cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ገብላዊ ዮሐንስ_Geblawi Yohannes

Рекламні дописи
655
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የሰላምታ ደብዳቤ፦ ይድረስ ለቸሩ እገዚአ ብሔር። ደህና ነህ?እግዜሩ ደህና ነህ?ፈጣሪ እንደምን ብለሀል?ከቶ እንደምን አለህ?ሰማዩ ደህና ነው?ኢዮር!ደህና ነዎይ ?ራማስ ደህና ነው ?የሆነውስ ሁኖ አዳም ደህና ነዎይ?ዛሬም እንደ ቀድሞው በለስን ይበላል?የሆነውስ ሁኖ በለስ አለች ወይ?ሄዋንስ ደህና ናት?የሆነውስ ሁኖ ገነት ደህና ናት ወይ?ዛሬም እንደ ቀድሞው መዓዛዋ አለ?አብርል ትገባለች?አዝርል ትወጣለች?ሰላምታ አድርስልኝ።መቼም እንደ ሌላው አንተ አትመካም ።እኔን ወደሌላ አትላኩኝ አትልም። ሄኖክስ ደህና ነው?ዛሬም እንደ ቀድሞው ይጽፋል?ያነባል?በል ሰላም በልልኝ።ሰላምታህ ይድረሰኝ ብሎሀል በልልኝ።እናሳ!ኖኅሳ ደህና ነው?ግሩም ነው!።የሆነውስ ሁኖ መርከቡ ደህና ናት? ዛሬም እንደ ቀድሞው ፍጥረት ታድናለች? ንገራት እግዜሩ።ዓለሙ ለመስጠም ተዘግጅቷል በላት።ማየ አይህም ቀርቧል ተዘጋጂ በላት።እና እግዜሩ፦እንደው ለመሆኑ አብርሃም ደህና ነው?ድንኳኑ አለች ወይ?ዛሬም እንደ ቀድሞው ከመንገድ ላይ አለች?ተመላላሺውን ታስተናግድ አለች?ምስኪኑን ደኃውን ኑ ግቡ ትላለች?በአጠገቧ ሲያልፉ ኑ ግቡ ታስተናግዳለች ? በል እንግዲህ ሰላምታ አድረስልኝ ። እኔም ከሷ ዘንዳ ውለታ አለብኝ። እምልህ ፦ ግን!እንደው ለመሆኑ ያዕቆብ ደህና ነው?ዛሬም እንደ ቀድሞው ሶርያ ይሄዳል?መሰላሏስ አለች?ንጉሡሥ እንዴት ነው?ይታያል?ኧረ ባክህ! ግሩም ነው?እኔ ምልህ !ሙሴ ደህና ነዎይ?በትሩስ!ደህና ናት!ዛሬም እንደ ቀደሞው ታምር ትሰራለች?ባሕር ትከፍላለች ?እባብ ትሆናለች?ትለዋዎጣለች?ፈርኦንስ አለወይ?ከሙሴ ጋር, ታርቋል?መቼስ የሱ ነገር እምቢ ብሎእንዳይሆን ?በል እስቲ ሰላምታ አድርስልኝ ።እዜሩ እንጅ ;እንደው ባሰለችኝ ዳዊትስ እንዴት ነው? የሆነውስ ሁኖ መሰንቆው ደህና ናት ?ግሩም !ግሩም!ግሩም! ሳኦልስ ደህና ነው? ዛሬም እንደ ቀድሞው ፈውሰኝ ይለዋል? ዳዊት በገናውን ይደረድራታል? ጎልያድ ደህና ነው? መገዳደር ትቷል? ይሄው ረስቼ ዳዊትን አንስቼ ወንጭፉን ረስቼ! ወንጭፉ ደህና ናት? በል! በል! ሰላምታ አድርስላት ። ደግሞም በአሁን ቋንቋ አድናቂሽ ነኝ በላት።ንገራት ።ንገራት።የላኩህን ሁሉ አንድም አትሰውራት።ኧረ ለመሆኑ ሰሎሞን ደህና ነው?ጥበቡስ ደህና ነው?ፍልስፍና ትቷል?ወይስ? ምልህ እዜሩ ማክዳ ደህና ናት ? ከሰሎሞን ልሂድ ማለቱን ትታለች?