uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

Відкрити в Telegram

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህጋዊ የይዞታ ካዳስተር (ድጅታል ካርታ)

Показати більше
3 051
Підписники
-124 години
+57 днів
+1230 днів
Архів дописів
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትከከተማዋ አስፈጻሚ አካላት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ። ​ምክር ቤት ጽ/ቤት — የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፥ ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው አስፈጻሚ አካላት ጋ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትከከተማዋ አስፈጻሚ አካላት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ። ​ምክር ቤት ጽ/ቤት — የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፥ ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው አስፈጻሚ አካላት ጋር የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች ስምምነት ተፈራረመ። "የጋራ ግብ፤ የተቀናጀ ተግባር፤ የላቀ ውጤት" ለማምጣት ባለመው በዚህ የየግብ ስምምነት መፈራረሚያ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋዒዛ መሐመድ እንደገለጹት፤ የስምምነቱ ዋና ዓላማ ለከተማችንና ለህዝባችን የተደመረ አቅም በመፍጠር፣ ተቀናጅቶና በአንድነት ለመሥራት የሚያስችል የጋራ ግብና አቋም ለመያዝ እንደሆነ ተናግረዋል። ​ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አክለውም፥ "በ4ኛው ዙር ምክር ቤታችን የሥራ ዘመን ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለመፈጸምና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ካለፈው የሥራ ዘመን የወሰድናቸውን መልካም ልምዶች በማጎልበትና በማሣደግ ከሕዝባችንና ከአስፈጻሚ አካላት ጋር የጋራ ግብ ይዘን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል። ይህም የከተማችንን ራዕይ እውን ለማድረግና የሕዝቡን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል። ​በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያም የምክር ቤቱ ሁሉም ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርጉባቸው አስፈጻሚ ተቋማት ጋር በበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል።

በሩብ ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ ከአገልሎት አንፃር የመጡ ለውጦችን አመላካች መሆኑ ተጠቆመ ---------------------------------------- ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም (የመ/ይ/መ/ነ/ን/ም/መ/ኤ) AA-LHPRIA አዲስ አበባ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እንዲሁም በባለፈው በጀት አመት ከአገልግሎት የተሰበሰበው ገቢ በመሠረታዊነት በአገልግሎት ላይ ያለውን ለውጥ እና መሻሻል አመላካች መሆኑን የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ም/ል ዋና ዳይሬክተር እና የካዳስተር ምዝገባ፣ መረጃና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር አሳሳኸኝ ተስፋዬ ገለጹ፡፡ የደንበኛን እርካታ ለመጨመር እንዲሁም አገልግሎትን ለማሻሻል በተደረገው ከፍተኛ ጥረትና ተግባር በባለፈው በጀት ዓመት በአገልግሎትም በገቢም ከእቅድ በላይ መሳካቱን የተናገሩት ኢንጂነር አሳሳኸኝ ተስፋዬ በዋናነት ትኩረታችን አገልግሎትን ማሻሻል በመሆኑ የነበሩ የአገልግሎት ችግሮችን በተለይም ከኪራይ ሰብሳቢነት እና ከቢሮክራሲ ጋር የነበሩ ክፍተቶችን ለማሰተካከል ጥረት አድርገናል ብለዋል፡፡ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የይዞታ ምዝገባ አገልግሎት ብቻ ከ22ሺ በላይ መደረጉን የገለፁት ኢንጂነር አሳሳኸኝ አዲስ የታወጀ ቀጠና ባይኖርም 97ሺ የሚደርሱ ከክርክር መዝገብ የወጡ ፋይሎችን በማጥራት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከታቀደው 5.1 ቢሊየን ብር በላይ 5.4 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉ እና የተገልጋይ እርካታም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መምጣቱ ተጠቅሷል፡፡ የካዳስተር ምዝገባና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ሞሳ በበኩላቸው አገልግሎት ላይ የተደረገው ክትትል እና ድጋፍ፣ ከአሰራር ጋር ያሉ ማሻሻያዎች፣ ቅዳሜ በሁሉም ጽ/ቤት አገልግሎት መሰጠቱ፣ ምሳ ሰአት ላይም አገልግሎት መኖሩ ተገልጋዩ ቶሎ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አገልግሎቶች በስታንዳርድ እንዲመዘገብ፣ በስታንዳርድ ንፅፅር እንዲሰራ፣ ስታንዳርድ ኦዲት እንዲደረግ፤ በመደረጉ የመጣ ለውጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ሩብ አመት በእቅድ የተያዙ ጉዳዮችን የገለጹት አቶ ሀሰን ሁሉንም የጋራ ህንፃ፣ አፓርትመንት፣ ማህደሮችን ጨምሮ የይዞታ ፓርስሎችን አገለግሎቱን ከማንዋል ወደ ዲጂታል በማድረግ እና ወደ አገልግሎት በማስገባት የሰዎች ምልልስ መቀነስ እንደሆነና በኢላንድ አገልግት በመስጠትም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማስተካከል መረጃ ለመቀባበል የሚፈጀውን ጊዜ በማሳጠር አገልግሎት በሲስተም ማሳለጥ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ ከአገልሎት አንፃር የመጡ ለውጦችን አመላካች መሆኑ ተጠቆመ ---------------------------------------- በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እንዲሁም በባለፈው በጀት አመት ከአገልግሎት የተሰበሰበው ገቢ በመሠረታዊነት በአገልግሎት ላይ ያለውን ለውጥ እና መሻሻል አመላካች መሆኑን የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ም/ል ዋና ዳይሬክተር እና የካዳስተር ምዝገባ፣ መረጃና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር አሳሳኸኝ ተስፋዬ ገለጹ፡፡ የደንበኛን እርካታ ለመጨመር እንዲሁም አገልግሎትን ለማሻሻል በተደረገው ከፍተኛ ጥረትና ተግባር በባለፈው በጀት ዓመት በአገልግሎትም በገቢም ከእቅድ በላይ መሳካቱን የተናገሩት ኢንጂነር አሳሳኸኝ ተስፋዬ በዋናነት ትኩረታችን አገልግሎትን ማሻሻል በመሆኑ የነበሩ የአገልግሎት ችግሮችን በተለይም ከኪራይ ሰብሳቢነት እና ከቢሮክራሲ ጋር የነበሩ ክፍተቶችን ለማሰተካከል ጥረት አድርገናል ብለዋል፡፡ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የይዞታ ምዝገባ አገልግሎት ብቻ ከ22ሺ በላይ መደረጉን የገለፁት ኢንጂነር አሳሳኸኝ አዲስ የታወጀ ቀጠና ባይኖርም 97ሺ የሚደርሱ ከክርክር መዝገብ የወጡ ፋይሎችን በማጥራት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከታቀደው 5.1 ቢሊየን ብር በላይ 5.4 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉ እና የተገልጋይ እርካታም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መምጣቱ ተጠቅሷል፡፡ የካዳስተር ምዝገባና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ሞሳ በበኩላቸው አገልግሎት ላይ የተደረገው ክትትል እና ድጋፍ፣ ከአሰራር ጋር ያሉ ማሻሻያዎች፣ ቅዳሜ በሁሉም ጽ/ቤት አገልግሎት መሰጠቱ፣ ምሳ ሰአት ላይም አገልግሎት መኖሩ ተገልጋዩ ቶሎ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አገልግሎቶች በስታንዳርድ እንዲመዘገብ፣ በስታንዳርድ ንፅፅር እንዲሰራ፣ ስታንዳርድ ኦዲት እንዲደረግ፤ በመደረጉ የመጣ ለውጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ሩብ አመት በእቅድ የተያዙ ጉዳዮችን የገለጹት አቶ ሀሰን ሁሉንም የጋራ ህንፃ፣ አፓርትመንት፣ ማህደሮችን ጨምሮ የይዞታ ፓርስሎችን አገለግሎቱን ከማንዋል ወደ ዲጂታል በማድረግ እና ወደ አገልግሎት በማስገባት የሰዎች ምልልስ መቀነስ እንደሆነና በኢላንድ አገልግት በመስጠትም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማስተካከል መረጃ ለመቀባበል የሚፈጀውን ጊዜ በማሳጠር አገልግሎት በሲስተም ማሳለጥ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ ---------------------------------------------- ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (የመ/ይ/መ/ነ/ም/መ/ኤ) AA-LHPRIA አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ሠራተኞች በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የሩብ ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ወ/ሮ ቅድስት መከተ እንደገለጹት፤ ኤጀንሲው በሩብ ዓመቱ በተቋም ግንባታ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ፣ በመረጃ መረብና በካዳስተር ምዝገባ እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ አበይት ተግባራትን አከናውኗል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ተገልጋዮች በስታንዳርዱ መሠረት የመረጃ መረብ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 118 በመቶ መከናወኑና ከተቋሙ ከሚሰጡ አገልግሎቶች ከ5.