cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

Більше
Рекламні дописи
9 036
Підписники
-724 години
+2817 днів
+1 26630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ተፈቷል! ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ከወራት እስር በኋላ ብዛሬው እለት ተፈቷል።
Показати все...
👍 41🔥 6 3
ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከሰራዊት አባላቱ ጋር ለግምገማ በተቀመጡበት የከባድ መሣሪያ ድብደባ ተፈፀመባቸው! በዚህም ከፍተኛ አዛዦቹን ጨምሮ ሕይወታቸው ያለፈ መስመራዊ የጦር መኮነኖችና የጦሩ አባላት መኖራቸው ነው የተሰማው! በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ከታዳጊዋ ሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት ይስማ ንጉስ በተባለ ቀበሌ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አዛዦች ከዕዙ ሰራዊት አባላት ጋር ግምገማ እያደረጉ ባለበት ከፋኖ በተወረወረ ሞርተር ከባድ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የአማራ ድምፅ ሚድያ የወሎ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። በዚህ የሞርተር ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ሕይወታቸው ያለፈ መስመራዊ የጦር መኮነኖችና የጦሩ አባላት መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በርካቶች ቆስለው ወደ ውጫሌ እና ሐይቅ ከተሞች ለሕክምና መወሰዳቸውን ጣቢያችን አረጋግጧል። የሞርተር ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ሰኔ 05/2016 ዓ/ም እኩለ ቀን ገደማ ሲሆን በወቅቱ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አዛዦቹ በተገኙበት ግምገማ እየተካሄደ ነበር ተብሏል። መከላከያ ሰራዊቱ በይስማ ንጉስ ቀበሌ ለግምገማ መቀመጡን መረጃው የደረሰው በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ልጅ እያሱ ክ/ጦር ሜካናይዝድ ክፍል ቅፅበታዊ የሆነ የሞርተር ጥቃት መፈፀሙን ነው የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ ሻለቃ ደምሌ ጣፋጭ ለአማራ ድምፅ ሚዲያ የገለፀው። "ንፁኋንን የመጨፍጨፍ አዲስ ኦፕሬሽን ለመውሰድ ግምገማ እያካሄደ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ በተከታታይ ሦስት ጊዜ ሞርተር ወርውረናል" ሲል ከጣቢያችን ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው ሻለቃ ደምሌ፡ ሦስቱም የሞርተር ጥቃት ታርጌትድ ሆኗል በዚህም በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ችለናል ብሏል። ከሞርተር ጥቃቱ በኋላ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹን አጅበው በመጡ ሁለት ዙ23 መሣሪያዎች በይስማ ንጉስ ዙሪያ ያሉ ተራራማ አከባቢዎች ሲደበደቡ መዋላቸው ተሰምቷል። ከወደ ውጫሌ ከተማ የመጣው ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ኃይል በጥቃቱ የተገደሉ የከፍተኛ አዛዦችንና መስመራዊ የጦር መኮነኖችን እንዲሁም የሰራዊት አባላቱን አስከሬን እና ቁስለኞችን በኦራል ጭኖ ወደ መጣበት መመለሱንም የአማራ ድምፅ የወሎ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። ጥቃቱ በተፈፀመባት ይስማ ንጉስ ቀበሌ ቁስለኛ ለማንሳት የመጡት ወታደሮች "አመራሮቻችን የሞርተር ጥቃት ሲፈፀምባቸው ለምን ዝም አላችሁ?" በሚል በርካታ የቀበሌዋን ነዋሪዎች መደብደባቸውም ነው የተገለፀው። ተጨማሪ ዝርዝር!👉 https://www.youtube.com/watch?v=FDkU0ds8708&t=12s
Показати все...
ሰበር ዜና!የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዦች ላይ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ተፈፀመባቸው!መርሳ ከተማ ዙሪያ የተፈፀመ አስደናቂ ኦፕሬሽን!The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 34 3
Показати все...
