cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

FreshFacts

እዉነተኛ እና ታማኝ መረጃ ለ ኢትዩጵያውያን

Більше
Рекламні дописи
189
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Repost from THIQAH
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ሩዋንዳ የተማሪዎች መማሪያ እና የመኖሪያ ቤትን በአንድ የያዘው ትምህርት ቤት ተዘጋ። በሩዋንዳ መድና ኪጋሊ ህገ ወጥ የመማር ማስተማር ሂደትን ተከትሏል የተባለው ትምህርት ቤት መዘጋጀቱን የአካባቢው ባለሥልጣን አስታውቀዋል። ትምህርት ቤቱ የአፀደ ህፃናትና ሌሎች ስድስት ክፍሎችን የያዙ ሁለት ብሎኮች አሉት ተብሏል። የአካባቢው ባለስልጣናት አራት መምህራን ጨምሮ የትምህርት ቤት ዳይሬክተሩን በቁጥጥር ስር አውለዋል ተብሏል። "ከአሰራሩ በሚፃረር መልኩ ሁለተኛ ፎቅ ላይ የመማሪያ ክፍሎች አሉ ከታች ደግሞ የመኖሪያ ቤት አለ" ሲሉ ወንጀሉን እየመረመሩ የሚገኙት ኢንስፔክተር ዶሬን ናኪቶ አብራርተዋል። በተመሳሳይ መልኩ ባለቤቱ የሚኖርበት የቤተሰብ ቤት መገኘቱንም ባለስልጣናቱ መግለፃቸውን BBC ዘግቧል። @ThiqaMediaEth
Показати все...
በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ 3 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ኬንያ የገቡ 3 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ሜሩ አውራጃ ውስጥ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን የኬንያው ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል። አደጋው የሰው አዘዋዋሪዎቹ 10 ኢትዮጵያውያንን በፕሮቦክስ መኪና ጭነው ሲጓዙ ተሽከርካሪያቸው ከሌላ መኪና ጋር በመጋጨቱ  የተከሰተ ሲሆን 8 ስደተኞች ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውና ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባለፈው ማክሰኞ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ወደ ናይሮቢ በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በታጠቁ ግለሰቦሶች ታጅበው በሞተር ሳይክል ሲጓዙ የነበሩ ስምንት ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ እንደተያዙ ተገልጿል። በዚሁ እለት ሌሎች 7 ኢትዮጵያዊያን በታጠቁ አጃቢዎቻቸውና በፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ ከተደረገ በኋላ እንዳመለጡ ሲገለፅ በመርሳቢት ግዛትም፣ በተመሳሳይ በታጣቁ ግለሰቦች ታጅበው ሲጓዙ የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው። Via. TikvahethMagazine
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በፍቼ ከተማ ሳይታገት ታግቻለሁኝ በማለት ቤተሰቦችን ለማጭበርበር የሞከረው  ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ቡርቃ ጎሮ በተባለ አካባቢ ሳይታገት ታግቻለሁኝ በማለት 150 ሺህ ብር ለማጭበርበር የሞከረው ግለሰብ  በቁጥጥር  ስር ዉሏል ተከሳሽ አርጋው  ይመር በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሪጅስትራል ክፍል ሰራተኛ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል ። ጥር 26 ቀን 2016 ዓ ም ንጋት11 ሰዓት ከመኖሪያ ቤቱ ቤተ ክርስቲያን እሳለማለሁኝ  በማለት ወጥቶ ሳይመለስ  ይቀራል። ከዛም በማይታወቅ ስልክ ለባለቤቱ እና ቤተሰቦቹ በመደወል በታጣቂ ሃይሎች ታግቻለሁኝ  150 ሺህ ብር አዘጋጁ በማለት ቤተሰቦቹ እንዲረበሹ እና እንዲጨነቁ  ሲያደርግ መቆየቱን የፍቼ ከተማ ፖሊስ ዋና አዛዥ  ምክትል ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለብስራት ሬዲዬ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በተደጋጋሚ  እየደወለ ሲያስጨንቃቸው ቆይቶ ከሶስት ቀናት በኋላ  ጓደኞቼ ከፈሉልኝ እና አስለቀቁኝ በማለት ወደ መኖሪያ ቤቱ ምንም ሳይሆን መመለሱ ለቤተሰቦቹ ጥርጣሬ ጭሮባቸዋል።ድርጊቱ  ግራ ያጋባቸው  ቤተሰቦች  ጉዳዩን  ወደ ፖሊስ ይወስዱታል:: በዚህም የፍቼ ከተማ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ   አርጋው ይመር የተባለ  ግለሰብ ፍቼ ከተማ ላይ ሆቴል ተከራይቶ ለሶስት ቀናት እንደቆየ   መረጃው ይደርሳቸዋል።  