 4) ነሃሴ 4/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ፣ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ እና በቂሊንጦ ታስሯል፤ በአማራዊ ማንነቱ እና በጋዜጠኝነት ሙያው ለህዝብ ድምፅ በመሆኑ እና ስር ነቀል ስርዓታዊ ለውጥ እንዲመጣ በመታገሉ አሁንም በግፍ እስር ላይ ይገኛል። ዓባይ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ-ደቡብ እዝ መከላከያ ካምፕ ለ6 ወራት ያህል በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ታግቷል፤ በሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮም ከ2 ወራት በላይ ከሌሎች የአማራዊ ማንነት ታጋቾች ጋር በሩ እንዲዘጋ ተደርጎ ታስሯል፤ ከሜክሲኮ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተዛውሮም ታስሯል። ዓባይ አሁን ላይ የፈጠራ የሽብር ክስ ተመስርቶበት በቂሊንጦ እስር ቤት ይገኛል። 4 ዓመት ከ6 ወራት በላይ በታች አርማጭሆ እና በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች በባህል እና ቱሪዝም የፕሮሞሽን ባለሙያነት እንዲሁም በህዝብ ግንኙነት ሙያ ያገለገለው ዓባይ ዘውዱ ህዳር 1/2010 ዓ/ም ከዝዋይ ማ/ቤት ተፈታበት ጊዜ ጀምሮም በጋዜጠኝነት ሙያው በሽብር ተግባር የተሰማራውንና የህወሀት ኢህአዴግ ተቀጥላ የሆነውን የኦህዴድ ብልጽግን አገዛዝና የስሪቱን ገመና በማጋለጥ ጭምር እየታገለ ይገኛል። ዓባይ ዘውዱ እና ቤተሰቦቹ ስለ እውነተኛ ለውጥ በሚል ኢሰብአዊነትን በመቃወም የከፈሉት መስዋዕትነት ከባድ ነው። በማንኛውም ስርዓታዊ ፈተና ሁሉ ከጎኑ የቆሙ ወገኖችን በሙሉ በእጅጉ ያመሰገነው ዓባይ ህዝባዊ ትግል ማሸነፉ አይቀርም ይሏል። ፍትሃዊ የሆነው የአማራው የህልውና፣ የነፃነት፣ የክብር፣ የእኩልነት እና የአብሮነት ትግል ያሸንፋል! ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት ይሁን! ፍትህ ለሁሉም! #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://t.me/minilikcom
Показати все...
ሚኒሊክ TV

He is still our hero!

ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍: ⭐️⭐️⭐️💡ዓውደ ፋኖ💡⭐️⭐️⭐️ 🫵 🫵 እስኪ… አባይን በጭልፋ‼️ "#አይበገሬው ሰሜናዊ ኮከብ" ዝና እና ክብር፣ ዓለም ዓቀፍ ሽልማትም በተገቢው ስፍራ እና ቦታ፣ በፍትሃዊ ማደሪያው ይገኝ ዘንድ ምድሪቷ በሀቅ መንገድ ብትራመድ ኖሮ… ይሄን ብርቱ ከዐለት የጠነከረው ሰው የሚያልፈው፣ አንዳች ክብረ-ሞገስ ባልተገኘ… #ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ… አዎ… ስለርሱ ላወራችሁ ነው። የዛሬው የዓውደ ፋኖ ገፅ፣ ልዩ እንግዳዬ ነው። ስለዚህ… መንጋ እና ቲፎዞ አልባ ታጋይ፣ ጥቂት ልል ብችል እንጅ… የዘመኑን ምልዐት፣ የትውልድ ውርስ በደም ዋጋ የታጀበ፣ የሰቆቃዎ ዐምሓራ ዘጽዐት አውድን በፅናት የተሻገረ፣ ዛሬም በተጋድሎ መስመር ላይ ስለሚገኘው መርኸኛ ታጋይ፣ ስለዚያ… "የግፉዐንን መሪር ለቅሶና ዋይታ በራማ እንደሰሙት መላዕክት መሳይ…" የፍትህ ቃታቾች ሰብዐውያን ድምፅ ስለሆነው ታላቁ ሰው… በዚህች ቅፅበት እና ገፆች ለማውሳት አልደፍርም። እርሱ ግን፣ ፍፁም ትሁት ነው። እጁን ጨብጦ ከፍ በማድረግ "ትግልን ከኔ በላይ ለዐሳር" ሲል አታዩትም። ሲበዛ አይን አፋርና የደግነት ባለ ፀጋ ነው። በጋዜጠኝነት ጥቂት ደሞዙ… 4 በኦሮሚያ ክልል ወላጆቻቸው በግፍ ያጡ፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን ሰብስቦ ያሳድጋል፣ ዛሬ ግን እጁ አጥሮት ብቻውን እየቆዘመ ነው። አባይ ዘውዱ፣ ያልተገለጠ መፅሀፍ ነው። ይህ፣ ሰው… ለውጥ መሳዩ ጎርፍ ገፍቶ ያመጣው ሰሞነኛ ፖለቲከኛ፣ የዩቲዩብ አማላይ ቅፈላ ወደ ሜዳ ያወጣው ጋዜጠኛ አይደለም። የማወጋላችሁ በጀብዱ የተሞላው ታሪከ ማስታወሻው… #ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ… ያልተዘመረለት፣ #ካባ ያልደረብንለት፣ የሰራና በሃቅ የታገሉን ከዋክብት ከተደበቁበት ቆፍረን በማውጣት… አክባሪ እና አመስጋኝ ያለመሆናች ገመናን ያሳብቅብናል። አባይ ዘውዱ፣ሰሜናዊ ኮከባችን… ዛሬም…በዚያው ግዞት ቤት በር እንደተዘጋበት ነው። በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ ዳግም እስር ላይ የሚገኘው ዓባይ ዘውዱ ማን ነው⁉️ ዓባይ ዘውዱ ደመቀ የተወለደው በድሮው አጠራር በሰሜን ጎንደር በጭልጋ ወረዳ፣ ዳዋ ዳንጉራ ልዩ ስሙ መንደር ጊዮርጊስ በተባለ ለማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ አዋሳኝ በሆነውና መዳረሻውን ሱዳን ድረስ ያደረገው ጓንግ ወንዝ በሚለዬው ቀበሌ ነው። ዓባይ ዘውዱ በጭልጋ ወረዳ ጊዮርጊስ መንደር ይወለድ እንጅ እድገቱና እስከ 6ኛ ክፍል የተማረው በድሮው አጠራር ታች አርማጭሆ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለአስተዳደር ያመች ዘንድ በሚል ማዕከላዊ አርማጭሆ ተብሎ ራሱን በቻለው ወረዳ ማሰሮ ደንብ ነው። በልጅነቱ ወደ ማዕከላዊ አርማጭሆ የተወሰደው አባቱ አቶ ዘውዱ ደመቀን እና ቤተሰቦቹን "ለለውጥ የታገሉ ፣ እምቢተኛ ናቸው፣ እየተገዙን አይደለም" በሚል ደርግ አባቱን ወደ ጭልጋ አፍኖ በመውሰድ ማሰር እና ማንገላታቱን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ዘውዱ ደመቀ ብቻ አልነበረም። አባቱ ደመቀ ሁነኛው፣ ታላቅ ወንድሙ መልካሙ ደመቀ እና ታናሽ ወንድሙ ጌጡ ደመቀምከመንደር ጊዮርጊስ ቀበሌ በዳንጉራ እስር ቤት አብረው ታስረው ነበር። ዘውዱ ደመቀ ግን "ዋናው ነው" በሚል ተፈርጆ ወደ ጭልጋ ወረዳ አይከል ማ/ቤት ተወስዶ ከ6 ወራት የግፍ እስር በኋላ፣ ባለቤቱን ባንች አምላክ በለጠን እና ልጆቹን ይዞ የጓንግን ወንዝ ከማዶ እና ማዶ ሶስትና አራት ረዣዥም እንጨት ጣል በማድረግ በሰራው ጊዜያዊ መሻገሪያ ድልድይ ወደ ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ተሻገረ። የቤተሰቡ በኩር ልጅ የሆነው ዓባይ ዘውዱ በጭልጋ ወረዳ መንደር ጊዮርጊስ ተወልዶ በአርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ ሳንኪ ሚካኤል ነው ያደገው። ዓባይ የተወለደበት ብቻ ሳይሆን ያደገበት አካባቢም በአብዛኛው በተራራ ሰንሰለት እና በተፈጥሮ የታደለ አካባቢ ነው። ዓባይ የት ተማረ⁉️ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እስከ 6ኛ ክፍል በማሰሮ ደንብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተማረ ሲሆን፣ የ7ኛ ክፍል ትምህርቱን ደግሞ በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ት/ቤት ተከታትሏል። ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን የተከታተለው ደግሞ በባህር ዳር ነው። ይኸውም፦ 1) 8ኛ ክፍል_በባህር ዳር ቁልቋል ሜዳ ት/ቤት 2) 9ነኛ እና 10ኛ ክፍል_በባህር ዳር ፋሲሎ ት/ቤት 3) 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ትምህርቱን በባህር ዳር መሰናዶ ት/ቤት እንዲሁም 4) የዩኒቨርስቲ ትምህርቱንም በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ ካምፓስ የተከታተለ ሲሆን በጋዜጠኝነትና ግንኙነት (Journalism and Communications) ትምህርት ዘርፍ 3.66 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ እና በሽልማት ተመርቋል። የትግል ሁኔታን በተመለከተ? በተለያዩ ጊዜያት በልዩ ልዩ በመድረክ እና በጽሁፍ ሲያደርገው የነበረው ትግል እንዳለ ሆኖ በዋናነት ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ነው። የህወሀት  ጠፍጥፎ የሰራው ሎሌው የብአዴን አስተዳድርን አምርሮ በመጥላት "አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ" (አንድነት)ን ተቀላቅሎ ታግሏል። በተለይ በወያኔ በኃይል ከአማራ የተወሰደው የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ እንዲሁም በሱዳን በጎንደር በኩል የሀገር ሉኣላዊነት ተደፍሮ ለሱዳን በወያኔ የተሰጠው ሰፊ ለም መሬት እና በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ላይ ይደርስ የነበረው ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል ምክንያት ወደ ትግል በመግባት ከብርቱ ለውጥ ፈላጊ እና የነቁ ጓደኞቹ ጋር በመሆን በአብርሃጅራ ከተማ የአንድነት ፖርቲን ቢሮ በመክፈት ጭምር አገዛዙን እንዲታገል ገፋፍቶታል። በለውጥ ትግሉ መስዋዕት ከሆኑት ጓዶቹ መካከል ነፍሳቸውን ይማርና እነ ደስታው ተገኘ፣ አንጋው ተገኘ እና ታናሽ ወንድማቸው ባበይ ተገኘ ጋር በመናበብ አገዛዙን አምርሮ ታግሏል። ደስታው ተገኘ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ አገዛዙን ለመታገል ሲመለስ በአብደራፊ/ምድረገነት አካባቢ ባጋጠማቸው ውጊያ ዶ/ር ብርሃኑ ከተባለ የትግል ጓዱ ጋር ስለ አማራ ህዝብ እና ስለ ሀገር ሲል በጀግንነት በክብር የተሰዋ ሲሆን ወንድሞቹ አንጋው ተገኘ እና ታናሻቸው ባበይ ተገኘ ደግሞ እምብኝ ለወገኔ በማለት በመጋቢት 2016 ዓ/ም ኦህዴድ መራሹን የብልጽግና አገዛዝ በነፍጥ ሲፋለሙ በክብር የተሰው ጀግኖች ናቸው። ዓባይ ከእነ እንግዳው ዋኘው፣ ስርዓቱ ለሰላማዊ ትግል ዝግጁ አይደለም በማለት ወደ ኤርትራ በማቅናት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅለው ሲታገሉ ከነበሩት ከእነ አብርሃም ልጃለም፣ ከአለልኝ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን በምዕራብ ጎንደር ዞን አብርሃጅራ ሲታገል ነበር። ከእነ አለላቸው አታለል፣ ቀለብ ስዩም፣ ተገኘ ሲሳይ፣ በላይነህ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞ፣ ፈረጃ ሙሉ፣ ሰጠኝ ቢልልኝ፣ አወቀ፣ እንዲሁም ከአግባው ሰጠኝና ከሌሎች ጀግኖች ጋርም በመናበብ ለእውነተኛ እና ስር ነቀል ለውጥ ይታገል ነበር። ዓባይ ዘውዱ ከጓዶቹ ጋር በመሆን ሲታገል ስለደረሰበት እስር፦ (1) በወያኔ መሩ ኢህአዴግ ዘመን ከ2/25/2007 ጀምሮ እስከ ህዳር 2010 ድረስ በሽብር ክስ 4 ዓመት ከ2 ወር ተፈርዶበት ታስሯል። በአብርሃጅራ፣ በጎንደር 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣በባህር ዳር 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ፣ በቂሊንጦ፣ በሸዋሮቢትና በዝዋይ በእስር ተሰቃይቷል። (2) በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ደግሞ ስለ ሰፊው የአማራ ህዝብ እና ስለተገፉ ወገኖች ድምፅ በመሆኑ 4 ጊዜ ታስሯል።
Показати все...
ሚኒሊክ TV

He is still our hero!

👍 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.