cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኩሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድህነነ እምዕለት እኪት ወባልሀነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ፀሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማእታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Більше
Рекламні дописи
1 171
Підписники
+524 години
+267 днів
+10130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ለአስራ ኹለተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድልን እንመኝላችዃለን፤ እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይኹን! ✝️+✝️ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ? (ምን ብለን እንጸልይ?) ✝️+✝️ ➞ ክፍል አንድ ክፍል ሁለት
Показати все...
ተዋሕዶን እንወቅ።

✝️+✝️ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ? (ምን ብለን እንጸልይ?) ✝️+✝️ #ክፍል_አንድ ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ። አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ። ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር። ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት (church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል። የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል። (ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ተጠቃሽ ናቸው።) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር። የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር። በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር። ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም። ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር። አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር። ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር። የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር። እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ…

👍 3🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Rate my work👆 ስንት ይገባዋል? ለማዘዝ ከፈለጉ➡️ @elbetma +25102374713
Показати все...
🆒 6🙏 5👌 1💔 1
እግዚአብሔርን ማወቅ' ግን በተግባር የሚገለጥና ከፈጣሪ ጋር የምናደርገው የአንድነት ሕይወት ነው። እኛ በእርሱ፣ እርሱም በእኛ የሚኖርበት ልዩ ምሥጢራዊ ውሕደት ነው። "እግዚአብሔርን ማወቅ" ማለት ስለ እርሱ ሲነገር በጆሮ የሰሙለትን አምላክ ከብቃት ደርሶ ማየትና በፍጹም ልብ መውደድ ነው። ይህ ደግሞ ራሱ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረው የዘላለም ሕይወት ነው። (ዮሐ 17:3) ይህን ሕይወት ቀምሶ ያጣጣመው ቅዱስ ዳዊት "ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው'' እያለ በሐሴት የከንፈሩን መሥዋዕት ለአምላኩ ያቀርባል።(መዝ 16፥8) በሌላ ጊዜ ደግሞ ይኸው መዝሙረኛ አይቶት እንደማያውቅ ነገር "ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?'' እያለ በናፍቆት ይዘምራል።(መዝ 42፥1-2) ምን ማለቱ ይሆን
Показати все...
🙏 3
ደና አደራቹ በአሪፍ ቁርስ እንጀምር ቀናችንን እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍስ ቅዱስ ባስልዮስ "ሰውነታችን ያለ እስትንፋስ መኖር እንደማይችል፣ ነፍሳችንም ፈጣሪዋን ሳታውቅ ሕያው ሆና ልትኖር አትችልም። የነፍስ ሞቷ እግዚአብሔርን አለማወቋ ነውና'' ይለናል፣ እውነት ነው፤ እግዚአብሔር ሕያው ነፍስ ላለው የሰው ልጅ ሁሉ የሰጠው ትልቁ ጸጋ "እርሱን ማወቅ'' ነው። ነፍስም ያለዚህ መኖር እንደማትችል ታውቃለችና ዘወትር ይህን ስትጠማ ትኖራለች። እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ስለ እርሱ የተጻፉ መጻሕፍትንና የተነገሩ ትምህርቶችን ማንበብ፣ መስማት ብቻ አይደለም። እነዚህ ብቻቸውን "ስለ እግዚአብሔር እንድናውቅ'' እንጂ "እግዚአብሔርን እንድናውቀው'' አያደርጉንም። ''ስለ እግዚአብሔር ማወቅ" የመጨረሻው ዓላማችን ወደ ሆነው "እግዚአብሔርን የማወቅ ሕይወት" የምንገሰግስበት መንገድ እንጂ ራሱን ችሎ መዳረሻና ማረፊያ ወደብ አይደለም
Показати все...