ገጸ በረከቱን መውሰድ አቁማለች ?ምኒሊክን መጽነስ ዛሬስ ትታዋለች? ይገርማል!እንደው አደከምኩህ ?መቼስ አንተ አትደክም እንኳን ልትደክም ታጸናለህ ደኩም።ምልህ፣ኢሳያስ ደህና ነው? ትንቢት ይናገራል? ድንግል ትጸንሳለች በማለት ይጽፋል? ንገረው።ንገረው።ሁሉንም ንገረው።ድንግልም ጸንሳለች።ሕጻኑም ተወልዷል በማለት አስረዳው።ትንቢት ተፈጽሞል ።ምሳሌውም ሁኗል።እያልክ ንገረው።ላልሰማም አሰማው።ግን!እዜሩ!ማርያም ደህና ናት?ዛሬም እንደ ቀድሞው ማድጋዋን ነጥቃ፣ ባጭር ባጭርታጥቃ ውሃ ትቀዳለች? የዮሴፍን ልጆች ትንከባከባለች? ይገርማል ይገርማል እንደው ይቅርታና፦ ልጨምር አንድ ቃል ከሰማይ ተልኮ ገብርኤል ይመጣል? ዛሬም እንደ ቀድሞው ተፈስሂ ይላል? በል አመሰግናለሁ።እግዜር ይስጥህ ብየ ምርቃት አልመርቅ፥ አንተ እግዜሩ ነህ ሁሉን የምጠብቅ።ግን አደራ ሁሉን አድርስልኝ ካሉበት ላይ ሁነው በጸሎት አይዘንጉኝ ቸው ቸው እዜሩ ሰላም ለሀገሩ ወሰላም ለደብሩ።(በመ/ር ጽጌ ሲሳይ))
Показати все...
@የማርታ ነገር@ የርሷን ነገር ስጽፍ እንባ ይቀድመኛል፤ጉረሮየን ሁሉ ይተናነቀኛል፤እምሽክ ድቅቅ ብየ እዝን ትክዝ እላለሁ። ፍጻሜዋን ሳየው እጹብ ድንቅ እላለሁ፤ማርታን ታውቂያታለሽ????እርሷ ጽርዓዊት(ግሪካዊት ናት)እና ማርታ ሁለት ሕይወት አላት።አንዱ የሞተ ነው፤አንዱ ግን ሕያው ነው።ማርታ እኮ የግሪክ ከተማ አቴናን(Ateansn)በዝሙቷ ያጥለቀለቀች ነበረች፤መዋዕለ ሕይወቷ እንደሚያስረዳን ማርታ በቀን እንኳን በርካታ ወንዶችን የምትቀያይር፤የደምግባቷ ነገር እንደ ጨረቃ የፈካ ውብ መልከ መልካም፤ይህ ቀረሽ የማትበል፤ጽጌ ረዳ ነበረች፤ታድያ ምን ታድርጊዋለሽ !!ያንን ውበት የዝሙት ምስጥ የዝሙት ነቀዝ እንኩት አድርጎ በላው።ማርታ ስታልፍ ስታገድም ወንዶች ሁሉ ይፈዙ ይጠቃቀሱባትም ነበር።ማርታን የማያውቅ ማንም አልነበረም፤አንዱ በዘማዊነቷ አንዱ በውበቷ ማርታን ያውቃትል።እና ለማርታ ውድቀት ምክንያት የሆናት የማርታ ደም ግባት ነበር።በቃ ደም ግባቷ ነው ።ምን ታድርግ ምርት ?? ማርታ እኮ የማርታን መልክ አልቀረጸችም!!የተሰራውን አካል ከማሳመር የዘለለ፤ከመቀባባት የዘለለ፤ምንም ምን አላደረገችም።ማርታን ያሳመራት የውበት ጌታ አምላክ ነው።ታድያ ማርታን ውበቷ ገደላት፤ ስታልፍ ስታገደም ወንዶች ሁሉ የጎሪጥም አፍጥጠውም ያይዋታል።ይጠቃቀሱባታል።ይስቋታል።ማርታም በውበቷ ተታላ የውስጥ ውበቷን አጣች።ምንም እንኳን ውበት በጎ ቢሆንም ግን ውበትም ይገድላል ለካ? በቃ ከማርታ ተማሩ።እስቲ አስቢው??አሁን ማርታ ሰሪዋን አሳምረህ ለምን ፈጠርከኝ"ማለት"ነበረባት?