cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

Більше
Рекламні дописи
3 793
Підписники
+1824 години
+617 днів
+32530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የሥራ ሥነ-ምግባር (Work Ethics) ላይ ስልጠና ተሰጠ ************* (ሰኔ 14/2016ዓ.ም አዲስ አበባ) በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት የስራ ላይ ሥነ-ምግባር (Work Ethics) በተመለከተ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ተቋማዊ ስራ አመራር ዘርፍ የተዘጋጀ ነው፡፡ ወ/ሮ አስቴር አዱኛ በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ገቢዎች አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ሥነ-ምግባር ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን ገልፀው የሥነ-ምግባር ግድፈት ከትንሹ ጀምሮ እያደገ የሚሄድ በመሆኑ ከጅምሩ መቅጨት ያስፈልጋል የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈው በስልጠናው ያገኘነውን ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ስልጠናው ለሁሉም የቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ለመስጠት ዕቅድ እንደተያዘ አክለው ተናግረዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዋናው መስሪያ ቤት የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት የሥነ-ምግባር ትምህርት እና ሀብት ምዝገባ መሪ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበራ አምሳሉ ነው፡፡ በስልጠናው የሥነ-ምግባር ፅንስ ሀሳብ፣ የስራ ላይ ሥነ-ምግባር ምንነት፣ የሥነ-ምግባር ጉድለቶች እና መገለጫዎች እንዲሁም የሚያስከትሉት ተፅዕኖ፣ በስራ ቦታ መልካም ሥነ-ምግባርን ለመገንባት መደረግ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በተመለከተ ሰፊ ገለፃ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚና ስራቸውን ሥነ-ምግባር ተላብሶ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዛቸው ጠቁመዋል፡፡ ተቋሙ መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸውን ሰራተኞች እውቅና እና ማበረታቻ ቢሰጥ ለሌላውም መነሳሳትን ይፈጥራል የሚል ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ እና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ በስልጠናው መክፈቻ ንግግራቸው የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴት ሥነ-ምግባርን ተላብሶ አገልግሎት መስጠት ወሳኝ በመሆኑ የዛሬው ስልጠና መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ወደ ዕራሳችን በመውሰድ ተቋሙ የሚፈልገውን ሥነ-ምግባር በመላበስ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ግብር÷ ለሀገር ክብር! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/mto2infoo ኢሜል፡- [email protected] ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2 በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Показати все...
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

ለስምንተኛ ዙር ሰልጣኞች ፈተና ተሰጠ ***************** በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክፍል ሶስት የሞጁለር ስልጠናን ላጠናቀቁ የስምንተኛ ዙር ሰልጣኞች ፈተና ሰጠ፡፡ የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሰጣጥ፣ ስለ ደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ፣ የታክስ ማስታወቂያዎችና ቅጾች፣ የታክስ ስሌቶችና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመክፈል፣ የታክስ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ ስልጠና በመውሰድ ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ ግብር÷ ለሀገር ክብር! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/mto2infoo ኢሜል፡- [email protected] ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2 በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Показати все...
የግንቦት ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ ******** (ሰኔ 14/2016 ዓ.ም አዲስ አባባ)፡- በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች  ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማኔጅመት አባላት የግንቦት ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል  አካሄዱ፡፡ በግምገማው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች፣ የሁሉም የስራ ክፍል የቡድን አስተባባሪዎችና የስራሂደቶች ተገኝተዋል፡፡   ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በግንቦት ወር እቅድ ብር1,559,989,523.75፣ ክንዉኑ ደግሞ ብር1,005,281,511.90 መቻሉ እና ከግንቦት ወር የሁሉም የሥራ ከፍልች የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ገቢን በተሻለ ሁኔታ ለመሰብሰብ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም የዘመቻ ስራ መስራት መቻሉ፣ ለፌደራል ኦዲት ግኝት ትኩረት በመስጠት ከዉስጥ ኦዲት ጋር በመነጋገር እና በመናበብ ማሰተካከያ መዉሰዱ መቻሉ፣የተሰጠንን እቅድ ለመሳካት የኦዲት ስራዎች የትርፍ ሰዓት ስራ ጭምር በመስራት የመደበኛ እቅድን በፋይል ማሳካት መቻሉ በዕቅድ አፈፃፀሙ ከታዩ ጠንካራ ጎኖች መካከል ሲገኙበት የግብር የውሰኔ ማስታወቅያ ድርሷቸው ክፍያ ያልፈፀሙ ድርጅቶችን የማስጠንቀቂያና የእግድ ድብዳቤ ሙሉ በሙሉ ማዳረስ አለመቻል፤ የተጠራቀመ የገቢ ጉድለት መኖሩ ደግሞ ከታዩ ክፍተቶች መካከል ይገኙበታል፡፡  የማኔጅመንትና መላዉ ሰራተኞች በመተባበር የልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን የዘመቻ ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ጥረት ማድረግ፣ ስራዎችን በጥብቅ ዲሲፒሊን መምራት፣በተነሳሽነት መስራት፣መገምገም፣የስራ አፈፃፀም አቅጣጫ ማስቀመጥ፣ ስራ ቆጥሮ መስጥትና መቀበል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ውስጥ ይገኙበታል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀሙ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ቡድን አስተባባሪ ኮማንደር ሞላ ተሾመ የቀረበ ሲሆን ውይይቱ በወ/ሮ ሮዛ ጀማል የዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ እና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅተ ተመርቷል፡፡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች ዋና ዋና የጥናቶቹ ግኝቶች ቀርበዋል፡፡   የውይይቱን የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጠቱት ወ/ሮ ሮዛ ጀማል በሰጡት አስተያየት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ያሉትን ግብር ከፋዮች በጥናት ላይ በመሞርከዝ ማወቅ መቻሉን ገልፀው በጥናቱ ለተሳተፉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀጣይ ባለው ጊዜ ውስጥ ሁሉም በቡድን ስሜት በመስራት ገቢውን ከፍ ማድድረግ እንደሚገባ ባፅኖት ከሰጡዋቸው የማጠቃለያ አቅጣጫዎች መካከል ይገኙበታል፡፡  
Показати все...
👍 3
👍 2
THE EXCISE STAMP MANAGEMENT DIRECTIVE_1004_2024.pdf3.77 KB
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 3
Показати все...
የግምት ታክስ ስሌት እንዴት ይከናወናል አሰፈላጊነቱስ

