cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethiopian Orthdoxe Mezmur and orthdoxawe temrtoce

🌠በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇 ✅መዝሙሮች✅ የንስሐ መዝሙሮች✅ የማርያም ውዳሴዎች✅........ ወ.ዘ.ተ የዜማሬ እና የኦርቶዶክስ እምነት የመጠየቂያእና መወያያ ግሩፕ @mezort777

Більше
Рекламні дописи
563
Підписники
-124 години
-27 днів
-1230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ስልጤ ዞን ቅባት ከተማ አጋጥሞ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሀይማኖት አባቶች ወደ ቡታጅራ ማቅናታቸው ታውቋል! ቡታጅራ በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ያለመ ነው ተብሏል።ቅባት ከተማ በተፈጠረው ግጭት ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።ሀብት ንብረት ወድሟል።ግጭቱ ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ነው ተብሏል።አሁን ላይ ከተማዋ አንፃራዊ መረጋጋት እየታየባት መሆኑን የመረጃ ምንጮቹ አረጋግጠዋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ትኩረት በስልጤ ዞን ቅባት ከተማ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መኖርያ ቤቶች ላይ ዘረፋ እና ጥቃት እየተፈፀመ እንደሆነ በስፍራው ያሉ ዜጎች አሳውቀውኛል። ሰኞ እለት ቤተክርስቲያን ላይ ጭምር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ ተደርጎ በፀጥታ አካላት ትብብር መክሸፉ ቢታወቅም አሁን ድረስ ጥቃቱን ፈርተው በየቤተክርስቲያኑ ተጠልለው የሚገኙ በርካታ ዜጎች እንዳሉ ታውቋል። ይህን ተከትሎ ከስልጤ ዞን ቅባት ከተማ የተወጣጡ የእስልምና እምነት ተከታይ የሀገር ሽማግሌዎች ከታቦተ ማርያም ጋር ተሰደው የሚገኙ ሰዎችን ቡታጅራ ድረስ በመሄድ አጽናንተዋል። እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ክርስቲያን ሙስሊም ሳንል ሁላችንም ልናወግዝ ይገባል። Photo: social media @EliasMeseret
Показати все...
✝️ ያልተቋረጠ የክህነት ቅብብሎሽ✝️ ፩) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪) ቅዱስ ማርቆስ ፫) አናንዮስ ፬) መልዮስ ፭) ካርዳኖስ ፮) ፐሪሙስ ፯) ዮስጦስ ፰) ኦማንየስ ፱) ማርያኒስ ፲) ክላንድንያስ ፲፩) አግሪጳኖስ ፲፪) ዩልያኖስ ፲፫) ዲሜጥሮስ ፩ኛ (ባሕረ ሐሳብ የተገለጠለት) ፲፬) ኤራቅሊስ ፲፭) ዲዮናስዮስ ፲፮) ማክሲመስ ፲፯) ቴዎናስ ፲፰) ጴጥሮስ ፩ኛ (ተፍጻሜተ ሰማዕት) ፲፱) አኪላስ ፳) እለእስክንድሮስ ፩ኛ (የጉባኤ ኒቅያ አፈጉባኤ) ፳፩) አትናቴዎስ ፳፪) ጴጥሮስ ፪ኛ ፳፫) ጢሞቴዎስ ፩ኛ (የጉባኤ ቁስጥንጥንያ አፈጉባኤ) ፳፬) ቴዎፍሎስ ፳፭) ቅዱስ ቄርሎስ ፩ኛ (የጉባኤ ኤፌሶን አፈ ጉባኤ ፳፮) ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፩ኛ ፳፯) ጢሞቴዎስ ፪ኛ ፳፰) ጴጥሮስ ፫ኛ ፳፱) አትናቴዎስ ፪ኛ ፴) ዮሐንስ ፩ኛ ፴፩) ዮሐንስ ፪ኛ ፴፪) ዲዮስቆሮስ ፪ኛ ፴፫) ጢሞቴዎስ ፫ኛ ፴፬) ቴዎዶስዮስ ፩ኛ ፴፭) ጴጥሮስ ፬ኛ ፴፮) ድምያኖስ ፴፯) አንስታትዮስ ፴፰) እንድራኒቆስ ፴፱) ብንያሚ ፩ኛ ፵) አጋቶን ፵፩) ዮሐንስ ፫ኛ ፵፪) ይስሐቅ ፵፫) ስምዖን ፩ኛ ፵፬) እለእስክንድሮስ ፪ኛ ፵፭) ቆዝሞስ ፩ኛ ፵፮) ቴዎድሮስ ፩ኛ ፵፯) ሚካኤል ፩ኛ ፵፰) ሚናስ ፩ኛ ፵፱) ዮሐንስ ፬ኛ ፶) ማርቆስ ፪ኛ ፶፩) ያዕቆብ ፶፪) ስምዖን ፪ኛ ፶፫) ዮሴፍ ፩ኛ ፶፬) ሚካኤል ፪ኛ ፶፭) ቆዝሞስ ፪ኛ ፶፮) ሱንትዩ ፩ኛ ፶፯) ሚካኤል ፫ኛ ፶፰) ገብርኤል ፩ኛ ፶፱) ቆዝሞስ ፫ኛ ፷) መቃርዮስ ፩ኛ ፷፩) ቴዎፋኖስ ፷፪) ሚናስ ፪ኛ ፷፫) አብርሃም ፷፬) ፊላታዎስ ፷፭) ዘካርያስ ፷፮) ሱንትዩ ፪ኛ ፷፯) ክርስቶዶሉስ ፷፰) ቄርሎስ ፪ኛ ፷፱) ሚካኤል ፬ኛ ፸) መቃርዮስ ፪ኛ ፸፩) ገብርኤል ፪ኛ ፸፪) ሚካኤል ፬ኛ ፸፫) ዮሐንስ ፭ኛ ፸፬) ማርቆስ ፫ኛ ፸፭) ዮሐንስ ፮ኛ ፸፮) ቄርሎስ ፫ኛ ፸፯) አትናቴዎስ ፫ኛ ፸፰) ገብርኤል ፫ኛ ፸፱) ዮሐንስ ፯ኛ ፹) ቴዎዶስዮስ ፪ኛ ፹፩) ዮሐንስ ፰ኛ ፹፪) ዮሐንስ ፱ኛ ፹፫) ብንያሚ ፪ኛ ፹፬) ጴጥሮስ ፬ኛ ፹፭) ማርቆስ ፭ኛ ፹፮) ዮሐንስ ፲ኛ ፹፯) ገብርኤል ፬ኛ ፹፰) ማቴዎስ ፩ኛ ፹፱) ገብርኤል ፭ኛ ፺) ዮሐንስ ፲፩ኛ ፺፩) ማቴዎስ ፪ኛ ፺፪) ገብርኤል ፮ኛ ፺፫) ሚካኤል ፭ኛ ፺፬) ዮሐንስ ፲፪ኛ ፺፭) ዮሐንስ ፲፫ኛ ፺፮) ገብርኤል ፯ኛ ፺፯) ዮሐንስ ፲፬ኛ ፺፰) ገብርኤል ፰ኛ ፺፱) ማርቆስ ፭ኛ ፻) ዮሐንስ ፲፭ኛ ፻፩) ማቴዎስ ፫ኛ ፻፪) ማርቆስ ፮ኛ ፻፫) ማቴዎስ ፬ኛ ፻፬) ዮሐንስ ፲፮ኛ ፻፭) ጴጥሮስ ፭ኛ ፻፮) ዮሐንስ ፲፯ኛ ፻፯) ማርቆስ ፯ኛ ፻፰) ዮሐንስ ፲፰ኛ ፻፱) ማርቆስ ፰ኛ ፻፲) ጴጥሮስ ፮ኛ ፻፲፩) ቄርሎስ ፬ኛ ፻፲፪) ዲሜጥሮስ ፪ኛ ፻፲፫) ቄርሎስ ፭ኛ ፻፲፬) ዮሐንስ ፲፱ኛ ፻፲፭) መቃርዮስ ፫ኛ ፻፲፮) ዮሳብ ፪ኛ ፻፲፯) ቄርሎስ ፮ኛ ፻፲፰) አቡነ ባስልዮስ ዘኢትዮጵያ ፻፲፱) አቡነ ቴዎፍሎስ ዘኢትዮጵያ ፻፳) አቡነ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ ፻፳፩) አቡነ መርቆሬዎስ ዘኢትዮጵያ ፻፳፪) አቡነ ጳውሎስ ዘኢትዮጵያ ፻፳፫) አቡነ ማትያስ ዘኢትዮጵያ የክህነት ምንጭ ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ እስከአሁኑ ፓትርያርካችን እስከ አቡነ ማትያስ ያለው የክህነት ቅብብሎሽ ከላይ ያለውን ይመስላል። የእያንዳንዱ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ጳጳስ ክህነት ቢቆጠር ነቁ እና የክህነቱ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በጉልበት ራሳቸውን የሾሙ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ የተሿሿሙ ሰዎች ክርስቶሳዊ የሆነው ክህነት የላቸውም። ይህም ማለት ቀድሰው ምሥጢራትን አይለውጡም። ጸጋ እግዚአብሔርን አያሰጡም። ስለዚህ ሕገወጥነትን አምርረን ልንቃወም ይገባናል።           
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ለ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር ሼር ሼር ለሁሉም ይዳረስ ፍኖተ ፅድቅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አይወክልም‼️‼️ ፍኖተ ፅድቅ ቤተ ክርስትያንን የሚመርዝ አደገኛ መርዝ ነው ፍኖተ ፅድቅ ተሐድሶ ነው ፍኖተ ፅድቅ አስመሳይ ተኩላ ነው ፍኖተ ፅድቅ መዝሙርን የሚመርዝ ምዕመናንን የሚያወዛግብ አንዴ ኦርቶዶክስ አንዴ ደግሞ ተሐድሶ አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንት ዝማሬ እያቀረበ ይገኛል ኦርቶዶክሳውያ ኦርቶዶክሳዊን ያልጠበቀ መዝሙራትን እየለቀቀ ነበር አሁንም እየለቀቀ ይገኛል በፍኖተ ፅድቅ ላይ የተገኛችሁ ሰባክያን ዘማርያን ይሄን እውነት ትቃወሙት እና ልታስቆሙት ይገባል እናንተም አንዱ ተሳታፊ ነበራችሁና በአስቸኳይ አስቁሙ እኛ ምፅመናን ደግሞ የ ዮቲዮብ ገፃቸውን ሪፖርት በማድረግ እንዲዘጋ ድርሻችንን እንወጣ ፍኖተ ፅድቅ ተዋህዶን አይወክልም‼️ ሼር ይደረግ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በትግራይ የሚገኙ ብፁን አባቶች ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ቅዱስ ሲኖዶስ በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡ 1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ 2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ    የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የትግራይ ቤተከርስቲያን አልመለሰም ብለው ዛሬ የጳጳሳት ማፅደቅ እንደሚጀምሩ አሳውቀዋል ።ቀጣይ የኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን ውሳኔ የትግራይ ቤተከርስቲያን ጳጳሳት ሹመት እንዲሻር እንዲወገዙ የሚያደረግ ውሳኔ ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን አባቶች በተደጋጋሚ የተማዕፅኖ "ኑ እንወያይ የሚል ጥሪ ለትግራይ አባቶች ቢያቀርቡም በራሳቸው ውሳኔ ይሁን በትግራይ በመንግሥት ወይም ብሄርተኞች ተፅዕኖ ደፍረው ያላቸውን ችግሮች ከመናገር ይልቅ ጭራሽ በራቸውን ዘግተው መሸሽን ነው የመረጡት። ወዲ ሻምበል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው:: ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።
