uk
Feedback
አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

Відкрити в Telegram

በዚህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት እና የፕሮፋይል ፎቶ የሚሆኑ ምስለ ስዕል የሚገኝበት ቻናል ነው....................................................................

Показати більше
304
Підписники
+224 години
+77 днів
+6430 днів
Архів дописів
ተወለደ ጌታ ተወለደ የአእላፋት ዝማሬ መዝሙራት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ያሬድ ተወለደ ጌታ ተወለደ ተወለደ አምላክ ተወለደ አንዲት ብላቴና የአስራ አምስት ዓመት ልጅ ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ በህቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ አዝ = = = = = ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ አዝ = = = = = ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ ወለደችው ጌጠ የሔዋን አለኝታ አዝ= = = = = አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም በምድር ተፈልጎ እንዳንች አልተገኘም በሀሳብ በግብር ንፁህ ስለሆነች የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች አዝ = = = = = ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ ወለደቸው ድንግል የሔዋን አለኝታ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

አዲስ የልደት ዝማሬ "
የምስራች ተወለደ
" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ https://t.me/zemariabelmekbib

_በኤፍራታ ምድር .mp36.61 MB

##ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/ በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር ተክለሐይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አክባሪው አምላክ ስላከበረህ ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ ደጅ እንጠናለን በትህትና የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና ተክለሐይማኖት ጸሐይ ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን የቃሉን ወተት አጠጥተኽን ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ ተክለሐይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ በደብረ አስኮ ቆመህ በአንድ እግርህ የመተ ሎሚ መሻት ቀረና የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና ተክለሐይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ገብርኤል ኃያል" ገብርኤል ሀያል መላከ ሰላም መላከ ብስራት የምታወጣ የእግዚአብሔርን ህዝብ ከሚነድ እሳት ፍቅርህ ተስሉዋል በልባችን ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን የፅናታቸው ዝናው ሲሰማ ከዚያች ቢያብሎን ከሞት ከተማ ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው ቁመህ ተገኘህ መሀከላቸው አዝ ውሀው ሲዘልል ቢያስደነግጥም በጋኖቹም ውስጥ ቢነዋወጥም ፀንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ አንተ ስትደርስ ከዚያ ከሳቱ ~~አዝ ቂርቆስም ፀና ሞትን ሳይፈራ አንተ ስላለህ ከነርሱ ጋራ አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ አምነው ድል ነሱት ያንን መከራ አዝ እኔም አምናለው አድነኝ ብዬ ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ ክፉውን ዘመን የማልፍበት ፅናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

እመቤታችን_በቀኝ_ቆማለች_መዝሙረ_ዳዊት_በቴሌግራም.mp34.13 MB

🔴 አዲስ ዝማሬ " ናፍቆት " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ገጣሚ ሕሊና ደሳለኝ. ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ብርና ወርቅ ሳይዙ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ብርና ወርቅ ሳይዙ ዓለማትን ዞሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ቃሉን እየዘሩ ሙታን እያስነሡ ድውያን ፈወሱ ስሙን ብቻ ይዘው(፪)ታምነው በንጉሡ ከቀራጩ መደብ ከሐጥያት ገበታ ከጥብርያዶስ ባሕር ከጠራቸው ጌታ ስሙን ተሸክመው ቃሉን መሰከሩ በመንፈስቅዱስ ኃይል ድንቅን እየሠሩ የነገስታቱን ቃል ዛቻውን ሳይፈሩ የመንግስቱን ወንጌል ለዓለም አስተማሩ ይሻለናል አሉ ማድላት ለእግዚአብሔር ለሰው ከመታዘዝ ዘላለም ለማይኖር ቆዳቸው ተገፎ በሰይፍ ተሰየፉ ስለጌታ ፍቅር በመከራ አለፉ የድንጋዩን ናዳ የእሣቱን ነበልባል የጀርባን ግርፋት በእምነት ታግሰዋል ስደት ነው መከራ ረሀብ ነው ወይስ ጥም ከክርስቶስ ወንጌል ከእውነት የሚያስቆም በእርሱ ስላመኑ በጽድቅ ተጋደሉ ደግሞም በእርሱ በላይ እንዳለ በቃሉ በዙርያችን ከበው ካሉ እንደ ደመና እነርሱን እያሰብን በእምነት እንፅና በእውነት እንደኖሩ መሥለው ክርስቶስን እኛም በኑሮችን እንምሰል እነርሱን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