ፖሊስም  ተከሳሹ  ቤተክርስቲያን  ብሎ ሆቴል ተከራይቶ  እንደቆየ እና በሀሰት ብር ከቤተሰቦቹ ለመቀበል ሲሞክር  መቆየቱ   ያረጋግጣል። በዚህም ፖሊስ ተከሳሹን  በቁጥጥር  ስር አውሎ ምርመራውን ሲያጣራ ድርጊቱን የፈጸመው  ወንድሙ ታግቶ ተወስዶ የነበረ መሆኑን እና ከቤተሰቦቹ ደብቆ ወንድሙን ለማስለቀቅ የከፈለው ብር ባለቤቱ እንደተከፈለ  ስለማታውቅ ብሩን ለመመለስ እንደፈጸመው ቃሉን ሰጥቷል። ስለሆነም ፖሊስ ይህ አይነቱ ድርጊት ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተከስቶ የነበረ መሆኑን እና ድርጊቱን  ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራበት በመጥቀስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን የፍቼ ከተማ ፖሊስ  ዋና አዛዥ  ምክትል ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዬ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በኤደን ሽመልስ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የቀድሞ ፍቅረኛውን ገድሎ የተከሰሰው ግለሰብ ከፓሊስ እጅ አመለጠ። በአሜሪካ ማሳሹትስ ከተማ የቀድሞ ፍቅረኛውን ገድሎ የተከሰሰው ግለሰብ በኬንያ በፓሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም አምልጦ ወጥቷል ተብሏል። ተከሳሹ የባለቤቱን አስክሬን በቦስተን አየር ማረፊያ ከመኪና ውስጥ ጥሎ መዉጣቱ ተገልጿል። ኬቪን አዳም የተባለው ወንጀለኛ ከእስር ቤቱ ዘሎ በመውጣት እንደጠፋ የኬንያ ፓሊስ አዛዥ አዳምሰን ቡንጋይ አስታውቀዋል። አዛዡ ወንጀለኛውን ለመያዝ የፍለጋ ስራ መጀመሩን ለAssociated press የተናገሩ ሲሆን፣ በግዳጅ ላይ የነበሩ የፓሊስ ኦፊሰሮች በቁጥጥር ስር ውለው ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ብለዋል።
Показати все...
ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ራሳ ጀነቴ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው የተለያዩ የኮስሞቲክስ እና የመዋቢያ ዕቃዎች ሲሸጡ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የግራዋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ የግራዋ  ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዋጋሪ ጀቤሳ እንደገለፁት 1ኛ ተከሳሽ አሚና ረባ መሀመድ 2ተኛ ተከሳሽ ያያ አብድል ጀባር መሀመድ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች መስከረም 30 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በራሳ ጀነቴ ቀበሌ ልዩ ቦታው ኬላ ቢቢኦ የተባለ ስፍራ ከሚመለከተው አካል የንግድ ፍቃድ ሳያወጡ የመዋቢያ ዕቃዎችን ሲነግዱ በመገኘታቸውን መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡ ተከሳሾቹ የንግድ ፍቃድ እና ምዝገባ ሳይኖራቸው ከሚመለከተው  አካል ፍቃድ ሳያገኙ ግምታዊ ዋጋቸው ከ69 ሺ ብር በላይ የሆኑ  የፀጉር መታጠቢያ ሻምፖ ፤የፀጉር ማፍታቻ ኮንድሽነር እና የተለያዩ ቅባቶችን ሲሸጡ እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡ ያለ ንግድ ፍቃድ ሲሸጡ የነበሩ የመዋቢያ ዕቃዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ፖሊስ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለግራዋ ወረዳ አቃቢ ህግ ልኳል፡፡ ዓቃቢ ህግም የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ፍቃድ መስጠት ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 980/2008 በመጥቀስ ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱን ሲመለከት የነበረው የግራዋ ወረዳ ፍርድ ቤትም እያንዳንዳቸውን በ4 ዓመት እስራት እና በ75 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን  ዋና ኢንስቴክተር ዋጋሪ ጀቤሳ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በምህረት ታደሰ
Показати все...
