cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799

Більше
Рекламні дописи
460
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

አሁንም ቢሆን አግለገባኝም ክፍል ሁለት ....ለዚህም ማሳያችን የ18ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በአካል ጉዳተኞች ላይ የተፃፉትን ቃኘት ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም አንድ ነገር ላይ ለመድረስ ነው፤ ዛሬ ዘመኑ ተቀይሯል፣ ትናንትና ያልሆኑ ዛሬ መሆን ችለዋል፣ ትናንትና የምንንቃቸውን ዛሬ አንንቃቸውም፣ ትናንትና የማናከብራቸውን ዛሬ እናከብራቸዋለን፣ ትናንትና ያላከበርናቸው አሊያም የናቅናቸው የማወቃችን ደረጃ ትክክል መስሎ ስለተሰማን ነበር፣ የሰው ልጅ እንደዚህ ነው፣ ነገሮችን እስኪያውቅ ድረስ ባወቀው ልክ ነገሮችን ይረዳል፣ አለማወቁ ሲቀረፍ ወደማወቅ ደረጃ ሲደርስ ስላለማወቁ አዝኖ ዛሬን ከትናንቱ በመረዳት ውስጥ ይኖራል፣ እኔም ብዙ የማላውቅበት ጊዜ አልፏል፣ ምን አሁን አወኩኝ ብል እንኳን የማውቀውን ልክ እንጂ ሌሎች እንደሚያውቁት ልክ ላይሆን ይችላል፣ ዛሬ ያወኩትን ደግሞ በነገ መነጸር ሳየው ኢምንት ሊሆን ይችላል፣ ግን ሁላችንም የሚያሳምን አንድ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ጥቂቱን ነገር ያውቃል እንጂ ሁሉንም ሊያውቅ ቢፈቀድለትም እድሜ ይገድበዋልና ሊያውቅ አይችልም፣ እኔም ከዚህ በፊት የማላውቀውን፣ ዛሬ ግን ያወኩትን በአጋጣሚ አወኩት፣ እናም አሁንም ቢሆን ግን አወኩት ልበል እንጂ እንዳወኩት መረዳት እንኳን ከብዶኛል፣ ያ ያወኩት ነገር ምን ሊሆን እንደሚችል ሳትገምቱ አልቀራችሁም፣ ወይም ምን እያለች ነው፣ ምንስ አውቃ ነው ብላችሁ እየገመታችሁ ሊሆን ይችላል፣ ምንም ችግር የለውም መገመታችሁ መልካም ነው፣ ግን ማናት እንደዚህ የምትባዝነው ልትሉ ስለምትችሉ እኔ ቅደስት ማህሪ እባላለው፣ ባለ ትዳር ነኝ፣ እናም የሁለት ልጆች እናት፣ በስራዬ መምህርት ነኝ፣ እዲሁም ኑሮዩን ለማሸነፍ በማታው ክፍለ ጊዜ ልጆችን አስጠናለው፣ ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ነው፣ ጠንካሮችን ያበረታታል፣ ድኩማንን እንዳይነሱ አድርጎ ከምድር እያላተመ ያኖራቸዋል፣ እኔም የኑሮን ዳገት እየወጣው እገኛለው፣ መቼም የሰው ልጅ በምድር ሲኖር ለመፈተን፣ ተፈትኖም ለማለፍ የተፈጠረ ነው፣ ድንገት በዚህ አሳብ የማይስማማ ካለ እኔ በዚህ ሃሳብ አብዝቼ አምናለው፣ ለዚህም ነው የትምህርት ስርዓታችን በፈተና ሰዎችን እየለየ ለመላሹ ሞራል ይሰጣል፣ የወደፊት እንጀራቸውን በተስፋ እንዲዝቁ ያደርጋል፣ ላላለፉት ደግሞ የጣርን ኑሮ ትቋደሳላችሁ እያለ ቀድሞ በተስፋቸው ላይ የውድቀት ድግስን ያበስራ፣ በፈተና ለሚያልፉ ምድር ምቹ ናት፣ ተስፋ ቆርጦ ለሚልፈሰፈስ ድግሞ ምድር የሲሆል ነጸብራቅ ናት፣ እኔም በቀለም ትምህርት ቀድሜ እነሳ እወድቅ የነበረውን፣ ዛሬ ደግሞ በሕይወት ፈተናዋ ከፍ ዝቅ ታደርገኛለች፣ ይህ ደግሞ የሕይወት አንዱ መስመር ነውና መቀበል ግዴታ ነው፡፡ ስጋ የለበሰ፣ ነፍሱ ከስጋው እስክትለይ ድረስ መፈተን ግዴታው ነው፣ ነገር ግን የመፈተኛ ትራኩ ለየቅል ሊሆን ይችላል እንጂ ፈተና ማንም ሕይወት ላይ አለ፣ እኔም ብቻን መሮጥ ድክም ሲለኛ፣ አግብቼ የኑሮ ዳገቴን ልቀንስ፣ ብዬ የሚመስለኝን፣ ሊረዳኝ የሚችለውን፣ ልረዳው የምችለውን፣ ስደክም ደገፍ የሚያደርገኝን፣ እርሱን የምደግፈውን አግኝቼ ሕይወቴን እየመራው የደስታ ጊዜን አስቆጠርኩኝ፣ መቼም በሰርጋችን ዕለት የዛሬ አመት የሚሚ እናት የዛሬ ዓመት የማሙሽ እናት ተብሎ ተዘፍኖልኝ እኔም ልጅ በመውለድ የሴት ወጉ ደርሶኝ ሰላማዊ ኑሮን እየኖርኩኝ ባለበት ሰዓት...ይቀጥላል ምንጭ:- አዲስ ዓለም ገጽ 38 ጸሐፊ:- በላይ ጌትነት ገጹ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ ያጋሩት https://t.me/autismfact
Показати все...
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799