ዜና! ፋኖ የፈፀመዉ የጎንደሩ ታላቅ ጀብድ! ከበባ ሰብሮ የወጣዉ የፋኖ ሀይል የወሰደዉ አፀፋዊ ዕርምጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 6 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 41 11
የፋኖ ኃይሎች ዛሬ አዳራቸውን ከመርሳ በቅርብ ርቀት በነበረ የፖሊስና ሚኒሻ ካምፕ ላይ በወሰዱት እርምጃ ከባድ ኪሳራ ማድረሳቸው ተሰማ! በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ በመርሳና በሲሪንቃ መካከል ልዩ ስሙ ገምቦ በር በተባለ አከባቢ በነበረ የፖሊስና ሚኒሻ ካምፕ ላይ ዛሬ አጥቢያ ለሊቱን በተወሰደ እርምጃ 13 የሚኒሻና ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ከ25 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ የገምቦ በር ቀበሌ ነዋሪዎችን እና እርምጃውን የወሰዱ የፋኖ አባላቱን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል። ከ25 በላይ የሚሆኑት ቁስለኞች ማርፈጃውን በፈረስ ጋሪ እና በወታደራዊ ፖትሮል ተጭነው ለሕክምና የሃብሩ ወረዳ መቀመጫ ወደ መርሳ ከተማ መወሰዳቸውንም ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልፀዋል። በወታደራዊ ካምፑ ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ሰኔ 06/2016 ዓ/ም አጥቢያ ለሊት አስር ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው መሆኑም ነው የተነገረው። በዚህ ጥቃት 13 የሚኒሻና የፖሊስ አባላት ሲገደሉ ከ25 በላይ የሚሆኑት የቆሰሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል አብዛኻኛውን ቁጥር የሚይዙት የሚኒሻ አባላት መሆናቸውን ነው የገምቦ በር ቀበሌ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ የገለፁት። እርምጃውን የወሰዱት በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ መቅደላ ፅናት ክፍለጦር ስር ከሚገኙ ከሻለቃ አንድ ከሻለቃ ሁለትና ከሻለቃ ሦስት የተወጣጡ የአንድ ሻምበል ፋኖ አባላት መሆናቸውም ታውቋል። በዚህ ኦፕሬሽን 18 ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ማርከን ታጥቀናል ሲል ሻምበሏን የመራው የክ/ጦሩ ሰው ሀብት ክፍል ኃላፊ ፋኖ ፈቃዱ አሰፋ ለአማራ ድምፅ ገልጿል። ፋኖ ፈቃዱ ከአማራ ድምፅ ጋር ባደረገው ቆይታ፡ኮሎኔል ፈንታው ሙሃቤ ያስተማረንን የሽምቅ ውጊያ ሳይንስ የተጠቀምንበት አስደናቂ ኦፕሬሽን ሲል በገለፀው በዚህ ጥቃት፡ ከባድ ጥቃት በመሰንዘር የጠላትን አከርካሪ መስበራቸውን ተናግሯል። በጥቃቱ ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ የፖሊስና ሚኒሻ አባላት በተጨማሪ በቁጥር አምስት አባላት በፋኖ የተማረኩ ሲሆን በአለም አቀፍ የምርኮኞች አያያዝ ሕገ ደንብ መሠረት እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንም ፋኖ ፈቃዱ አሰፋ ለጣቢያችን ጨምሮ ገልጿል። ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ቻናል ይወዳጁ👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8 የቴሌግራም ገፃችን ነው https://t.me/realthevoiceofamhara
Показати все...
The Voice of Amhara 8 - የአማራ ድምጽ 8

Share your videos with friends, family, and the world

👍 18 4
የአማራ ክልል መንግስት ክዶናል፡ ለዳግመኛ ወረራ ዳርጎናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ! ክልሉን እየመራሁ ነው የሚለው የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያን ሕዝብ ክዷል፡ የደም ዋጋ ከፍለን ያስመለስነውን ማንነታችንን ለማስነጠቅ ዳግመኛ ወረራ አስከፍቶብናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ሚድያ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ይሄን የተናገሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሳምንታት በፊት ጀምሮ በተፈናቃይ ስም ከነ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቆቻቸው በሰሜን ወሎ ዞን ስር በነበሩ በአራት ወረዳዎችና በሁለት ከተማ መስተዳድሮች በመግባት ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዲሁም ንብረት ዘረፋ እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ታጣቂዎቹ ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በመግባት በሰሜን ወሎ ዞን ስር በሚገኙ ራያ ባላ፣ ራያ ኦፍላ፣ ራያ ዘቦ፣ ራያ አላማጣ በተባሉ አራት ወረዳዎች እንዲሁም በአላማጣ ከተማ አስተዳደርና ኮረም ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ግድያ እየፈፀሙ ሲሆን፡ ለአብነትም ሰኔ 01/2016 ዓ/ም በአላማጣ ከተማ የተገደለው ወጣት ያሬድ መልካሙን ጨምሮ አስር የሚደርሱ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ታውቋል። ከአማራ ድምፅ ሚዲያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው ቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች "አማራ ክልልን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያ አከባቢ አማራዎችን ክዶናል" ያሉ ሲሆን ቀጠናው ለዳግመኛ ወረራ እንዲጋለጥ አድርጓል ብለዋል። ህዝቡ በከባድ መከራ ውስጥ ይገኛል የሚሉት ነዋሪዎቹ ከዚህ መከራ ሊታደገው የሚችል አካል ጠፍቷል ሲሉ ተናግረዋል። የአማራ ድምፅ ያነጋገራት አራት ታዳጊ ልጆችን እንደያዘች ስትኖርበት ከነበረው ከራያ ባላ አከባቢ ተፈናቅላ ቆቦ ከተማ ተጠልላ የምትገኝ አንዲት እናት" የሕወሓት ታጣቂዎች በባለፈው አመት ባለቤቴን ገድለውብኛል፡ መኖሪያ ቤታችን ተቃጥሏል ንብረታችን ተዘርፏል ያለች ሲሆን "ዘንድሮም የእርሻ ማሳየ እንዳይታረስ ዳግመኛ ወረራ ተፈፀመብን፡ ታጣቂዎቹ ሊገድሉን ልጆቼን እንደያዝኩ አምልጬ ወጣሁ" ስትል ቃል በቃል ተናግራለች። ሌላኛው የአማራ ድምፅ ያነጋገራቸው በራያ ኦፍላ ወረዳ ስር በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ሲያስተምሩ የነበሩ መምህር"በተለየ ሁኔታ ከአራት አመታት ወዲህ አርሶ አደሩ አርሶ መብላት አልቻለም፡ ነጋዴው ነግዶ ማደር አልቻለም ተማሪዎችም አልተማሩም፡ ይባስ ብሎ ትምህርት ቤቶችም የጦር ካምፕ ሁነዋል ያሉ ሲሆን ገዢው አካል የራያን ህዝብ ክዷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እኛ አማራ ነን አንጂ አማራ እንሁን አላልንም ያሉ ሲሆን የኛ ያልሆነውን ማንነት ተገደን ልንቀበል ወይንም ሊጫንብን አይችልም ብለዋል። አገዛዙ የራያን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ህይወታቸውን የገበሩ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን አፈረሰ አሁን ደግሞ አንድ አሉን የምንላቸውን ፋኖዎችን ለማጥፋት በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጦርነት ከፍቷል ይህ የሚያሳየው የራያን ህዝብ ማንነት ለማጥፋትና መሬቱን አሳልፎ ለመስጠት ቆርጦ መነሳቱን ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት እንድንወረር ወዶ ፈቅዶ ከሰጠ በኋላ አሁን ላይ በኛላይ የሚደርሰውን ግና መከራን ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት እያዋለው ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ከአማራ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጨምረው ገልፀዋል። በመጨረሻም ነዋሪዎቹ፡ ገዢው መንግስት ደምና አጥንት ገብረን ያስመለስነውን ማንነታችንን እና እርስታችንን በሕጋዊ መልኩ ያፀድቅልናል በሚል በሰላማዊ መንገድ በትዕግስት ስንጠብቅ ብንቆይም ነገር ግን ሊሆን ስላልቻለ ከዚህ በኋላ እንደ ህዝብ ተነስተን ከፋኖዎቻችን ጋር በመሰለፍ ወረራ ባስከፈተብን የአገዛዝ ስርዓት ላይ የኃይል አማራጮችን ለመጠቀም እንገደዳለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተጨማሪ ዝርዝር ይከታተሉ👉 https://www.youtube.com/watch?v=vJmFC-VCGc8
Показати все...
