cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🎄 HOLY SPIRIT TUBE🎄🎚

Рекламні дописи
206
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
+630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#Bereket_Lema sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ  @wolaitagosplesongs  @wolaitagosplesongs
Показати все...
01 Bereket Lemma(ትሁን ፈቃድህ).mp310.43 MB
04 Bereket Lemma (ከማየው በዓይኔ).m4a7.67 MB
08 Bereket Lemma (የሚገባው አለ).m4a5.83 MB
13 Bereket Lemma (ይብዛልኝ መታዘዜ).mp35.87 MB
07 Bereket Lemma (ይኑርልንጌታ).m4a5.51 MB
02 Bereket Lemma (እንደ ኢየሱስ).mp36.41 MB
03 Bereket Lemma (ያቦቅን ስሻገር).mp313.26 MB
.      #አረ_ሴቶች_ስርዓት_ያዙ ሁሉም ባይሆኑም አብዛኞቹ እህቶች ቤተክርስቲያን ስሄዱ ለብሰው የሚሄዱት ልብስ እንኳን አማኝ ይቅርና አንድ በክርስቶስ ያልሆነ ሰው የማይለብሰውን ልብስ ለብሰው እኮ ነው የሚሄዱት። አረ እባካችሁ ስርዓት ያለውን ሰውንም የማያሰናክል ልብስ ለብሳችሁ ሂዱ። ወንጌልን በአፋችሁ በትነገሩ እንኳ በአለባበስ ለወንጌል እንቅፋት አትሁኑ። እኔ ብዙ ጊዜ ከተማችን ሆሳዕና ላይ ብዙ ወጣቶች ያሉበት የጫት ሰፈራ ወንጌል ልሰብክለቸው እሄዳለሁ እናም ሁሌም ምንድነው የሚሉት እኛ እናንተ ጋ ቤተክርስቲያን መምጣት እንፈልጋለን ግን እናንተ ጋ ያሉ ሴቶች ያሰነክሉናል በምን ስላቸው በአለባበሰቸው እናም ከዚህ ኃጢአት ወጣን ብላን ቼርች ሄዳን ደግሞ ሌላ ኃጢአት መስረት አንፈልግም እረፍት ፈለገን ሄዳን መጨነቅ አንፈልግም ይላሉ። ሰውን ማየት  ትክክል ባይሆንም ግን ልጆቹ ላይ መፍረድ አንችልም። ስለሆነም እባካችሁ እህቶች ስርዓት ያለ ልብስ ልበሱ። ሰውነታችሁን ገልጦ መሄድ እርድና አይደለም ስርዓት ያዙ እንጂ። “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።”   — ሮሜ 12፥1 አንድ ነገር ዕወቁ የሰውነታችሁን ቅርጽ አይቶ የሚመጣ ወንድ መቼም ቢሆን ለቁም ነገር አይፈልጋችሁም። ስርዓት ያዙ እንጂ በጌታ ለወጣቶች የማጥፊያ ምክንያት አትሁኑ። ወንድ ልጅ ቼርች ቁጭ ብሎ በእናንተ ምክንያት በሀሳቡ ዝሙት እንድሰራ ምክንያት አትሆኑ። ልብ በሉ በእናንተ ምክንያት አንድ ሰው ብሰናካል በጌታ ፊት እንደምትጠያቁ። “በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።”   — ማቴዎስ 18፥6 አንድ ጊዜ ከጓደኛዬ ጋር ቤተክርስቲያን አንድ ቦታ ላይ ተቀምጠን ሰለ የሆነች ልጅ መጣችና ከፊት ለፊታችን ባለው ወንበር ላይ ተቀመጠች በጊዜው ልጅቷ በጣም አጭር ትሸርት ከሱር ጋ ለብሳ ነበር እናም የሰውነቷ ቅርጽ እንደለ ይታይ ነበር እኔ ሀሳቤ ልሰራቅ እንደሆነ አየሁና ፊቴን ወደ መድረክ አገልግሎት አዞሩኩ ግን ላከ አጠገቤ የነበረው ጓደኛዬ ቼርች መቀመጡን እረስቶ የልጅቷን ገላ እያየ ሌላ ዓለም ሄዶል ከዚያ የአምልኮ ጊዜ አልቆ ወደ ቤት እያሄድን እንዲህ አለኝ ዛሬ ጉድ ሆንኩኝ እኮ አለኝ እኔም ምንድነው ስል ልጅቷ ከገባች በኃላ ቼርች መቀመጤን እረስቼ ሌላ ዓለም ሄድኩኝ ዛሬ ምንም ሰልሰማ ወጣው አለኝ። ለዚህ ምክንያት ደግሞ የልጅቷ አለባበስ ነበር ስለዚህ እባካችሁ ሴቶች ስርዓት ያለ ሰውነትን የማያሳይ ልብስ ልበሱ። በመሰረቱ ልባም ሴት ምን አይነት ልብስ መልበስ እንደለበት ታውቃለች። ልባም ወንድ ከፈለግሽ ከልብስ መቀደስ ጀምርህ። “እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፥ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።”   — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥9-10 .    እወዳችኋለሁ 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @birhan_lijoch @birhan_lijoch @birhan_lijoch sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሟር አድርጉለት
Показати все...
የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት ፅንሰ ሐሳብ መነሻ ••• የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት አሁን የመጣ ሀሳብ ወይም ሰይጣን እኛን ለማጥመድ ብሎ የፈጠረው ሳይሆን በእግዚአብሔር የዘላለም ፕሮግራም ውስጥ የነበረ ደግሞም ኃጢያት ወደ ምድር ከገባ በኋላ ምንም እንኳን የዘላለም ዕቅድነቱ ቢቀርም የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ ሆኖ የቀጠለ ነው፡፡ ••• ለአዳም እግዚአብሔር እጅግ በጣም ብዙ ነገሮችን ሰጥቶታል ለምሳሌ ምንም የማይጎድልበትን መኖሪያ (ኤድን ገነት)፣ በጣም ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸውን እንስሳት፣ ለመብላት ደስ የሚያሰኙ ፍራፍሬዎችን፣ ወዘተ... ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር :: (ዘፍ 2፤20) ለመጀመሪያ ጊዜ አዳም የተሟላ የደስታ ኑሮ መኖር የጀመረው እንደ እርሱ ያለች ረዳት ሔዋን ስትፈጠርለት ነበር፡፡ ••• እንደውም እግዚአብሔር ከአዳም የጎን አጥንቱ ላይ ወስዶ ሔዋንን በመፍጠር ወደ አዳም ሲያመጣት በሚገርም ሁኔታ ከየት እንደመጣች እንኳን ማንም ሳይነግረው በቀጥታ እንዲህ ነበር ያለው “አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍ 2፤23-24) ይሄ የሚያሳየን የሴትና ወንድ ጓደኝነት የሰይጣን ፈጠራ ወይም ደግሞ የሰዎች ስሜት ብቻ የፈጠረው ሳይሆን ከጅምሩ የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ እንደነበረ ነው፡፡ ••• እንደዚህ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ለጥቅማችንም የተፈጠረ ሆኖ እያለ ግን አዳም በሰራው ኃጢያት ምክንያት ሰው ስለወደቀ ሰይጣንም ለክፉ ስራው ማስፈፀሚያነት ይጠቀምበት ጀመር፡፡ እኛ ክርስቶስ ኢየሱስን አምነን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም የተወለድን ቅዱሳን በሙሉ ለየት የሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ አንዱ በሰይጣን ተበላሽቶ ከወደቀው ዓለም የተዋጀንና በአዲሱ አዳም (ኢየሱስ) የዘር ግንድ የገባን መሆናችን ነው፡፡ ••• የወደቀውና የተበላሸው ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ የአኗኗር ስርአትና የሚመሩበት ሕግ (መልካምም ሆነ ክፉ) እንዳላቸው ሁሉ እኛም ደግሞ የሚገዛንና ስርአት የሚያስይዘን የህይወት መንፈስ ሕግ አለን፡፡ ••• ሾለ ሰው ለሚፈጠርብን ማንኛውም ጥያቄ መልስ የምናገኘው መሪያቸን ከሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ሴት እና ወንድ እርስ በርስ እንዲፈላለጉ እና እንዲፋቀሩ የሚያደርግ ስሜት በውስጣቸው አስቀምጧል፡፡ ••• እንግዲህ የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነትና የትዳር ዲዛይነር እግዚአብሔር ከሆነ፤ እንዴት በቅድስና እንደምንይዘው የሚያሳይ ደግሞ መንገድ አለው ማለት ነው፡፡ ••• ታዲያ ፈጣሪችን የሆነው እግዚአብሔር እንተዳደርበት ዘንድ የሰጠን ማኑዋል መፅሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ ስለኛ አፈጣጠር የማይመለከተው አካል አቅጣጫ ሊያሳየን አይችልም፡፡ መቼ? ••• የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር ትክክለኛ ጊዜውን ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የብዙ ሰዎች ጓደኝነት ትዳር ላይ ሳይደርስ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ያለጊዜው መጀመሩ ነው፡፡ ጓደኝነትን ያለጊዜ በመጀመር ከሚደርሱት ጉዳቶች ውስጥ ደግሞ ዋነኛው የቅድስና ችግር ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ችግሮች ለመዳን የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት አሁን ትክክለኛ ጊዜው ነውን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፤ ምን መጠየቅ ብቻ እርግጠኛ የሆነ መልሱንም ማወቅ አለብን!! ••• ጊዜ አለመጠበቅ የሚያመጣውን ጉዳት በሚገባ ያስተዋልን እንደሆነ “ታዲያ እንዴት ነው ጊዜውን ማወቅ የምንችለው?” የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮአችን ይመጣል፡፡ ••• የዘጠኝ ዓመት ሕፃን ልጅ ፍቅረኛ ልያዝ ወይ ብላ ብትጠይቃችሁ በእርግጠኝነት የምትመልሱላት መልስ አንቺ እኮ ገና ሕፃን ልጅ ነሽ ፍቅረኛ ለመያዝ ትንሽ ማደግ አለብሽ የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አንድ የሀያ አምስት አመት ኮረዳ ተመሳሳይ ጥያቄ ብትጠይቃችሁ ህፃን ነሽ እደጊ አትሏትም ወይም ደግሞ እንዴት በሀያ አምስት ዓመትሽ አትሏትም ይልቁንም ልጁ ማነው? ክርስትያን ነው ወይ? ባሕርይው ምን ዓይነት ነው? እና ሌሎችንም ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለማጣራት ነው የምንሞክረው፡፡ ከዚህ የምንረዳው የፍቅር ጓደኝነትን መያዝ ወይም አለመያዝ የሚወሰነው በእድገታችን ነው ማለት ነው፡፡ እድገት ምንድን ነው? በእድሜና በአካለመጠን የመግዘፍ ብቻ ወይስ አርቆ የማሰብና የማስተዋል መጠን? ክፍል እየቆጠሩ መመረቅ ብቻ ወይስ በማህበራዊና ስነልቦዊ ዕውቀት መራቀቅ?፣ እድገት ምንድን ነው? ስንት ዓይነት እድገት አለ? እድገት የሚለካው ሁሉን አቀፍ በሆነ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ አንድ ሰው ሀያ እና ሀያ አንድ አመት ስለሞላው ብቻ አድጓል ማለት አንችልም፡፡ በትምህርት ልቆ ዶክተር ኢንጂነር ቢባል ይህ ብቻውን የእድገቱ ማሳያ ሊሆን አይችልም፡፡ እድገት ዘርፈ ብዙ፣ መጠነ-ሰፊና፣ እና ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት በቅድሚያ ሁለንተናዊ የሆነ እድገታችንን መመርመር መቻል አለብን፡፡ ይህን ስናደርግ ትክክለኛ ጊዜው ይሁን አይሁን መወሰን ቀላል ይሆንልናል፡፡   .    #እወዳችኋለሁ❤❤ 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @birhan_lijoch @birhan_lijoch @birhan_lijoch sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሟር አድርጉለት
Показати все...
