cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

⛪️ማዕደ ኦርቶዶክስ

በዚህ ቻናል ፈቃደ እግዚአብሔር ከሆነ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ግጥሞች ዜማዎች ቅኔዎች እንዲሁም የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ይለቀቅበታል።

Більше
Рекламні дописи
398
Підписники
+224 години
+37 днів
+630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ሳትስቅ ያረጀችው ሣራ፥ የሳቀችበት ዕለት ነው ዛሬ፡፡ የማያደርገውን የማይናገር፥የተናገረውን የማያስቀር ሥላሴ"ሚስትህ ሣራ ልጅን ታገኛለች" ብለው ሲናገሩ ሰምታ በመገረም ሳቀች፡፡ የሴቶች ልማድ ከተወኝ በኋላ መውለድ እንምን ይቻለኛል ብላ፡፡ ለእሷ የማይቻለውን የሚችል አምላክ ግን ልጅ ሠጣትና ስሙን ይስሐቅ አለቺው፡፡ በቀሪ ዕድሜዋ ደስታና ሳቅ ወደ ቤቷ ገባ፡፡ ዕንባና ኀዘን ሰው ሰራሽ ሞት ያጠላበት ሕይወት ኹሉ፥ ቀሪ ዘመኑ ደስታና ሳቅ ይኾን ዘንድ፥ አብርሃም ወሣራ ሰአሉ በእንቲአነ፡፡ ቅድስት ሥላሴ እንደ እናት፦ ቅድስት የሚለው ስም ለሴት የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ እናት ልጅን እንደምታስገኝ ሥላሴም ይኽን ዐለም ካለመኖር ወደመኖር አምጥተው አስገኝተዋል፡፡ እናት ለልጇ አስገኚ ብቻ አይደለቺም፡፡ ምግብም ናት፡፡ ልጆች ወተት ብለው የሚጠጡት ምግብ የእናቶች ነጭ ደም ነው፡፡ ሥላሴም ለሰው ፈጣሪው ብቻ አይደሉም፡፡ ምግቡም ናቸው እንጂ፡፡ ከሦስቱ አካል አንዱ ወልድ ክርስቶስ፥ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሕይወት ምግብና መጠጥ ኾኖናል፡፡ይኽ ሥጋና ደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አንድነት ያለው መኾኑን ልብ ይሏል፡፡ የጌታችን ክርስቶስ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ነውና፡፡ " ኀበ ርኅራኄክሙ በዝኃ ወኀበ አልቦቱ መሥፈርት፤ እለ ትሰመዩ በስመ ብእሲት፤ ሥላሴ ዕደወ ምሕረት፤ ግናይ ለክሙ። ቸርነታችሁ ከበዛና መሥፈሪያና መጠን የሌለው ከመኾኑ የተነሣ በሴት የምትጠሩ የይቅርታ ባለቤት ሥላሴ ሆይ ለእናንተ ምስጋና ይገባል።"
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሙሉ የመዝሙረ ዳዊት ንባብ ለየብቻ መስማት ከፈለጉ መዝሙረ ዳዊት ዘሰኑይ ንባብ (፩-፴) ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/538?single መዝሙረ ዳዊት ዘሠሉስ ንባብ  (፴፩-፷) ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/575?single መዝሙር ዘዳዊት ዘይትነበብ በእለተ ረቡዕ (፷፩--፹) ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/606?single መዝሙር ዘዳዊት ዘይትነበብ በእለተ ኃሙስ (፹፩-፻፲) ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/628?single መዝሙር ዘዳዊት ዘይትነበብ በእለተ ዓርብ (፻፲፩-፻፴) ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/660?single መዝሙር ዘዳዊት ዘይትነበብ በእለተ ቀዳሚት ሰንበት ( ፻፴፩-፻፵፯ )እና መኃልየ መኃልይ ዝ ውእቱ ዘሰሎሞን  ከ፻፵፰-፻፶ ያሉት መዝሙራት በስብሐተ ነግህ የሚደረሱ ናቸው። ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/703?single መዝሙረ ዳዊት ዘይትነበብ በእለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት -መኃልየ ነቢያት ወጸሎቱ ለሙሴ ለየብቻ በጥሩ መምህር በአነስተኛ mb 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/749?single መዝሙረ ዳዊት በውርድ ንባብ 👇👇👇 https://t.me/abnetbete/899?single ብሉይ ኪዳን አንድምታ 👇👇👇👇 https://t.me/abnetbete/805 አዲስ ኪዳን አንድምታ 👇👇👇 https://t.me/abnetbete/862?single መልክዐ ሕማማት ዜማ እና መጽሐፍ 👇👇👇 https://t.me/abnetbete/904 አገልግሎቱን ለሰው እንዲደርስ እርዱን🙏🙏🙏
Показати все...
⛪️ማዕደ ኦርቶዶክስ

