cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የዕውቀት ማዕድን

Більше
ЕфіопіяАмхарськаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
189
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
-1030 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

1. ከሰዎች ጋር ለመስራት ስትፈልግ ሶስት ነገሮቻቸውን ተመልከት፦ ብልህነት (intelligence)፣ ጉልበት (energy) እና ታማኝነት (integrity)፡፡ እና የመጨረሻው ከሌላቸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት ስብእናዎች አትጨነቅ! ☞ ምክንያቱም በእውነት (truth)፣ በሐቀኝነት (honesty) እና በስነ-ምግባር (ethics) ልኬቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማንም ባይመለከታቸው እንኳ ልባቸውን ያዳምጣሉ፣ ትክክለኛውን ነገርም ያደርጋሉ ፡፡ 2. ስኬታማ በሆኑና ያልተሳካላቸው ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ስኬታማ ሰዎች በማያስፈልጉ ነገሮች ላይ 'ምንጊዜም 'አይሆንም' (no) ስለሚሉ ነው። ☞ በየቀኑ ወደ እኛ አቅጣጫ ለሚመጡ አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ደግመን ደጋግመን 'አይሆንም' (no) ማለት እና አስፈላጊ ለሆኑ ጥቂት ነገሮች ትኩረት በመስጠት 'እሽ' ማለት አለብን። ይህን መርህ በየትኛውም ነባራዊ ሁኔታ፣ በዕለት ተዕለት የውሳኔ አሰጣጥ መንታ መንገድ ላይ ስትደርስ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ይህን ካደረክህይወትህን ማቅለል ትችላለህ። 3. ከአንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ! ☞ በባህሪያቸው ከአንተ የተሻሉ ጓደኞችን መምረጥ ከቻልክና ከእነሱ ጋር ጊዜህን ካሳለፍክ አንተም ወደዚያ አቅጣጫ መጓዝ ትችላለህ፡፡ ዕድሜህም ሆነ ያለህበት ደረጃ ምንም ይሁን ምን እንደ መሪ፣ የንግድ ሰው ፣ ሠራተኛ እና ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ የሚያደርግህን ጥበብ ፣ ልምድ እና ባህርይ የበለጠ ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች መማር አስፈላጊ ነው፡፡ . 4. ሀብታም ብትሆን ወይም የገንዘብ ነጻነት ቢኖርህ ልትሰራው የምትችለውን ስራ ለመስራት ወስን! ☞ ይህን ስታደርግ የምትወደውን እና የምትጓጓለትን ነገር መፈለግና ያንን የህይወትህ ዋና ተግባር እንድታደርገው ይረዳሃል። ይህ ማለት በየቀኑ ልትሰራው የምትጓጓለት ስራ ስላለህ ከአልጋህ ዘለህ ትነሳለህ፣ ምንጊዜም አንድ ነገር ትማራለህ ይህም ደስታን ይሰጥሃል። 5. ዝናን ለመገንባት 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል ይህን ለማበላሸት ግን አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል ፡፡ ይህን ማስብ ከቻልክ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግ ትችላለህ። ☞ የማንኛውም ሰው ዝና ወይም እውቅና በአሸዋ እንደተገነባ ቤት በፍጥነት ሊወድቅ ይችላል። ስለሆነም በህይወት ጉዞህ የምትመራበትን ታማኝነት (integrity) በውስጣዊ የጂፒኤስ ስርዓትህ ውስጥ ሳትገነባ ከቀረህ መውደቅህ የማይቀር ነገር ነው፡፡ የትኞቹ ምክሮች ተመቿችሁ? Comment አድርጉልን!
Показати все...