አሁንም ቢሆን አልገባኝም የምድር ሕግ በምንም መንገድ ትክክል ሆኖ አያውቅም፣ አንዱ በአንዱ ላይ ለመሰልጠን ስለሚሻ መቼም ቢሆን ሁለት ነገሮች እኩል ገነው አያውቁም፣ ሰላም እንዲከስም ሁልጊዜ ጠብ ጠንክሮ ይሰራል፣ እውነት ከምድሪቷ እንዲጠፋ ውሸት በሰዎች ላይ አድሮ የእውነትን ዓለም እንዲሚቆጣጠር ምንም ጥያቄ የለውም፣ ድሎት ከችግር ጋር በአንድ ማዕድ ተቀምጠው አያውቁም፣ ምቀኝነት ከልግስና ጋር ሕብረት የላቸውም፣ ሁሉም የእራሳቸው መንገድን ለማቅናት ስለሚተጉ እርስ በእርሳቸው ሰላምን ፈጥረው አያውቁም። እነዚህ ደግሞ ማንነታቸውን የሚገልጹት በእኛ ላይ አድረው መሆናቸው እጅጉን ያስገርማል፣ የሰው ልጅ የተጫነለትን የሚያውጣ ነው ብለን ባንደመድምም የተጫነለትን ግን በአመዛኙ ያወጣል፣ ፈጣሪ ከመጀመሪያ ከምድር አፈር አበጅቶ የሕይወት እስትንፋሱን እፍ ሲልብን አስተዋይነት፣ ባለ አእምሮ፣ ነገሮችን ማገናዘብ የሚችል፣ ሚዛናዊ አመክኖያዊ አእምሮ ቢያድለንም ቅሉ ያደግንበት ማህበረሰብ፣ የተወለድንበት ቤተሰብ፣ በቅርባችን ያሉ ቤተዘመዶቻችን ፣ጓደኛ ትምህርት ቤት፣ ሃይማኖት፣ ባህሉ ተደማምሮ ወደ ውስጣችን ገብቶ እኛን ይሰራናል፣ ከዚህ ሕግ ውጭ የሆነው ሰው ብሎ መጣራት እንኳን የሚያስደፍር አይደለም፣ ምክንያቱም በቀደሙት ዘመን በ18ኛ መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ እንዲሁም በ19ኛ መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ያሉ ስንክሳሮችን ብንቃኝ በአካል ጎደሉ! ተብለው ከሰውነት ክብር ሲቀነሱ የነበሩ የሰው ዘሮች ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ካልተገደሉ እጣ ክፍላቸው እንደ አውሬ በጫካ መጣል ነበር፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ ምንም እንኳን አእምሮው ሁሉን እንዲችል ተደርጎ ቢበጅም በጊዜውና በሰዓቱ ሊጠቀምበት ካልቻለ አእምሮው መስራት የሚያቆም፣ ከጊዜ በኋላ ነገሮችን መረዳት የማይችልበት የጊዜ ገደብ ያለው ነው፡፡ ለዚህም በእድገት ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙዎች አሊያም ተመራማሪዎች ሰው በመጀመሪያው የውልደት ጊዜ እድገቱ እንሚፈጥን ሁሉ በምድር ያሉ ነገሮች ለመረዳት በዛው ልክ የተዘጋጀ ንፁህ አእምሮ አለው በዚህም በአእምሮ፣ እጅጉን ፐርሰንት በዚህ በልጅነት ጊዜው እንደሚሸፍን እንዲያውም ከውልደት እስከ ስምንት ዓመት የእድገቱን ሰማንያ ፐርሰንት እንደሚሸፍን በእድገት ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች ይገልፃሉ ነገር ግን በዚህ ጊዜ የሚያስፈልገውን፣ የሚያሻውን ልናደርግለት ካልቻልን የማገናዘብ አቅሙ፣ እንዲሁም ነገሮችን የመረዳት ጥበቡ ከእንሰሳት በልጦ እንደማይበልጥ ትንታኔ ይሰጣሉ... ይቀጥላል ምንጭ :- አዲስ ዓለም ገጽ 37 ጸሐፊ:- በላይ ጌትነት ገጹ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ ለወዳጅ ያጋሩት https://t.me/autismfact
Показати все...
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799