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቅሷል። በተጨማሪም 84 ሺህ 673 የይዞታ ማኅደራትን ዲጂታይዝ በማድረግ የ114.8 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡ ተገልጷል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መነሻነት በሠራተኞች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፤ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አራርሳ ድሪባ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው፤ በተለይም በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚታዩ የቢሮ ጥበት፣ የግብዓትና የመሣሪያ እጥረት ለማሟላት እንዲሁም የአሠራር ጥራት ኦዲትን በማጠናከር የተጠያቂነት ሥርዓትን ለማስፈን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካት የጋራ ጥረትና የመደመር አስተሳሰብ ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ -------------------------------------------- ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHPRIA አዲስ አበባ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ወርቃማ ሰኞ መርሃ-ግብር ላይ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አራርሳ ድሪባ ተነሳሽነት፣ አስተሳሰብ እና መደመር ለተቋሙ ስኬትና ለአገልግሎት አሰጣጥ እድገት ያላቸውን የጎላ ሚና አስመልክተው ለሰራተኞች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ አራርሳ በማብራሪያቸው እንዳመለከቱት፣ ተነሳሽነት እያንዳንዱ የመንግሥት ሠራተኛ የተጣለበትን የሕዝብ አደራ በአስፈላጊው ፍጥነት፣ ጥራትና ትጋት ለመወጣት የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል።  የተቋማዊ እድገት ዋና እና ቁልፍ አዎንታዊና በጎ አስተሳሰብ መሆኑን ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በተለይም ግልጽነት፣ ታማኝነትና ቅንነት ያለው አገልግሎት መስጠት የህዝብን እምነት ለመገንባትና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም የመደመር ጽንሰ-ሀሳብን ከአገልግሎቱ ጋር በማያያዝ ሲያብራሩ፤ ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካት የጋራ ጥረትና የተቀናጀ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የኤጀንሲው አመራሮችና ሠራተኞች እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውንና ጉልበታቸውን በማስተባበር ሲሰሩ የመሬት ይዞታና ንብረት መረጃ ምዝገባ ስርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚቻል አስረድተዋል።

City transformation as a driving force of African Progress: The Experience from Addis Ababa Addis Ababa hosted the 2026 Afric
+9
City transformation as a driving force of African Progress: The Experience from Addis Ababa Addis Ababa hosted the 2026 African Mayoral Leadership Initiative (AMALI) Reunion this week. The city has shared its experiences in various developmental interventions. The city has demonstrated its undivided attention for Early Childhood Development (ECD) for the mayors and governors during the field visits. As Mayor Adanech Abiebie underscored during the opening of the reunion, Addis Ababa has integrated the thought of Medemer Government in its human-centered developmental interventions. As a result, the city has achieved direct and equitable benefit of its residents through which changes in the everyday life of the people is https://www.facebook.com/share/p/1Bz9L5ziJu/