🥰 3
እግዚአብሔርን ማወቅ' ግን በተግባር የሚገለጥና ከፈጣሪ ጋር የምናደርገው የአንድነት ሕይወት ነው። እኛ በእርሱ፣ እርሱም በእኛ የሚኖርበት ልዩ ምሥጢራዊ ውሕደት ነው። "እግዚአብሔርን ማወቅ" ማለት ስለ እርሱ ሲነገር በጆሮ የሰሙለትን አምላክ ከብቃት ደርሶ ማየትና በፍጹም ልብ መውደድ ነው። ይህ ደግሞ ራሱ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረው የዘላለም ሕይወት ነው። (ዮሐ 17:3) ይህን ሕይወት ቀምሶ ያጣጣመው ቅዱስ ዳዊት "ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው'' እያለ በሐሴት የከንፈሩን መሥዋዕት ለአምላኩ ያቀርባል።(መዝ 16፥8) በሌላ ጊዜ ደግሞ ይኸው መዝሙረኛ አይቶት እንደማያውቅ ነገር "ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?'' እያለ በናፍቆት ይዘምራል።(መዝ 42፥1-2) ምን ማለቱ ይሆን
Показати все...
#አዋልድ_መጻሕፍት ✝ ✝ አዋልድ መጻሕፍት መሰረታቸውና አባታቸው መጽሐፍቅዱስ በመሆኑ ባህርያቸውም በአብዛኛው የሚወርሱት ከመጽሐፍቅዱስ ነው። አዋልድ የተባሉ መጻሕፍት በዓይነት በዓይነታቸው ተመድበው ሲቆጠሩ ድርሳን፥ ተዓምር፥ ገድል፥ መጽሐፈ ታሪክ ይባላሉ። ሆኖም ዋና ዋናዎቹን ለምሳሌ ያህል እንደሚከተለው እንጠቅሳለን። ወንጌልን የሚመስለው ተአምረ ኢየሱስ፥ ግብረ ሐዋርያትን የሚመስለው ተአምረ ማርያም፥ ራእየ ዮሐንስን የሚመስለው ራእየ ማርያም፤ ኦሪት ዘዳግምን የሚመስለው ዜና አይሁድን፤ መዝሙረ ዳዊትን የሚመስለው መጽሐፈ ቅዳሴ፥ ድርሳነ ማኅየዊ፥ ድርሳነ ሚካኤል፥ መጽሐፈ መነኮሳት፥ ገድለ ጊዮርጊስ፥ ገድለ ተክለሃይማኖት፥ የሰሎሞንን ጥበብ የሚመስለው የሰማየ ሰማያትን፥... ወ.ዘ.ተ ጥንታዊት የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሰማንያ አሐዱ ቅዱሳት መጻሕፍት መሰረተ ሐሳብ የወጡ አዋልድ መጻሕፍት የሏትም፥ ወደፊትም አይኖራትም። ሁሉም አዋልድ መጻሕፍቶቿ ከመጽሐፍቅዱስ ሃሳብ ጋር አንድ የሆኑ፥ ከመጽሐፍቅዱስ የተወለዱ መጻሕፍት ናቸው።  ✝ የአዋልድ መጻሕፍት ጥቅም ✝ ✝ አዋልድ መጻሕፍት ለሰው ለጆች የዕለት ተዕለት ኑሮና ሥነ-ምግባር እንዲሁም መሠረተ ሃይማኖት እጅግ ከፍተኛ ጥቅም አላቸው። እነዚህም መጻሕፍት፦ ከቅዱሳት መጻሕፍት ንባቡ ያጠረውን አስረዝመው፥ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ኃይለ ቃል በንባብ ተቃጥቶ ሳይሟላ የቀረውን አሟልተው፥ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰለውን ምሳሌ ተርጉመው፥ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሰውን ጥቅስ በበለጠ አብራርተው፥ ብሉያትንና