cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

Рекламні дописи
45 628
Підписники
+10224 години
+5107 днів
+2 76630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

57👍 53😭 29🤩 3🎉 2👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በ11/09/2016 ዓ.ም ፓስፓርት የምትወስዱ ደንበኞቻችን በ 7876 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የላክን ሲሆን እሁድ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-06:00 ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት We've sent a text message to our customers scheduled for passport collection on May 19, 2024. If you've received a text message from us via 7876, please visit our Gotera Office in Addis Ababa on Sunday, May 19, 2024. Our offices will be open from 9:00 AM to 12:00 PM for passport collection. Remember to bring a printout of your online application form when you visit us. Immigration And Citizenship Service __ Telegram: https://t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 40 7👎 5
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የቻይና ብሔራዊ የኢምግሪሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ። የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅንጅት አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች በተለይም የኢሚግሬሽን ዘርፉን ከማዘመን፣ የድንበር ቁጥጥር ስርዓቶችን ማሻሻል እንዲሁም የአቅም ግንባታ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን በተለይ ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች (forged documents) መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ የቻይና ብሔራዊ የኢምግሬሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማቸው ጋብዘዋል። ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልዩ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተው ዘርፉን ማዘመንና ማሻሻል በዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናግረዋል። Telegram :- t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 126 33🔥 13👎 12😁 9🥰 4
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባቀረባቸው 3 ረቂቅ አዋጆች እና 1 ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል። ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ የመጀመሪያው የኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር 354/1995ን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን መሰረታዊ ከሆኑ መብቶች አንዱ የሆነውን የመዘዋወር ነፃነትን ለማስከበር፣ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን ለኢትዮጵያዊንና ለውጭ አገር ዜጎች በተሻለ ጥራትና ቅልጥፍና መስጠት እንዲቻል፣ የተቀናጀ የድንበር ቁጥጥር እና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የተሟላ የመንገደኛ ቅድመ ጉዞ መረጃ መያዝ አስፈላጊ በመሆኑ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ሁለተኛው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን በድጋሚ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ተቋሙ በሚሰጠው አገልግሎት የዜጎችን ፍላጎት የሚያሟላ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት ስርዓት የሰፈነበት እንዲሆን፣ የአገራችንን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት በሚገባ የሚያስጠብቅ ስልጣንና አደረጃጀት እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ሶስተኛው የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን በማሻሻል አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ግልጽና ውጤታማ ማድረግ፣ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መሰረታዊ የዜጎችን መብትና ነፃነት ለማክበርና ለማስከበር ሁሉን አቀፍ የምዝገባ ስርዓት መዘርጋት የሚገባ በመሆኑ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረቡት 3 ረቂቅ አዋጆች ላይ በሰፊው ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ አራተኛው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጡትን ወጪ መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ Telegram: https://t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
Ethiopian Passport Service(ICS)

ICS Facebook:-

https://www.facebook.com/EthiopianPassportServiceAgency

👍 105 29👎 5
👍 8 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
➖ፓስፖርት ኦላይን መመዝገብ ለምትፈልጉ ፦ 1. አዲስ ፓስፖርት ለመሙላት፦ - የልደት ካርድ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌ መታወቂያ 2. ፓስፖርት ለማሳደስ፦ - የፓስፖርት የመጀመሪያው ገጽ ፎቶ እና - አንድ ጉርድ ፎቶ 3. የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርት፦ - መጥፋቱን የሚያረጋግጥ የፖሊስ ጣቢያ ወረቀት፣ - ፓስፖርት ኮፒ/ የፓስፖርት መረጃ፣ - ጉርድ ፎቶ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌመታወቂያ 4. የተበላሸ/ የተቀደደ ፓስፖርት፦ - የፓስፖርቱ የመጀመሪያ ገጽ ፎቶ፣ - አንድ ጉርድ ፎቶ እና - መታወቂያ ማሳሰቢያ፦ የየትኛውም አይነት አገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ የምትፈልጉ ክፍያ ቅድሚያ ነው። ቀጠሮ ለማስያዝ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን 📥 @Passport_Agency ✅Share and Join✅ @EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 138 32🥰 23👎 15🔥 14
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ተወያዩ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ሁለቱ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ላይ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ በዘረጋው የጋራ የአሰራር ስርዓት የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለመሻገር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግልጽና የተቀላጠፈ አሰራር ስርዓትን በማስፈን የተጀመሩትን ዜጎችን በህጋዊ መንገድ  ለስራ ወደ ውጭ የመላክ ስራ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ አፈፃፀሙን ከፍ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅበት ሁኔታ ላይም ውይይት በማካሄድ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል:: Telegram: t.me/@EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 166 28👏 11🤯 10🤔 4
➖ፓስፖርት ኦላይን መመዝገብ ለምትፈልጉ ፦ 1. አዲስ ፓስፖርት ለመሙላት፦ - የልደት ካርድ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌ መታወቂያ 2. ፓስፖርት ለማሳደስ፦ - የፓስፖርት የመጀመሪያው ገጽ ፎቶ እና - አንድ ጉርድ ፎቶ 3. የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርት፦ - መጥፋቱን የሚያረጋግጥ የፖሊስ ጣቢያ ወረቀት፣ - ፓስፖርት ኮፒ/ የፓስፖርት መረጃ፣ - ጉርድ ፎቶ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌመታወቂያ 4. የተበላሸ/ የተቀደደ ፓስፖርት፦ - የፓስፖርቱ የመጀመሪያ ገጽ ፎቶ፣ - አንድ ጉርድ ፎቶ እና - መታወቂያ ማሳሰቢያ፦ የየትኛውም አይነት አገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ የምትፈልጉ ክፍያ ቅድሚያ ነው። ቀጠሮ ለማስያዝ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን 📥 @Passport_Agency ✅Share and Join✅ @EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 147 31👎 22🔥 12🥱 7
👍 192😭 68 60👎 41🥰 24👏 22😁 20
በ03/09/2016 ዓ.ም ፓስፓርት የምትወስዱ ደንበኞቻችን በ 7876 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የላክን ሲሆን ቅዳሜ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-08:00ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት We've sent a text message to our customers scheduled for passport collection on May 11, 2024. If you've received a text message from us via 7876, please visit our Gotera Office in Addis Ababa on Saturday, May 11, 2024. Our offices will be open from 9:00 AM to 2:00 PM for passport collection. Remember to bring a printout of your online application form when you visit us. Immigration And Citizenship Service __ Telegram: t.me/@EthiopianPassportServiceICSETH
Показати все...
👍 70 22🔥 3