#ራስህን_አትዋሽ_ስልህ ያንተን ገጸ -ባህሪ ማንም አይወድልህም። ሁሉም ሰው ያለህበትን ቦታ ነው የሚወደው። ሁሉም ሰው የሚወደው ያለህን የሀብት ልክ ነው ! ሁሉም ሰው የሚወደው ያገኘኸን የግልም የሆነ የመንግስት ስራ ነው። ያንተ መኪና፣ ቤት፣ ሳይክልህን፣ መንገድ ዳር ያለ አማላይ ቤትህን ሁሉም የሚወደው መኖርህን ሳይሆን ያለህን ነው! አንተን እሚወድህ የለም ወዲያ! ኧረ ተረጋጋ ወንድሜ ማነው እንዲህ ያለው?😅 ወዳጄ ሲጀመር መወደድ የተፈጥሮ እንጂ የማግኘት የማጣት አይደለም። ቢኖርህ ቆንጆ፣ ቆንጆ ሴቶችን እንደ'ቃ ትገዛ ይሆናል እንጂ፣ መልከ ጥፉ እንኳ ልትወድህ አትችልም። መኪና ቢኖርህ ጓደኛህ ከስራ ሲወጣ እንድትሸኘው፣ ማንም ሳይስቅልህ ሲቀር ይገለፍጥልህ ይሆናል እንጂ... ባለመኪና ስለሆንክ ብቻ ሊወድህ አይችልም። ቤት ስላለህ ብቻ ኑሮ የጠበሳቸው ደርዘን ሴቶች ሊያገቡህ ፍቃደኛ ሊሆኑ ይችላሉ። አባ አንዷም ላትወድህ ትችላለች። ብር ስላለህ ብቻ ጋባዥ ስለሆንክ ሰፈሬው አገጩ መሬት እስኪልስ ለጥ ብሎ ሰላም ሊልህ ይችላል። ያ ማለት ተወዳጅ አያስብልህም ስልጣን ወይም አሪፍ ስራ ስላለህ ብቻ ''የተከበሩ'' ትሰኝ ይሆናል እንጂ ክብር ካንተ የራቀ ሊሆን ይችላል። አባ ስላለህ ሳይሆን ስለማንነትህ ሰዎች ሊወዱህ ተፈጥሮ ነው። ቤት፣ መኪና፣ ገንዘብ ያንተ ስለሆኑ የሰው ቀፎ የሆኑ ግለሰቦችን እንዳሻህ ትገዛ ይሆናል፤ ልባቸውን ግን አታገኘውም። ስለዚህ ያለህ መልካም ስብእና፣ ፍቅር እና ፍቅር ያስገኝልሃል። ☑️ ገንዘብ ገዢ ቢሆን ፣ መውደድ አይሸጥም ምግባር የሌለው ሰው፣ ላፉ -ስ አይጣፍጥም ስልጣን ምን ቢፈራ፣ ክብር እንዲሁ አይደል ሁሉን እንዲያገኙ፣ መልካም ባህሪ እንጂ፣ በምግባር መታደል በል ደግሞ እነዚህን መጽሐፍት አንብብ #በራስ_መተማመን መጽሐፍ 5ተኛ ዕትም #ራስን_መምራት 2ተኛ ዕትም ሁለቱም መጽሐፍት በገበያ ላይ ይገኛሉ 📕📕📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) ቴሌግራም- https://t.me/teklu_tilahun ፌስቡክ ገጽ 1- https://bit.ly/3sNq5Kd ፌስቡክ ገጽ 2- https://bit.ly/3sJcsMa
Показати все...

