cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office

Більше
Рекламні дописи
204
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
+230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
የስልጤ ዞን ክፍት የዐቃቤ-ህግ የስራ ማስታወቂያ SILTIE ZONE PUBLIC-PROSECUTOR LEGAL VACANCY
Показати все...
⚖️በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office⚖️ የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በፍትህ ስርዓት ማሻሸያ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት አካሄደ። ሚያዚያ 29/2016 (አለም ገበያ ) የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በፍትህ ስርዓት ማሻሸያ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት አካሂደዋል። በፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ዓቃቤ ህግ ባለሙያ በሆኑት አቶ አህዲን ሁሴን ለባለድርሻ አካላት ቀርቧል። የፍትህ ስርዓት መሻሻያ በዋናነት በየደረጃው የሚስተዋሉ    ችግሮችን በመለየት ለመፍታት የአጭር ጊዜ ፣የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ በማቀድ የህዝቡን ፍትህ የማግኘት መብት ማረጋገጥ እና የለወጥ አቅሞችን በሚያሳትፍ መንገድ ውጤት ለማምጣት  የጋራ ጥረትና ርብርብ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተማላክቷል። የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ፣ፍትሀዊ፣ወጪ ቆጣቢ፣ተደራሽ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የተቀናጀ የፍትህ ማሻሻያ ኮሚቴ ሚና የጎላ ስለመሆኑ ተገልጿል። በውይይቱ መድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ከንቲባ አቶ ሙሰፋ ሸ/ነስሮ የፍትህ ማሻሻያ ኮሚቴው ለፍትህ በጣም አጋዥ በመሆኑ በላድርሻ ተቋማት በጋራም በተናጠል በመስራት ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ እንድሆን ማድረግ አለባቸው በማለት ተነግረዋል። በቀረበው ሰነድ ባለድርሻ አካላት ሰፋ ያለ ወይይት በማካሄድ በላድርሻ ተቋማት የጋራ የፍትህ ማሻሻያ ዕቅድ አቅደው ለፍትህ ጽ/ቤት እንዲያስገቡ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል። JOIN                                                     👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office just like our page and Telegram channal share your friends and others.                                                                                                                             👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                                                                                                                   1. TELEGRAM Channel and discussion group 👉👉 https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL                                                                                             2. Facebook page 👉👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61553801575660 TELEGRAM Channel and discussion group                                                                                                                                                👇👇👇👇👇                                                                                       https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

⚖️በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office⚖️ ✍ዜና የወንጀል-ችሎት ሚያዝያ 18/2016 #በ8 አመት ጽኑ እስረት እንዲቀጣ ተወሰነ !! ✍✍ዜና ችሎት ✍ከሳሽ -የአለም-ገበያ ከተማ አስተዳደር ዐ/ህግ ተከሳሽ- ተማም ባሙድ   አድራሻ:- አለም-ገበያ 01  ቀበሌ። 👉ተከሳሽ በወንጀል ህግ አንቀፅ 675/1/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ በቀን 17/06/2016 ዓ.ም በዚሁ በአለም-ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ከቀኑ 11:00 አካባቢ ከሙስጠፋ አ/ስራጎ  125 CC DISCOVER ሞተር ወስዶ የሰወረ በመሆኑ በፈጸመው የእምነት ማጉደል ወንጀል ክስ የከተማ አስተዳደሩ ዐ/ህግ በከተማዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ እቅርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት የግራ ቀኙን ጉዳይ ሲያከራክር የነበረዉ የከተማዉ ፍርድ ቤት በዛሬው እለት ሚያዝያ 18/2016 በዋለው የወንጀል ችሎት ዐ/ህግ ያቀረባቸዉን ሁለት ማክበጃዎች ማለትም ከዚህ በፊት በተመሳሳይ የሞተር መሰወር/የእምነት ማጉደል በዚሁ ፍ/ቤት ተከሶ የተወሰነበት እና እስራቱን ጨርሶ እንደወጣ ድጋሚ ይህን ወንጀል መፈፀሙን ሙያዉ አድርጎ የያዘ መሆኑን እና ይህን ወንጀል የፈፀመዉ የበፊቱን ወንጀል ከፈፀመ ገና አምስት አመት ሳይሞለዉ በመሆኑ የወንጀል ድርጊት ደጋጋሚ የሚሉ ማክበጃዎችን ከግምት ዉስጥ በማስገባት እና ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት  ተከሳሽን በ8 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ፍርድ ሰጥቷል። ወንጀልን በጋራ እንከላከል!! የአለም-ገበያ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት!! JOIN                                                     👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office just like our page and Telegram channal share your friends and others.                                                                                                                             👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                                                                                                                   1. TELEGRAM Channel and discussion group 👉👉 https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL                                                                                             2. Facebook page 👉👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61553801575660 TELEGRAM Channel and discussion group                                                                                                                                                👇👇👇👇👇                                                                                       https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