ሐዲሳትን አስማምተው፥ ምስጢሩ የረቀቀውን አጉልተው፥ መሰረቱን ሳይለቅ ለሰው እንደሚረዳው እንደሚገባው ለመተርጎም የሃይማኖትን ምስጢር፥ የስነምግባርን(ትሩፋትን) ነገር መማሪያ እና ማስተማሪያ፥ መመከሪያ መምከሪያ በመሆን ከፍተኛ ጥቅም አላቸው። አዋልድ መጻሕፍትን የሚጽፏቸው ቅዱሳን ጻድቃን፥ ሰማዕታት፥ ሊቃውንት (መምህራን) ናቸው። ✝ የአዋልድ መጻሕፍት ዓይነት ✝ ✝ በቤተክርስቲያናችን የሚገኙ አዋልድ መጻሕፍት ዓይነቶች ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለው ናቸው።  ✝ 1. የትርጓሜ መጻሕፍት፦ የቅዱሳት (የቀኖናውያት) መጻሕፍትን ምስጢር የሚያስረዱና የሚተነትኑ ናቸው።  ✝ 2. የመናፍቃን ምላሽ ላይ የተጻፉ ልዩ ልዩ መጻሕፍት፦ በተለያየ ዘመን የተነሱ መናፍቃን ለሚያነሷቸው የተሳሳቱ አስተሳሰቦችና እምነቶች መልስ ለመስጠት በየዘመኑ የተነሱ አባቶች የጿፏቸው መጻሕፍት ናቸው።  ✝ 3. የጸሎት መጻሕፍት፦ በግልና በማኅበር ለጸሎት የሚያገለግሉትን መጻሕፍት ናቸው። እነዚህም መጽሐፈ ክርስትና፥ ውዳሴ ማርያም፥ ወ.ዘ.ተ... ✝ 4. የሥርዓት መጻሕፍት፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያየ ቦታና ዘመን በርካታ ሥርዓቶች ተገልጸዋል። ከህብረተሰቡ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ዘርዘር ያሉ የአሰራር፥ የአኗኗር ... ሥርዓቶችን የሚገልጹ መጻሕፍት ናቸው።  ✝ 5. የተዓምራት መጻሕፍት፦ እግዚአብሔር በቅዱሳን ላይ እያደረ የሚሰራቸው ተዓምራት በርካቶች ናቸው። በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ራሱ በቀጥታ ያደረጋቸው በወዳጆቹ ሰዎች አማካይነት ያደረጋቸው ብዙ ተዓምራት ተመዝግበዋል። እንደዚህ ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት እና ቦታዎች ተዓምራት የተደረገባቸውን (እግዚአብሔር ድንቅ ስራን የሰራባቸው) የተዘገበባቸው መጻሕፍት ናቸው። ✝ 6. የገድላት መጻሕፍት፦ ገድል ትግል፥ ፈተና፥ ውጊያ፥ ሰልፍ፥ ድልና አክሊል እስኪገኝ ድረስ የሚደክሙት ድካም፥ የሚሰሩት ስራ፥ የሚቀበሉት መከራ፥ መንፈሳዊ ዜና፥ ታሪክ፥ የቅዱሳን መከራና ጸጋ፥ እንዲሁም ተጋድሏቸውን የሚናገር መጽሐፍ ነው። የአንድን ሰማዕት ወይም ጻድቅ ስራና ተጋድሎ ዘርዘር ባለ ሁኔታ የያዘ መጽሐፍ ሲሆን የክርስቶስ አገልጋዮች ከክፉ ሰዎችና ከአጋንንት ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ የሚገልጹ መጻሕፍት ናቸው። ጻድቁ ከመነሻው እስከ ፍጻሜው ያሳለፈውን ሕይወት የደረሰበት ፈተናና በገድል እንደተቀጠቀጠ በመጨረሻም ይህን ዓለም ድል አድርጎ ወደ ፈጣሪው የመሄዱን ነገር ያስረዳል። 
Показати все...