👍 1
ሸሽተህ አታተርፍም! ፨፨፨//////////፨፨፨ የተስተካከለ፣ ለአውሎ ንፋስ ያልተጋለጠ ውቂያኖስ የተዋጣለት መርከበኛ ሊፈጥር አይችልም፤ አልጋ በአልጋ የሆነ ህይወት ጥበበኛን አይፈጥርም። ጥበብ ያለችው በበፈተና ውስጥ ነው፣ እውቀትና እድገት የሚገኘው በመሰናክል ከተሞላው ጉዞ ነው። ዛሬ ፍልሚያ ውስጥ ከሆናችሁ እያደጋችሁ እንደሆነ እወቁ፣ ዛሬ በህይወት እየተፈተናችሁ ከሆነ የተሻለ ነገር እየጠበቃችሁ እንደሆነ እመኑ። ከባዱን ጦርነት ያሸነፈ ጦረኛ የሚበረከትለት ማዕረግ፣ የሚያገኘው ክብር እጅጉን የተለየ ነው። ህይወትም አብዝቶ በመፋለም ፈተናዎችዋን ላለፈ ሰው የተለየ ክብርና ቦታን ትሰጣለች። በሂደት አንድ ነገር ይገለጥላችኋል ቀላል የተባለው አካሔደ እያደር ሲያሰንፋችሁ፣ የተመቻቸው ጉዞ በሒደት ዋጋ ሲያሳጣችሁ ታስተውላላችሁ። የሚበጃችሁን ፈጣሪ ያውቃልና በመከራ መሃል ለላቀው በረከት ተዘጋጁ፣ ለተሻለው ክብር እራሳችሁን አዘጋጁ። አዎ! ጀግናዬ..! ሸሽተህ አታተርፍም፣ ተደብቀህ አታድግም፣ እያማረርክ አትቀየርም። ይልቅ ለየትኛውም ፍልሚያ እራስህን አዘጋጅ፣ መንፈስህን አጠንክር፣ ወደ ድል እራስህን አቅርብ፣ ዛሬ ካለህ የተሻለ እንደሚገባህ እመን። ያሰብከው ላይሆን ይችላል፣ ምኞትህ ላይሞላ ይችላል፣ እቅድህ ላይሳካ ይችላል፣ ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ ነገር ግን በዚህ ሁሉ ባልተመቻቸ አካሔድ ያንተ እድገት አያቆምም። ምንም ቢሆን እየተንቀሳቀስክ ነው፤ ምንም ቢፈጠር የቻልከውን እየጣርክ ነው፤ ምንም ቢመጣብህ ወደፊት እየተጓዝክ ነው። የቆምክ እለት ህይወትህ እንደምትቆም አስተውል፣ የተሻልክ የመሆን ፍላጎት ስታጣ እድገትህ የኋሊት እንደሚሆነ አስተውል። ህይወት በየጊዜው እድል በማይመስሉ አስደናቂ እድሎች የተሞላች ነች፤ ህይወት ፈተና በመሰሉ በረከቶች የተከበበች ነች። ሁሉን በምክንያት የመጠቀሙ ድርሻም የእኛ የባለቤቶቹ ነው። አዎ! የትኛውም ፈተና በስተመጨረሻ የእራሱ ውጤት ይኖረዋል፣ ማንኛውም ውጣውረድ በስተመጨረሻ ለድል ያበቃል። ለዚህ ነው ፅናትን እንደ ብቸኛ ምርጫ የምትወስደው። እያንዳንዱን የግል ጦርነት ማሸነፍ በአደባባይ ለድል እንድንበቃ ያደርገናል። ሁላችንም ልክ እንደ ከባዱ ቀላልና የተመቻቸ ምርጫ አለን፣ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ከአደጋ የፀዳና የተመቻቸ መንገድ አለን። ለተሻለ ስፍራ የሚያበቃንን ምርጫ የምንመርጠው ግን እኛው እራሳችን ነን። ጨለማውን መርጦ ለአስፈሪው ጨለማ የሚያመሰግን ጠንካራ ሰው አለ፣ ከምቾት አደጋን መርጦ በምርጫው የሚኮራ ሰው አለ፣ ስጋት ከሌለው አካባቢ አስፈሪና በውጣውረድ የተሞላ ከባቢ ውስጥ እራሱን የሚያስገባ የላቀውን ስኬት የተጠማ ደፋር ሰው አለ። በምርጫችሁ እደጉ፣ ሊፈትናችሁ የመጣን አጋጣሚ እንደ አድል ተጠቀሙት። ሰናይ ምሽት
Показати все...