#Hawassa " ተማሪው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሟል " በሚል #የተጠረጠረው ርእሰ መምህር በቁጥጥር ስር እንዳሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። በሀዋሳ ከተማ ታቦር  አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወስጥ አንዲት ተማሪ ርእሰ መምህሯን " ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሞብኛል " በሚል ክስ መመስረቷን ተከትሎ  ፖሊስ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ከስራ ገበታዉ ድረስ በመሄድ በቀን 20/05/2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል። የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ ጉዳዩን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጽያ የሀዋሳው አባል ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ፤ " የተጠቂዋ ቤተሰቦች ጉዳዩን ይዘዉ ቅድሚያ ለማመልከት የመጡት ወደእኛ ቢሮ ነበር " ያሉ ሲሆን ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስዱት በማድረግ ማንኛዉንም የህግ ከለላና አስፈላጊ ድጋፎችን ሊሰጡ እንደሚችሉ ቃል ገብተው አንዳበረታቷቸው ገልጸዋል። ከዚህ በኋላ ክሱ ተመስርቶ ተጠርጣሪዉ በህግ ጥላ እንደዋለና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ " አሁን ላይ የሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ መረጃዎችን አጠናክሮ የክስ ሂደቱን ከኛ ጋር ለመደገፍ እንቅስቃሴ ላይ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዉ በትምህርት ቤት ውስጥ ሲያዝ የነበረዉን ሁኔታ እና ድርጊቱን በተመለከተ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚያውቀዉ ነገር እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር  አቶ ሀንዳሞ ፈይሳ ፤ በወቅቱ ተጠርጣሪው ለጥያቄ  ትፈለጋለህ ተብለዉ መሄዳቸውን ፤ አሁን ላይ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ሳምንት እንዳለፋቸው ገልጸዋል። ክስ አቅራቢዋ ተማሪ ከትምህርት ገበታዋ ደጋግማ በመቅረቷ ምክንያት " ወላጅ አምጭ አታምጭ " በሚል ከሚመለከታቸዉ መምህራኖቿ እና ከተጠርጣሪው ርእሰ መምህር ጋር ስትጨቃጨቅ እንደነበር የሚያስታዉሱት አቶ ሀንዳሞ ፤ ይህ ጉዳይ ለእርሳቸውም ሆነ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ #አስደንጋጭ እና ግራ ያጋባ መሆኑን አስረድተዋል። ፖሊስ አስፈላጊዉን ማጣራት አድርጎ እዉነቱ ላይ እስኪደርስ እየጠበቁ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሐዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።
Показати все...