ውበት ጥሩ ቢሆንም ብዙዎች በውበታቸው ክብራቸውን አጡ፤ሕይወታቸውን ተነጠቁ፥ካሰቡት ሳይደርሱ ራሳቸውን አጡ።ማርታን ይህ ነው የገጠማት።ታድያ ማርታ በአቴና ውስጥ ስትኖር አንድ ቀን እንዲህ ሆነ። ዕለቱ ልደት ነው።የጌታችን ልደት ይከበራል።ሰው ሁሉ ነጫጭ ልብስ ለብሶ ወደ/ቤተክርስቲያን ሲሄድ ማርታ ቀናች።ማርታ እንባዎቿን እያፈሰሰች አግድማ ታያለች።ሰው ግን መስቀለኛ ልብስ ለብሶ ይነጉድ ነበር ።ማርታ ቀናች አየ ማርታ እኔ ልዘንልሽ!!!!! አብራ እንዳትሄድ በሕይወቷ ከቆነጀች በኋላ ቤ/ክርስቲያን ሂዳ አታውቅም።ደግሞ ሰው መሳቂያ መሳለቂያ ያደርጋታል። ማርታ በጨፋሪነቷ በውበቷ በዝሙቷ እውቅ ነች።ያኔ ግን ማርታ ቅናቷ ገነፈለ ፤ቆነጃጅት ሁሉ ወደ ቤ/ክርስቲያኑ ይገሰግሳሉ፤ማርታ ግን ጨነቃት አንድ ሀሳብ አሰበች።በቃ እኔም መስቀለኛ ልብስ ለብሼ፤በነጫጭ ልብሶቼ አምራ ተውቤ ቤ/ክርስቲያን መሄድ አለብኝ"የሚል ሀሳብ አሰበች ማርታ ተነሳች ልብሷን ለበሰች ከሕዝቡ ጋራ ተጓዘች፤ከደብሩ ደረሰች።ሁሉ እየሰገደ ተሳለመ።ወደውስጥም ሁሉ ገባ።ማርታም እንደ ሁሉ ሰግዳ ልትገባ ስትሞክር ፥አንድድድ አሳዛኝ ክስተት ተፈጠረ።የቤ/ክስቲያኑ ዘበኛ ሩጦ መጣ፤ማርታን አያት ግን ልትገባ እግሯን ስታነሳ አንች! አንች! ማርታ ዘማዋ አይደለሽ"?? አላት እርሷም እየተጨነቀች እንባም እያፈሰሰች አዎ! አዎ! አለችው።አየ የኔ እናት ዘማዋ ነሽ?"ሲላት ምን አባህ!!አላለችውም፤ማርታ ትሁት ናት ።ትሁቴ ራሷን አዋረደች።ያ ገብጋባ ዘበኛ አንገቷን አንቆ ይዞ የት አባሽ ትገቢያለሽ?የት??አንች እርኩስ አንች እኮ ወጣቱን ሁሉ ያበላሸሽ የከተማችን ገጽታ ያረከስሽ ክፉ ነሽ አንች ወንዶችን ሁሉ ያሳትሽ ነሽ።በአንች ምክንያት ወጣቶች ብቻ አይደሉም አረጋውያንም ረክሰዋል።ብዙ ሽማግሌዎች ከአንች ደርሰዋል።እና ደግሞ ብለሽ ብለሽ ይህንን እርኩስ ገላሽን ቤ/\ክርስቲያን ታመጭው"ብሎ ጮኸባት።እንዲህ አላት ውጭ ውጭ "እያለ ጮኸባት። ማርታ ድሮውንም ተጨንቃ ነው የሄደች ይበልጥ ተጨነቀች ሁሉ ገባ ማርታ ግን በር ላይ እንደ ሌባ አንገቷን ተይዛ ቀረች።።።።ቀረች። በነገራችን ላይ ማርታ አሁን ትታየኛለች።እርሷን እያሰብኩ እንባየ ይፈሳል።ዘበኛው ሲይዛት ሀፍረቱ ሲውጣት በሀሳቤ ትታየኛለች።የኋላዋ ማርታ እናቴ ሆይ??በረከትሽ ይድረሰኝ።ከዚያ በኋላ ዘበኛው ጨካኝ ስለሆነ እየገፋ አወጣት። እርሷም አልወጣም አልወጣም"የሚል የሴት ድምጿን ብዙ ሺህ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ አደባለቀችው ፤ሕዝቡ ተጨነቀ።እኩሉ ሳቀ።ይህንን የሰሙት ጳጳሱ ምን ተፈጠረ ብለው ወደበሩ መጡ።