🛑 አዲስ ዝማሬ ዘማሪት ሲስተር ልድያ ታደሠ ቅድስት ሥላሴ Kidst Silasse ቅድስት ሥላሴ እንላለን ምሥጢሩን እናደንቃለን መጻህፍት እንደነገሩን ግብሩን እንመስላለን ❤

#ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ ልሳለማት ልሂድ እቤቷ ፍቅሯ ልዩነው ደግነቷ እናቴ አርሴማ ሰማእቷ    እግሩ ያነከሰ ክንዱ የዛለበት ደስታ የራቀው ሰው ህመም የጸናበት ልቡ የደከመ መንገድ የጠፋበት አፍሮ አይመለስም ደጅሽ የመጣለት ያንሁሉ ቁልቁለት ያንሁሉ ጋራ እንዴት ልጓዝ ብዬ ስፈራ ስፈራ ድረሽልኝ ብዬ ላንቺ ስናገር እንደእንቦሳ ጥጃ እዘለው ጀመር ላይድን መችይመጣል ላይለቀው ችግሩ አንቺስ መችልጠሪው ሲነሳ ከክብሩ አቤት ቃል-ኪዳንሽ እንዴት ይገለፃል አምኖ የመጣ ሰው ድኖ ተመልሶል የውስጥ ደዌውን ህመሙን ደብቆ ገስግሶ የመጣ ካለሽበት ዘልቆ ድኖ ተመለሰ ዝናሽን አሰማ ሰማቷ እናቴ እያለሽ አርሴማ አንደበትን ስጪኝ እመሰክራለው በሶስት ፍሬቆሎ ስታድኚ እያየው ነግሬሽ ነበረ ችግሬን በሙሉ አላሳፈርሽኝም ተፈታልኝ ሁሉም

🔴 አዲስ ዝማሬ " አኑርልኝ ለአፌ ጠባቂ " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤት በምድር" ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር (2) ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር (2) አዝ -- ትጸንሲ ሲልሽ በከበረ ዜማ ይሁንልኝ አልሽው ትውልደ እንዲጽናና ከገብርኤል ሰምተው መላዕክቱ ሁሉ ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን የራማውን ልዑል አብነት አድርገን ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር (2) ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር (2) ስርሽ በምድር ነው ማዕረግሽ በሰማይ ንፁ መሰቦ ወርቅ የተሞላሽ ሲሳይ የማይፀንሽ ፍሬን በላነው ጠጣነው በኤፍራታ ሰምተን በዱር አግኝተነው ይተሰወረውን መና በልተነዋል ከተመረጡት ጋር ብፅዕት ብለናል ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር (2) ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር (2) ከተፈጥሮ በላይ ፅንስን ያዘለለ የእሳት ምሶሶ ባንቺ ተተከለ የእግዚአብሔር ሀገሩ የእንጀራ ቤታችን ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር (2) ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር (2) ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት ሰውና መላዕክት አብረው አከበሩት የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፈረሰ በዳግሚት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ እጅ እንነሳለን ሆነን በትህትና ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነውና ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር (2) ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር (2) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ሀገረ እግዚአብሔር" ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ

“ እመቤቴ የአምላክ እናት" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እመቤቴ የአምላክ እናት ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት ለልጅሽም ክብር ውዳሴ ታቀርባለች ዘወትር ነፍሴ (2) ልቤ ተነሳሳ ተቀኘ ለክብርሽ በፍጹም ትህትና ሊያመሰግንሽ ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን የታጠረች ተክል እመ ብርሃን። ……አዝ…. የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት የሰማይ የምድር ንግሥት ናትና ክብር ይገባታል ዘወትር ጠዋት ማታ። ….አዝ…. አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት በምልጃሽ አስቢኝ ኋላ ስራቆት ያንን የእሳት ባሕር አሻግርኝ ድንግል ሆይ እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ። ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

*አዲስ ዝማሬ* ያለፈው ዘመኔ ይብቃ" ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ ዝማሬው ለሌሎች ተደራሽ እዲሆን ላይክ ሼር  ማድረግ አይርሱ @Abel_mekebeb