"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ ኔቫዳ በይፋ ተከፍቷል! አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬ
+5
"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ ኔቫዳ በይፋ ተከፍቷል! አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል:: ይህ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ፣ በአለም ቀዳሚ ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ኤክስፖ አንዱ ሲሆን፣ ከ150 በላይ የአለም ሀገራት የተውጣጡ ከ3,700 በላይ ተሳታፊ ድርጅቶችን ተገኝተዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ታላቅ የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ ላይ በመተሳተፍ የከተማዋን የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የቱሪዝም ሀብቶችን ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል:: አዲስ አበባ ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍረንሶችን በማስተናገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷ መሆኗን ተከትሎ፣ እንዲህ አይነቱ የቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ ይበልጥ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ ካሉት ተዋናዮች ትስስር ለመፍጠር ያግዛል::

As Africa, Ethiopia makes us proud. Addis Ababa is a city transforming it's self. we have seen the capacity of Mayor Adanech Abiebie's transformative leadership. :-Mamphela Ramphele; Advisor of AMALI project

የኤጀንሲው የሩብ ዓመት ግምገማና አዲስ የ90 ቀናት የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ ሆኑ --------------------------------------------             ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም (የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHPRIA አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የማዕከልና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮች እንዲሁም ዳይሬክተሮች የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ90 ቀናት ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ። በመድረኩ ላይ የእቅድ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት ወ/ሮ ቅድስት መከተ የቀረበው ሪፖርት ኤጀንሲው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት ረገድ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገቡን አመልክቷል። ከዲጂታላይዜሽን አሠራር አንጻር 73,749 የይዞታ ማህደራትን ዲጂታይዝ ለማድረግ ታቅዶ 84,673 ማህደራትን ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም የመረጃ መረብ አገልግሎትን በማሳለጥ ለ58,608 ተገልጋዮች አገልግሎት በመስጠት የ118% አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን፣ ከተያዘው 5.12 ቢሊዮን ብር በላይ 5.24 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል። ይህም አፈጻጸም ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገቢ በ70% እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ በ50.03% ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ኤጀንሲው ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ሰፊ ሰው ተኮር ተግባራትን ማከናወኑም ተገልጿል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ደረጃ የሚታዩ የቴክኒክ፣ የግብዓት እና የተሽከርካሪ እጥረት ችግሮችን በማንሳት ማነቆዎች የሚፈቱበትን አግባብ በተመለከተ አስተያየቶች ሰጥተዋል። የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ኤጀንሲው ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 30 የሚተገበሩ 8 ዋና ዋና ግቦችን ያካተተ የ90 ቀናት የተግባር ዕቅድ ይፋ አድርጓል። እነዚህም ግቦች በ82 ቀጠናዎች የሚገኙ 66,218 ይዞታዎችን የማረጋገጥ ሥራ ማከናወን፣ 5.12 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ፣ ውዝፍ ቀሪ የሆኑ 71,462 የጋራ ሕንፃ ማህደራትን ጨምሮ በአጠቃላይ 267,951 ማህደራትን ዲጂታይዝ በማድረግ ለኦንላይን (e-land) አገልግሎት ዝግጁ ማድረግ፣ የዲጂታል አድራሻ (Digital Addressing) ሥርዓት የመስክ መረጃ ማጥራት ሥራዎችን ማጠናቀቅ እና የመሬትና መሬት ነክ ረቂቅ ደንቦችን አዘጋጅቶ ማጽደቅን ያካተቱ ስለመሆናቸው ተጠቅሷል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የታቀዱ ሥራዎችን ስኬታማ ለማድረግ አመራሩና ባለሙያው በከፍተኛ የኃላፊነትና የ"ጊዜ የለኝም" ስሜት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተጨማሪም አገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከሌብነትና ብልሹ አሠራር የጸዳ አሠራር በመገንባት የተገልጋዩን ማኅበረሰብ እርካታና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችንና ባለድርሻ አካላትን በመስክ ሥራዎቻችን በማስጎብኘት፣ የከተማችንን የለውጥ ተሞክሮ አካፍለናል። We shared Addis Ababa’s transformation journey
+9
የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችንና ባለድርሻ አካላትን በመስክ ሥራዎቻችን በማስጎብኘት፣ የከተማችንን የለውጥ ተሞክሮ አካፍለናል። We shared Addis Ababa’s transformation journey with mayors from across Africa and other stakeholders through field visits showcasing our development initiatives. ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ስለ አድራሻ ሥርዓት ምን ያህል ያውቃሉ? *** እንደ አዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትልቅና ሰፋፊ ከተሞች ሰው ቀጥረው አልያም ከውጭም ይሁን ከአንዱ የሀገራችን ክልል ወደ ከተማችን ብቅ ብለው አንድን ስፍራ ወይንም ቤት ትክት እስኪልዎ ፈልገው ያውቃሉ?   በአዲስ አበባ ከተማ አሁን ባለው ፈጣን የመሰረተ ልማት እና እየታየ ባለው የዘመናዊ ከተማ ጉዞ ዲጂታል አድራሻ ሥርዓት መዘርጋት ለስማርት ከተማ መሰረታዊ እሳቤ ነው።      በከተማችን ዘመናዊና ተደራሽ የአድራሻ ስርዓት በመዘርጋት እንግዶችን እና ባለሀብቶችን መሳብ ይቻላል፡፡ የአድራሻ ሥርዓት በተለይ ለከተሞች እድገት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍተኛ አስዋፅኦ ይኖረዋል። በመሆኑም ዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ስማርት ከተሞችን ለመመስረት ወሳኝ ሚና አለው፡፡ የከተማ አካባቢዎች ይበልጥ የተሳሰሩ እና በቴክኖሎጂ የሚመሩ እንዲሆኑ በማስቻል የዜጎችን አጠቃላይ የህይወት ጥራትም ያሻሽላል።   የአድራሻ ሥርዓት ምንድን ነው? የአድራሻ ሥርዓት፡- ማለት በመንገድ ሥያሜና በቁጥር አሰጣጥ ሥርዓት አማካይነት የአንድን ቁራሽ መሬት ወይም ቤት አድራሻ ለማመላከት የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡ ይህ ጽንሰ-ሃሳብ በመሬት ላይ የአንድ ቁራሽ መሬትም ሆነ ቋሚ ንብረት የሚገኝበትን አድራሻ ለመለየት ማለትም መንገዶችና፣ ቁራሽ መሬቶች/ቤቶች የጂኦ ኮዲንግን አሠራርን መሰረት በማድረግ ኮድ/ቁጥር በመስጠት የካርታ እና የምልክት ሥርዓት በመጠቀም ግልጽና ለተደራሽነት የሚያገለግል ኮድ የመስጠት ሥርዓትን ይመለከታል፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አስፈሊጊነቱም የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት፣ የቋሚ ንብረት ባለቤቶችና የተጠቃሚዎች መረጃ ለማዘመን ነው፡፡ ዓላማው፡- ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ለተጠቃሚው ምቹ የሆኑ የአድራሻ ሥርዓት በመጠቀም የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን፣ መኖሪያ አድራሻን ለመለየት እና በእንቅስቃሴ ህብረተሰቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ እንዲሁም አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት ለተቋማትና ለዜጎች ለማቅረብ ማስቻል ነው፡፡   የአድራሻ ሥርዓት ጠቀሜታዎች  👉 በዋናነት የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ቁጥር ከቁራሽ መሬቱ ልዩ መለያ ኮድ ጋር በማስተሳሰር የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረቱን አድራሻ ለመለየት ወይም ለማመልከት ያግዛል፡፡ 👉 የከተማ አስተዳደሮች ያላቸውን መሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ሃብትና ዋጋውን መዝግቦ መያዝና ወቅታዊ ጥገና ለማድረግ የአድራሻ ሥርዓት እገዛ ያደርጋል፡፡ 👉 የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሥራን በዕቅድ ለመተግበር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ አገራዊና አካባቢያዊ ምርጫዎችን ለማካሄድ ያግዛል፡፡ 👉 የመንገድ ሥርዓቱን በማሻሻል ህብረተሰቡ በከተማው ውስጥ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ አንድን ቦታ በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል፡፡ 👉 የከተማ ውስጥ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ለማግኘት ያስችላል፡፡ 👉 የመሰረተ ልማት አውታሮችን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበርና በማስተዳደር የአድራሻ ሥርዓት የውሃ፣ የመብራት እና የቴሌኮም አቅራቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጥገና እና ክፍያ ማሰባሰብን ለማቀላጠፍ ያስችላል፡፡ ¨ አጣዳፊ የጤና፤የእሳት አደጋና የፖሊስ አገልግሎቶችን አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ይረዳል፡፡  ወዘተ... ዲጂታል አድራሻ ሥርዓት የፊዚካል አድራሻ ማለትም የአድራሻ መሰረተ ልማት ሳይን ፖስት እና የአድራሻ ጠቋሚ ምልክቶችንና ዲጂታል ካርታዎችን (Base Map) በማቀናጀት የአንድን ቦታ የመገኛ አቅጣጫ በሕንፃዎች በመንገዶች ላይ ልዩ የሆነ ኮድ በመሰየም በእጅ ስልኮችና በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ የፊዚካል አድራሻ እና የዲጂታል ካርታን በማስተሳሰር ለዲጅታል ኢኮኖሚ፣ ኦንላይን የንግድ ልውውጥ፣ ቤት ለቤት ፖስታን ለማደል እንዲሁም ለትራፊክ ፍሰት መሳለጥ፣ ለቱሪስት መዳራሻን ለመጠቆም የጀርባ አጥንት በመሆን ስማርት ከተማን በመገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡  የቤት ቁጥር መረጃ የቤት ቁጥር መስጠት የአድራሻው አንድ አካል ሲሆን በከተማ ውስጥ ወጥ የሆነና የማይደጋገም ቁጥር በመስጠት አገልግሎት ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡ ህብረተሰቡ ግንዛቤ ሊይዝባቸው የሚገቡ ጉዳዮች:-   ➻ ዲጂታል አድራሻ ሥርዓት የዜጎችን ተሳትፎ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም (ለምሳሌ ጉድጓዶች፣ የተሰበሩ የመንገድ መብራቶች)፣ ስጋቶች በፍጥነት እንዲፈቱ ማድረግ የሚያግዝ በመሆኑ ጠቀሜታውን መረዳት ይጠበቃል። ➻ አዲስ ቤት ቁጥር የመስጠት አገልግሎት ይኖራል፡፡ ➻ የቤት ቁጥር የመስጠት ተግባር የሚከናወነው ህጋዊ ይዞታ ላላቸው የቤት ባለቤቶች ሲሆን በቅድሚያ ከግለሰብ ሊረጋገጡ የሚገባቸው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶች ቤት ቁጥር ለሚለጥፉ አካላት ማሳየት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቤት ቁጥር በራሱ የህጋዊነት ማረጋገጫ አለመሆኑን ህብረተሰቡ በግልፅ እንዲያውቀው ያስፈልጋል፡፡ ➻ የአድራሻ ሥርዓት ዝርጋታ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶችን እንዲሁም ቋሚ ምሰሶዎች በይዞታቸው አካባቢ ለሚተከለው ቀና ትብብር ማድረግ ይገባል፡፡ ➻ በመሰረተ ልማቶች ላይ ለሚንጠለጠሉ እና ለሚለጠፉ የአድራሻ ሰሌዳዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡   ከህብረተሰቡ ምን ይጠበቃል? ➻ የአድራሻ ሥርዓት ቤት ለቤት በመዘዋወር የሚሰራ በመሆኑ ስራውን ለሚሰሩ አካላት ነዋሪዎች የሚጠየቁትን መረጃዎች አሟልተው በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ➻ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓቱን በስልክዎ ተጠቃሚ በመሆን እና ሌሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስተዋወቅ! ➻ የአድራሻ ሥርዓት መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ የሀገር እና የህዝብ ሀብት ወጥቶባቸው የሚተከሉ፣ የሚለጠፉ፣ እና የሚንጠለጠሉ እንደመሆናቸው በመኪና ሲገጩ ወይም ሲቆረጡ አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡ የህግ አካላት እና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ ለፖሊስ ጽ/ቤት፣ ለደንብ ማስከበር መጠቆም ይቻላል፡፡