ነገሩ ከበደ።ማርታ ጳጳሱ ሲመጡ በቃ ልቀቃት የሚሉላት መስሏት ነበር።ግን እንዳሰበችው አልሆነም።ለካ ማርታን ይህ ጳጳስ ያውቋት ነበር።ማርታ በከተማው አተራማሽ መሆኗ በጣም ታውቋል ። ደግሞ በከተማዋ ውበቷ አንደኛ ነው።።ታድያ ጳጳሱም የእርሷ ዜና ይደርሳቸው ነበር።ፎቶዋንም ያውቁታል።ገና ሲደርሱ አንች እርኩስ ደገሞ ከዚህ ምን አመጣሽ??አሏት፥ማርታ ያልጠበቀችው ሆነ።አንጀቷ አረረ ልቧ ተሰበረ።ጳጳሱም አንች እርኩስ በርሱ በረከሰ እጅሽ፤ምሰሶውን ስትዳስሽ፤በረከሱ እግሮችሽ ቅዱሱን ስፍራ ስትረግጭ፤በረከሱ እጆችሽ ቅዱሱን ስፍራ ስትዳስሽ አታፍሪም?"አላት።ውጭ ውጭ "ብሎ ጳጳሱም ጮኸባት።ማርታ ግን አልወጣም ብላ ጮኸች።በመጨረሻ ማርታን መንፈስ ቅዱስ ጎሰማት። እንዲህ አለች። አባ አባ የዛሬን የዛሬን ተወኝ።አታሳፍረኝ።አባ አባ!የዛሬን ከተውከኝ ዳግም እንኳን ወደ ዝሙት እንኳን ወደ ዓለም።ወደቤቴም አልመለስም "አለችው።ጳጳሱ ግን የለም አንችን አላምንሽም መጀመሪያ ተመለሽና በዝሙት የሰበሰብሽውን ገንዘብሽን ሁሉ ሰብስበሽ ይዘሽ ነይ "አላት።ማርታ ተመለሰች !!እያዘነች ሂዳ ወርቋን ቀለባቷን ብሯን ንብረቷን ሁሉ ጭና ይዛ መጣች ጳጳሱ በፊቷ ያንን አካሏን ሽጣ ያከማቸችውን ሀብት ሁሉ እሳት አስነድዶ በእሳት አቃጠለው ያን ጊዜ ነው የማርታ ሀብቷ ንብረቷ ሲቃጠል ኀጢአቷም አብሮ ተቃጠለ።።። ወዲያው!ወዲያው ሳትቆይ አበ አበ !!ጠጉሬን ላጨው አለችው።ያ ዞማ ጠጒሯ ብዙ ሽቱዎች የተርከፈከፈበትና ብዙ ጎረምሶች የደነሱበት ጠጒሯ ተላጭቶ ወደቀ ማርታ መነኮሰች እንዳለችውም ስንኳን ወደቤቷ ወደ ዓለምም ሳትመለስ ቀረች።ማርታ መነነች፤ እድሜ ልኳን ስታለቅስ ስትጸልይ ኖረች።ማርታ ቅድስት ሆነች፤ማርታ ቡርክት ሆነች በመጨረሻም ማርታ በገዳሙ እንዳለች ከመብል ከመጠጥ ተከልክላ ኑራ ሰውነቷ አልቆ ፤ውበቷ ተሟጦ ማርታ ሞትች(አረፉች)))) መላእክት ወረዱ፤ቅዱሳን ወረዱ ።ዳዊት በመሰንቆ እዝራ በበገና ወረዱ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ምን ይባላል ?ወደሰማይ ብርሃን አልብሰው ዘውድ ደፍተው አሳረጓት።።።።።።።።።።።።።የማርታ ነገር ተቀየረ።።።።።።። ማርታ ዛሬ ሰማያዊት ናት።ያችን ዘማዋን ማርታን ማግኘት አይቻልም። ቅድስት ማርታ ናት እንጅ።።።ስም ተቀየረ ከዘማዊነት ወደ ቅድስትነት አደገች።።።።።።።።።።።።።።።። ማርታ ሆይ!! በረከትሽ አይለየኝ። በመምህር ጽጌ ሲሳይ (ኢትዮጵያ።።።።።።።።፤።።።።።። ለአንዲት እኅት የተጻፍኩት ነበር።ግን ሌሎችንም እኅቶቼን እና ወንድሞቻን ከጠቀመ ብየ ይሄው አካፈልኩት
Показати все...