በፈረንጆቹ 2024 ዝቅተኛ የኑሮ ውድነት ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት እነማን ናቸው? Business Daily አደረኩት ባለው ጥናት መቶ በመቶ የሚሆኑት ተሳታፊዎች "አሁን ባለው የኑሮ ውድነት ደስተኛ አይደሉም" የተባለ ሲሆን፣ 75 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ "መንግሥት የሚጠበቅበትን አላደረገም" ብለው የሚያምኑ ናቸው። በተሰራው የኑሮ ውድነት ጥናት ኢንደክስ መሰረት ናይጀሪያ በ19.0 ኢንደክስ ዝቅተኛ የኑሮ ውድነት ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚዋ ናት። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያለችው ሊቢያ በ21.7 ሁለተኛ ስትሆን፣ ጎረቤት ሀገር ኬንያ በ24.6 ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እንደ Business daily ሪፖርት፣ ማዳጋስካርና ሩዋንዳ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና፣ ግብፅና ሶማሊያ በቅደም ተከተል እስከ ዘጠነኛ ደረጃ ተመድበዋል። በሪፖርቱ መሰረት በ2024 ሁለተኛ ወር ላይ ቱኒዚያ 28.9 ነጥብ በመያዝ ዝቅተኛ የኑሮ ውድነት አላቸው ተብሎ ከተዘረዘሩት የአፍሪካ ሀገራት እስከ አስር ባለው ምድብ ውስጥ መጨረሻ ላይ ተመድባለች። በአንጻሩ ኢትዮጵያ በዚህ ምድብ ውስጥ ባትካተትም በቅርብ ጊዜ በወጣ ጥናት መሰረት እንደ ከተማ አዲስ አበባ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ከሚገኝባቸው የአለም ከተሞች አንዷ ሁና ተመድባ እንደነበር አይዘነጋም።
Показати все...
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ማክሰኞ ምላሽ ሊሰጡ ነው  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አስገብተው ያጠናቀቁት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የፓርላማ አባላት፤ ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጣቸው ቀናት ብዛት ሶስት ብቻ እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም መሰረት የፓርላማ አባላቱ ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጥር 18 ጀምሮ እስከዚህ ሳምንት ሰኞ ጥር 20 ድረስ ጥያቄዎቻቸውን ማስገባታቸውን አስረድተዋል። በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ “ማንኛውም የቃል መልስ የሚፈልግ ጥያቄ የሚያቀርብ አባል፤ ጥያቄውን ቢያንስ ከአስር ቀናት በፊት ለአፈ ጉባኤው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት” ሲል ይደነግጋል። የፓርላማው አፈ ጉባኤ፤ ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች መርምረው የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ ስልጣን በደንቡ ተሰጥቷቸዋል። Via Ethiopian Insider
Показати все...
የጋምቤላ ክልል ፤ በተፈጥሮ እና ሠው ሰራሽ አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ በቂ  አይደለም ተባለ በጋምቤላ ክልል በተፈጥሮ እና ሠው ሰራሽ አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት እና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመልክቷል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በጋምቤላ ክልል በላሬ እና ጋምቤላ ወረዳዎች በጎርፍ አደጋ እንዲሁም አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ግጭቶች የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ በክልሉ ያለው የተፈናቃይ ቁጥር ብዛት በውል ተለይቶ የማይታወቅ በመሆኑ የሚደረገውን ድጋፍ ውጤታማ እንዳይሆን እንቅፋት ስለሚፈጥር ክልሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የችግሩን መንስኤና መፍትሄ በሳይንሳዊ ጥናት በማስደገፍ ለዘላቂ መፍትሄ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ ክልሉ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ያለው መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ፈትሂ ፤ በምግብ ራስን ለመቻል እየተከናወነ ያለው ስራ ዝቅተኛ መሆኑ ቁጭት ሊፈጥር ይገባል ማለታቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከም/ቤቱ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል። የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋትቤል ሙን መንግስት ለተፈናቃዮች የሚያደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆን ፣ አልፎ አልፎ የሚከሰት የጸጥታ ችግር መኖሩ ገልፀው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደ ክልል ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ የፌደራል መንግስት ድጋፍ እንደሚያፈልግ ተናግረዋል ። ይህንን የተመለከቱት የቋሚ ኮሚቴው አባላት በየአመቱ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ እና አልፎ አልፎ የሚከሰተውን የጸጥታ ችግር ለመግታት በቅንጅት መረባረብ የሚገባ መሆኑን ገልፀው፤  መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚያደርጉት የሰብዓዊ ድጋፍ በተቀናጀ መልኩ ሊሰራጭ እንደሚገባ አሳስበዋል ። በበረከት ሞገስ
Показати все...