🙏 3👍 2
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበቡ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ክፍል ውስጥ ባለፈው ሳምንት ተሳንፌ አልያም ሳልችል ቀርቼ ስላልጻፍኩላችሁ ዛሬ ከሁሉም ከተነበቡት መጽሐፍት ውስጥ የሆነች የሆነች ጥቅስ ነው ማጋራችሁ 1️⃣ከወንጌል:- [የዘሪው ምሳሌ] “ሌላውም(ዘር) በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው።” [ሉቃስ 8:7] ጌታችን በምሳሌ ሲናገር ዘሪ ዘሩን ሊዘራ እንደወጣና ዘሩም በተለያየ ቦታ ላይ እንደወደቀ ይናገራል.. ከነዚህ ውስጥ አንዱ በእሾህ መካከል ነው የወደቀው.. በእሾህ መካከል በመውደቁም ፍሬ እንዳይኖረው እሾሁ አነቀው ይለናል.. ምሳሌውንም ጌታ ኢየሱስ ሲያብራራ ዘር የተባለው “የእግዚአብሔር ቃል” እንደሆነ ከተናገረ በኋላ እንዲህ ይላል: “በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ (ቃሉን)የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።” 2️⃣ ከሐዋርያት ሥራ: “የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከብ መሪውንና የመርከቡን ባለቤት ያምን ነበር።” [ሐዋ 27:11] ክቡር ቅዱስ ጳውሎስ በእስር ሆኖ ለይግባኝ ወደ ሮም በሚሄድበት ጊዜ በመርከብ ላይ ያዩት መከራ በስመአብ.. አንተርፍም ብለው ተስፋ ቆርጠው ነበር.. ጳውሎስ ግን በኋላ ያጽናናቸዋል መልአክ እንደተገለጠለትና በሰላም እንደሚደርሱ እንደነገረውም ይነግራቸዋል.. “እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።” ይላቸዋል.. ሙሉውን አንብቡት 3️⃣ከጳውሎስ መልእክታት:- “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” [1ቆሮ 15: 33] ሰውን አንጸየፍም.. ግን ደግሞ በቅድስና እና በሃይማኖት እንኖር ዘንድ የታዘዝን እኛ አዋዋላችን በኃጢአት እና በኑፋቄ መንደሮች ቢሆን እኛም ቀስ በቀስ ወደ እነርሱ አስታሳሰብ ልንሳብ እንችላለን.. አስቀድሞም በምሳሌ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ነበር: “ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።” [ምሳሌ 13:20] 4️⃣ከቀሩት መጽሐፍት:- (እንዴት እንደሆነ ባላውቅም እዚህ ክፍል ላይም እኛ ጋር ዕብራውያን ነው የተነበበው.. ያው ይህ መጽሐፍ የጳውሎስ እንደሆነ እኛ ሃገር አከራካሪም አይደለም ብዬ ነው) “እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፡ ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፡ ያለው እርሱ ነው” [ዕብ 5:5] ለክህነት አገልግሎት ማንም ቢሆን ራሱን አያከብርም.. ለምሳሌ እነ አሮን.. ኋላ ክርስቶስም ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም አለ.. ሥጋ እንደመሆኑ ራሱን የሚያከብር ሳይሆን በተዋሕዶ የቃል ገንዘብን ገንዘቡ አድርጎ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” የሚለው ቃል ለእርሱም ተነገረ እንጂ.. ንስጥሮስ ስለ ኢየሱስ ሊቀ ክህነት ሲናገር ሰውነቱ ብቻ ነው ሊቀ ካህናት ይላል.. ቄርሎስ እንደመለሰው.. ኋላም በ11ኛው ቃለ ግዘቱ(በኤፌሶን ግባዔ) ላይም እንደ ገለጸው ሊቀ ካህናት እርሱ ሥግው ቃል ነው…” መልካም የጌታ ቀን @Apostolic_Answers
Показати все...