በደብስራት_ቅገብርኤል_ቤክርስቲያን_እናቱን_ያሳርፋታል.3gpp27.11 MB
ሁለቱ ብርሃናት × ከአማናዊው ብርሃን ከክርስቶስ ብርሃንነት የተገኙ ሁለቱ ብርሃናት"ብርሃናቸው እና ብርሃንነታቸው ከክርስቶስ የበራላቸው ፤የአንድ ጎጥ፥የአንድ መንደር ፥የአንድ ሰፈር ወይም የአንድ ቀበሌ ፤የአንድ ወረዳ፤ወይም የአንድ ክልል ብቻ ሳይሆን የዓለም ብርሃንነታቸው፤ዛሬ ይዘከራል፤ ክርስቶስ ለጨለማው ዓለም ከአርያም የመጣ ብርሃን ሲሆን ብርሃንነት በኔ ብቻ ይብቃ አላለም፤እርሱ ራሱ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ከማይቀድመው ብርሃን የተገኘ የማይቀደም ብርሃን ሲሆን፤አባቱ ብርሃን ፤እርሱ ብርሃ ን፤ሕይወቱ ብርሃን ሲሆኑ፤ለጨለማው ዓለም ሁለቱ ያልተለዩት አንድ ብርሃን ክርስቶስ ሥጋን ልብሶ በሥጋ ተገለጠ፤ ከብርሃን የተገኘው ያ ብርሃንም ብርሃናትን አስገኘ፤በእርግጥ የእርሱ ብርሃንነት "ባሕርያዊት ዘለዓለማዊት፤ቀዳማዊት ፤ጥንታዊት አማናዊት ፤መሰረታዊት ናት።የእርሱ ብርሃንነት የእርሱ ብቻ እንጅ የማንም አይደለችም መገኘቷም እርሱ ሲኖር የኖረች እንጅ ከእርሱ በኋላ የመጣች አይደለችም፤የእርሱ ብርሃንነት ከእርሱ ፤እርሱ ደግሞ ከእርሱ ብርሃንነት አይቀዳደሙም፤ እርሱ የሰማይ ብርሃናት፤የመላእክት ከተማ ብርሃን፤የመላእክትም ብርሃን ሁሉ" ብርሃን ሁነው ከመምጣታቸው በፊት በብርሃንነቱ የኖረ የነበር ብርሃን ነው፤በጨለማ ውስጥ ለነበረው ሕዝብ የወጣ ሰማያዊ ብርሃን ነው፤በሄዋን በአዳም በእባብም ምክንያት ጨልሞ የነበረውን ዓለም ሊያበራው የሚችል ብርሃን አልተገኘም ነበር፤የሚደንቀው የሙሴ ብርሃን እስራኤልን ሲበዘብዛቸው ፤እስራኤል ፊትህን ተሸፈንልን ይሉት ነበር፤ሙሴ ግን ሲወለድም በፊቱ ብርሃን ተስሎበት ነበር፤ ነገር ግን ያ ብርሃን እስራኤልን ከማስፈራት የዘለለ በእስራኤል ውስጥ የነበረውን የኀጢአት ጨለማ መግፈፍ አልቻለም ነበር፤ሙሴ እርሱ በግምባሩ ብርሃን ተስሎለታል፤ነገር ግን የአዳም እና የሄዋን የመርገም ጥላ አርፎበት ነበርና ብርሃኑ ፍጹም ብርሃን መሆን አልቻለም፤ብርሃንነቱ ለሥጋ ዐይን ብቻ ሆነ፥ጨለሞ የነበረውን የነፍሳትን ዐይን ማብራት አልቻለም፤ እርሱ ራሱ ሙሴ ግን ትልቅ ብርሃን ይጠባበቅ ነበር፤ታስታውሱ ከሆነ የሥነ ፍጥረት ምሁሩ ሙሴ እግዚአ ብሔርም ብርሃን ይሁን"አለ"ብርሃንም ሆነ ያም ብርሃን መልካም እንደሆነ አየ።ብሎ ስለ ብርሃን ተናግሮ ነበር። ያ ሙሴ የተናገረለት ብርሃን በውስጡ ሌላ ብርሃንን የሚገልጥ ሌላ ብርሃን ነበር፤ያ ብርሃን በቃል የተገለጠው ለፍጡር ጆሮ የመጀመሪያው ቃል ያ ብርሃን ነበር፤ያ ብርሃን በመላእክት መካከል ነግሦ የነበረውን፤የፍርሃት ፤የድንጋጤ ጨለማን ያስወገደ ለመላእክቱ ጥበብ እውቀት የሆነ ብርሃን ነበር።