ይህ ቻናል በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅ/ጽ/ቤት የከፈተው ኦፊሴላዊ የዩቲዩብ ቻናል ሲሆን በዚህ ቻናል ስለታክስ እና ግብር ነክ የሆኑ ቪዲዮችን የምንጭን ይሆናል፡፡ ሰብስክራይብ በማድረግ የኛ ቤተሰብ ይሁኑ!! This is the ministry of revenue medium tax payers’ number 2 branch office the official YouTube channel. In this channel we upload tax and revenue related videos. Subscribe and be our family!

👍 6
ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ ሕግ መሠረት በማንኛውም የታክስ ጊዜ ማቅረብ የሚገባውን የታክስ ማስታወቂያ ያላቀረበ እንደሆነ ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ የሚያገኘውን ማስረጃ መሠረት በማድረግ ለታክስ ጊዜው ታክስ ከፋዩ ሊከፍል የሚገባውን ታክስ በግምት (የግምት ስሌት" ተብሎ የሚጠራ) ማስላት የሚችል ሲሆን የግምት ስሌቱ የሚከተሉትን ይመለከታል፦ ሀ) በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ሠንጠረዥ "ለ" ወይም “ሐ” ኪሳራን በሚመለከት የታክስ ጊዜውን የኪሳራ መጠን፤ ለ) በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሠረት በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስን በሚመለከት ለታክስ ጊዜው በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለውን የታክስ መጠን፤ ሐ) በሌላ ማንኛውም ሁኔታ ዜሮ መጠንን ጨምሮ በታክስ ጊዜው ሊከፈል የሚገባውን የታክስ መጠን፡፡ ባለሥልጣኑ ታክሱ በግምት ለተሰላው ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ያካተተ የታክስ ግምት ስሌት ማስታ ወቂያ መስጠት አለበት፡- U) እንደሁኔታው የተሰላውን የታክስ መጠን፤ ወደፊት የሚሸጋገር የኪሣራ ወይም በብልጫ የተከፈለን የግብዓት ታክስ መጠን፣ ለ) በተሰላው ታክስ ላይ ሊከፈል የሚገባ የቅጣት መጠን ካለ፣ ሐ) በተሰላው የታክስ መጠን ላይ ሊከፈል የሚገባ የዘገየ ክፍያ ወለድ መጠን ካላ፤ መ) የታክስ ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ጊዜ ሠ) ማስታወቂያው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ፴ (በሰላሳ) ቀናት ውስጥ ታክሱ፣ ቅጣቱ እና ወለዱ የሚከፈልበትን ቀን፤ ረ) ቅሬታ ማቅረብ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ጨምሮ በታክስ ግምት ስሌቱ ላይ ቅሬታውን የሚያ ቀርብበትን አኳኋን፡፡ የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ታክሱን በሚጥለው የታክስ ሕግ መሠረት በተዘጋጀው የታክስ ግምት ስሌት ሊከፈል የሚገባው ታክስ የሚከፈልበትን ጊዜ ( "የመጀመሪያው የታክስ መክፈያ ጊዜ" ተብሎ የሚጠቀስ) ሊለውጥ የማይችል ሲሆን፣ የታክስ ክፍያው በመዘግየቱ ምክንያት የሚጣል ቅጣትና ወለድ መታሰብ የሚጀምሩት ከመጀመሪያው የመክፈያ ጊዜ አንስቶ ይሆናል፡፡ •ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው በታክስ ስሌት ለሚሰበሰብ ታክስ ብቻ ነው። •ይህ አንቀጽ በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት የደረሰው ማንኛውም ታክስ ከፋይ የግምት ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታውን አያስቀርም፡፡ •በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከደረሰው በኋላ ለዚያ የታክስ ጊዜ. ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የታክስ ማስታወቂያ ለታክስ ጊዜው እንደቀረበ በታክስ ከፋዩ የተዘጋጀ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ሆኖ አይቆጠርም፡፡ •ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ በግምት ላይ የተመሠረተ የታክስ ስሌት ሊያዘጋጅ ይችላል። •ባለሥልጣኑ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም የሚያግዙ መመሪያ ዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
Показати все...
👍 3🔥 2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.