"ደሙ'' 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ /2×/ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል በመመላለሻ በአደባባይ እርቃኑን ተሰቅሎ ለሰው ልጅ ሲታይ በግፍ እየተገፋ ተራራን ነጎደ በቀራንዮ ስፍራ በመስቀል ሞተ አይተው እንዳይወዱት ደም ግባት የለውም እጅግ የተጠላ ቁስለኛ ነዉ ታዲያ ይሄማ እንዴት መድኃኒት ይሆናል ያለ ሁሉ ይስማ ደሙ ያነፃል የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል እንደ አሮን ልጆች ክህነት እንደ ሌዊ ዘር ስርዓት አይደለም የውዴ አይደለም የውዴ የኮርማና የዋኖስን ደም መች ይዞ ገባ እኔን ለማፅደቅ /2×/ ስጋውን አንዴ አቅርቦ ዘላለሜ አማረ ደሙ ፈሰሰና ኃጥያቴ ተሻረ በቀራንዮ ሞቱ ዳግም ወለደና አብን አባ አልኩት ልጅነሽ ተባልኩና /2×/ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ     🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics      ❖ ───✝️─── â–
Показати все...
Selam Desta - Demu.mp34.42 MB
✴️ውድ የቻላናችን ቤተሰቦች በዚህ ድንቅ 💽አልበም ውስጥ የሚገኙ  💿መዝሙሮች እነዚ ናቸው። እንደምትባረኩባቸው እርግጠኛ ነኝ:: የግጥም ስህተት ካለ በዚህ ንገሩን እንዲሁም ሀሳብ አስተያየት ካላቹ አድርሱን🙏 👇 @Eyosii @DN1Asaf2 💛የወደዳቹትን መዝሙር ለምትወዷቸው ሰዎች #share አድርጉላቸው። ተባረኩልኝ እወዳቹሃለው💛 🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼 @mezemur_lyrics @mezemur_lyrics ❖ ───  ✦ ─── ❖
Показати все...
"ፍፁም አላፈረም" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ሾለ በደላችን ደቀቀ ሾለ ኃጥያታችን ቆሰለ ሾለ መተላለፋችን ሞተ በመገረፉ ቁስል ፈወሰን /*2 በቀራንዮ ስፍራ በመስቀል የሞተው በእሾህ ሲጎነጉኑ ደሙ የፈሰሰው በጦር ጎኑን ሲሉ በአለንጋ ሲልጡ ዝም ማለቱ ለእኛ ነው መራራን ሲያጠጡ ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም ሥሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር /*2 በእራስ ቅሉ መንደር የፈሰሰው ደሙ ንጹህ ነው ያለዋኖስ ያለበጐች ደም የአለምን በደል ጠረገው ደሙን ይዞ ገባ ወደ አባቱ አወረደ ከላይ ምሕረቱን አመጻችን ሁሉ ተወግዶ ተቆጠረ በእኛ ላይ ፅድቁ ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም ሥሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር እጅጉን በችንካር አጥብቀው ወጠሩ ጀርባውን በጅራፍ እያቆሰሉ የአለማት ፈጣሪን ያለእፍረት ቢንቁ ጸሀይ እና ጨረቃ እርሱን አከበሩ /*2 በምሕረቱ ነው ባለጠጋ እኛን ሊምር ወደደ ጌታ በምሕረቱ ነው ባለጠጋ እኔን ሊምር ወደደ ጌታ እኛን አለ ሩሃማ /*2 እኔን አለ ሩሃማ /*2 share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ     🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics      ❖ ───✝️─── â–
Показати все...
Fitsum_Alaferem(256k).mp34.67 MB
"አልደራደርም" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ሃይማኖቴን እምነቴን/ማኅተሜን አንተን ጌታ ከላይ ያኔ ያገኘሁህ የእኔን ቤዛ ያምላኬን ፀጋ በመሴሰን አለውጥም ንጉሤን አንተን ኢየሱሴን አልክድም አልደራደርም በአንተ ጉዳይ እንደ ቀልድ አላይም የሆንከውን መስቀል ላይ ከአብ ዘንድ ያገኘሁህ ውዱ ስጦታ አንተ ነህና የእኔ ጌታ /*2 በመረቀልን በአዲሱና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስቲቱ በኢየሱስ ቀርበን የእውነትን እውቀት ካገኘን ወይ ወደን ከሃጥያት እንዴት እንፀናለን ወደን ሃጥያትን እንዴት እናደርጋለን አንደራደርም በአንተ ጉዳይ እንደ ቀልድ አናይም የሆንከውን መስቀል ላይ ከአብ ዘንድ ያገኘንህ ውዱ ስጦታ አንተ ነህና የእኛ ቤዛ /*2 share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Показати все...