ታድያ በዲያብሎስ በኩል የገባው ጨለማ ብርሃን ይሁን ተብሎ በመጣው ብርሃን ተወገደ፤በአዳም በኩል የገባው ጨለማ ግን ለዘመናት ብርሃናትን ያደከመ ከባድ ጨለማ ነበር፤ለዚያ ነው ፤ነቢያቱ ሁሉ ወደፈነኒ ጽልመት እያሉ የጮሁት፤ጨለማ ውስጥ የነበረ ሕዝብ እያሉ ድምጽ ሲያሰሙ የነበሩት፤ ይህም ጽኑ ጨለማ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የተዘረጋ የጨለማ መጋረጃ ነበር፤ታድያ ያንን የጨለማ መጋረጃ ማን ይቅደደው???ማንስ ያስወግደው??ለዚያ ነው ታላቅ ብርሃን ያስፈለገው፤፤መኖርማ በሙቀቷ የምታቀልጥ፤ በብርሃኗ የምታስጌጥ የፀሐይ ብርሃን አልነበረችምን ??ይሁን እንጅ የእርሷ ብርሃን ለተራራው ለኮረብታው ለጋራው ለሸንተረሩ ፤ለጓዳው ለጎድጓዳው ሲያበራ ለልቡና ግን፤ለሕሊና ግን፤ለአእምሮ ግን፤ለነፍስ ግን ማብራት አልተቻለውም፤እውነት ነው የነፍስ ብርሃኗ ሌላ ትልቅ ብርሃን ነው፤እርሱን ነው ስትጠብቅ የነበረችው ፤በእርግጥ የፀሐይ ብርሃን ረቂቅ ነው፥ነገር ግንበነፍስ ላይ ነግሦ የነበረው ጨለማ ከፀሐይ ብርሃንይልቅ የረቀቀ ጨለማ በመሆኑ በፀሐይ ብርሃን መወገድ አይችልም፤የነቢያት የትንቢት ብርሃን፤የመሥዋዕት ብርሃን፤የቤተ መቅደሱ ብርሃን ሁሉ፤የብርሃን መጥሪያ ብርሃን እንጅ አማናዊ ብርሃን ግን አልነበረም፤አዎ የአሮን ልጆች ሲያጠፉት ሲያለሙት የነበረ የእሳት ብርሃን፤የኤሊ ልጆች ሲጠፋ ዝም" ያሉት ብርሃን ነበር፤ ነገር ግን ያንን ጽኑ ጨለማ ማስወገድ አልተቻለውም፤ቢሆንም የብርሃን መጥሪያ ብርሃን ነበር። እንዲህ እያለ መጣ።የሚደንቀው ኦሪት ማለት ብርሃን ማለት ነው፤ነገር ግን ኦሪት ብርሃንነቷ ከታላቁ ብርሃን የምታደርስ፤ፀሐይ እስከሚወጣ የበራች የሻማ መብራት ነበረችና ሕጓ ሥርዓቷ ተሰብስቦ የአዳምን ጨለማ ማራቅ አልተቻለም፤ኤርምያስ ማለትም ብርሃን ዘተፈነወ "ከእግዚአ ብሔር ዘንድ የተላከ ብርሃን ማለት ነበር፤ነገር ግን ኤርምያስ በእስራኤል ላይ የነገሠ የጣኦት አምልኮ ጨላማን ከማራቅ የዘለለ ያንን ድቅድቅ ጨለማ ማራቅ አልተቻለውም፤ከዚህም የተነሳ ብርሃናት ሁሉ በየጊዜው ብርሃንን ይፈልጉ ነበር፤እጅህን ከአርያም ላክ "ብሎ ታላቅ ነቢይ ትልቅ ድምጽ ወደ ሰማይ አስተጋባ፤ታድያ ይህንን ድምጽ ሰምቶ ታላቅ ብርሃን ወጣ፤በጨለማ የነበረ ሁሉ ብርሃን ወጣለት፤ከታላቁ ብርሃን ቀደም ብሎ አንድ ትንሽ ብርሃን መጣ ፤እርሱ ስለ ብርሃን የሰበከ ብርሃን ነው፤ብዙዎች አንተ ይመጣል የምትባለው ትልቅ ብርሃን ነህን?"