Показати все...
#Update በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን  ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም  ወደ ትግራይ  ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ .ም ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ  ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር  መሆኑ ታውቋል። ይህንን በተመለከተም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተላከው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማለዳ እንዲደርስ ተደርጓል። መረጃው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
Показати все...
💙 ✞ የኢቲሳ አንበሳ ✞ 🦁 የኢቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሳ ወገንክን ታደገው ከኃጥያት አበሳ ተኩላው ለምድ ለብሶ በእርግጥ መጥቷልና ጴጥሮስ ሆይ ዝምአትበል እንደጥንቱ ቅና ዮሐንስ ዝም አትበል እንደጥንቱ ቅና   የዓለም ምናምንቴ የተባልከው ቅዱስ የዋሁ መነኩሴ አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያምን ናና ዛሬም ቀድስ በዕጣኑ መዐዛ ድውያንን ፈውስ(2) ⏰⏰⏰⏰ የወንጌል አንበሳ ጎርጎርዮስ ፍጠን ምሰሶው ሳይወድቅ መንጋው ሳይበተን መብረቁ አትናቴዎስ ሞገዱን ገስፀው አፈ ጉባያችን በመስቀልህ ዳኘው(2) ⏰⏰⏰⏰ መርከቧን የሚያውክ ነፋስ መጥቷልና አምላካችን ፈጥነህ አድነን ቶሎና ጴጥሮስ ሆይ ቀስቅሰው ልንጠፋነው ብለህ ሞገዱ እያየለ ዝም እንዳይል ጌታ(2)  ⏰⏰⏰⏰ ከሣቴ ብርሃን ሰላማ ቶሎና ኖላዊ እረኛ ያስፈልጋልና ሥጋውን የጎዳ ነፍሱን የጠቀመ ነቅ ጉድፍ የሌለው ግብሩ የታረመ(2)                     መዝሙር     🫶 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ🫶
Показати все...
የኢቲሳ አንበሳ .mp34.93 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ሰበር_ዜና  ቅዱስ ሲኖዶስ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫን አካሔደ !!! * ሲመታቸው ሐምሌ 9 ይከናወናል፤ * ከነገ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠና ይገባሉ፤ +++++ (አደባባይ ሚዲያ ሰኔ 28 /2015 ዓ.ም፤ July 5/2023) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሔደው ልዩ ስብሰባ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች፣ በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ፣ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ አካሒዷል፡፡ በዚኽም መሠረት፡- ለኦሮሚያ ክልል ሰባት አህጉረ ስብከት፤ 1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት 2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት 3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት 5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት 6. አባ ተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት 7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ለደቡብ ኢትዮጵያ ኹለት አህጉረ ስብከት፤ 8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌድኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት 9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.