Alederaderem(256k).mp33.30 MB
"አቤቱ" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ምን አቃተህና ማህተሙን ፈትተሀል ሰባቱን ጥቅልል መጽሐፍ ልትከፍት ችለሀል እንቆቅልሽ ፈቺ በማደሪያህ አለህ በዙፋን ላይ ሆነህ ሁሉን ታድሳለህ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ሾር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ ጅማሬህ አይታወቅ ያንተ መጨረሻ ገደብ ልክ የሌለህ ሀያል የእኛ ጌታ በግርማ ሞገስህ ሁሉን የምትረታ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ሾር እና ዘር ስግደት ይገባሃል የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጅህ ነው በላይ ቢሆንም በታች ስልጣን ያንተ ነው አዶናዩ ጌታ ምንስ ይሳንሀል ቋጠሮውን ልትፈታ ብቻህን ችለሀል አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ሾር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በረከት እና ክብር ጥበብም ምስጋና ለታረደው በግ ይሁን ለዚያ ለገናና ሰቃይን እና ችግር መከራን ያስረሳ ኢየሱስ ብቻ ነው የይኁዳ አንበሳ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ሾር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ /3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ /3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Показати все...
Abetu(256k).mp34.49 MB
"ተመርጫለው" ዘማሪት ሰላም ደስታ ተመርጫለው ፡ እኔ ተወድጃለው ፡ እኔ ፀድቄአለው ፡ በእርሱ እንድኖርለት ፡ ለእርሱ (፪x) ፀጋው ፡ በእምነት ፡ አድኖኝ ኢየሱስ ፡ ጽድቁን ፡ አልብሶኝ ስለኔ ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ታይቶ ፈጽሞታል ፡ ሥራዬን ፡ ጨርሶ (፪x) ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል ገና ፡ ከፍጥረት ፡ በቁጣ ፡ ነበርኩኝ በበደሌ ፡ ምክንያት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ በኃጢአቴ ፡ መብዛት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ (፪x) ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ አደለ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ እንኪ ፡ አለ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Показати все...
Temerechalew(256k).mp33.47 MB
"በቂ ነው" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° በጣም የከበረ እጅግ ያየለ ከወርቅ ከእንቁ ይልቅ የተሻለ በፍፁም ድርድር አብ የማያውቅበትን አንድያ ልጁን/ክንዱን ሰጠን እየሱስን በቂ ነው ከበቂም በላይ /*3 ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ/*2 ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኝ መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ የቅዱሳን ተስፋ በረከቴ ሆኖኛል ቀረኝ ምለው የለም አብ ጨርሶ ባርኮኛል ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኜ መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ የቅዱሳን ተስፋ ስጦታዬ ሆኖኛል ቀረኝ ምለው የለኝ አብ ሁሉንም ሰቶኛል ከዚ በላይ ባርኮት ምናለ ከዚህ በላይ በላይ ከዚ በላይ ደስታስ ምናለ ከዚህ በላይ በላይ ከዚ በላይ ሰላም ምናለ ከዚህ በላይ በላይ አለም የሌላትን አገኘሁ ከላይ ከሰማይ አሳ በምድር/በየብስ ላይ ሕይወት አያምረው ከባህር እርቆ ህይወት አያሰኘው ሁል ጊዜ መገኛው አንድና አንድ ነው ከውሀ የወጣ እለት መሞቻው ቅርብ ነው የእኔም ህይወት ያለ እየሱስ ልክ እንዲ ባዶ ነው ከመገኛ እርቆ መኖር ኧረ እንዴት ከንቱ ነው የህይወት እንጀራ ጠግቤ የህይወት ዉሃ ረክቼ ከሱ ወዴት ሄዳለው መገኛዬ አንድና አንድ ነው በረከቴ እየሱስ ብቻ ነው በቂ ነው ከበቂም በላይ /*3 ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ/*2 share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Показати все...
Beki_New(256k).mp34.01 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.