ቢሉት እንኳን በፍጹም ራሱን መካድ አልፈለገም እኔ እኔ ነኝ"ብሎ"ራሱን ገለጠ እርሱ ዮሐንስ ነው፤ሌላኛው ዮሐንስም ፡ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ፤ እርሱ ግን ብርሃን አልነበረም፤ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ነው እንጅ "ብሎ"ዮ፩፥፰ ከታላቁ ብርሃን አንጻር ብርሃንነቱን ቢሰውረውም በሌላ ቦታ ግን ብርሃንነቱ የተመሰከረለት ዮሐንስ ብርሃንነቱን አስቀድሞ መሰከረ፤።በመጨረሻም ሲጠበቅ የነበረው ታላቁ ብርሃን ከታላቋ ምስራቅ ወጣ፤እርሱ ራሱ እኔ የዐለም ብርሃን ነኝ"አለ።ዮሐ ፰፥፲፪ ዮሐ ፱፥ ፭ ይህ የዐለም ብርሃን ለዐለም የበራ እውነተኛ ብርሃን ነው፤እርሱ ሲመጣ በሰው ልጅ ሁሉ የነገሠው ጨለማ ተቀደደ.....የተሰረው ሁሉ ተገለጠ፤ የጨለማ አበጋዝ የጨለማ መንግሥቱን ለቀቀ፤በጨለማ የማረከውን ሁሉ ለብርሃን አስረከበ።የወጣው ታላቅ ብርሃን ለምድሪቱ ሌሎች ብርሃናትን መረጠ፤የተመረጡትን ብርሃናት ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ ብሎ ሾማቸው፤ያ ብርሃን ዐይነ ሥጋ ተራራውን ኮራብታውን የሚያይበት ብርሃን ሳይሆን ፥ወንድም ወንድሙን የሚያይበት፥ፍጡር ፈጣሪውን የሚያውቅበት የምግባር የሃይማኖት ብርሃን ነበር።እነዚያ ብርሃን የልቡና መብራት ናቸው፤ እነዚያ ብርሃናት ሮም ላይ ዐለም ላይ ነግሦ የነበረውን ጨለማ ያጠፉ ናቸው፤እነሱም ሐዋርያት ናቸው፤እርሱ ራሱ የዐለም ብርሃን ሲሆን ሐዋርያትን የዐለም ብርሃን አደረጋቸው፤..........ዛሬ ታድያ ከብርሃናት መካከል ሁለቱ ታላላቅ ብርሃኖች የብርሃንነታቸው ነገር በጎላ በተረዳ ይታሰበል፤፤፤ይህ ብርሃንነታቸው..ድንቅ ምሥጢር አለው።።...በረከተ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይህድር በላዕሌክሙ+ አሜን፫........…..+++
Показати все...
ሽሽታችሁ_በክረምትና_በሰንበት_አይሁን.3gpp35.95 MB
መጻሕፍትን_ማንበብ_ዮሐ_አፈ_ተግ፯_ይጨርሱት.3gpp47.46 MB
መጻሕፍትን_ማንበብ_ዮሐ_አፈ_ተግ፯_ይጨርሱት.3gpp47.46 MB
አስይፍተ ፋርስ ወርዘውት ጊዮርጊስሀ ጊዮርጊስሀ አዘዙ፤ ወጊዮርጊስሀ ይስተዩ እሙንቱ ጊዮርጊስሀ አኀዙ ። (ዘአምላኪየ) ዘምስለ ሠብዓ ነገሥት ተዋናይያን ስብዐ፤ ጊዮርጊስ አመ ተዋነየ ጊዮርጊስ ሞዐ ኳሄላ ሃይማኖት ወገይል እንተ ጊዮርጊስ አምጽአ። (ሚበዝኁ) ግ
Показати все...
ጊዮርጊስ ሎሙ ለአስይፍት አርዳአ ሥጋሁ ወደሙ፤ ከመ ሕጻናት ሀሊበ ወጋዕኩክሙ ይብሎሙ።
Показати все...
ጊዮርጊስ ጠቢብ ለተዋሕዶ ብእሲተ ተአኲቶ ተአኲቶ ፤ አአምር ለኪ ይቤላ ዐውደ ንግሥት ከሲቶ ።
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.