#ያለው_ድሀ_አትሁን! ምንድነው መሰለህ ወዳጄ አንዴ ከድህነት አለም ተነስተህ የሆነ የማግኘት ደረጃ ላይ ትደርሳለህ። ሀብት ታገኛለህ owwww that's great for you; but you have to know something here. ልክ አንድ አስፈላጊ ደረጃ ላይ ስትደርስ፤ መኖር መቻል አለብህ። ገንዘብን ዛሬም አጠራቅመዋለሁ፣ ነገም አጠራቅመዋለሁ ብትል ጭንቀት ነው የሚሆንብህ። የማያኖርህ ከሆነ እኮ ማጠራቀም የማይወጡበት ሱስ ማለት ነው። አስበው ሚሊየነር ሁነህ 'ፌድ' ያደረገ አላቂ ልብስ ስትለብስ😀 አባ አብጃለሁ በልና ህመምህ ታውቆ በገንዘብህ ታከምበት። ይህ አይነቱ ቁጠባ መስገብገብ እንጂ ምንም ሊባል አይችልም። ቢሊየነር ሁነህ የሰራተኞችህን ደሞዝ በጊዜ የማትለቅ ከሆነ ያለው ድሀ ማለት አንተ ነህ። አባ መኪናህን እያሽከረከርክ ስትሄድ ምን እንደሚያጋጥምህ አይታወቅም። መቼስ እግዜሩ ይሄ ሰው ሀብታም ነውና ሞት ይለፈው አይልልህም። ፈጣሪን ጉቦ ሰጥተህ እድሜ አትቀጥል ነገር ነው -ና። ብዙም የሰው ጅብ ለመሆን አታቅድ። በቃ ቆጥቤ ቆጥቤ ቆጥቤ ቆጥቤ ...ብቻ አላማህ አይሁን። ገንዘብ ማግኘት በራሱ የስኬት በር እንጂ ስኬት ሆኖ አያውቅም። በርግጥ እንደ አንድ ተራ ሆዳም እንዲያ ማሰብ ይቻላል። ለብልህ ሰዎች ግን ገንዘብ ድልድይ መስሪያ እንጂ፣ በራሱ ድልድይ አይደለም። በገንዘብ የምታገኘው ከፍ ያለ ድል እንጂ ራሱ ገንዘብ አላማህ ከሆነ እነሆ፤ አንተ ማለት ከድህነት ወደ ድህነት ለመሸጋገር የምትለፋ ብኩን ፍጥረት ነህ። ያለው ድሀ አይተህ አታውቅም? ሀብቱን ሰዎችን ዝቅ ለማድረግ የሚጠቀም -እንደዛማ ተራ መሆን የለብህም። ገንዘብ ስትፈልግ ለምን ፈለግኩ ማለት የሚኖርብህ ለዚህ ነው! ለተግሳጼ ይቅርታ አልጠይቅህም  አስብበት! ለቸገራቸው አካፍል የሰራተኞችህን ደሞዝ በጊዜ ስጥ በተቸገረ ሰው ፊት ምን ያህል እንዳለህ አታውራ! ሸጋ ቀንን ተመኘሁ🙏
Показати все...
🥰 2
🌞 ሰበብ አታብዛ! ከእንቅልፍ መነሳት ካለብህ አሁኑኑ ተነስ አልጋ ውስጥ እየተገላበጥክ ምንም አትፈጥርም። መስራት ያለብህ ነገር ካለ ተነስና ስራ፤ መሄድ ያለብህ ቦታ ካለ በኋላ እሄዳለው አትበል። ዛሬን ሳትጨርስ ነገን እንዳትጀምር! ለዛሬ ያሰብካቸውን ሁሉ መፈፀም አለብህ። አለበለዚያ ሰበብ ስታበዛ ባልህበት እየረገጥክ ቆመህ ትቀራለህ! ለምክንያትና ሰበብ ቦታ የማትሰጥ ከሆነ በህይወት ስኬት ረጅም ርቀት ትጓዛለህ። ሰበብን ለሰነፎች ተውላቸው ያንተ ፀባይ አይደለም ወዳጄ! የሚደንቅ ውሎ ተመኘንላችሁ🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Показати все...