Фото недоступнеДивитись в Telegram
Follows on ticktock
Показати все...
3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"Happy Mother's Day to all the incredible moms of autistic children. Your journey is filled with unique challenges, and your strength and resilience in facing them inspire us all. Today, we celebrate you and the love, care, and dedication you pour into your children every day. You are true heroes, and this day is a tribute to your unwavering commitment. Happy Mother's Day!" Dr Simegn.T
Показати все...
4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬ ቅዳሜ ምሽት 2:30 ጀምሮ የመወያያ ርዕስ:- "ስለ ኦቲዝም ማወቅ ቀድሞ ለመጠንቀቅ" ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት በቲክቶክ ለማንኛውም ሃሳብና አስተያየት ገጹ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ ለወዳጅ ያጋሩ
Показати все...
👍 2
ከአሜሪካን ኒዎርክ (ዳግማዊት ካሳሁን ) የሳምንቱ ተጋባዥ እንግዳ "ሁለቱም ልጆቼ በኦቲዝም ጥላ ውስጥ ናቸው የእግዚአብሔር በረከቶቼ" ትለናለች ዳጊ ሰላም ለዚህ ገጽ ታዳሚዎች እንደምን ሰነበታችሁ አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ፣ ትምህርትም ሆነው የሃስተሳሰብ አድማስን በማስፋት የተግባር ሕይወታችን ላይ ቅመም ይጨምራሉ ብለን በማሰብ የተለያዩ ልምድ እና ተሞክሮ ያላቸውን ሰዎች እየጋበዝን እንደሆነ ይታወቀል ። በዚህ ሳምንትም ወ/ሮ ዳግማዊት ካሳሁን ከአሜሪካን ኒዎርክ እስቴት ስንጋብዝላችሁ ታላቅ ክብር ይሰማናል። ወ/ሮ ዳግማዊት የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱም ልጆቿ በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ናቸው። ዳግማዊት ግን እነዚህ ልጆቼ ማመስገኛዩ ናቸው፣ አዲስ ነገርም ያየውባቸው በረከቶቼ ናቸው ትለናለች። ታዲያ ዳግማዊት በሕይወቴ ብዙ ውጣ ወረድ ተሻግሪያለው፣ በጭንቅ እና በጣር ጊዜዬ ፈጣሪ ብርታት እየሰጠ እዚህ አድርሶኛል አሁን ብዙ የሚነገሩ ልምዶች አለኝ፣ ለወላጆች ብቻ ሳይሆን ወደ ትዳር ለምትገቡ እህት ወንድሞቼ ሳይቀር ትምህርት የሚሆን ልምዴን ተካፈሉልኝ ትለናለች። ታዲያ አዲስ ዓለምም የዳግማዊትን መልካም ፍቃድ እያመሰገነች የምትታደሙ ወላጆች በሉ ባለሙያዎች ብዙ ቁምነገር እንደምታተርፉ ጥርጥር የለውም። የአንዱ ሕይወት ለአንዱ ትርጉም አልባ ትምህርት ነው። ሁሉም የእራሱን ታሪክ ቢያወራ ተነቦ የማይጠገብ መጽሐፍ ነው። ታዲያ ለዚህ ሳምንት የዳግማዊት የሕይወት ተሞክሮን መውጣት