⚖️በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office⚖️ 🌟⭐️ የስጦታ ውል ስምምነት ምንንነት በጥቂቱ ⭐️🌟 👉 የስጦታ ምንነት:- በአጭሩ ለማስቀመጥ ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው  ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው። በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው። 👉 የስጦታ ልዩ ባህሪያት:- በመርህ ደረጃ ስጦታ ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ሰጪው እራሱ የሚያድርገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ለይ ብቻ ነው።ስጦታ አደርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በህጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን መግለፅ ይኖርበታል። ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም። 👉 የስጦታ ሥርዓት ፎርም:-  ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ  ወይም በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል። 1) በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ህጉ ያስረዳል። በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ህግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት። 2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም መሰረት ሊሰጥ ይችላሉ። ስጦታ እንደማድረግ የማይቆጠርባቸው ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች። 1) ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ ወይም የራሱን እቃ ያለ ዋጋ ዝግጁ ማድረግ ስጦታ አይባልም የፍ/ህግ አንቀጽ 2430             2) መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ስራ ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2432። 3) አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መክፈል ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2433። 4) ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም ኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም የፍ/ህግ 2431።         ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች*    በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ለይ የተደረገው ስጦታ በህጉ በተጠቀሱት  በተለያየ ምክንያቶ ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-        1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን    ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ  ፈራሽ ሊሆን ይችላል ።የፍ/ህ አንቀጽ 2437        2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ህገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ህ አንቀጽ 2438       3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ።የፍ/ህ አንቀጽ 2439       4ኛ በ ፍ/ህ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።   5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል። JOIN                                                     👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office just like our page and Telegram channal share your friends and others.                                                                                                                             👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                                                                                                                   1. TELEGRAM Channel and discussion group 👉👉 https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL                                                                                             2. Facebook page 👉👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61553801575660 TELEGRAM Channel and discussion group                                                                                                                                        👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                      https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

⚖️በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office⚖️ የ10 ዓመት ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ ተሰዉሮ የነበረዉ ተጠርጣሪ ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረደ የ10 ዓመት ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ ተሰዉሮ የነበረዉ ተጠርጣሪ ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር መዋሉ የዞኑ ፖሊስ ገለፀ። በዞኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረደ በሙጎ ከተማ ልዩ ስሙ ሀሊቾ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተጠርጣሪ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 4:30 ግድም ለጊዜው ምክንያቱ በግልፅ ባልታወቀ አኳሀን ከራሱ አብራክ የተገኘን የ10 ዓመት ታዳጊ ሕፃንን ከመኖሪያ ቤቱ ጓሮ በመውሰድ መሬት ላይ አጋድሞ በቢላዋ አርዶት ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ ለጊዜው ከአካባቢው ተሰዉሮ እንደነበር የስልጤ ዞን ፖሊስ ገልጿል። በመሆኑም ወንጀል መፈፀሙ መረጃ የደረሰዉ የወረዳው ፖሊስ ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር በመሆን ድርጊቱ ከተፈፀመ ከደቂቃዎች በኋላ በፍጥነት በተደረገ ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን ከገባበት ገብቶ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ የሟቹን አስክሬን በማንሳት ወደ ወራቤ ኮምፕርሄኔሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመላክ አስክሬኑን በማስመርመር የሟች በድን ገላ በክብር እንዲያርፍ ለቤተሰቦቹ ተመላሽ መደረጉ ተገልጿል። ተጠርጣሪዉን ከተደበቀበት ጫካ ተደርሶበት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቱ ያበረከተዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበር ያለዉ ፖሊስ ህብረተሰቡ ላደረገዉ እገዛ አመስግኗል። የተፈፀመው ድርጊት አፀያፊና አሳፋሪ መሆኑና ድርጊቱ የአካባቢዉን መሀበረሰብ በጣም ያሳዘነ መሆኑ የገለፀዉ ፖሊስ ምርመራዉ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተጣርቶ መዝገቡን በአጭር ጌዜ ዉስጥ ለሚመለአተዉ የህግ አካል የሚላክ መሆኑ የዞኑ ፖሊስ የወረዳዉን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል። #መረጃዉ:- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ነዉ። JOIN                                                     👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office just like our page and Telegram channal share your friends and others.                                                                                                                             👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                                                                                                                   1. TELEGRAM Channel and discussion group 👉👉 https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL                                                                                             2. Facebook page 👉👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61553801575660 TELEGRAM Channel and discussion group                                                                                                                                        👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                      https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL
Показати все...