🥰 5
እራት ጋብዤ ልተኛ ጨርሳቹ አንብቡ 🙄 በመንፈስ_ጀምሮ_በሥጋ_መጨረስ ፨ ተወዳጆች ሆይ ጌታችን በውኃ ላይ እየተራመደ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ተመልክቶ በእምነት "ጌታ ሆይ በውኃ ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው። ጌታም እምነቱን ተመልክቶ "ና" አለው። ቅዱስ ጴጥሮስ ከታንኳይቱ ወርዶ ወንድሞቹ ሐዋርያት እስኪደነቁ ውኃውን እንደ የብስ በመቁጠር በባህር ላይ እየተራመደ ወደ ጌታ ४९:: ልክ ጌታችን ጋር ሊደርስ ሲል የንፋሱ ኃይል ሲያናውጠው ባህሩ የሚያሰጥመው ስለመሰለው እምነቱ ጎደለ። አጠገቡ በባህሩ ላይ የቆመውን ና ያለውን ጌታ ማሰብ ትቶ በሥጋ ፈርቶ "እሰጥም ይሆን" አለ። በባህሩ ላይ ያስኬደው፣ያቆመው እምነቱ ሲከዳው፣ ባህሩ አሰጠመው። ጴጥሮስም በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ ጨረሰ። አንተም በእምነት ጀምረህ እምነትህ ልክ ጌታህ ጋር ሊያደርስ ሲል በሥጋ ፍላጎት መናወጥ ከጀመርክ በኃጢአት ባህር ትሰጥማህ። ብዙዎች መንፈሳዊነትን በጽኑ እምነት ጀምረው፣ልክ ጌታ ጋር ሊደርሱ ሲሉ፤የሰይጣን የፈተና ንፋስ እያንገዳገዳቸው፣ትዕግስት እያሳጣቸው ከመጽናት፤ በኃጢአት ባህር ሰጥመው መዋኘት ይጀምራሉ። ቅዱስ ጴጥሮስ በእምነት የጀመረውን በሥጋ ቢጨርስም በባህሩ ሰጥሞ እንዳይቀር ጌታውን "ጌታ ሆይ አድነኝ" ብሎ ጮኸ። ጌታችንም ቅዱስ ጴጥሮስን "አንተ እምነት የጎደለህ፣ስለምን ተጠራጠርህ?'' ብሎ ወቅሶት እጁን፣ዘርግቶለት ከባህሩ አውጥቶታል። አንተም ምንም በኃጢአት ባሕር ብትሰጥምም፣ እምነት ቢጎድልህም ጌታህን "አድነኝ" ብለህ ብትጮህ ለጴጥሮስ የተዘረጋ እጁም ላንተ ይዘረጋል፣ከሰጠምክበትም ያወጣኃል። ብቻ አድነኝ ብለህ ጮህ። ማቴ 14÷25 የአለቱ የቅዱስ ጴጥሮስ እና የብርሃነ ዓለም የቅዱስ ጳውሎስ ጸሎታቸው በረከታቸው
Показати все...