መውረዷን ስታስቃኝ አይ የሰው ልጅ ፈተናው እያልን የማይበገር ልቧን እያደነቅን የእኛን ድካም እያየን ብርታት ትሆነን ዘንድ ኑ እንማከር፣ የአንዱ ሕይወት ለአንዱ የጥንካሬ ምንጭ ነው። ያለ ጥርጥር ይህን ፕሮግራም የምታዳምጥ እናት ከድካሟ ብርትት ብላ ተነስታ ልጇ ላይ ለመስራት ሃይል የሚሆናት ነው። በእርግጠኝነት ይህን ፕሮግራም የሚያደምጡ እጮኞች ስለ ኦቲዝም ግንዛቤ ማካበታቸው ጊዜ እና ሰዓቱን የዋጀ መልካም ውሳኔ ለመውሰድ ይረዳቸዋል በእርግጠኝነት ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ያለች እናት አባት፣ ነገሩ ጨልሞብኛል ልጄ ተስፋ የለውም የምትል ወላጃ አይ ስንፍናዬ ነው እንጂ ለልጄስ መንገድ አለ ብላ/ብሎ ሥራ ለመስራት ስንቅ የምትይዝበት/የሚይዝበት ጭምር ነው በእርግጠኝነት የልዩ-ፍላጎት ባለሙያዎችና በዘርፉ የሚሰሩ አካላት አዲስ ሃሳብ በመቃረም የአሰራር ስነ ዘዴያቸውን የሚያድሱበት እና በብርታት ለመስራት አቅም የሚያካብቱበት ነው። ተወዳጆች ማወቅ ከመስማት ነው፣ እውቀትም ከልምድ ነው፣ ማድረግም ከማወቅ ነው፣ ሁሉን ታገኙ ዘንድ ቅዳሜን ከኛ ጋር ብቻ መሆን ነው። በተለይ እንደ ዳግማዊት ሁለት ልጆች በኦቲዝም ውስጥ ያላቸውን እናቶች ከእናት በላይ መሆናቸውን ኑና አድምጡ፣ ጠይቁ፣ አድንቁም ፕሮግራም  የሚተላለፍበትቲክ ቶክ(ticktock) ገጽ http://tiktok.com/@belayzgetnet ቅዳሜ ምሽት 2:30 ✍በላይ ጌትነት አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት አብራችሁ ለመስራት ብሎም ልዩ-ልዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከስር ያለውን ስልክ መጠቀም ትችላላችሁ። 📞0941537799 📞0978115992 በማጋራትዎት ለስንቶች መንገድ እንደሚሆኑ ያውቃሉ?👏 https://t.me/autismfact
Показати все...
አዲስ_ዓለም on TikTok

@belayzgetnet 5255 Followers, 710 Following, 71.8k Likes - Watch awesome short videos created by አዲስ_ዓለም

ተወዳጆች ከቲክቶክ በተጨማሪ በቴሌ ግራምም ቢቀርብ ለብዙዎች ይደርሳል ላላችሁን በቅርቡ ቋሚ ፕሮግራም እንጀምራለን። ይጠብቁን አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ከብዙዎች ለብዙዎች ገጹን ማጋራት አይዘንጉ https://t.me/autismfact
Показати все...
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799

👍 1
ይህ ገጽ ግን ስንቶቻችሁን እየጠቀመ ነው? ሃሳብ አስተያየታችሁን ያለ ስስት ስጡን ቅያሜም ካላችሁ እንደዛው የምትሰጡት ሃሳብ ክፍተቶቻችንን አይተን እርምት እንድንወስድ ይረዳናል። ሃሳብ ለምትሰጡ ሁላችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው https://t.me/autismfact
Показати все...
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799