ዜና ሕዝቡ የኃይል እርምጃ ሊጀምር ነው! ከወደ ራያ የተሰማው አዲስ መረጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 27
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሰበር ዜና! የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከሰራዊታቸው ጋር ግምገማ እያደረጉ ባለበት የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተፈፀመባቸው። የከባድ መሣሪያ ድብደባውን የፈፀመው የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ሜካናይዝድ ጦር መሆኑም ታውቋል። በዚህ ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ሕይወታቸው ያለፈ መስመራዊ የጦር መኮነኖች መኖራቸው ተሰምቷል...ዝርዝሩን ይጠብቁን! እስከዚያው ዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ፣ላይክና ሼር አድርጉ! ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ቻናል ይወዳጁ👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8
Показати все...
👍 63👏 7 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንደምን አደራችሁ! ወሎ ቤተ አማራ! ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ቻናል ይወዳጁ👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8 የቴሌግራም ገፃችን ነው https://t.me/realthevoiceofamhara
Показати все...
👍 61 1🥰 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ሞት እና ስቃይ መዘገብ ሰለቸኝ፣ አሁን ደግሞ በጦርነት የተጎዱ ሰዎችን ለማገዝ እርዳታ ወደማሰባሰብ ለማተኮር እያሰብኩ ነው" ይህን ከመታሰሩ በፊት ያለኝ ብርቱው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነበር። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቤታቸው ላይ በተወረወረ ከባድ መሳርያ ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ እና ቤታቸው ለተቃጠለባቸውን የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች የዛን ሰሞን ወደ 800,000 ብር የሚጠጋ ድጋፍ በራሳቸው የባንክ አካውንት እንዲሰባሰብ አርገን ቤታቸው ታድሶ እንዲገቡ አደረግን። ሌላም፣ ሌላም በርካታ የበጎ አድራጎት ሀሳቦች ነበሩት። ነገር ግን ግድያ፣ ጥቃት እና ግፍ ከሚደርስባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከማንም ቀድሞ መረጃ እያሰባሰበ ለህዝብ የሚያቀርበው ስራው ያልተወደደለት ጎበዜ ሀገር ጥሎ ከሄደበት ጅቡቲ ታፍኖ መጥቶ ለእስር በቃ። እርግጠኛ ነኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእስር ያበቃውን የጋዜጠኝነት ስራውን በደንብ የሚረዳበት እና የሚያመሰግንበት ግዜ ይመጣል። via EliasMeseret #JournalismIsNotACrime
Показати все...
👍 56😢 20 6
https://www.youtube.com/watch?v=vJmFC-VCGc8 የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያን ሕዝብ ክዷል፡ የደም ዋጋ ከፍለን ያስመለስነውን ማንነታችንን ለማስነጠቅ ዳግመኛ ወረራ አስከፍቶብናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ፡ ገዢው መንግስት ደምና አጥንት ገብረን ያስመለስነውን ማንነታችንን እና እርስታችንን በሕጋዊ መልኩ ያፀድቅልናል በሚል በሰላማዊ መንገድ በትዕግስት ስንጠብቅ ብንቆይም ነገር ግን ሊሆን ስላልቻለ ከዚህ በኋላ እንደ ህዝብ ተነስተን ከፋኖዎቻችን ጋር በመሰለፍ የኃይል አማራጮችን ለመጠቀም እንገደዳለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዝርዝሩን ይከታተሉ!
Показати все...
ዜና ሕዝቡ የኃይል እርምጃ ሊጀምር ነው! ከወደ ራያ የተሰማው አዲስ መረጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 25