የፀሀይ መውጫ ምስራቅ ነሽ ሊቀመዘምር ቴዎድሮስ ዮሴፍ የፀሀይ መውጫ ምስራቅ ነሽ/2/ ድንግል የእኛ እናት በብርሃን የተከበብሽ ማርያም የእኛ እናት በብርሃን የተከበብሽ አዝ ታምረኛ ነው ክርስቶስ ሁሉን በጥበብ ያረገው ብርሀን ተክሎ በላይሽ በማህፀንሽ ያደረው አይመረመር ጥበቡ እፁብ እፁብ ብለናል ያስደነቀንን አምላክ በዝማሬ ከበናል አዝ ጨለማው ተሰዶ ሄደ ፀሃይ ከሆድሽ ሲወጣ አለፈ የጭንቁ ዘመን ምድር በብርሃን ተውጣ ከድቅድቁ ወተናል በወለድሽልን ፀሃይ አያልፍም ብርሃኑ ኤልሻዳይ ነው አዶናይ አዝ አንቺ የምስራቅ ደጃፍ ሕዝቅኤል በረዕይ ያየሽ የመዳናችን ምዕራፍ የፅድቃችን ምክንያት ነሽ ህይወት ፈሰሰ መቅደስሽ እየቀዳን ጠጣነው ልጅሽ ሲዳስሰን ነው በልምላሜ ያደግነው አዝ የማይጠፋ ፋኖስ ነው በመቅረዛችን ያበራ ከአንቺ የተወለደው በጎቹን በፅድቅ የመራ የአንፀባራቂው አለት አምዱ ተተክሎልናል የሌሊቱንም ግርማ ያለፍርሃት አልፈናል አዝ አንቺ የምስራቅ ደጃፍ ሕዝቅኤል በራዕይ ያየሽ የመዳናችን ምዕራፍ የፅድቃችን ምክንያት ነሽ ህይወት ፈሰሰ መቅደስሽ እየቀዳን ጠጣነው ልጅሽ ሲዳስሰን ነው በልምላሜ ያደግነው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

🛑 ዘማሪ አቤል መክብብ "#ምን_ሊለውጠው_ያንተን_ውለታ" ምን ሊለውጠው ያንተን ውለታ ምን ሊቀይረው ያንተን ስጦታ ለዘላለም ታትሞ የሚኖር ማን ይስተካከላል ጌታ ያንተን ፍቅር ጎብጬ ስኖር በሀዘን እዘራው ነበር እንባዬን እሩሩህ አምላኬ ደረስክ እና ሰው አደረከኝ እንደገና /፪/ ሲሸሸኝ ሁሉም ሲርቀኝ ሳትፀየፈኝ ቀረብከኝ ዘይት ያፈሰስክ በቁስሌ ላይ ወዳጅስ ማነው ካንተ በላይ /፪/ አዳም ወዴትነክ እያልከኝ በፍቅር ድምፅህ ፈለከኝ አልብሰኸኛል ነጩን ልብስ እወድሀለው ኢየሱስ አከብርሀለው ክርስቶስ አልመለስም ወደኀላ አያይም አይኔ ካንተ ሌላ አልፈራም የጠላትን ዛቻ አድነህኛል አንተ ብቻ ሞተክኽልኛል አንተ ብቻ

❤️ስለወደደኝ❤️ ስለወደደኝ አዳነኝ በቸርነቱ ፈወሰኝ አቆመኝ ስለ ክብሩ ከሞት ነጥቆኛል ፍቅሩ 🌺 #አዝ... 🌺 ዘርግቶልኛል እጁን ለህማም አፍቅሮኛል እስከ ዘለዓለም ስታወክም ነው ጸጥታዬ የወደደኝ ቸሩ ጌታዬ 🌺 #አዝ... 🌺 በሞት ጫንቃ ላይ ተረማመድኩኝ ሰንሰለቴ ተፈቶ ዳንኩኝ በዝማሬ አፌ ሰልጥኖ አርፏል ልቤ በእርሱ ተማምኖ 🌺 #አዝ... 🌺 ወርዶ ሳምራዊው ከአህያው ላይ ዘይትን ቀባኝ በቁስሎቼ ላይ ደግፎኛል በንጹህ ፍቅር ከፍሎልኛል ሁለቱን ዲናር 👉በዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻዲቅ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲዳረስ

+7
eyrusalem_tube_አዲስ_የልደት_መዝሙር_እንደ.mp39.09 MB