⚖️በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office⚖️ ⭐️🌟ከባንኮች የራሳችን ያልሆነን ገንዘብ ማውጣት፣ ማስተላለፍ ወይም ከሌላ ሰው መቀበል ያስጠይቃል?🌟⭐️ የወንጀል እና የፍትሐብሔር ተጠያቂነት ሊኖር ይችላል። 1. #የወንጀልን_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ በሳይበር ምህዳር መስፋፋት ምክንያት አዳዲስ ወንጀሎችና አዳዲስ የወንጀል አፈፃፀም ስልቶች በመፈጠራቸው እንዲሁም  በሃገሪቱ የኮምፒውተር ወንጀልን የሚገዙ መሰረታዊም ሆነ የሥነ-ሥርዓት ሕጎች በበቂ ሁኔታ ባለመኖራቸው ምክንያት የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ወጥቶ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ አዋጅ ታዲያ በኮምፒውተር አማካይነት የሚፈፀሙ የማታለል ወንጀል፣ ማለትም በተጭበረበረ መንገድ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት የኮምፒውተር ዳታን በመለወጥ፣ በማጥፋት ወይም ሌላ ማንኛውንም ጉዳት በማድረስ ሌላ ሰው ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደረሰ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 50,000 በሚደርስ መቀጮ ወይም ወንጀሉ ከባድ በሆነ ጊዜ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ ይደነግጋል። ገንዘቡን ራሱ በተለያየ የኤሌክትሮኒክስ መንገዶች የፈፀመው ሰው በላይኛው ድንጋጌ ሊጠየቅ ይችላል። ገንዘቡ የተላለፈለት ወይም የተቀበለ ሰውስ? የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ የወንጀል ፍሬ ወይም ውጤት የሆኑ ንብረቶችን መያዝ፣ መደበቅ ወይም ማስቀመጥ ኃላፊነት እንደሚያስከትል በግልፅ ይደነግጋል። ይህ የመሸሸግ ወንጀል በሁለት መንገዶች ሊፈፀም ይችላል። የመጀመሪያው ወንጀለኞቹን ለመርዳት ወይም በቀጥታ ከወንጀል ድርቲቱ ጥቅም ለማግኘት ታስቦ ሲፈፀም ሲሆን ሁለተኛው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን ማወቅ ሲገባቸው በቸልተኝነት ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ገንዘቡን ተቀብሎ ይዞ መገኘት ነው። ገንዘቡ የሚላክበት ምክንያት መኖሩን እና አግባብነቱን እንዳጣራ ሕጉ ይጠብቅብናል። የራሱን ገንዘብ የሚልክበት ምክንያት የሌለው ሰው ገንዘብ ሲያስተላልፍልን መጠየቅ እንዲኖርብን ያደርጋል። በተለይ የአንድ ባንክ ሥርዓት መበላሸቱን የሚገልፅ ዜና በማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች የዜና ምንጮች በስፋት ተወርቶ ሲገኝ ገንዘቡ ተሰርቆ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚያስቸሉን አመላካች ነገሮች በመሆናቸው ከወንጀል ተጠያቂነት አናመልጥም። ገንዘቡ ከትክክለኛ ባለቤቱ በወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተወሰደ መሆኑ ሲረጋገጥ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል። ድርጊቱ በኮምፒውተር ሥርዓት አማካኝነት የተፈፀመ እንደመሆኑ መጠን በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጁ ሊታይ ቢችልም፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች በተጨማሪ የአዋጁ ድንጋጌ ላይ ያለውን ቴክኒካል ቃላት አያሟላም የሚባልበት ሁኔታ ቢኖር ድርጊቱ መደበኛውን የስርቆት ወንጀልን ሊያቋቁም ይችላል። በባንኩ የኮምፒውተር ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ያላደረሰ ሰው፣ ነገር ግን 2ሺ ብር ሊያወጣ ጠይቆ ኤቲኤም ማሽኑ 5ሺ ብር ቢሰጠው ግለሰቡ ልዩነቱን እና የርሱ ያልሆነውን 3ሺህ ብር የመመለስ ግዴታ አለበት። ያንን ባያደርግ አግኝቶ በመደበቅ ወንጀል ሊጠየቅ ይችላል። ይህ ወንጀል አንድ ሰው ከህጋዊ መንገድ ውጪ ንብረት አግኝቶ በዚሁ ንብረት ያለአግባብ ለመበልጸግ በማሰብ ንብረቱን ለመደበቅ የሚፈጽመው የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ማንም ሰው የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን በስህተት ወይም ባልታሰበ ድንገተኛ አጋጣሚ ነገር፣ ከባለንብረቱ ፈቃድ ውጭ በሆኑ ማናቸውም ሁኔታ ከባለቤቱ እጅ ወጥቶ በእጁ የሚገኝን ንብረት ወይም እቃ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ካደረገ በወንጀል ያስጠይቀዋል፡፡ ይህንን የፈፀመ ሰው በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ያስቀጣል ሲል የወንጀል ህጉ ደንግጓል፡፡ 2. #የፍትሐብሔር_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡ ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡    1ኛ. ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ፤    2ኛ ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም     3ኛ. የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ የማይቀርብበት መሆኑ ናቸው፡፡ JOIN                                                     👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ጽ/ቤት- Siltie Zone Alem Gebeya Town Adminstration Justice Office just like our page and Telegram channal share your friends and others.                                                                                                                             👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                                                                                                                   1. TELEGRAM Channel and discussion group 👉👉 https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL                                                                                             2. Facebook page 👉👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61553801575660 TELEGRAM Channel and discussion group                                                                                                                                        👇👇👇👇👇👇👇👇👇                                                                                      https://t.me/ALEMGEBYA_OFFICIAL
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.