🙏 9👍 1
Repost from N/a
ጥያቄ፡ በማቴ 15 ፥ 24 ላይ ጌታችን ለእስራኤል በጎች ብቻ እንደተላከ ያሳያል። ታዲያ ጌታችን የእስራኤላውያን ብቻ ነውን? መልስ፡ /ማቴ 15 ፥ 24/ “24 እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።” {ይህ ጥቅስ ጌታችን የእስራኤላውያን ብቻ እንጂ ለሌሎች አዳኝ እንዳልሆነ ያሳያል? እስኪ ይህንን ጥቅስ ከራሱ ከማቴዎስ ወንጌል እናብራራ፥ ሀ) ማቴዎስ ቀድሞ ጌታችን ለአሕዛብም እንደመጣ አሳውቆናል /ማቴ 2 ፥ 1 - 2/ “1-2 ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።” [በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ላይ ጌታችን እንደተወለድ ያወቁት ቀድመው ማን ናቸው? አስቀድመው የጌታችንን ንጉሥነት የጌታችንን አዳኝነት የጌታችንን ማንነት ተረድተው ሊሰግዱለት የመጡት አይሁዳውያን አልነበሩም ፥ ይልቁንም ከምሥራቅ የመጡ ሰብአ ሰገል ነበሩ እንጂ። ይህ ጌታችን ለአሕዛብም እንደመጣ ያሳውቀናል።] /ማቴ 4 ፥ 14 - 16/ “14-16 በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።” /ማቴ 12 ፥ 16 – 20/ “16-17 በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ 18 እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። 19 አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። 20 ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።” [ይህ ትንቢት ስለጌታችን የተነገረ ትንቢት እንደሆነ ማቴዎስ ነግሮናል ፥ ይህ ትንቢት ደግሞ ‘ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል’ ይለናል። አያችሁ? የማቴዎስ ወንጌል በግልጥ ጌታችን ለሰዎች ሁሉ እንደተላከ ነግሮናል።] /ማቴ 24 ፥ 14/ “14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” [‘የመንግሥት ወንጌል’ ማለትም የጌታችን ወንጌል ለአሕዛብም ሁሉ ይሰበካል ማለት ነው።] ለ) ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ራሱንና ሐዋርያቱን በእስራኤል ውስጥ ወስኗል በብሉይ ኪዳን ውስጥ የቃልኪዳኑ ልጆች የሆኑት እስራኤላውያን የያዕቆብ ልጀች ናቸው። ስለዚህ በመጀመሪያ ጌታችን የመጣውና ትምህርቱእ ተአምራቱን የፈጸመው ለእስራኤል ልጆች ለአይሁዳውያን ነው። ስለዚህ ጌታችን በሕይወቱ ሳለ ራሱን የወሰነው እኒህን የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች እየፈጸመ የቃልኪዳኑን ልጆች ለማዳን ነው። ማቴ 15 ፥ 24ም እያመላከተን ያለው ይህንን ራሱን መልእክት ነው። /ማቴ 10 ፥ 5-6/ “5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤ 6 ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።” [አያችሁ? ጌታችን ሐዋርያቱን መጀመሪያ የወሰናቸው ለአይሁዳውያን ብቻ ነው። እነርሱ ቀድመው የሙሴን፣ የአብርሃምን፣ የዳዊትን ቃልኪዳን ተቀብለው የጠበቁ ናቸው። መጀመሪያ እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ለአይሁዳውያን እንጂ ለአሕዛብ አልሰጠም። ስለዚህ ጌታችንም መዋዕለ ሥጋዌውን የወሰነው በእስራኤል ውስጥ በማስተማር እና የጠፉ የተባሉትን በጎች በመመለስ ነው።] /ማቴ 15 ፥ 24/ “24 እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።” [አሁንም በዚህ ጥቅስ ውስጥ እየነገረን ያለው እኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ የመጣሁት ለእስራኤላውያን ነው። እነርሱ ቃልኪዳኑን በመጠበቅ የታመኑ ነበሩና መጀመሪያ እርሱ ይገባቸዋል። ለአሕዛብን ግን ልክ ከጌታችን ዕርገት በኋላ የጌታችን ትምህርት እንዲተላለፍ እያዘጋጀን ነው።] ሐ) ጌታችን ከመዋዕለ ሥጋዌው በኋላ ግን ለአሕዛብ መልእክቱ እንዲደርስ አድርጓል ታዲያ ጌታችን ለእስራኤል ከመጣ መልእክቱ ለሌላ ትውልድ እንዳይደርስ አድርጓልን? አይደለም ፥ ምክንያቱም ራሱ ማቴዎስ ደግሞ ልክ ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ መልእክቱ ለአሕዛብ እንደሚደርስ ነግሮናል። /ማቴ 10 ፥ 16 – 18/ “16 እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። 