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሐምሌ 7 ቅድስት ሥላሴ (በአብርሃም ቤት የተገኙበት) በአዲስ አበባበ አህጉረ ስብከት በእነዚህ አብያተክርስትያናት በአለ ንግሱ ይከበራል። ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው። ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ። በቴሌግራም https://t.me/NIGSE6 በፌስቡክ https://www.facebook.com/በኢኦተቤክ-የአዲስ-አበባ-አብያተ-ክርስትያናት-109013113871986/ ይቀላቀሉን:: በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ። 🙏 ቅድስት ሥላሴ ይጠብቁን 🙏 1) ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ዊንጌት ጠሮ አራት መንታ 2) ደብረ ቀራንዮ መድሃኔአለም እናገብርኤል ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቀራንዮ 3) ደብረ መድሃኒት አቡነ ሃብተማርያም ወቅድስት ልደት ወቅድስት አርሴማ ገዳም ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ አስኮ ካኦጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ቃሌ ተራራ ላይ 4) የረር ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ የኤረር በር 5) መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ 6) ቦሌ ኆህተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ 7) ጽርሃ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ልዩ ስም፦ቦሌ ሰፈራ 8)መሪ ቅድስት ሥላሴ፤ቅዱስ ኡራኤል፤ቅድስት ድንግል ማርያም፤ቅዱስ ጊዮርጊስ ወአቡነ አረጋዊ ቤ/ክ ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ መሪ 9) ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልዩ ስም፡-ጉለሌ /ክ/ከ አዲሱ ገበያ 10) መንበር ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ልዩ ስም፦ጉለሌ ሽሮ ሜዳ 11) መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩስም፦አራዳ ክ/ከ አራት ኪሎ 12) አየር ጤና አንቀፀ ብርሃን ቅድስት ኪዳነምህረት ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አየር ጤና 13) አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ደብረ ፍስሃ ቅዱስ ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ሳሪስ አዲስ ሰፈር 14) ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ላፍቶ 15) ለቡ ደብረ ታቦር በዓለወልድና አበ ብዙሃን አብርሃም ገዳም ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ /ክ/ከ ለቡ 16) ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት 17) ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ሳሪስ 58 18) ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ አቃቂ ኬላ ዝቅ ብሎ 19) ቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 ሰሪቲ 20) ወለቴ ለሚ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ልዩ ስም፦ክ/ከ ሰበታ ወለቴ 21) ቃሊቲ አረጋውያን ክብካቤ መካነ ስብሀት ቅድስት ስላሴ እና አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን ክ/ከ አቃቂ ቃሊቲ ወ/08 ልዩ ስሙ ጨፌ (አረጋውያን ክብካቤ) ጀርባ 22) ጎተራ ፈለገዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴ እና ቅድስት አርሴማ 44ቱ ፀበል ልዩ ስም:-ጎተራ 44ቱ ፀበል ከሳሪስ ወደ አጎና በሚወስደው መንገድ
Показати все...
ንግሥ

ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው። ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ። በቻናሉ ላይ አስተያየት ካሎት

https://t.me/DAN_TRADING_PLC

ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።

Фото недоступнеДивитись в Telegram
+++ "እኔ መንገድና እውነትም ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም::" ዮሐ.14፥6 ✍️ በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 'እኔ አማላጅ ነኝ' የሚል ቃል አልተናገረም:: ወንጌላዊውም ቅዱስ ዮሐንስም ቢሆን አልጻፈልንም:: ➔ ምንም እንኩዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 'እኔ አማላጅ ነኝ' ብሎ ባይናገርም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ባይጽፍልንም ጌታችን "በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" ማለቱ በእኔ አማላጅነት ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ለማለት ፈልጎ ነው ተብሎ ተገምቶ ከሆነ ግምታዊ ትርጉም ሃይማኖት አይሆንም:: ✍️ "አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም" |ዮሐ.6፥44| ተብሎ ስለተጻፈ 'በአብ አማላጅነት በቀር ወደ ወልድ የሚመጣ የለም' የሚል ትርጉም እንደማይሰጠን ሁሉ "በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" የሚለው ጥቅስም 'በወልድ አማላጅነት ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም' የሚል ትርጉም አይሰጠንም:: ➜ በተመሳሳይ መልኩ "መንፈስ ቅዱስ ካደረበት በቀር ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ ገዢ(ጌታ) ነው ብሎ ማመን የሚችል የለም" 1ኛ.ቆሮ.12፥3 ተብሎ ስለተጻፈ 'መንፈስ ቅዱስም አማላጅ ነው' አንልም:: በአንጻሩ ግን በእነዚህ ጥቅሶች የሥላሴን የአካል ሦስትነት፤ የፈቃድ አንድነት እንረዳለን:: ✍️ በተጨማሪም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለውን አለመበላለጥ ለሕሊና ሚዛንነት በሚመች ንጽጽር ለመገንዘብ እንዲረዳን የሚከተሉት ጥቅሶችን እንመልከት:: ➺ "እግዚአብሔር ለሕዝቡ "ኃይልን" ይሰጣቸዋል" |መዝ.28፥11| "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ::"|ፊል.4፥13| "መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ግን "ኃይልን" ትቀበላላችሁ::" |ሐዋ.1፥8| ➲"አብ ሙታንን እንደሚያስነሳ "ሕይወትንም" እንደሚሰጣቸው" |ዮሐ.5፥21| "እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው "ሕይወትን" ይሰጣል" | ዮሐ.5፥21| "የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ "ሕይወትን" ይሰጠዋል::" |ሮሜ 8፥11| ➾ እንግዲህ በትክክል ለሚያስብ ሰው እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች የሚያስረዱት የወልድ አምላክነት እንጂ አማላጅነት አይደለም:: ሰዎቹ በምን አስበው ወልድን አማላጅ ነው ለማለት እንደደፈሩ የሚያሳዝንና የሚያስገርም ነው::
Показати все...
አባ ጲዮር የሚመገበው እየሄደ ነው። ለምንድነው እየሄድክ የምትመገበው? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቀው "መመገብን እንደሥራ ሳይሆን እንደተጨማሪ ነገር ማሰብ ስለምፈልግ ነው" አለ በሌላ ጊዜ ደግሞ "ነፍሴ በምግብ ሥጋዊ ደስታ እንዳይሰማት ብዬ ነው" ብሎ መለሰ። 🔆🕯🌟🔆🕯🌟🕯🌟🔆🕯🌟🔆
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.