👍 1
አዎንታዊ አመለካከት! አዎንታዊ አመለካከት በችግሮች ላይ ሳይሆን በመፍትሔዎች ላይ በማተኮር ብሩህ አመለካከት መያዝን ይጨምራል። እሱን ለመገንባት፣ ምስጋናን ያሳድጉ፣ አእምሮን ፀጥ ማድረግ መለማመድ እና እራስዎን በአዎንታዊ ተፅእኖዎች ይክበቡ። ጥቅሞቹ የተሻሻለ የአዕምሮ ደህንነትን፣ ጽናትን እና የተሻሻለ ግንኙነቶችን ያካትታሉ። አመለካከትን መለካት ብዙውን ጊዜ ባህሪን እና የግንኙነት ዘይቤዎችን መከታተልን ያካትታል። አዎንታዊ አመለካከት ጽናትን፣ እና ለችግሮች ንቁ አቀራረብን በማጎልበት ለስኬት አስተዋፅኦ ያደርጋል። ችግርን የመፍታት ችሎታን ያሳድጋል እና አወንታዊ እድሎችን ይስባል፣ በመጨረሻም ግቦችን ለማሳካት አስተሳሰብን ይቀርፃል። ቀና አመለካከትን ለመገንባትና ስልጠናዎችን ለሥትፈልጉ በኢን ቦክስ አውሩኝ ስልጠናዎች አሉን። Bisrat0642 Bisrat 0938423207 ቀና እና ቡሩህ ቀንን ተመኘሁ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ስህተትህን ተጠቀምበት ! ከዚህ በፊት ሰዎች በተለያየ አጋጣሚ ደጋግመው አሞኝተው ሸውደውህ ይሆናል፤ እና ሞኝ ነህ ማለት ነው? አይደለህም! አየህ በዚህ አለም ለአላማህ ስትሮጥ ደጋግመህ መውደቅና መሳሳት ያለ እኮ ነው፤ የውድቀት ሰው ነህ ማለት ግን አይደለም! 🙏🙏የስኬት ቀን ተመኘን🙏🙏
Показати все...
🔥 2
ማቆም የለም! ነገሮች ከፍ ዝቅ እያሉ ይሆናል፣ ከመቀጠል ይልቅ ማቆም የተሻለ የሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህ ግን ሁሉንም እርግፍ አርጎ መተው ቀላል ነው፤ ሀይል ሰብስቦ መቀጠል ነው ከባዱ! ወዳጄ ለራስህ የምትሆነው ከዛ ለምትወዳቸው የምትደርሰው ተስፋ ሳትቆርጥ ከቀጠልክ ብቻ ነው። ለዛ ነው መበርታት ያለብህ፤ ዳይ ያቆምከውን ቀጥል አሁኑኑ! ተስፋ የሞላው ህይወት ተመኘንላችሁ🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Показати все...
1
ሁሉም ቀን ጥሩ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን በእያንዳንዱ ቀን ቢያንስ አንድ የምናመሰግንበት ጥሩ ነገር አይጠፋም።ለእያንዳንዱ ነገር ሁልጊዜም ማመስገን ገንዘባችን ሊሆን ይገበዋል።  ማመስገን ሌላ የምናመሰግንበት የተሻለ ነገር  እንዲጨመርልን ያደርጋል። ምስጋና የተሰጠንን ስለመቀበላችን ማረጋገጫ ነው። የተሰጠውን ያልተቀበለ ሌላ ሊሰጠው አይችልም። ብዙዎቻችን የዘነጋው ትልቁ የህይወት ቁልፍ ማመስገን ማመስገን ማመስገን ነው። ቆንጆ እለተ ሰንበት ተመኘሁ!
Показати все...
2