17 ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ 18 ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።” [ከላይ በማቴ 10 ፥ 5-6 ላይ ‘ለእስራኤል ሂዱ’ ብሏቸው ነበር። ‘ሂዱ’ ሲላቸው ጌታችን በሕይወት ያለውን ጊዜ እየነገራቸው እንደሆነ መመልከት ትችላላችሁ። ራሱ እየነገራቸው ስለሆነ ፥ ከዚያ ግን እየቀጠለ ኋላ ስለሚመጣው ነገር ደግሞ ይነግረናል። ኋላ ከሚመጡት ነገሮች መካከል አንዱ ‘ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ፥ ስለእኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።’ ነው። ቆይ? ከላይ ለእስራኤል ብቻ ነው የምትሄዱት ካለ እንዴት ነው መልሶ ‘ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ’ የሚለን? አያችሁ? አሁን ወደአሕዛብ አትሂዱ አላቸው። ከዚያ ግን ኋላ ለአሕዛብም ምስክር ትሆናላችሁ አላቸው። አያችሁ የማቴዎስን መልእክት? እየነገረን ያለው መልእክት ፥ አሁን በአይሁዳውያን መካከል ቆዩ እነርሱ የቃልኪዳን ልጆች ናቸውና። ኋላ ግን ድኅነቴን ስፈጽም ፥ ስነሣ ከዚያ በኋላ ለምስክርነት ወደአሕዛብ ደግሞ ትሄዳላችሁ። ያንን ራሱ ማቴዎስ እንዴት መጨረሻ ላይ እንደሚነግረን ደግሞ ተመልከቱ።] /ማቴ 28 ፥ 19-20/ “19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” [ቀድሞ ወደ አሕዛብ አትሂዱ እንዳለው ሁሉ ፥ ልክ ጌታችን ከሙታን በክብር ከተነሣ በኋላ ደግሞ አሁን ሁሉም ነገር ተፈጽሟል ስለዚህ ወደአሕዛብ ደግሞ ለምስክርነት ሂዱና ስበኳቸው ብሎ አስተማረን። የማቴዎስን ወንጌል አንድ ጥቅስ እየቦጨቅን ካልተመለከትነው ፥ እንደምልዐቱ ከተመለከትነው ውብ የሆነ መሰናሰል አለው። ጌታችን የሰው ልጆች ሁሉ ምኀኒት ነው ፥ መጀመሪያ መዋዕለ ሥጋዌውን በእስራኤል ውስጥ ወሰነ ፥ ከዚያ ግን በሐዋርያቱ በኩል ደግሞ የአሕዛብ መሲሕ መሆኑን ነገረን።]} አስጀምሮ ላስፈጸመ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር እና ምሥጋና ይሁን። ክርስቶስ ተነሥቷል በእውነት ተነሥቷል ኪርያላይሶን እግዚአብሔር አብ ሆይ ማረን ፥ ኪርያላይሶን እግዚአብሔር ወልድ ሆይ ማረን ፥ ኪርያላይሶን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆይ ማረን። ማራናታ ፥ ጌታ ሆይ አትዘግይ ቶሎ ና። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለመ ዓለም አሜን
Показати все...
👍 4
ምክር ከብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ “ወንድሜ አንተ ግን አሁንም የተወሰኑ ምድራዊ ፍላጐቶች አሉህ፡፡ “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና” (ማቴ. 6፥21)፡፡ ልብህ የተሞላው በኃላፊው ክብር ነው፡፡ መንፈሳዊ ሕይወት በአንተ ዘንድ ዋጋውን አጥቷል፡፡ ይህ ሰይጣን ጌታችንን የፈተነው ዓይነት ፈተና ነው፡፡ “ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፡፡ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።” (ማቴ. 6፥8-9) ተመልከት የምትፈልገውን ሁሉ አግኝተህ ነፍስህ ብትጐዳ ለአንተ ምንድን ነው ጥቅሙ? እባክህ ነፍስህ ነፃ መሆን ትፈልጋለች እና ወደ ልብህ ተመለስ፡፡” የሕይወት መዐዛ ገጽ 49
Показати все...
🙏 5👍 4
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.